የኪዳነምህረት ልጆች ✝ 1⃣6⃣
Статистика🌠፥የናቁሽ ሁሉ ወደ እግርሽ ጫማ ይሰግዳሉ፤🌠 🌠"ስምሽ ጉልበት አለው ጨካኝን ያራራል ስለ እመ አምላክ ብሎ ደሀው ጠግቦ ያድራል" 🌠 ➡Comment @amye16
- Последний пост
- 22 февр.
- Последнее чтение
- 15 авг.
- Постов за неделю
- 0
- Всего постов
- 20
- Тип
- открытый
- Язык
- und
- В каталоге с
- 15 авг.
- 1/24сутки в ленте
- —
- 1/48двое суток
- —
- 1/72трое суток
- —
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
በክርስትናው ዓለም በዓለም አቀፍ ደረጃ ታሪካቸው ከሚነገርላቸው ሰማዕታት አንዱ በሀገራችን በኢትዮጵያም በአማላጅነቱ የሚታወቀው ታላቁ ሰማዕት ቅዱስ መርቆሬዎስ፡፡ መርቆሬዎስ ማለት የአብ ወዳጅ ማለት ነው። በሁለተኛ ትርጉሙ የኢየሱስ ክርስቶስ አገልጋይ ማለት ነው። በሀገራችን በኢትዮጵያም በበርካቶች ዘንድ በፍጣን ተራዲኢነቱ ይታወቃል፡፡ በትውልዱ ሮማዊ ሲሆን አረማውያን የነበሩት ቤተሰቦቹ ከአምልኮተ ጣኦት ወደ አምልኮተ እግዚአብሔር የተመለሱ ናቸው፡፡ አባቱ ፊታቸው የውሻ የሆነ፣ የአውሬነት ጸባይ ያላቸው በእግዚአብሔር ኃይል የሚታዘዙት ሁለት አገልጋዮች ነበሩት፡፡ በመርዶሳውያን ሀገር ተማርኮ የሔደው አባቱ ጸጋ እግዚአብሔር በዝቶለት በዚያ ሹመት አጊኝቷል፡፡ አባትና እናቱ ሲያርፉም ልጃቸው ስልጣኑን ተረክቧል፡፡ በእምነቱ የጸናው ፍጹም ክርስቲያናዊ ቅዱስ መርቆሬዎስም የአባቱን ስልጣን ወርሶ በንጉስ ዳኪዮስ ስር በመርዶሳውያን አገር ላይ ተሾመ፡፡ መርቆሬዎስ መኰንንነት በተሾመም ጊዜ ገጸ ከለባት የሚባሉት የውሻ ፊት ያላቸው የአባቱ አገልጋዮች አብረውት ነበሩ፤ ለመዋጋትም በወጣ ጊዜ የቀድሞው የአራዊት የሆነ ተፈጥሯቸውን እግዚአብሔር ይመልስላቸው ስለነበር ማንም አይቋቋመውም ነበር፡፡ ለቅዱስ መርቆሬዎስ ታላቅ የድል አድራጊነት ኃይል ተሰጠው፡ ዜናውም በሁሉም ሀገሮች ተሰማ፤ በሀገረ ሮሜ ጣዖት የሚያመልከው ዳኬዎስ የተባለውም ንጉሥ ከበርበር ሰዎች ጋር ጦርነት ሊገጥም በወጣ ጊዜ እጅግ ሲበዙበት ፈራ፡፡ ቅዱስ መርቆሬዎስ ግን በጦሩ መካከል የተሳለ ሰይፍ የያዘ የእግዚአብሔርን መልአክ ስላየ ንጉሡን “እግዚአብሔር ያጠፋቸዋልና አትፍራ” አለው፤ ከዚያም ሰይፉን ለቅዱስ መርቆሬዎስ ሰጠውና “ጦርነቱን ድል ባደረግህ ጊዜ እግዚአብሔርን አስበው” አለው፡፡ የመልአኩ ተራዳኢነት፣ የቅዱስ መርቆሬዎስ ጀግንነት ትልቅ ድርሻ አበርክቶበት ድል አድርጉ፡፡ መልአኩም ዳግም ተገልጦለት “ለምን የፈጣሪህን ስም መጥራት ረሳህ” አለው፡፡ ጦርነቱ በንጉሱ ዳኪዮስ ወገን አሸናፊነት ሲጠናቀቀ ንጉሡ ከጦርነቱ በኋላ ለጣዖታቱ ዕጣን በማሳረግ በዓልን አደረገ፡፡ የእግዚአብሔር መልአክ በጠላቶቹ ፊት ድል ያጎናጸፈው ቅዱስ መርቆሬዎስ ግን በዚህ ድርጊት በማዘኑ በበዓሉ ላይ አልተገኘም፡፡ ንጉሡ ዳኪዮስ ይህንን ሲያውቅ መልእክተኞችን ልኮ አስጠራውና “ከእኔ ጋር ለምን አታጥንም?” አለው፡፡ ቅዱስ መርቆሬዎስ ትጥቁንና ልብሱን አውልቆ ከወረወረለት በኋላ “ክብር ይግባውና እኔ አምላኬ ኢየሱስ ክርስቶስን ፈጽሞ አልክደውም፤ ለረከሱ ጣዖቶችህም አልሰግድም” አለው፡፡ ከዚህ በኋላ ነበር ሰማዕቱ ቅዱስ መርቆሬዎስ በክርስትናው የተፈተነው፡፡ ቅዱስ መርቆሬዎስ ግን በጽናት በሃይማኖት ቆመ፡፡ በዚህ የተናደደው ንጉሡ ዳክዮስ አብሮት በጣኦት አምልኮው ስላልተሳተፈ በልዩ ልዩ ሥቃዮችም እጅግ አሠቃየው፡፡ በኋላም ስለ መርቆሬዎስ ብለው የሀገሩ ሰዎች እንዳይነሡበት ፈርቶ በብረት ችንካር ቸንክሮ የቀጵዶቅያና የእስያ ክፍል ወደ ሆነች ወደ ቂሳርያ ከደብዳቤ ጋር ላከው፡፡ በዚያም እጅግ ካሠቃዩት በኋላ በንጉሥ ዳኬዎስ ትዕዛዝ አንገቱን በሰይፍ ቆረጡትና የሰማዕትነት ተጋድሎውን ፈጸመ፤ የሕይወትንም አክሊል ተቀዳጀ፤ በዓለሙ ሁሉ አብያተ ክርስቲያናት ታነጹለት፡፡ እግዚአብሔርም ድንቅ ድንቅ የሆኑ ተአምራትን በቅዱስ መርቆሬዎስ ስም አደረገ፡፡ በየቀሩ በ25 ቀንም መታሰቢያው ነው፡፡ የሰማዕታቱን አሰረ ፍኖት የሚከተሉት ገዳማውያንም ዓለም የምትሰጣቸውን ተድላና ደስታ ንቀው ክርስቶስን ብለው ወጥተዋልና ጸሎታቸው ኃይልን ታደርጋለች፡፡
https://vm.tiktok.com/ZMkJjeDUf/
видео или голосовое, без подписи
Channel photo updated
https://vm.tiktok.com/ZMheXdWm1/
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
✝እንኳን አደረሰን! ✝ማኅበረ በኩር ወአቡነ ዓቢየ እግዚእ ጻድቅ! ☞ዛሬ (ነሐሴ ፲) ጻድቁ ጎንደርን ከአራዊት ለመጠበቅ ቃል ኪዳን ከመድኃኒታችን የተቀበሉበት ቀን ነው! #ጎንደሬ(?) ቢዘነጋውም እኛ በደብራችን እናከብራቸዋለን። ✝ማኅበረ በኩር ወሰማዕት ተአይነ ማርያም ወወልዳ፤ ወዓቢየ እግዚእ ጻድቅ ገባሬ መንክራት በበዳ፤ ዘከፈሎ ለተከዚ ወለአድያመ ጎንደር ዘዖዳ፤ ቢካቦስ ወዮሐንስ ወመጥራ ዕንቆ ባሕርይ ጸአዳ፤ ወሐርስጥፎሮስ ዘጾረ ለሕማም ክበዳ! (አርኬ - ዝክረ ቅዱሳን ርቱዓነ ሃይማኖት) ከአባታችን በረከት አይለየን !
видео или голосовое, без подписи
ጩጌ ማርያም አጽማቸው የማይፈርስ ፍየሎች የሚገኙባት ገዳም። ጩጌ ማርያም ከጎንደር ከተማ በስተሰሜን በኩል 25 ኪሎ ሜትር ርቀት ተጉዘን በወገራ ወረዳ አካባቢ የኮሶየ አምባ ራስ ቀበሌን አልፈን ወደ ገዳማቱ ለማምራት የዘጎል አምባን፡የጅብ ዋሻን ጥቅጥቅ ያሉ ደኖችን አልፈን ወደ ምስራቅ ስንታጠፍ በተፈጥሮ ክብ ቅርፅ ያለውን ቤተ ክርስቲያን መስሎ የሚታየውን ተራራ እናገኛለን። በዚህ ተራራ ላይ አባ ምዕመን ድንግል የገዳም ህይወታቸውን እንዳሳለፉ የታሪክ ድርሳናት ያስረዳሉ። በተራራው ማየ ዮርዳኖስ ፀበልና ዋሻ ቅዱስ ሩፋኤል ክርስቲያን እናገኛለን ቤተ ክርስቲያኑ ቅድስትና መቅደስ ያለው ሲሆን በቅድስቱ ማየ ዮርዳኖስን ያለ ሲሆን ይህን በመጠጣታቸው ስጋቸው ያልፈረሰ የፍየል አፅሞች ይገኛሉ። በዚህም በአመት አንድ ጊዜ ብቻ ጳጉሜ 3 ይቀደሳል። የጩጌ ማርያም ገዳም በ17ኛው መቶ ክፍለ ዘመን የተመሰረተ ጥንታዊ ገዳም ሲሆን የመሰረቱትም አባ ምእመነ ድንግል የተባሉ ጻድቅ ናቸው፡፡ ገዳሙም ጻድቁ የጸለዩበት እና ከጌታችን ከመድኀኒታች ከኢየሱስ ክርስቶስ ቃልኪዳን የተቀበሉበት ቅዱስ ቦታ ሲሆን የጻድቁ በዓት መጸለያ ዋሻም በስማቸው “ምእመነ ድንግል” እንደተባለ አለ፡፡ ጻድቁም በሕይወት እንደነ ሄኖክ፣ ኤልያስ፣ ቅዱስ ያሬድ እና አባ ዮሃኒ በህቡእ አሉ ተብሎ ይታሰባል ፡፡የጻድቁ መጸለያ ቦታ በተፈጥሮው የተሸነቆረ መስኮት አለው፡፡ በዚህ ቦታ ላይ መኻን የሆኑ ሁሉ በመስኮቱ ወጥተው ሲመለሱ ማየ ዮርዳኖሱን ጠጥተው ሲሳሉ ልጅ ለማግኘት ይበቃሉ፡፡ ይህን ቃል ኪዳን የሚያውቁ ጳጉሜን በሙሉ በማየ ዮርዳኖሱ በመጠመቅ ትልቅ ሐብተ ፈውስ ያገኛሉ፡፡ የዮርዳኖሱን ጸበል የጠጣ ሲሞት ሥጋው አይፈርስም፣ አይበሰብስም፡፡ እንኳን በአርአያ ሥላሴ የተፈጠረው ሰው እንስሳቱ እንኳን አካላቸው ሳይፈርስ ይቆያል፡፡ ለማስረጃ ያህል እንኳን 16 የሚሆኑ ፍየሎች አካላቸው ሳይፈርስ 400 ዘመን ያስቆጠሩ አሉ፡፡ ገዳሙ የወንዶችና የሴቶች ተብሎ በሁለት የተከፈለ ሲሆን ቤተ ክርስቲያኑ በወንዶች ገዳም በኩል ሲገኝ ወደ ሴቶቹ ገዳም ስናመራ ደግሞ አንድ ትልቅ የችብሀ ዛፍ ወድቆ እንደተነሳ ይኸውም ከሰው ልጅ ሞቶ መነሳት ጋር የተያያዘ እግዚአብሔር ተአምራትን አሳይቶበታል። ዛፉ ከ15ዓመት በሗላም እንደገና እንደወደቀና በስሩ የፈለቀው ፀበልም ህመምተኞችን እየፈወሰ እንደሚገኝ አባቶች ያስረዳሉ። የገዳሙን ተራራ የወጣ ሰው እስከ 3000 እንደሰገደ ይቆጠርለታል የሚል ቃልኪዳን አላቸው። ✥#ከጩጌ_ማርያም ገዳም ረድኤት በረከት ያሳትፈን። ደጇን ተሳልመን በረከት እንድናገኝ የአምላካችን ቅዱስ ፍቃድ ይሁንልን። ዓመታዊ ክብረ በዓሏም በነገው እለት ሰኔ 21 በደማቅ ይከበራል።
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
❤አንብቡት_ይጠቅማቹሃን‼ #ልጹም ትላለህ ፤ ተው አትጹም ይልሃል!አንተም ትተወዋለህ። #ልመጽውት ትላለህ ፤ ተው አትመጽውት ይልሃል። አንተም ትተወዋለህ። #ንስሐ ልግባ ትላለህ ፤ ትንሽ ቆይ ይልሃል። አንተም ያለንስሐ ትሞታለህ። #ልቁረብ ትላለህ ፤ ገና ነህ ትንሽ ቆይ ይልሃል። አንተም ሳትቆርብ ትሞታለህ #ላስቀድስ ትላለህ ፤ ተው ትንሽ ተኛ ይልሃል። አንተም ሳትሄድ ታረፍዳለህ። #ጸበል ልግባ ትላለህ ፤ ጤነኛ ነህ ይልሃል። ገዳም ልባረክ ልሂድ ትላለህ ፤ ተው ስራን ስራ ይልሃል፡፡ አንተም ሳትሄድ ስትቆጭ ትኖራለህ። #አስራት በኩራት ልስጥ ትላለህ ፤ ተው አትስጥ የለህም ይልሃል። አንተም ትተወዋለህ። #በአንድ ልወሰን ትላለህ ፤ ተው ቆንጆዎቹ ያልፉሃል ይልሃል። አንተም በዝሙት ትወድቃለህ። የሞዐ Aklilu #በመጨረሻም_የተወሰነልህ_ግዜ_ያልቃል ። ነፍስህን አጋንንት እንደ ኳስ እየተቀባበሉ ይወስዷታል። #ልጠጣ ስትል ፤ ጠጣ ይልሃል። ያሰክርሃል። #ልዝፈን ስትል ፤ዝፈን ይልሃል። ያስጨፍርሃል! #ልስረቅ ስትል ስረቅ ይልሃል። ያሰርቅሃል! #ልጣለው ስትል ተጣላ ይልሃል። ያጣላሃል። #ልዋሽ ስትል ዋሽ ይልሃል። ያስዋሽሃል! ስጋዊ ተድላን ይሰጥሃል። ይመችሃል፡ስጋህ ወፍሮ ፣ ቀልቶ ፣ ወዝቶ በጓደኞችህ ‹ ተመቸህ እኮ ! › ያስብልሃል። አንተም ደስ ይልሃል! በዛው ትገፋበታለህ። #ሃሳብህ ሁሉ ወደ ቤተክርስቲያን መሄድ ቀርቶ ወደ ጅምናዝየም ቤት መሔድ ይሆናል። #ሃሳብህ ሁሉ የተመጣጠኑ ምግቦችን መመገብ ይሆናል። ሃሳብህ ሁሉ ሳውና ባዝ ፣ ስቲም ቤት ፣ማሳጅ ቤት ሂደህ መታሸት እና መዝናናት ይሆናል። #እግርህ ሁሉ ወደ ሲኒማ ቤት ፣ ወደ ናይት ክለብ ቤት ፣ ወደ ሆቴል ቤት ፣ ወደ ግሮሰሪ ቤት ፣ ወደ ሱፐር ማርኬት ፣ ወደ ምናምን ቦታ ይሆናል። #በእነዚህ_ሁሉ_ስጋህ_ሲመቸው #ቁሞ መጸለይ ይደክምሃል። #መስገድ ያቅትሃል። #መጾም ይከብድሃል። #ቤተክርስቲያን ለመሄድ ይጨልምሃል። #ስጋህ በአጋንንት መረብ ይጠመዳል። #ደም ብዝት አስይዞ ሴት ያዝልሃል። #ደም ብዛት አሲይዞሽ ወንድ ያዝልሻል። #የነርቭ በሽታ አስይዞ መቆምና መሄድ ያስቅትሃል። #ስኳር በሽታ አሲይዞ ከጾም ይከለክልሃል። #ጨጓራ በሽታ አስይዞ ጾምን ይከለክልሃል። #ምላስህ እግዚአብሔርን ማመስገንን ሳይሆን ዘወትር ስለ በሽታህ እንድትዘምር ያደርጋታል። በጣም ብዙዎች ሃብት ሞልቷቸው በሽተኛ ያደርጋቸዋል። ገና ከጥዋቱ እነዚህ ሰዎች የእግዚአብሔርን መንገድ ተከትለው ቢሄዶ ኖሮ ፤ እንደ አብርሃም ፣እንደ ይስሐቅ እና እንደ ያዕቆብ በምድር ሃብታም እንደ ሆኑ ሁሉ በሰማይም እንደ ቅዱሳኑ የገነት ባለቤት በሆኑ ነበር። #ሰይጣን ክፉ ነው! ሃብታሙን በሽተኛ ፣ ድሃውን ደግሞ ጤነኛ አድርጎ አምላክን ወቃሽ ያደርገዋል።እንዲህ እንዲህ እያለ የመሰናበቻ ጊዜ ይደርሳል። በኃጢአት የዳበረው ስጋችን አፈር ነውና በቅጽበት እሬሳ ተብሎ ወደ አፈር ይገባል። ነፍስ ግን እያዘነችና እየተፀፀተች ወደ ሲዖል ትወረወራለች። #የምናያቸው ቆንጆ ሴቶች ፣ የምናያቸው ቆንጆ ወንዶች ፣ የምናየው የልኳንዳ ስጋ ፣ የምናየው መጠጥና ምግብ ሁሉ ያምረናል። ስጋችን ያሸንፈናል፥ ነፍሳችን ትሸነፋለች። ለገነት ተፈጥረን ለሲዖል እንሆናለን። ሁላችንም ወደ እግዚአብሔር ተመልሰን ንሰሀ እንግባ።። 👉የቅዱሳን አምላክ ለንስሃ የተዘጋጀ ልብ ይፍጠርልን 👉ለንስሃ ሞት ያብቃን አሜን🙏 ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክብር አሜን ይቆየን🙏 @amann