Amhara Prosperity Party/APP2
Статистика- Последний пост
- 10 авг.
- Последнее чтение
- 15 авг.
- Постов за неделю
- 2
- Всего постов
- 80
- Тип
- открытый
- Язык
- und
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 631
- 1/48двое суток
- 723
- 1/72трое суток
- 779
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
видео или голосовое, без подписи
ሣምንታዊ መልዕክት! ዛሬ የተከልነዉ ችግኝ ነገ ጥላ እንደሚሆን ሁሉ፤ ዛሬ የምንገነባው የጋራ እሳቤም ነገ የሀገር ጽናት ይሆናል! እኛ ኢትዮጵያውያን በኅብረት ስንቆም የሚያስቆመን ምድራዊ ሀይል አለመኖሩን የቀደመዉ ታሪካችን ይመሰክራል፡፡ አድዋ ላይ በልዩነቶቻችን ሳንከፋፈል፣ በአንድ ልብና በአንድ ዓላማ ተሰልፈን የቅኝ ግዛት ሥርዓት ካባ ሊያላብሰን ድንበር ተሻግሮ የመጣዉን ወራሪ ድል ነስተናል። ይህ ታሪካችን ትልቅ ትምህርት ነው፤ የጋራ ዓላማችንን ከግለሰባዊና ከቡድናዊ ልዩነቶቻችን በላይ ስናደርግ ትላልቅ ድሎችን እንደምናስመዘግብ ህያዉ ምስክር ነዉ፡፡ የዛሬውም ትውልድ ይህንኑ የቀደምቶቹን ታሪካዊ መንፈስ በአዲስ መልክ መድገሙን ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የኅብረትና የሀገራዊ ቁርጠኝነት ምልክት ሆኖ በመቆም አረጋግጧል፡፡ የአረንጓዴ አሻራም በተመሳሳይ መንፈስ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ዜጎችን በአንድ ዓላማ አሰባስቦ ሀገራዊ ለውጥን በተግባር እያሳየ ይገኛል። በ2011 ዓ.ም በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ(ዶ/ር) የተጀመረዉ የአረንጓዴ አሻራ መርሀግብር በስምንት ዓመት ጉዞዉ 48 ቢሊዮን በላይ ችግኞች እንዲተከሉ አድርጓል፡፡ በዚህም ለቀጣዩ ትውልድ የተሻለች ሀገር የመተው ኃላፊነት፣ የምግብ ዋስትናን የማጠናከር ጥረት፣ የአካባቢ ጥበቃ፣ የኢኮኖሚ ሉዓላዊነትና የጋራ ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ ተችሏል፡፡ በዚህ ዓመት “ተስፋን እንትከል” በሚል መሪ ቃል በአንድ ጀምበር 805.3 ሚሊዮን ችግኞችን መትከላችን በኅብረት ስንንቀሳቀስ ምን ያህል ታላቅ ግብ ማሳካት እንደምንችል ያሳየን የአንድነት ድል ነው። በሁሉም ኢትዮጵያዊያን ዘንድ ባህል እየሆነ የመጣዉ የአረንጓዴ አሻራ መርሀግብር የደን ሽፋን ወደ 23.4 በመቶ እንዲያድግ ምክንያት ሆኗል፡፡ የጋራ ዓላማን ለማሳካት ከሚደረግ ጥረት ጎን ለጎን አብሮነትን፣ ወንድማማችነትን/ እህትማማችነትን በማጎልበት ለሀገራዊ አንድነት መጠናከር የአንበሳዉን ሚና እየተወጣ ይገኛል፡፡ በብልጽግና ፓርቲ የሚመራዉ የመደመር መንግሥት አረንጓዴ ኢኮኖሚን፣ የአካባቢ ጥበቃንና የተፈጥሮ ኃብት መንከባከብን ትልቅ ትኩረት በመስጠት ከ2011 የክረምት ወቅት ጀምሮ በየዓመቱ ‘አረንጓዴ አሻራ’ ገቢራዊ እያደረገ ይገኛል። በመላ አገሪቱ ከሊቅ እስከ ደቂቅ ሁሉንም የኅብረተሰብ ክፍሎች እያሳተፈ መርሃ-ግብሩ እንደቀጠለ ነው። ይህ መርሀግብር ኢትዮጵያን በአፍሪካና በዓለም አቀፍ መድረክ የአረንጓዴ ኢኮኖሚ ተምሳሌት ያደረገ ተግባር ነው። አሁን ላይ ደግሞ የችግኝ መትከል ባህል ከመንግሥት ቅስቀሳና ከግለሰቦች ጥረት ባለፈ ሀገራዊ ቅርፅ የያዘ ሲሆን ባለፉት ስምንት ዓመታት የተካሄደው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር ትልቁ ማሳያ ነው። የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር የኢትዮጵያን አለም አቀፍ ገፅታና ተጽዕኖ ፈጣሪነት በማጠናከሩ ሀገራችን ኢትዮጵያ የCOP32 አስተናጋጅ እንድትሆን አስተዋጽኦ አበርክቷል፡፡ በመሆኑም በተፈጥሮ እንክብካቤ መሪ መሆኗን አሻራዋን በማኖር እያረጋገጠች ከፊት ወደሚጠብቃት የCOP32 አስተናጋጅነት ታሪካዊ ኃላፊነት ታቀናለች፡፡ በአንድ ጀምበር የተከልናቸዉ ሚሊዮን ችግኞች ተከታታይ ክትትልና እንክብካቤ ይፈልጋሉ፡፡ በመሆኑም የተከልነውን ማሳደግ፣ ያስጀመርነውን ማስቀጠል እና የጋራ ጉዳዮቻችንን በኅብረት ማሳካት ይጠበቅብናል። እንዲሁም ዘላቂ ልማትና ሰላም፣ የኢኮኖሚ እድገት፣ ሀገራዊ አንድነትና ሌሎች የጋራ ጉዳዮቻችን ላይ በህብረት መረባረብ ይገባናል፡፡ ዛሬ የተከልነዉ ችግኝ ነገ ጥላ ይሆናል፤ ዛሬ የምንገነባው የጋራ እሳቤም ነገ የሀገር ጽናት ይሆናል። ስለዚህ ችግኝ መትከል ለአካባቢ ጥበቃ ብቻ የሚደረግ ተግባር አይደለም፤ ለልጆቻችንና ለልጅ ልጆቻችን የምናስረክበውን ሀገር ዛሬ የመገንባት ሀገራዊ ኃላፊነትም ጭምር ነው።
https://youtube.com/shorts/3iVV08_Ov8Q?feature=share
https://youtu.be/jgmmyzJV6IM?si=MeIKshQB19MpApoH
እንኳን ደስ አላችሁ👇 https://youtube.com/shorts/tliN5D84d7M?si=rzGbH2yD8-U4Tfee https://youtube.com/shorts/tliN5D84d7M?si=rzGbH2yD8-U4Tfee
https://youtube.com/shorts/hUj-YxEDai0?feature=share
https://youtube.com/shorts/rlC9aebKs-k?si=XhZHaxfPy_yM3Y-Q https://youtube.com/shorts/rlC9aebKs-k?si=XhZHaxfPy_yM3Y-Q
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ከአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን (አሚኮ) ጋር ያደረጉት ቆይታ ክፍል 1 አርብ ምሽት 2:30 ይጠብቁ።
ሣምንታዊ መልዕክት! የፓርቲያችን አመራሮችና አባላት የሕዝብ አገልጋይነታቸውን በተጨባጭ ውጤት ማረጋገጥ አለባቸው። የ2018 በጀት ዓመት አፈጻጸም ግምገማና የ2019 በጀት ዓመት መሪ ዕቅድ የውይይት መድረክ ባሳለፍነው ሳምንት ከሀምሌ 13 እስከ 15/2018 ዓ.ም ተከታታይ ቀናት በስፋት ተካሂዷል። በዚህ መድረክ የአፈጻጸም ውጤቶችን በጥልቀት ተገምግሟል፤ በስራ ዕድል ፈጠራ፣ በኑሮ ውድነት ቅነሳና ገበያ ማረጋጋት ዙሪያ በንቅናቄ የተከናወኑ አበይት ተግባራት ውይይት ተደርጎባቸዋል፤ በቀጣይም የሕዝቡን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የትኩረት አቅጣጫዎችም ተቀምጠዋል። 2018 በጀት ዓመት ኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ፣ ፍትሃዊ፣ ነፃና ተዓማኒ የሆነውን 7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ ያካሄደችበት ነው። ፓርቲያችን ብልፅግና ይህ ታሪካዊ ስኬት በዋናነት በመምራት አንፀባራቂ ድል ያስመዘገበ ሲሆን በመራጩ ህዝብ ዘንድ ባገኘው ቅቡልነትም ሀገርንና ህዝብን ለቀጣይ 5 ዓመታት የመምራት እድል አግኝቷል። 2019 በጀት ዓመት ደግሞ መራጩ ህዝብ የሰጠውን ታሪካዊ ኃላፊነት መወጣት የምንጀምርበት፤ ህዝቡ በተለያዩ ጊዜያት የሚያነሳውን የልማት፣ የመልካም አስተዳደርና ሌሎች ጥያቄዎችን ለመፍታት በትጋት የምንሰራበት እንዲሁም ፓርቲያችን የጀመራቸውን የልማት ኢኒሼቲቮች ስኬት በይበልጥ የምናረጋግጥበትና የዜጎችን ተጠቃሚነት የምናረጋግጥበት ነው። ለዚህ ስኬት ደግሞ የላቀ የአመራርና አባላት ቁርጠኝነት፤ የህዝብ የነቃ ተሳትፎ የሚጠይቅ በመሆኑ ሁሉም የድርሻውን ሊወጣ ይገባል። በ2018 በጀት ዓመት በስራ ዕድል ፈጠራ፣ በገበያ ማረጋጋትና በኑሮ ውድነት ቅነሳ ዙሪያ የተከናወኑ ስራዎች የፓርቲያችን አቅጣጫ ትክክለኛ መሆኑን ያረጋገጡ ናቸው። በሁሉም ክልሎች በተፈጠሩ የስራ ዕድሎች፣ በምርት አቅርቦት መጨመር፣ በገበያ ማረጋጋትና በሕዝቡ የኑሮ ሁኔታ ላይ የተመዘገቡ መሻሻሎች የፓርቲያችን የሕዝብ ተጠቃሚነትን ያማከለ ፖለቲካ ውጤቶች ናቸው። ይሁን እንጂ የተገኙት ውጤቶች የጉዟችን መጨረሻ ሳይሆኑ የቀጣይ ከፍተኛ ስኬት መነሻዎች ናቸው። ከሀገራችን አቅምና ከሕዝባችን ፍላጎት አንጻር ገና ብዙ ሊሰራ የሚገባ ስራ አለ። በመሆኑም በየደረጃው ያለው አመራር የሕዝብን ችግር ዋና የስራ አጀንዳው በማድረግ የተጀመሩ ለውጦችን ወደ ከፍተኛ ውጤት ማሸጋገር አለበት። የስራ ዕድል ፈጠራና የኑሮ ውድነት ቅነሳ የአንድ ተቋም ወይም የአንድ ዘርፍ ብቻ ኃላፊነት አይደሉም። እስከ ቀበሌ ድረስ በሁሉም የፓርቲ አደረጃጀቶች፣ በመንግሥት ተቋማትና በሕዝቡ የተቀናጀ እንቅስቃሴ ሲኖር ብቻ ዘላቂ ውጤት ማስመዝገብ ይቻላል። በቀጣይ የእያንዳንዱን አካባቢ እምቅ አቅም በአግባቡ በመጠቀም፣ የሕዝብ ተሳትፎንና ባለቤትነትን በማጠናከር፣ ከአሰራር፣ ከአመለካከትና ከአስተሳሰብ ጋር የተያያዙ ማነቆዎችን በመፍታት የብልፅግናን ጉዞ ወደ ከፍተኛ ደረጃ ማሸጋገር አለብን። በተለይም የፓርቲያችን አመራሮችና አባላት የሕዝብ አገልጋይነታቸውን በተጨባጭ ውጤት ማረጋገጥ አለባቸው። ሕዝባችንም በልማት ስራዎች የጀመረውን ንቁ ተሳትፎና ባለቤትነት በቀጣይነት በማጠናከር የሀገራችንን የብልፅግና ጉዞ የበለጠ እንዲፋጠን የበኩሉን ሚና መወጣት ይጠበቅበታል። በ2019 በጀት ዓመት የተቀመጡትን ዕቅዶች ከግብ ለማድረስ በአንድነት፣ በቅንጅት፣ በተጠያቂነትና በውጤት ተኮር አሰራር መስራት ይገባል። የሕዝባችንን ተስፋ ወደ ተጨባጭ ውጤት፣ የሀገራችንን አቅም ወደ ሁለንተናዊ ብልፅግና ለመቀየር ሁላችንም በላቀ ቁርጠኝነት ልንረባረብ ይገባል። ብልፅግና ፓርቲ ሀምሌ 20/2018 ዓ.ም አዲስ አበባ #Prosperity
видео или голосовое, без подписи
ሀገራዊ ምክክር ለብልፅግና ጉዞ የጀመርነው ሁለተናዊ ብልጽግና ከዳር ለማድረስ እና ለቀጣዩ ትውልድ የበለጸገች ኢትዮጵያን ለማስረከብ ያሉብንን ችግሮች በንግግር መፍታት ይጠበቅብናል ። ሀገርን ማሻገር የሚቻለው በጠብመንጃ ሳይሆን በጠረጴዛ ዙሪያ በሚደረግ ውይይት ብቻ ነው። በሀገራችን ባለፉት ዘመናት የተከማቹ ፖለቲካዊ፣ ማህበራዊና የታሪክ ቅሬታዎች አሁንም ድረስ የጉዞዋ ማነቆ ሁነው ቆይተዋል ። እነዚህን ውስብስብ ችግሮች በሃይል ሳይሆን በውይይትና በሃሳብ የበላይነት ለመፍታት ሀገራዊ ምክክር ወሳኝና አማራጭ የሌለው መሻገሪያ ድልድያችን ነው። ስለሆነም ቀጣዩ ትውልድ ሰላማዊና የበለጸገች ሀገርን እንዲረከብ ቁርሾዎችን በመተው የተሻለችና ብልጽግናዋ የተረጋገጠ ሀገር መገንባት የሚቻለው በምክክርና በውይይት ነው ። የሀገራችንን ችግሮች በመወያየትና መፍትሄ በመስጠት፣ ለቀጣዩ ትውልድ ሰላማዊት ሀገር ለማውረስ ዛሬ የሚጣለው ታሪካዊ አሻራ እጅግ ወሳኝ ነው ። በመሆኑም ኢትዮጵያ በታሪኳ አዲስ ምዕራፍ ላይ ትገኛለች የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን እየመራ ያለው ሂደት ለሀገራችን ዘላቂ ሰላም፣ መረጋጋት እና የጋራ አንድነት ወሳኝ ምዕራፍ ነው። ስለሆነም ልዩነቶችን በውይይት በመፍታት በጋራ በሆኑ ጉዳዮች ጋር በጋራ በመስራት የምናመውን የብልጽግና ጉዞ ማሳካትና ከዳር ማድረስ ይጠበቅብናል ። ይህ ምክክር የሀገራችንን የጉዞ አቅጣጫ የሚያቀና፣ ለቀጣዩ ትውልድም ጠንካራ እና አስተማማኝ ሀገር ለመገንባት የሚያስችል አዲስ ምዕራፍ ከፋች ነው ። #prosperity
https://youtube.com/shorts/Lj9pONx9z2k?si=8QPhFBBVEY4GcKZu
https://youtube.com/shorts/FQxyJzfxhyo?si=TcLRmKKMUkXZbOEd
https://youtu.be/YAkpioO57tM https://youtu.be/YAkpioO57tM
https://youtu.be/IqUJNzhJWpk https://youtu.be/IqUJNzhJWpk
https://youtu.be/olcAtDYVy_4 https://youtu.be/olcAtDYVy_4
https://youtube.com/shorts/YYHj0YRIWc0?feature=share
ጥቆማ ይህ በአማራ ክልል የብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽኅፈት ቤት ይፋዊ የዩቲዩብ ቻናል ነው። በመሆኑም Subscribe በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን ያግኙ።በዚህ ሊንክ Subscribe ያድርጉ።👇 https://www.youtube.com/@amharaapp https://www.youtube.com/@amharaapp
ሶስት መሰረታዊ ቁምነገሮች👇 https://youtu.be/vBE1nb-I1D8 https://youtu.be/vBE1nb-I1D8
ከፖለቲካዊ ልዩነት ባሻገር👇 https://youtu.be/9WDezTR1a1Q https://youtu.be/9WDezTR1a1Q