tgindex
አሪፍ መጻሕፍት

አሪፍ መጻሕፍት

Статистика

አሪፍ መጻሕፍት ጥሩና የተመረጡ መጻሕፍትን ተደራሽ ከማድረግ ባሻገር፥ "የንባብ ሱሰኞችን እንፈጥራለን!" በሚል መሪ ቃል ሥር የሀገራችንን የንባብ ባሕል ለማዳበር የተቋቋመ ነው። መጻሕፍትን ለመግዛትና ለማዘዝ ከፈለጉ፦ 0966-76-71-68 ላይ ይደውሉ!

Последний пост
30 дек. 2024 г.
Последнее чтение
13 авг.
Постов за неделю
0
Всего постов
21
Тип
открытый
Язык
ti
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
1 008
+1 за 2 дн.
Сутки
0
0,00%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
1 423
21 постов
Вовлечённость
141,2%
к подписчикам
Постов в день
0,0
всего 21
Упоминаний
0
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
1/48двое суток
1/72трое суток

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • ምኞት አይከለከል... መጽሐፍ ጽፎ ባስነበበን ብለው የሚመኙት ሰው አለ ይኾን? እስቲ ይንገሩን! #አሪፍ_መጻሕፍት #ማንበብ_አሪፍ_ነው #arif_books

  • видео или голосовое, без подписи

  • አሪፍ መጻሕፍትን ጎብኝተዋል? አሪፍ መጻሕፍት ለእርስዎ የአእምሮ ምግብ የሚሆኑ ግሩም መጻሕፍትን ይዞ እየጠበቅዎት ነው። ሃይማኖታዊ ቢሉ ልብወለድ፥ ግጥም ቢሉ ታሪክ፥ ራስ አገዝ ቢሉ ፍልስፍና... ሁሉንም ይዘናል! እርስዎ ብቻ ብቅ ይበሉ! አድራሻ - መኻል 4 ኪሎ አብርሆት ላይብረሪ ግቢ ውስጥ #አሪፍ_መጻሕፍት #ማንበብ_አሪፍ_ነው #arif_books

  • “ከሰማና ከፀሃይ በስፋት የሚተልቀዉ ማነዉ?” አለኝ ከመቅፅበት፡፡ “ሰማይ ነዋ !” “ብርሃንን የምታጎናፅፈን ግን ትንሽዋ ፀሃይ ናት፡፡” ገረመኝ፡፡ “ከዋክብት ኢምንቶች ናቸዉ አይደል? ማታ ማታ ግዙፉን ሰማይ የሚያስዉቡት ግን እነሱ ናቸዉ ፡፡" "ከበጋ እና ከክረምት የሚረዝመዉ የቱ ነዉ?" "በጋ ነዉ ፡፡" "ዘር እየተዘራበት ፣ እህል እየታጨደበት የፍጥረት እስትንፋስ እንዳይቆም ፣ ሕይወት እንድትቀጥል የሚያደርገዉ ግን ከበጋ የሚያንሰዉ ክረምት ነዉ ፡፡" ---/---/--- መጥተው ይሸምቱማ! አድራሻ - መኻል አራት ኪሎ አብርሆት ላይብረሪ ግቢ ውስጥ #አሪፍ_መጻሕፍት #ማንበብ_አሪፍ_ነው #arif_books

  • መንገድ ዓይኑ ይፍሰስ! ጋዜጠኛ ሄኖክ ስዩም "ተጓዡ ጋዜጠኛ" የተባለው ያለ ምክንያት አይደለም። ሀገራችን ውስጥ ያልደረሰበት ጥግ አለ ለማለት ይከብዳል። እርሱ የሚወድደው መጓዝ ነው። መጓዝ... መጓዝ... አሁንም መጓዝ! እድለኛ በመኾናችን ያየውን ነገር ይጽፍልናል። ልምዱንም ያጋራናል። "መንገድ ዓይኑ ይፍሰስ" የሚለው መጽሐፍ ላይም ከኮንሶ ባህል እስከ ወፎች ተፈጥሮ፥ ከጌዲኦ እስከ ወረኢሉ ድረስ ያስቃኘናል። ከተፍ ብለው ይሸምቱማ! #አሪፍ_መጻሕፍት #ማንበብ_አሪፍ_ነው #arif_books

  • #አሪፍ_መጻሕፍት #ማንበብ_አሪፍ_ነው #arif_books

  • አንዳንዴ የታቀደ ሳይሳካ ይቀራል! ለመሆኑ እርስዎ ሁሌም ለማንበብ ፈልገው ቀጠሮ እየሰጡ ሳያነቡ የቀሩት መጽሐፍ አለ ይኾን? እስቲ ሹክ ይበሉን! #አሪፍ_መጻሕፍት #ማንበብ_አሪፍ_ነው #arif_books

  • ሸሙኔ! ለመሆኑ ይህንን ውብ መጽሐፍ አንብባችኋል ወይ? የመስፍን ወንድወሰን "ሸሙኔ" በታሪክ ውስጥ የተደረገ የአንድ አዝማሪ ጉዞ ነው። በውብ ቋንቋ ተከሽኖ ከመቅረቡ ባሻገር፥ ስለ ባሕል፥ ስለ ቋንቋ፥ ስለ አኗኗራችን ቆም ብለን እንድናስብም የሚያስገድድ ድርሳን ሆኖም እናገኘዋለን። መጥተው ይሸምቱ! አድራሻ - መኻል አራት ኪሎ አብርሆት ላይብረሪ ግቢ ውስጥ #አሪፍ_መጻሕፍት #ማንበብ_አሪፍ_ነው #arif_books

  • የዛሬው ንባብ ነክ ቃል ደግሞ እነሆ! አንዳንድ ሰው ሐሳቡን ለመግለጽ ሲፈልግ እጅግ ብዙ ቃላትን ይጠቀማል። እንዲህ አይነት ሰው ታውቃላችሁ? እንግሊዝኛው ሐሳብን ለመግለጽ ቃላትን ማብዛትን "ፔሪፍራሲስ" ይለዋል። እንዲህ አይነት ወዳጅ ካለዎት እስቲ ይጥቀሷቸው! #አሪፍ_መጻሕፍት #ማንበብ_አሪፍ_ነው #arif_books

  • ማሙሽ! “እነዚህ ከእንቅልፋቸው ለምን እንደሚነቁ ያውቃሉ፤ ያዙትም አልያዙትም የሆነ የሚያሯሩጡት ነገር አላቸው። እኔ ግን ህይወት ‘ላንተ የሚሆን ድራማ የለኝም ዝም ብለህ የሌሎቹን ኑሮ መመልከት ትችላለህ’ ብላ ያገለለችኝ መስሎ ይሰማኛል” (ገጽ 71) መጥተው ይጎብኙን! #አሪፍ_መጻሕፍት #ማንበብ_አሪፍ_ነው #arif_books

  • አንዳንድ መጻሕፍት ይገርማሉ! ይህ ዘመን 'ሰው ከተፈጥሮ ጋር ያለው ግንኙነት እየላላ ሄዷል' የሚባልበት ሆኗል። በእርግጥ ሁሉን ነገር ስናየው እንደዚያ ይመስላል። የመምህረ መምህራን በጽሐ ዓለሙ "ምዕላደ ጥበብ" ግን ሰው አሁንም ተፈጥሮን አብጠርጥሮ እየመረመረ እያለ እንደሆነ ምስክር ነው። ለካ እንዲህ ከፍ ብሎ መራቀቅም ይቻላል? ይምጡና ይሸምቱ! አድራሻ: መሃል 4ኪሎ አብርሆት ላይብረሪ ግቢ ውስጥ #አሪፍ_መጻሕፍት #ማንበብ_አሪፍ_ነው #arif_books

  • አሪፍ መጻሕፍትን ጎብኝተዋል? እርስዎ ብቻ ብቅ ይበሉ! አድራሻ - መኻል 4 ኪሎ አብርሆት ላይብረሪ ግቢ ውስጥ #አሪፍ_መጻሕፍት #ማንበብ_አሪፍ_ነው #arif_books

  • አሪፍ መጻሕፍትን ጎብኝተዋል? አሪፍ መጻሕፍት ለእርስዎ የአእምሮ ምግብ የሚሆኑ ግሩም መጻሕፍትን ይዞ እየጠበቅዎት ነው። ሃይማኖታዊ ቢሉ ልብወለድ፥ ግጥም ቢሉ ታሪክ፥ ራስ አገዝ ቢሉ ፍልስፍና... ሁሉንም ይዘናል! እርስዎ ብቻ ብቅ ይበሉ! አድራሻ - መኻል 4 ኪሎ አብርሆት ላይብረሪ ግቢ ውስጥ #አሪፍ_መጻሕፍት #ማንበብ_አሪፍ_ነው #arif_books

  • የዛሬው ልዩ ቃል ደግሞ እነሆ! አንዳንድ የድሮ መጻሕፍት ወይም ከገበያ የጠፉ መጻሕፍት የሚሸጡ ሰዎች አሉ አይደል? እንግሊዝኛው "ቢብሊዮፖል" ብሎ ይጠራቸዋል። የጠፉ መጻሕፍትን እየገዙ መልሰው የሚሸጡ ሰዎች ማለት ነው። እርስዎ የሚያውቁት ቢብሊዮፖል የሆነ ሰው አለ ይኾን? #አሪፍ_መጻሕፍት #ማንበብ_አሪፍ_ነው #arif_books

  • ከአመጿ ጀርባ! የኤደን ሀብታሙ "ከአመጿ ጀርባ" በሁለት መቶ አስራ አራት ገጾችን እና ሰባት ምዕራፎችን የተዘጋጀ የረጅም ልብወለድ መጽሐፍ ነው። በሥነ-ልቡና እና ራስን ፍለጋ ላይ የሚያጠነጥነው ይህ መጽሐፍ ማኅበራዊ ጉዳዮችን እያነሳ በሚገባ የሚሞግት ነው። ይህንን አንዲት የአይምሮ ሐኪም ጋር እየተመላለሰች የህይወቷን ውጣ ውረድ የምታጋራ አመጸኛ ሴት ታሪክ ጋብዘነዎታል! #አሪፍ_መጻሕፍት #ማንበብ_አሪፍ_ነው #arif_books

  • የዛሬው አዲስ ቃል ደግሞ እነሆ! በመጻሕፍት የሚሰጥ ሕክምና መኖሩን ያውቁ ኖሯል? ይህንን ሕክምና "ቢብሊዮቴራፒ" የሚሉት ሲሆን፥ እንደ ጭንቀት፥ ደብርት እና የመሳሰሉትን በመጻሕፍት ንባብ የማከም እና የማሻሻል ተግባርን ይጠቁማል። መጻሕፍት የውስጥ መድኃኒት ናቸው የሚባለው በምክንያት ነው! #አሪፍ_መጻሕፍት #ማንበብ_አሪፍ_ነው #arif_books

  • የእውቀት ፋና መጻሕፍት የእውቀት ፋና፥ የጥበብ ቀንዲል፥ የብሩህ ሕይወት መክፈቻ ቁልፍ ናቸው። ዓለማዊም ቢሉ መንፈሳዊ፥ ሁሉን ከየዓይነቱ ይዘን ከተፍ ብለናል። መጥተው ይሸምቱ፥ ሕይወትዎን ብሩህ የሚያደርገውን የእውቀት ፋኖስም ይለኩሱ! ማንበብ ሙሉ ብቻ ሳይሆን ብሩህ ሰውም ያደርጋል! #አሪፍ_መጻሕፍት #ማንበብ_አሪፍ_ነው #arif_books

  • ቤታችን ሙሉ ነው! ሰውነት ምግብ የሚሻውን ያህል አእምሯችንም እውቀትና ጥበብን ይሻል። እኛ ደግሞ የአእምሮ ምግብ በአይነት በአይነቱ ይዘናል። ከተፍ ይበሉ... ቤታችን ሙሉ ነው። ለእርስዎ የሚሆን መጽሐፍ አያጡም! እኛም ከጥሩ ቅናሽ ጋር እንጠብቅዎታለን! #አሪፍ_መጻሕፍት #ማንበብ_አሪፍ_ነው #arif_books

  • የዛሬው ንባብ ነክ ቃል ደግሞ እነሆ! አንዳንድ ሰዎች ማንበብ የማይወድን ሰው ሲወርፉት "የመጽሐፍ ፎቢያ አለብህ እንዴ?" ይላሉ። ነገር ግን... የመጽሐፍ ፎቢያ የሚባል ነገር እንዳለ ያውቁ ኖሯል? ቢብሊዮፎቢያ የሚለው ቃል "የመጻሕፍት ወይም የንባብ ፍራቻ ያለበት ሰው" የሚል ትርጉም አለው። እርስዎ እንዲህ አይነት ወዳጅ አለዎት ይኾን? #አሪፍ_መጻሕፍት #ማንበብ_አሪፍ_ነው #arif_books

  • ከዓለም አንደኛ የግዕዝ ሊቅ በቅርቡ ከዚህ ዓለም እስከሚለዩበት ጊዜ ድረስ፥ ታዋቂው የግዕዝ ቋንቋ እና ድርሳናት ተመራማሪ የነበሩት ፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌ በውጪው ዓለም "The foremost scholar of Ge'ez in the World" (በዓለም ላይ ቀዳሚው የግዕዝ ሊቅ) በመባል ይታወቁ ነበር። እኚህ የሀገር ኩራት የሆኑ ሊቅ ከጻፏቸው ጽሑፎች መካከል "ከግዕዝ ሥነ ጽሑፍ ጋር ብዙ አፍታ ቆይታ" የተሰኘው መጽሐፋቸው በመደብራችን ይገኛል። ይኽንን ከሁሉም መጽሐፍ መደርደሪያ ላይ ሊጠፋ የማይገባ መጽሐፍ ከተፍ ብለው በእጅዎ ያደርጉት ዘንድ ጋብዘናል! #አሪፍ_መጻሕፍት #ማንበብ_አሪፍ_ነው #arif_books