- Последний пост
- 14 авг.
- Последнее чтение
- 15 авг.
- Постов за неделю
- 1
- Всего постов
- 21
- Тип
- открытый
- Язык
- ti
- В каталоге с
- 15 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 78
- 1/48двое суток
- 89
- 1/72трое суток
- 96
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
без подписи
без подписи
ናዚዎች እጆቿን ሰበሩ… እግሮቿንም ሰበሩ… ስም እንድትጠራ አስገደዷት። እሷ ግን 2,500 ሕፃናትን የደበቀችበትን ምስጢር አልተናገረችም! #የአይሪና_ሴንድለር_አስደናቂ_ታሪክ አንድ እናት ልጇን ለማያውቀው ሰው አሳልፋ ትሰጣለች? ይህ ዛሬ የማይታመን ጥያቄ ይመስላል። ግን 1942 በፖላንድ፣ ይህ የፍቅር ውሳኔ ሳይሆን የሕይወትና የሞት ምርጫ ነበር። በዋርሶ ጌቶ ውስጥ መቶ ሺዎች አይሁዶች በረሃብ፣ በበሽታ እና በፍርሃት ተዘግተው ይኖሩ ነበር። በየቀኑ ሕፃናት ይሞቱ ነበር። የተረፉትም የሚጠብቃቸው ሞት እንደሆነ ማንም ያውቅ ነበር። በዚያን ጊዜ አንዲት ወጣት ማህበራዊ ሠራተኛ እዚያ በየቀኑ ትገባ ነበር። ስሟ… አይሪና ሴንድለር። ሌሎች ሞትን ሲያዩ… እሷ ተስፋን ታይ ነበር። አንድ ቀን ለራሷ እንዲህ አለች፦ "ሁሉንም ማዳን አልችልም፤ ግን የምችለውን አላቆምም።" ከዚያ የማይታመን ተልዕኮ ጀመረች። ሕፃናትን ከጌቶው በድብቅ ማውጣት። አንዳንዶቹን በአምቡላንስ ውስጥ አስተኝታ… አንዳንዶቹን በእቃ ሳጥን… አንዳንዶቹን በድንች ከረጢት… አንዳንዶቹን በመሣሪያ ሳጥን… እንኳን በመሬት ስር ባሉ መስመሮች አሳልፋ አውጥታለች። ነገር ግን ከሁሉ የሚያሳዝነው ቅጽበት ይህ ነበር። አንድ እናት ልጇን አቅፋ ታለቅስ ነበር። አይሪናም እንዲህ ትላት ነበር፦ "ከእኔ ጋር ከሄደ ምናልባት ይኖራል። እዚህ ከቀረ… እድሉ በጣም ትንሽ ነው።" እናቶች በእንባ ልጆቻቸውን ይሰጡአት ነበር። ምናልባት ለመጨረሻ ጊዜ እያዩአቸው። አይሪና ግን አንድ ምስጢር ነበራት። የእያንዳንዱን ሕፃን እውነተኛ ስም፣ የወላጆቹን ስም እና የተደበቀበትን ቦታ በትንንሽ ወረቀት ላይ ትጽፍ ነበር። እነዚያን ወረቀቶች በመስታወት ማሰሮ ውስጥ አስቀምጣ… በአንድ ዛፍ ስር ትቀብር ነበር። ምክንያቱ? "ጦርነቱ ሲያበቃ እነዚህ ልጆች ማን እንደሆኑ እንዲያውቁ፤ ቤተሰባቸውንም እንዲፈልጉ።" ነገር ግን… አንድ ቀን ናዚዎች ያዟት። በጭካኔ ጠየቋት፦ "ሕፃናቱ የት ናቸው?" ዝም አለች። ደበደቧት። እግሮቿን ሰበሩ። እጆቿን ሰበሩ። እንደገና ጠየቋት። "ስሞቹን ንገሪ!" እሷ ግን… ዝም አለች። ስለ አንድም ሕፃን አልተናገረችም። የሞት ፍርድ ተፈረደባት። ነገር ግን ከመገደሏ በፊት የመሬት ውስጥ ተቃውሞ ቡድን አንድ የናዚ ጠባቂን ጉቦ ሰጥቶ አስመለጣት። ለዓለም ሞታለች ተባለ። ግን እሷ በሌላ ስም ተደብቃ ሕፃናትን ማዳን ቀጠለች። ጦርነቱ ሲያበቃ… ወደ ዛፉ ሄደች። ያንን ማሰሮ ከመሬት አወጣች። የሕፃናቱን ስም በመያዝ የቀሩትን ዘመዶቻቸውን መፈለግ ጀመረች። ነገር ግን ለብዙዎቹ… ወላጆቻቸው አልነበሩም። በካምፖች ውስጥ ተገድለው ነበር። አይሪና በሕይወቷ 2,500 ያህል ሕፃናትን ከሞት ለማዳን ተሳክቶላታል። በጣም የሚገርመው ግን ይህ ነው፦ አንድ ሰው "ጀግና ነሽ" ሲላት፣ እንዲህ ብላ መለሰች፦ "ብዙ ልጆችን ማዳን እችል ነበር። ያላዳንኳቸው ልጆች ናቸው የሚያሳዝኑኝ።" ከዚህ ታሪክ የምንማረው ❤️ ጀግንነት ፍርሃት አለመኖር አይደለም፤ ፍርሃት ቢኖርም ትክክለኛውን ነገር መሥራት ነው። ❤️ አንድ ሰው ያለው ሥልጣን ሳይሆን፣ ያለው ልብ የዓለምን ታሪክ ሊቀይር ይችላል። ❤️ እውነተኛ ሰብዓዊነት የሚለካው ለራስህ በምትኖረው ሳይሆን፣ ለሌሎች በምትደፍረው መስዋዕትነት ነው። ምናልባት አንተ ዓለምን ሙሉ መቀየር አትችልም፤ ግን የአንድን ሰው ዓለም ሙሉ መቀየር ትችላለህ። እና አንዳንድ ጊዜ ያ ብቻ በቂ ነው።
አንድ አባት ለልጃቸው ስለ ሕይወት እውነታ እንዲህ ሲሉ አስተማሩት ልጄ ሆይ፣ በእያንዳንዱ ሰው ልብ ውስጥ ትልቅ ጦርነት አለ። ይህ ጦርነት በሁለት ተኩላዎች መካከል የሚደረግ ነው። አንደኛው ተኩላ፦ ክፉ ነው። እሱ ቁጣን፣ ቅናትን፣ እብሪትን፣ ንስሐ የለሽነትን፣ ሐሰትን እና ስግብግብነትን ይወክላል። ሁለተኛው ተኩላ፦ መልካም ነው። እሱ ሰላምን፣ ፍቅርን፣ ተስፋን፣ ትህትናን፣ እውነትን እና ልግስናን ይወክላል። ልጁም ለትንሽ ጊዜ ካሰበ በኋላ፣ ታዲያ መጨረሻ ላይ የትኛው ተኩላ ነው የሚያሸንፈው? ብሎ ጠየቃቸው። እሳቸውም እንዲህ ሲሉ መለሱለት አንተ የምትመግበው ተኩላ ነው የሚያሸንፈው! SHARE||@astemari_tarik
በአንድ ጥንታዊ ሀገር ውስጥ የሚኖር በጣም ደሃ የሆነ አንድ ገበሬ ነበረ። ገበሬው ከዕለት ጉርስ በቀር ምንም የሌለው ቢሆንም፣ ሁልጊዜ በፊቱ ላይ ታላቅ ሰላምና እርካታ ይነበብ ነበር። አንድ ቀን የዚያች ሀገር ንጉሥ አደን አድኖ ሲመለስ መንገድ ጠፍቶበት በገበሬው ጎጆ አቅራቢያ አለፈ። ንጉሡ በጣም ደክሞትና ተርቦ ስለነበር፣ ገበሬው ማንነቱን ሳያውቅ በደስታ ተቀብሎ ያለችውን አንዲት ዳቦና ውሃ አቅርቦ አስተናገደው። ንጉሡ በገበሬው ደግነትና በቤቱ ባለው ሰላም እጅግ ተደሰተ። በማግስቱ ንጉሡ ወደ ቤተመንግስቱ ከመመለሱ በፊት እውነተኛ ማንነቱን ገለጠና ለገበሬው እንዲህ አለው፦ ስላደረግህልኝ መልካም መስተንግዶ ትልቅ ስጦታ ልሰጥህ እፈልጋለሁ። አሁን ካለህበት ቦታ ተነስተህ መሮጥ ጀምር፤ እስከ ዛሬ ምሽት ፀሐይ እስክትጠልቅ ድረስ በገዛ እግርህ እየረገጥክ የዞርከውና የሸፈንከው መሬት በሙሉ ለአንተና ለልጆችህ የዘላለም ርስት ሆኖ ይሰጥሃል አለው። ገበሬው ይህንን ሲሰማ በደስታ ፈነጠዘ። ይህማ ሕይወቴን ሙሉ በሙሉ የሚለውጥ ታላቅ ዕድል ነው ብሎ ወዲያውኑ ሮጦ መውጣት ጀመረ። ⌛ ጠዋት 4 ሰዓት፦ ገበሬው በጥሩ ፍጥነት እየሮጠ ነው። ውብ የሆኑትን ሜዳዎችና ለምለም ሸለቆዎች አቋረጠ። ይህ መሬት ለቤቴና ለሰብሌ ይበቃኛል ብሎ አሰበ። ነገር ግን ትንሽ ራቅ ብሎ የሚታየው ሌላኛው መስክ ይበልጥ ለምለም ስለነበር እሱንም ጭምር ልጨምረው ብሎ ፍጥነቱን ጨመረ። ⌛ ከሰዓት 7 ሰዓት፦ የቀትር ፀሐይ በኃይል ትፋጃለች። ገበሬው እጅግ በጣም ተርቧል፣ ተጠምቷል፣ እግሮቹም ዝለው መተርተር ጀምረዋል። ነገር ግን ወደኋላ ዞር ብሎ ሲያይ ገና ሰፊ ጊዜ አለኝ፣ ይቺን ኮረብታም ብጨምራት ለልጆቼ ታላቅ ሀብት ይሆናል እያለ ውሃ እንኳ ሳይጠጣ ሩጫውን ቀጠለ። ⌛ ከሰዓት 11 ሰዓት፦ ፀሐይ ቀስ በቀስ ወደ መጥለቂያዋ እያዘመመች ነው። ገበሬው አሁን በጣም ሩቅ ቦታ ላይ ነው ያለው። ድንገት የንጉሡ መመሪያ ትዝ አለው፦ ፀሐይ ከመጥለቋ በፊት መጀመሪያ ከተነሳህበት ቦታ ላይ ተመልሰህ መድረስ አለብህ፤ አለበለዚያ የሮጥከው መሬት በሙሉ አይሰጥህም የሚል ነበር። ገበሬው በድንገት ከባድ ፍርሃት ወረረው። የተነሳበት ቦታ በጣም ሩቅ ነው። አሁን መሬት ለመጨመር ሳይሆን የገዛ ሕይወቱን ለማዳን በረሃብና በጥም የዛለውን አካሉን እያስገደደ በኃይል ወደ ኋላ መሮጥ ጀመረ። ልቡ በጠና ትመታለች፣ ሳንባው አየር አጥሮታል፣ እግሮቹ ሊሸከሙት አልቻሉም። ፀሐይዋ ልክ ልትጠልቅ ጥቂት ደቂቃዎች ሲቀሯት፣ ገበሬው ንጉሡ ወደቆመበት መነሻ ቦታ ላይ እየተንገዳገደ ደረሰ። በጥፍሩ ጭረና መሬቱ ላይ ተዘረረ። ንጉሡም ፈገግ ብሎ እንኳን ደስ አለህ! መሬቱን በሙሉ አሸንፈሃል! አለው። ነገር ግን ገበሬው አልመለሰም። ንጉሡ ጠጋ ብሎ ሲመለከተው፣ ገበሬው በከፍተኛ ድካምና በጥም ብዛት ሕይወቱ አልፋ ነበር። የንጉሡ አገልጋዮችም አካፋ አምጥተው እዚያው ገበሬው በወደቀበት ቦታ ላይ ጉድጓድ ቆፈሩ። ለአንድ ሰው የሚበቃ ስድስት ስንዝር (ሁለት ሜትር) መሬት ብቻ ተቆፍረው ቀበሩት። ⌛ ጊዜና ጤናን መሸጥ እኛ ሰዎች ብዙ ጊዜ ሀብትና ቁሳቁስ ለማከማቸት ስንል የገዛ ጤናችንን፣ ከቤተሰብ ጋር ያለንን ጊዜና የሕይወታችንን ውብ ወራት በሩጫ እንገብራለን። ነገር ግን መጨረሻ ላይ የምንሰበስበውን ሀብት የሚያጣጥም ጤናማ ሕይወት እናጣለን! ሕይወት ማለቂያ የሌላት ሩጫ ናት። ዛሬ ይህ ሲኖረኝ እረካለሁ የምንለው ነገር ነገ ሲገኝ በሌላ ምኞት ይተካዋል። ስለዚህ በሩጫው መሃል ቆም ብሎ ያለንን ማድነቅና መደሰት ብልህነት ነው። ከታሪኩ ቢያንስ አንድ ነገር ከተማራችሁበት like share እያደረጋችሁ አበረታቱኝ @astemari_tarik
አስተማሪ ታሪክ pinned «ሰላም ቤተሰብ ስለቻናላችን ያላችሁን ሀሳብ አስተያየታችሁን በ comment ስር ፃፉልኝ ምን ይጨመር ምን ይቀነስ»
ሰላም ቤተሰብ ስለቻናላችን ያላችሁን ሀሳብ አስተያየታችሁን በ comment ስር ፃፉልኝ ምን ይጨመር ምን ይቀነስ
ሁለት ወጣቶች ወደ አንድ ጠቢብ ሰው ዘንድ ሄደው ህይወትን እንዴት መኖር እንዳለባቸው ጠየቋቸው። ጠቢቡ ሰውዬ ምንም ሳይናገሩ ሁለቱንም ወደ አንድ ትልቅ የአትክልት ስፍራ ወሰዷቸው። አንደኛውን ወጣት እንዲህ አሉት፡- በዚህ ስፍራ ውስጥ በጣም አስቀያሚ የሆኑትን ነገሮች ፈልገህ አምጣልኝ። ሰውየውም ሄዶ ወዲያውኑ የተበላሹ ፍራፍሬዎችን፣ የጠወለጉ ቅጠሎችን እና እሾሃማ አረሞችን ሰብስቦ መጣ። ይኸው አስቀያሚ ነገሮች እዚህ አሉ አለ። ለሁለተኛው ወጣት ደግሞ እንዲህ አሉት፡- አንተ ደግሞ በዚህ ስፍራ ውስጥ በጣም ውብ የሆኑትን ነገሮች ፈልገህ አምጣልኝ። ወጣቱም ሄዶ የሚያምሩ አበቦችን፣ ጣፋጭ ፍራፍሬዎችን እና ጥሩ ሽታ ያላቸውን ቅጠሎችን ሰብስቦ መጣ። ይኸው ውብ ነገሮች እዚህ አሉ አለ። ጠቢቡ ሰውዬ እንዲህ አሉ፦ሁለታችሁም በአንድ የአትክልት ስፍራ ውስጥ ነበር ያሳለፋችሁት። ነገር ግን አንዱ ለዓይኑ ያየው አስቀያሚውን ብቻ ሲሆን፣ ሌላኛው ደግሞ ያየው ውበቱን ብቻ ነው። አለም እንደዚህ ናት ህይወትህ ውስጥ በቂ አበባ እና እሾህ አለ። ማማረር ማለት እሾሁን ብቻ መርጠህ በውስጡ መቆየት ማለት ነው። የሚያማርር ሰው የፈለገውን ቢሰጡት፣ በውበት ውስጥ እንኳን እድፍ ይፈልጋል። ደስተኛ ሰው ግን በችግር ውስጥ እንኳን ውበትን ይፈልጋል። የአለም ሁኔታ በአንተ ቁጥጥር ስር ላይሆን ይችላል፣ ነገር ግን ያን አለም በምን አይነት መነፅር እንደምታየው በአንተ ቁጥጥር ስር ነው። ህይወትህን የምታማርረው በውስጧ እሾህ ስለሌለ አይደለም፤ ይልቁንም እሾሁን ብቻ ለመፈለግ ስላሰብክ ነው። የምታማርር ከሆነ ህይወትህ ሁልጊዜ እሾህ ትሆናለች፤ አመስጋኝ ከሆንክ ደግሞ ህይወትህ ሁልጊዜ አበባ ትሆናለች። ከታሪኩ ቢያንስ አንድ ነገር ከተማራችሁበት like share እያደረጋችሁ አበረታቱኝ @astemari_tarik
አንድ አዛውንት ሰው ለልጅ ልጃቸው አንድ ያረጀ የኪስ ሰዓት ሰጡት። ሰዓቱ በጣም ያረጀ፣ ጥንታዊ ሰዓት ነበረ አያቱ እንዲህ አሉት፦ ልጄ፣ ይህን ሰዓት ወደ ሰዓት ጥገና ሱቅ ውሰደውና ዋጋውን ጠይቅ። ከዚያ ምን እንደሚሉ ንገረኝ። ልጅ ልጁም ሰዓቱን ይዞ ወደ መጀመሪያው ሱቅ ሄደ። የሱቁ ባለቤት ሰዓቱን በደንብ ካየ በኋላ፣ ይህ በጣም ያረጀ ሰዓት ነው ዋጋው ምናልባት 100 ብር ሊሆን ይችላል አለው። ልጁ ተስፋ ቆርጦ ተመለሰ። አያቱ እንደገና፣ አሁን ደግሞ ወደ አሮጌ እቃዎች ገዢ ውሰደው አሉት። ልጁ ሄደ፤ ገዢው ሰዓቱን አየና ይህ ለስብስብ የሚሆን ብርቅዬ ዕቃ ነው፣ 5,000 ብር እሰጥሃለሁ አለው። ልጁ ተደስቶ ተመለሰ። አያቱ ለመጨረሻ ጊዜ፣ አሁን ደግሞ ወደ ሙዚየም ውሰደውና እዚያ አሳይ አሉት። ልጅ ልጁም ወደ ሙዚየሙ ሄደ። የሙዚየሙ ባለሙያ ሰዓቱን እንደተመለከተ፣ ዓይኖቹ በደስታ አበሩ። ይህ ታሪካዊ ሰዓት ነው! በእጅ የተሰራ፣ ጥንታዊ እና ብርቅዬ ነው። ለዚህ ሰዓት 5 ሚሊዮን ብር ወይም ከዛ በላይ እንከፍልሃለን አለው። ልጅ ልጁ በመገረም ተውጦ ወደ ቤቱ ተመለሰ። አያቱ ፈገግ ብለው እንዲህ አሉት፦ ልጄ፣ ይህ ሰዓት እውነተኛ ዋጋውን እንዲያውቅ ትክክለኛ ቦታ ላይ መገኘት ነበረበት። አንተም እንደዚህ ነህ። በሕይወትህ ውስጥ አንዳንድ ጊዜ በስህተት ሰዎች መካከል ትሆናለህ፤ እነሱ ዋጋህን ሊያዩልህ አይችሉም። ያ ማለት አንተ ዋጋ የለህም ማለት አይደለም፤ የቆምክበት ቦታ ትክክል አይደለም ማለት ነው። እውነተኛ ዋጋህን የሚያውቅ ቦታ እና ሰው እስክታገኝ ድረስ ተስፋ አትቁረጥ! ከታሪኩ ቢያንስ አንድ ነገር ከተማራችሁበት like share እያደረጋችሁ አበረታቱኝ @astemari_tarik
🛑 በሳይኮሎጂ_Psychology እ.ኤ.አ. ከክርስቶስ ልደት በፊት በ75 ዓመተ ዓለም ገደማ፣ ወጣቱ ጁሊየስ ቄሳር በኤጅያን ባህር ላይ በመርከብ እየተጓዘ ሳለ፣ በወቅቱ በጣም አስፈሪ እና ጨካኝ በነበሩ የኪልቅያ የባህር ላይ ወንበዴዎች ተማረከ። ወንበዴዎቹ ቄሳርን ወደ አንድ ገለልተኛ ደሴት ወስደው አገቱት። በተለመደው ሁኔታ አንድ ሰው በታጣቂዎችና በወንበዴዎች እጅ ሲወድቅ ይፈራል፣ ያለቅሳል ወይም ህይወቱን ለማዳን ይለምናል። ቄሳር ግን ፍጹም ተቃራኒ የሆነ የሳይኮሎጂ ዘዴ ተጠቀመ። እራሱን እንደ ታጋች ሳይሆን እንደ ወንበዴዎቹ ጌታ እና የበላይ አድርጎ ማሳየት ጀመረ። ወንበዴዎቹ ቄሳርን ለማስለቀቅ ከሮም መንግስት 20 ታላንት (Talents) የብር ሳንቲም ለመጠየቅ ወሰኑ። ቄሳር ይህንን ሲሰማ በታላቅ ድምፅ ሳቀ። እናንተ እኔ ማን እንደሆንኩ አታውቁም! ለኔ 20 ታላንት ብቻ መጠየቅ ውርደት ነው። ቢያንስ 50 ታላንት ጠይቁ! አላቸው። ወንበዴዎቹ ግራ በመጋባት ዋጋውን ወደ 50 ከፍ አደረጉት። ቄሳር በራሱ ላይ ትልቅ ዋጋ በመስጠቱ፣ ወንበዴዎቹ በንቃተ-ህሊናቸው (Subconsciously) እሱ በጣም ትልቅ እና ልዩ ሰው እንደሆነ አምነው እንዲፈሩት አደረጋቸው። ቄሳር በደሴቱ ላይ ለ38 ቀናት ታጋች ሆኖ ቆየ። ነገር ግን በእነዚያ ቀናት ውስጥ ወንበዴዎቹን ያዛቸው ነበር። ሊተኛ ሲል ዝም በሉ፣ መተኛት እፈልጋለሁ እያለ ያንቀጠቅጣቸው ነበር። እሱ የጻፋቸውን ግጥሞች እና ንግግሮች እንዲሰሙ ያስገድዳቸው ነበር፤ ካላደነቁት ደግሞ እናንተ ያልተማራችሁ አረመኔዎች! እያለ ይሰድባቸው ነበር። ቄሳር ከወንበዴዎቹ ጋር በነበረው ቆይታ እየሳቀ አንድ ነገር በተደጋጋሚ ይነግራቸው ነበር፡- ከዚህ በነፃ እንደተለቀቅኩ፣ ትልቅ ሰራዊት ይዤ ተመልሼ እመጣና ሁላችሁንም እሰቅላችኋለሁ! ይላቸው ነበር። ወንበዴዎቹ ግን ይህንን እንደ ጨዋታ እና እንደ እብድ ሰው ቀልድ ቆጥረው ይስቁበት ነበር። የሮም መንግስት የ50 ታላንት ብሩን ከፍሎ ቄሳርን አስለቀቀው። ቄሳር ነፃ እንደወጣ ግን በቀጥታ ወደ ሚሊተስ ወደብ በመሄድ የጦር መርከቦችን አደራጀ። ወዲያውኑ ወደ ደሴቱ ተመልሶ በመሄድ ወንበዴዎቹን ባልጠበቁት ሰዓት በቁጥጥር ስር አዋላቸው። ልክ አስቀድሞ እንደዛተባቸውም፣ ንብረታቸውን በሙሉ ቀምቶ ሁሉንም በስቅላት ቀጣቸው። ከዚህ ታሪክ የምንማራቸው 3 የስትራቴጂ እና የሳይኮሎጂ አሉ 1️⃣ Set Your Own Value (ዋጋህን እራስህ ወስን)፦ ሰዎች ለአንተ የሚሰጡህ ክብር እና ዋጋ፣ አንተ ለራስህ ከምትሰጠው ዋጋ ጋር እኩል ነው። ቄሳር እራሱን ዝቅ አድርጎ ቢለምናቸው ኖሮ ሊገሉት ወይም ሊያንገላቱት ይችሉ ነበር። ነገር ግን በራስ መተማመኑን (Confidence) በጣም ከፍ በማድረጉ በጠላቶቹ አእምሮ ውስጥ ፍርሃትን መዝራት ችሏል። 2️⃣ The Illusion of Control (የመቆጣጠር ቅዠት)፦ በጣም አስቸጋሪ ወይም አቅም በሌለህበት ሁኔታ ውስጥ እንኳ ስትሆን፣ ፍርሃትህን ደብቀህ ሁኔታውን እንደምትቆጣጠረው ሰው በቁርጠኝነት መንቀሳቀስ የተቃራኒ ወገንን የስነ-ልቦና መከላከያ እና የበላይነት ስሜት ሙሉ በሙሉ ያፈርሰዋል። 3️⃣ Boldness over Weakness (ድፍረት ከሽንገላ ይበልጣል)፦ በሰዎች መካከል በሚደረግ የስልጣን እና ፉክክር ውስጥ፣ እራስን ዝቅ አድርጎ ከመለማመጥ ይልቅ ፍጹም ድፍረትን ማሳየት፣ ተቃዋሚዎችህ ለአንተ እጅ እንዲሰጡ ወይም ጥንቃቄ እንዲያደርጉ የሚያስገድድ ታላቅ መሳሪያ ነው። ከታሪኩ ቢያንስ አንድ ነገር ከተማራችሁበት like share እያደረጋችሁ አበረታቱኝ @astemari_tarik
በጥንት ዘመን አንድ ሰው ወደ ጥበበኛው ንጉሥ ዘንድ ሄዶ፣ ንጉሥ ሆይ፣ አንድ ሚስጥር አለኝ፤ ስለ አንድ ሰው መጥፎ ነገር ሰምቻለሁ፣ ልነግርህ እፈልጋለሁ አለው። ንጉሡም ሰውየውን ተመለከተና እንዲህ አለው፦ ጥሩ፣ ግን ያገኘኸውን መረጃ ለኔ ከመናገርህ በፊት፣ ይህ መረጃ የሦስቱ በሮች ማለፍ አለበት። ዝግጁ ነህ? ሰውየውም አዎ፣ ዝግጁ ነኝ አለ። ንጉሡም የመጀመሪያውን በር አሳየው፦ 1. የእውነት በር: የምትነግረኝ ነገር 100% እውነት መሆኑን እርግጠኛ ነህ? ሰውየው፣ አላውቅም፣ ሰዎቹ ሲያወሩ ሰምቻለሁ እንጂ አለ። ንጉሡም፣ እንግዲያውስ ይህ መረጃ የመጀመሪያውን በር አላለፈም አለ። ንጉሡ ወደ ሁለተኛው በር ቀጠለ፦ 2. የጥሩነት በር: የምትነግረኝ ነገር ስለዛ ሰው የምትናገረው መልካም ነገር ነው? ሰውየው፣ አይደለም፣ መጥፎ ነገር ነው አለ። ንጉሡም፣ እንግዲያውስ ሁለተኛውን በርም አላለፈም አለው። ንጉሡ ወደ መጨረሻው በር አመራ፦ 3. የአስፈላጊነት በር: የምትነግረኝ ነገር ለእኔ ወይም ለግዛቴ ጠቃሚ ወይም አስፈላጊ ነገር ነው? ሰውየው፣ አይደለም፣ ጠቃሚ አይደለም አለ። ንጉሡም ፈገግ ብሎ እንዲህ አለው፦ እንግዲያውስ፣ እውነት መሆኑን የማታውቀው፣ ጥሩ ያልሆነና ምንም ጥቅም የሌለው መረጃ ከሆነ ለምን ትነግረኛለህ? ሚስጥር ብለህ የምትይዘው ነገር እነዚህን ሦስት በሮች ካላለፈ፣ መናገር ብቻ ሳይሆን ማወቅም አያስፈልግህም። ከታሪኩ ቢያንስ አንድ ነገር ከተማራችሁበት like share እያደረጋችሁ አበረታቱኝ @astemari_tarik
በአንድ ወቅት ናፖሊዮን ቦናፓርት ከጠላቶቹ ጋር በጣም ከባድ ጦርነት ውስጥ ነበር። የፈረንሳይ ሰራዊት ሌሊቱን ሙሉ ነቅቶ የጠላትን እንቅስቃሴ መጠበቅ ነበረበት። ናፖሊዮንም ሰራዊቱ እንዴት እየጠበቀ እንደሆነ ለማየት ሌሊት እኩለ ሌሊት ላይ በካምፑ ውስጥ ብቻውን እየተዘዋወረ መመልከት ጀመረ። በድንገት ግን በአንድ በጣም ወሳኝ በሆነ የጥበቃ ቦታ ላይ፣ አንድ ጠባቂ ወታደር ጠመንጃውን አቅፎ መሬት ላይ ተኝቶ አገኘው። በወቅቱ በነበረው የሚሊተሪ ሕግ መሰረት፣ አንድ ወታደር በጦርነት መሃል ጥበቃ ላይ እያለ ቢተኛ ፍርዱ ፍጹም የሞት ቅጣት ነበር። ምክንያቱም የእሱ መተኛት መላውን ሰራዊት ለአደጋ ያጋልጣል። ማንኛውም ሌላ መሪ ቢሆን ወዲያውኑ ወታደሮቹን ጠርቶ ይህንን ከሃዲ ወታደር እሰሩት ነገ ጠዋት ይገደላል ብሎ ይፈርድበት ነበር። ናፖሊዮን ግን ፍጹም የተለየ የሳይኮሎጂ ዘዴ ለመጠቀም ወሰነ። ናፖሊዮን ወታደሩን ቀስቅሶ አላስደነገጠውም። ወይም ወታደሮቹን ጠርቶ አላሳሰረውም። ይልቁኑ፣ የተኛውን ወታደር ጠመንጃ ቀስ አድርጎ ከእጁ ላይ ወሰደው። ከዚያም ናፖሊዮን ራሱ የፈረንሳይ ንጉሠ ነገሥት እና የጦር አዛዥ መሆኑን ዘንግቶ፣ በዚያ ወታደር ምትክ ጠመንጃውን ይዞ ጥበቃውን ቀጠለ! ከጥቂት ሰዓታት በኋላ ወታደሩ ከእንቅልፉ ሲነቃ፣ ከፊቱ ቆሞ ጥበቃ እያደረገ ያለውን ሰው አየ። ዓይኑን ማመን አልቻለም፤ ናፖሊዮን የእሱን ጠመንጃ ይዞ እየጠበቀለት ነበር! ወታደሩ በከፍተኛ ፍርሃት ተንቀጠቀጠ፣ መሬት ላይ ተደፍቶም ጌታዬ ሆይ፣ በጣም ደክሞኝ ነው፣ እባክህ ግደለኝ፣ ፍርዴን አውቃለሁ እያለ ማልቀስ ጀመረ። ናፖሊዮን ግን ጠመንጃውን በፈገግታ እየመለሰለት እንዲህ አለው፦ አይዞህ ወዳጄ። ሌሊቱን ሙሉ በጣም እንደደከማችሁ እና እንደለፋችሁ አውቃለሁ። አንተ ለአፍታ ያህል እንቅልፍ በወሰደህ ሰዓት እኔ ጥበቃውን ባደርግልህ ምንም ጥፋት የለውም። አሁን ግን እኔም ደክሞኛል፣ ጥበቃውን መልሰህ ተረከበኝ። ናፖሊዮን ይህንን ያደረገው ዝም ብሎ በደግነት አልነበረም። ወታደሩን ቢገድለው ኖሮ በሌሎች ወታደሮች አእምሮ ውስጥ መሪአችን ጨካኝ ነው የሚል ፍርሃት እና ጥላቻ ይነግስ ነበር። ነገር ግን ናፖሊዮን የሞት ፍርድ ከማስተላለፍ ይልቅ ይህንን የሳይኮሎጂ ዘዴ በመጠቀሙ፣ ያ ወታደርም ሆነ መላው ሰራዊት ለናፖሊዮን ያላቸው ክብር እና ፍቅር እጥፍ ሆነ። ከዚያ ቀን ጀምሮ ያ ወታደር ለናፖሊዮን ሲል ህይወቱን ለመስጠት ወደማያቅማማ እጅግ ታማኝ ጀግና ተቀየረ። 1. The Pygmalion Effect (የከፍተኛ ተስፋ ውጤት) ሰዎችን በሕግ እና በጥፋታቸው ልክ ሁልጊዜ በቅጣት ብቻ ለመግራት ከመሞከር ይልቅ፣ ባልጠበቁት መንገድ ምህረትን ማሳየት እና አንተ የተሻልክ ሰው ነህ የሚል እምነት መስጠት፣ ባህሪያቸውን ሙሉ በሙሉ ይለውጠዋል። ሰዎች የተሰጣቸውን ጥሩ ስም ለመጠበቅ ሲሉ ታማኝ ይሆናሉ። 2. Lead by Example (በተግባር መሪ መሆን) ናፖሊዮን እራሱ ወርዶ ጥበቃ ማድረጉ፣ በበታቾቹ አእምሮ ውስጥ መሪዬ እኔ የምደክመውን ድካም ያውቃል የሚል ጥልቅ የስነ-ልቦና ትስስር ፈጠረ። ከአንድ ሰው ታማኝነትን እና ስራን ከመጠበቅህ በፊት፣ አንተም ያንን ስራ ለመስራት ዝግጁ መሆንህን ማሳየት አለብህ። 3. Subverting Expectations (የሰዎችን ግምት ማፍረስ) ሰዎች ጥፋት ሲያጠፉ ቅጣትን ይጠብቃሉ። ያንን የሚጠብቁትን ግምት ሰብረህ ፍጹም ተቃራኒ የሆነ ፍቅር ወይም ምህረት ስትሰጣቸው አእምሯቸው በድንጋጤ ውስጥ ሆኖ ለአንተ ፍጹም ታዛዥ እና ባለዕዳ ይሆናል። ከታሪኩ ቢያንስ አንድ ነገር ከተማራችሁበት like share እያደረጋችሁ አበረታቱኝ @astemari_tarik
ስለ ታላቁ ተጫዋች የእግርኳስ ንጉስ ስለሆነው ብዙ ክብሮች ኖሮት ስለ ራሱ እኔ እንዲህ ነኝ ብሎ ለማይለው ብዙዎች ሪከርድ ሲያሳዱ እሱ ግን ሪከርድ የሚያሳደው እግርኳስ ምን አይነት እንደሆነ ላሳየን ስለ Lionel Messi ብዙ የሚተነተንበት ቻናል ነው ተቀላቀሉን 👇👇👇 https://t.me/+AdT2NXE-3CkzODVk
በአንድ ወቅት በአንድ በጣም ረጅም ተራራ ጫፍ ላይ የሚገኝ ታላቅ የንሥር ጎጆ ነበረ። በጎጆው ውስጥ አራት ትላልቅ የንሥር ዕንቁላሎች ነበሩ። አንድ ቀን ግን ባልተጠበቀ ሁኔታ የተከሰተ ኃይለኛ የመሬት መንቀጥቀጥ ተራራውን አናወጠው። በዚህ ጊዜ አንደኛው ዕንቁላል ከጎጆው ወጥቶ ተንከባለለ፤ ከተራራው ግርጌ ወደሚገኘው የአንድ ገበሬ የዶሮ ማደሪያ ውስጥ ገባ። ማደሪያው ውስጥ የነበሩት ዶሮዎች ይህንን ትልቅ ዕንቁላል አዩት። አንዲት ዶሮም ዕንቁላሉን ልክ እንደ ገዛ ዕንቁላሎቿ አቅፋና ሙቀት ሰጥታ ልትፈለፍለው ወሰነች። ከቀናት በኋላ ዕንቁላሉ ተሰበረ። በውስጡም በጣም ውብና ኃይለኛ የሆነ ትንሽ ንሥር ወጣ። ነገር ግን ይህ ንሥር ያደገው ከዶሮዎቹ ጋር ስለነበረ፣ ራሱን እንደ ዶሮ አድርጎ ያስብ ነበር። ልክ እንደ ዶሮዎቹ መሬት መሬቱን እየቧጠጠ ትሎችን ይፈልግ ነበር። ዶሮዎቹ ከጥቂት ሜትሮች በላይ መብረር ስለማይችሉ፣ እሱም ክንፎቹን አጣጥፎ ከጥቂት እርምጃዎች በላይ ለመብረር ሞክሮ አያውቅም ነበር። አንተ እኮ ዶሮ ነህ፤ ስለዚህ መሬት ላይ መኖር አለብህ የሚለውን የዶሮዎቹን ወሬ ሙሉ በሙሉ አምኖ ተቀብሎት ነበር። ዓመታት አልፉ። ንሥሩ በዕድሜና በአካል እያደገ ሄደ። አንድ ቀን ማለዳ መሬት ላይ ሆኖ ምግቡን እየፈለገ ሳለ ወደ ሰማይ ቀና ብሎ ሲመለከት አንድ አስደናቂ እይታ አየ። እጅግ በጣም ግርማ ሞገስ ያለው፣ ክንፎቹን በሰፊው የዘረጋ አንድ ትልቅ ንሥር በነፃነት ሰማዩን እየቀደደ ሲበር ተመለከተ። ንሥሩ በአድናቆት ተሞልቶ አጠገቡ ለነበረችው ዶሮ እንዲህ ሲል ጠየቃት፦ ያ የሚያምር ወፍ ማን ይባላል? እንዴትስ ነው እንደዚያ በጥንካሬ መብረር የቻለው? ዶሮዋም አሽሟጣጭ በሆነ ድምፅ እንዲህ አለችው፦ እሱን ተወው! ያ እኮ የአእዋፍ ሁሉ ንጉሥ የሆነው ታላቁ ንሥር ነው! እሱ የተፈጠረው ለሰማይ ነው። አንተ ግን ዶሮ ነህ፤ የአንተ ዓለም ይሄው መሬት ብቻ ስለሆነ ሰማዩን ማየትህን ትተህ ትልህን ፈልግ! ይህ ምስኪን ንሥር ያንን የዶሮዋን ቃል እውነት ነው ብሎ አመነ። ከዚያ ቀን በኋላ ወደ ሰማይ ማየቱን ተወ። የዕድሜ ልክ ሙሉ የንሥርነት ኃይልና ክንፍ እያለው፣ ራሱን እንደ ዶሮ ቆጥሮ በዚያው በዶሮ ማደሪያ ውስጥ በችጋር ሞተ። በሕይወትህ ውስጥ ትልቅ ራዕይና አቅም እያለህ፣ ሁልጊዜ የምትውለው አነስተኛ አስተሳሰብ ካላቸው ሰነፍና ተስፋ ከቆረጡ ሰዎች ጋር ከሆነ ሳታውቀው የነሱን የዶሮነት አስተሳሰብ ትወርሳለህ። ሰዎች አትችልም፣ ይህ ላንተ አይሆንም ስላሉህ ብቻ ያንን የነሱን ደካማ እይታ የራስህ ጣሪያ አታድርገው። ከታሪኩ ቢያንስ አንድ ነገር ከተማራችሁበት like share እያደረጋችሁ አበረታቱኝ @astemari_tarik
በአንድ ወቅት በአንድ ተራራማ መንደር ውስጥ የሚኖሩ አንድ አባትና ልጅ ነበሩ። አንድ ቀን ሁለቱም አብረዋቸው የነበረውን ያረጀ አህያ እየነዱ ወደ ከተማው ገበያ ለመሄድ ጉዞ ጀመሩ። አህያው ምንም የተጫነው ነገር አልነበረም፤ አባትና ልጅም ከጎኑ በእግራቸው እየተጓዙ ነበር። ገና ጥቂት እንደተጓዙ፣ መንገድ ላይ የተቀመጡ አንዳንድ ሰዎች አዩአቸውና መሳቅ ጀመሩ። እነዚህን ሞኞች እስቲ እዩአቸው! የሚጋለብ አህያ እያላቸው ሁለቱም በእግራቸው በጭቃው ውስጥ ይሄዳሉ አሉ። አባትየው ይህንን ሲሰማ አፈረ። ሰዎቹ ልክ ናቸው አሰበና ልጁን አህያው ላይ አስቀመጠው፤ እሱ ግን በእግሩ መጓዙን ቀጠለ። ትንሽ ራቅ ብለው ሲሄዱ፣ ሌላ ቡድን ሰዎችን አገኙ። ሰዎቹም ወደ ልጁ እያመለከቱ በቁጣ እንዲህ አሉ። ይህንን ዘመን የማይፈራ ጨካኝ ወጣት እዩት! እሱ በምቾት አህያው ላይ ተቀምጧል፤ በዕድሜ የገፋውን ምስኪን አባቱን ግን በፀሐይ ውስጥ በእግሩ ያስኬደዋል። ምን ዓይነት ክፉ ልጅ ነው! ልጁ ይህንን ሲሰማ በጣም አዘነ። ወዲያውኑ ከአህያው ላይ ወረደና አባቱን አባት ሆይ፣ አንተ ተቀመጥ አለው። አባትየው አህያው ላይ ወጣ፣ ልጁ ደግሞ በእግሩ መከተል ጀመረ። ገና አንድ ኪሎ ሜትር ሳይሄዱ፣ ሌሎች መንገደኞች አጋጠሟቸው። ሰዎቹም በአባትየው ላይ አፌዙባቸው። "እንዴ! ይህንን ራስ ወዳድ አባት እዩት እስቲ! እሱ በትልቅነቱ አህያ ላይ ተቀምጦ፣ ይህን ምስኪን ልጁን በባዶ እግሩ ያንከራትተዋል አሉ። አባትና ልጅ ምን ማድረግ እንዳለባቸው ግራ ገባቸው። በመጨረሻም የሰዎቹን ወሬ ለማስቆም ሁለታችንም አህያው ላይ እንቀመጥ ተባባሉና ሁለቱም በአንድነት አህያው ላይ ተጫኑበት። ወደ ከተማው መግቢያ ሲደርሱ፣ የእንስሳት መብት ተሟጋች የሚመስሉ የከተማ ሰዎች አዩአቸውና ክፉኛ ይጮኹባቸው ጀመር። እንዴት እንዲህ ዓይነት ጨካኝ ትሆናላችሁ? ይህንን የዛለና ያረጀ ምስኪን አህያ ሁለታችሁ ተጭናችሁ ልትገድሉት ነው እንዴ? ብለው ጮሁባቸው! በሕይወትህ ውስጥ የምታደርገው ማንኛውም ነገር (መልካምም ይሁን ክፉ) ሁልጊዜ የሚተችህና የማይስማማ ሰው አይጠፋም። ሕይወት የምትመራው በራስህ እምነትና ትክክለኛ ሕሊና እንጂ፣ ሰዎች በየደቂቃው በሚቀይሩት አስተያየት መሆን የለበትም። ሰዎች ስለ አንተ የሚናገሩት ነገር የእነርሱን አመለካከት እንጂ የአንተን እውነተኛ ማንነት አይወክልም። ስለዚህ ለሰዎች ወሬ ከልክ በላይ መጨነቅ የገዛ ሕይወትን ማበላሸት ነው። ሕይወት ያንተ ናት፤ ጉዞውን የምትጓዘውም በገዛ እግርህ ነው። ሰዎች ሁልጊዜ ያወራሉ፤ አንተ ግን ልብህ የሚያውቀውን ትክክለኛውን መንገድ መርጠህ በሰላም ተጓዝ። ከታሪኩ ቢያንስ አንድ ነገር ከተማራችሁበት like share እያደረጋችሁ አበረታቱኝ @astemari_tarik
some one 🗣 ከአባትክ ምኑን ትወድለታለክ? me:-መኖሩን🥺
አንድ ትምህርት ቤት ውስጥ ነበር የሆነው ፕሮፌሰሩ ሁሉንም ተማሪዎች ከላይ በምስሉ በምታዩት መልክ ፊኛ እየነፉ ስማቸውን እንዲፅፉበት አደረጉ።ቀጥሎ ሁሉም ፊኛዎች ወደ አዳራሽ ተለቅቀው እያንዳንዱ ተማሪ የየራሱን ስም(ፊኛ) እንዲፈልግ ታዘዘ።5 ደቂቃ ተሰጣቸው ምንም ያህል በችኮላ ቢፈልጉም ማንምየራሱን ፊኛ ማግኘት አልቻለም ጊዜውም አለቀ። ፕሮፌሰሩ ቆይቶ ደግሞ ተጨማሪ 5 ደቂቃዎች በመስጠት ሁሉም ተማሪ ያገኘውን የሌላ ሰው ፊኛ ለባለቤቱ እንዲሰጥ አደረገ። አስገራሚ ውጤት ታየ ተማሪው በሙሉ እየተጠራራ አንዱ ለሌላው እያቀበለ 5 ደቂቃው ሳይገባደድ ሁሉም የየራሱን ፊኛ ተቀበለ።ፕሮፌሰር ነገሩን ከሕይወት ልምድ ጋር ያቆራኘበት አግባብ ነው ያስደሰተኝ። "አያችሁ የናንተ ደስታና የልብ መሻትም እንደ ፊኛው ናቸው።የራሳችንን ደስታ(ፊኛ) ብቻ ባሳደድን ቁጥር ልናገኘው አንችልም ወይም እስክናገኘው ይቆያል።ይልቅዬ ለሰዎች ደስታ ፍላጎት ባሳየን በተባበርን መጠን ለራሳችንንም ደስታን በቀላሉ እንጎፀፋለን SHARE||@astemari_tarik
ውይ ሜሲሲ 🙆♂🐐 አንቀጠቀጣቸውኮ🥶
ልጁ ከረጅም መንገድ መልስ ደክሞት እረፍት ፍለጋ በአንድ አሮጌ ዛፍ ስር ተቀመጠ። ጫማዎቹ በአቧራ ተሸፍነዋል፣ ልብሱም አልቋል። ከሁሉ በላይ ግን ተስፋ መቁረጡ ፊቱ ላይ ይነበብ ነበር። ያሰበው ሁሉ አልተሳካለትም፣ የደከመበትም ሁሉ መና ቀርቷል። “እስከ መቼ?” አለ ወደ ላይ እያየ። “እስከ መቼ ነው የምፈተነው? ድካሜን አታይም?” ልክ ይሄን ብሎ ሲያበቃ፣ ድንገት ነፋሱ ቀሰቀሰና የዛፉ ቅጠሎች ተንቀሳቀሱ። በልጁ አእምሮ ውስጥ ደግሞ አንድ የድሮ ትዝታ ብልጭ አለ። ህጻን እያለ መራመድ ሲጀምር በተደጋጋሚ ይወድቅ የነበረው ትዝ አለው። በወደቀ ቁጥር ግን አባቱ እየመጣ ያነሳው፣ እጁን ይዞ እንዲበረታ ያደርገው ነበር። ያኔ ህጻኑ ልጅ አባቱን ያየው የነበረው በአክብሮትና በፍጹም መታመን ነበር። በዚያች ቅጽበት ልጁ ትልቅ እውነት ገባው። ፈጣሪ እኮ ከዛ አባት በላይ ነው። በዚህ የህይወት መንገድ ላይ ሲደናቀፍ፣ ሲወድቅና ሲቆስል ፈጣሪ አልተለየውም። እንዲያውም እሱ ደክሞት መራመድ ባቃተው ጊዜ ሁሉ፣ ፈጣሪ በትከሻው ላይ አዝሎት እንደነበረ ተሰማው። በጫማው ላይ ያለው አቧራ የራሱ ድካም ብቻ ሳይሆን፣ ፈጣሪ አብሮት በዚያ አስቸጋሪ መንገድ ላይ እንደተጓዘ የሚያሳይ ምስክር ይመስል ነበር። ልጁ ተነሳ። አቧራውን አራገፈ። ምንም እንኳ ኪሱ ባዶ ቢሆንም፣ ልቡ ግን ፍርሃት በሌለው ፍቅር ተሞላ። በፈጣሪና በወንድ ልጅ መካከል ያለው ዝምድና ይሄው ነው፤ ልጁ መንገድ ሲጠፋው ፈጣሪ መብራት ይሆናል፣ ልጁ ሲደክመው ፈጣሪ ብርታት ይሆናል። ሁልጊዜም የማይለቅ የፍቅር ትስስር። SHARE||@astemari_tarik
አንድ ቀን በአንድ የኢኮኖሚክስ ኮሌጅ ውስጥ የሚያስተምር ታዋቂ ፕሮፌሰር ወደ ክፍሉ ገባ። ተማሪዎቹ ደብተራቸውን አውጥተው ማስታወሻ ለመያዝ ሲዘጋጁ፣ እሱ ግን ጥቁር ሰሌዳው ላይ አንድ ትልቅ ቁጥር ጻፈ 86,400። ፕሮፌሰሩ ወደ ተማሪዎቹ ዞር አለና እንዲህ ሲል ጠየቀ፦ በየቀኑ ጠዋት ጠዋት፣ በአለም ላይ ለሚገኝ ለእያንዳንዱ ሰው እኩል 86,400 ብር የሚያስገባ አንድ ሚስጥራዊ የባንክ አካውንት ቢኖራችሁ ምን ታደርጉታላችሁ? ተማሪዎቹ በደስታ ተገረሙ። አንደኛው ተማሪ እጁን አውጥቶ ሁሉንም ሳንቲም ተጠቅሜበት እውላለሁ፤ አንድም ብር አላስቀርም! አለ። ሌሎቹም ተማሪዎች የፈለግነውን እንገዛበታለን እያሉ ተስማሙ።ፕሮፌሰሩ ፈገግ አለና የባንኩን ሦስት ጥብቅ መመሪያዎች ማስረዳት ጀመረ፦ 1. የመጀመሪያው መመሪያ፦ በየቀኑ የተሰጣችሁን ገንዘብ ተጠቅማችሁበት ካልዋላችሁ፣ ማታ 6 ሰዓት ሲሆን የተረፈው ሳንቲም በሙሉ ተኖ ይጠፋል፤ ወደ ሌላ ቀን ማዛወር (Carry forward) አይቻልም። 2. ሁለተኛው መመሪያ፦ ገንዘቡን በሙሉ ማውጣት እንጂ በቁጠባ አካውንት ውስጥ ማስቀመጥ ፈጽሞ አይፈቀድም። 3. ሦስተኛው መመሪያ፦ ይህ ባንክ ያለምንም ቅድመ ማስጠንቀቂያ በማንኛውም ቀን አካውንቱን ሙሉ በሙሉ የመዝጋት ስልጣን አለው። ፕሮፌሰሩ ታዲያ አሁን ምን ታደርጋላችሁ? አላቸው። ተማሪዎቹም አንድም ሳንቲም ሳናባክን በየቀኑ ለራሳችንም ሆነ ለምንወዳቸው ሰዎች መልካም ነገር ላይ እናውለዋለን አሉ። ፕሮፌሰሩ ነጭ ጠመኔውን አነሳና ከቁጥሩ ጎን ሰከንድ የሚል ቃል ጻፈ። ክፍሉ በሙሉ ጸጥ አለ። ይህ ባንክ ምናባዊ ሳይሆን ሁላችንም እጃችን ላይ ያለ እውነተኛ ባንክ ነው፤ ስሙም ጊዜ ይባላል። በየቀኑ ጠዋት ስንነቃ ፈጣሪ ለሁላችንም እኩል 86,400 ሰከንዶችን በነፃ ይሰጠናል። ማታ ስንተኛ የተጠቀምንበት አልቆ፣ ያልተጠቀምንበት ደግሞ ለዘላለም ተኖ ይጠፋል። ለነገ ማሳደር ወይም ለሌላ ቀን ማከማቸት አንችልም። በዚያች ቀን የተሰጠንን ጊዜ በመልካም ሥራ፣ በፍቅርና በደስታ ካልኖርንበት፣ ባንኩ ያንን ጊዜ መልሶ አይሰጠንም። ከሁሉም በላይ ደግሞ፣ ይህ የሕይወት ባንክ ያለምንም ማስጠንቀቂያ በማንኛውም ሰከንድ አካውንታችንን የመዝጋት (የመሞት) መብት አለው። ብዙ ጊዜ እኛ ሰዎች ትናንት በደረሰብን እክል እያለቀስን ወይም ስለ ነገው ጭንቀት እያሰብን የዛሬውን ውብ 86,400 ሰከንዶች በከንቱ እናባክናለን። ነገር ግን እውነተኛው ሕይወት ያለው አሁን በምንኖራት ሰከንድ ውስጥ ብቻ ነው። ሀብታም ስሆን እደሰታለሁ፣ ሥራ ስይዝ እረካለሁ፣ ትዳር ስመሠርት ሰላም አገኛለሁ እያሉ ደስታን ለነገ ቀጠሮ መቅጠር የሕይወትን ባንክ ማባከን ነው። ዛሬ ባለን ነገር መደሰትና ማመስገን መጀመር አለብን። የተሰጠንን ውድ ጊዜ በቂም፣ በጭቅጭቅ፣ በቅናትና በሐሜት የምናጠፋ ከሆነ፣ የገዛ ሀብታችንን እያቃጠልን መሆኑን ማወቅ ያስፈልጋል። ሕይወት ሰከንዶች ተደምረው የሚሰጡን ውብ ስጦታ ናት። ዛሬ ጠዋት የተሰጠህ 86,400 ሰከንድ ነገ አይመለስምና መልካም ሁን መልካምም አድርግ መልካም ቀን 🙌❤️ SHARE||@astemari_tarik