tgindex
ባህል አደራሽ አንድ ማዕከል

ባህል አደራሽ አንድ ማዕከል

Статистика

የባህልአደራሽ ክ/ከተማ ስራ ሰራተኛ እና ቴክኖሎጂ /ል/ጽ/ቤት መረጃ እና ማስታወቂያዎች እዚህ መከታተል ይችላሉ @bahiladerash

Последний пост
24 июл.
Последнее чтение
14 авг.
Постов за неделю
0
Всего постов
20
Тип
открытый
Язык
ti
В каталоге с
14 авг.
Подписчики
474
мало замеров
Замеров пока мало
Сутки
0
0,00%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
570
20 постов
Вовлечённость
120,3%
к подписчикам
Постов в день
0,0
всего 20
Упоминаний
0
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
227
1/48двое суток
260
1/72трое суток
280

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • Visit Hawassa https://vt.tiktok.com/ZSX7QrA7r/

  • https://vt.tiktok.com/ZSXtnS5oC/

  • 🔊‼️ የስራ ማስታወቂያ‼️🔊 በጥር 06፤2018 ዓም ለተባበሩት አረብ ኤምሬትስ (UAE) የሥራ ማስታወቃያ ማውጣታችን ይታወሳል።  በመሆኑም ከታች በተዘረዘሩት የስራ መደቦች በቂ የሰው ሀይል ባለመገኘቱ  ለሳስተኛ ጊዜ የወጣ የስራ ማስታውቂያ ላይ ከስር በተዘረዘሩት የስራ ዘርፎች መወዳደር የምትፈልጉ ባለሙያዎች በመጀመሪያ lmis.gov.et ብላችሁ በመመዝገብ አቅራቢያችሁ ባለ የአንድ ማዕከል (ወረዳ ወይም ቀበሌ) በመሄድ የባዮሜትሪክስ መረጃ በመስጠት የሰራተኛነት መለያ ቁጥር /Labor ID/ ከያዛችሁ በዚህ https://forms.lmis.gov.et/uae-new/ በመግባት ትክክለኛ መረጃዎችን ሞልተው ማመልከት የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን። 📍 FISHERY STAFFS - የአሳ ማጥመጃ ሰራተኞች- 20 (ብዛት) 📍STEEL FIXER- የብረት በያጅ 60(ብዛት) 📍SHUTTERING CARPENTER- የሸተሪንግ አናፂ 📍CONCRETE PLASTER MASON-የኮንክሪት ፕላስተር ሜሰን 60(ብዛት) 📍CHARGEHAND CIVIL-  የሲቪል ቻርጅሃንድ- 25 (ብዛት) 📍SUPERVISOR CIVIL-የሲቪል ሱፐርቫይዘር- 25 (ብዛት) 📍AC TECHNICIAN- የAC ቴክኒሻን- 100 (ብዛት) 📍 POT WASHERS -እቃ እአጣቢ- 40 (ብዛት) 📍 DIGGER- ቆፋሪ-500(ብዛት) 📍CARPENTERS – አናጺዎች- 100 (ብዛት) 📍Chief – (ምግብ አብሳይ)- 20 (ብዛት) 📍BRICK MASON –(ግንበኛ) 100 (ብዛት) 📍Scaffolders ( የብረት ምጣጫ)

  • 📢 ለሁሉም የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ (UAE) የሥራ ፈቃድ አመልካቾች በሙሉ በተባበሩት አረብ ኤምሬትስ (UAE) የሥራ ፈቃድ ሂደት ላይ የማመልከቻ ሂደታችሁ ሳይጠናቀቅ ለቀረ አመልካቾች፤ ጉዳያችሁን በአግባቡ ለማጣራትና ተገቢውን መፍትሔ ለመስጠት እየሰራን ነው። ስለዚህ ከዚህ በታች በተቀመጠው ማመልከቻ ሊንክ በመግባት የሚጠየቀውን መረጃ በትክክል እንድትሞሉ በአክብሮት እንጠይቃለን። በተጨማሪም፣ ከኤጀንሲው ጋር ያደረጋችሁትን ግንኙነት፣ ሂደቱ የቆየበትን ጊዜ እና የተሰጣችሁን ምላሽ (ካለ) በዝርዝር እንድታስገቡ እንጠይቃለን። የምትሰጡት መረጃ ጉዳያችሁን በፍጥነት ለማጣራትና ተገቢውን እርምጃ ለመውሰድ ያግዘናል። 🔗 የማመልከቻ ሊንክ: https://forms.lmis.gov.et/agancy_form/

  • 3 июл.501710

    ለጣሊያን ሀገር የሥራ ዕድል የምዝገባ ጥሪ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር በገባው የሁለትዮሽ ስምምነት መሰረት በህጋዊ የውጪ ሀገር ሥራ ስምሪት ፕሮግራም በጣሊያን ሀገር በሆቴልና መስተንግዶ (Hospitality) ዘርፍ የሰው ኃይል ይፈለጋል። የዜጎችን መብት፣ ደህንነት እና ጥቅም በማስጠበቅ ህጋዊ በሆነ መንገድ ወደ ጣሊያን ሄደው መስራት የሚፈልጉ አመልካቾች እንዲያመለክቱ እናሳውቃለን። 🏨 የሥራ መደቦች፦ 🔹ጸሐፊ(Commis de Rang / F&B Server) – 19 ቦታዎች 🔹 የፅዳት ሰራተኛ (Room Attendant / Housekeeping) – 20 ቦታዎች 🔹 ረዳት ሼፍ (Commis Chef) – 13 ቦታዎች 🔹 የእቃ አጣቢ (Kitchen Steward / Dishwasher) – 11 ቦታዎች 🔹 የወለል ረዳት (Floor Porter / Houseperson) – 3 ቦታዎች 🔹 የቢሮ አስተናጋጅ (Front Office Agent / Receptionist) – 4 ቦታዎች 🔹 የጥገና ቴክኒሺያን (Maintenance Technician) – 1 ቦታ 🔹 የስፓ ቴራፒስት / የማሳጅ ባለሙያ (Spa Therapist / Masseuse) – 1 ቦታ 📌 የማመልከቻ መስፈርቶች ✅ ከስራው ጋር ተያያዥ የስራ ልምድ ያላቸው ተመራጭ ናቸው። ✅ ለአብዛኛዎቹ የስራ መደቦች የእንግሊዝኛ እና/ወይም የጣሊያንኛ ቋንቋ እውቀት ያስፈልጋል። ✅ ለአንዳንድ የሙያ መደቦች ተዛማጅ የሙያ ማረጋገጫ ወይም የሆቴል እና መስተንግዶ ትምህርት ተመራጭ ነው። 📅 የሥራ ቆይታ አብዛኛዎቹ የስራ መደቦች ለ2026/2027 የክረምት የቱሪዝም ወቅት የሚቀጠሩ ሲሆን፣ አንዳንድ የስራ መደቦች ዓመቱን ሙሉ ወይም በበጋና በክረምት ወቅት የሚሰሩ ናቸው። ✅ ለመመዝገብ 1.Labor ID ካሎት በተሰጠው የማመልከቻ ማስፈንጠሪያ በመጠቀም ያመልክቱ። 2.Labor ID ከሌሎት የሚከተሉትን ሂደቶች ይከተሉ፦ 1. በ lmis.gov.et ይመዝገቡ። በአቅራቢያዎ ባለ የአንድ ማዕከል (ወረዳ ወይም ቀበሌ) በመሄድ የባዮሜትሪክስ መረጃ ይስጡ እና የሰራተኛነት መለያ ቁጥር (Labor ID) ይያዙ። 1. Labor ID ካገኙ በኋላ በተሰጠው የማመልከቻ ማስፈንጠሪያ https://forms.lmis.gov.et/italy-hotel/ ገብተው መረጃዎትን በትክክል ሞልተው ያመልክቱ። ማሳሰቢያ • ምዝገባም ሆነ ስምሪቲ በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የኢትዮጵያ የሥራ ገበያ ብቻ የሚከናወን ሲሆን ሚኒስቴሩ ለየትኛውም አካል ውክልናም ሆነ ፈቃድ አለመስጠቱን እንገልፃለን። • ምንም አይነት ክፍያም የለውም

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • #ጥቆማ #USA የ2027-2028 የ " ሁበርት ኤች. ሃምፍሬይ " ፕሮግራም ክፍት መደረጉን በአዲስ አበባ የአሜሪካ ኤምባሲ አሳውቋል። ምዝገባም ተጀምሯል። የአሜሪካ መንግሥት ሙሉ ውጪውን የሚሸፍነው ይኸው ፕሮግራም በመካከለኛ ደረጃ ላይ የሚገኙ ባለሙያዎችን (እድሜያቸው ከ32 እስከ 45) የሚመለከት ሲሆን አሜሪካ ውስጥ በተለያዩ ዘርፎች ለአንድ የአካዳሚክ አመት ብቃትን ለማሳደግ እና ለልምድ ልውውጥ እድል የሚሰጥ ነው። ይህ ፕሮግራም የዲግሪ ፕሮግራም ሳይሆን፣ ባለሙያዎች ብቃታቸውን የሚያሳድጉበትና ከአሜሪካውያን አቻዎቻቸው ጋር ጠንካራ የሥራ ትስስር የሚፈጥሩበት ልዩ መድረክ ነው። የ2027-2028 መስኮች ምን ምን ናቸው ? ➡️ ኮሙኒኬሽን እና ጋዜጠኝነት (Communications and Journalism) ➡️ ሕግ እና መልካም አስተዳደር (Law and Governance) ➡️ የተፈጥሮ ሀብት ፖሊሲ (Natural Resources Policy) ➡️ የሕዝብ እና ኢኮኖሚ ፖሊሲ (Public and Economic Policy) ➡️ የሕዝብ ጤና ፖሊሲና አስተዳደር (Public Health Policy and Management) ➡️ የቴክኖሎጂ ፖሊሲና አስተዳደር (Technology Policy and Management) መመዘኛዎቹ ምንድናቸው ? አመልካቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል።

  • 1. በመንግሥታዊም ሆነ በግል ተቋማት ውስጥ የሚሰሩ፣ የአመራር ብቃት ያላቸውና ለሕዝብ አገልግሎት ቁርጠኝነታቸውን ያሳዩ ባለሙያዎች። 2. ዕድሜያቸው ከ32 እስከ 45 ዓመት የሆኑ። 3. የዩኒቨርሲቲ መጀመሪያ ዲግሪ (የ4 ዓመት የባችለር ዲግሪ ወይም ተመጣጣኝ) ያላቸው። 4. አመልካቾች የመጀመሪያ ዲግሪ ከተጠናቀቁ በኋላ በተሰማሩበት የሙያ መስክ ቢያንስ የ5 ዓመት የሙሉ ጊዜ ፕሮፌሽናል የሥራ ልምድ ያላቸው፤ እንዲሁም በሙያ ዘርፋቸው ውስጥ ያሉ የፖሊሲ ጉዳዮች ላይ ፍላጎት ያላቸው መሆን ይኖርባቸዋል። 5. ለፕሮግራሙ ቆይታ ጊዜ ከሚሰሩበት ተቋም የሥራ ፈቃድ ማግኘታቸውን የሚያሳይ የድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ መቻል አለባቸው። 6. በሥራ ገበታቸው ላይ የአመራር ወይም የፖሊሲ ኃላፊነት ያላቸው መሆን ይኖርባቸዋል፤ ይህም የዩኒቨርሲቲ መምህራንን እና እንግሊዘኛን እንደ ውጭ ቋንቋ የሚያስተምሩ መምህራንን (የኃላፊነት ቦታ ላይ ያሉትን) ያጠቃልላል። 7. በጽሑፍም ሆነ በንግግር እንግሊዘኛ ቋንቋ አቀላጥፈው መፃፍም መናገርም የሚችሉ እና ከተመረጡ ለTOEFL ፈተና ለመቀመጥ ፈቃደኛ የሆኑ (ተመጣጣኝ ውጤት 72/100/60)። 8. የኢትዮጵያ ዜጋ የሆኑ ወይም በሀገሪቱ የተሰጠ ሕጋዊ ፓስፖርት ያላቸው ቋሚ ነዋሪዎች። 9. ትምህርቱን እንዳጠናቀቁ ያገኙትን ዕውቀትና ክህሎት ሀገርንና ማኅበረሰብን ለመጥቀም ቢያንስ ለሁለት ዓመታት ወደ ሀገር ተመልሶ ለማገልገል ቁርጠኝነት ያላቸው። 10. በአሜሪካ ሀገር ውስጥ በሚገኝ ድኅረ-ምረቃ ለአንድ የትምህርት ዓመት ወይም ከዚያ በላይ የተማሩ ባለሙያዎች ለዚህ ፕሮግራም ብቁ አይደሉም (ማመልከት አይችሉም)። 11. ባለፉት 3 ዓመታት ውስጥ በአሜሪካ መንግሥት በሚደገፉ ማናቸውም ፕሮግራሞች ላይ የተሳተፉ አመልካቾች ማመልከት አይችሉም። ለማመልከት የሚያስፈልጉ ሰነዶች ምን ምንድናቸው ? ምዝገባው ሙሉ በሙሉ በኢንተርኔት (ኦንላይን) ብቻ የሚከናወን ሲሆን የሚከተሉት ሰነዶች ያስፈልጋሉ። 1. CV ፦ የአመልካቹን አጠቃላይ የሥራ ልምድ እና የሙያ ብቃትን በዝርዝር የሚያሳይ ማብራሪያ። 2. የፕሮግራም ዕቅድ ፦ አመልካቾች በዚህ ፕሮግራም ላይ በመሳተፍ ምን ለማሳካት እንደሚያስቡና ወደፊት ምን ለመሥራት እንዳቀዱ የሚያሳይ ዝርዝር መርሐ-ግብር። 3. የተሟሉ የጽሑፍ መልሶች ፦ ለቀረቡ ጥያቄዎች በሙሉ የተሟላ ምላሽ መስጠት፤ በእንግሊዘኛ ቋንቋ የሚዘጋጁት እነዚህ መልሶች (Essay) የቀረቡትን ዋና ዋና ነጥቦች በጥልቀትና በዝርዝር የዳሰሱ መሆን ይኖርባቸዋል። 4. የድጋፍ ደብዳቤ ፦ የሁለት ሰዎች የድጋፍ ደብዳቤ ያስፈልጋል። አንዱ አሁን ከሚሰሩበት ተቋም ኃላፊ/አሰሪ መሆን አለበት። 5. የትምህርት ማስረጃ ፦ ለመጀመሪያ ዲግሪ (Bachelor's) የተወሰዱ ኮርሶችን እና የተገኙ ውጤቶችን የሚያሳይ በእንግሊዘኛ የተዘጋጀ የውጤት መግለጫ መያያዝ አለበት። 👉 የማመልከቻ ጊዜ፦  እስከ ሐምሌ 12 ቀን 2018 ዓ.ም (July 19, 2026) ድረስ ነው። 👉 የማመልከቻ ድረ-ገጽ፦ https://apply.iie.org/huberthhumphrey 👉 ለተጨማሪ መረጃ ፦ et.usembassy.gov/announcements/ PASaddisexchanges@state.gov

  • ካናዳ፤ ምዝገባም ሆነ ስምሪት አልተጀመረም! 🛑 የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ዜጎች ክብራቸውና ደህንነታቸው ተጠብቆ በውጭ ሀገራት በሚፈጠሩ የሥራ ዕድሎች ላይ በህጋዊ መንገድ እንዲሰማሩ ለማስቻል በትኩረት እየሰራ ይገኛል፡፡ በአሁኑ ወቅት ዜጎች በሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ የሥራ ገበያ መረጃ ሥርዓት (lmis.gov.et) ላይ በመመዝገብና ህጋዊ ሂደቶችን በመከተል፣ ኢትዮጵያ የሁለትዮሽ ስምምነት ወደተፈራረመችባቸው የሚከተሉት ሀገራት በህጋዊ መንገድ በመሰማራት ላይ ይገኛሉ፦ 👉ሳውዲ አረቢያ 👉የተባበሩት አረብ ኢምሬትስ 👉ጆርዳን 👉ኳታር 👉ሊባኖስ 📍ወደ ካናዳ የሚደረግ የሥራ ስምሪት አለ? የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር መቀመጫውን ካናዳ ካደረገው "ፊውቸር ፊት ኢንተርናሽናል" (FUTURE FIT INTERNATIONAL INC.) ጋር ስምምነት የፈጸመው በዋነኛነት ኢትዮጵያውያን ወጣቶች በዓለም አቀፍ የሥራ ገበያ ብቁና ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ለማስቻል ነው። ስምምነቱ በሚከተሉት ነጥቦች ላይ ብቻ ያተኩራል፦ • ከካናዳ ኮሌጆች ጋር በመተባበር ተማሪዎችን በዓለም አቀፍ የሥራ ገበያ በሚፈለጉ ክህሎቶች ማሰልጠን፤ • ብቁ የሆኑ ተማሪዎች በካናዳ በሚገኙ የትምህርትና ስልጠና ተቋማት የነፃ ትምህርት ዕድል እንዲያገኙ ማመቻቸት። ⚠️ ከፍተኛ ጥንቃቄ ይደረግ! ከዚህ ስምምነት ውጪ፦ ✅"ሚኒስቴሩ ወደ ካናዳ ህጋዊ የሥራ ስምሪት ጀምሯል" በማለት የተሳሳተ መረጃ ከሚሰጡ፤ ✅"ወደ ካናዳ እንልክዎታለን" በማለት ከፍተኛ ገንዘብ ከሚጠይቁ፤ ✅"ከሚኒስቴሩ ህጋዊ ውክልና ተሰጥቶናል" ከሚሉ አጭበርባሪዎች ራሳችሁን ጠብቁ! 📍ምን ማወቅ ይኖርብዎታል? ✍️ከፊውቸር ፊት ኢንተርናሽናል ጋር የተደረገው ስምምነት ወደ ተግባር ሲገባ፣ ዝርዝር መረጃው በሚኒስቴሩ ይፋዊ የማህበራዊ ትስስር ገጾች እና በብሔራዊ ሚዲያዎች ብቻ ይፋ ይደረጋል። ✍️ለዚህ ፕሮግራም ተጠቃሚ ለመሆን ምንም ዓይነት ክፍያ መፈጸም አይጠበቅብዎትም! ክፍያ የሚጠይቁ አካላት ሁሉ አጭበርባሪዎች መሆናቸውን ይወቁ። ግንቦት 26/2018 ዓ.ም፤ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ለወቅታዊ ትኩስ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር

  • የ"ከወንጀል ነጻ" ማረጋገጫ ሰርተፊኬት አገልግሎትን በዲጂታል አማራጭ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር አገልግሎት አሰጣጡን በማዘመን ይበልጥ ቀልጣፋ፣ ተደራሽ እና ግልጽነት የተላበሰ ለማድረግ ሰፊ ርብርብ እያደረገ ይገኛል። ይህን ተግባር ይበልጥ በማጠናከር፣ የ"ከወንጀል ነጻ" ማረጋገጫ ሰርተፊኬት አሰጣጥ ስርዓቱን ከኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ጋር በመተባበር በኢትዮጵያ የሥራ ገበያ መረጃ ስርዓት (lmis.gov.et) ውስጥ እንዲካተት ማድረግ ተችሏል። በዚህም በውጭ ሀገር የሥራ ስምሪቱ ተጠቃሚ የሚሆኑ ዜጎች አገልግሎቱን ባሉበት ሆነው እንዲያገኙ ያስችላቸዋል። ቀደም ሲል አመልካቾች ሰርተፊኬቱን ለማግኘት አዲስ አበባ በሚገኘው የፌዴራል ፖሊስ ፎረንሲክ ማዕከል በአካል መገኘት ግዴታ የነበረባቸው ሲሆን፤ በአዲሱ የዲጂታል ስርዓት አማካኝነት ግን ዜጎች ሂደቱን ባሉበት ሆነው በቀላሉ ማጠናቀቅ ይችላሉ። በዚህ መሠረት ማንኛውም የ"ከወንጀል ነጻ" ማረጋገጫ የሚፈልግ የውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት አመልካች፦ ✅ወደ አዲስ አበባ ፌዴራል ፖሊስ ፎረንሲክ ማዕከል በአካል መገኘት አይጠበቅበትም ✅በኢትዮጵያ የሥራ ገበያ መረጃ ስርዓት (lmis.gov.et) ላይ በመመዝገብ፣ በአቅራቢያቸው በሚገኙ የአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ ጣቢያዎች አስፈላጊውን የባዮሜትሪክስ መረጃ መስጠት ይኖርባቸዋል፤ ✅የ"ከወንጀል ነጻ" ማረጋገጫ ሰርተፊኬቱን የሥራ ስምሪት ሂደቱን በሚያስፈጽመው ሕጋዊ ኤጀንሲ አማካኝነት በቀላሉ ማግኘት ይቻላል፣ ይህ አገልግሎት በራስ ጥረት የሚገኙ የሥራ ዕድሎችን ለጊዜው አያካትትም፤ ይህ የተቀናጀ አሰራር በዜጎች ላይ ይደርስ የነበረውን አላስፈላጊ የጊዜ፣ የጉዞ ወጪ እና የአስተዳደራዊ ጫናን በከፍተኛ ሁኔታ የሚቀንስ ሲሆን፤ በመንግስት በተቋማት መካከል ያለውን ቅንጅት በእጅጉ የሚያሳድግ ነው። የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የዲጂታል አገልግሎት ስርዓቶቹን በማስፋፋት የዜጎችን ተጠቃሚነት ለማላቅ ከሁሉም አስፈጻሚ አካላት ጋር በመቀናጀት የጀመረውን ሥራ አጠናክሮ ይቀጥላል። የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር

  • ወደ ፌደራል ፖሊስ መሄደ ቀረ‼️ ከዛሬ ግንቦት 6 ቀን 2018 ዓ/ም ጀምሮ ወደ መካከለኛው ምሥራቅ ለሥራ ለመሰማራት የወንጀል ነጻ ሠርቲፊኬት የሚፈልጉ ተገልጋዮች በአካል አዲስ አበባ በሚገኘው ፎሬንሲክ ወንጃል ምርመራ አሻራ ምርመራ ዋና ክፈል መምጣት እንደማያስፈልጋቸው የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ አሳወቀ። ወደ መካከለኛው ምሥራቅ ለሥራ ለመሰማራት የወንጀል ነጻ ሠርቲፊኬት የሚፈልጉ በሥራ እና ክህሎት ሚኒስቴር በተዘጋጁ ማዕከላት አማካኝነት በየአካባቢያቸው በሚገኙና በሚልኳሸው ኤጀንሲዎች በኩል አገልግሎቱን ማግኘት እንደሚችሉ ገልጿል። ‎

  • https://www.facebook.com/share/r/1HhQ9NxMvM/ #ሰውን_ለመርዳት_ሰው_ብቻ_መሆን_በቂ_ነው! እህታችን ወ/ሪት ለምለም ኤልያስ ትባላለች የሀዋሳ ከተማ ኑዋር ስትሆን ለበርካታ አመታት በሀዋሳ አንድነት ቀበሌ ስራ-አስኪያጅ በመሆን በባህል አደራሽ ክ/ከተማ ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት ባለሙያ ሆና እያገለገለች ባለችበት ጊዜ ባጋጠማት ሁለቱም ኩላሊቱዋ በከባድ ሁኔታ ስለተጎዳ ከቀን 16/01/2018 ጀምሮ በሳምንት 2 ቀን የኩላሊት እጥበት ነበር አሁን ግን የኩላሊት ንቅለ ተከላ ህክምና ስለተወሰነ ወጭው ከፍተኛ በመሆኑ የህኪምና ወጭ ለመሽፈን ስላቃተን ደጋግ ወገኖቻችን እህታችንን ልጃችንን አድኑን እያሉ ቤተሰቦቹዋ በፈጣር ስም እየተማፀኑ ይገኛሉ ሰውን ለመርዳት ሰው ብቻ መሆን በቅ ነውና በተቻለን አቅም እህታችንን ባለን አቅም በፀሎታችሁ በተቻላችሁ መጠን በገንዘባችሁ ያልቻላችሁ መርዳት ለምችሉ ወገኖች እንድደርስ Share በማድረግ ተባበሩን አካውንት ቁጥር ወ/ሪት ለምለም ኤልያስ 1000182020277

  • 👷🏾‍♂️ወደ ውጭ አገር የምሥራት ህልም አሎት?👷🏾‍♂️ ✈️✈️🌏🌎 በተለያዩ ተፈላጊ በሆኑ የሙያ መስኮች ላይ እየተጠየቀ ባለው የሥራ እደሎች ላይ E-LMIS  በኩል ተጠቃሚ ይሁን። ከታች በተዘረዘሩት በርካታ የስራ መስኮች ላይ በማመልከት ዛሬዎኑ የስራውን ዓለም በመቀላቀል ዕውቅዎቶንና እና ልምዶን ወደ ገንዘብ ይቀይሩት:- 🔹 የግንባታ ሰራተኛ/Carpenter / Construction Worker 🔹 የብረታ ብረት  ባለሙያ/ Steel Fixer 🔹 ቴክኒሻን /  Technician 🔹 ሲቪል ሱፐርቫይዘር / Civil Supervisor 🔹 ምግብ አብሳይ / Chef 🔹 የግንባታ ረዳት ሰራተኛ / Construction Helper 🔹 አጠቃላይ ግንበኛ / General Mason 🔹 የጽዳት ሰራተኛ / Cleaner 🔹 የኤሌክትሪክ ባለሙያ  /Electrician 🔹 የቧንቧ ሰራተኛ /Plumber 🏫 ስለሆነም ይሆንን እድል ለትጠቀሙ የምትፈልጉ በመጀመሪያ lmis.gov.et ብላችሁ በመመዝገብ አቅራቢያችሁ ባለ የአገልግሎት መስጫ ማዕከል (ወረዳ ወይም ቀበሌ) በመሄድ የባዮሜትሪክስ መረጃ በመስጠት የሰራተኛነት መለያ ቁጥር /Labor ID/ ከያዛችሁ በዚህ https://forms.lmis.gov.et/uae-new-2/  በመግባት ትክክለኛ መረጃዎችን ሞልተው ማመልከት የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን።

  • https://vt.tiktok.com/ZS9UAdcnk/

  • ምዝገባ ብቻውን በቂ አይደለም ! የባዮሜትሪክ ምዝገባዎን አጠናቅቀው የሰራተኛ መለያ(Labor ID) ማግኘትዎ የመጀመሪያው እና ትልቁ እርምጃ ነው። ነገር ግን ስራ ለማግኝት በእነዚህ አማራጮች መጠቀም ይኖርብዎታል ፦ 1. lmis.gov.et ድረ-ገጽ ላይ በመግባት National Job portal ላይ በየቀኑ የሚወጡ በመቶዎች የሚቆጠሩ አዳዲስ ስራዎችን በመመልከት ለእርስዎ ተስማሚ የሆነው ስራ ላይ ያመልክቱ። 2.ማህበራዊ ገጾቻችንን በመጎብኘት እንዲሁም የምንለጠፋቸውን የስራ ዕድሎች በንቃት በመከታተል ከማስታወቂያው ጋር ተያይዞ በተቀመጠው ማስፈንጠርያ አማካኝነት ማመልከቻዎን ያስገቡ። 3.SMS መልዕክቶችን ይከታተሉ በስልክዎ ከ E-LMIS ወይም ከ MoLS (ስራና ክህሎት ሚኒስቴር) የሚላኩ መልዕክቶችን በየጊዜው ያረጋግጡ። የቃለ መጠይቅ ጥሪዎች እና ጠቃሚ መረጃዎች የሚደርስዎት በዚህ መንገድ ነው። https://lmis.gov.et/

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • በክህሎት ልማትና በሥራ ስምሪት በትብብር መስራት የሚያስችል ስምምነት የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ከፊውቸር ፊት ኢንተርናሽናል ጋር ዜጎችን አሰልጥኖ በማብቃት ወደ ካናዳ መላክ የሚያስችል ስምምነት ተፈራረመ፡፡ በፊርማ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወይዘሮ ሙፈሪሃት ካሚል፣ በኢትዮጵያ የካናዳ አምባሳደር ክቡር ኒኮላስ ሪቻርድሰን እና የፊቸር ፊት ኢንተርናሽናል ማኔጂንግ ዳይሬክተር አቶ አብይ ራይሞንድ ተገኝተዋል። ክብርት ወይዘሮ ሙፈሪሃት ካሚል በወቅቱ እንደገለጹት፤ ይህ ስምምነት ወጣቶች በክህሎት በቅተው፣ በስነ-ምግባር ታንጸው ውጤታማ የሚያደርጋቸውን የሥራ ስምሪት ማገኝት የሚያስችላቸው ነው፡፡ ሚኒስቴሩ ወደ ካናዳ የሥራ ስምሪት ለመስጠት ለመጀመሪያ ግዜ በህጋዊ መንግድ የተፈራረመው ከዚህ ድርጅት ጋር መሆኑን ገልጸው ምዝገባም ሆነ ስምሪት ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ የሚደረገው በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር በለማው የኢትዮጵያ የሥራ ገበያ መረጃ ስርዓት(E-Lmis) አማካኝነት ብቻ ነው ብለዋል፡፡ ምንም አይነት ህጋዊ ፍቃድ ሳይኖራቸው ወደ ካናዳ እንልካለን በሚል ዜጎችን በሚያጭበረበሩ አካላት መኖራቸውን ጠቁመው ህብረተሰቡ ከእነዚህ ህገወጦች እራሱን እንዲጠብቅ አሳስበዋል፡፡ የካናዳ አምባሳደር ክቡር ኒኮላስ ሪቻርድሰን በበኩላቸው፤ ስምምነቱ ካናዳ ከአፍሪካ አገራት ጋር የጀመረችው አዲስ ስትራቴጂ አካል መሆኑን ጠቅሰው፣ በካናዳ የሚኖሩ ትውልደ ኢትዮጵያውያን (ዳያስፖራ) ለሁለቱ አገራት ግንኙነት መጠከር ያላቸውን ሚና አድንቀዋል። የፊቸር ፊት ኢንተርናሽናል ማኔጂንግ ዳይሬክተር አቶ አብይ ራይሞንድ፤ ዓላማችን ዜጎችን ካናዳ መላክ ብቻ አይደለም ፤ ዜጎችን በዓለም አቀፍ ደረጃ ተፈላጊና ብቁ እንዲሆኑ ማድረግ ዋና ዓላማው ነው ብለዋል፡፡ ስምምነቱ የዜጎችን መብትና ደህንነት ባከበረ መልኩ ሕጋዊ የሆነ የሰው ኃይል ስምሪት ለመዘርጋት የሚያስችል መሆንንም ጨምረው ገልጸዋል። በቀጣይ የሚኖሩ የሥልጠና ማስታወቂያዎች በሚኒስቴሩ ትክክለኛ ማህበራዊ ሚዲያዎችን፣ በድርጅቱ ህጋዊ ዌብሳይት እና በተመረጡ ሚዲያዎች እንደሚገለጹ ጠቁመዋል፡፡

  • መረጃ የሰጣችሁኝ ልጆች መረጃችሁን ስለወሰድኩ ሌላ ክፍለ ከተማ እንዳትመዘገቡ ድግግሞሽ ይሆናል