ቅኔ-ዘረፋ !
Статистикаየኑኃሚን ወግ! ከእንጀራው መሶብ ፥ እንጀራው ቢታጣ ሞዓብ ብትልከኝ ፥ ነገር ልታመጣ ብት'ነሳኝም ልጅ ፥ ብታሳጣኝም ባል ማራም ይወደዳል ፥ ለወደድከው ሲባል፤ https://vm.tiktok.com/ZMHwa3UQCFxq8-9YGn1/
- Последний пост
- 14 авг.
- Последнее чтение
- 15 авг.
- Постов за неделю
- 3
- Всего постов
- 24
- Тип
- открытый
- Язык
- ti
- Категория
- В каталоге с
- 14 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 169
- 1/48двое суток
- 193
- 1/72трое суток
- 208
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
https://vm.tiktok.com/ZSVR1K2se/ This post is shared via TikTok Lite. Download TikTok Lite to enjoy more posts: https://www.tiktok.com/tiktoklite ይኸው ለሙከራ ያህል..🙏😁 ምስልን ከድምጽ ጋር ... ምንድነው ምትሉት ..👇👇 #Copy link #Share አድርጉ ከተመቻችሁ ኮምቱ...👍😁
ውሃም ሲወስድ እያሳሳቀ ነው! 👇👇 https://t.me/balamberas87 @balambaras8
ጸሎትና የወዳጅነት ንግግር! አንዳንዴ ጌታን ስለወደድነው ነገር የጸለይነው ጸሎት እና የወዳጅ ማማከር ሙላበትና ይሁን ይመስላል። እሱ እምነነታችንን በነገሩ ሲሻ እኛ የልቡን ባንደርስበት ያለንን እምነት ይዘንና ትንፋሻችንን ሰብስበን ይህችን ነገር እባክህ። እርሱ በምህረቱ ምሮ፣ በጸጋው ችሎ፣ በፍቅሩ ደግፎ ያሳልጠዋል። በዚህ ሁሉ ደርሰን ብንረሳው እንጂ ደርሶ የታደገን ስንት አቻምናና አምና ፣ ስንትስ ትናንትና ቅድም አለፈ። ጌታ ምህረቱን አበዳሪ ቢሆን ሁላችን የህይወት ባለ እዳዎች ነን! የእርሱ ብልጥግና በማይመለስ በጸጋው ቸሮታ የተሞላ ነው። ብዙ ኃጢአቶቻችን በሸንጎ ፊት ምዕተ አመታት ቢነበቡ የጌታ የሰከንድ ቃል ሁሉን ይከድነዋል። ምሬዋለሁ! ሰይጣን ስለትናንት ተግባራችን የክስ ወረቀት አለው። እግዚአብሔር ግን የምህረት ትናንት እንጂ የበደል ትናንት የለውም። ዘወር ሲል የዛሬ ሁለት ሺ አመት የኢየሱስን የመሰቀል ገድል እንጂ የትናንትን በደል የማየት መሻት የለውም። እርሱ ይቅር ለተባለ ድካም ሸንጎ አይቀመጥም፤ በቀደምም... አሁንም እያለ ስንፍናን አይቆጥርም። እርሱ ሲተው ትቶ፤ ሲምር ረስቶ እንጂ መዝገብ ይዞና ደልዞ አይደለም። ይሁን እንጂ ይህ ሁሉ... ለኃጢአት መሸፈኛን አይሰጠንም። አንሸወድ ጌታ አይቶ በምህረት እንጂ ባላየ አያልፍም! ገመናችንን ጋርዶ እንጂ ተጋርዶበት፤ ከቶ እንጂ ተደብቆበት አይደለም። ማነው ያለው? ቅባቱ ያወዛን፤ ምህረቱ ነው እንጂ ሞገስ የሆነን። አንዳች ሊገዛ ከወዳጁ ጋር ገበያ እንደወጣ ሰው ነን። ፍላጎትና ገንዘቡ እንደማይጣጣሙ ነገር ግን ምን ቢመጣ በወዳጁ ላይ ያለው መተማመን እንደሚበረታበት። "ወደድኩት፤ ሙላበትና እንግዛው" ነገሩ እንዲያው ነው። በኛ ልመና ጌታ ስንቱን እየሞላ ቻለን። ዘንድሮንም ምህረት ሞልቶበት ቀጣዩን ያሳየን! 🙏 ለተባረኩት!
ሰላም እንዴት ናችሁ? 🙏 ዛሬ አመስግን አመስግን ስላለኝ ነው የምር..🙏😁 እና እዚህ በአደባባይ የምለጥፋቸውን ግጥሞቼን በማየትና react በማድርግ እንዲሁም Inbox እየመጣችሁ ለምትሰጡኝ አስተያየት እና ለምታሳዩኝ ምላሽ የላቀ ምስጋና አለኝ !🙏 👉ከወገቤ ቅንፍ ብዬ እጅ ለእናንተ እነሳለሁ። [ ከልቤ ነው የእውነት] 📍ምክንያቱም #ከእግዚአብሔር በታች እዚህ ያላችሁ ሁላችሁ ለመጻፍ እንድችል አቅም ስለሆናችሁኝ ነው። 🙏 በድጋሚ ምስጋና አለኝ ለሁላችሁ 🙏 ጌታ ከረዳኝ ደግሞ ሁሌ React ለሚያደርግ ሰው የሆነ ነገር ይታሰብለታል...🙏😁 🤝 👇👇 https://t.me/balamberas87 @balambaras8
"ቆይኝ መጣኹ አንዴ " ብሎ መሄድ ምኑ ነው ትቷት የሄደ የሚያስመስለው ? : : አስቀምጧት እንጂ ፥ ጥሏት የሄደ የመሰላት ይህች ሙሽራስ ፥ እኔ እንጃላት! [ መብራት መያ'ዙ ብቻ ሳይሆን ማሰሮው ዘይት መኖሩን ልብ ይሏል ] ማቴዎስ 25 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ¹ በዚያን ጊዜ መንግሥተ ሰማያት #መብራታቸውን ይዘው ሙሽራውን ሊቀበሉ የወጡ አሥር #ቆነጃጅትን ትመስላለች። ² ከእነርሱም #አምስቱ ሰነፎች አምስቱም ልባሞች ነበሩ። ³ ሰነፎቹ መብራታቸውን ይዘው ከእነርሱ ጋር #ዘይት አልያዙምና፤ ⁴ ልባሞቹ ግን ከመብራታቸው ጋር #በማሰሮአቸው ዘይት ያዙ። ⁵ ሙሽራውም #በዘገየ ጊዜ ሁሉ እንቅልፍ እንቅልፍ አላቸውና ተኙ።
без подписи
ቅኔ-ዘረፋ ! pinned a photo
[ ሞትና - ትንሳኤ ] በኢያሪኮ - በሞቴ ሀገር ማነኝ ብዬ - ምን ልናገር ሁለቴ እርማም - አንዷ ረዓብ ለሰው አልጥም - እንኳን ለአብ፤ ፡ ነፍሴን ስቼ - ስገለሙት ኖርኩ አልልም - ብሼ ከሙት እንደቀሩት - ምን ብ'ገደል ቅጥሩ ሙሉ - የእግዚያር አይደል! ፡ የዳንኩባት - ያች ፈትል 'ቃል አለባት - ማሯት' ባትል መኖር ሰጥቶኝ - ባላደልኩት እል አልነበር - ''ሞቼ ካስኩት'' ፡ ግን ሆነና...! ግብሬ የኃጥዕ - ቤቴ ቅጥር ሊያዉም ከዳር - ኖሬ ባጥር አንዳች ችዬ - ለማልፈጥር እምነት ገባኝ - ልድን ሳልጥር! ፡ መግደል ሲችል - ማዳን የ'ርሱ ለሚጠይቅ - እምነት መልሱ ነፍሴም ዳነች - ተገን-ጥላ ሞት አለፋት - እንደ ጥላ ሊያዉም በክር - ተንጠላጥላ። ኢያሱ 6 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ²¹ በከተማይቱም የነበሩትን ሁሉ፥ ወንዱንና ሴቱን፥ ሕፃኑንና ሽማግሌውን፥ በሬውንም በጉንም አህያውንም፥ በሰይፍ ስለት #ፈጽመው አጠፉ። ²² ኢያሱም ምድሪቱን የሰለሉ ሁለቱን ሰዎች፦ ወደ #ጋለሞታይቱ ቤት ግቡ፥ ከዚያም ሴቲቱንና ያላትን ሁሉ እንደ #ማላችሁላት አውጡ አላቸው። … ²⁵ ኢያሪኮን ሊሰልሉ ኢያሱ የሰደዳቸውንም መልክተኞች ስለ ሸሸገች ጋለሞታይቱን #ረዓብን፥ የአባትዋንም ቤተ ሰብ፥ ያላትንም ሁሉ ኢያሱ #አዳናቸው፤ እርስዋም በእስራኤል መካከል እስከ ዛሬ ድረስ ተቀምጣለች። 👇👇 https://t.me/balamberas87 @balambaras8
ቅኔ-ዘረፋ ! pinned a photo
[ ኑዛዜ ፍቅር ] ለፍቅር ሲል ፥ አስጎንብሶት ለማዳን ሲል ፥ አሳንሶት አንበሳ እጁን ፥ አስሮ በድር 'እንካችሁ' ሲል ፥ ሰማይ ለምድር ፤ በሸንጎ ፊት ፥ የቃል ጌታ ጊዜ ቢሰጥ ፥ ለዝምታ ሽንፈት ይምሰል ፥ ግን ለበጎም ማሸነፍ ነው ፥ አፍ መለጎም[ም]፤ መቼት እርሱ ፥ የማይጠፋው የአጀብ ልቡ ፥ እንዳይከፋው ለምላሹ ፥ ማይተነፍስ ሊታደጋት ፥ አንዲትን ነፍስ ፤ የሚድን ግን ፥ ቢል 'ስቀለው ከፍ አድርገህ ፥ አንጠልጥለው ' የሚያድነው ... 'ማራቸው' ሲል ፥ ያው አንዱ ቃል ሰዉን ከሞት ፥ ይናጠቃል፤ ኢሳይያስ 53 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ⁷ #ተጨነቀ ተሣቀየም #አፉንም አልከፈተም፤ ለመታረድ እንደሚነዳ ጠቦት፥ በሸላቶቹም ፊት #ዝም እንደሚል በግ፥ እንዲሁ አፉን አልከፈተም። ⁸ በማስጨነቅና በፍርድ ተወሰደ፤ ስለ ሕዝቤ ኃጢአት ተመትቶ #ከሕያዋን ምድር እንደ ተወገደ ከትውልዱ ማን አስተዋለ? #👇join us now! https://t.me/balamberas87 @balambaras8
ባላም'ባራስ !: https://youtu.be/ivN5gQsZ6IQ?si=mAJSatipqxvsqM63 እስኪ ይህን መዝሙር ስሙትማ የሰማችሁም ድገሙት 🙏 የሳምንቴ መዝሙር ነው!
እያኮ [፪] ይዛ እንዳትዘልቃቸው ደግሞ የሞት ቀን ትውስታዎቿ ሆኑባት። እየተወቻቸው ሲያሳምሙዋት፥ እየዛተችባቸው ሳትቆርጣቸው እስከዛሬ ዘለቀች። ትናንትን ገደልኩት ትላለች ፤ነገር ግን ትናንት ከዛሬዋ ተልቆ ዛሬም በትውስታ ፈረስ ይንጣታል፣ በቁጭት መጋዝ እየገዘገዘ፣ ከሞት ተዳፋት አንደርድሮ፣ ብርሃንዋን እያከሰመ፣ ወደ ጽልመቱ ይሞጅራታል። እያኮ ዘለግ ያለ ቁመትና መሃከለኛ የሚባል ተክለ ሰውነት ያላት፣ ጠየም የምትል፣ ቆንጅዬ ከሚባሉት ኮረዳዎች መሃከል የምትመደብ፣ በሀያ ሁለት የእድሜ ክልል ያለች ጉብል ናት። ጠቆር ብለው ረዘም ያሉቱ ጸጉሮቿ ሲዘናፈሉ አትኩሮትን ይስባሉ። ብዙውን ጊዜ ፈትታ ቁልቁል ወደ ጀርባዋ ትለቀዋለች። ለዚህም ነው መሰል ይህንን ያየ ባለ ቅኔ እንዲህ ሲል የተቀኘላት። “አእላፍ ባለ ሟል ስላንቺ ያዜማል፤ ስላንቺ ይቀኛል ውበትሽን አይቶ ያልተደናቀፈ ውግዝነው ይሰኛል። እኔ አላዜምም ለፍቅርሽ በእውነቱ መረዋ አይደለም የለኝም ድምጸቱ እያልኩ አዜማለሁ እያልኩ እቀኛለሁ ላለማዜም ምዬም ሳዚም እገኛለሁ።” ዘወር ብላ ከራስጌዋ ያለውን የሰዓት ጠቋሚ ተመለከተች ገና ከማለዳው አስራ ሁለት ሰዓት ስለመሆኑ ጠቆማት። እርሷም ብትሆን የብርሃን ወጋገን ከጎን ካለው መስኮት ወደ ክፍልዋ ሾልኮ በማየቷ፥ ከተጋደመችበት ተነስታ ተቀመጠች እንጂ እንደ እውነታው ከእንቅልፍ አልነቃችም። ለነገሩ ወዳጅዋ ኤሮሜ የራስዋን ቤት ገዝታ ከወጣች ጀምሮ፥ ላለፉት ሁለት ዓመታት በወሬ ጠምዶ በድካም ብዛት ለእንቅልፍ የሚዳርጋትን ወዳጅ ማፍራት ተስኗታል። ኤሮሜ በእያኮ ባህርይ፥ ቅንጣት ታክል የቅይማት ነጥብ ሳታነሳ፥ ነገሮችን ልትረዳው በማይሳናት ምሳሌዎች ልታዋያት የምትችል ድንቅ ሰው ናት። ስለ ምሳሌ ከተነሳም በሰንበት ትምህርት ቤት በልጅነት የተማረቻቸውን ታሪክና ገጠመኞች አንድ ሁለት እያለች ስታወጋት ትወድላታለች። ከዚያ ሁሉ ታሪኮች ውስጥ ምንም ያህል ብትወደው ንዴቷን የሚያጭረው የኢዮብ ታሪክ መሆኑን ደጋግማ ነግራታለች። እያኮ ስለ እምነትና ስለሀይማኖት ያላት አመለካከት ፈጽሞ የተቃረነ ቢሆንም ከኤሮሜ ያደመጠቻቸው ነገሮች ሁሉ ደስታና ንዴትን በማፈራረቅ ጨምረውላታል። ይለጥቃል ።🙏 #እያኮ ዘውግ :- ልብወለድ ( ክብርዓብ ደሳለኝ) ይቀጥል የምትሉ react አድርጉ እስኪ 👍
[16] ሁላችንም ገጣሚ ነን እውነት ለመናገር ሁላችንም ደራሲ ነን ሁላችንም ገጣሚ ነን ለመጻፍ ግን እንደክማለን ! ! የሕይወትን መዝገብ እየው ተመልከተው ሁሉም በጥቅስ ነው ፥ ፍርሃት 'ሚመክተው እየው ተመልከተው ያለስገጠመችው ያለስለቀሰችው ያለስደረሰችው ማነው ኀዘን ልካ ፥ ጥበብ ያልጠራችው? (ሄኖክ በቀለ 👉 እንደጻፈው) ይናፍቀኛል!
👉👉 በዚህ ክረም ...አስባችሁታል እሳት ዳር ተቀምጣችሁ የበቆሎ እሸት 🌽 ተፈልቅቆ እየተጠበሰ ሲሰጣችሁ እና ስትበሉ ያለው ድባብ ....🙆🙆🙈 👉👉 ምን አለፋችሁ፥ ይኸው ነፍስን የሚያሞቅ ፥ ለምልሰት የሚሆን የስልጠና እሸት ቤተክርስቲያን አዛጅታላችኋለች፥🙏 ...ነፍሱን እና መንፈሱን #ብርድ #ብርድ ያለው ብቻ #ይምጣና ይካፈል ፤ ለነፍሱ የሚሆን ማሞቂያ ያገኛል ብዬ አስባለሁ ። @TESHUVA 👈 ( ምልሰት ) @HKC YOUTH MINISTRY @Register now https://t.me/hkcyouthministry
እያኮ ጠየም ብሎ ረዘም ያለውን የፊቷን ገጽ፣ ሸካራ በሆኑ የእጆቿ መዳፎች፣ ከግንባሯ አንስታ እስከ ጉንጯ ድረስ መላልሳ እየዳበሰች ከእንቅልፏ ተነስታ የአልጋዋን ራስጌ ተደግፋ ተቀመጠች ። መዳፎቿ ያለፈችባቸውን የሕይወት ውጣውረዶች የሚተርኩ የዘመናት ሰሌዳ መስለው ይታያሉ ። ይህንን ስለምታውቅ እርሷም ብትሆን እጆቿን ገልጣ ማሳየትን የሕይወት ታሪኳን ከጅምር እስከ አሁን እንደመዘክዘክ ትጸየፈዋለች ። ለዚህም ኖሯል ተመልካች ጠያቂ መሆኑ ስለማይቀር መዳፏን ለማሳየትን የማትመርጠው። ይሁን እንጂ በመዳፎቿ ላይ ያሉት ጥልፍልፍ መስመሮች ሰነፍ ብዕረኛ የነቀሳቸው ይመስላሉ ። እነዚያ መስመሮች የሕይወት ሳይሆኑ የሞት ቁልቁለቶችን ፥ የደስታ ሳይሆን የኃዘን ድባቦችን ያስታውሷታል። ቆርጣ እንዳትጥላቸው እጆቿ ናቸው ፤ ይዛ እንዳትዘልቃቸው ደግሞ የሞት ቀን ትውስታወቿ ሆኑባት ... ፡ ፡ ይለጥቃል ።🙏 #እያኮ ዘውግ :- ልብወለድ ( ክብርዓብ ደሳለኝ) ይቀጥል የምትሉ react አድርጉ እስኪ 👍
[ ጸሎትና ግጥም ! ] እንደ አበው ተረት ! እባብ ምን ቢቀጥን ፥ ራሱ አይረገጥም መነደፍ ነው ትርፉ ፥ ከእግዜር ማፈንገጥም ካምላክ ጋር ግብግብ ፥ እንደሰውብንገጥም አፍርሶን ይሰራል ፥ ከ'ጁ ልክ አንበልጥም! ፡ ሳቅ ይፈጥራል ብለን - በሚኮረኩረን በልፊያችን ብዛት - ማልቀስ እንዳይመክረን! ባስቆጣነው ቁጥር - ጅራፉን ቢያቀምሰን የሰራናትን ሸር' - አንክስም አልቅሰን ! ፡ አለም ግሳንግሷ - ሞልቶ ላያጠግበን ያስገባን ሰፊ በር - ስንወጣ ሚጠበን! ላጠፋነው ጥፋት - ከነማጣቀሻው ላምላክ ልቡ ቁስል - ምን ይሆን ማርከሻው ? ፡ ቁጣው እንዲመለስ ፥ ንዳዱ እንዳይቀስፈን ጸሎትን በግጥም ፥ ብንልክለት ጽፈን ለቋጠርናት ስንኝ ፥ ከእምባችን ብንቀልም የኃጢአታችን ግዝፈት ፥ በማንባት አይቀል'ም ! ፡ ለሳትንበት ሁሉ ፥ ብናወጣለት ስም ያለፈን ማስታወስ ፥ ጥፋት ባይቀንስም ! ዛሬን ምሮ ቢያልፈን ፥ ለነገ ካልሰጋን እንዳይርቀን ፍሩ ፥ እስከማይጠጋን! ፡ ድሮም ቢሆን እርሱ.. በውትወታ አይደለም ፥ በቃላችን ግፊት ቀድሞ ነው የማረን ፥ ከጸሎታችን ፊት! እንደዉም እንደዉም ! መጸለይ ሲከብደን ፥ አሳ'በን ብንገጥም ለፈጣሪ አይጥምም - የፍጡራን ግጥም ። መዝሙር 63 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ² ኃይልህንና ክብርህን አይ ዘንድ እንዲሁ በመቅደስ ውስጥ ተመለከትሁህ። ³ #ምሕረትህ ከሕይወት ይሻላልና ከንፈሮቼ ያመሰግኑሃል። ግጥም ወዳጅ ወዳጃችሁን ጋብዙ👇👇 https://t.me/balamberas87 @balambaras8
[ ጸሎቴን በግጥም ] 👈ርዕስ ነው : : : #ግጥሙን ጠብቁ..🙏
без подписи
🎙️[ የነፍስ ዜማና ግጥም ] "ይልቅ ይልቅ ይቅርብኝ ልመለስ ወደ ልብህ ወደ ሃሳብህ ልድረስ ልሸከመው የመስቀልህን ፍቅር ተመልሼ ወደ ኋላ እንዳልቀር #አድስልኝ የቀድሞዉን ዘመን #ናፍቆት ሆኖ #ምኞት ሆኖ እንዳይቀር ሰምቼ አንተን እዳፈራበት #ለም አድርገው #የልቤን መሬት።''
(ሰነፍ ገበሬ በሰኔ ይሞታል ) እንዲሉ አበው ! ፡ ፡ ምኞት ልቤ ፥ ያሰነፈኝ ስንኩል አይኔ ፥ ያከነፈኝ ከድሉ ሰልፍ ፥ ተጣለፈኝ እኔን ከእኔው ፥ አስታቀፈኝ አስሸነፈኝ ...! በቤቴ አምባ - ሰገነቴ ጠልፎ ጣለኝ -መቀነቴ በእኔው ጠላት - በእኔነቴ ሲዖል አየሁ - በገነቴ፤ ወደራሴ - ቀኝ ሳጋድ'ል የቀባኝን - እስክበድል ሽንፈት ጠራሁ - ምኞት ሳድል፣ በክረምቴ - ያሟሟቀኝ ከበጋዬ - አራራቀኝ ደላኝ ያልኩት - አስጨነቀኝ ግራ ሆነኝ - የልቤ ቀኝ ። “እንዲህም ሆነ፤ በዓመቱ መለወጫ ነገሥታት ወደ ሰልፍ በሚወጡበት ጊዜ፥ ዳዊት ኢዮአብን ከእርሱም ጋር ባሪያዎቹን እስራኤልንም ሁሉ ሰደደ። የአሞንም ልጆች አገር አጠፉ፥ ረባትንም ከበቡ፤ ዳዊት ግን በኢየሩሳሌም #ቀርቶ ነበር።” — 2ኛ ሳሙኤል 11፥1 # ይነበብ 👇👇 እንደዚህ ነው ሚለው...#ወቅቱ የምንድነው ስትሉ ነገሥታት ወደ ሰልፍ የሚወጡበት ይላል... ዴቭ ወቅት ነው #ያዛባው... ያኔ ተከታታይ የሆኑ ስህተቶችን ተሳሳተ...ወቅት መሳት መዘዙ ቀላል አይደለም... #ክረምት መተኛት መዘዙ ክረምት ላይ አያበቃም #በጋ ሲመጣ ምትበሉትን ታጣላችሁ, #አንዝራ ብትሉ ዝናብ ታጣሌችሁ, #ሆድ ደሞ ክፉ ነው #ዘሩን ትበሉታላችሁ! ከዛስ? ቀጣይም ምትዘሩትን ስለበላቸሁት ጣጣው ይከታተላችኋል ነው ...🙏 https://t.me/balamberas87 @balambaras8