ማሕተቤ Profile pictures
Статистикаየኢኦተቤክ አስተምህሮ እና ስርአትን የጠበቁ የተለያዩ 🦋ከመዝሙሮች 🦋ከስብከቶች 🦋 እንዲሁም 🦋ከመንፈሳዊ ትምህርቶች 🦋ከመንፈሳዊ ግጥሞች 🦋ከመንፈሳዊ ጥያቄዎች የተሰሩ ምርጥ ምርጥ ለፕሮፋይ የሚሆኑ ፎቶዎችን ያገኛሉ🦋🦋🦋🦋🦋🦋🦋🦋follow and share በማድረግ እንተባበር ክርስትያኖችን ለማብዛት እና ቻናሉን ለማሳደግ ይተባበሩን🙏
- Последний пост
- 6 дек.
- Последнее чтение
- 15 авг.
- Постов за неделю
- 0
- Всего постов
- 21
- Тип
- открытый
- Язык
- ti
- В каталоге с
- 14 авг.
- 1/24сутки в ленте
- —
- 1/48двое суток
- —
- 1/72трое суток
- —
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
የአእላፋት ዝማሬ መድኃኔዓለም መድኃኔዓለም የለም የሚሳነው አማኑኤል የለም የሚሳነው እርሱ ቃል ሲናገር ተራራው ሜዳ ነው መድኃኔዓለም የለም የሚሳነው አላስብም ነበር አልፈዋለው ብዬ ጉንጭ አልፎ ትራሴን እያጠበ እንባዬን እየተፈጸመ ሀይሉ በድካሜ ማዕበሉን አለፍኩት ቀለለልኝ ሸክሜ የቤቴ እራስ ነው የእቅዴ መሪ በክፉም በደጉም ነፍሴን አስተማሪ ፈጥሮ የማይረሳኝ ቤዛዬ ደረሰ ቤቴን ደስታ ሞላው እንባዬ ታበሰ ትናንት ባዶ ነበር የለኝ የሚሰፈር አንዳች አልነበረኝ ሚታይ የሚቆጠር ከእርሱ የተነሳ ዛሬ ግን ሙሉ ነኝ ክብር ለእርሱ ይሁን አለ የማይተወኝ እየከለከለ ለኔ ማይጠቅመኝን በጊዜው እየሰጠኝ ደሞ ሚረባኝን ሁለም በእርሱ ሆኗል አልሆነም ያለእርሱ ውዳሴ ምስጋና ይድረስ ለንጉሱ https://t.me/m_ezmur21 https://t.me/m_ezmur21
የ2018 የአእላፍት ዝማሬ ተጀመረ 🙌🥰
እንኳን ለእመቤታችን ለቅድስት ድንግል ማርያም ጾመ ፍልሰታ ፍቺ በዓል በሰላምና በጤና አደረሰን አደረሳችሁ! በየትም ዓለም የምትኖሩ የክርስትና እምነት ተከታዮች ሰላምታችን ይድረሳችሁ፡፡ የእመቤታችን ትንሣኤና ዕርገት እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በዚህ ምድር የኖረችው ስልሳ አራት ዓመት ነው፡፡ እነዚህ ዓመታት ሲተነተኑ ሦስት ዓመት በወላጆቿ ሐናና ኢያቄም ቤት፣ ዐሥራ ሁለት ዓመት በቤተ መቅደስ፣ ሠላሣ ሦስት ዓመት ከሦስት ወር ከልጇ ከወዳጇ ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር አሥራ አምስት ዓመት ከሐዋርያው ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ ጋር ነው፡፡ ያረፈችውም ጥር 21 ቀን በ50 ዓ.ም ነው፡፡ ባረፈችበት ወቅት ቅዱሳን ሐዋርያት ክቡር ሥጋዋን ለማሳረፍ ወደ ጌቴ ሴማኒ ሲሔዱ አይሁድ "ቀድሞ ልጇ በሦስተኛው ቀን ሞትን ድል አድርጎ ተነሣ፤ በአርባኛውም ቀን ወደ ሰማይ ዐረገ፤ ተመልሶም ይህን ዓለምን ለማሳለፍ ይመጣል እያሉ በማስተማር ሕዝባችንን ወስደውብናል፡፡ አሁን ደግሞ ዝም ብለን ብንተዋት እርሷም እንደ ልጇ ተነሳች እያሉ በማስተማር ሊያውኩን አይደለምን? ኑ! ተሰብስበን በእሳት እናቃጥላት" ብለው ክፉ ምክር ተማከሩ፡፡ ከመካከላቸውም ብርቱ ሰው የሆነው #ታውፋንያ የተባለ ቅድስት ሥጋዋን ከሐዋርያት ነጥቆ ለማስቀረት ክቡር ሥጋዋ ያለበትን የአልጋ ሸንኮር ሲይዝ በመልአከ እግዚአብሔር እጁ ተቆርጣ ከአልጋው ላይ ተንጠልጥላ ቀረች፤ ከዚህ የጥፋቱ ሥራው ተምሮ እመቤታችንን በመለመኑ እመቤታችን የተቆረጠች እጁን መልሳለታለች፡፡ ከዚህ በኋላ መልአከ እግዚአብሔር የእመቤታችንን የተቀደሰ ሥጋዋን ጌታችን ይወደው የነበረ ተብሎ የተነገረለት ሐዋርያው ቅዱስ ዮሐንስን ይዞ በገነት በዕፀ ሕይወት ሥር አስቀመጠው፡፡ ቅዱስ ዮሐንስም የሆነውን ሁሉ ለወንድሞቹ ቅዱሳን ሐዋርያት ነገራቸው፡፡ እነሱም የእመቤታችን ሥጋ በክብር ለማሳረፍ ካላቸው ጉጉት የተነሣ ከነሐሴ 1 ቀን ጀምሮ ሱባኤ ገቡ፡፡ ከሁለተኛ ሱባኤ ቆይታቸው በኋላ በአሥራ አራተኛ ቀናቸው ጌታችን የእመቤታችንን ትኩስ ሥጋ ሰጣቸው፡፡ ሐዋርያትም በዝማሬና በታላቅ ምስጋና በጌቴ ሴማኔ ቀበሯት፡፡ ነቢየ እግዚአብሔር ቅዱስ ዳዊት ‹‹አቤቱ ወደ ዕረፍትህ ተነሥ አንተና የመቅደስህ ታቦት› › ተብሎ ትንቢት የተናገረውን ሲተረጉሙት ‹‹ፈጣሪያችን እግዚአብሔር ሆይ፥ ወደ መንግሥተ ሰማያት የምታሳርፈው የመቅደስህ ታቦት የሆነችውን ድንግል ማርያምን ይዘህ ተነሥ›› ብለው ያመሰጥሩታል፡፡ /መዝ. 131፥8/፡፡ የእመቤታችንን ቅድስት ሥጋዋን ሐዋርያት ሲቀብሯት በሀገረ ስብከቱ ሕንድ የነበረው ሐዋርያው ቅዱስ ቶማስ ከሀገረ ስብከቱ ሲመለስ እመቤታችን ስታርግ ያገኛታል ለምልክት እንዲሆነው ሰበኗን (የመግነዟን ጨርቅ) ተቀብሏት ይለያያሉ፡፡ ለወንድሞቹ ሐዋርያት ያየውን ይነግራቸዋል፡፡ ለበረከት የሰጠችውንም ሰበን ያካፍላቸዋል፤ ሐዋርያት ‹ ‹ዕርገቷን እንዴት እሱ ብቻ ተመልክቶ ለምን እኛ ይቀርብናል› › ብለው በዓመቱ ነሐሴ አንድ ቀን ሱባኤ ገቡ፡፡ ነሐሴ 16 ቀን የልባቸው መሻት ተፈጸመላቸው፡፡ ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እመቤታችንን መንበር፣ ቅዱስ ጴጥሮስን ንፍቀ (ረዳት) ቄስ፣ ቀዳሚ ሰማዕት ቅዱስ እስጢፋኖስን ገባሬ ሰናይ (ዋና ዲያቆን) አድርጎ ቀድሶ ሁሉንም አቆረባቸው፡፡ በትኅትና የያዙት ሱባኤም የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያምን ዕርገቷን ለማየት አበቃቸው፡፡ ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችንም ይህን መሠረት አድርጋ ከነሐሴ 1-16 ጾመ ፍልሰታ በማለት ከሰባቱ አጽዋማት አንዱ አድርገን እንድንጠቀምበት ሥርዐት ሠራችልን፡፡ በነቢያና በሐዋርያት መሠረት ላይ የታነጽን ኦርቶዶክሳውያን የተዋሕዶ ልጆች በየዓመቱ ይህን ጾም በሱባኤ በማሳለፍ ከእመቤታችን ጸጋና በረከት ተሳታፊዎች እንሆናለን፤ ሆነናልም፡፡ የዓመት ሰዎች ይበለን፡፡ ከእመቤታችን ረድኤት በረከት ተቋዳሾች ያድርገን፡፡ አሜን! ለወዳጅዎ ሼር ያድርጉ! 💚 @ortodoxmezmur 💚 💛 @ortodoxmezmur 💛 ❤️ @ortodoxmezmur ❤
видео или голосовое, без подписи
የወር አበባ ጊዜ ሴት ልጅ በቤተ ክርስቲያን እይታ። ፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠ 👉 ሴት ልጅ በወር አበባ ጊዜ መፀለይ ትችላለች ? በወር አበባ ጊዜ መስቀል መሳለም፣ መጽሐፍ ቅዱስ እና ሌሎች ጸሎት መጽሀፍትን ማንበብ ይቻላል? እንዲሁም ወደ ቤተክርስትያን መሄድ ይቻላል ? የወር አበባ በሴቶች ላይ በየወሩ የሚታይ የደም መፍሰስ ነው፡፡ በቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ “ደመ ጽጌ፣ አበባ ደም” በመባል ይጠራል፡፡አሰያየሙም የወንድ ዘር ካላገኘ ከማህጸን ግድግዳ ፍራሽ ጋር በደም መልክ ስለሚፈስና የኋለኛው ማንነቱ ደምነት ስለሆነ ነው፡፡ ይህም ማለት አገልግሎቱን የጨረሰ፣ ያረጀ፣ ቆሻሻ ማለት ነው፡፡ ይህ በየወሩ ዑደትን ተከትሎ የሚሄደው የዘር ፍሳሽ በስነ ህይወት ትምህርት ኦቫሪ (ከዘር ከረጢት) የሚለቀቅ የወንድ ዘር ካላገኘ ኦቫ (ሴቴ ዘር) ጋር እየተቀላቀለ የሚወርድ ነው፡፡ የወር አበባ በቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ በሁለት ከፍለን ነው መመልከት ያለብን፤ በዘመነ ኦሪትና ዘመነ አዲስ ኪዳን በማለት፡፡ በርግጥ በዘመነ ኦሪት የወር አበባ የርኩሰትና የመርገም ምልክት ነበር፡፡ ለዚህም ማስረጃነት በመጽሃፍ ቅዱስ ዘሌ 18÷19፣ 20÷18 ያሉ ጥቅሶች “በመርገምዋ ርኩሰት ሳለች” እና “ባለ መርገም ሴት” በማለት ሲገልጸው፤ ባንጻሩ ደግሞ ከወር አበባዋ ነጻ የሆነችውን ሴት “ከርኩሰትዋ ነጽታ” በማለት የወር አበባ የርኩሰትና የመርገም ምልክት መሆኑን ይጠቁማል፡፡ በዘመነ አዲስ ደግሞ የወር አበባ የርኩሰትና የመርገም ምልክት መሆኑ ቀርቷል፡፡ ርኩሰት አይደለም፤ ርኩስም አያሰኝም፡፡ በብሉይ ኪዳን አዳምና ሄዋን በገነት በነበሩ ጊዜ ዕጸ በለስን በልተው እግዚአብሔርን በደሉ፤ እግዚአብሔርም ሄዋንን ደመ ዕጸ በለስን አፍስሰሻልና “ወበከመ አድመውኪያ ለእንትኩ ዕጽ ከማሁ ድምዊ ለለወርኁ፡፡” በማለት ደሟ በየወሩ እንዲፈስ ፈጣሪ ፈረደባት፡፡ ስለዚህ የሄዋን ደም መፍሰስ መነሻው መርገም ነው፡፡ በአዲስ ኪዳን ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርሥቶስ በፈጸመው ቤዛነት መርገምነቱና ርኩስነቱ ተወግዷል፡፡ የወር አበባ በዚህ ዘመን ርኩሰት ወይም መርገም ባይሆንም እድፍ (ቆሻሻ) ነው፡፡ እድፍና ርኩሰት ልዩነት አላቸው፡፡ ርኩሰት ውስጣዊ ነው፤ በንስሃ እንጂ በውሃ አይጠራም፡፡ እድፍ ደግሞ ግዘፍ አካል ያለው፣ የሚታይና ውሃ የሚያነጻው ነው፡፡ የወር አበባ በሴቶች ባህሪ ሳለ እንደ ቆሻሻ አይቆጠርም፣ ከሰውነት ሲወገድ ግን ይቆጠራል፡፡ ይህንን ለማስረዳት ምሳሌ መሆን ከሚችሉት ውስጥ ዛህል (ንፍጥ)፣ ሽንት፣ ምራቅ፣ ዓይነምድርና ሌሎችንም መጥቀስ ይቻላል፡፡ ወር አበባ ርኩሰት ባለመሆኑ መስቀል ከመሳም፣ ከመጸለይ፣ ቅዱሳት መጻህፍትን ከማንበብና ከመድገም አያግድም፡፡ ነገር ግን ከሩካቤ፣ ከመጠመቅ፣ ከመቁረብና ቤተ መቅደስ ከመግባት ይከለክላል፡፡ ከሩካቤ:- ሩካቤ በወር አበባ ጊዜ ከሚከለከሉ ነገሮች አንዱ ነው፡፡ በወር አበባ ጊዜ የሚደረግ ግንኙነት የህክምና ባለሙያዎች ሳይቀር ለአባላዘር፣ ለልዩ ልዩ በሽታዎችና ለኢንፌክሽን ሊያጋልጥ እንደሚችል በመናገር እንዳይፈጸም ይመክራሉ፡፡ በመንፈሳዊው አስተምህሮ ስንመለከተው ደግሞ የሰው ልጅ ዘር ቅዱስ በሆነው በእግዚአብሔር አምሳል በመፈጠሩ፣ ይህንን የተከበረ ዘር፣ እዳሪ ወይም ቆሻሻ ከሆነ ደም ጋር ማዋሃድ ኃጢያት እንደሆነ ይቆጠራል፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ ሴት ልጅ በወር አበባዋ ጊዜ እንዳለች የሚፈጸምን ሩካቤ “እርሷም በመርገምዋ ርኩሰት ሳለች ኃፍረተ ሥጋዋን ትገልጥ ዘንድ ወደ እርሷ አትቅረብ” ዘሌ 18÷19፣ ዘሌ 20÷18። በዚህም ምክንያት በወር አበባ ጊዜ የሚፈጸም ሩካቤ በኦሪትም ይሁን በአዲስ ኪዳን ክልክል ነው፡፡ ከመጠመቅ:- ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ “ይህም ውኃ ደግሞ ማለት ጥምቀት ምሳሌ ሆኖ አሁን ያድነናል፤ የሰውነትን እድፍ ማስወገድ አይደለም፡፡ ለእግዚአብሔር በጎ ህሊና ልመና ነው እንጂ” 1ኛ ጴጥ 3÷21 በማለት ተናግሯል፡፡ ስለዚህ ጥምቀት ስጋዊ እድፍን ማስወገጃ ስላልሆነ፣ ከመጠመቅ በፊት ተጣጥበው እንጂ ከእድፍ ጋር ለመጠመቅ መቅረብ ተገቢ አይደለም፡፡ የወር አበባም ከላይ እንደተመለከተው ከሰውነት ሲወጣ እድፍ (ቆሻሻ) በመሆኑ፣ ከዚህ የቤተ ክርስቲያን ስርዓት ውጪ እንዲሆን ተደርጓል፡፡ ቤተመቅደስ መግባት፡- ሴት በወር አበባዋ ጊዜ የምትከለከለው ነገር ቤተመቅደስ መግባትን ነው፡፡ይህም የሆነው በርኩሰት ምክንያት ወይም በኦሪት ሕግ ምክንያት ሳይሆን በቤተመቅደስ መፍሰስ ያለበት ደም አማናዊ የሆነው የክርስቶስ ደም ብቻ በመሆኑ ነው!ይህ ስርዓት ለሴቶች ብቻ ሳይሆን ለወንዶችም ነው፡፡ አንድ ወንድ እየነሰረው ወይም የሆነ ነገር አካሉን ቆርጦት ደም እየፈሰሰው ከሆነ ወደ ቤተ መቅደስ መግባት የለበትም!ምክንያቱም በቤተ መቅደስ ከ ክርስቶስ ደም ውጪ ሌላ ነገር መፍሰስ ስለሌለበት ነው፡፡ **በወር አበባ ላይ ሳለች ሴት ወደ ቤተመቅደስ አትግባ ማለት ቤተ ክርስቲያን አትሂድ ማለት ሳይሆን ወደ ቤተ ክርስቲያን ሄዳ የመጀመሪያውን ቅጽር (አጥር) ከገባች በኋላ በመጠለያ ውስጥ በመሆን ትጸልይ፣ ትማር ወይም ማንኛውንም አይነት መንፈሳዊ ስራዎችን ሰርታ ትመለስ ማለት ነው፡፡ ከመቁረብ፡- ሴቶች ከወር አበባ ሳይነጹ ሥጋ ወደሙ መቀበል አይችሉም፡፡ ይህንን ስርዓት ተላልፈው ወደ ሥጋ ወደሙ እንዲቀርቡ ያደረገ ዲያቆንም ይሁን ቄስ ከክህነቱ እንዲሻር ፍትሕ ነገስት ይደነግጋል፡፡ “ከግዳጅዋ ያልነጻችውን ሴት በደሟ ወራት ከቤተ ክርስቲያን አግብቶ ሥጋውን ደሙን ያቀበለ ከክህነቱ ይሻር፡፡” ፍትነገ 6፣ ዘሌ 7፡19 ይህ ሥርዓት በሴቶች ላይ ብቻ ሳይሆን ወንዶችም ህልመ ለሊት በሚያጋጥማቸው ሰዓት እንዳይገቡ ይከለከላል፡፡ ቤተ ክርስቲያን የገነት ምሳሌ ናት፡፡ ሔዋን ከአዳም ጋር በገነት ለሰባት ዓመታት ስትኖር የወር አበባ አታይም ነበር፡፡ ቤተ መቅደስ የገነት ምሳሌ መሆኗ የተሟላ እንዲሆን የወር አበባ የምታይ ሴት ወደ ቤተ መቅደስ አትገባም፡፡ ይህን የእናት ቤተክርስቲያን ትምህርት ለሌሎቹም እህቶቻችን ሼር በማድረግ እናካፍላቸው፡፡ አንቺ ከተረዳሽ ለማያቁ እህቶችሽ ሼር አርጊ ። ወንድሜ ለእህቶችህ ሼር አርግ ። ዝሙት የኃጢአት ነው። ዝሙት ከፈጣሪ ጋር መጣያ ነው። ዝሙት ማንነትን የሚሸጥ ነው። ዝሙት በሽታ ነው። እባክዎ እራስዎን ይጠብቁ ። ❤🩹✞︎መዝሙር ግጥሞች ቤት✞︎⛪️❤🩹 •➢ ሼር // SHARE ✧━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━✧ ❇ አዘጋጅ :- ስርዓተ ቤተክርስቲያን ❇ ╔═════════════════════╗ ║|✥https://t.me/orthodoxs_mezmur የቀረበ✥| ╚═════════════════════╝ ✧━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━✧ Join
🍃 ታሪክን መርምሩ! 🍃 ስሟን ስትሰማ፤ ልጇ ሲላት እማ፤ ልብህ ይናደዳል፤ ተራራን ይንዳል፤ ቤዛ ዓለም ስላት፤ የእግዚአብሔርን እናት፤ ደምህ ይፎክራል፤ ፊትህም ይበግናል። ጻድቃን ይፈርዳሉ፣ ምሕረት ያሰጣሉ፤ ብዬ ሳስተምርህ፤ ስድብ ታዘንባለህ። ለስድብ ዘለፋ ስሟ ሚቀናቹ፤ ፓስተር ሚልየነሮች በምቾት ያላቹ፤ በጎችን ለመንጠቅ ስሟን የምትጠሩ፤ በስንዴው አዝመራ እንክርዳድ ምትዘሩ፤ የሲኦልን ጉድጓድ ለሰው ምትቆፍሩ፤ ማርያም ሐዋርያት ጴንጤዎች ነበሩ፤ ማለታቹ ለሕዝብ ታሪክን ሳትፈሩ፤ መባሉ ይረሳ፤ ባይሆን ... እንዳይባል ቃላቹ አባሳ! ጴንጤ ናት ካላቹ ድንግል ሶልያና፤ የርሷን ንጽኅና፤ አርምሞ ትሕትና፤ ፍቅር ልግስና፤ በእግራቹ ረግጣቹ በዝሙት ሰክራቹ፤ በላይዋ ስድብና ዘለፋ አብዝታቹ፤ በካራቴ ከንፈር ሰይጣን ካላስወጣን ለምን ትላላቹ? ሐዋርያት አባቶች ጴንጤ ከነበሩ፤ ስለስሙ ብለው ዞረው በየምድሩ፤ ለምን ተገረፉ? ለምን በነቀፋ በአይሁድ ተወረፉ? ካልተገባም ለኛ መቀበል መከራ፤ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ልብን የሚያበራ፤ ምን ይሠራል ሠፍሮ የሐዋርያት ሥራ? እኔምኮ ቢሆን ... ለስድባቹ ቡጢ፤ ሞኛሞኝ መናጢ፤ ፍቅርን ማዝለፌ፤ ስድብን ማለፌ፤ አይደለም ደንቁሬ፤ እርቄ ፈርቼ ከጥበብ ሰፈሬ! እሺ ፕሬዝዳንቱ ... ማርያም ሐዋርያት ጴንጤዎች ነበሩ፤ ብለህ ማስተማርህ ለዓለም ሀገሩ፤ ይደምሰስ ይረሳ፤ ባይሆን ... እንዳይባል ቃላትህ አባሳ! ማርያም ሶልያና ጴንጤ ከነበረች፤ አምላክን ታቅፋ፤ ገና ልጅ እያለች፤ በበረሐ በዱር ደምን እየደማች፤ ለምን ተሰደደች? ለምንስ ተናቀች? ሐዋርያት አባቶች ጴንጤ ከነበሩ፤ ሲሹ ሲፈልጉ ሊያስተምሩ ሊሾሙ፤ ስለምን ጸዊምን አስቀድመው ጾሙ? ሐዋርያት ከሆኑ ከጥምቀት የራቁ፤ ሕጻናትን አብረው ከወላጆች ጋራ ለምን አጠመቁ? ስለዚህ ... ጴንጤነት ከሆነ መሰደድ መሰደብ፤ ካልሆነ በሰይጣን ቤልሆር መጋለብ፤ ጴንጤነት ከሆነ መጾምና መስገድ፤ ስለአምላክ ብሎ ከምቾት መሰደድ፤ ጴንጤነት ከሆነ ... ኢየሱስን ማለት እግዚአብሔር ፈጣሪ፤ ሳይሉት አማላጅ ከአምላክ ዘንድ አስማሪ፤ እኛ ሁላችንም ያለአንዳች ውላጤ፤ ሳንሆን ወጠጤ፤ እንሆናለን ጴንጤ! ስለዚህ ... እውነት ቅድስናን ታሪክ ተንተራሱ፤ ዕውቀት ማዕድንም ንዑ ተቋደሱ፤ ታሪክን መርምሩ፤ በራሳቹ ዛቢያ የታሪክ ፈጠራ፤ የውሸት መራራ፤ ትርጉም አትዙሩ! ታሪክን መርምሩ! ወስብሐት ለእግዚአብሔር!!!
ዮም ፍስሐ ኮነ😍😍 ተጨማሪ ለማግኘት Join ያድርጉ ➪@m_ezmur21 ➪@m_ezmur21
✞ ዮም_ፍስሐ_ኮነ ዮም /ፍስሐ ኮነ/(2) በእንተ ልደታ ለማርያም በባርነት ሳለን ፍስሐ ኮነ ኃጢአት በአለም ነግሳ ፍስሐ ኮነ በድንግል መወለድ ፍስሐ ኮነ ቀረልን አበሳ ፍስሐ ኮነ እግዚአብሔር መረጠሸ ፍስሐ ኮነ ልትሆኚው እናቱ ፍስሐ ኮነ ይኸው ተፈፀመ ፍስሐ ኮነ የዳዊት ትንቢቱ ፍስሐ ኮነ አዝ____ የሔዋን ተስፋዋ ፍስሐ ኮነ የአዳም ዘር ህይወት ፍስሐ ኮነ የኢያቄም የሐና ፍስሐ ኮነ ፍሬ በረከት ፍስሐ ኮነ ምክንያተ ድኂን ፍስሐ ኮነ ኪዳነምህረት ፍስሐ ኮነ ድንግል ተወለደች ፍስሐ ኮነ የጌታዬ እናት ፍስሐ ኮነ አዝ____ በሔዋን ምክንያት ፍስሐ ኮነ ያጣነውን ሰላም ፍስሐ ኮነ ዛሬ አገኘነው ፍስሐ ኮነ በድንግል ማርያም ፍስሐ ኮነ የምስራች እንበል ፍስሐ ኮነ ሀዘናችን ይጥፋ ፍስሐ ኮነ ተወልዳለችና ፍስሐ ኮነ የአለም ሁሉ ተስፋ ፍስሐ ኮነ መዝሙር ዘማሪ ፍቃዱ አማረ ተጨማሪ ለማግኘት Join ያድርጉ ➪@m_ezmur21 ➪@m_ezmur21
💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠 #በሰሙነ_ሕማማት_ይህንን_አድርጉ!!! (ሊቀ ሊቃውንት ስምዐ ኮነ መልአክ እንደጻፉት) ሰሙነ ሕማማት አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለዓለም ሁሉ ቤዛ ሆኖ ተላልፎ መሰጠቱን የምናስታውስበት ሳምንት ነው። ይህንን ምክንያት በማድረግ የሥርዓት ለውጥ ሲደረግ ሲመለከቱ ግራ የሚጋቡና ሥርዓተ አምልኮውን በሚገባ ከመከታተል ይልቅ ሥርዓት የጣሱ እየመሰላቸው የሚጨነቁ ስላሉ ልናደርገው የሚገባንን እጽፍላችኋለሁ። 1. በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ብሎ ፊትንና መላ ሰውነትን በትዕምርተ መስቀል {በመስቀል ምልክት} ማማተብ አይከለከልም። ከካህን እጅ ቡራኬ አንቀበልም በካህኑ እጅ ያለውን መስቀል አንሳለምም እና ማማተብም የለብንም በሚል ፍልስፍና ካልሆነ ማማተብ ክልክል ነው ተብሎ የተጻፈበት ቦታ የለምና። 2. የሚከለከል ጸሎት የሌለ መሆኑን አውቃችሁ ያስለመዳችሁትን ጸሎት በትጋት ጸልዩ። መሥዋዕት ካለመሠዋታችን ቅዳሴ ካለመቀደሳችን በቀር በዚህ ሳምንት ከብሉይ ኪዳን መጻሕፍት ጀምሮ እስከ ሊቃውንት ድርሳናት ድረስ በቤተ ክርስቲያን የማይጸለይ ጸሎት የለምና። 3. ሰላምታ መስጠት ከጸሎተ ሐሙስ ዕለት በቀር አልተከለከለም፤ እሱም ቢሆን አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ በይሁዳ ሰላምታ ተላልፎ መሰጠቱን ለማስተዎስ እንጅ ሌላ የተለየ ምክንያት ስለሌለው በመርሳት ወይም በሌላ ከድፍረት በተለየ ምክንያት ሰላምታ ያቀረበላችሁን ሰው ልታስደነግጡና ትልቅ ኃጢአት እንደሠራ አድርጋችሁ ልታስጨንቁት አይገባም። 4. “በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ፩ አምላክ” ብሎ መጻሕፍትን ማንበብ ወይም ሌላ ሥራን መጀመር ይቻላል። ስመ እግዚአብሔር መጥራት የምንከለከልበት ጊዜ መቸም የለምና። 5. የጌታችንን ሕማሙንና ሞቱን የሚያስታውሱ መጻሕፍትን በማንበብና በመስማት ጊዜአችንን መወሰን ይገባናል። 6. በዚህ ሳምንት ተድላ ደስታን ሲያደርጉ መገኘት ከአይሁድ ጋር እንደ መተባበር የሚያስቆጥር ስለሆነ አብዝቶ በመብላትና በመጠጣት፣ ያማረውንና ጌጠኛውን ልብስ በመልበስ፣ ባልና ሚስት በምንጣፍ በመገናኘት እንዲሁም በልዩ ልዩ ምክንያት ከምናደርጋቸው ተድላ ደስታዎች መራቅ ይገባናል። ቅዱሳን በዘመናቸው ሁሉ ባሰቡት ጊዜ የሚያስጨንቃቸውን የክርስቶስን መከራ እያሰብን ለጥቂት ጊዜም እንኳን ቢሆን የክርስቶስን መከራ በሰውነታችን ማሰብ ይገባናል። የተቻለው እንደ ጴጥሮስ የራሱን ኃጢአት እያሰበ እንደ ማርያም መግደላዊት የክርስቶስን ሞት እያዘከረ ሊያለቅስ ይገባዋል። በወዲያኛው ዓለም ከማልቀስ የሚያድነን ዛሬ የራሳችንን ኃጢአት አስበን የክርስቶስን ሞት አዘክረን የምናለቅሰው ለቅሶ ነው እንጅ ዛሬ ከተደሰትን ደስታችንን በዚህ ዓለም ማድረጋችን አይደለምን? 7. በተቻለን መጠን በቤተ ክርስቲያን መዋል ይገባናል፤ ሕማማተ መስቀልን የሚያስታውሱ መጻሕፍት የሚነበቡበት ሳምንት ስለሆነ ነው። ነገር ግን በልዩ ልዩ ምክንያት በቤተ ክርስቲያን መዋል እንኳን ባይቻላችሁ ባላችሁበት ቦታ ሁናችሁ እየዋሻችሁ በሐሰት የከሰሱትን፣ እየቀማችሁ ልብሱን የገፈፉትን፣ ሰው እየደበደባችሁ በጅራፍ የገረፉትን፣ በወንድሞቻችሁና በእኅቶቻችሁ ላይ እየፈረዳችሁ በክርስቶስ ላይ የፈረዱበትን፣ በሰዎች ላይ እየተዘባበታችሁ የተዘባበቱበትን፣ በሳቅና በሽንገላ ሰውን እየሸነገላችሁ ሽንገላ በተሞላበት ሰላምታ ጌታውንና መምህሩን አሳልፎ የሰጠ ይሁዳን ልትመስሉ አይገባም። ይልቁንም በአይሁድ እጅ ተላልፎ ቢሰጥም ንጹሓ ባሕርይ መሆኑን በማመን እስከ ቀራንዮ የተከተሉትን ደቀመዛሙርት ልትመስሉ ይገባል። እግራችሁ በመቅደሱ ውስጥ ባይቆምም ልባችሁን ከመቅደስ ልታወጡት አይገባም። እያዘናችሁ ባላችሁበት ቦታ ዋሉ። 8. በቤታችሁም ሆነ በቤተ ክርስቲያን አብዝታችሁ ስገዱ። ስለሁላችንም ቤዛ የሚሆን ክርስቶስ በፊታችን መስቀል ተሸክሞ ሲወድቅ እያያችሁት ትቆማላችሁን? አይሁድ ገፍተውት አንድ ጊዜ ወደ ምድር በወደቀ ጊዜ ለወደቀው መውደቅ ዘመናችንን ሙሉ ብንወድቅ ብንነሣ ውለታ መክፈል እንችል ይመስላችኋል? ቅዱሳን ሳያቋርጡ ሲሰግዱ የሚኖሩት ክርስቶስ በፊታቸው በአይሁድ እጅ እየተገፋ መስቀሉን እንደተሸከመ ሲወድቅ በዓይነ ሕሊናቸው ስለሚያዩት ነው። በስንክሳር ተጽፎ የምናገኘው ዜና ሞታቸው እየሰገዱ ሳሉ ሞት ነፍሳቸውን ከሥጋቸው ለይቶ እንደሚወስዳትና ለስገደት ታጥቀው እንደተንበረከኩ እንደሚገኙ ይነግረናል። የተሰቀለውን ክርስቶስን የሚያስብ ሰው ለሰውነቱ ዕረፍትን አይሻም። 9. ከሁሉም ሰው ጋር ፍቅርን አድርጉ። ሰውን ለመውደድ ምክንያት አታብጁ። ክርስቶስ አሳልፎ የሰጠውን ይሁዳን “ወዳጄ” ብሎ ሲጠራው አትሰሙትም? እግዚአብሔርን አንተን ያለ ምክንያት እንደ ወደደህ አንተም ያለ ምክንያት ሰውን መውደድ ልመድ። ክርስቶስ አንተን ጠላቱ ሆነህ ሳለ ፍቅርን ካላጎደለብህ ለጠላትህ ፍቅርን አታጉድልበት። ክርስቶስ ይሁዳን ‘’ወዳጀ’’ ብሎ ከጠራው አንተም ይሁዳዎችህን ወዳጀ ብለህ ጥራቸው። አውቃለሁ ጠላትን መውደድ መራራ ሐሞትን ከመጠጣት በላይ መራራ ነው። ነገር ግን እኔም ለይሁዳዎቻችን ፍቅርን እንስጥ ማለቴ መራራ ሐሞት የጠጣ ክርስቶስን እንድንመስለው ነው። 10. ለሁሉም መስጠት በምትችሉት መጠን ስጡ እንጅ አትቀበሉ። ከሚቀበል ይልቅ የሚሰጥ ብፁዕ ነውና በመስጠታችሁ ብፁዓን ተብለው ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ከሚገቡት ትቆጠራላችሁ። ምናልባትም የምትሰጡት ገንዘብ ባይኖራችሁ ገንዘብ ለሰጧችሁ ባለጠጎች የምትሰጡት ጸሎት ሊኖራችሁ ይገባል። ከምንጊዜውም የበለጠውን ስጦታ የተቀበልንበት ሳምንት መሆኑን እያሰባችሁ አንዳች የምትሰጡት ሥጋዊም ሆነ መንፈሳዊ ስጦታ የሌላችሁ ባዶዎች እንዳትሆኑ ተጠንቀቁ። ከሁሉ በላይ የሆነውን ስጦታ የጌታን ሥጋና ደም እነሆ ተቀብለናል። ክርስቶስ መድኃኒነ መጽአ ወሐመ በእንቲአነ ወበሕማማቲሁ ቤዘወነ! 💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠
https://youtu.be/GtILIZC2cN0?si=NHkW-f1cN6YRP3eW
በሚፈርደው ፈረዱበት በሚፈርደው ፈረዱበት በሚምረው ጨከኑበት /2/ በቁጣ ጎተቱት ቀይ ግምጃ አለበሱት አዝ አዳምን የፈጠረ እጅ በመስቀል ቀኖ ተቸነከረ ቅዱሱ የእግዚአብሔር ልጅ ከወንበዴ ጋር ተቆጠረ ህይወትን እፍ ያለዉን አፍ ጨክነው ሀሞት አጠጡት በሞቱ ሞትን ይሽር ዘንድ ጌታን በመስቀል ሰቀሉት ይህን ያህል ትህትና ይህን ያህል ትዕግስት ይህን ያህል ሰው ማፍቀር ይህን ያህል ምህረት ዝም አለ አማኑኤል በግፍ ለሚሰቅሉት አዝ በመፍራትና በመራድ መላእክት ፊቱ ለሚሰግዱለት የአለሙን ሁሉ ጌታ በአደባባይ አቆሙት ለሱራፌል የክብር ዘውድ ያቀዳጃቸውን ጌታ ፍቅር ያነበብንበት ፊቱ በክፉ ባሪያ ተመታ ይህን ያህል ትህትና ይህን ያህል ትዕግስት ይህን ያህል ሰው ማፍቀር ይህን ያህል ምህረት ዝም አለ አማኑኤል በግፍ ለሚሰቅሉት አዝ ጽድቅና የጸና ሰላም የሀጢአት ስርየት በሰጠን እንደ ክፉ ሰዉ ተቆጥሮ በእሾህ አክሊል አጌጠ ለኪሩቤል የግርማን ልብስ የሚያለብሳቸው እርሱን እርቃኑን ይሰቀል ብለው አጣ ተጣጣሉበት ልብሱን ይህን ያህል ትህትና ይህን ያህል ትዕግስት ይህን ያህል ሰው ማፍቀር ይህን ያህል ምህረት ዝም አለ አማኑኤል በግፍ ለሚሰቅሉት አዝ በኢየሱስ መንገላታት አለም እንዲድን ከፍዳ ቅዱሱ ደምና ዉሃ ከአምላካችን ጎን ተቀዳ ሰላም ለእናንተ ሲለን እጅና እግሩን አየን ሙስና መቃብር ጠፋ ይኸዉ በአዲሱ ኪዳን ይህን ያህል ትህትና ይህን ያህል ትዕግስት ይህን ያህል ሰው ማፍቀር ይህን ያህል ምህረት ዝም አለ አማኑኤል በግፍ ለሚሰቅሉት ዘማሪ ገ/ዮሐንስ ገ/ጻድቅ 💚 @ortodoxmezmur 💚 💛 @ortodoxmezmur 💛 ❤️ @ortodoxmezmur ❤️
ፍትሐ ነገሥት ስለ ሰሙነ ህማማት ምን ይላል ፍትሐ ነገሥት አንቀጽ ፲፭ ------------------------------------------ ቁጥር 578፡ በሊህ በስድስቱ ቀኖች ከቂጣ ከጨው ከውኃ ብቻ በቀር አይብሉባቸው፡፡ በሊህ ቀኖች ከወይን ከሥጋ ተለዩ የኀዘን ቀኖች ናቸውና የደስታ ቀኖች አይደሉም፡፡ ዓርብንና ቅዳሜን ግን ሁለቱንም በአንድነት ጹሟቸው፡፡ የሚችል እስከ ሌሊቱ ዶሮ ጩኸት ጊዜ ድረስ ምንም ምን አይቅመስባቸው ሰውየውም ሁለቱን ቀኖች በአንድነት መጾም ባይቻለው ግን የቅዳሜን ጾም ይጹም፡፡ ቁጥር 588፡ አንድ ሰው በባሕር ቢኖር ሰሙነ ሕማማትን ባያውቅ ከበዓለ ሃምሳ በኋላ ይጹም፡፡ ይኸውም ሰሙነ ሕማማትን የሚጠብቅ አይደለም፡፡ ምሳሌውን ብቻ ነው እንጅ ስለእርሱ መጾም ይገባዋል፡፡ ቁጥር 590፡ ካህን ሰሙነ ሕማማትን ቀንና ሌሊቱን ሳያስተካክል አስቀድሞ ቢያውል ይሻር፡፡ ከሕማማት ቀጥላ ከምትሆን ከቅዳሜ ስዑር በቀር እሑድንና ቅዳሜን የጾመ ካህን ቢኖር ይሻር፡፡ ቁጥር 596፡ ክብርት በምትሆን በአርባ ጾም በመጀመሪያው ሱባዔ ፀሐይ እስኪገባ ድረስ ይጹሙ፡፡ የመጀመሪያው ሱባዔ ካለፈ በኋላ እስከ 11 ሰዓት ድረስ ይጹሙ፡፡ በሰሙነ ሕማማት ግን ኮከብ እስኪወጣ ድረስ ይጹሙ፡፡ በእነዚህም ወራቶች አያጊጡ፡፡ ቁጥር 597፡ ሴቶችም ጌጣቸውን ይተዉ፡፡ ሁሉም ለእያንዳንዱ በአርባ ጾምና በሰሙነ ሕማማት መጠበቅ ይገባዋል ድኅነታችንና የኃጢአታችን ሥርየት በእነርሱ ነውና፡፡ ይኸውም ሥራ አንዱስ እንኳ በአርባ ጾም ወራት በምንጣፍ ፈጽሞ እንዳይገናኝ ከጋብቻ ሕግ የወጣ ነው፡፡ ክብርት በምትሆን በሕማማት ወራት ይህችን ኃጢአት የሚሠራት ሰው ወዮለት፡፡ በአርባ ጾም በተድላ በደስታ ፈቃዳችንን ካደረግን ትንሣኤውን ባየን ጊዜ ተድላ ደስታችን ወዴት አለ? ቁጥር 600፡ በሰሙነ ሕማማት ክርስትና ማንሣት ክህነት መስጠት ለሞቱ ሰዎች መጸለይ አይገባም፡፡ በእነዚህም ቀኖች በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ፈጽሞ ማገልገል ይገባል እንጅ፡፡ በሰሙነ ሕማማት ስለሚሞቱት ሰዎች የሙታን ግንዘትና የሐዋርያት ሥራ ወንጌላት የሙታን ፍትሐት በሆሣዕና በዓል ቀን ይነበብ እንጅ፡፡ ቁጥር 601፡ በጸሎተ ሐሙስ ጸሎተ ተአምኆ እግዚአ ሕያዋን የቡራኬ ጸሎት አይባልም (አይጸለይም)፡፡ ቅዳሜ ግን እግዚአ ሕያዋን ይባላል ፍትሐት ይፈታል፡፡ ከመሳለም በቀር ጸሎተ ዕጣንም ይጸለያል፡፡ በዕለተ እሑድ ግንዘት ማድረግ በፋሲካ ቀንም ማልቀስ አይገባም፡፡ ዳግመኛም በውስጧ በአርባ ጾም ከተድላ ከደስታ ወገን ምንም ማድረግ አይገባም። መጋባት ክህነት መስጠት ክርስትና ማንሣት ከሹመትም ወገን ስለሚሞቱት ከመጸለይ በቀር ምንም ማድረግ አይገባም፡፡ ይሞታል ተብሎ ለሚያስፈራው ግን ጥምቀተ ክርስትና ይደረግለታል፡፡ https://t.me/weladite_amlaki https://t.me/weladite_amlaki https://t.me/weladite_amlaki
ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅድስት ማርያም ጸሎት ይማረን በረከቷም ይደርብን ለዘላለሙ አሜን። ✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞ ❤️ቅዱስ ቶማስ ሐዋርያ❤️ በዚህችም ዕለት የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በትንሣኤው ሳምንት ለሐዋርያው ቶማስ ተገለጠለት በእጆቹና በእግሮቹ ውስጥ የችንካሮቹን ምልክትም አሳየው የቶማስንም እጅ ይዞ በመለኮታዊ ጐኑ ውስጥ አኖረውና በጦር የተወጋበትን ቦታ አሳየው ቶማስም ጌታዬና ፈጣሪዬ መነሣትህን አመንኩ አለ። ጌታችንም ብታየኝ አመንከኝ የሚመሰገንስ ሳያየኝ የሚአምንብኝ ነው ብሎ መለሰለት።በትርጓሜ ወንጌልም እንዲህ ይላል ቶማስ በመድኃኒታችን ጐን ውስጥ እጁን በአስገባ ጊዜ እጁ በመለኮት እሳት ተቃጠለ በመለኮቱም ደግሞ በታመነ ጊዜ እጁ ከመቃጠል ዳነች። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን በሐዋርያቶቹም ጸሎት በታጋዮች ጻድቃንም በድል አድራጊዎች ሰማዕታትም ጸሎት ይልቁንም በእመቤታችን ማርያም በአማልጅነቷ ይምረን ዘንድ ወደርሱ እንለምን ለዘላለሙ አሜን።
@በጾመ ሁዳዴ ሳትሰራ አርባዉን ቀን አለፈብህ ? አትጨነቅ አርባዉን የምተካ ታላቅ ሳምንት ሰሙነ ሕማማት አለና እራሳቹህን ለተጋድሎ አዘጋጁ............ተዋሕዶ አንዲት ናት @hanu_yeldetye
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
+++ና ና የምስጋና ጌታ+++ ና ና የምስጋና ጌታ ና ና የምህረት ጌታ ማዳንህ ተገኝታለችና ሰላምህ ተገኝታለችና (፪) ኢየሩሳሌም ሆይ ምስጋና ጀምሪ መለከትን ንፊ ነጋሪት ጎስሚ ሰላምሽ ታውጇል መዳንሽም ቀርቧል ጌታ ሊጎበኝሽ ከበራፍሽ ቆሟል ያልታደልሽው ሀገር ጌርጌሲዮን ሆይ ለምን ተቃወምሽው አምላክሽን ስታይ የከተማውን በር መዝጊያውን ቆለፈሽ ከሩቅ የሸኘሽው ሲመጣ ሰላምሽ የቢታንያ ድንጋይ አንደበት አውጥቶ ምስጋና ጀመረ አምላኩን ለይቶ ሳርና ቅጠሉ ዘንባባው ሰገደ ፍጥረት ሊያመሰግን አምላኩን ወደደ ህፃን ሽማግሌው ምስጋና ሲያቀርቡ ተቆልፎ ነበር ፈሪሳዊ ልቡ ዛሬም በምስጋና ልባችን ይለወጥ ሆሳዕና ጌታ ይመላለስበት ህፃን ሽማግሌው ምስጋና ሲያቀርቡ ተቆልፎ ነበር ፈሪሳዊ ልቡ ዛሬም በምስጋና ልባችን ይለወጥ ሆሳዕና ጌታ ይመላለስበት "ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር" አሜን https://t.me/mezmur_Debtere https://t.me/mezmur_Debtere
ሆሳዕና በአል በሰላም በጤና እንኳን አደረሳችሁ