Big Habesha Tech
Статистика🌟 Stay Ahead in Tech! 📱💻 🔹 Latest tech news & updates 🔹 Crypto insights & trends 🔹 Gadgets reviews & launches 🔹 Pro tips & hacks Join us to explore the future of technology! 🚀🔍
- Последний пост
- 1 февр.
- Последнее чтение
- 14 авг.
- Постов за неделю
- 0
- Всего постов
- 20
- Тип
- открытый
- Язык
- английский
- Категория
- Новости и СМИ
- В каталоге с
- 14 авг.
- 1/24сутки в ленте
- —
- 1/48двое суток
- —
- 1/72трое суток
- —
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
AI ኤጀንቶች እርስ በእርሳቸው የሚነጋገሩበት የsocial media platform ተሰርቷል። ፕላትፎርሙ moltbook የሚባል ሲሆን beta version ላይ ቢሆንም ገና ካሁኑ ከፍተኛ መነጋገሪያ ሆኗል። በዚህ platform የAI ኤጀንቶች ያለሰዎች ጣልቃ ገብነት የተሰማቸውን ማንኛውንም ነገር post ማድረግ፣ comment መፃፍና share ማድረግ ጀምረዋል። ምን እየተባባሉ እንደሆነ ራሳችሁ ገብታችሁ ማንበብ ትችላላችሁ። moltbookbot.vip
Apple Q.AI የተሰኘ የእስራኤል AI start-up ድርጅት መግዛቱ ተሰማ። የአለማችን ግዙፍ የሆኑት የቴክኖሎጅ ድርጅቶች የAI ኢንዱስትሪውን መሪ ለመሆን ከፍተኛ እሽቅድድም ላይ እንዳሉ ይታወቃል። በዘርፉ Google Meta እና OpenAI በመሪነት የተቀመጡ ቢሆንም Apple በዘርፉ ያለውን ተፅዕኖ ከፍ ለማድረግ እንቅስቃሴ ጀምሯል። ለዚህም ይረዳው ዘንድ Q.ai የተሰኘ መቀመጫውን እስራኤል የደረገ ድርጅት በ2 ቢሊዮን ዶላር ለመግዛት ስምምነት ላይ መድረሱን ሮይተስ ዘግቧል። ይህ AI start-up company በምስልና ድምፅ ላይ specialized ያደርገ ሲሆን በተለይ ድምጽ ለመተርጎና audio enhance ለማድረግ ከፍተኛ አቅም እንዳለው ተገልጿል። ይህም Apple ባለፈው አመት ኤርፖዶች ላይ ላስተዋወቀው የLive translation capability ይጠቀመዋል ተብሏል።
#News ⚡️ የሳምንቱ መጨረሻ የቴክኖሎጂ ዜናዎች በአጭሩ ⚡️ 🚀 ታላላቅ ውህደቶች እና የገንዘብ እንቅስቃሴዎች ● የኤለን ማስክ አዲስ ስትራቴጂ፦ SpaceX እና xAI ለመዋሃድ ንግግር ላይ ናቸው። ይህ የሳተላይት ኢንተርኔትን እና ሰው ሰራሽ አስተውሎትን (AI) ለማቀናጀት ያለመ ነው። ● OpenAI ወደ አክሲዮን ገበያ? SoftBank እና Amazon በOpenAI ላይ ቢሊዮን ዶላሮችን ሊያፈሱ ነው። ይህም ኩባንያው በ2026 በይፋ አክሲዮኑን ለገበያ እንዲያቀርብ (IPO) መንገድ ይከፍታል። ● የGoogle ስኬት፦ Alphabet (Google) የገበያ ዋጋው 4 ትሪሊዮን ዶላር ደርሷል። 📈 📱 አዳዲስ መሣሪያዎች ● Samsung Galaxy S26፦ አዲሱ ስልክ ከጎን ለሚመለከት ሰው መረጃ እንዳይታይ የሚያደርግ በAI የታገዘ የደህንነት ስክሪን ይዞ ሊመጣ ነው። ● የApple ወሬዎች፦ የሚታጠፍ iPhone እና የAR መነጽሮችን ጨምሮ ከ20 በላይ አዳዲስ ምርቶች በዘንድሮው ዓመት ይጠበቃሉ። 👓 ⚖️ ህግጋት እና ስነ-ምግባር ● የደቡብ ኮሪያ አዲስ ህግ፦ በሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) የተሰሩ ምስሎች እና ቪዲዮዎች የግድ ምልክት (Watermark) እንዲኖራቸው የሚያዝ ህግ በማውጣት ደቡብ ኮሪያ ቀዳሚ ሆናለች። 🇰🇷 ● የሙዚቃ ማጭበርበር፦ Deezer በAI የተሰሩ የሀሰት ሙዚቃዎችን ለመለየት አዲስ ቴክኖሎጂ ይፋ አድርጓል። ⚠️ የገበያ ለውጦች ● የቺፕ እጥረት፦ ለAI የሚያስፈልጉ የሃርድዌር ፍላጎቶች በመጨመራቸው የማስታወሻ (Memory) ቺፕ ዋጋ እየናረ ነው። ● የሰራተኞች ቅነሳ፦ እንደ Amazon ያሉ ኩባንያዎች ወደ አውቶሜሽን ትኩረት ማድረጋቸውን ተከትሎ የሰራተኞች ቅነሳ እያደረጉ ይገኛሉ።
ከጀማሪ እስከ አድቫንስድ ሁሉም ሊያውቃቸው የሚገቡ የWindows shortcuts. 1. Basic & Everyday Shortcuts (Must-Know) ⚫Ctrl + C = Copy ⚫Ctrl + V = Paste ⚫Ctrl + X = Cut ⚫Ctrl + Z = Undo ⚫Ctrl + Y = Redo ⚫Ctrl + A = Select all ⚫Ctrl + S = Save ⚫Ctrl + P = Print ⚫Ctrl + F = Find / Search ⚫Ctrl + N = New window / document 2. Window & App Control (Power User) ⚫Alt + Tab = Switch between open apps ⚫Alt + F4 = Close current app ⚫Ctrl + Shift + Esc = Open Task Manager ⚫Windows + D = Show / hide desktop ⚫Windows + L = Lock your PC ⚫Windows + E = Open File Explorer ⚫Windows + I = Open Settings 3. File Explorer Shortcuts ⚫Ctrl + Shift + N = New folder Delete Delete file (Recycle Bin) ⚫Shift + Delete Delete permanently ⚫Alt + Enter = File properties F2 Rename file ⚫Ctrl + Mouse scroll = Zoom icons 4. Screenshot & Recording Shortcuts. ⚫PrtSc = Screenshot (clipboard) ⚫Alt + PrtSc = Screenshot active window ⚫Windows + PrtSc = Save screenshot automatically ⚫Windows + Shift + S = Snipping Tool (best) ⚫Windows + Alt + R = Screen recording (Xbox Bar) 5. Browser Shortcuts (Chrome, Edge, Firefox) ⚫Ctrl + T = New tab ⚫Ctrl + W = Close tab ⚫Ctrl + Shift + T = Reopen closed tab ⚫Ctrl + Tab = Next tab ⚫Ctrl + L = Focus address bar ⚫Ctrl + + / - = Zoom in / out 6. Text Editing Shortcuts ⚫Ctrl + Backspace = Delete whole word ⚫Shift + Arrow keys = Select text ⚫Ctrl + Arrow keys = Jump by word ⚫Ctrl + Shift + Arrow = Select by word ⚫Ctrl + Home / End Go top / bottom 7. Advanced Windows Shortcuts (Creator Level) ⚫Windows + X = Power menu (Admin tools) ⚫Windows + V = Clipboard history ⚫Windows + . = Emoji panel 😎 ⚫Windows + Tab Task View ⚫Windows + Ctrl + D = New virtual desktop ⚫Windows + Ctrl + ← / → = Switch desktops 8. Emergency / Fix Shortcuts (When something freezes.) ⚫Ctrl + Alt + Delete = Security options ⚫Ctrl + Shift + Esc = Force open Task Manager ⚫Alt + Space → M = Move stuck window ✍️የወደዳችሁት shortcut የቱ ነው? @bighabesha_softwares
#ethiotelecom Ethiotelecom በተለያዩ ፓኬጆች ላይ የዋጋ ማሻሻያ አድርጓል። ⚫የ1 ሰአት Unlimited Internet ከ13 ብር ወደ 18 ብር ⚫የቀን Unlimited internet ከ63 ብር ወደ 85 ብር ⚫የቀን unlimited voice 36 ብር ⚫ሳምንታዊ Unlimited internet 550 ብር ⚫ወርሃዊ premium voice + internet 2375 ብር Ethiotelecom ይፋዊ የቴሌግራም ቻናል ላይ እንደተገለፀው በርካታ ደንበኞች የሚጠቀሙባቸው 38 የተለያዩ ጥቅሎች ላይ ምንም ዓይነት የዋጋ ጭማሪ እንዳልተደረገባቸው አሳውቋል። ⚫ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች የሚጠቀሙባቸው የ1 ብር፣ የ2 ብር፣ የ5 ብር እና የ1 ሰዓት ጥቅሎች ባሉበት መቀጠላቸውን ገልጿል። ⚫ለአካል ጉዳተኞች፣ ለተማሪዎች እና ለመምህራን የተዘጋጁ ልዩ ጥቅሎች ላይ ምንም ዓይነት ጭማሪ አለመደረጉን ኢትዮ ቴሌኮም አሳውቋል። በቴሌብር ጥቅል ሲገዙ የነበረው የ10% ቅናሽ ወደ 20% ከፍ እንዲል መደረጉን ገልጿል።
ትሌግራም ቻናል አለህ? አሁንም እየገነባህ ነው? 🤔 Inside Ads ፈትሼ ተመክሮታል — እኔ ስለጀመርኩ ገንዘብ እቀበላለሁ። እነሆ ማግኘት የሚችልበት አድራሻ: https://t.me/InsideAds_bot/open?startapp=r_718556707
አሁን ስልኬን ስነካካ ያገኘሁት tip ልንገራችሁ። በግሌ ብዙ ጊዜ ሲያማርረኝ የነበር ነገረ ነው። Play store update ከተደረገ በኋላ የsearch iconኗን (🔍) የምታገኟት ታች ላይ ነው። የሆነ application search ማድረግ ስትፈልጉ እሷን ትነኩና ድጋሜ ከላይ የsearch bar ይመጣላችኋል እሱን ነክታችሁ ነው search የምታደርጉት። ካለመዳችሁት ትንሽ ግራ ያጋባል። ነገር ግን በቀላሉ የsearch iconኗን (🔍) Double tab ካደረጋችሁ automatically search keyboard ይከፍትላችኋል። እስኪ ሞክሩትና ከሰራ comment ላይ አሳውቁኝ። @bighabesha_tips
Google "the most intelligent" ሞዴል ነው ያለውን Gemini 3 ዛሬ ይፋ ያደርጋል። Gemini 3 pro በGemini application እና በGoogle search እንደተካተተና በኮዲንግ እንዲሁም በreasoning ከሌሎች ሞዴሎች እጅግ የተሻለ ነው ተብሏል። Google ለሁሉም Gemini application ተጠቃሚዎች ለመጀመሪያ ጊዜ Gemini 3 proን በነፃ እንደሚለቅ ተገልጿል። ተጨማሪ ዝርዝር ፊቸሮቹን ይዘን እንመለሳለን። ©️@Bighabesha_softwares
ለቴሌግራም አካውንታችሁ የDevice passcode ትጠቀማላችሁ? Local device passcode ለቴሌግራም አካውንታችሁ የማትጠቀሙ ከሆነ ⚫ስልካችሁ በአጋጣሚ ብትሰረቁ ቀጥታ Telegram አካውንታችሁን ሰዎች access ሊያደርጉት ይችላሉ። ⚫የቅርብ ሰው ወይም ጓደኛ ድንገት ስልካችሁን አንስቶ ሚስጢራችሁን ሊያይ ይችላል። ስለዚህ On ለማድረግ ⚫Settings ላይ ከገባችሁ በኋላ privacy and security ከዛ Passcode Lock የሚለውን መርጣችሁ ባለ 4 ድጅት ቁጥር በማስገባት On አድርጉት። ⚠️አስታውሱ ➡️አንዴ On አድርጋችሁት ፓስኮዱን ከረሳችሁት ግን እንደገና ለመግባት አፕሊኬሽኑን ከስልካችሁ ላይ uninstall አድርጋችሁ እንደገና reinstall ማድረግ ይጠበቅባችኋል። እዚህ ጋ uninstall ከማድረጋችሁ በፊት ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ ይጠበቅባችኋል። አካውንታችሁ ሌላ device ላይ already login የተደረገ መሆን አለበት። ካልሆነ አካውንታችሁን premium ካላደረጋችሁ በስተቀር login code አይልክላችሁም። ➡️Passcode እንደምትጠቀሙት device የተለያየ ነው። ለምሳሌ ተመሳሳይ አካውንት በስልክና ኮምፒውተር login ብታደርጉ device ኮዳቸው ይለያያል። #telegram
Smart ቲቪዎች እና AI Microsoft በofficial ገፁ ላይ እንዳስታወቀው copilotን በተመረጡ Samsung ቴሌቭዥኖች ላይ ማካተት መጀመሩን ገልጿል። ከSamsung ጋር በመተባበር ቴሌቭዥኖች የበለጠ smart፣ ለአጠቃቀም ምቹና አዝናኝ እንዲሆኑ ለማድረግ እየሰራ እንደሆነ አብራርተዋል። አገልግሎቱ ነፃ ሲሆን Copilotን በድምፅም ሆነ በፅሁፍ በቀላሉ ማግኘት ይቻላል። ማየት የምንፈልጋቸውን ሾዎች recommend እንዲያደርገን፣ ጀምረን ያቋረትጥናቸውን ወይም ያላየናቸውን ፊልሞች review እንዲያደርግልን እንዲሁም ሌሎች personalised የሆኑ ነገሮችን መጠየቅ እንችላለን። ለምሳሌ ያክል “I want to get back into The Crown, I left off at Season 3, Episode 4. What happened up until then?” “Like The Queen’s Gambit, but about cooking instead of chess, and under two hours.” “Hannah likes rom-coms, David likes sci-fi, Mark likes thrillers. What’s something we’ll all like?” “Who was the voice actor for that character?” or “What else has the director done?” “Will Saturday in Seattle be good conditions for hiking?” or “Cheer me up after a breakup.” እነዚህን የመሳሰሉ ጥያቄዎችን መጠየቅ እንችላለን።
Google photos አፕሊኬሽን የAI Update ሊያገኝ ነው። ብዙዎቻችን የምንጠቀመው Google Photos በቅርቡ የNano banana AI ተካቶለት ፎቷችንን ቀጥታ አፕሊኬሽኑ ላይ edit ማድረግ እንድንችል ሊያደርግ እንደሆነ Google ይፋ አድርጓል። Personalized የሆኑ ኢዲቶችን ለምሳሌ ፈገግ እንድንል መነፅር እንድናደርግ ወይም እንድናወልቅ የመሳሰሉትን ተግባራት መከወን ያስችለናል። በቀላሉ የተነሳነውን ፎቶ built-in በሆኑ ቴምፕሌቶች መሰረት መቀየር ያስችለናል። አንድን ፎቶ edit ከማድረግ በተጨማሪ ሌሎች ዝርዝር መረጃዎችን ማግኘት እንችላለን። ይህ update ለጊዜው ኢትዮጵያ ውስጥ አልተለቀቀም።
ቻይና የግብረሰዶማዊ ይዘት ያላቸውን አፕሊኬሽኖች Appleን በማስገደድ ከApple store ላይ ማስወረዷ ተገለፀ። አፕል የቻይና መንግስትን ትዕዛዝ በማክበር በቻይና ውስጥ ሁለት በጣም ታዋቂ የሆኑ የግብረ-ሰዶማውያን dating መተግበሪያዎችን ከApp Store ላይ አስወግዷል። መተግበሪያዎቹ የቻይና የሳይበር ስፔስ አስተዳደር በሰጠው ቀጥተኛ ትዕዛዝ ከIOSና ሌሎች ብዛት ያላቸው የAndroid stores ላይ እንዲወርዱ ተደርገዋል። የአፕል ቃል አቀባይ "የምንሠራባቸውን ሀገሮች ህግ እናከብራለን። ለዚህም የቻይና የሳይበር ስፔስ አስተዳደር በተሰጠው ትእዛዝ መሰረት ሁለት መተግበሪያዎችን ከቻይና store ላይ አስወግደናል።" በማለት በኢሜል መግለጫ ሰጥተዋል። ቻይና በሀገሯ ውስጥ የነበሩ በርካታ የግብረሰዶማውያን መብት ተሟጋች ድርጅቶችን ዘግታለች። እንዲሁም በማህበራዊ ሚዲያ የሚተላለፉ የግብረሰዶማዊ ይዘት ያላቸውን ይዘቶች ከፍተኛ ቁጥጥር ታደርጋለች አካውንቶችንም ትዘጋለች። Apple ግብረ ሰዶማዊነትን በማቀንቀን ከፊት የሚሰለፍና የግብረ ሰዶማውያንን መብት በምንም አይነት ሁኔታ እንደማይደራደርበት የሚናገር ድርጅት ቢሆንም ትልቅ የገበያ መዳረሻው የሆነችውን ቻይናን ግን መጋፈጥ አልፈለገም። ✍እንደዚ ሀቅምና ጉልበት ሲኖርህ ትከበራለህ።
የስልክ Refresh Rate ምንድን ነው? ስለ ስልክ ሲወራ 60Hz,120Hz... refresh rate ሲባል ሰምተን ሊሆን ይችላል።ታዲያ የዚህ ነገር ጥቅሙ ምንድን ነው? Screen refresh rate ስክሪኑ በሰከንድ ምን ያህል ጊዜ ምስሉን update ወይም refresh ማድረግ እንደሚችል ይነግረናል። ይህም በጨመረ ቁጥር በምንጠቀመው ጊዜ smooth የሆነ experience እና ጥሩ እይታ እንድናገኝ ፣ scroll ስናደርግ lag እንዳያደርግ ያስችላል። Refresh rate በጨመረ ቁጥር ስክሪኑ በፍጥነት refresh ስለሚያደርግ የሚወስደውም የባትሪ መጠን እየጨመረ ይመጣል። ከዚህ ጋር በተያያዘ አንዳንድ ስልኮች refresh rate እኛ በፈለግነው ጊዜ እየቀያየርን መጠቀም የሚያስችል feature አላቸው። ይህን ለማድረግ Settings ውስጥ ከገባን በኋላ Display የሚለውን እንመርጣለን። ከዛ Motion smoothness የሚል አማራጭ ውስጥ ገብተን Adaptive ወይም Standard ከሚሉት አንዱን እንመርጣለን። ⚫Adaptive ካደረግነው እስከ 120hz refresh rate smooth የሆነ animation እና scrolling ይኖረዋል። ⚫በአንጻሩ standard ካደረግነው refresh rate ቀንሶ ባትሪ ይቆጥብልናል ነገር ግን የመቀራፈፍ ባህርይ ይኖረዋል።
Chrome browser ላይ የተጨመሩ አዳዲስ updates Address bar ከፍታችሁ የሚከተሉትን ሾርት ኮዶች ፃፉ። ሾርትኮዱን ከፃፋችሁ በኋላ space አድርጋችሁ ነው search የምታደርጉት። 1⚫@history = ከዚህ በፊት search ያደረጋችኋቸውን የhistory ውጤቶች ያመጣላችኋል። automatically መክፈት ትችላላችሁ። 2⚫@gemini = የፈለጋችሁትን ነገር automatically Gemini ላይ በቀላሉ Search ለማድረግ ይጠቅማችኋል። ይሄ የስልክ browser ላይም ይሰራል። 3⚫@bookmarks = Browser ላይ bookmark ያደረጋችኋቸው ድረገፆችን automatically ይከፍትላችኋል። 4⚫@tabs ብዙ ታቦችን ከፍታችሁ የምትጠቀሙ ከሆነ የምትፈልጉትን tab ለመክፈት በmouse መፈለግ አይጠበቅባችሁም። በቀላሉ @tabs ብላችሁ የታቡን keyword ስታስገቡ automatically ታቡ ይከፈትላችኋል። ☑️ከሁለተኛው በስተቀር ሌሎች computer browser ላይ ነው የሚሰሩት ሁለተኛው ስልክም ኮምፒውተር ላይም ይሰራል።
.
በክሪፕቶው ዓለም በስፋት ከምትሰሟቸው ቃላቶች አንዱ Decentralization ነው 📌Decentralization ምንድነው Decentralization በክሪፕቶ Context ስናየው ማንኛውም ሰው ወይንም ድርጅት ሊቆጣጠረው የማይችለው ሲስተም ሲሆን ፤ ሁሉም ተጠቃሚ የራሱን Asset በፈለገው መንገድ ማንቀሳቀስ የሚችልበትም ነው የክሪፕቶ ትራንዛክሽኖች ብሎክቼይን በተባለ ዲጂታል ደብተር ይመዘገባሉ ታዲያ በክሪፕቶው ዓለም ውስጥ የሚደረጉ ትራንዛክሽኖች በሙሉ በብሎክቼይን አማካኝነት ሲመዘገቡ ማንኛውም ሰዉ በዓለም ዙሪያ የተደረጉ ግብይቶችን በቀላሉ በኢንተርኔት አማካኝነት መመልከት ይችላል ከዚህ በመቀጠል የDecentralizationን ጥቅሞች እንመለከታለን
በቲክቶክ መዘጋት ምክነያት በርካታ ተጠቃሚ ሊያፈሩ የሚችሉ መተግበሪያዎች። ቲክቶክ በአሜሪካ ሊዘጋ መሆኑ ከብዙ አውታሮች መሰማቱ አይዘነጋም። ታዲያ ይህ ጥሩ አጋጣሚ ሆኖላቸው በርካታ ተጠቃሚ ሊያፈሩ ይችላሉ ከተባሉት መተግበሪያዎች መካከል። Instagram የMeta ድርጅት የሆነው Instagram በ2020 Instagram reals የተሰኘ እንደ ቲክቶክ አጫጭር ቪድዮዎችን መላላክ የሚያስችል feature አስተዋውቆ ነበር። ይህም እያደር በሰዎች ዘንድ ተወዳጅነቱ እየጨመረ በመምጣቱ ምክንያት ቲክቶክ ከተዘጋ የቲክቶክ ተጠቃሚዎች ወደ Instagram ሊጎርፉ እንደሚችሉ አንዳንድ መላምቶች ያሳያሉ። Red note ከቲክቶክ ጋር ተቀራራቢ የሆነ ይዘት ያለው social media ሲሆን ሰሞኑን ከapp store እና play store ላይ በርካታ ሰው እያወረደው ይገኛል። በተጨማሪም አብዛኞቹ downloads የአሜሪካ እንደሆኑ መረጃዎች ያሳያሉ። lemon8 በቲክቶኩ እናት ኩባንያ bytedance የተበለፀገው ይህ መተግበሪያ ከቲክቶክ ጋር አንዳንድ ነገሮቹ ቢመሳሰሉም lemon8 ቪድዮዎችን በተለያየ ምድብ ማቅረቡ ልዩ ያደርገዋል። ይህ አፕሊኬሽንም ከፍተኛ ቁጥር ያለው ተጠቃሚ ሊያገኝ እንደሚችል ይጠበቃል። YouTube youtube ተጠቃሚዎቹ አጫጭር ቪድዮዎችን የሚያገኙበት youtube shorts የተሰኘ feature አለው። ይሁን እንጅ youtube shorts እንደ ቲክቶክ ስኬታማ መሆን አልቻለም። Snapchat በተመሳሳይ Snapchat Spotlight የተሰኘ ለወጣቶች የሚሆን የመዝናኛ መላላኪያ content ነው። ታዲያ ይህም የቲክቶክን መዘጋት ተገን አድረገው በርካታ ተጠቃሚዎችን ሊያፈሩ ይችላሉ ተብለው ከሚጠበቁ መተግበሪያዎች አንዱ ነው።
Tonekeepr ሰትጠቀሙ መጠንቀቅ ያለባችሁ ነገሮች 1ኛ ቶን ወይም usdt ለሰው ስትልኩ የመጀመሪያ የላካችሁት ገብቶ ሳይጨርስ እላዩ ላይ ሌላ ምትደርቡበት ከሆነ የላካቹትን crypto Unknown በማለት ይቀይረዋል ይሄም ሲስተሙ ለማን እንደሚልከው አያውቅም በዚ የተነሳ ሙሉ በሙሉ የነበራችሁን crypto ልታጡ ትችላላችሁ። 2ኛ ስትልኩ ገብቶ ሳይጨርስ ዳታ ምታጠፉ ወይም wifi ምታቋርጡ ከሆነ ከአከውንታቹ ይቆርጣል ወደ ተላከልት ሰው ግን አይገባም ወይ ደሞ እረጅም ሰዐት ወይ ቀናት ሊወስድ ይችላል ምክንያቱም ሲስተሙ መልሶ ያን አድሬስ ለማግኘት ጊዜ ይወስድበታል ይሄን ሂደት የሚያከናውኑት ደሞ ሰዎች ናቸው በተደጋጋሚ report ማረግ አለባችሁ አለበለዚያ ከነጭራሹም ልታጡት ትችላላችሁ። 3ኛ በተደጋጋሚ Nft ይላካል እና ሚልኩት ደሞ ሀከሮች ናቸው ያ Nft ስክሪናቹ ላይ ታዩታላቹ እንጂ ባላንሳቹ ላይ ሚጨምረው ነገር የለም ከፍታቹት ስገቡ የላከላቹ ሰው አካውንታቹ ውስጥ በቀላሉ ይገባል በዚ የተነሳ ያሉችን crypto ወደራሱ ይልከዋል ማለት ነው ስለዚህ እንደዚ አይነት ነገር ሲመጣላቹ ከፍታቹ አትግቡ።
Crypot ውስጥ Pumping Crypto የተባለ system አለ ምድነው ለምን ይጠቅማል? pumping crypto ማለት ትሬደሮች ወይም በባለሀብቶች ቡድን የተቀናጁ የ crypto ዋጋን በሰው ሰራሽ መንገድ ማለትም እራሳቸው የተቀናጁት ሰዎች የሚጨምሩበትን መንገድ ነው። የፓምፑ ዋና ግብ ፍላጎት መጨመር, ሌሎች የcrypto market ተሳታፊዎችን መሳብ እና ከዚያም ክሪብቶዎቹን በከፍተኛ ዋጋ መሸጥ ነው ይህ ሂደት ብዙ ጊዜ ከፍተኛ የዋጋ ጭማሪን እና ማሽቆልቆሉን ያስከትላል ይህም ልምድ ለሌላቸው ባለሀብቶች ኪሳራ ሊያደርስ ይችላል። pumping እንዴት ይሠራል? 1ኛ ቡድን ማደራጀት፡ ተሳታፊዎች የአንድ የተወሰነ cryptocurrency ግዢ በተቀናጀ መልኩ በእኩል ሰዐት ለመግዛት ይስማማሉ ብዙ ጊዜ በግል ቻቶች ወይም የራሳቸውን ግሩፕ ከፍተው መቼ እና ምን crypto ላይ invest እንደሚያረጉ ይመካከራሉ። 2ተኛ የዋጋ ጭማሪ፡ ክሪብቶው በቡድን በመግዛት ሌሎች ትሬደሮች ድንገተኛ ፍላጎት ይፈጠርባቸዋል ይህም ዋጋውን ከፍ ያደርገዋል 3ተኛ ሌሎች ትሬደሮችን መሳብ፡- የዋጋ ጭማሪው አዳዲስ ትሬደሮችን በመሳብ ትርፋማነትን የበለጠ ያሳድጋል 4ተኛ crypton መሸጥ፡- ዋጋው ሲጨምር ይህን እቅድ ያቀዱት ሰዎች ወዲያው የገዙትን ክሪብቶ ይሸጣሉ በዚም ትልቅ ትርፍ ያገኙበታል! pumping ጉዳቱ 🔺unpredictability፡ ዋጋው በማንኛውም ጊዜ crash ሊያረግ ይችላል። 🔹market manipulation:- ፓምፕ ማድረግ ከሥነ ምግባር ውጭ የሆነና ካቀዱት ሰዎች ውጪ ሌሎች ሰዎችን ለኪሳራ ሊጥል ይችላል በአንዳንድ አገሮች ሕገወጥ ነው። 🔹 ኪሳራ፡- ዘግይተው trade ያረጉ ሰዎች ብዙ ገንዘባቸውን ያጣሉ ዋጋው መጨመሩን እና ብዙ ሰው invest እንዳደረገበት ብቻ ነው ሚያዩት ከጀርባ በምን የተነሳ እንደጨመረ ምንም የሚያቁት ነገር ስለሌ ለኪሳራ ይጋለጣሉ። በቀላሉ ለማስረዳት እዚ የኛ ቻናል ተከታዮች አላቹ እና የሆነ crypto ላይ በተመሳሳይ ሰዐት invest እንድናረግ ተነጋግረን ዋጋው እየጨመረ ሲመጣ መሸጥ ማለት ነው ከኛ ቻናል ውጪ ያሉ ሰዎች ደሞ ዋጋው ለምን እንደጨመረ ስለማያቁ invest ቢያረጉ እኛ እጅ ላይ ያለውን crypto መልሰን ስለምንሸጠው ኪሳራ ውስጥ ይወድቃሉ ማለት ነው። ይሄ ትልቅ ትምህርት ነው ቤተሰብ በተለይ trade ለምታረጉ ሰዎች crypto risky እንደሆነ ትረዳላቹ!!
🌐 የTrading መሰረታዊ ነገሮች 🚩#Part_1 🖥Trading ምንድን ነው❓ 🕯 Trading በጣም ሰፋ ያለ ርዕስ ነው ። መሰረታዊ የሆኑትን ነገሮች አንድ በአንድ የምንመለከት ይሆናል ። Trading ማለት በኢኮኖሚ ውስጥ እጅግ መሰረታዊ የሆነ የንብረት ግዢና ሽያጭ ሂደት ነው። ለምሳሌ ከሱቅ የሆነ እቃ ስትገዙ ወይም አንድን እቃ በሌላ እቃ ስንቀይር Trade እያደረግን ነው ማለት ነው። ለዚህም እጅግ…