tgindex
ቦኩ ፈለገ ምህረት ሚዲያ Boku Felege Meheret Media

ቦኩ ፈለገ ምህረት ሚዲያ Boku Felege Meheret Media

Статистика

ይህ የና/ቦ/ደ/ም/ቅ/ሚካኤል ቤ/ክ ፈለገ ምህረት ሰንበት ትምህርት ቤት ብቸኛው አጠቃላይ መረጃ እና ትምህታዊ ሀሳቦች መስጫ ነው።

Последний пост
10 авг.
Последнее чтение
14 авг.
Постов за неделю
0
Всего постов
24
Тип
открытый
Язык
ti
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
334
−1 за 3 дн.
Сутки
0
0,00%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
97
22 постов
Вовлечённость
29,0%
к подписчикам
Постов в день
0,0
всего 24
Упоминаний
0
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
82
1/48двое суток
93
1/72трое суток
101

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • Channel name was changed to «ቦኩ ፈለገ ምህረት ሚዲያ Boku Felege Meheret Media»

  • Channel name was changed to «ቦኩ ፈለገ ምህረት ሚዲያ»

  • без подписи

  • “መልእክተ ቅዱስ ፓትርያርክ" በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሓዱ አምላክ፣ አሜን ! በሀገር ውስጥና በመላው ዓለም የምትገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እምነት ተከታዮች በሙሉ! የሰውን ወገን ለማዳን የልጁ ማደሪያ ትሆን ዘንድ ድንግል ማርያምን የመረጠ መፍቀሬ ሰብእ እግዚአብሔር ኣምላካችን እንኳን ለሁለት ሺሕ ዓሥራ ስምንት ዓመተ ምሕረት ጾመ ማርያም ኣደረሰን ኣደረሳችሁ! “ወእመሰ ታፈቅሩኒ ዕቀቡ ትእዛዝየ፡- ከወደዳችሁኝስ ትእዛዜን ጠብቁ" (ዮሐ.14፥15)፤ ፍቅር የሕያዋን ኣካላት ረቂቅ መገናኛ ነው፣ ሕያዋን ኣካላት በውጫዊው ግዙፍ ኣካላቸው በተወሰኑ ጊዜያትና ቦታ ይገናኛሉ ፤ ስለ ጋራ ጉዳያቸውም በጋራ ይመክራሉ፤ ይበልጥም ይቀራረባሉ፡፡ ይሁንና የሕያዋን ኣካላት ግንኙነት በኣካል በጊዜና በቦታ ብቻ የተወሰነ ኣይደለም፣ በፍቅረ መንፈስ ተገናኝተውም ይግባባሉ፣ ከኣካላዊ ግንኙነት በላይ የበለጠም ይኸው ፍቅረ መንፈስ ነው፤ ከዚህ ኣንጻር እግዚአብሔርንም ማግኘት የምንችለው በዚሁ ፍቅረ መንፈስ ሆነን በእምነት ዓይን ነው! ይህም በመሆኑ ሓዋርያው ቅዱስ ዮሓንስ በመልእክቱ “በፍቅር የሚኖር በእግዚአብሔርይኖራል፣ እግዚአብሔርም በእርሱ ይኖራል" በማለት ያስተምረናል፣ (1ዮሐ. 4፥16) ይህም ማለት ከሱ ጋር በፍቅር ስንገናኝ፤ እሱም በኛ፣ እኛም በእሱ የመኖሩ ኩነት ይፈጠራል ማለት ነው፡፡ የተወደዳችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን ምእመናንና ምእመናት! ጌታችን “አፍቅሮ ለእግዚአብሔር ኣምላክከ፤- አምላክህን እግዚአብሔርን ውደደው" በማለት በፍጹም ልባችን እንድንወደው፣ እንደዚሁም ራሳችንን በምንወድበት መጠን እርስ በእርሳችን እንድንዋደድ ማዘዙን እናውቃለን፤ የመውደዳችን መለኪያ ሚዛንና መገለጫ ምልክትም ትእዛዙን ማክበርና መጠበቅ እንደሆነ “ብትወዱኝስ ትእዛዜን ጠብቁ” በማለት ኣስተምሮናል ከዚህ ኣኳያ ጌታን መውደድ ማለት ትእዛዙን በመጠበቅ የሚገለጽ ግዙፍ ነገር እንጂ ምናባዊና የማይታይ ድብብቆሽ ነገር ኣይደለም ማለት ነው፣ ጌታችንን የመውደድ ነገር ትእዛዙን በመጠበቅ የሚገለጽ ከሆነ ትእዛዙ ምንድን ነው? የሚለውን ማየት ኣስፈላጊ ይሆናል፤ ትእዛዙን በጥቅል ስናይ እግዚአብሔርንና ባልንጀራን በመውደድ እንደሚጠቃለል ራሱ ጌታችን ኣስገንዝቦናል፣ በተለይም በባልንጀራችን ላይ የምንከተለው መውደድ ከላይ እንደተገለጸው “እንደራስህ ኣድርገህ ውደድ" ተብለ በግልጽ ተቀምጦኣል፤ የሰው ባልንጀራ እነማን ናቸው? በሕይወት ያሉት ናቸው? ወይስ የሞቱት? ወገን ዘመድ? ወይስ የሰው ወገን በሙሉ የሚለውንም ማወቅ ኣስፈላጊ ነው፡፡ ጌታችን ነገሩን በዚህ ደረጃ ለያይቶ ኣላስቀመጠም፣ ለምን? ቢባል ባልንጀራ ማለት የተወሰነን የማኅበረ ሰብ ወገን የሚያሳይ ሳይሆን መላውን የሰው ወገን የሚገልጽ በመሆኑ፤ እንደዚሁም የሞቱም ሆኑ ያለነው ሁላችን በእሱ ፊት ሕያዋንና እርስ በእርሳችን ባልንጀሮች በመሆናችን ነው፤ በመሆኑም መዋደዳችንም ሆነ መከባበራችን በሕይወተ ሥጋ ሳለን ብቻ ሳይሆን ከዚያም በኋላ እስከ በሌለው ዕድሜ በመሆኑ ጌታችን በጊዜ በቦታና በከፊል ለይቶ ኣላስቀመጠም፡፡ የተወደዳችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን ምእመናንና ምእመናት ! ከነሐሴ ፩ ቀን ጀምሮ ለ፲፭ ቀናት የምንጾመው የጾመ ማርያም መነሻ ምክንያቱ የእግዚአብሔርትእዛዝና ፍቅር ነው፣ እግዚአብሔር ሰውን በኣጠቃላይ በተለይም ደግሞ እንደፈቃዱ የኖሩ ቅዱሳንን እንድናከብርኣዞናል ክቅዱሳን ፍጥረታት መካክል ደግሞ ቅድስት ድንግል ማርያም የመጀመሪያውን ደረጃ ትይዛለች፤ ይህም በመሆኑ ከፍጥረት ወገን ከሏ ክብር የሚደርስ ባለመኖሩ ከሁሉም ኣብልጠን እናክብራታለን፤ ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በዚህ ደረጃ የድንግል ማርያምን ክብር ስትገልጽ ክእግዚአብሔርና ለባስያነ እግዚአብሔር ክሆኑ ቀደምት ኣበው ተምራ ነው! በአራተኛው መቶ ክፍለ ዘመን የነበረው ዕውቁ ቅዱስና ዓለም ዓቀፋዊው አባት ቅዱስ ኤፍሬም የድንግል ማርያምን ክብር! ቅድስና እና ልዕልና ሲናገር “ይእቲ ተዓቢ እምኪሩቤል፡ ወትፈደፍድ እምሱራፌል፣ እስመ ኮነት ታቦተ ለአሓዱ ዘእምቅድስት ሥላሴ- እሷ ከኪሩቤል ትበልጣለች! ከሱራፌልም ትልቃለች፣ ከቅድስት ሥላሴ ኣንዱ ለሆነው ታቦት ወይም ማደሪያ ሆናለችና" በማለት አስተምሮናል፡፡ በመሆኑም ለስሟ መታሰቢያ በሆነው በዚህ ጾም ድንግል ማርያምን በዚህ ደረጃ ስናክብርትእዛዙን እንጠብቃለን፤ ትእዛዙን በመጠበቃችን ደግሞ እሱን መውደዳችንን እናረጋግጣለን ! እኛ ድንግል ማርያምን እንድንወዳት "እናታችሁ'' ብሎ እንዳዘዘ፣ እሷም ልትወደን “ልጆችዅ ተብላ ታዛለችና ስለኛ ትጸልያለች፡፡ በጸሎቷም ከመከራ ትታደገናለች፤ በኣጠቃላይ በእግዚአብሔር' በቅዱሳንና በእኛ መካከል ያለው ግንኙነት በዚህ ትእዛዝና ፍቅር በትዕይንተ ዓለም ባለች ቤተ ክርስቲያን ዘንድ የተሳሰረ ነው፡፡ ስለሆነም በዚህ የጾመ ፍልሰታ ለማርያም ሱባዔ የተራቡትን በመመገብ፣ የታረዙትን በማልበስ፣ የተጣሎትን በማስታረቅ፤ የታመሙትንና የታስሩትን በመጠየቅ፤ ቅዱስ ቍርባንን በመቀበልና ለኃጢኣታችን የንሥሐ ሥርየትን በመለመን ሱባዔውን ልናሳልፍ ይገባል፡፡ በመጨረሻም በሀገራችንም ሆነ በዓለም ዙሪያ ከባድ ስጋት የሆነው የፍጥረት ኣውዳሚ ጦርነትን በመለኮታዊ ጥበቡና ሥልጣኑ እንዲያስቆምልን በቅን ልቡና፤ በትሑት ሰብእና ሆነን እግዚአብሔርን በዚህ ሱባዔ እንድንጠይቀው ኣደራ ጭምር ኣባታዊ መልክታችንን በእግዚአብሔር ስም እናስተላልፋለን፤ የተባረከና የተቀደስ ጾም ያድርግልን፤ እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቦችዋን ይባርክ! ወስብሐት ለእግዚአብሔር፣ አሜን! አባ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእስ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘኣኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ነሐሴ 1 ቀን 2018 ዓ.ም አዲስ አበባ፤ ኢትዮጵያ

  • без подписи

  • без подписи

  • без подписи

  • без подписи

  • የምሥራቅ ሸዋ ሀገረስብከት ሰ/ት/ቤቶች አንድነት በተጠናቀቀው የ2018 ዓ.ም የአገልግሎት አፈፃፀም ዙሪያ ለብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ የምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ የዝዋይ ሐመረ ብርሃን ቅ/ገብርኤል ገዳም የካህናት ማሰልጠኛ እና መንፈሳዊ ኮሌጅ የበላይ ጠባቂ ጋር  በ27/11/2018 ዓ.ም ውይይት አደረገ ። የአንድነቱ ሥራ አመራር በተጠናቀቀው በጀት ዓመት የተሰሩ  ዋና ዋና ስራዎችን እና ያገጠሙ ተግዳሮቶች የተወሰዱ የመፍትሔ እርምጃዎች እንዲሁም የ2019 ዓ.ም ዋና ዋና እቅድ  ለብፁነታቸው የቀረበ ሲሆን ፤ አንድነቱ ከሀገረ ስብከቱ ከብፁዕ ሊቀ ጳጳሱ ጀምሮ በክቡር ሥራ አሰኪያጅ እና በክቡር ም/ሥራ አስኪያጅ እየተደረገ ያለውን ድጋፍ ምስጋና አቅርቧል። ብፁዕ አባታችን አቡነ ጎርጎርዮስም የተሰሩ ስራዎችን መልካም እና ተስፋ ሰጪ ናቸው ነገር ግን ብዙ ስራ ከአንድነቱ ይጠበቃል ሲሉ አሳስበው አባታዊ መመሪያ ሰጥተዋል። በመርሐግብሩ ላይ የሀገረ ስብከታችን ዋና ሥራ አስኪያጅ መልአከ ሣሕል ቀሲስ ነጋሽ ሀብተ ወልድ የሀገረ ስብከቱ ም/ስራ አስኪያጅ መጋቢ ጥበባት ቀሲስ ጌቱ ሞቲ የሀገረ ስብከቱ የሰ/ት/ቤቶች ማደረጃ መምሪያ ሀላፊ ሊቀ ካህናት ቀሲስ ሻውል ታዬ ተገኝተዋል። **** መረጃው ፡-የምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት ሰ/ት/ቤቶች አንድነት ነው።

  • без подписи

  • без подписи

  • без подписи

  • без подписи

  • без подписи

  • без подписи

  • без подписи

  • без подписи

  • без подписи

  • የ2018 ዓ.ም 4ኛ እና 8ኛ ክፍል የሚኒስትሪ ፈተና እና የ10 ክፍል ማትሪክ ፈተናን አስመልክቶ ከመንበረ ጵጵስና ርዕሰ ከተማ ወረዳ ቤተ ክህነት ሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት የተላለፈ የምስጋና መልዕክት፡፡ እንውደሚታወቀው ሀገረ ስብከት አቀፍ ፈተና  ከላይ ለተጠቀሱት ክፍሎች ተዘጋጅቶ በዛሬው እለት ሐምሌ 26/11/2018 ዓ.ም ሲሰጥ መዋሉ ይታወቃል፡፡ በዚህም ፈተና ሂደት ከሀገረ ስብከቱ ልዑካን ጀምሮ እስከ አጥቢያ ሰንበት ትምሀርት ቤት በፋታኝነት እና በሱፐር ቫየዘርነነት እንዲሁም ፈተናውን ለመፈተን የጠዋቱን ዝናብ በመታገስ ፈተናው በተሳካ ሁኔታ እንዲጠናቀቅ ላደረጋችሁ አካላ በመሙሉ ልባዊ ምስጋናችንን እያቀረብን ይበልጥ ፈተናው አንዲሳካ የመፈተኛ ቦታ በመፍቀድ ትልቁን ድርሻ የተወጣችሁ የናዝሬት ደብረ ፀሐይ ቅድስተ ማርያም ካቴድራል ሰበካ ጉባኤ እና የትምህርት ቤቱ ስራ አስኪጅ እንዲሁም የፍሬ ሃይመኖት ሰንበት ትምሀርት ቤት አመራሮች የጥበቃ አካት ምስጋናችን ከልብ ይድረሳችሁ እያልን ተማሪዎች የተፈተናችሁተ ፈተና ታርሞ አስኪደርሳችሁ በትዕግስት እንድትጠባባቁን መልዕክታችንን እናስተላልፋለን፡፡ መንበረ ጵጵስና ርዕሰ ከተማ ወረዳ ቤተ ክህነት ሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት ጽ/ቤት

  • ❗️❗️ማሳሰቢያ /Hubachiisa❓ ለሁሉም አድባራት እና ገዳማት ሰንበት ት/ቤት ሚኒስትሪ ፈተና ተፈታኝ ተማሪዎች በሙሉ። Barattoota Manneen Amantaa Qormaata Ministirii Fudhatan hundaaf. ሐምሌ26/2018 ዓ.ም አኅጉረ ስብከት አቀፍ  የሚኒስትሪ ፈተና ለ4ኛ፣ 8ኛ እና 10ኛ ክፍል ተማሪዎች ሙሉ ቀን ማለትም #ጠዋት 2:30_6:00 #ከሰዓት 7:30_10:30 ይሰጣል። የመፈተኛ ቦታ:- በአዳማ ደ/ፀ ቅድስት ማርያም ካቴድራል ትምህርት ቤት Adoolessa26/2018 Qorumsa Ministrii akka biyya Lallabaatti qophaa'ee kutaa 4ffaa,8ffaa fi 10ffaa guyyaa guutuu jechuun #Ganama 2:30_6:00 #Guyyaa 7:30_10:30 ni kennama. Iddoo Qormaata:-  Mana Barumsaa Kaatediraala Dabra Tsehay Qulqulleettii Maariyaam Adaamaa. ❗️ማንኛውም ተማሪ ከ 2:00 በፊት በመፈተኛ ክፍል በመገኛት የእራሱን ሙሉ መረጃ እና መፈተኛ ክፍል (Exam Room) በማያት በመፈተኛ ክፍል እንድትገኙ በጥብቅ ለማሳሰብ እንወዳለን። Barataan kamiiyuu dursee ganama sa'aatii 2:00  argamuun Kutaa qormaata fi oddeefanno isaa guutuu ilaalun akka kutaa qorumsaatti argamuu cimsinee sin akkeekachisna. 👉በአረፍት ሰዓት ተማሪዎች በት/ቤቱ ቅጥረ ጊቢ መውጣት እና ወደ ቤት በፊጹም አይፈቀድም/ Yeroo Boqonnaa Barataan kamuu mooraa M/barumsaa keessa bahuun gara mana deemun goonkuma dhoorkadha. ተማሪዎች ወደ ፈተና ስመጡ/Barattotni gara qormaata yoo dhufan ✏️ እርሳስ እና ላፕስ ይዘው መምጣት ይጠበቅባችኋል/Irsaasii fi haqxuu qabatani dhufuu qabu 🍱ፈተነ ሙሉ ቀን እንደ መሆኑ መጠን #ምሳ(ምግብ) ይዛችሁ እንድትመጡ/Qormaanni guyyaa guutuu waan ta'eef  #laaqana(nyaata) keessan qabatani akka dhuftan. 🥞☕️ምሳ ይዛቹ መምጣት ለማትችሉ/ Warraa Laaqana Qabatanii dhufuu hin dandeenyef በእለቱ ምግብ ፣ሻይ፣ቡና፣ውሃ እና ፍሬሽ ምግም በተመጣጣኝ ዋጋ ስለ ተዘጋጀ ተማሪዎች በእረፍት ሰዓት ከግቢ ውስጥ ሳይወጡ እዛው መጠቀም እንድችሉ ተድርጎ ተዘጋጅተዋል። Sooranni fi dhugaatin garagaraa Shaayii, Bunni, Bishaan fi nyanni fireeshin gatii madaalawan waan qophaa'eef mooraa keessaa osoo hin bahiin fayyadamuu dandeessu. ተማሪዎች ወደ ፈተና ቦታ ምንም አይነት የኤሌክትሮንክ እቃዎች ይዘው ምጣት በፍጹም የተከለከለ ነው/ Barattootni meeshaa electrooniksii garagaraa qabatani gara qoormaata dhufuun goonkuma dhoorkadha. 👇👇👇👇👇👇👇👇 የመንበረ ጵጵስና ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት/Tokkumaa Manneen Barnoota Dilbataa Magaalaa Adaamaa. የሰ/ት/ቤቶች አንድነት የማኅበራዊ የትስስር ገጾችን ቤተሰብ ይሁኑ! 👉 Telegram https://t.me/adamaunity 👉 Tiktok https://www.tiktok.com/@adama_unityss 👉 Facebook https://www.facebook.com/profile.php?id=61586186442185