tgindex
Condominuim Market in Addis Ababa

Condominuim Market in Addis Ababa

Статистика

በዚህ የቴሌግራም Chanel ከ10,000 ተከታይ በላይ ባለው facebook page በቀን እስከ 500 ሰው ጎብኚ ብለው condoaddis.etsecurities.com በማስታወቂያ ክፍያ ቤትዎን እና መኪናዎን መሸጥ ፣ ማከራየት ይችላሉ ኮሚሽን መክፈል ለማይፈልጉ buy ads here https://telega.io/c/condoaddis 0913587955 መረጃ ለመላክና ለጥያቄ @antget1

Последний пост
12 авг.
Последнее чтение
15 авг.
Постов за неделю
2
Всего постов
21
Тип
открытый
Язык
und
Категория
Новости и СМИ (по похожим)
В каталоге с
14 авг.
Подписчики
3 605
+6 за 1 дн.
Сутки
0
0,00%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
1 445
20 постов
Вовлечённость
40,1%
к подписчикам
Постов в день
0,3
всего 21
Упоминаний
2
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
334
1/48двое суток
382
1/72трое суток
412

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • የውጭ ዜጎች በአዲስ አበባ ቤት ለመግዛት 150 ሺህ ዶላር ያስፈልጋቸዋል የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር የውጭ ዜጎች በኢትዮጵያ የመኖሪያ ቤት ባለቤት ሊሆኑ የሚችሉበትን የአፈጻጸም ማዕቀፍ ይፋ ማድረጉን ተከትሎ፣ በአዲስ አበባና ሸገር ከተሞች የሚገዙ የውጭ ዜጎች ቢያንስ 150 ሺህ የአሜሪካ ዶላር በሕጋዊ የባንክ መስመር ማቅረብ እንደሚጠበቅባቸው ተገለጸ። የአዲሱ ማዕቀፍ መሠረት የሆነው የውጭ ዜጎች የመኖሪያ ቤት ባለቤትነት መብት አዋጅ ቁጥር 1388/2025 ሲሆን፣ አዋጁ የውጭ ዜጎች በኢትዮጵያ የመኖሪያ ቤት እንዲገዙ የሚያስችል አዲስ የሕግ ማዕቀፍ ዘርግቷል። መመሪያው እንደሚያስቀምጠው የሚፈለገው የውጭ ምንዛሬ መጠን በአካባቢው የልማት ደረጃ መሠረት የሚለያይ ሲሆን፣ በአዲስ አበባና ሸገር 150 ሺህ ዶላር፣ በተለያዩ የክልል ከተሞች 120 ሺህ ዶላር፣ በአፋር፣ ቤኒሻንጉል ጉሙዝና ጋምቤላ 100 ሺህ ዶላር የዝቅተኛ መጠን ገደብ እንደተቀመጠ ተገልጿል። ይህ ገደብ ከኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ፈቃድ ካላቸው የውጭ ባለሀብቶች የተለየ አተገባበር እንዳለውም ተመልክቷል። አዋጁ የውጭ ባለሀብቶችን ከመደበኛው የ150 ሺህ ዶላር መስፈርት የተለየ ሁኔታ ውስጥ ያስቀምጣል። አንድ ቤት ብቻ አዲሱ ማዕቀፍ የውጭ ዜጎች የመኖሪያ ንብረት ባለቤትነትን በቁጥርም ይገድባል። በአጠቃላይ አንድ የውጭ ዜጋ አንድ የመኖሪያ ቤት ብቻ እንዲኖረው ተደንግጓል። የሚገዛው ንብረትም በኢትዮጵያ የመሬት ሕግ መሠረት በሊዝ መሬት ላይ የተገነባ መኖሪያ ቤት መሆን አለበት፤ የመሬት ባለቤትነት ግን ለውጭ ዜጎች አይሰጥም። በተጨማሪም በመንግሥት ድጎማ የተገነቡ እና ለዜጎች ተብለው የተዘጋጁ የኮንዶሚኒየም ቤቶች በዚህ የባለቤትነት መብት ሊገዙ እንደማይችሉ ተቀምጧል። ከኢትዮጵያ ባንኮች ብድር አይፈቀድም የውጭ ዜጎች የመኖሪያ ቤት ግዢን ለመፈጸም ከኢትዮጵያ የፋይናንስ ተቋማት ብድር መውሰድ አይችሉም። ይህም የግዢው ገንዘብ ከውጭ ምንዛሬ ምንጭ በሕጋዊ የባንክ ሥርዓት ወደ ኢትዮጵያ መግባቱን የሚያረጋግጥ መስፈርትን ያጠናክራል። የቤቱን ንብረት ማከራየት ይቻላል የውጭ ባለቤቶች የገዙትን ቤት ለመኖሪያ ዓላማ ማከራየት ይችላሉ። ነገር ግን ንብረቱን እንደ ካፌ፣ ቢሮ ወይም ሌላ የንግድ ቦታ መጠቀም በዚህ ማዕቀፍ አይፈቀድም። ከዚህ በተጨማሪ ከንብረቱ ኪራይ ወይም ከሽያጭ የሚገኝ ገቢ በሕጋዊ የውጭ ምንዛሬ ሥርዓት መሠረት ወደ ውጭ አገር ሊተላለፍ ይችላል። የቪዛ እና የመኖሪያ ጥቅሞች በሕጋዊ መንገድ ቤት የገዙ የውጭ ዜጎች ከንብረት ባለቤትነቱ ጋር ተያይዞ የመኖሪያ ፈቃድ ወይም እስከ አምስት ዓመት የሚቆይ ብዙ ጊዜ መግቢያና መውጫ ቪዛ ሊያገኙ ይችላሉ። በተጨማሪም የባለቤትነት መብቱ በ“Principle of Reciprocity” መርህ የተመሠረተ ሲሆን፣ የውጭ ገዢው ዜግነት ያለበት አገር ለኢትዮጵያውያን ተመሳሳይ የመኖሪያ ንብረት ባለቤትነት መብት መፍቀዱ ከሚታዩ መስፈርቶች አንዱ ነው። አዲሱ ማዕቀፍ በአንድ በኩል የውጭ ምንዛሬ ፍሰትን ለማሳደግ እና የሪል እስቴት ዘርፉን ለውጭ ካፒታል ለማስፋት የታቀደ ሲሆን፣ በሌላ በኩል የውጭ ገዢዎች በሀገር ውስጥ ባንኮች ከሚሰጡ ብድሮች ይልቅ የውጭ ምንዛሬ እንዲያስገቡ በማስገደድ በውጭ ምንዛሬ ገበያው ላይ ተጨማሪ ፍሰት ለመፍጠር ያለመ ነው። የአዋጁ መሠረታዊ ማዕቀፍ ከጥቅምት 2 ቀን 2025 ጀምሮ ተፈጻሚ ሆኗል። https://condoaddis.etsecurities.com/2026/08/12/foreigners-must-bring-150000-to-buy-a-home-in-addis-ababa-under-new-directive/

  • видео или голосовое, без подписи

  • https://tglink.io/a2c45087aa1f7d

  • 29 июл.1 371412

    በአከራይ ተከራይ ውል እድሳት ፈፅሞ የተከለከሉ ጉዳዮች? ✍ የመኖሪያ ቤት ኪራይ ውል ሳያስመዘግቡ መከራየትና ማከራየት፤ ✍ የውል እድሳት ምዝገባን አለመፈጸም በአከራይ ወይም ተከራይ ቸልተኝነት ከሐምሌ  1 ቀን ጀምሮ የተጀመረውን አዲስ የመኖሪያ ቤት ኪራይ ውል እድሳት ምዝገባ ሳያከናውን መቅረት ወይም መሸሽ አይቻልም።  ✍ የመኖሪያ ቤት ኪራይ ውል ዕድሳት አለማስመዝገብ፤ ✍ ሕገ-ወጥ የዋጋ ጭማሪ ማድረግ በከተማ አስተዳደሩ       ከተቀመጠው የ11.5% ዓመታዊ የቤት ኪራይ ጭማሪ ጣሪያ በላይ መጨመር ወይም በየምክንያቱ ዋጋ ማናር በጥብቅ የተከለከለ ነው። ✍ አዋጁ ከሚፈቅደው ውጪ የውል ዘመን ሳይጠናቀቅ ከቤት ማስወጣት፤ ✍ በአዋጁ የተቀመጠውን የማስታወቂያ ወይም የማስጠንቀቂ ጊዜ ሳይሰጥ ውል ማቋረጥ፤ ✍ አዋጁ ላይ ከተቀመጠው መጠን በላይ የቅድመ ክፍያ       እንዲፈጸም ማስገደድ፤ ✍ በባንክ ወይም በሌላ ሕጋዊ የሆነ የኤሌክትሮኒክስ መንገድ የመኖሪያ ቤት ኪራይ ክፍያ አለመፈጸም፤ ✍ ቀደም ሲል ሲከራይ የቆየ የመኖሪያ ቤት ወይም ግንባታው ሙሉ ለሙሉ የተጠናቀቀ አዲስ መኖሪያ ቤት ያለአገልግሎት  እንዲቀመጥ ማድረግ፤ ✍  የመንደር ወይም የ«ልዩ» ውል ማሰር፦ በየደረጃው በሚገኙ የቤቶች ልማትና አስተዳደር ፅህፈት ቤቶች ሳይመዘገብና ዕውቅና ሳይሰጠው፣ በአከራይና ተከራይ መካከል ብቻ የሚደረግ ማናቸውም ዓይነት "የመንደር ውል" ወይም "የውስጥ ስምምነት" በሕግ ፊት ዋጋ የለውም፤ የተከለከለም ነው። ✍ በጋራ መኖሪያ ቤቶች (ኮንዶሚኒየም) አካባቢ የሚደረጉ ሕገ-ወጥ ውሎች በኮንዶሚኒየም መንደሮች ውስጥ የሚገኙ መኖሪያ ቤቶችን  ያለ ቢሮው ዕውቅናና ምዝገባ በሕገ-ወጥ መንገድ ማከራየትና ውል መዋዋል የተከለከለ ነው። ከላይ የተጠቀሱ ክልከላዎችን የፈጸመ አስተዳደራዊ ቅጣት ይጠብቀዋል፡፡ " ሕጋዊ ምዝገባን ባለመፈጸም ራስዎን ለሕግ  ተጠያቂነትና   ለአላስፈላጊ ቅጣት አያጋልጡ!" Condoaddis.com

  • 29 июл.1 0862

    видео или голосовое, без подписи

  • 29 июл.1 1022

    видео или голосовое, без подписи

  • 19 июл.1 5963

    https://youtu.be/IFrcCXtnFvM?si=7yGvBDGkChDoQnfn

  • 13 июл.1 84111

    "የጋራ መኖሪያ ቤቶችን ድሮ በነበረው ዋጋ ለማስረከብ እንቸገራለን"ከንቲባ አዳነች አቤቤ ​ የጋራ መኖሪያ ቤቶች (ኮንዶሚኒየም) ተረካቢዎች ወቅቱን ያገናዘበና ምክንያታዊ የሆነ ዋጋ መክፈል ግድ እንደሚላቸው የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ። ከንቲባዋ ትናንት በከተማው ምክር ቤት ተጠይቀው እንደተናገሩት፥ ቤቶቹን የዛሬ 20 ዓመት በነበረው የዋጋ ተመን ማስተላለፍ የማይቻል ቢሆንም፣ አሁንም ዋጋው ተመጣጣኝ (Affordable) እንዲሆን ጥረት እየተደረገ ይገኛል። ማንበብ ይቀጥሉ👇 ​condoaddis.com

  • 12 июл.1 7552

    видео или голосовое, без подписи

  • 12 июл.1 8512

    8ኛ ዙር የ40/60 እና 2ኛ ዙር ካፒታል ኘሮጀክት የንግድ ቤት ጨረታ 2ኛ ደረጃ አሸናፊዎች ሸያጭ ውል ጥሪ ማስታወቂያ የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ሀምሌ 4 ቀን 2018 ዓ.ም Condoaddis.com

  • 9 июл.1 76111

    https://youtu.be/P6jElvUjMyg?si=aGdrnZXvC7XIkhiq

  • 4 июл.1 88853

    በአዲስ አበባ የቤት ኪራይ ቁጥጥር አዋጅን ተከትሎ ተከራዮች «ቤት ልቀቁ» የሚል ጫና እየበረታባቸው መሆኑን ገለጹ:: በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኙ የተለያዩ የኮንዶሚኒየም ሳይቶች የሚኖሩ ነባር ተከራዮች፣ አዲሱን የቤት ኪራይ ቁጥጥር አዋጅ ተገን በማድረግ በአከራዮች አማካኝነት «ቤት ልቀቁ» የሚል ከፍተኛ ጫና እና ማስጠንቀቂያ እየደረሳቸው መሆኑን በምሬት በመግለጽ ላይ ናቸው። መንግሥት በቅርቡ ባወጣው አዋጅ መሠረት በአከራይና ተከራይ መካከል የሚደረገው የዋጋ ጭማሪ በተወሰነ ልክ ብቻ መሆን እንዳለበት ቢደነግግም፣ በርካታ አከራዮች ግን በተቀመጠው ሕጋዊ የዋጋ ገደብ መሠረት ማከራየት ስላልፈለጉ ነባር ተከራዮችን አስወጥቶ በአዲስና ከፍ ባለ ዋጋ ለሌሎች ማከራየትን እንደ ዋነኛ አማራጭ እየወሰዱት ይገኛል። ተከራዮች እንደሚሉት ከሆነ፣ አከራዮች ይህንን ሕጋዊ የዋጋ ገደብ ለመሸሽና ተከራዮችን ለማስገደድ የተለያዩ ምክንያቶችን በመደርደር ላይ ናቸው። «ራሴ ልገባበት ነው» ወይም «እህቴ/ወንድሜ ሊኖሩበት ነው» የሚሉ የቤተሰብ ሰበቦችን በማቅረብ ተከራዮች በአስቸኳይ እንዲለቁ በማድረግ ላይ እንደሚገኙ ተነግሯል። በተለይም የሰኔ ወር መጠናቀቅን ተገን በማድረግ፣ አሮጌውን ውል ለማደስ ፈቃደኛ ያልሆኑና አዲስ ተከራይ በከፍተኛ ዋጋ ለማስገባት የሚፈልጉ አከራዮች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩ በሺዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎችን ለእንግልትና ለቀውስ እየዳረገ ነው። በከተማዋ የተፈጠረው ይኸው ሕገ-ወጥ አሠራርና ጫና ከቁጥጥር ውጪ ከመሆኑ በፊት፣ የሚመለከተው የመንግሥት አካል በአስቸኳይ ጣልቃ እንዲገባና መፍትሔ እንዲሰጣቸው ተከራዮች ጠይቀዋል፡፡ Website| TikTok | YouTube | Facebook | LinkedIn

  • 29 июн.1 7006

    🔍 ቤት እየፈለጉ ነው? 🏠 ቤት እያከራዩ ነው? 💼 ወኪል (ደላላ) ነዎት? KIRAYE ለአዲስ አበባ ተከራዮች እና አከራዮች ፍፁም መፍትሄ ይዞ መጥቷል! 🇪🇹 በየቀኑ ከሚሰማው የቤት ኪራይ ማጭበርበር እና ውክቢያ ራስዎን የሚጠብቁበት የመጀመሪያው ታማኝ መድረክ፦ ✅ Verified Profiles — ሁሉም ተጠቃሚ በማንነት መታወቂያ የተረጋገጠ ነው ⭐️ Trust Score— ከማን ጋር እንደሚስማሙ ከፊርማ በፊት አስቀድመው ይወቁ 📄 Digital Agreement — ህጋዊ የኪራይ ውል በስልክዎ በሰከንዶች ውስጥ ያዘጋጁ 🔒 Secure Deals — ከአሰልቺ ሩጫ እና ከማጭበርበር ሙሉ በሙሉ ይገላገሉ 👉 kiraye-xy6c.vercel.app ፍጹም ነፃ ነው — ዛሬውኑ ይመዝገቡ! 💡 ቤት ለሚፈልግ ወይም ለሚያከራይ ወዳጅዎ ሼር በማድረግ ከማጭበርበር ይታደጓቸው!

  • 27 июн.1 5982

    https://youtu.be/06zTKHBoDD4?si=tdznz2YbTkXVT94i

  • 26 июн.1 5572

    ከ2019 ጀምሮ የቤት ኪራይ ዋጋ በአዲስ መተመኛ ሊወሰን ነው በአዲስ አበባ ከተማ የመኖሪያ ቤት ኪራይ ዋጋን ፍትሃዊ፣ ሳይንሳዊና ምክንያታዊ በሆነ መንገድ ለመወሰን የተዘጋጀ የዋጋ መተመኛ ጥናት ዛሬ ቀርቦ በባለድርሻ አካላት ፊት ውይይት ተካሂዷል። የአዲስ አበባ ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ቅድስት ወልደ ጊዮርጊስ እንደገለጹት፣ ከተማ አስተዳደሩ የኑሮ ጫናን ለመቀነስ እና በቤት ኪራይ ገበያ ውስጥ የተስፋፉ ሕገ-ወጥና ዘፈቀዳዊ አሰራሮችን ለመግታት በተከታታይ እየሰራ ነው። እንደ ኃላፊዋ ገለጻ፣ በ2016 ዓ.ም. የተከናወነው ሰፊ የአከራይና ተከራይ ውል ምዝገባ በዘርፉ አዲስ ምዕራፍ የከፈተ ሲሆን፣ አሁን የቀረበው የኪራይ ዋጋ መተመኛ ጥናትም የውል ማደስ ሂደትን ፍትሃዊና ግልጽ ለማድረግ ያግዛል። ጥናቱ የአከራዮችን ተገቢ ገቢ ከወቅታዊ የኢኮኖሚ ሁኔታ ጋር በማጣጣም የሚያረጋግጥ ሲሆን፣ በሌላ በኩል ተከራዮችም ከገቢያቸው ጋር የተመጣጠነ ኪራይ እንዲከፍሉ እና የተረጋጋ የኢኮኖሚ ኑሮ እንዲመሩ እንደሚያስችል ተገልጿል። እንዲሁም ጥናቱ የቤት ኪራይ ገበያውን ጤናማና ሊተነበይ በሚችል መልኩ በማደራጀት፣ በአከራይና ተከራይ መካከል ያለውን የእምነት ክፍተት ለመቀነስ እንዲሁም የሕገ-ወጥ ደላሎችን ጣልቃ ገብነት ለመግታት እንደሚረዳ ተጠቁሟል። ጥናቱ በአዲስ አበባ አመራር አካዳሚ ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች መምህራን ጋር በመተባበር የተዘጋጀ ሲሆን፣ በ2019 በጀት ዓመት በተግባር እንደሚውል ተገልጿል።

  • видео или голосовое, без подписи

  • 24 июн.1 32332

    በሚኪሊላንድ ኮንዶሚኒየም የተደቀነው አደጋ!😡 #condoaddis : በአዲስ አበባ ፣አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 13 የሚገኘው የሚኪሊላንድ (ብርጭቆ) ኮንዶሚኒየም ነዋሪዎች ካለፈው ዓመት የክረምት ወራት ጀምሮ በሚኖሩበት የኮንዶሚኒየም ግቢ ውስጥ ባጋጠመ የመሬት መንሸራተትና መሰነጣጠቅ ሳቢያ ለከፍተኛ ስጋት መጋለጣቸውን ገለጹ። ችግሩ ከተከሰተ አስር ወራት ቢቆጠሩም፣ የሚመለከታቸው የመንግስት አካላት ለጉዳዩ አፋጣኝ ምላሽ ባለመስጠታቸው ነዋሪዎቹ አሁንም ለሞትና ለንብረት ውድመት አደጋ ተጋልጠው እንደሚገኙ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል። እንደ ነዋሪዎቹ ገለጻ፣ የመሬት መሰነጣጠቁ የጀመረው በ2017 ዓ.ም ክረምት መውጪያው ላይ ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅት ጥልቀቱ እስከ ሦስት ሜትር የሚደርስ ጉድጓድ ፈጥሯል። ይህ አደጋ የመኖሪያ ህንጻዎችን ግድግዳ ከማላቀቁ ባለፈ በአቅራቢያው በሚገኘው የሚኪ ሌላንድ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ላይም ጉዳት አድርሷል። ስጋቱን አስመልክቶ ያነጋገርናቸው አንድ ነዋሪ “መሬቱ እየተንሸራተተና እየተሰነጠቀ መጣ፤ አስፋልቱም ወደ ታች ወረደ አሁን ወደ ሦስት ሜትር ያክል ወደታች ወርዷል በጥልቅ ወደ ታች ጉድጓድ ይታያል” በማለት የሁኔታውን አሳሳቢነት ገልጸዋል። አደጋው በተከሰተበት ወቅት የአዲስ አበባ አደጋ ስጋት እና ስራ አመራር ኮሚሽን እንዲሁም የአዲስ አበባ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት ሃላፊ ኢ/ር ወንዱሙ ሴታ ቦታው ድረስ በመገኘት የተመለከቱ ሲሆን ችግሩ እስከሚስተካከል ለደህንነታቸው ሲባል ነዋሪዎች አካባቢውን ለቀው እንዲወጡ እና በሌሎች አካባቢዎች ተጠልለው እንዲቆዩ ምክረሃሳብ ማስቀመጣቸውን አስታውሰዋል። በሁለት ብሎክ 58 አባውራ በችግሩ ምክንያት ለአደጋ ተጋልጠው የነበረ ቢሆንም የበለጠ የሚያሰጋቸው 29 አባውራ መኖሪያዎች በወቅቱ እንዲታሸጉ እና ለደህንነታቸው ሲባል ለቀው እንዲወጡ ተደርጎ ነበር። ይሁን እንጂ ለተፈናቀሉት 29 አባወራዎች ዘላቂ የመኖሪያ መፍትሄ ባለመሰጠቱና የቤት ኪራይ ዋጋ በመናሩ፣ ነዋሪዎቹም አቅም የሌላቸው በመሆኑ ስጋት ወዳለበት መኖሪያ ቤቶቻቸው ለመመለስ መገደዳቸውን ገልጸዋል። ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ቃላቸውን የሰጡ ነዋሪ ጉዳዩን ሲያስረዱ “ ወጥቶ የመከራየት አቅም ስለሌለው [ነዋሪው] ተመልሶ ገብቷል።ጥቂት ሰው ቢቀር ነው እንጂ ሁሉም ገብቷል፤ አሁን ደግሞ ክረምት ሲመጣ ቦታው በጣም ያሰጋል ” ብለውናል። ነዋሪዎቹ መፍትሄ ፍለጋ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳድር ጀምሮ እስከ መንገድ ትራንስፖርት ቢሮና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ድረስ ደጋግመው ቢመላለሱም፣ እስካሁን ያገኙት ምላሽ “ይሰራል” የሚል የተስፋ ቃል ብቻ መሆኑን ይገልጻሉ። በተለይም የመንግስት መስሪያ ቤቶቹ ሃላፊነቱን አንዱ ወደ ሌላው በመግፋት መፍትሄውን እንዳዘገዩት ነዋሪዎቹ ይናገራሉ። “ከማዘጋጃ ወደ መንገዶች ደብዳቤ ተልኳል ይሉናል፤ መንገዶች ስንሄድ ደግሞ መልሰው ወደዚህ ይልኩናል። ስራውን አስጀምረው ኦፊሻሊ እንኳን ኑሩበት የሚባል መልስ የለም፤ በእንጥልጥል ላይ ነው ያለነው” ሲሉ በቢሮክራሲው መጉላላታቸውን ነዋሪው ገልጸዋል። በአሁኑ ወቅት የክረምቱ ወቅት መቃረቡ ስጋቱን እጥፍ ድርብ አድርጎታል ብለውናል። በህንጻው ውስጥ የሚኖሩ ህጻናትና አረጋውያን ህንጻው ላይ በሚፈጠር ንቅናቄና ንዝረት ሳቢያ ከፍተኛ ጭንቀት ውስጥ እንደሚገኙ ነግረውናል። ነዋሪዎቹ “ሰው በስጋት ነው፤ ኃይለኛ ዝናብ ሲጥል ሁሉም ወደ ውጭ ነው የሚወጣው ቢያንስ መንገዱ ባይሰራ እንኳ ህንጻው እንዳይናድ ማጠናከሪያ ስራ እንዲሰራ ነው ጥያቄያችን” በማለት የሚመለከተው አካል ከመዘናጋት ወጥቶ አስፈላጊውን እርምጃ እንዲወስድ ጥሪያቸውን አቅርበዋል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ ጉዳዩን ይመለከታቸዋል የተባሉት እና በቦታውም ተገኝተው ተመልከተው ለነበሩት በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ኢ/ር ወንዱሙ ሴታ ተደጋጋሚ የስልክ ሙከራ ቢያደርግም ስልክ ሊነሳለት አልቻለም። መረጃው የቲክቫህ ኢትዮጵያ ነው Tiktok.com/@condoaddis https://m.youtube.com/@condoaddis T.me/condoaddis Linkedin.com/company/condoaddis Facebook.com/condoadis

  • 24 июн.1 2171

    видео или голосовое, без подписи

  • 24 июн.1 52613

    በአያት፣ በአራብሳ እና ጀሞን በመሳሰሉ ሰፋፊ የጋራ መኖሪያ ቤቶች በሚገኙባቸው አከባቢዎች ከፍተኛ የሆነ የኪራይ ዋጋ ጭማሪ መታየቱ ተሰምቷል፡፡ የቤት ኪራይ ጭማሪው በተለይም ከሁለት ወራት ወዲህ በከፍተኛ መጠን ማሻቀቡን ነው ለማወቅ የተቻለው፡፡ በአያት ኮንዶሚኒየም ከ20 እስከ 22 ሺሕ ብር ኪራይ ይከፈልበት የነበረው ባለ ሁለት ክፍል መኝታ ቤት ወደ 30 ሺሕ ብርና ከዚያ በላይ ያሻቀበ ሲኾን፣ እስከ 15 ሺሕ ብር ይከፈልበት የነበረው ባለ አንድ ክፍል መኝታ ቤት ደሞ እስከ 25 ሺሕ ብር መድረሱን እንዲሁም 'ስቱዲዮ' ተብሎ የሚጠራው አንድ ወጥ የመኖሪያ ክፍል ከ10 ሺሕ ብር ወደ 16 ሺሕ ብር ገደማ ማሻቀቡን የዋዜማ ሬዲዮ ዘገባ ጠቁሟል፡፡ በገላን፣ ቦሌ አራብሳ እና ጀሞ በሚገኙ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ላይ በተመሳሳይ አከራዮች ከፍተኛ የኪራይ ጭማሪ ማድረጋቸውም ተሰምቷል። የከተማዋ አሥተዳድር በበኩሉ የቤት ኪራይ ጭማሪ እንዳይደረግ አከራዮችን ቀደም ሲል ውል ማስገባቱ አይዘነጋም። ሆኖም በአዲስ አበባ ከተማ ላለፉት ሁለት ዓመታት ሲተገበር የቆየው የቤት ኪራይ ቁጥጥር ውል ሊጠናቀቅ ጥቂት ጊዜ መቅረቱን ተከትሎ በከተማዋ የመኖሪያ ቤቶች ላይ ከ50 እስከ 100 በመቶ የሚደርስ ከፍተኛ የዋጋ ጭማሪ እየተደረገ ስለመሆኑ ከቀናት በፊት የወጡ ዘገባዎች አመላክተዋል፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በበኩሉ ያለፉት ሁለት ዓመታት የቤት ኪራይ ውል በመጪው ሰኔ 30 ቀን 2018 ዓ.ም የሚያበቃ መሆኑን ተከትሎ ጥናት እያስጠና እንዳለ ገልፆ በጥናቱ ውጤት መሠረት አሁን በስራ ላይ ያለው የኪራይ ዋጋ ባለበት የሚቀጥል፣ የሚጨምር ወይም የሚቀንስ ከሆነ ለሕዝብ ይፋ እንደሚያደርግ ተናግሯል።

  • Condominuim Market in Addis Ababa pinned «https://youtu.be/hB2OuyZvslE?si=yoQg5pM1fOLpkbhJ»

Condominuim Market in Addis Ababa — tgindex