tgindex
The daily News Network

The daily News Network

Статистика
@dailynews151английский

The channel delivers free, right and Timid informations. Socio - Economic, political issues are priorly granted coverages. Information is power but delivering right information is quite modernity.

Последний пост
6 мар.
Последнее чтение
13 авг.
Постов за неделю
0
Всего постов
34
Тип
открытый
Язык
английский
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
392
0 за 5 дн.
Сутки
0
0,00%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
248
34 постов
Вовлечённость
63,3%
к подписчикам
Постов в день
0,0
всего 34
Упоминаний
0
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
1/48двое суток
1/72трое суток

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • #viral |🔥 በታይላንድ የቀለም ማቅጠኛ ፋብሪካ ላይ ከፍተኛ የእሳት አደጋ ተከሰተ እሳት አደጋ ተከላካዮች እጅግ አስፈሪ የሆነውን እሳት ለመቆጣጠር እየተረባረቡ መሆኑ ተገልጿል። እስካሁን የደረሰ የጉዳት ስለመኖሩ የተባለ ነገር የለም። በእንግሊዘኛ ያንብቡ ✅ ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X

  • የአቶ አማን ፍስሐ ጽዮን ሥርዓተ ቀብር ተፈጸመ በኢትዮጵያ የሚዲያ ዘርፍ አዲስ ምዕራፍ የከፈቱት እና የኢቢኤስ ቴሌቪዥን መሥራች እና ዋና ሥራ አስፈጻሚ የነበሩት የአቶ አማን ፍስሐ ጽዮን የቀብር ሥነ-ሥርዓት በዛሬው ዕለት ተፈጽሟል። ቀደም ሲል በዓድዋ ድል መታሰቢያ በተከናወነው የክብር ሽኝት መርሐ-ግብር ላይ የቤተሰብ አባላት የአቶ አማንን መልካም አባትነት እና ለቤተሰባቸው የነበራቸውን ጥልቅ ፍቅር የሚዘክሩ ልብ የሚነኩ ንግግሮችን አድርገዋል። የሃይማኖት አባቶች አቶ አማን በኢቢኤስ ቴሌቪዥን ሁሉም እምነቶች በእኩልነት ለተከታዮቻቸው አስተምህሮታቸውን መንገድ የከፈተ ሚዲያ እንዲሆን ማስቻላቸውን መስክረዋል። በተለይም በኮቪድ 19 ወቅት ከእምነት ተቋማት ጋር የሠሩት ሥራ ሲያስመሰግናቸው እንደሚኖር ነው የገለጹት። ባለትዳር እና የሦስት ልጆች አባት የነበሩት አቶ አማን ፍስሐ ጽዮን ከቤተሰብ ኃላፊነታቸው ባሻገር፣ በሚሊዮኖች ዘንድ ተወዳጅ የሆነውን ኢቢኤስን በመመሥረት ለሀገራቸው ተወዳጅ የሚዲያ ውጤት ያበረከቱ ታታሪ መሪ እንደነበሩ ይመሰከርላቸዋል። የአቶ አማን ፍስሐ ጽዮን ሥርዓተ ቀብር ዛሬ በአዲስ አበባ የቅዱስ ጴጥሮስ ወጳውሎስ መካነ መቃብር ወዳጅ ዘመዶቻቸው፣ የሥራ ባልደረቦቻቸው እና በርካታ የጥበብ ሰዎች በተገኙበት ተፈጽሟል። #EBC

  • የፊሊፒንስ ምክትል ፕሬዝዳንት እና የቀድሞ ፕሬዝዳንት ልጅ ሳራ ዱተርቴ በ2028 ዓመት ለፕሬዚዳንትነት እንደምትወዳደር አስታዉቃለች የፊሊፒንስ ምክትል ፕሬዝዳንት ሳራ ዱተርቴ በመጪው የ2028 ምርጫ ለፕሬዚዳንትነት ለመወዳደር እንዳሰች በመናገር፣ በአሁኑ ጊዜ በዓለም አቀፉ የወንጀል ፍርድ ቤት በሰብአዊነት ላይ በተፈፀመ ወንጀል ክስ ችሎት ላይ የሚገኙትን የቀድሞ ፕሬዝዳንት እና ወላጅ አባቷን ሮድሪጎ ዱተርቴን ፈለግ ተከትላ እንደሆነ አስታዉቃለች፡፡ ሳራ ዱተርቴ ረቡዕ ዕለት “ሕይወቴ የእኔ ብቻ እንዲሆን የታሰበ እንዳልሆነ ለመረዳት 47 ዓመታት ፈጅቶብኛል” ብላለች።“ለረጅም ጊዜ ለቤተሰቤ፣ ለአገሬ፣ ለሚጠሩኝ ሁሉ የኃላፊነት ክብደትን እጠይቅ ነበር” ስትል ሳራ ዱተርቴ በቀጥታ ስርጭት በተላለፈ ንግግሯ ገልጻለች፡፡ “እኔ ሳራ ዱተርቴ ነኝ፣ እናም በፊሊፒንስ ለፕሬዚዳንትነት እወዳደራለሁ” ብላለች።ሳራ ዱተርቴ ባለፈው የፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ወቅት ለወቅቱ ፕሬዝዳንት ፈርዲናንድ ማርኮስ ጁኒየር ባደረገችዉ ድጋፍ ተከታዮቿን “ይቅርታ” ጠይቃለች። ፊሊፒንስ ከሙስና እስከ ድህነት ብሎም የኑሮ ውድነት ቀውስ ድረስ በተስፋፉ ችግሮች ትግሏን ቀጥላለች።“ይቅርታ ለመጠየቅ በእያንዳንዱ የፊሊፒንስ ዜጋ ፊት ተንበርክኬ አልችልም። በምትኩ፣ ህይወቴን፣ ጥንካሬዬን እና የወደፊት ህዝቤን ለአገራችን አገልግሎት አቀርባለሁ” ስትል አክላለች።ከአምስት ዓመታት በፊት ለማርኮስ ምርጫ ድጋድ ብትሰጥም፣ ሳራ ዱተርቴ እና ፕሬዚዳንቱ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ መራራ ተቀናቃኞች ሆነዋል፣ በተለይም በ2024 ሳራ ዱተርቴ የመንግስትን ገንዘብ አላግባብ ስለመጠቀሟ የሙስና ምርመራ ከተጀመረ በኋላ ነዉ። ማርኮስ ባለፈው ዓመት የሳራ ዱተርቴን አባት በፊሊፒንስ ብሔራዊ ፖሊስ እና ኢንተርፖል በመወከል በዓለም አቀፉ የወንጀል ፍርድ ቤት በቁጥጥር ስር እንዲዉሉ በፈረመችበት ወቅት ግንኙነታቸው የበለጠ ሻክሯል፡፡ በስምዖን ደረጄ #ዳጉ_ጆርናል

  • без подписи

  • без подписи

  • በናይሮቢ አውሮፕላን ማረፊያ ለሁለተኛ ቀን የቀጠለው የአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪዎች የሥራ ማቆም አድማ ለመንገደኞች እንግልት መፍጠሩ ተገለፀ 🇰🇪 በናይሮቢ ጆሞ ኬንያታ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በኬንያ አቪዬሽን ሠራተኞች ማኅበር የተጀመረው የሥራ ማቆም አድማ፤ አገልግሎት በማስተጓጎሉ በርካታ መንገደኞች ለሰዓታት በአውሮፕላን ማረፊያው እንዲቆዩ መገደዳቸውን የአካባቢው መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል። ✈️ በርካታ አየር መንገዶች የበረራ መዘግየቶች ሲያጋጥማቸው፣ አንዳንድ በረራዎች የተሰረዙ ሲሆን ሌሎች አየር መንገዶች ደግሞ መንገደኞቻቸው ማስታወቂያ እስከሚወጣ ድረስ ወደ አውሮፕላን ማረፊያው እንዳይሄዱ አሳስበዋል። ❌ የሠራተኞች ማኅበሩ በፍርድ ቤት ቢከለከልም የጋራ ድርድር ውይይቶች አለመቋጨታቸውን እና ለቋሚ የሥራ መደቦች ጊዜያዊ የቅጥር ውል ጥቅም ላይ መዋሉን በመጥቀስ የሥራ ማቆም አድማውን ሰኞ ጀምሯል። 🔊 የኬንያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን ጉዳዩን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት እንደሚፈልግ ገልጿል፡፡ የሀገሪቱ የትራንስፖርት ሚኒስትር ደግሞ የተፈጠረውን አለመግባባት ለመፍታት ከሁለቱም ወገኖች ጋር ማክሰኞ አስቸኳይ ውይይት መጥራታቸው ተነግሯል። በእንግሊዘኛ ያንብቡ ✅ ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X

  • ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ የዓቢይ ጾምን አስመልክተው አባታዊ መልዕክት አስተላለፉ የካቲት 08 ቀን ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ዘኢትዮጵያ ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት፣ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም፤ በነገው ዕለት የሚጀመረውን የ2018 ዓ.ም የጌታችን የአምላካችንና የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የዓቢይ ጾም ሱባኤ በማስመልከት አባታዊ መልዕክት አስተላልፈዋል። በመልዕክታቸውም፤ ጾም መጾም ከፍቅረ መባልዕት፣ ከፍቅረ ንዋይና ከፍቅረ ሢመት ፍላጎት ጨርሶ መራቅ መሆኑን ገልጸዋል። የጾም ዋና ዓላማ ሥጋዊ ፍላጎትን መግራትና በምትኩ ደግሞ መንፈሳዊ ፍላጎትን ማጎልበት መሆኑን የጠቀሱት ቅዱስነታቸው፤ በመሆኑም ምዕመናን ይህንን መርሕ ጠብቀው መጾም ግዴታቸው እንደሆነ ገልጸዋል። የጾሙ ዓላማና ግብ ጽኑ ሃይማኖትን፣ እውነተኛ ፍቅርን፣ ዘላቂ ሰላምን፣ ልባዊ አንድነትን፣ የማይናወጽ ፍትሕንና እኩልነትን፣ እንዲሁም ወሰን የሌለው ርኅራሄን በውስጣችን ብሎም በዓለማችን ማሥረጽ መሆኑን በውል ተገንዝበን መጾም ይገባል ሲሉም አስገንዝበዋል። ቅዱስነታቸው አክለውም፤ በጾሙ ወቅት * ከልብ በመጸለይ፣ * የተራቡትን በማጉረስ፣ * የታረዙትን በማልበስ፣ * የተጠሙትን በማጠጣት፣ * የተጣሉትን በማስታረቅና * ፍትሕ ለተነፈጉት እውነተኛ ፍትሕን በመስጠት ጾሙን መጾም እንደሚገባ አሳስበዋል። በተለይም የሕዝባችንና የሀገራችን ዋነኛ ችግር ሆኖ የሚገኘውን ያለመግባባት ዝንባሌ ለመቅረፍ፤ በመተሳሰብና በበጎ ተግባራት መዋዕለ ጾሙን እንድንጾመው አባታዊ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል። ©️መናኸሪያ ሬዲዮ

  • በኢትዮጵያ የወላድ እናቶች ሞት ቁጥር በ85.9 በመቶ መቀነሱን የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ 🤰 ከዚህ ቀደም ከ100 ሺ ወላድ እናቶች አንድ ሺህ የሚሆኑት እንደሚሞቱ የገለፀው ሚኒስቴሩ አሁን ላይ ይህ ቁጥር ወደ 141 መውረዱን አስታውቋል፡፡ 📉 ከአራት ዓመት በኋላ አሁን ያለውን ቁጥር ወደ ግማሽ በማውረድ 70 ለማድረስ ግብ ተቀምጦ እየተሠራ መሆኑን የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ደረጀ ዱጉማ፤ የኢትዮጵያ የጽንስና ማህፀን ሐኪሞች ማኅበርና የአፍሪካ የጽንስና ማህፀን ፌዴሬሽን የጋራ  ኮንፈረንስ ላይ ገልፀዋል፡፡ “የእናቶችና የህጻናት ሞትን በከፍተኛ መጠን መቀነስ ተችሏል፣ የእናቶች ጤና መሻሻሎችን አሳይቷል፣ የፖሊሲ ለውጦች በመደረጋቸው ምክንያት ደህንነቱ ባልተጠበቀ የጽንስ ማቋረጥ ምክንያት የነበረው የሞት ምጣኔ አሳማኝ በሆነ መልኩ ቀንሷል” ሲሉ የኢትዮጵያ የጽንስና ማህጸን ሐኪሞች ማህበር ፕሬዚደንት ዶ/ር ሃይለማርያም ሰኚ ተናግረዋል። 💉 ካገቡ ሴቶች መካከል ዘመናዊ የእርግዝና መከላከያ መድኃኒቶችን የሚጠቀሙ ሴቶች 35 በመቶ ደርሷል ተብሏል።

  • #CR7 ዛሬ 41 ዓመት ሞላው!

  • ፌደራል ፖሊስ የተሽከርካሪ ሰሌዳን ቀየረ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ የተሽከርካሪ ሰሌዳ ቀየረ፡፡ የፌደራል ፖሊስ ሎጂስቲክስ ዋና መምሪያ ኃላፊ ረዳት ኮሚሽነር እሸቱ ፊጣ÷ ከ50 ዓመታት በላይ አገልግሎት ላይ የነበረው የፌደራል ፖሊስ ተሽከርካሪ ሰሌዳ የተዘበራረቀና ወጥነት የሌለው እንዲሁም ለቁጥጥር አመቺ እንዳልነበር ተናግረዋል። በንጽጽርም አዲሱ የተሽከርካሪዎች ሰሌዳ ከቴክኖሎጂ ጋር የተሳሰረ እና ከመረጃ ቋት ጋር የተጣመረ መሆኑን ጠቁመዋል። ሰሌዳው በህገወጥ መንገድ የማይባዛ ሚስጥራዊ መለያዎችን የያዘ መሆኑ ለቁጥጥር እንዲሁም የስራ እንቅስቃሴን ቀልጣፋ ከማድረግ አኳያ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ይኖረዋል ነው ያሉት። የተሽከርካሪ ሰሌዳው የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስን ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነት ከማላቅ ረገድ ሚናው የጎላ መሆኑን ገልጸው÷ ለሕዝቡ የሚመጥን አገልግሎት ለመስጠት እንዲሁም የወንጀል ምርመራና ክትትል ስራን ለማሳለጥ አጋዥ እንደሚሆን አመልክተዋል። ይህም ኢትዮጵያ የጀመረችውን የዲጂታል 2030 ግብ ከማሳካትና አገልግሎቶችን ከቴክኖሎጂ ጋር የማስተሳሰር ትልም ጋር የተዛመደ መሆኑን ጠቅሰዋል።

  • የጋዳፊ ልጅ  ተገደለ! የቀድሞው የሊቢያ መሪ ሙዓመር ጋዳፊ ልጅ ሰይፍ አል ኢስላም በአራት ታጣቂዎች ግድያ እንደተፈፀመበት ተገለፀ። ሰይፍ አል ኢስላም በመኖሪያ ቤቱ ሳለ ማንነታቸው ባልታወቁ ታጣቂዎች ህይወቱ ማለፉ ነው የተሰማው ። በምዕራባዊ ሊቢያ ዚንታን ከተማ ጥቃቱ መድረሱን የሀገሪቱ መገናኛ ብዙሀን አረጋግጠዋል። የአል ኢስላም የፖለቲካ አማካሪ  አብዱላህ ኦዝማን ግድያው መፈፀሙን በፌስ ቡክ ገፃቸው አስፈረው ፣ ግድያው በማን እንደተፈፀመ ግን  ዝርዝር ማብራሪያ አልሰጡም። አብዱላህ ኦዝማን ከባድ ሀዘን ውስጥ መሆናቸውን ገልፀው ፣ ለሟች የሚደረግ ሀይማኖታዊ ስርዓት እያከናወኑ መሆኑን ተናግረዋል። በጥቃቱ ዙሪያ እስካሁን የጠራ መረጃ አለመኖሩን ወደፊት ግን አዳዲስ ጉዳዮች እንደሚኖሩ የዘገበው ዩሮ ኒውስ ነው። ሰይፍ አል ኢስላም የቀድሞው የሊቢያ መሪ ሙዓመር ጋዳፊ ሁለተኛ ልጅ ሲሆን፣ የጋዳፊ ሁለተኛ ሚስት የነበረችው የሰይፋ ፋርካሽ ልጅ ነበር።

  • የኢትዮጵያ አየር መንገድ መግለጫ ባለፈው ሃሙስ ጥር 21፣ 2018 ዓ.ም ለሊት በኒጀር ዋና ከተማ ኒያሚ አውሮፕላን ማረፊያ በደረሰው ጥቃት ሁለት የአስካይ አየር መንገድ ቦይንግ 737 አውሮፕላኖች ላይ መጠነኛ ጉዳት መድረሱ መዘገቡ ይታወሳል። ሁለቱ አውሮፕላኖች የኢትዮጵያ አየር መንገድ አጋር የሆነው የአስካይ አየር መንገድ በኢትዮጵያ አየር መንገድ አማካኝነት ከአውሮፕላን አከራዮች የተከራያቸው እና በኢትዮጵያ ሲቪል አቪየሽን ባለስልጣን የተመዘገቡ ናቸው። በአውሮፕላኖቹ ላይ የደረሰውን ጉዳት ለመገምገም የተላከው የቴክኒክ ቡድን ጉዳቱ መጠነኛ መሆኑን ያረጋገጠ ሲሆን አውሮፕላኖቹ ተጠግነው በቅርቡ ወደ አገልግሎት እንደሚገቡ ለማሳወቅ እንወዳለን። የኢትዮጵያ አየር መንገድ

  • የሞባይል ባንኪንግ የአገልግሎት ክፍያ ጭማሪ ቅሬታ አስነሳ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ወደ ቴሌብርና ሌሎች ባንኮች የሚደረጉ ዲጂታል ዝውውሮች ላይ የታየው ከፍተኛ የዋጋ ጭማሪ፣ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የፕላን በጀት እና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ዘንድ ጥያቄ አስነስቷል። ቋሚ ኮሚቴው የብሔራዊ ባንክን የ6 ወራት ሪፖርት በገመገመበት ወቅት፣ የኤቲኤም (ATM)፣ የፖስ (POS) እና የሞባይል ባንኪንግ የአገልግሎት ክፍያዎች በከፍተኛ ሁኔታ መጨመራቸው "አበረታች" የተባለውን የዲጂታል ጉዞ ጥላ እያጠላበት መሆኑን ገልጿል። ዶክተር አብርሃም አለማየሁ የቋሚ ኮሚቴው ምክትል ሰብሳቢ፣ ባንኮቹ "ኪሳራ ደረሰብን" የሚሉትን ምክንያት ጥያቄ ውስጥ ከትተውታል። "ለመሆኑ ባንኮች የሚሉት ኪሳራ እውነት ነው? ወይስ ትርፍ ለማጋበስ የሚጠቀሙበት ዘዴ?" ሲሉ ብሔራዊ ባንክ ጉዳዩን በጥልቀት እንዲያጠናው አሳስበዋል። የብሔራዊ ባንክ የፋይናንስ ተቋማት ሱፐርቪዥን ምክትል ገዥ አቶ ሰለሞን ወርቅነህ ለቀረበው ወቀሳ ምላሽ ሰጥተዋል፡፡ ለአገልግሎት ክፍያ ጭማሪው ባንኮቹ እንደገለጹላቸው ከጠቀሱት መካከል የሚከተሉት ይገኙባቸዋል፡- • የሶፍትዌር ወጪ ጣሪያ መንካት፡ ባንኮች ለቴክኖሎጂው የሚከፍሉት የውጭ ምንዛሬና የባለሙያዎች ስልጠና ወጪ "ከፍተኛ" ነው። • የእርስ በርስ ትስስር ጣጣ፡ አንዱ ባንክ ከሌላው ጋር ለመናበብ የሚያወጣው ወጪ ለጭማሪው ምክንያት ሆኗል። • መቆጣጠር አይቻልም፡ ብሔራዊ ባንክ ለባንኮች "ይህንን ያህል ቁረጡ" ብሎ ትዕዛዝ መስጠት እንደማይችልና ይህም "ዓለም አቀፍ አሰራር አይደለም" ሲሉ እጃቸው የታሰረ መሆኑን ገልጸዋል። ብሔራዊ ባንክ ባንኮቹ ለአገልግሎት የሚቆርጡትን ክፍያ ለተጠቃሚው በግልጽ "እንዲለጥፉ" አቅጣጫ መስጠቱን አቶ ሰለሞን ተናግረዋል፡፡ የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ… (AdissAdmas)

  • ከ2ሺህ እስከ 50ሺህ ብር የሚያስቀጣው ፌስታል ማምረትን፣ መጠቀምን እና ወደ ሐገር ውስጥ ማስገባትን የሚከለክለው አዋጅ ተግባራዊ በመደረጉ ማኅበረሰቡ ከመሰል ድርጊቶች እንዲቆጠብ ጥሪ ቀረበ በአዲስ አበባ ከተማ ለአንድ ጊዜ አገልግሎት ብቻ የሚውሉ የፕላስቲክ ከረጢቶችን ይዞ የተገኘ ማንኛውም ግለሰብ ላይ የገንዘብ ቅጣት እንዲጣልበት የሚደነግገው አዋጅ ተግባራዊ መደረግ በመጀመሩ የከተማዋ ነዋሪዎች ይህንን አውቀው ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ የአዲስ አበባ ከተማ የአካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን አሳስቧል። አዋጁን ለማስፈጸም ተሰጥቶ የነበረው የ6 ወራት የዝግጅት ጊዜ መጠናቀቁን ተከትሎ፤ ከጥር 23 ቀን 2018 ዓ.ም. ጀምሮ ወደ ጥብቅ ቁጥጥርና ቅጣት መገባቱን የባለሥልጣኑ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ዲዳ ዲሪባ ለአሐዱ ገልጸዋል። እንደ ዋና ሥራ አስኪያጁ ገለጻ፤ ማንኛውም ግለሰብ ፌስታል ሲያመርት፣ ሲያከማች ወይም ይዞ ሲንቀሳቀስ ከተገኘ እንደ ጥፋቱ ክብደት እርምጃ ይወሰድበታል። በተለይም የፕላስቲክ ከረጢቶችን ያመረተ፣ ወደ ሀገር ውስጥ ያስገባ፣ የሸጠ ወይም ለንግድ ዓላማ ያከማቸ አካል እስከ 50 ሺህ ብር በሚደርስ የገንዘብ ቅጣትና በሕግ ተጠያቂ የሚሆንበት አሠራር ተዘርግቷል ተብሏል። ይህ ውሳኔ ተግባራዊ የተደረገው ባለፈው ዓመት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የጸደቀውን የደረቅ ቆሻሻ አያያዝ እና አወጋገድ አዋጅ መሠረት በማድረግ ነው። ለአንድ ጊዜ ብቻ ለአገልግሎት የሚውሉት የፕላስቲክ ምርቶቹ ክልከላ የተደረገባቸው ከተወገዱ በኋላ ለመበስበስ ረዥም ዓመታትን የሚፈጁ በመሆናቸው በአካባቢና በጤና ላይ የሚያደርሱት ብክለት ከፍተኛ በመሆኑ ነው ተብሏል። ሕብረተሰቡ ከ‘ፌስታል’ ይልቅ ሌሎች ለአካባቢ ተስማሚ የሆኑ አማራጮችን እንዲጠቀምና መመሪያውን እንዲያከብር የባለስልጣኑ ስራ አስኪያጅ አቶ ዲዳ ጥሪ አቅርበዋል። ሕጉን ለማስፈጸምም የሕግ አስከባሪ አካላት አስፈላጊውን ሥልጠና ወስደው በየአካባቢው ለክትትል ዝግጁ መሆናቸውን ባለሥልጣኑ አረጋግጧል። አሐዱ ራድዮ

  • የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የምርጫ ጣቢያዎችን ዝርዝር ይፋ አደረገ ** የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ እያከናወናቸው ያሉ የቅድመ-ምርጫ ተግባራት አካል የሆነውን የምርጫ ጣቢያዎች ዝርዝር ይፋ ማድረጉን አስታውቋል። ቦርዱ ቀደም ሲል ባወጣው የምርጫ ጊዜ ሠሌዳ መሠረት፣ በጥር ወር 2018 ዓ.ም. ምርጫ ለማስፈጸም የለያቸውን የምርጫ ጣቢያዎች ዝርዝር ለሕዝብ ግልጽ አድርጓል። ቦርዱ በሰጠው ማሳሰቢያ አሁን ይፋ የተደረጉት የምርጫ ጣቢያዎች ቦርዱ ለምርጫ ማስፈጸሚያነት እየተዘጋጀባቸው ያሉ መሆናቸውን ጠቁሞ፤ ወደፊት በመሬት ላይ ያለውን ተጨባጭ ሁኔታ በመዳሰስና በመገምገም አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ተጨማሪ መረጃዎችን ለሕዝብ ይፋ እንደሚያደርግም አስታውቋል። በዚህም መሠረት መራጮች በዲጂታል እና በማንዋል (በሰው ኃይል) ምዝገባ የሚከናወንባቸውን ጣቢያዎች ዝርዝር በተዘጋጀው የድረ ገፅ (Link) በመግባት ማግኘት ለህዝብ ይፋ ማግኘተ እንደሚችሉ ተገልጿል። የምርጫ ጣቢያዎችን ዝርዝር ለማግኘት፦ 🔗 https://url-shortener.me/9X67

  • ዜና እረፍት #Ethiopia | በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የገዳማት መምሪያ የበላይ ኃላፊ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ዕንባቆም ከዚህ ዓለም ድካም አረፉ። #eotc_tv

  • без подписи

  • በሚሰራበት ሆቴል ከምትስተናገድ የውጪ ዜጋ ገንዘብ የሰረቀዉ ተከሳሽ በእስራት ተቀጣ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል በካፋ ዞን ቦንጋ ከተማ አስተዳደር ኮሌጅ ቀጠና ተብሎ በሚጠራበት አካባቢ የወንጀል ድርጊቱ ተፈጽሟል፡፡ተከሳሽ ታሪኩ ቆጭቶ የተባለ ሲሆን  ተቀጥሮ ከሚሰራበት አንድ አለም አቀፍ ሆቴል ውስጥ ከውጪ ሀገር ዜጋ ላይ የገንዘብ ስርቆት መፈፀሙ ተገልጿል። ተከሳሹ በዕለቱ ከድርጅቱ ደንበኛ ከውጪ ሀገር ዜጋ ግለሰብ ከእጅ ቦርሳ ላይ 5 ባለ 20 ዩሮ በወቅቱ ምንዛሪ ወደ ኢትዮጵያ ሲመነዘር 17ሺህ 500 ብር ሰርቆ በመውሰዱ እና ደንበኛዋ ለሆቴሉ ኃላፊው በማሳወቋ በተደረገው ፍተሻ በካልሲ ውስጥ ደብቆ በመገኘቱ ቁጥጥ ስር መዋሉን የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች  ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር ኢንስፔክተር ደጀኔ አሰፋ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል። ፖሊስ ግለሰቡን ከነኤዚግብቱ በቁጥጥር ስር አውሎ በሰው ማስረጃ የምርመራ መዝገቡን አደራጅተው ለዐቃቤ ህግ መዝገቡን ያስተላልፋል።የቦንጋ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ዐቃቤ ከከተማ ፖሊስ የደረሰውን የምርመራ መዝግብ መነሻ በማድረግ ግለሰቡን የተጣለበትን ኃላፊነት ወደጎን በመተው በፈፀመው ስርቆት ወንጀል ክስ መስርቶበት ለመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ያቀርበዋል። የቦንጋ ከተማ አስተዳደር የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የቀረበለትን የክስ መዝገብ ግራ ቀኙን አከራክሮ ግለሰቡን በዐቃቤ ህግ የቀረበበት ክስ ማስባበል ባለመቻሉ ተከሳሹን  በ1 ዓመት ከ 8 ወር እስራት እንዲቀጣ መወሰኑን ኢንስፔክተር ደጀኔ አሰፋ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል። ሳምራዊት ስዩም #ዳጉ_ጆርናል

  • በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ ሙሉ በሙሉ የተቆረጠ የብልት ክፍልን በረቀቀ የቀዶ ህክምና በተሳካ ሁኔታ በመቀጠል አዲስ የሕክምና ታሪክ ተመዘገበ 🏥 የአለርት ኮሞፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ዶክተሮች አደጋ ከደረሰበት 9 ሰዓት ያለፈውን ወጣት ብልት ለማዳን የነበረውን ጠባብ ግዜ በአግባቡ በመጠቀም ሕክምናውን እንዳከናወኑ ተገልጿል፡፡ ⏰ 6 ሰዓታትን በፈጀው አስቸኳይ የቀዶ ጥገና የሽንት ቱቦው፣ የቆዳው እና ሌሎች የድጋፍ አካላቶችን ቅርጽ እና ተግባር ወደነበረበት መመለስ ተችሏል። ሆስፒታሉ ተከላው ስኬታማ እንደነበር እና ታካሚው በጥሩ ሁኔታ እያገገመ እንደሚገኝ ገልጿል። 🇪🇹 ይህ ስኬት ለኢትዮጵያ ረቂቅ የተከላ ቀዶ ጥገና ትልቅ እርምጃ እና በጣም ውስብስብ እና ጊዜ የሚወስዱ ጉዳቶች ሀገር ውስጥ በብቃት፣ በቡድን ሥራ እና በላቀ የቀዶ ጥገና ሊታከሙ እንደሚችሉ ያሳያ ነው ሲል አለርት ኮሞፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በማኅበራዊ ገጹ አስፍሯል። ✅ ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X

  • ​💔 ጠበላ ከተማ በከባድ ሃዘን ውስጥ ትገኛለች፡ የባልና ሚስት ሕይወት በአሰቃቂ አደጋ አለፈ ​በዛሬው ዕለት በወላይታ ዞን ጠበላ ከተማ የተከሰተው የትራፊክ አደጋ መላውን የከተማዋን ነዋሪዎች እጅግ አስደንግጧል። በአንድ የትዳር ጣራ ስር ይኖሩ የነበሩ ባልና ሚስት በድንገት በተከሰተ አደጋ ሕይወታቸው ማለፉ ተረጋግጧል። ​📌 የአደጋው ዝርዝር ሁኔታ፦ አደጋው የተከሰተው ከጠበላ ከተማ ወደ ሶዶ ይጓዝ የነበረ የሕዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ (ሚኒባስ) በተቃራኒ አቅጣጫ ሲጓዝ ከነበረ የሞተር ብስክሌት ጋር ፊት ለፊት በመጋጨቱ ነው። ​📊 አስደንጋጭ መረጃዎችና የጉዳት መጠኑ፦ ​የሟቾች ቁጥር፦ በሞተር ብስክሌቱ ላይ የነበሩት ባልና ሚስት ወዲያውኑ ሕይወታቸው አልፏል። ​የቆሰሉ ዜጎች፦ በሕዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪው ውስጥ የነበሩ ከ4 በላይ ተሳፋሪዎች ላይ ቀላልና ከባድ የአካል ጉዳት ደርሶ በአቅራቢያ በሚገኝ ሆስፒታል የሕክምና እርዳታ እየተደረገላቸው ይገኛል። ​መንስኤ፦ የጥንቃቄ ጉድለትና የተሽከርካሪ ፍጥነት ለአደጋው መንስኤ መሆናቸው እየተጠቆመ ሲሆን፣ ፖሊስ ተጨማሪ ምርመራ እያደረገ ይገኛል። ​ክልላዊ መረጃ፦ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ባለፉት ጥቂት ወራት በደረሱ አደጋዎች ከሟቾች መካከል ከፍተኛውን ቁጥር የሚይዙት በሞተር ብስክሌት የሚጓዙ ዜጎች መሆናቸውን መረጃዎች ያሳያሉ። ​📢 የፖሊስ መልዕክት፦ የክልሉ ፖሊስ የሕዝብ ግንኙነትና ገጽታ ግንባታ ዳይሬክተር ምክትል ኮማንደር አሸናፊ ሃይሌ እንደገለጹት፤ አሽከርካሪዎች የሌሎችን ዜጎች ሕይወት ከግምት ውስጥ በማስገባት በከፍተኛ ጥንቃቄ ሊያሽከረክሩ ይገባል። "የአንድ ቤተሰብ አባላት የሆኑ ባልና ሚስትን በአደጋ ማጣት እጅግ አሳዛኝ ነው" ብለዋል።