Debark Gebiya-ደባርቅ ገብያ
Статистикаበዚህ ቻናል በሰሜን ጎንደር ዞን ደባርቅ እና አካባቢዋ እንዲሁም የደባርቅ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የሚፈልጉትን እቃዎች ካሉበት ሁነዉ የሚያዙበትና መግዛት የሚችሉበት ነዉ :: ነጋዴዎችም ምርታቸውን ዕቃቸውን በቀላል መንገድ በድጅታል የሚያስተዋዉቁበት ነው። በተጨማሪም በአካባቢው የሚውጡ የስራ ማስታወቂያዎች ይለቀቅበታል።
- Последний пост
- 15 авг.
- Последнее чтение
- 15 авг.
- Постов за неделю
- 29
- Всего постов
- 52
- Тип
- открытый
- Язык
- ti
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 281
- 1/48двое суток
- 322
- 1/72трое суток
- 347
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
📍 አዲስ የሥራ ማስታወቂያ ከደባርቅ ዩኒቨርሲቲ! ደባርቅ ዩኒቨርሲቲ ባሉት ክፍት መደቦች ላይ መምህራንን አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል። 💼 የክፍት መደቦች ዝርዝር ለደባርቅ ዩኒቨርሲቲ 1ኛ ደረጃ ማህበረሰብ ትምህርት ቤት የርዕሰ መምህርነት መደብ (1) ደመወዝ፦ 25285 የትምህርት ደረጃ፦ በትምህርት አመራር በመጀመሪያ ዲግሪ ወይም ከዚያ በላይ የተመረቀ/ች የደረጃ መምህራን መደቦች አማርኛ (2) እንግሊዝኛ (2) ሂሳብ (2) አካባቢ ሳይንስ ወይም ባዮሎጂ (2) ግብረ-ገብ ወይም ሥነ-ምግባርና ሥነ-ዜጋ (1) ሥነ-ጥበብ (1) ሰውነት ማጎልመሻ (ስፖርት ሳይንስ) (1) ግዕዝ (1) ደመወዝ፦ 13732 (ለትምህርት ደረጃቸው የተመደበው የመነሻ ደመወዝ) 📝 ማሳሰቢያ ምዝገባው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ላሉት 10 ተከታታይ ቀናት ይቆያል። ተወዳዳሪዎች ከ8ኛ ክፍል ጀምሮ ያለውን ሙሉ የትምህርት ማስረጃቸውን እንዲሁም የማይመለስ ፎቶ ኮፒ ማቅረብ ይኖርባቸዋል። የምዝገባ ቦታ፦ ደባርቅ ዩኒቨርሲቲ የብቃትና የሰው ሀብት አስተዳደር ሥራ አስፈጻሚ ቢሮ ቁጥር 4። ተጨማሪ መረጃን ከማስታወቂያው ሰሌዳ ላይ ይመልከቱ። 💡 ይህንን መልካም አጋጣሚ ለመጠቀም ዛሬውኑ ያመልክቱ! ጽሑፉን #ሼር በማድረግ ለሌሎችም አድርሱ። #DebarkUniversity #JobOpportunity #TeacherHiring #Debark #Education #JobAlert #EthiopiaJob #DebarkCommunitySchool #TeacherVacancy
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
ሰላም እንዴት አላችሁ የደባርቅ ገብያ አባላት የዲጂታል አይዲ (National ID ) ማዘዝ ፈልጋችሁ የት መሄድ እንዳለባችሁ ግራ የገባችሁ ከእኛ ጋር መፍትሄ ይዘን መተናል ካላችሁበት ሁናችሁ በመደወል ብቻ በአንድ ቀን ደባርቅ መጥታችሁ ወይም ካላችሁበት እኛ እንካለን ። 🛑 በኮሚሽን መስራት ለምትፈልጉ አናግሩን 👉 0988232340 ይደውሉ 👉 በቴሌግራም @Habmisget ላይ ያናግሩን
без подписи
без подписи
#ቀን_07_12_2018 ዓ/ም እጅግ በጣም አስቸኳይ መረጃ #ለደባርቅና_አካባቢው_የጠፋች_ህፃን_ልጅ_መረጃ_ስለማስተላለፍ ****** እባካችሁ ይህን መረጃ ለሚመለከታቸው ያድርሱ! #ምናልባት_የእርስዎ_ላይክ_ሸርና_ኮሜንት_ለወላጅ_እናቷ_ታላቅ የምስራች ልትሆን ትችላለች!! #መሰንበት የምትባል፣ የናቷ ስም #አበበች ተባላልች ዕድሜዋ 8 ዓመት የሆነች ህፃን ጠፍታ ከቆየች በኋላ በጭልጋ ወረዳ ተገኝታለች።የመጠችው ከደባርቅ ወረዳ ነው። ➜ቦታውን በድንብ አታስረዳም አሰቸጋሪ ነው። ህፃኗ እንደተናገረችው፣ #ከደባርቅ ከተማ እንደመጣች እና አባቷን እንደማታውቀው፣ ቀደም ብሎ እንደሞተ ተናግራናለች። አሁን ግን በጭልጋ ወረዳ ፖሊስ ፅ/ቤት ተገኝታለች። ስለሆነም #በደባርቅ ከተማና በአካባቢው የፖሊስ ጽ/ቤቶች ይህችን ህፃን በተመለከተ የጠፋሽ ልጅ ሪፖርት ወይም የእለት ሁኔታ ተዛማጅ መረጃ ሊኖር ስለሚችል፣ ይህንን መረጃ ለሚመለከታቸው አካላት በማድረስ የህፃኗን ቤተሰቦች ለማግኘት ትብብር እንድናደርግ እንጠይቃለን። 🙏 Share በማድረግ ለቤተሰቦቿ እንድታደርጉ በእግዚአብሔር ስም ተጠይቃችኋል። መልካም ትብብራችሁን እንጠይቃለን። ስልክ ቁጥር 0918807319 ቤተሰቡ ከተገኛ በዚህ ስልክ ይደውሉ። 🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏 Via Bewuket Gonderew ሼር ያድርጉ👇👇👇 @debarkgebiya
без подписи
Debark Gebiya-ደባርቅ ገብያ pinned a photo
ውድ የደባርቅ ገበያ ቤተሰቦችና ተከታዮች! በዛሬው ዕለት የቤተሰባችን አባላት ቁጥር 500 መድረሱን ስናበስር በታላቅ ደስታና አክብሮት ነው! 🥳✨ ከእኛ ጋር ስላላችሁ፣ ለምትሰጡን ድጋፍ፣ ላሳያችሁን እምነት እና አብራችሁን ስላላችሁ በሙሉ ልብ እናመሰግናለን! 🙏💛 እርሶም የማህበረሰባችን አካል በመሆን የንግድ፣ የግብይት እና የስራ እድል መረጃዎችን በፍጥነትና በጥራት ማግኘት ይችላሉ። 🔄 መልእክቱን Share በማድረግ ድጋፍዎን ያሳዩ! የደባርቅና የአካባቢዋ ነዋሪዎች፣ የደባርቅ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች እና የዞኑ ማህበረሰብ የበለጠ ተጠቃሚ ይሆኑ ዘንድ ይህን መልእክት ለወዳጅ ዘመድዎ Share በማድረግ ይተባበሩን! 📲 📌 የማህበራዊ ሚዲያ ገጾቻችንን ተቀላቀሉ፡ 📱 Telegram Channel: 💬 Telegram Group: 🎵 TikTok: 📘 Facebook 🎬 YouTube: ደባርቅ ገበያ — "ከራስ ደጀን ስር ያለ ገበያ" 🏔🛒
#ኑ በጋራ ታሪካዊቷን እና ጥታዊቷን የቱሪስት መዳረሻ ከተማ የሆነችውን ደባርቅን በጋራ እናልማ (ተቀዳሚ ከንቲባ አቶ ጌትነት ፀጋየ) #ሐምሌ 05/2018 ዓ/ም #የደባርቅ ከተማ ኮሙዩኒኬሽን። የደባርቅ ከተማ ተቀዳሚ ከንቲባ አቶ ጌትነት ፀጋየ የኮሪደር ልማት ገቢ ማሰባሰቢያ አስመልክቶ መልዕክት አስተላልፈዋል። ደባርቅ ከተማ በአዲያም ሰገድ እያሱ ዘመነ መንግስት በደጃች አምሳሌ ዘሴ በ1674 የተቆረቆረች ሲሆን ከተማዋ ባለፉት ዘመናት በርካታ የለውጥ ጎዳናዎችንና ጊዚያትን አሳልፋለች ብለዋል። የኮሪደር ልማት ስራ ለመስራት እቅድ አዘጋጅተን ወደ ስራ ገብተናል መነሻ ሁኔታችን ከተማዋ ቀደምት ፣ የዞን መቀመጫ ፣ የሰሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ የሀገር ወስጥና የውጭ ቱሪስቶች መዳረሻ ከተማ በመሆኗ ይችን ውብና ጥንታዊ ከተማ የሚመጥን ፅዱና ማራኪ ከተማ ለመገንባት በማሰብ እንደሆነ አብራርተዋል። ከዚሁ ጋር ተያይዞ ሰፊ የህዝብ ግንኙነት ስራዎችን በየደረጃው በማካሄድ የሀብት አሰባሳቢ ኮሚቴዎቾን በጎንደር ፣ ባህርዳር ፣ አዲስ አበባ አቋቁመናል ብለዋል። ኮሪደር ልማቱን ወደ መሬት ለማውረድ ከሶስተኛ ወገን የማፅዳት ስራ በአጭር ጊዜ ውይይት ትልልቅ ፎቆች ሳይቀሩ ያለምንም ካሳ ክፍያ ማስፈረስና ለስራ ምቹ ማድረግ ተችሏል ብለዋል። በተጨማሪ የመብራትና የውሀ መስመሮችን ካሳ በመክፈል ማስነሳትና ለመሰረተ ልማት ግንባታ ስራው ምቹ ማድረግ ስራ ተሰርቷል ብለዋል። ከዲዛይን አኳያ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በርካታ ውይይቶች እና ማስተካከያዎች ተደርገው ወደ ስራ መገባቱን ተቀዳሚ ከንቲባ አቶ ጌትነት ፀጋየ ገልፀዋል። አሁናዊ የኮሪደሩ የስራ እንቅስቃሴ በመንገድ ግራና ቀኝ የአፈር ቆረጣ ፣ ተዳፋታማ ቦታዎች ላይ የአፈር ማቀፊያ ግንባታ ፣ የቴራዞን ማምረት ፣ የግንባታ ድንጋይ እና ገረጋንቲ ማምረት ተግባራት እየተከናወኑ ይገኛል ብለዋል። እስካሁን የገቢ ምንጫችን የውስጥ ገቢያችን በመሆኑ ከዚህ አኳያ ገቢን የማሳደግ ስራ በስፋት ተሰርቷል ጎን ለጎንም ከመንግስት ሰራተኞች ፣ ከተማሪዎች ፣ ከነጋዴው ገቢ ለመሰብሰብ አቅደን ወደ ስራ ገብተን ሀብት የመሰብሰብ ስራ በተግባር እየተሰራ ይገኛል ብለዋል። በሀገር ውስጥ እና በውጭ የሚኖሩ ተወላጆች ፣ በአካባቢው ድጋፍ የሚያደርጉ እና የሚሰሩ መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት እንዲሁም የግል ድርጅቶች የበኩላቸውን ድርሻ ይወጣሉ በሚል አቅደን እየተንቀሳቀስን እንገኛለን። በቀጣይ ነሀሴ 18/2018 ዓ.ም አዲስ አበባ በሚገኘው ሂልተን ሆቴል እና ነሀሴ 23/2018 ዓ.ም ጃንሜዳ ጤና ጣቢያ በሚገኘው የመሰብሰቢያ አዳራሽ ገቢ የማሰባሰብ መድረክ እንፈጥራለን በመድረኩ የፌደራል እና የክልል ከፍተኛ ባለስልጣናት ፣ ዲፕሎማቶች እንዲሁም ባለሀብቶች ይገኛሉና የደባርቅን ልማት የምትፈልጉ በሙሉ ድጋፍ እንድታደርጉ ጥሪ አስተላልፈዋል። ከተማዋ ላይ ማልማት ለሚፈልጉ ባለሀብቶች በማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ 21.5 ሄክታር መሬት ፣ በአገልግሎት ዘርፍ ኢንቨስት ማድረግ ለሚፈልጉ 20 ሄክታር መሬት የተዘጋጀ በመሆኑ እና አስፈላጊውን ድጋፍ ከተማ አስተዳደሩ ስለሚያደርግ መዋዕለ ንዋያቸውን አፍስሰው ከተማችን ማልማትና ራሳቸውን መጥቀም ለሚፈልጉ ባለሀብቶ ጭምር ክቡር ከንቲባ አቶ ጌትነት ፀጋየ ጥሪ አስተላልፈዋል።
✨ ሰላም እንዴት ናችሁ የ«ደባርቅ ገበያ» አባላቶች በሙሉ! ✨ የሀገራችን፣ የደባርቅ ልጅ የሆነው አርቲስት ቴዎድሮስ ዳኘው አዲስና ድንቅ ሙዚቃ ለቅቋል! 🎶🔥 የራሳችንን አርቲስት ማበረታታትና ከጎኑ መቆም የሁላችንም ኃላፊነት ነውና ሁላችሁም ወደ ዩቲዩብ (YouTube) ገብታችሁ ሙዚቃውን እንድታዩለት፣ Like፣ Share እና Subscribe በማድረግ ወንድማችንን እንድታበረታቱት በትህትና እንጠይቃለን። የሀገራችንን ልጅ አንድ ላይ ሆነን እናሳድግ! 🙏💛 👇 ሙዚቃውን ለማየትና ለመደገፍ ይህንን ሊንክ ይጫኑ https://youtube.com/@tewodrosedagnew?si=ns2He679E_EMstiK
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи