Debre Markos University ® students /ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ® ተማሪዎች
Статистикаእንኳን ወደ ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ማህበር በሰላም መጡ! በዚህ ቻናል፦ ✅ ስለ ግቢያችን አዳዲስ ትኩስ እና እውነተኛ መረጃዎችን ✅ የትምህርት ማስታወቂያዎች እና መርሐግብሮች ✅ ልዩ ልዩ ኩነቶች እና የተማሪዎች ህይወት በፍጥነት የሚያገኙበት ብቸኛው ገጽ ነው 👇👇👇 🔗 t.me/debre_markos_universityy ለቡሬ ካምፓስ ተማሪዎች 🔗 t.me/buriecampuss
- Последний пост
- 14 авг.
- Последнее чтение
- 15 авг.
- Постов за неделю
- 10
- Всего постов
- 56
- Тип
- открытый
- Язык
- ti
- Категория
- Образование
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 54
- 1/48двое суток
- 61
- 1/72трое суток
- 66
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ለተመረጡ የኮሌጅ እና ተቋማት ዌብ አድሚኖች በድረ-ገጽ ዜና ዘገባ አጻጻፍ ዙሪያ ስልጠና ሠጠ። የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት ከየኮሌጆችእና ተቋማት ለተመረጡ ዌብ አድሚኖች በድረ-ገጽ ዜና ዘገባ አጻጻፍ ዙሪያና ድረ-ገፁን መጠቀም በሚችሉበት ሁኔታ ላይ ያተኮረ ስልጠናተሰጥቷል። የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ በዕውቀት ሲሳይ እንዳሉትየስልጠናው ዋና ዓላማ ኮሌጆች እና ተቋማት ዩኒቨርሲቲው ባሰራው አዲስ ድረ ገጽ ላይ የተጓደሉ መረጃዎች ለመጫን እንዲችሉና በኮሌጅ ደረጃ የሚሰሩ ስራዎችንና መረጃዎችን ተከታትሎ በማደራጀትና በማጠናቀር በበቂ ሁኔታ አሟልቶ በድረ ገጹ ላይ በመጫን ስለ ዩኒቨርሲቲው ሌሎች አካላት መረጃ እንዲያገኙ ለማድረግ ያለመ መሆኑ ገልፀዋል። ስልጠናውን የሰጡት በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ኦፊሰር ደመቀ ጣሰው (ዶ/ር) ሲሆኑ በስልጠናው ላይ ትኩረት የተደረገባቸውን ዜናዎች እና መረጃዎችን ስናዘጋጅ መቼ፣ እንዴት፣ ማንና ምንየሚሉትን ሀሳቦች በትኩረት በመከተል ላይ ያተኮረ እንዲሆን አስገንዝበዋል። በተጨማሪም ዜናዎች ግልፅ፣ ወቅታዊና በአጫጭር አረፍተነገሮች የሚገለፁ መሆን እንዳለባቸውና የአጻጻፍ ዘይቤውም ከፍተኛ ጥራት ያለው መሆን እንደሚገባው ተጠቁሟል። ዋና ዋና የዜና መረጃ ምንጮችን በተመለከተም የትምህርትና ምርምር ዜና፣ ይፍዊ ማስታወቂያዎች፣ የተለያዩ ዝግጅቶች፣ ኮንፈረንሶች፣ የማህበረሰብ ተሳትፎ፣ የኮሌጅና ተቋማት ስኬቶች መሆናቸው ተገልጿል። ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ነሐሴ 08/2018 ዓ.ም
የችግኝ ተከላ ዘመቻ! ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ነሀሴ 6/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 2:30 በጤና ካምፓስ ታላቅ የችግኝ ተከላ ፕሮግራም አዘጋጅቷል። በመሆኑም ሁሉም የዩኒቨርሲቲያችን ማህበረሰብ በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት በጤና ካምፓስ አጥር ግቢ በመገኘት የበኩለዎን አስተዋጽኦ እንዲያደርጉ ጥሪያችንን ከወዲሁ እናስተላልፋለን፡፡ “ዛሬ በመትከል ነገን እናለምልም”
#NGAT_Updates የድኅረ-ምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና (NGAT) ምዝገባ እስከ ረቡዕ ሐምሌ 29/2018 ዓ.ም የተራዘመ ሲሆን፣ ተከታዮቹን መረጃዎች ያስተውሉ፦ ➻ የፈተና ጣቢያ ምርጫችሁን አሁን ላይ Update ማድረግ የምትችሉ መሆኑ ተገልጿል። ➻ መስማት ወይም ማየት የማትችሉ አመልካቾች ፕሮፋይል ገፃችሁን Refresh በማድረግ የተደራሽነት ሁኔታችሁን (Accessibility Status)…
#ማስታወቂያ የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ማኅበረሰብ ትምህርት ቤት ከመስከረም 2019 ዓ.ም ጀምሮ የመማር-ማስተማር ሥራውን ከቅድመ-መደበኛ እስከ አራተኛ ክፍል ተማሪዎችን በመቀበል ይጀምራል፡፡ ስለሆነም:- ለደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ አካዳሚክና አስተዳድር ሰራተኞች፡- 👉ለትምህርት ክፍያ - 600 ብር በወር 👉ለትራንስፖርት ክፍያ - 400 ብር በወር 👉ለምዝገባ - 100 ብር #ለአካባቢዉ_ማህበረሰብ 👉ለትምህርት ክፍያ - 750 ብር በወር 👉ለትራንፖርት ክፍያ - 450 ብር በወር 👉ለምዝገባ - 100 ብር #ማሳሰቢያ የዩኒቨርሲቲዉ ሰራተኞች ለማመልከት ስትመጡ ከዩኒቨርሲቲው የብቃትና ሰው ሃብት አስተዳደር ስራ አስፈጻሚ የስራ ልምዳችሁን፤ የትምህርት ማዕረጋችሁን እና የሃላፊነት ልምዳችሁን የሚገለጽ ማሰረጃ እንዲሁም የልጆቻችሁን የልደት ሰርቲፊኬት ማቅረብ ይጠበቅባችኋል። ✍️ከአካባቢው ማህበረሰብ የምትመጡ አመልካቾች የወላጅ የቀበሌ መታወቂያ እና የተማሪው/ዋ የልደት ሰርቲፊኬት ማቅረብ ይጠበቅባችኋል፡፡ ✍️የመመዝገቢያ ቀን ከሐምሌ 27 ቀን እስከ ነሐሴ 8 ቀን 2018 ዓ.ም ሲሆን ✍️የመመዝገቢያ ቦት፡ በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ህንፃ ቁጥር 07 (1ኛ ፎቅ) ቢሮ ቁጥር 03 ነው። የዕውቀት አውድማ ከጮቄ ማማ! ህዝብ እና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት ሀምሌ26/2018 ዓ.ም
#NGAT_Updates የድኅረ-ምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና (NGAT) ምዝገባ እስከ ረቡዕ ሐምሌ 29/2018 ዓ.ም የተራዘመ ሲሆን፣ ተከታዮቹን መረጃዎች ያስተውሉ፦ ➻ የፈተና ጣቢያ ምርጫችሁን አሁን ላይ Update ማድረግ የምትችሉ መሆኑ ተገልጿል። ➻ መስማት ወይም ማየት የማትችሉ አመልካቾች ፕሮፋይል ገፃችሁን Refresh በማድረግ የተደራሽነት ሁኔታችሁን (Accessibility Status) Update ማድረግ ትችላላችሁ። ➻ ኢትዮጵያዊ ያልሆኑ አመልካቾች አሁን ላይ የNGAT ምዝገባቸውን ማድረግ ይችላሉ። Non-Ethiopian applicants can now register for NGAT.
Telebirr payment issue has been resolved. You can now complete your payment. Thank you for your patience. A notice from NGAT - Official Support Channel.
# የሀዘን መግለጫ
#NGAT የድኅረ-ምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና (NGAT) ምዝገባ እስከ ሐምሌ 25/2018 ዓ.ም ብቻ የሚከናወን መሆኑን የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቋል፡፡ የመመዝገቢያ ሊንክ 👇 https://ngat.ethernet.edu.et ፈተናውን ለመውሰድ የፋይዳ መታወቂያ የግድ ያስፈልጋል፡፡ የአገልግሎት ክፍያ 750 ብር ሲሆን፤ በምዝገባ ወቅት በቴሌብር በኩል መክፈል ይጠበቅባችኋል። ምዝገባው በሁሉም የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች የሚከናወን መሆኑን የገለፀው አገልግሎቱ፤ የፈተና ጣቢያዎች ከምዝገባ በኋላ የተመዝጋቢ ቁጥሩ ታይቶ የሚወሰን መሆኑን ጠቁሟል፡፡ የፈተና መስጫ ጊዜው ወደፊት ይገለጻል ተብሏል፡፡ ''ትምህርት ሚኒስቴር''
NGAT Registration! Link: ngat.ethernet.edu.et/registration
የሀዘን መግለጫ! በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ጤና ካምፓስ የአካባቢ ጤና አጠባበቅ ትምህርት ክፍል ሶስተኛ ዓመት ተማሪ የነበረችው አዛኘ አለሙ ባደረባት ህመም ምክንያት የህክምና እርዳታ ቢደረግላትም ህይወቷን ማትረፍ ባለመቻሉ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይታለች። ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ በተማሪያችን ህልፈተ ህይወት ጥልቅ ሀዘን የተሰማው መሆኑን እየገለጽን ለቤተሰቦቿ፣ ለወዳጅ ዘመዶቿና ለዩኒቨርሲቲያችን ማህበረሰብ በሙሉ መጽናናትን እንመኛለን።
በሩሲያ ሥነ-ጽሑፍ ውስጥ በጣም ከሚያሳዝኑኝ አንቀጾች አንዱ፦ እናቴ መከራው ሲበዛባት ፍቺ ፈጸመችና የራሷን መንገድ መረጠች። አባቴ በቤት ውስጥ ስሟ እንዳይነሳና ሄደንም እንዳናያት በከባዱ አስጠነቀቀን። ነገር ግን እኔን በሁለት አመት የሚበልጠኝ ወንድሜ ከኔ በላይ ጀግና ነበር። ይህ ሁሉ ማስጠንቀቂያ አልበገረውም። ቀኑን እናቱ ጋር ውሎ ማታ ወደቤት መመለስ ጀመረ። ይህን ያስተዋለች የእንጀራ እናታችን አባቴ ሲመለስ ጠብቃ የሆነውን ሁሉ ነገረችው። አባቴ በሰማው ነገር እጅግ በጣም ተበሳጭቶ ህሊናውን እስኪስት ደበደበው። ወንድሜ ከማንም በላይ የቅርብ ጓደኛየ ነው፤ ነገር ግን ከቤት ሲወጣ የት እንደሚሄድ አይነግረኝም ነበር። አንድ ጊዜ ወንድሜ ሶስት ቀን ውጪ አድሮ ወደ ቤት ተመለሰ። ሲመለስ ግን ስቃይ ጠበቀው፤ እስከ ሞት ድረስ ድብደባ አስተናገደ። ብዙ አልቆየም ቁስሉ ሳይደርቅ አልጋው ላይ ሞቶ ተገኘ። ዛሬ ወንድሜ ከሞተ ሳምንት አልፎታል። በጣም ናፍቆኛል እጀግ በጣም!። ናፍቆቱ ሲበረታብኝ በቤታችን ውስጥ ካሉ አንዳንድ የድሮ ትዝታዎችን የሚቀሰቅስ ነገሮች ማገላበጥ ጀመርኩ። የሚተኛበትን አልጋ ልብስ እያነሳው ጠረኑን እያሸተትኩ ሳለ ከትራሱ ስር የሆነ ነገር የተጻፈበት ወረቀት አገኘው። እንደዚህ ይል ነበር፦ ``እኔ እንደማደርገው አድርግ እስከመጨረሻው ወደ እናታችን መሄድ እንዳታቆም። ከእርሷ ጋር መነጋገር ቀጥል። ምክንያቱም አሁን ላይ ሁለቱም አይኗ ማየት አቁሟል። በድምፅም እኛን ለመለየት ትቸገራለች። እና እንዳለንላትና እንደምንከባከባት ንገራት። ነገር ግን ከእኛ አንዱ እንደሄደ በፍጹም እንዳነግራት!👍❤
видео или голосовое, без подписи