የሚ.ደብረ በረከት ሰ/ት ቤት ፍሬዎች
Статистикаይህ ቻናል እንደ እግዚአብሔር መልካም ፈቃድ በተለያዩ መምህራነ ወንጌል መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትምህርቶች የሚለቀቁበት ነው:: @debreberketSs "ነገር ግን በክርስቶስ ሁልጊዜ ድል በመንሣቱ ለሚያዞረን በእኛም በየስፍራው ሁሉ የእውቀቱን ሽታ ለሚገልጥ ለአምላክ ምስጋና ይሁን" 2ኛ ቆሮ. 2:14
- Последний пост
- 11 авг.
- Последнее чтение
- 15 авг.
- Постов за неделю
- 0
- Всего постов
- 24
- Тип
- открытый
- Язык
- ti
- В каталоге с
- 14 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 7
- 1/48двое суток
- 8
- 1/72трое суток
- 8
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
#ከሌሎች_ይልቅ_ብዙ_የሚደክመው_ያ_ሰው ሰባኪው በአንድ ቤተ-ክርስቲያን እየተገኘ ዘወትር ያስተምራል። በየእለቱ በርካታ ምእመናን በቦታው እየተገኙ ይሰበካሉ (ይማራሉ)። ከእነዚህ በርካታ ምእመናን ውስጥ አንደኛው ራቅ ካለ ቦታ ነው ሚመጣው። ወደ ቤተክርስቲያን ሲመጣም ሆነ ሲመለስ መሻገሪያ ድልድይ የሌለውን ወንዝ እየዞረ ስለሆነ ከሌሎች ይልቅ ብዙ የሚደክመው እሱ ነው። #አንድ_ቀን_ግን_እንዲህ_ሆነ፦ ሰባኪው የሚያስተምረው ስለ ጽኑ እምነት ነበር። " የሰናፍጭ ቅንጣት የሚያህል እምነት ቢኖራችሁ፥ ይህን ተራራ፦ ከዚህ ወደዚያ እለፍ ብትሉት ያልፋል፤ የሚሳናችሁም ነገር የለም።” የሚለውን ማቴ. 17፥20 ያለውን የመጽሃፍ ቅዱስ ኃይለ ቃል ጠቅሶ ሰው በእምነቱ ጽኑ ሲሆን የሚሳነው ነገር እንደሌለ ለምእመኑ አስረዳና የዕለቱን ስብከት አጠናቀቀ። መሻገሪያ በሌለው ትልቅ ወንዝ ምክንያት ከሌሎቹ ምእመን ይልቅ ብዙ የሚደክመው ያ ሰው ከቤተክርስቲያኑ ቅጥር ወጥቶ ወደ ቤቱ ሲያቀና እንደተለመደው እዛ ድልድይ አልባ ወንዝ ላይ ደረሰ። ወንዙን ሲያየው ሰባኪው ያስተማረው የእምነት ትምህርት ድቅን አለበት። ወዲያውኑ "እኔ እኮ በእግዚአብሔር አምናለሁ እግዚአብሔርም ይህን ለእኔ ማድረግ አይሳነውም" በማለት በፍጹም እምነት ወደ ጥልቁ ወንዝ በመሄድ ረገጠው እንዳለውም ተሳካለት መራመድም ቻለ። ያን ዙሪያ ጥምጥም የሆነ የቤቱን ጎዳና በጣም አጭር በሆነ ደቂቃ አጠናቆ ቤቱ ግባ። ሚስቱም በመደንገጥ "ቤተ-ክርስቲያን አልሄድክም እንዴ? ምነው በጊዜ መጣህ?" ብላ ብትጠይቀው የሆነውን ሁሉ ነገራት። እሷም በጣም ተደንቃ "ባለቤቴ ይህ ተዐምር ከተደረገለት መምህሩማ ምን ያህል ኣምላክ የመረጠው ቅዱስ ነው" ብላ "በል ነገ ይዘኸው ና! ቤታችንን በበረከት ይጎብኝልን።" በማለት ባለቤቷን ተማጸነች። በማግስቱ የዋሁ ባል ያለምንም ፍርሃት እና ጥርጣሬ በወንዙ ላይ ተረማምዶ ከተሻገረ በኋላ ትምህርቱን ተከታትሎ ጉባኤው ሲፈጸም ሰባኪውን ሄዶ፥ "ባለቤቴ እቤት እየጠበቀችን ነው እባክህን አብረን እንሂድ አለው።" ሰባኪውም ግብዣውን ተቀብሎ ጉዞ ጀመሩ። ሁለቱም እዚያ ወንዝ አጠገብ ሲደርሱ የዋሁ ሰውዬ እንደለመደው በውሃው ላይ እየተራመደ ጥቂት ከተጓዘ በኋላ ዞር ብሎ ሰባኪውን ሲመለከት ከወንዙ ዳር እንደቆመ ነው። በሰባኪው መቆም ተገርሞ "ና እንጂ መምህር ምን ሆነሃል?" ሲል ጠየቀው። ሰባኪውም "ፈራሁ" ሲል ይመልስለታል። ውሃውን እየረገጠ ወደኋላ ተመልሶ "ምነው መምህር? እኔን ለዚህ አብቅተህ እንዴት ትፈራለህ? ና ተሻገር እባክህን" ሲል ጠየቀው በሰውዬው ንግግር ጭንቅላቱ የተነካው መምህርም፡ "ወዳጄ እኛ #እናሻግራለን እንጂ #አንሻገርም!" ሲል መለሰለት። እኛስ የምንናገረውንና የምናዳምጠውን፣ የምናስተምረውንና የምንማረውን፣ የምንሰብከውንና የምንሰበከውን እየኖርን ነውን? የበለጠ መረጃ እንዲደርሶ የደጉ ሳምራዊ መልካምነት ቴሌግራም ቻናላችንንቤተሰብ ይሁኑ! ለወዳጅ ዘመድዎ እንዲሁም ለጓደኛዎ ያጋሩ:👇🏽 ☞ https://t.me/+S3QVyScP7Saom-Lv
የ2019 ዓ.ም የሥርዓተ ትምህርት ማስተግበሪያ የጊዜ ሰሌዳ በተመለከተ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት ከቅዱስ ሲኖዶስ በተሰጠው ተልዕኮ በሀገር ውስጥ እና ከሀገር ውጭ የሚገኙ ሕፃናት፣ ወጣቶች እና ጎልማሶችን በኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ሃይማኖት የጸኑ፣ ሥነ ምግባራቸው ያማረ፣ ቀደምት አባቶቻቸውን በመምሰል ቤተ ክርስቲያንን የሚረከቡ እና ሀገርን የሚጠብቁ ትውልድን የማፍራት ሥራውን በመሥራት ላይ ይገኛል። ይህንንም ከተዥጎረጎረ እና ወጥነት ከጎደለው፣ ለአንድ ዓላማና ግብ የተናጠል ሩጫ ከበዛበት አሠራር ሰንበት ትምህርት ቤቶቻችን ተላቀው በዓለም ዙሪያ የሚገኙ የሰንበት ትምህርት ቤት ወጣቶች በአንድ ሐሳብና በአንድ ቃል እንዲጓዙ የሚያስችል ሥራን በመሥራት ላይ ይገኛል። ከነዚህም አንዱና ዋነኛው የሰንበት ትምህርት ቤቶች ሥርዓተ ትምህርት ነው። ይህም ሥርዓተ ትምህርት በሀገር ውስጥም ሆነ ከሀገር ውጭ ባሉ አህጉረ ስብከት በትግበራ ላይ ይገኛል። ሰንበት ትምህርት ቤቶችም ለአተገባበር ያመቻቸው ዘንድ ዓመታዊ የትምህርት መርሐ ግብር የሚያስፈልግ በመሆኑ በሀገር ዐቀፍ ደረጃ ይህን ማስተገበሪያ ሰነድ ማዘጋጀት አስፈላጊ ሆኗል። ይህም ዓመታዊ የትምህርት ማስተግበርያ ሰነድ ለ2019 ዓ.ም የትምህርት ዘመን እንዲሆን ተደርጎ ተዘጋጅቷል። በዚህ ማስተግበርያ ሰነድ ውስጥ የዓመቱን የትምህርት መርሐ ግብር መጀመርያ እና መጨረሻ ጊዜ፣ የፈተና መርሐ ግብራት፣ የሴሚስተር የሪፖርት ጊዜያትን፣ የመርጃ መሣርያ ዝግጅትን ወዘተ በዝርዝር የያዘ ነው። ለዚህም የትምህርት መርሐ ግብር የየአህጉረ ስብከት ሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት እንዲሁም አጥቢያ ሰንበት ትምህርት ቤቶች ሓላፊነታቸውን በአግባቡ በመወጣት ሰፊውን ድርሻ መያዝ ይጠበቅባቸዋል። ይህ የትግበራ ሰነድ ወይም የትምህርት መርሐ ግብር በተቀመጠለት ጊዜና ሰዓት ተፈጻሚ መደረግ ይኖርበታል። ሰነዱንም በአንድነቱ የዌብሳይት ገጽ ላይ ከስር ያለውን ማስፈንጠሪያ በመጫን ማግኘት ይችላሉ። https://eotc-gssu.org/a/የ2019-ዓ-ም-የሥርዓተ-ትምህርት-ማስተግበሪያ/ መንበረ ፓትርያርክ የሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ሀገር አቀፍ ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ሐምሌ 2018 ዓ.ም የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት የማኅበራዊ የትስስር ገጾችን ቤተሰብ ይሁኑ! (የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት) 👉 Youtube 👉 Facebook 👉 Telegram 👉 Tiktok 👉 Website
#ወደ_እኔ_ና_ሳበኝም በህይወታችን አንዳንድ ጊዜ አለ አይደል? ሁሉ ነገር የሚደራረብባችሁ ዙሪያው ጨላማ የሚሆንባችሁ መከራው ሁሉ የሚከብዳችሁ ሸክም ሁሉ የሚጸናባችሁ ጊዜ አለ አይደል? ልክ እሱ ጊዜ ላይ ሆኜ በጣም ስጨነቅ ለአንድ ወዳጄን አማከርኩት እርሱም ይህን ጥቅስ ጠቅሶ ሊያጽናናኝ ሞከረ “እናንተ ደካሞች ሸክማችሁ የከበደ ሁሉ፥ ወደ እኔ ኑ፥ እኔም አሳርፋችኋለሁ።” ማቴ 11፥28 ውስጤ በጥያቄ ተወጠረ ደካማ መሆኔን ተርድቶ ሸክሜ መክበዱን አውቆ ሳለ እንዴት ወደእኔ አይመጣም? እንዴት ወደ እኔ ና ይለኛል? በእኔ ደካማነት ያውም ሸክሜ ከብዶ እንዴት እርሱ ድረስ ችዬ እሄዳለሁ? የሚል ጥያቄ ውስጤን ይንጠው ጀመረ። ጌታዬ ሆይ አንተ ወደ እኔ ና አቅሜን ታውቀው አይደል፤ አንተ ጋር እንዴት እደርሳለሁ? ሸክሜንስ ታውቀው አይደል እንዴት እችለዋለሁ? እኔ ግን እንደ ጴጥሮስ በማዕበል ውስጥ ሆኜ "ጌታ ሆይ አድነኝ" ስል እጣራለሁ። ጴጥሮስን እጁን ስበህ የማዕበሉን ሸክም አቅልለህ እንዳወጣኸው እኔንም ሸክሜን አቅልለህ ወደ አንተ ሳበኝ። ጌታዬ ሆይ ሳበኝ ሸክሜንም አራግፍልኝ ያኔ ሸክሜ ቀሏልና ከአንተ ኋላ እሮጣለሁ። ስምህ እንደሚፈስ ሽቱ ነውና ስምህን በላዬ ላይ አፍስልኝ ደናግል በወደዱህ መውደድም ልውደድህ። ጌታዬ ሆይ ሰሎሞን በመኃልየ መኃልዩ "ስምህ እንደሚፈስ ሽቱ ነው፤ ስለዚህ ደናግል ወደዱህ።" እንዳለ እንደደናግሉ ያለ ፍቅር በእኔ ልብ የለም። የተገዛውላቸውና የማደርጋቸው ሥጋዊ ምኞቶቼ ሸክም ሆነው ከብደውኝ ወደ አንተ መድረስ አልቻልኩምና ሸክሜን አራግፈህ ሳበኝ በእራሴ ወደአንተ መምጣት አይቻለኝምና። ጌታዬና መድኃኒቴ ሆይ ማቴዎስን ከቀራጭነቱ ሸክም አላቀህ ተከተለኝ እንዳልከው እኔንም ሸክሜ አላቀህ ተከተለኝ በለኝ። ወደቤቴ ግባና እንደዘኪዮስ ዛሬ ለዚህ ቤት መዳን ሆኗል የሚል ቃልን አሰማኝ። ይህን ለማድረግ ዛፍ ላይ መውጣት ካለብኝም እንደ ዘኪዮስ ምድራዊ በሆነ በሾላ ዛፍ ላይ ያይደለ ሥሮቿ በምድር ቅርንጯፋ በሰማይ የሆነችውን ዛፍ/ሀረግ/ እናትህን እርሷን ተጠግቼ በእርሷ አማላጅነትም ተንጠላጥዬ አንተን ለማየት ተስፋ አደርጋለሁና ጌታዬ ሆይ ወደ እኔ ና ዛሬ በቤትህ እውል ዘንድ ይገባኛልም በለኝ። ይህን እያሰብኩ ወደተነሳሁበት ጥቅስ ኀሊናዬ መለሰኝ “እናንተ ደካሞች ሸክማችሁ የከበደ ሁሉ፥ ወደ እኔ ኑ፥ እኔም አሳርፋችኋለሁ።” ማለቱ ለካ የሚያሳየው ቅርብ መሆኑን ነው። ኑ ማለቱም እንዳግዛችሁ ፍቀዱልኝ ሲል ነው ለካ! ጌታዬ ሆይ አንተ በሁሉ የሞላህ አይደለህ የትም ብሔድ አንተ ከእኔ ጋር ነህ ስለዚህ ጌታ ሆይ አድነኝ ሳበኝም ሸክሜንም አራግፈህ አሳርፈኝ። ይኸው ፍቃዴን ሰጥቼሀለሁ ጌታዬ ሆይ አሳርፈኝ። የደጉ ሳምራዊ መልካምነት ቴሌግራም ቻናላችንን ቤተሰብ ይሁኑ! ለወዳጅ ዘመድዎ እንዲሁም ለጓደኛዎ ያጋሩ: 👇👇👇 ☞ https://t.me/+S3QVyScP7Saom-Lv
እመቤታችንን ንጽሕት፣ ጽንዕት፣ ክብርት፣ ልዩ ትባላለች። ይህም፡- "#ንጽሕት" ስንል፡- ሌሎች ሰዎች (ቅዱሳን) ቢነጹ ከገቢር፣ ከነቢብ ኃጢአት ነው እንጂ ከኃልዮ ኃጢአት አይደለም፡፡ እርሷ ግን ከነቢብ፣ ከገቢር፣ ከኃልዮ ንጽሕት ናት፡፡ "ለመኑ ተውኅቦ ተደንግሎ ኅሊና ለመላእክትሂ ኢተክህሎሙ" ኃጢአትን ከማሰብ መጠበቅ ከሰው ልጆች ለማን ተሰጠው ይህስ ለመላእክትም አልተቻላቸውም" እንዲል፡፡ (ተአምረ ማርያም) "#ጽንዕት" ስንል:- ሴቶች ቢጸኑ ለጊዜው ነው እንጂ በኋላ በጊዜው ተፈትሆ አለባቸው:: እመቤታችን ግን ቅድመ ጸኒስ ጊዜ ጸኒስ ድኅረ ጸኒስ ቅድመ ወሊድ ጊዜ ወሊድ ድኅረ ወሊድ ድንግል ናትና:: "ጽንዕት በድንግልና አልባቲ ሙስና" እንዳላት ቅዱስ ያሬድ "ወትረ ድንግል ማርያም" ማርያም ዘለዓለማዊት ድንግል ናት" እንዳለ፡፡ (መጽሐፈ ቅዳሴ) "#ክብርት" ስንል፡- ሌሎች ሴቶች ቢከብሩ ጻድቃን ሰማዕታትን ነቢያት ሐዋርያትን ወልደው ነው እመቤታችንን ግን የምናከብራት "የአምላክ እናቱ" ብለን ነውና፡፡ "#ልዩ" ስንል፡- ከእርሷ በቀር እናት ሆና ድንግል እመቤት ሆና አገልጋይ የሆነች በድንግልና ወልዳ ወተትን (ሐሊበ ድንግልናዌን) ያስገኘች ሌላ ሴት የለችምና፡፡ በዚህም እመቤታችንን ንጽሕት፣ ጽንዕት፣ ክብርት፣ ልዩ እንላታለን፡፡ ☞ https://t.me/+S3QVyScP7Saom-Lv
без подписи
#ጾመ_ፍልሰታን_ለምን_እንፆማለን?❗️ ,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,, 👉ፆመ ፍልሰታ እንደ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ መሠረት ከሰባቱ የአዋጅ አፅዋማት መካከል አንዱ ሲሆን ጾመ ፍልሰታ ለማርያም ተብሎ ተወስኖ ይጾማል። #ፍልሰታ :- ፈለገ፣ ተሰደደ (ተገለጠ) ፣ መከፈት፣ መገለጥ፣ ከሚለው የግእዝ ስውር ቃል የተገኘ ሲሆን የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያምን ትንሳኤ ያመለክታል። 👉የጾሙ ዋና ምክንያት ሐዋሪያት የእመቤታችንን የእረፍቷን ነገር አስመልክተው የጾሙት ፆም ነው። 👉ታሪኩን በአጭሩ እንዲህ እንመለከታለን :- 👉እመቤታችን በጥር እሁድ በ21 ቀን አረፋለች ። ሐዋሪያት በአጎበር አድረገው ወደ ጌቴሴማኔ ይዘው ሲሄዱ አይሁድ ቀድሞ ልጇን ተነሳ አረገ እያሉ ሲያውኩን ኖረዋል። ዛሬ ደግሞ እሷን ተነሳች አረገች እያሉ ሊያውኩን አይደለምን ስለዚህ አስክሬኗን በእሳት እናቃጥላለን ብለው ተነሱ። 👉ታውፋንያ የሚባል አይሁዳዊ ተራምዶ አጎበሯን ጨበጠው መልአኩ ሁለት እጁን ቆረጠው፣ እጁ ከአጎበሩ ተንጠጥሎ ቀረ ከዚህ በኃላ መላዕክት የእመቤታችንን አስክሬን ወስደው በገነት አኑረዋታል። 👉በ8 ወሩ በነሐሴ ሐዋርያት አስከሬኗን እንደገና ከጌታ ተቀብለው በፀሎት እና በምህላ እሑድ ሥጋዋን ቀብረዋታል። ማስከኞ ተነስታለች። ከመትንሳኤ ወልድ/ እንደ ልጇ ትንሳኤ ያሰኘው ይህ ነው፡፡ በዚህ የቀብር ስነ ስርዓት ላይም ከ12 ቱ ሐዋርያት አንዱ ቅዱስ ቶማስ አልነበረም። 👉ቅዱስ ቶማስም ደመና ጠቅሶ ከሀገረ ስብከቱ ሲመጣ ስታርግ አገኛት፣ ወፈቀደ ይደቅ እምደመናሁ/ ከሚጓዝበት የደመና ጉዞ ላይም ለመውደቅ ወደደ ተበጠበጠ፣ ቀድሞ የልጇን ትንሳኤ ሳላይ ቀረሁ ዛሬ ደግሞ ያንቺን ትንሳኤ ሳላይ ቀረሁ ብሎ፣ አይዞህ አትዘን ወንድሞችህ ሐዋርያት ትንሳኤዬን ዕረገቴን አላዩም አንተ አይተሀል ፣ ተነሳች አረገች ብለህ ንገራቸው ብላ ምልክት ይሆነው ዘንድ የያዘችውን ሰበን ሰጥታ ሰደደችው። 👉 ከዚህ በኃላ ቶማስ የእመቤታችን ነገር እንደምን ሆነ ብሎ ሐዋርያትን ጠየቃቸው አግኝተን ቀበርናት አሉት፣ ሞት በጥር በነሐሴ መቃበር ተው ይሄ ነገር አይመስለኝም አላቸው። 👉 ቅዱስ ጴጥሮስም አንተማ ልማድህ ነው ፣ አንተ ብቻ ተጠራጥር አትቀርም አንተ እየተጠረጠርክ ሰውን ሁሉ ስታጠራጥር ትኖራለህ አለው። 👉እርሱም የያዘውን ያውቃልና ፀጥ ብሎ ይሰማቸዋል። ከዚህ በኃላ ጴጥሮስ ተቆጥቶ ሂዶ መቃብሩን ቢከፈተው አጣት፣ ደንግጦ ቆመ፤ አታምኑኝም ብዬ ነው እንጂ እመቤታችን ተነሰታለች፣ አረጋለች አላቸው የያዘውን ሰበን ሰጥቶአቸው ለበረከት ተከፋፍለው ወደ ሀገረ ስብከታቸው ተበታትነዋል። 🔶👉 በዚህ ምክንያት በአመቱ ቶማስ ትንሳኤሽን፣ ዕረገትሽን አይቶ እኛ ሳናይ ብለው ቅዱሳን ሐዋሪያት ነሐሴ 1 ሱባኤ ጀመሩ ሱባኤ በጀመሩ በ14 ተኛው ቀን ትኩስ በድን አድርጎ ሰጣቸው ከቀበሯትም በኃላ በነሐሴ 16 ቀን በክብር ተነስታለች። 👉 በዚህ ቀን ጌታችን መድሐኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ቀድሶ እመቤታችንም ከልጇ እጅ ቆርባለች። ከዚህ ጊዜ ጀምሮ የሐዋርያት ቤተ ክርስቲያን የእመቤታችንን በረከት ለማግኘት ይህቺ ጊዜ ትፆማለች። ⏩ እኛም ከእናታችን ከቅድስት ኪዳነ ምህረት በሱባኤውና በፆሙ ስንጠነክር የእሷ አማላጀነት የልጇ የመድሐኔዓለም ቸረነት ከመከራ ስጋና ከመከራ ነፍስ አድኖ ለንሰሀ ጥሪ እንደሚያበቃንና ቅዱስ ስጋውን እና ደሙን ለመቀበል እንደሚፈቅድልን አምነን ልንጾምና ልንጸልይ ይገባናል ። ፨ ወስብሐት_ለእግዚአብሔር ፨ የበለጠ መረጃ እንዲደርሶ የደጉ ሳምራዊ መልካምነት ቴሌግራም ቻናላችንን ቤተሰብ ይሁኑ! ለወዳጅ ዘመድዎ እንዲሁም ለጓደኛዎ ያጋሩ:👇🏽 ☞ https://t.me/+S3QVyScP7Saom-Lv
https://www.youtube.com/watch?v=viLl8A4DNzE
#ታላቅነት_የሚገኘው_በትሑት_ነው ወደ ክብር የሚወስደው መንገድ ትህትና ነው፡፡ ይህን በጎነት ከየት እናገኘዋለን? ትህትና ወደሚኖርበት ወደ መልካም ማደሪያ መሄድ ትፈልጋለህ? በዚያም በየደረጃቸው በሀብታቸው የታወቁ፤ በኹሉም የሕይወት ዘርፍ ራሳቸውን ዝቅ የሚያደርጉ፤ ሰዎችን እናገኛለን፡፡ በሕይወታቸውም ላይ "ትህትና" የሚለውን ቃል በብዕርና በቀለም ይጽፋሉ፡፡ የተንቆጠቆጡ አለባበሶች፤ የተንቆጠቆጡ ቤቶች ከንቱነትን ይወልዳሉና ብዙውን ጊዜ ሰዎች በትዕቢት ወጥመድ ይወድቃሉ፡፡ ኾኖም በትህትና ውስጥ የሚኖሩት እነዚህ ሰዎች ምንም ያህል አገልጋዮች ቢኖሯቸውም፤ የራሳቸውን እሳት ያቀጣጥላሉ የራሳቸውን እንጨት ይፈልጣሉ፤ የራሳቸውን ምግብ ያዘጋጃሉ በግላቸውም እንግዶቻቸውን ያስተናግዳሉ፡፡ ከእነርሱ በታች ያሉትን በስድብ ከፍ ዝቅ አያደርጉም፤ ማንም ሌላውን አይገዛም፡፡ ኹሉም በአገልግሎት ላይ ይሳተፋሉ፡፡ እያንዳንዱም ሰው የእንግዶችን እግር ያጥባል እናም እኔ አጥባለሁ እኔ በማለት ጠብን ያነሳሉ፡፡ እግሩንም የሚያጥቡለት ስው ባርያም ሆነ ባለስልጣን ግድ አይሰጣቸውም፡ በእነርሱ ፊት ማንም ትልቅም፤ ትንሽም አይደለም፡፡ ራሱን ከንቱ እንደሆነ የሚቆጠር ሰውም ከባርያ ጋር እኩል መቆጠሩ አያስከፋውም፡፡ ባሮችም የተከበሩ እንግዶች የሚቀርብላቸው ተመሳሳይ አይነት ምግብ፤ ተመሳሳይ ማረፊያ ነው፤ በአንድ ጠረጴዛ ዙሪያም ይቀርባሉ፡፡ ታላቅነት የሚገኘው ትሑት በመሆን ነውና፡፡ “የእኔ” እና “ያንተ" የሚሉት ሃሳቦች ከንቱ ናቸው, ማለቂያ የሌለውን የግጭት ምንጭ ይፈጥራሉ፡፡ እነርሱን የሚያስተሳስራቸው አንድ መንፈስ ኖሮ ሳለ ስለምን አገልጋዮችና ጌቶች በአንድ ጠረጴዛ ዙሪያ መታደማቸው ያስገርመናል? በዚህ ድህነት እና ባለጠግነት ስልጣን የላቸውም፤ ዝናና ውርደትም የለም፡፡ ስለዚህም ስንፍናና ከንቱ ውዳሴ በመካከላቸው ቦታ አያገኙም፡፡ አብርሃምም በከነዓናውያን ፊት ራሱን ዝቅ አደረገ፣ ከአፈርና ከአመድ በላይ እንዳልሆነ ያውቅ ነበር። ዳዊት ምን ያህል እንኳ የታላቅ ግዛት ንጉስ ቢሆንም ራሱን ከትል በታች ዝቅ አድርጎ ገለጸ። ታዲያ ትሑት ላለመሆናችን ምን ሰበብ ልንሰጥ እንችላለን? ከአብርሃምና ከዳዊትስ በምን ብንበልጥ ነው? የበለጠ መረጃ እንዲደርሶ የደጉ ሳምራዊ መልካምነት ቴሌግራም ቻናላችንን ቤተሰብ ይሁኑ!ለወዳጅ ዘመድዎ እንዲሁም ለጓደኛዎ ያጋሩ: 👇🏽👇🏽👇🏽 Telegram: ☞ https://t.me/+S3QVyScP7Saom-Lv
#ጥሩ_ሕልም_አላየሁምና_አይሂዱ ✍🏽ያኔ የገዳሙ መጋቢ የነበሩት አባ ተጠምቀ በጭንቀት ተውጠዋል። ከአቡነ ጎርጎርዮስ ካልዕ እግር ስር ወድቀው "ግድ የልዎትም አባ የዛሬው ጉዞ ይቆይዎ። እኔ ጥሩ ሕልም አላየሁም። እባክዎ እግርዎን ከዚህ ቤት አያንሡ፤ እንደው እባክዎ" እያሉ ይለምኗቸዋል። አቡነ ጎርጎርዮስ ግን ወደ መቂ ጊዮርጊስ ለአገልግሎት ለመሄድ ቆርጠው ተነሥተው ነበርና ሳልሄድ አላድርም ብለው እምቢ አሉ። በእርግጥ በዚያች የጉዞ ቀን ምን ሊሆኑ እንደሚችሉ ቀድመው ሳይረዱት ቀርተው አይመስልም። ምክንያቱም "ዛሬ ጥሩ ሕልም አላየሁምና አይሂዱ" ላሏቸው አባ ተጠምቀ "እኔስ ብሆን አንዳች ምልክት ያላየሁ ይመስልሃል። ዛሬ ጠዋት ሱሬን ስታጠቅ ሰባት ጊዜ መልሶ ሲፈታብኝ ነበር" ሲሉ መልሰውላቸዋል። ይሁን እንጂ በመቂ የሚገኝ እጅግ ሕመም የጸናበት አንድ የሚያውቁት ክርስቲያን ስለ ነበር ከራሳቸው ሕይወት ይልቅ ለዚያ ሰው ነፍስ ዋጋ ሰጥተው "ኸረ ሳላቆርበው እንዳይሞትብኝ" እያሉ አባ ጎርጎርዮስ ወደ መኪናው ፈጥነው ወጡ። ነገር ግን ከዚያ መኪና በሕይወት አልወረዱም። ከአዲስ አበባ ሕዝብ ጭኖ ከመጣ ተሽከርካሪ ጋር እርሳቸው ያሉበት መኪና ተጋጭቶ እሑድ ሐምሌ 22 ቀን ጠዋት አንድ ሰዓት ገደማ እኛ ደግ እና ባለ ብዙ ራእይ አባት አረፉ። ብፁዕነታቸው ከማረፋቸው ከአንድ ሳምንት በፊት በአላጌ ሕፃናት አምባ የልጆች ማሳደጊያ ተገኝተው በዚያ ቦታ ለሚሠራ ቤተ ክርስቲያን መሠረት ካኖሩ በኋላ "ሰው የሚፈልገውን ከሠራ የሚጠብቀው ሞቱን ነው" ብለው ተናግረው ነበር። በውስጣቸውም የነበረው የአገልግሎት እሳት ገና እየተቀጣጠለ ቢሆንም በዚህች ምድር የሚቀራቸው የእንግድነት ዘመን ግን ጥቂት መሆኑን ስለተረዱ በዚያ ለነበሩት መንፈሳዊ ልጆቻቸው እየደጋገሙ "ልጆቼ ከመሸ ተገናኘን" ይሏቸው ነበር። ከዚህች ክፋት ከነገሠባት ዓለም ጠልቀው ፈጣሪያቸው ካለበት መንፈሳዊ አገር የሚወጡበት ጊዜ መቃረቡን ቀድመው የተረዱ አባት ነበሩ። አቡነ ጎርጎርዮስ ከዘመናቸው ቀድመው የኖሩ፣ ትውልዱ ሃይማኖቱን ያቆዩለትን አባቶች እንዲያውቅና የኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ እምነቱንም ታሪክ ከመሠረቱ ተረድቶ ቤተ ክርስቲያኑን እንዲያፈቅር በቃልም በመጽሐፍም የተጉ አባት ናቸው። ቅዱስ አባታችን የነበሩበትን ዘመን አልፎ በሚሄደው ተራማጅ አሳቢነታቸውና ለቤተ ክርስቲያን ሁለንተናዊ ዕድገት ያሳዩት በነበረው ትጋት አሁን ላይ ላሉትና ወደ ፊትም ለሚነሡ በእውነት ለሚደክሙ ቅን አገልጋዮች ሁሉ ትልቅ አርአያ ይሆናሉ። የአገልግሎት ድካማቸው በረከት በሁላችን ላይ ይደርብን። እኛንም የአባቶቻችን ልጆች ያድርገን!!! (*የያኔው አባ ተጠምቀ የአሁኑ ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ሣልሳይ የምሥራቅ ሸዋ አገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ናቸው።) ሐምሌ 22 የአቡነ ጎርጎርዮስ ካልዕ የዕረፍት መታሰቢያ ቀን Telegram: ☞ https://t.me/+S3QVyScP7Saom-Lv
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሲማሩ የነበሩ የግቢ ጉባኤ ተማሪዎች መመረቃቸው ተገለጸ በማኅበረ ቅዱሳን አዲስ አበባ ማእከል ግቢ ጉባኤያት አገልግሎት ዋና ክፍል የቅዱስ ጊዮርጊስ ማስተባበሪያ መንፈሳዊ ትምህርት ሲያስተምራቸው የነበሩ 6 የግል እና 2 የመንግሥት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሲማሩ የነበሩ የግቢ ጉባኤ ተማሪዎችን አስመርቋል። በዕለቱም ትምህርተ ወንጌል በመምህር ቢትወደድ ውቤ ፣ሕይወት ከምረቃ በኋሏ ተሞክሮ በዲያቆን ደሳለኝ አበባው ፣መዝሙር በግቢ ጉባኤ አባላት፣ወረብ በተመራቂ ተማሪዎች የቀረበ ሲሆን ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች፣የተመራቂ ወላጆች፣የማስተባበሪያው ኀላፊዎችና ተመራቂዎች ተገኝተዋል። በመርሐ ግብሩ የማኅበሩን መልእክት በአዲስ አበባ ማእከል ጽ/ቤት ኀላፊ አቶ ካሳሁን ኀይሌ የተላለፈ ሲሆን "ተመራቂዎች ሀገርንና ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን በቅንነት እንዲታገለግሉ አሳስበዋል። በመጨረሻም ለተመራቂ ተማሪዎች የአደራ መስቀል በአባቶች ቡራኬ ተሰጥቶ መርሐ ግብሩ ተጠናቋል።
без подписи
без подписи