ዲያቆን ሕዝቅያስ | Deacon Hizkyas
Статистикаይህ ቻናል መንፈሳዊ ትምህርቶች እና መልእክቶች ብቻ የሚተላለፉበት ነው ! https://t.me/dn_hizkew ለሌሎች እናጋራ ! https://t.me/dnhizke_w ፦ የቴሌግራም ግሩፕ ጥያቄ እና አስተያየት ፦ @Dnhizkew
- Последний пост
- 12 авг.
- Последнее чтение
- 13 авг.
- Постов за неделю
- 1
- Всего постов
- 21
- Тип
- открытый
- Язык
- ti
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 55
- 1/48двое суток
- 63
- 1/72трое суток
- 67
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
| #Share #Like #Post |
መልሺው ስለእያንዳንዱ ነገር ከማመስገን ርቆ ዘወትር የሚያማርረውን ሥርዓተ ቤተክርስቲያንን ትቶ በራሱ ሕግ የሚመራውን ቤቱ የሆነች ቤተክርስቲያንን ትቶ በባዕድ አገር የተሰደደውን ሕይወት የሚሆን መብል ትቶ ከሞት መዓድ የሚቋረሰውን ወዳጅ ዘመድ የሆነውን ልጅሽን ርቆ ወደ ጠላት የሔደውን እመብርሃን እመአምላክ እናታችን ከተቀደሰው ሁሉ ርቆ የሔደውን ልጅሽን መልሺው🙏 ✨✨✨ሠናይ ቀን ✨✨✨
“መልእክተ ቅዱስ ፓትርያርክ" በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሓዱ አምላክ፣ አሜን ! በሀገር ውስጥና በመላው ዓለም የምትገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እምነት ተከታዮች በሙሉ! የሰውን ወገን ለማዳን የልጁ ማደሪያ ትሆን ዘንድ ድንግል ማርያምን የመረጠ መፍቀሬ ሰብእ እግዚአብሔር ኣምላካችን እንኳን ለሁለት ሺሕ ዓሥራ ስምንት ዓመተ ምሕረት ጾመ ማርያም ኣደረሰን ኣደረሳችሁ! “ወእመሰ ታፈቅሩኒ ዕቀቡ ትእዛዝየ፡- ከወደዳችሁኝስ ትእዛዜን ጠብቁ" (ዮሐ.14፥15)፤ ፍቅር የሕያዋን ኣካላት ረቂቅ መገናኛ ነው፣ ሕያዋን ኣካላት በውጫዊው ግዙፍ ኣካላቸው በተወሰኑ ጊዜያትና ቦታ ይገናኛሉ ፤ ስለ ጋራ ጉዳያቸውም በጋራ ይመክራሉ፤ ይበልጥም ይቀራረባሉ፡፡ ይሁንና የሕያዋን ኣካላት ግንኙነት በኣካል በጊዜና በቦታ ብቻ የተወሰነ ኣይደለም፣ በፍቅረ መንፈስ ተገናኝተውም ይግባባሉ፣ ከኣካላዊ ግንኙነት በላይ የበለጠም ይኸው ፍቅረ መንፈስ ነው፤ ከዚህ ኣንጻር እግዚአብሔርንም ማግኘት የምንችለው በዚሁ ፍቅረ መንፈስ ሆነን በእምነት ዓይን ነው! ይህም በመሆኑ ሓዋርያው ቅዱስ ዮሓንስ በመልእክቱ “በፍቅር የሚኖር በእግዚአብሔርይኖራል፣ እግዚአብሔርም በእርሱ ይኖራል" በማለት ያስተምረናል፣ (1ዮሐ. 4፥16) ይህም ማለት ከሱ ጋር በፍቅር ስንገናኝ፤ እሱም በኛ፣ እኛም በእሱ የመኖሩ ኩነት ይፈጠራል ማለት ነው፡፡ የተወደዳችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን ምእመናንና ምእመናት! ጌታችን “አፍቅሮ ለእግዚአብሔር ኣምላክከ፤- አምላክህን እግዚአብሔርን ውደደው" በማለት በፍጹም ልባችን እንድንወደው፣ እንደዚሁም ራሳችንን በምንወድበት መጠን እርስ በእርሳችን እንድንዋደድ ማዘዙን እናውቃለን፤ የመውደዳችን መለኪያ ሚዛንና መገለጫ ምልክትም ትእዛዙን ማክበርና መጠበቅ እንደሆነ “ብትወዱኝስ ትእዛዜን ጠብቁ” በማለት ኣስተምሮናል ከዚህ ኣኳያ ጌታን መውደድ ማለት ትእዛዙን በመጠበቅ የሚገለጽ ግዙፍ ነገር እንጂ ምናባዊና የማይታይ ድብብቆሽ ነገር ኣይደለም ማለት ነው፣ ጌታችንን የመውደድ ነገር ትእዛዙን በመጠበቅ የሚገለጽ ከሆነ ትእዛዙ ምንድን ነው? የሚለውን ማየት ኣስፈላጊ ይሆናል፤ ትእዛዙን በጥቅል ስናይ እግዚአብሔርንና ባልንጀራን በመውደድ እንደሚጠቃለል ራሱ ጌታችን ኣስገንዝቦናል፣ በተለይም በባልንጀራችን ላይ የምንከተለው መውደድ ከላይ እንደተገለጸው “እንደራስህ ኣድርገህ ውደድ" ተብለ በግልጽ ተቀምጦኣል፤ የሰው ባልንጀራ እነማን ናቸው? በሕይወት ያሉት ናቸው? ወይስ የሞቱት? ወገን ዘመድ? ወይስ የሰው ወገን በሙሉ የሚለውንም ማወቅ ኣስፈላጊ ነው፡፡ ጌታችን ነገሩን በዚህ ደረጃ ለያይቶ ኣላስቀመጠም፣ ለምን? ቢባል ባልንጀራ ማለት የተወሰነን የማኅበረ ሰብ ወገን የሚያሳይ ሳይሆን መላውን የሰው ወገን የሚገልጽ በመሆኑ፤ እንደዚሁም የሞቱም ሆኑ ያለነው ሁላችን በእሱ ፊት ሕያዋንና እርስ በእርሳችን ባልንጀሮች በመሆናችን ነው፤ በመሆኑም መዋደዳችንም ሆነ መከባበራችን በሕይወተ ሥጋ ሳለን ብቻ ሳይሆን ከዚያም በኋላ እስከ በሌለው ዕድሜ በመሆኑ ጌታችን በጊዜ በቦታና በከፊል ለይቶ ኣላስቀመጠም፡፡ የተወደዳችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን ምእመናንና ምእመናት ! ከነሐሴ ፩ ቀን ጀምሮ ለ፲፭ ቀናት የምንጾመው የጾመ ማርያም መነሻ ምክንያቱ የእግዚአብሔርትእዛዝና ፍቅር ነው፣ እግዚአብሔር ሰውን በኣጠቃላይ በተለይም ደግሞ እንደፈቃዱ የኖሩ ቅዱሳንን እንድናከብርኣዞናል ክቅዱሳን ፍጥረታት መካክል ደግሞ ቅድስት ድንግል ማርያም የመጀመሪያውን ደረጃ ትይዛለች፤ ይህም በመሆኑ ከፍጥረት ወገን ከሏ ክብር የሚደርስ ባለመኖሩ ከሁሉም ኣብልጠን እናክብራታለን፤ ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በዚህ ደረጃ የድንግል ማርያምን ክብር ስትገልጽ ክእግዚአብሔርና ለባስያነ እግዚአብሔር ክሆኑ ቀደምት ኣበው ተምራ ነው! በአራተኛው መቶ ክፍለ ዘመን የነበረው ዕውቁ ቅዱስና ዓለም ዓቀፋዊው አባት ቅዱስ ኤፍሬም የድንግል ማርያምን ክብር! ቅድስና እና ልዕልና ሲናገር “ይእቲ ተዓቢ እምኪሩቤል፡ ወትፈደፍድ እምሱራፌል፣ እስመ ኮነት ታቦተ ለአሓዱ ዘእምቅድስት ሥላሴ- እሷ ከኪሩቤል ትበልጣለች! ከሱራፌልም ትልቃለች፣ ከቅድስት ሥላሴ ኣንዱ ለሆነው ታቦት ወይም ማደሪያ ሆናለችና" በማለት አስተምሮናል፡፡ በመሆኑም ለስሟ መታሰቢያ በሆነው በዚህ ጾም ድንግል ማርያምን በዚህ ደረጃ ስናክብርትእዛዙን እንጠብቃለን፤ ትእዛዙን በመጠበቃችን ደግሞ እሱን መውደዳችንን እናረጋግጣለን ! እኛ ድንግል ማርያምን እንድንወዳት "እናታችሁ'' ብሎ እንዳዘዘ፣ እሷም ልትወደን “ልጆችዅ ተብላ ታዛለችና ስለኛ ትጸልያለች፡፡ በጸሎቷም ከመከራ ትታደገናለች፤ በኣጠቃላይ በእግዚአብሔር' በቅዱሳንና በእኛ መካከል ያለው ግንኙነት በዚህ ትእዛዝና ፍቅር በትዕይንተ ዓለም ባለች ቤተ ክርስቲያን ዘንድ የተሳሰረ ነው፡፡ ስለሆነም በዚህ የጾመ ፍልሰታ ለማርያም ሱባዔ የተራቡትን በመመገብ፣ የታረዙትን በማልበስ፣ የተጣሎትን በማስታረቅ፤ የታመሙትንና የታስሩትን በመጠየቅ፤ ቅዱስ ቍርባንን በመቀበልና ለኃጢኣታችን የንሥሐ ሥርየትን በመለመን ሱባዔውን ልናሳልፍ ይገባል፡፡ በመጨረሻም በሀገራችንም ሆነ በዓለም ዙሪያ ከባድ ስጋት የሆነው የፍጥረት ኣውዳሚ ጦርነትን በመለኮታዊ ጥበቡና ሥልጣኑ እንዲያስቆምልን በቅን ልቡና፤ በትሑት ሰብእና ሆነን እግዚአብሔርን በዚህ ሱባዔ እንድንጠይቀው ኣደራ ጭምር ኣባታዊ መልክታችንን በእግዚአብሔር ስም እናስተላልፋለን፤ የተባረከና የተቀደስ ጾም ያድርግልን፤ እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቦችዋን ይባርክ! ወስብሐት ለእግዚአብሔር፣ አሜን! አባ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእስ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘኣኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ነሐሴ 1 ቀን 2018 ዓ.ም አዲስ አበባ፤ ኢትዮጵያ
без подписи
ሠሌዳ ሚዲያ ምን እንድትሰሙ ተጠበቁ Youtube https://www.youtube.com/@seledamedia.megabehadiseshetu Tiktok http://www.tiktok.com/@seledamedia Instagram https://www.instagram.com/seledamedia/ Facebook https://web.facebook.com/profile.php?id=61591554360962
ሀ ብላ ሀለዎተ እግዚአብሔርን በየኔታ እግር ስር ትህትናን ከቀለም ያስተማረች፤ ብራና ፅፋ ታሪክ ከትባ ያቆየች፤ ቅርስ አሽሽታ ከጠላት ሸሽጋ የጠበቀች ቅድስት ቤተክርስቲያን የትናንቱን ለነገ ልታሻግር ያለፉትን አውስታ ልትዘክር ዛሬም ደግሳ ትጣራለች! የምድር ጌጥ ኢትዮጵያ በሆላንድ ፓርክ ከነሐሴ 28 እስከ መስከረም 3 ለተከታታይ 10 ቀናት ከልጆችዎ እና ከቤተሰብዎ ጋር በፍቅር ጋበዝንዎ!
https://youtu.be/AQ_z48j-rEQ?si=a4c4AwZxGeWIWtga
«ነገረ ገድሉ ወራእዩ ለቅዱስ ኒፎን» በቀሲስ ታምራት ውቤ #ንቁ #booklaunch #epiphaniatube #explore #EOTC
ዲያቆን ሕዝቅያስ | Deacon Hizkyas pinned «ዓለምን ሁሉ የምትገዛ የአባቶቻችን የአብርሃምና የይስሐቅ የያዕቆብም የጻድቃን ልጆቻቸውም አምላክ ሆይ ፥ ሰማይንና ምድርን ከዓለሞቻቸው ጋር የፈጠርህ ፥ በቃልህ ትእዛዝ ባሕርን የገሠጽሃት ፥ ቀላዮችን የዘጋህ የሚያስፈራውንም የወሰንህ ፥ ይኸውም በተመሰገነው ስምህ ነው ፥ ኀይልህ ከመገለጡ የተነሣ ሁሉ የሚርድና የሚንቀጠቀጥ ፥ ለክብርህ ከፍተኛነት ፍጻሜ የለውምና ፥ የቁጣህም መቅሰፍት በኃጥአን ላይ ግሩም…»
" የሕይወት ምንጭ ከአንተ ዘንድ ነውና በብርሃንህ ብርሃንን እናያለን ። " መዝ 61 ፥ 9 የክርስቶስ ዝናም መሆን ልጅነትን የሚያሰጥ ነው ። የክርስቶስ ዝናምነት ከኃጢአት የሚያነጻ ነው ። የክርስቶስ ዝናምነት የእግዚአብሔርን ጸጋ የሚያድል ነው ። የክርስቶስ ዝናምነት ድኅነተ ሥጋ ወድኅነተ ነፍስ የሚያሰጥ ነው ። የክርስቶስ ዝናምነት የመለኮቱ ተካፋዮች እንሆን ዘንድ የሚያደርግ ነው ። የክርስቶስ ዝናምነት የተጠማ ቢኖር ወደ እርሱ መጥቶ የሚረካበት የሕይወት ውኃ ነው ። የክርስቶስ የሕይወት ውኃ መሆን በእርሱ የሚያምን ሁሉ የሕይወት ውኃ የሚያፈልቅ የሕይወት ምንጭ ነው ። የክርስቶስ የሕይወት ውኃ መሆን ጽድቅን የተራበ ሁሉ ወደ እርሱ ቀርቦ የሚበላው የሚጠጣው ሕይወት ነው ። የክርስቶስ የሕይወት ምንጭ መሆን ሙታን ከእርሱ ጠጥተው ሕያዋን የሆኑበት ነው ። የክርስቶስ የሕይወት ውኃነት መድኃኒት ነው ። የክርስቶስ የሕይወት ውኃነት በውስጣችን ሃይማኖትን ከምግባር ይዘን ፍሬ እንድናፈራ የሚያደረግ ነው ። የክርስቶስ ውኃነት በኃጢአትና በትዕቢት ዐለት የሆነውን ልባችንን በነጠብጣቡ የሚሰብር እና ትሑት የሚያደርግ ነው ። የክርስቶስ የሕይወት ውኃነት ከባሕርይ አባቱ ከአብ ፣ ከራሱ እና ከባሕርይ ሕይወቱ መንፈስቅዱስ ጋር በጸጋ የሚያዋሕድ ነው ። ✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨ የመልካሞች መልካም ቀዳሜ ጸጋ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ የሕይወት ውኃን አድለን !
“ነፍሴ አንተን እስክታገኝ ድረስ እንዳትረካ አድርገህ ፈጠርካት።” የሂፖዉ ሊቀ ጳጳስ አውግስጢኖስ
📍መስቀል አደባባይ ደብረ ሰላም ቅዱስ እስጢፋኖስ ቤተክርስቲያን በብዙ ስለሚያተርፉ እንዳያመልጦ !
без подписи
እንኳን ለቅዱስ ጳውሎስ ወጴጥሮስ ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሰን አደረሳችሁ! “የጳውሎስ የመጨረሻዋ ቀን” ተራኪ፡ ገጣሚ ኤልያስ ሽታሁን ቅዱስ ጳውሎስ፣ ገጽ፡ 409
6: እርሱ በእግዚአብሔር መልክ ሲኖር ሳለ ከእግዚአብሔር ጋር መተካከልን መቀማት እንደሚገባ ነገር አልቈጠረውም 7: ነገር ግን የባሪያን መልክ ይዞ በሰውም ምሳሌ ሆኖ ራሱን ባዶ አደረገ 8: በምስሉም እንደ ሰው ተገኝቶ ራሱን አዋረደ ለሞትም ይኸውም የመስቀል ሞት እንኳ የታዘዘ ሆነ ። ፊልጵስዩስ 2 ፥ 6 - 8 ✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨ | ብርሃነ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ጳውሎስ |
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи