tgindex
Do you know ?

" በእዉነትህ ቀድሳቸዉ ፤ ቃልህም እዉነት ነዉ። " ዮሀ 17:17 የዚህ ቻናል አላማ ✢ እዉነት በሆነዉ የእግዚአብሔር ቃል መቀደስ ፣ መታነፅ ፣ ለሌሎች መትረፍ ✢ ከዚህ አለም ስልጣን በላይ በሆነ ቃል ህይወታችንን ማቃናት ለማንኛዉም ጥያቄና አስተያየት :- @Expectation23 Dm : - @Expectation23

Последний пост
12 авг.
Последнее чтение
14 авг.
Постов за неделю
2
Всего постов
25
Тип
открытый
Язык
am
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
10 926
+67 за 5 дн.
Сутки
−3
−0,03%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
391
25 постов
Вовлечённость
3,6%
к подписчикам
Постов в день
0,3
всего 25
Упоминаний
0
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
84
1/48двое суток
96
1/72трое суток
103

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • ✅በቴሌግራም ቆይታችሁ መንፈሳዊ ህይወቶን የሚየሳድጉበት ቻናሎች ልጠቁማችሁ😍 @seer_lewi

  • ፃፍ ለትውልዱ 🔥🔥🔥🔥

  • 3 авг.3423из Yirgalem_apologetics

    ⭕️ ኤልሮኢ የመልአኩ ስም ነው ‼️ ♨️ "ኤልሮኢ" የሚለውን ቃል ሁላችንም ከልጅነታችን ጀምሮ ስንሰማ ስላደግን በደንብ እናውቀዋለን ፤ ነገር ግን በዚህ ስም የተጠራው የእግዚአብሔር መልአክ መሆኑን ሳናስተውል ቀርተናል ። 📜 “እርስዋም ይናገራት የነበረውን የእግዚአብሔርን ስም ኤልሮኢ ብላ ጠራች የሚያየኝን በውኑ እዚህ ደግሞ አየሁትን? ብላለችና።” — ዘፍጥረት 16፥13 🔰 አጋር "ኤልሮኢ" ብላ የጠራችው ይናገራት የነበረውን ማንነት ነው ፤ ያ ማንነት ደግሞ የእግዚአብሔር መልአክ እንደሆነ ከላይ ያሉትን ቁጥሮች በማየት መረዳት እንችላለን ። 📜 “የእግዚአብሔር መልአክም፦ ዘርሽን እጅግ አበዛለሁ፥ ከብዛቱም የተነሣ አይቆጠርም አላት።” — ዘፍጥረት 16፥10 🔰 መልአኩ ለአጋር ዘሯን እንደሚያበዛ እየነገራት ነው ፤ "ዘርሽን እጅግ አበዛለሁ" ባዩ መልአኩ እራሱ ነው ። መልአኩ የሌላን ማንነት ንግግር በ reported speech እያቀረበ አይደለም ፤ ከዛ ይልቅ የዘፍጥረት መፅሐፍ ፀሐፊ የመልአኩን ንግግር በ direct reported speech እያቀረበ ነው ። ነገሩን ይበልጥ ግልፅ ለማድረግ እስኪ ከ direct ወደ indirect ቢቀየር ምን እንደሚል እንመልከት ። የእግዚአብሔር መልአክም "ዘርሽን እጅግ አበዛለሁ፥ ከብዛቱም የተነሣ አይቆጠርም" አላት ። ይሄ 👆👆 የዘፍጥረት ፀሐፊ የመልኩን ንግግር በ direct reported speech ያቀረበበት ነው ፤ ወደ indirect reported speech ሲቀየር እንደዚህ የሚል ይሆናል 👇👇👇 የእግዚአብሔር መልአክም ዘሯን እጅግ እንደሚያበዛውና ከብዛቱም የተነሳ እንደማይቆጠር ነገራት ። 🧱 መልአኩ ዘሯን የሚያበዛ ከሆነ እንዴት ፍጡር ሊሆን ይችላል ?? ዘርን የሚያበዛ ፈጣሪ ብቻ እንደሆነ ግልፅ ነው ፤ እየፈጠረ ነው ዘርን የሚያበዛው ። 📜 “ታላቅ ሕዝብም አደርግሃለሁ፥ እባርክሃለሁ፥ ስምህንም አከብረዋለሁ፤ ለበረከትም ሁን፤” — ዘፍጥረት 12፥2 🔰 አብርሃምን "ታላቅ ሕዝብም አደርግሃለሁ" ያለውን ፈጣሪ ነው ብለን አጋርን "ዘርሽን እጅግ አበዛለሁ" ያላትን ፍጡር ነው ማለት አንችልም ። መልአኩ ዋሽቷል ካልተባለ በስተቀር ፈጣሪነቱን እየተናገረ እንዳለ መካድ አንችልም ። ♨️ "ዘርሽን እጅግ አበዛለሁ" ማለት "ፈጣሪ ነኝ" እንደማለት ነው ፤ እንደዚህ አይነቱን ንግግር ፍጡር ሊናገር አይችልም ፤ ስለዚህ መልአኩ ፈጣሪ ነው ። አጋር ኤልሮኢ ብላ የጠራችሁ ይሄንን ንግግር የተናገረውን መልአክ ነው ። የጌታ ፀጋ ከሁላችንም ጋር ይሁን 🙏🙏🙏

  • 2 авг.2645из Yirgalem_apologetics

    ⭕️ ክርስቶስ መልአክ ነበር ‼️ ♨️ ክርስቶስ በብሉይ ኪዳን መልአክ እንደነበር የሚያስተምሩ ሰዎች እነማን እንደሆኑ የወንጌል አማኞችን ብትጠይቁ "የይሆዋ ምስክሮች" የሚባሉትን የሚጠቁሙ ጥቂት የማይባሉ ናቸው ። ይሄ ትምህርት የራሳችን መሆኑን ብነግራችሁ ምን ትሉኛላችሁ ?? አዎ !! ክርስቶስ በብሉይ ኪዳን የእግዚአብሔር መልአክ ነበር !! ይሄ ጉዳይ በሥላሴ አስተምህሮ ውስጥ በጣም ትልቅ ቦታ ያለው ወሳኝ ጉዳይ ነው ። 🔰 ክርስቶስ መልአክ ነበር ሲባል ፍጡር ነበር ማለት የሚመስላቸው ብዙ ክርስቲያኖች አሉ ፤ ምክንያቱም "መልአክ" የሚለው ቃል ለፍጡራን ብቻ ጥቅም ላይ እንደዋለ ስለሚታሰብ ። 🏷 "መልአክ" የሚለው ቃል ባህሪን ወይም ተፈጥሮን የሚያመለክት ስያሜ ሳይሆን ግብርን (ተግባርን) የሚያመለክት ስያሜ ነው ። ለምሳሌ ፦ ሀኪም ፣ አርሶአደር ፣ አሽከርካሪ ፣ ወዘተ ያሉ ስያሜዎች ባህሪን የሚያመለክቱ ስያሜዎች አይደሉም ፤ "መልአክ" የሚለውም ቃል ለየትኛውም የተላከ ማንነት የሚውል ስያሜ እንጂ ተፈጥሮን የሚያመለክት ስያሜ አይደለም ። 🔰 እግዚአብሔር ፍጡራን የሆኑ መልዕክተኞች አሉት (ቅዱሳን መናፍስት እና ቅዱሳን ሰዎች) ፤ ነገር ግን ፍጡር ያለሆነ መልዕክተኛም ነበረው ፤ ይሄም መልዕክተኛ "የቃል ኪዳን መልዕክተኛ" ተብሎ ተጠርቷል ። 📜 “እነሆ፥ መልእክተኛዬን እልካለሁ፥ መንገድንም በፊቴ ያስተካክላል፤ እናንተም የምትፈልጉት ጌታ በድንገት ወደ መቅደሱ ይመጣል፤ የምትወዱትም የቃል ኪዳን መልእክተኛ፥ እነሆ፥ ይመጣል፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።” — ሚልክያስ 3፥1 📜 Malachi 3:1 [1]“Behold, I send My messenger, And he will prepare the way before Me. And the Lord, whom you seek, Will suddenly come to His temple, Even the Messenger of the covenant, In whom you delight. Behold, He is coming,” Says the Lord of hosts. 🧱 በዚህ ትንቢት ውስጥ ስለ ሁለት አካላት የተፃፈ ነገር እናገኛለን ። "መልዕክተኛዬ" የተባለው መጥምቁ ዮሐንስ ነው ፤ ስለእርሱም የተነገረው "መንገድንም በፊቴ ያስተካክላል" የሚለው ብቻ ነው ፤ ከዛ በታች ያለው መጥምቁ ዮሐንስን አይመለከትም ። 📜 “እነሆ፥ መንገድህን በፊትህ የሚጠርግ መልክተኛዬን በፊትህ እልካለሁ ተብሎ የተጻፈለት ይህ ነው።” — ሉቃስ 7፥27 🧱 ስለዚህ የቃልኪዳን መልዕክተኛ የተባለው መጥምቁ ዮሐንስ አይደለም ፤ ከዛ ይልቅ መጥምቁ ዮሐንስ አስቀድሞ የቃልኪዳን መልዕክተኛ ከመምጣቱ በፊት አስቀድሞ መንገድ እንዲያስተካክል የተላከ መልዕክተኛ ነው ። ከመጥምቁ ዮሐንስ በኋላ የሚመጣው ደግሞ ክርስቶስ እንደሆነ በመፅሐፍ ቅዱስ ውስጥ በግልፅ ተፅፏል ። 📜 “እኔስ ለንስሐ በውኃ አጠምቃችኋለሁ፤ ጫማውን እሸከም ዘንድ የማይገባኝ ከእኔ በኋላ የሚመጣው ግን ከእኔ ይልቅ ይበረታል፤ እርሱ በመንፈስ ቅዱስ በእሳትም ያጠምቃችኋል፤” — ማቴዎስ 3፥11 🔰 ከመንገድ ጠራጊው መልዕክተኛ በኋላ የሚመጣው የቃልኪዳን መልዕክተኛ በመንፈስ ቅዱስ የሚያጠምቀው ክርስቶስ ነው ። "መልዕክተኛ" እና "መልአክ" የሚሉት ሁለት ቃላት ደግሞ በመፅሐፍ ቅዱስ ውስጥ ተመሳሳይ ትርጉም ነው ያላቸው ፤ የዕብራይስጥ ትርጉሙ ላይ ለሁለቱም የምናገኘው "ማላክ" የሚለው ቃል ነው ። 🔰 ይሄ የቃል ኪዳን መልዕክተኛ (የቃል ኪዳን መልአክ) በብሉይ ኪዳን መፃህፍት ውስጥ በተደጋጋሚ "የእግዚአብሔር መልአክ" ተብሎ ተጠርቷል ። ክርስቶስ በሥጋ ተገልጦ በደሙ አዲስ ኪዳንን ከመመሥረቱ በፊት ከእስራኤል ሕዝብ ጋር በኮሬብ ቃልኪዳን አድርጓል ፤ ይሄንንም በራሱ አንደበት ተናግሯል ። 📜 “የእግዚአብሔርም መልአክ ከጌልገላ ወደ ቦኪም ወጥቶ እንዲህ አለ፦ እኔ ከግብፅ አውጥቻችኋለሁ፥ ለአባቶቻችሁም ወደ ማልሁላቸው ምድር አግብቻችኋለሁ፤ እኔም፦ ከእናንተ ጋር ያደረግሁትን ቃል ኪዳን ለዘላለም አላፈርስም፤” — መሳፍንት 2፥1 🧱 መልአኩ የራሱን ድርጊት እየተናገረ እንጂ የሌላውን ድርጊት ሪፖርት እያደረገ አለመሆኑን እስከ ቁጥር 4 ድረስ ሄደን መመልከት እንችላለን ። መልአኩ በንግግሩ መግቢያ ሆነ መጨረሻ ላይ "እግዚአብሔር እንዲህ ይላል" ወይም "ይላል እግዚአብሔር" የሚል ነገር ፈፅሞ ሲናገር አንመለከትም ፤ ስለዚህ መልአኩ ከእስራኤል ሕዝብ ጋር ቃል ኪዳን አድርጓል ማለት ነው ። ከእስራኤል ሕዝብ ጋር ደግሞ ቃል ኪዳን ያደረገው እግዚአብሔር ነው ። 📜 “አምላካችን እግዚአብሔር በኮሬብ ከእኛ ጋር ቃል ኪዳን አደረገ።” — ዘዳግም 5፥2 🧱 ስለዚህ መሳፍንት 2:1 ላይ የተናገረው መልአክ እግዚአብሔር ነው ማለት ነው ። የቃልኪዳን መልዕክተኛ የተባለው ክርስቶስ ስለሆነ መሳፍንት 2:1 ላይ የተናገረው መልአክ ክርስቶስ ነው ። 🔰 ክርስቶስ በብሉይ ኪዳን መልአክ ነበር የሚለው ትምህርት የእኛ የወንጌል አማኞች አስተምህሮ ነው ፤ "የይሆዋ ምስክሮች" ፍጡር መልአክ ነበር ብለው ነው የሚያምኑት ፤ እኛ ደግሞ ያልተፈጠረ መልአክ ነው የምንለው ። የጌታ ፀጋ ከሁላችንም ጋር ይሁን 🙏🙏🙏

  • አንተም አምላክህን እግዚአብሔርን በፍጹም ልብህ በፍጹምም ነፍስህ በፍጹምም ኃይልህ ውደድ።        ዘዳግም 6:5

  • 25 июл.454из Yirgalem_apologetics

    የመጨረሻ የድጋፍ ጥሪ ለወንጌል አማኞች ሐምሌ 25 ቀጣይ ቅዳሜ ወደ ለኩ እንሄዳለን ፤ ለዚህም የሚያስፈልገው የትራንስፖርት እና የምሳ ወጪ ተሸፍኗል ፤ በገንዘባችሁ ያገዛችሁንን ከልብ እናመሰግናለን ። ከዚህ በኋላ የቀረው ሥራ በራሪ ወረቀቶችን ማዘጋጀት ነው ፤ ለዚህ ሥራ የሚያስፈልገው 2000 ብር ብቻ ነው ። 40 ሰዎች 50 ብር ቢልኩ ሥራውን ማጠናቀቅ እንችላለን ። ✅ 1000529093776 CBE Samuel Adane የሚሰራጨው በራሪ ወረቀት በጣም አስፈላጊ እና ወሳኝ ስለሆነ በዚህ ጉዳይ ሁላችሁም ተሳተፉ ።

  • 24 июл.3641из Yirgalem_apologetics

    Shared by One Read - an all-in-one file viewer: https://st.simplehealth.ltd/uAJjyu

  • 23 июл.4451из Yirgalem_apologetics

    የፎቶ ማስረጃዎችን የያዘ Pdf ነው Shared by One Read - an all-in-one file viewer: https://st.simplehealth.ltd/uAJjyu ይሄንን Pdf Document Reader PDF Editor በሚለው app ክፈቱት ። በሌላ app ከሰራላችሁም ችግር የለውም ፤ ካልሠራ ግን ሊንኩን ነክታችሁ ከ play store አውርዱት

  • 22 июл.482из exposingOJ

    ወገኖች ይህን ዲቤት በደንብ ማስታወቂያ ስሩበት እሺ በየቻናሎቻችሁ ለጥፉ

  • 22 июл.3761из Yirgalem_apologetics

    "እኔ እግዚአብሔር ነኝ" የማለት መብት ያለው ብርቅዬ ፍጡር 😳😳😳😳 "በዚህ መልአክ ላይ የእግዚአብሔር ስም እየተጠራ ይጠቀምበት ነበር ይህ መልአክ ነበር ለሙሴና ለእግዚአብሔር ሕዝብ የተገለጠው ፤ "እኔ እግዚአብሔር ነኝ" እያለ ከእግዚአብሔር የሰማውን ለመናገር መብት የተቀበለ የአምላካችን ተወካይ ነበር" ኢየሱስን ማን ይሉታል = ገፅ 25

  • 20 июл.3942из Yirgalem_apologetics

    💢 ይሄንን ጥያቄ ጠይቋቸው 🤔🤔 🔰 የእግዚአብሔር ስም ፣ ሥልጣን እና ክብር ላይ የወደቀ ቤተ-እምነት እንዴት ዶክትሪን አለኝ ይላል ?? 😳😳 🔰 ከኦጄዎች ጋር መወያየት ያለብን "እግዚአብሔር" ተብሎ የሚጠራው ማነው ፣ እንደ እግዚአብሔር መናገር የሚችል ማነው የሚለው ርዕስ ላይ ነው

  • 20 июл.4231из Yirgalem_apologetics

    💢 የቃልኪዳን መልዕክተኛ (መልአክ) 🔰 እግዚአብሔር "መልአክ" ተብሏል ‼️ 🔰 ያዕቆብ የታገለው ከፍጡር መልዓክ ጋር አይደለም 😨😨😨😨 🔰 እስራኤላውያንን ከግብፅ ያወጣቸው ፤ ቀን በደመና ሌሊት ደግሞ በእሳት አምድ በፊታቸው የሄደው እግዚአብሔር መልአክ እግዚአብሔር ነው ♨️ ይሄንን audio #download አድርጋችሁ (አውርዳችሁ) ለጓደኞቻችሁ ቀጥታ ላኩላቸው ፣ ይሄ audio በሁሉም አቅጣጫ መሰራጨት አለበት ‼️

  • ወደ ለኩ ለመምጣት ወስነናል ‼️ እኛ የ ይርጋለም ከተማ የእቅበተ-እምነት (Yirgalem Apologetics Team) ቡድን አባላት የሐምሌ ወር የመጨረሻ ሳምንታት ውስጥ ( በተለይ ከሐምሌ 20 እስከ ሐምሌ 30 ) ወደ ለኩ ከተማ መጥተን የወንጌል ሥራ ለመሥራት ተስማምተናል ። ወደ ለኩ ከተማ የምንመጣው ደግሞ የሥላሴን አስተምህሮ የማይቀበሉ ወገኖችን በጥያቄ ለመሞገት እና ትምህርታቸውን challenge ለማድረግ ነው ። ይሄንን ሥራ ለመሥራት ከሚመጡት ወጣቶች መሀከል ጥቂት የማይባሉ የትራንስፖርት እና የምሳ ወጪ ማግኘት የማይችሉ ልጆች ስላሉ የእናንተን ድጋፍ እንፈልጋለን ፤ ለጥቂት ሰው ሸክም ከመጫን ብዙ ሰው ጥቂት ነገር ማድረግ ቢችል በሚል እንጂ ገንዘብ የምንጠይቀው ሰው ጠፍቶ አይደለም ይሄንን ጥሪ ያቀረብንላችሁ ። 20 ሰው 100 ብር ቢልክ የ 5 ሰዎችን የትራንስፖርት እና የምሳ ወጪ መሸፈን ይቻላል ። መቅረት የሌለባቸው ሰዎች እንዳይቀሩ በዚህ አግዙን ። 20 ሰው ብቻ 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇 1000529093776 CBE Samuel Adane ከኦጄዎች የሚመጣው ስድብ እና ማንጓጠጥ አይቀሬ እንደሆነ ሁሉ ከእናንተ ዘንድ የምንጠብቀው ፈጣን ምላሽ እንደማይቀርብን ተስፋ እናደርጋለን ። የጌታ ፀጋ ከሁላችንም ጋር ይሁን 🙏🙏🙏

  • https://vt.tiktok.com/ZS9MELyVPor8t-7HsLP/

  • https://vt.tiktok.com/ZS9MELyVPor8t-7HsLP/

  • 15 июл.5563из Yirgalem_apologetics

    💢 የእግዚአብሔርን መልአክ በተመለከተ ለኦጄዎች የቀረቡ 10 ጥያቄዎች 23 mb 💾 98 min 🕰 🔰 መልአኩና አጋር 🔰 መልአኩና አብርሃም 🔰 መልአኩና ያዕቆብ 🔰 መልአኩና ሙሴ 🔰 መልአኩና የደመናው አምድ 🔰 እግዚአብሔር ስለ መልአኩ የተናገረው 🔰 መልአኩና በለዓም 🔰 መልአኩ በቦኪም የተናገረው ቃል 🔰 መልአኩና ጌዴዎን 🔰 መልአኩና የሳምሶን ወላጆች ⚜️ ይሄ audio በዋናነት የተዘጋጀው በለኩ ከተማ ያሉ የሥላሴ አማኞች በከተማቸው ያሉ ኦጄዎችን እነዚህን ጥያቄዎች እንዲጠይቁ ለማነሳሳትና ለማገዝ ነው ። ♨️ ይሄንን audio #download አድርጋችሁ (አውርዳችሁ) ለጓደኞቻችሁ ቀጥታ ላኩላቸው ፣ ይሄ audio በሁሉም አቅጣጫ መሰራጨት አለበት ‼️

  • የለኩ ነዋሪዎች ይሄንን ግሩፕ join በሉ https://t.me/Leku_Apologetics

  • https://t.me/Leku_Apologetics?videochat

  • 11 июл.56534из doyouknow34

    ‎➊ "የእግዚአብሔር ልጅ" በሚለው መጠሪያ ውስጥ "እግዚአብሔር" የተባለው አብ ነው [ 2 ዮሐ 1:3 ] ፤ "የሰው ልጅ" በሚለው መጠሪያ ውስጥ "ሰው" የተባለው ማነው ?? ‎ ‎❷ ኢየሱስ "የሰው ልጅ" የተባለው በትክክል የሰው ልጅ (እንደ እኛ) ስለሆነ ነው ወይስ እንዲያው ለስሙ ብቻ ነው የሰው ልጅ የተባለው ?? የኢየሱስ ሥጋ ሰማያዊ ከሆነ ለምን "የሰው ልጅ" ተባለ ?? የሰው ልጅ የተባለበት ምክንያት ይብራራ ። ‎ ‎❸ የኢየሱስ ሥጋ ሰማያዊ ሥጋ ከሆነ ፣ እንዴት መፅሐፍ ቅዱስ ኢየሱስ የማርያም የበኩር ልጅ እንደሆነ ሊናገር ቻለ ?? ( የበኩር ልጅዋንም ወለደች ...  ሉቃስ 2:7)  እንዴትስ ማርያም የጌታ እናት ተባለች ?? (የጌታዬ እናት ...  ሉቃስ 1:43)   ‎ ‎❹ ኢየሱስ እንደሌሎቹ ልጆች በሥጋና በደም እንደተካፈለ መፅሐፍ ይነግረናል ‎ ‎📜 “እንግዲህ ልጆቹ በሥጋና በደም ስለሚካፈሉ [Forasmuch then as the children are partakers of flesh and blood ] ፥ እርሱ ደግሞ በሞት ላይ ሥልጣን ያለውን በሞት እንዲሽር፥ ይኸውም ዲያብሎስ ነው፥ በሕይወታቸውም ሁሉ ስለ ሞት ፍርሃት በባርነት ይታሰሩ የነበሩትን ሁሉ ነጻ እንዲያወጣ፥ በሥጋና በደም እንዲሁ ተካፈለ ። [he also himself likewise took part of the same ] ‎  — ዕብራውያን 2፥14-15 ‎ ‎◆ "እንዲሁ ተካፈለ" (He also ... took part of the same)  ከተባለ እንዴት ነው ከሌሎቹ በተለየ የኢየሱስ ሥጋ ሰማያዊ የሚሆነው ??  ልጆቹ የሥጋና የደም ተካፋዮች ናቸው (የእንግሊዘኛ ትርጉሙ) ፣ ኢየሱስም ከዚያው ተካፍሏል (የእንግሊዝኛ ትርጉሙ) ‎

  • 11 июл.42912из doyouknow34

    ‎➊ ኢየሱስ አብም ወልድም ከሆነ ፣ ኢየሱስ የማን አባት የማንስ ልጅ ነው ?? ‎አብ ልጅ አለው ?? ➾ ወልድ አባት አለው ?? ➾ ‎ኢየሱስ የአብ ልጅ ነው ?? ➾ ኢየሱስ የወልድ አባት ነው ??  ኢየሱስ የአብ ልጅ ተብሏል [ 2ኛ ዮሐ 1:3 ] ፤ ኢየሱስ የወልድ አባት ተብሎ የተጠራበትን ቦታ አሳይ ። ‎ ‎❷ ኢየሱስ ወልድ ስለሆነ አብን አባት ሆይ ብሎ ይጠራዋል [ ሉቃስ 23:24 ፣ ማቴ 11: 25-26 ] ፤ አብ ከሆነ ወልድን ልጄ (ልጄ ሆይ) ብሎ ሲጠራ መደመጥ አለበት ፣ በአራቱም ወንጌላት ከኢየሱስ ንግግሮች ኢየሱስ ወልድን "ልጄ" ብሎ የጠራበትን ቦታ አሳይ ። ‎ ‎❸ አብ ክርስቶስ አለው [ መዝ 2:2 ፣ ሉቃስ 2:26 ] ፣ አብ ክርስቶስ የሆነ ልጅ አለው [ 2ኛ ዮሐ 1:3 ] ፣ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ነው [ 1ኛ ቆሮ 3:23 ] ፣ የክርስቶስ ራስ እግዚአብሔር ነው [ 1ኛ ቆሮ 11:3 ]   አብ ልጁን ቀብቷል [ ሐዋ 4:27 ] ‎ ‎➤ ኢየሱስ ክርስቶስ አለው ?? ‎➤ ክርስቶስ የኢየሱስ ነው ?? ‎➤ የክርስቶስ ራስ ኢየሱስ ነው ?? ‎➤ የኢየሱስ ክርስቶስ አለ ??      (the Christ of Jesus) ‎➤ በኢየሱስ የተቀባ መሲሕ አለ ?? ‎