tgindex
ኑ አብረን እናንብብ 📖📚

ኑ አብረን እናንብብ 📖📚

Статистика

ማንበብ ፋሽን ነው 📖📚 ኑ አብረን በማንበብ ፋሽን እንከተል

Последний пост
12 июн.
Последнее чтение
14 авг.
Постов за неделю
0
Всего постов
22
Тип
открытый
Язык
ti
В каталоге с
14 авг.
Подписчики
352
0 за 1 дн.
Сутки
0
0,00%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
184
22 постов
Вовлечённость
52,3%
к подписчикам
Постов в день
0,0
всего 22
Упоминаний
0
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
1/48двое суток
1/72трое суток

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • "በህይወትሽ ውስጥ ካገኘሻ ቸው ጥሩ ምክሮች የማትረሺ ው የቱን ነው?" አለኝ ወሬ ለመጀመር ያክል..... "ሁሉም ሰው ለራሱ ጥቅም ብቻ ነው የሚያስበው ለሰው ብለህ እራስህን አትጉዳ፤ ደስታህን አትጣ!"... አልኩት በሃሳብ እየሄድኩ.. "ደስ የሚል ምክር ነው ግን ማን ነው እንደዛ ያለሽ ?" አለኝ ቀና ብሎ... "በጣም የወደድኩት... በጣም የጠላሁት ሰው ነው!" የህይወቴን ትልቁን ክህደት ያስተማረኝ ሰው! አልኩት በሃዘን... ወደ ዝምታችን ተመለስን! ሰውን ማመን እንደሌለብን የሚያስተምሩን በጣም ያመናቸው ሰዎች ናቸው!

  • አንዳንዴ መጨረሻዎች እንደ ቡና መራራ ቢሆኑም ያነቁናል! ☕️💡 ታዋቂው ፀሀፊ ማህሙድ ዳርዊሽ እንደተናገረው: “አንዳንድ መጨረሻዎች እንደ ቡና መራራ ናቸው፤ ነገር ግን ንቁ ሰው ያደርጉናል።” ይህ ማለት፣ በህይወታችን ውስጥ የሚያጋጥሙን አንዳንድ ክስተቶች ወይም ግንኙነቶች ሲያበቁ ከባድ እና አሳዛኝ ሊሆኑ ይችላሉ። ልክ እንደ መራራ ቡና መጀመሪያ ላይ ለመዋጥ የሚያስቸግር ቢሆንም፣ ከዛ በኋላ ግን አይናችንን እንድንከፍት፣ ነገሮችን በተለየ መንገድ እንድናይ እና አዲስ ትምህርት እንድንቀስም ይረዱናል። መራራ መጨረሻዎች ለቀጣይ ጉዟችን ጠቃሚ ትምህርት ሰጥተውን፣ ይበልጥ ጠንካራ እና ንቁ እንድንሆን ያደርጉናል። . .

  • ......! ልብ ተስፋ ሲቆርጥ ሆድ መቻል ሲያቅተው እንጀትም ሲቆረጥ አይንም እምባ ሲያጥረው አለኝ ያሉት ሲተን በእጅ ያለ ሲበተን ያመኑት ሲከዳ ዘመድ ሲሆን ባዳ ነገርም ሲከፋ ጨለማም ሲነግስ ሰው ነኝ ባይ ቢጠፋ                    ለችግር የሚደርስ ፈተና ቢበዛ እንቅፋትም ቢኖር መሄጃ ቢጠፋ እግርም ቢታሰር     አለም ብትከፋ መግፋት ቢያስደስታት     መች ትቶ ይተዋል የላይኛው አባት!!

  • #ማርቆስ 8÷34 ሁሉም አለው አንድ መስቀል... ሚስጢር  ለሰው ማይነገር፤ ብቻውን አስታሞት የሚቀር፤           በፈገግታ የሚሸፈን፤           በጌጣጌጥ የሚዳፈን፤          በብልጭልጭ የሚታፈን፤ አለው ህቡእ ማንነት፤ ፈጣሪ ብቻ የሚያውቅለት፤ እንባ  አፍሶ የማይበርድለት፤ ዛሬና ነገ አንድ የሆኑበት፤           ሰአት የማያቅ .....           እለት እለት የሚጨንቀው፤           ለሌላ ሰው የማይደንቀው፤           ለርሱ ብቻ የሚዘልቀው፤           እድሜ ልኩን የማይለቀው፤ አንድ መስቀል አንድ መከራ፤ ቦታ የማይመርጥ በሁሉ ስፍራ፤           ሁሉ አለው አንድ መስቀል፤           እንደ ሰንኮፍ ማይነቀል፤ የዘመናት የአመታት የእድሜ ልክ ፤ ብቻህን ስትሆን የሚጥልክ፤        ያንተው ሚስጥር..       ያንቺው ሚስጥር...       ሰው ማይገለጠው፤       ለአፍታ ጆሮውን የማይሠጠው፤                 ግና ካልፀና ከራሱ ተርፎ፤ መውደቅ አይቀርም....              በራሱ መረብ እራሱን ጠልፎ፤              መጮህ ብቻ ነው...              በራሱ ጅራፍ ራሱን ገርፎ፤ ሚዛን እንዲኖር ጥሩና መጥፎ፤ በመስቀሉን ይዞ... ለሚታገስ ግን ያየዋል አልፎ።

  • የጠቋር ሚስት ጓደኛዬ አዲስ ሙሽራ ነው። ገና ስድስት ወሩ ነው ካገባ። የሆነ እሁድ ጠዋት ልጠይቃቸው ቤታቸው ስሄድ ይሄን ገንገበት ጓደኛዬን ባለቤቱ “ዳዲ” እያለች ስትጠራው ሰማሁ። ተወልዳ እስክታድግ በአንድ የአምበሳ ቆዳ ጫማ እየዳከረ ያሳደጋትን የአባቷን ስም እንደቀልድ ለስድስት ወር ባሏ መስጠቷ ግርም አለኝ። አጎቴ "ሴትና የቀበሌ ቤት የኔ ነው አይባልም" የሚለው እውነት ሳይሆን አይቀርም። ቤታቸው የሄድኩት እሁድ ጠኋት ስለነበር “ቸርች ልንሄድ ስንል መጣህ” ብለው አብረን ካልሄድን አሉኝ። ላለመሄድ ብሞክርም ባለቤቱ ቆጣ ብላ “ኖህ! ወደድራፍት ቤት እንሂድ ቢሉህ መች እምቢ ትላለህ? በል ተነስ” አለችኝ። ይሄ ግምብ ራስ ባሏ ድራፍት እንደምወድ ነግሯታል ማለት ነው። ሰነድ መሻሻጥ ተጀመረ? ብዬ እያመነታሁ አብሬያቸው ሄድኩ። የወሰዱኝ ቸርች አንድ ነብይ የሚያገለግልበት አዲስ የፕሮቴስታንት ቤተክርስቲያን ነው። ጓደኛዬ ባለቤቱ በቅርቡ ጌታን እንደተቀበለች ነግሮኛል። ገና ውስጥ ገብተን አረፍ እንዳልን በከፍተኛ ድምፅ እየጮኸች ትፀልይ ጀመር። “ጌታ ሆይ ለዚህ አብሮን ለመጣው፣ ነፍሱ በሃጢአት ለታሰረችው ጎስቋላ ወንድሜ ዛሬ ድረስለት” ስትል ደነገጥኩ። ጭራሽ ስለኔ ነው ፀሎቱ? “ጌታ ሆይ” አለች ጭራሽ ተንጠራርታ እጇን ትከሻዬ ላይ ጭና። ድምጿ እየጨመረ ነው “ጌታ ሆይ፥ ዛሬ ስለዚች ነፍስ እፀልያለሁ ...” አለች። {እቺ ነፍስ የተባልኩት እኔው ነኝ} “ዛሬ እቺ ነፍስ ከስካርና ከሃጢአት ቀምበር እንድትላቀቅ እፀልያለሁ፥ እቺ ነፍስ ዛሬ ከዝሙትና ጌታ ከማይከብርበት የሃጢአት ልምምድ እንድትፈታ እፀልያለሁ” ስትል ቀና ብዬ ምእመኑን አየሁ። እኛ አጠገብ ያሉ ምእመናን ሁሉም ወደኔ እጃቸውን ዘርግተው ይፀልዩልኛል። የት ልግባ? ጭራሽ በሰው ሁሉ ፊት ሰካራም ነው። ያመነዝራል። ትበለኝ? ለምን አንደኛዋን የቲክቶክ ቪዲዮ አትሰራብኝም? ዞር ብዬ ጓደኛዬን ሳየው ሳቁን አፍኖ በቆረጣ ያየኛል። በስጋ ብገለጥበት ደስ ባለኝ። እሱ ነው አብረን በነበርን ግዜ ምንሰራውን ነገር ሁሉ ዘክዝኮ ነግሯት የሰው መሳቂያ ያረገኝ። የተወሰነ ቆይቶ ነብዩ ወደመድረክ ወጥቶ ፀሎት ማድረግ ጀመረ። ቤቱ ፀጥ አለ። አንዳንድ ሰዎች ብቻ በየመሃሉ አሜን ይላሉ። እሱም ትንሽ ከፀለየ በኋላ ... “የጌታ መንፈስ ጅብ ጋላቢ መንፈስ ያሳየኛል” አለ። የዚህ ግዜ የጓደኛዬ ሚስት ዞር ብላ አታየኝም መሰላችሁ? ምናባሽ ላርግሽ? ብላት ደስ ባለኝ። አንተ ነህ ለማለት ፈልጋ ነው? ይሄ የተረገመ ልጅ ጅብም ይጋልባል ብሏት ይሆን እንዴ? ነብዩ ቀጠለ። “በጉባኤ ውስጥ አንድ ሰው ይታየኛል። ቤተሰቦቹ ቃልቻ ነው ሚያመልኩት። እሱንም በልጅነቱ በአጋዘን ደም ያጥቡት ነበር። ዋናው የአጋንንቶች አለቃ ይጠቀምበታል” ሲል በሃዘኔታ እንደገና ዞራ አየችኝ። አረ እቺ ሴትዮ ለምን አትፋታኝም? እያልኩ ፀሎቱን መከታተል ጀመርኩ። ነብዩ ወደኔ አካባቢ ፍጥጥ ብሎ ካየ በኋላ ከመድረክ ወርዶ ቀጥ ብሎ መጣ ..... አሁንስ እኔም ፈራሁ። ስለኔ ነው እንዴ ሚያወራው? የሚል ሃሳብ ውልብ አለብኝ። ምናልባት ነፍስ ሳላውቅ ቤተሰቦቼ እንዳለው በአጋዘን ደም አጥበውኝ ይሆን እንዴ? መቸስ ሰው ማመን ከባድ ነው በዚህ ዘመን ምናምን እያልኩ ሳስብ ነብዩ አይኑን አፍጥጦ ቀጥ ብሎ እኛ ወዳለንበት መጣና እጁን አንስቶ....... የጓደኛዬ ሚስት ላይ ሲጭን ከተቀመጠችበት ወምበር ሁለት ሜትር ወደላይ ነጥራ መሬት ላይ ተነጠፈች። እግዚኦ ማህረነ ክርስቶስ። ምን ጉድ ነው? በኔ ሲስቅ የነበረው ጓደኛዬ ሚስቱ እንደዚያ ስትሆን ሲያያት ክፉኛ ደነገጠ። እኔም ምን መጣ ብዬ አንዴ ነብዩን አንዴ እሷን ማየት ጀመርኩ ነብዩ “ዋናው መንፈስ ተያዘ!” ሲል ጉባኤው በጩኸትና በጭብጨባ ተሞላ። ከዚያማ ያቺ ድምፀ ለስላሳዋ የጓደኛዬ ሚስት በሙላቱ አስታጥቄ ድምፅ ትለፈልፍ ጀመር “ተቃጠልኩ! አረርኩ!” “ማነህ?” አለ ነብዩ “ጠቋር ነኝ” “ተናገር የት ነው የያዝካት?” “ባሏ ነኝ። ከልጅነቷ አሳድጌ ነው ያገባኋት” አለ ሴጣኑ። ጓደኛዬን አየሁት ሚገባበት ጠፍቶታል። “ጭራሽ የሌላ አካልን ሚስት ነው ያገባሁት?” የሚል ይመስላል። አጋንንቱ ጭራሽ ወደሱ አፍጥጦ “አጠፋሃለሁ አንተ እርጉም ሚስቴን ነጠቅከኝ” እያለ መጮህ ጀመረ። ቺት አድርጋበት መሆኑ ነው። ጓደኛዬ እንዲሁም ፈሪ ነው ጭራሽ አሁን ከሰይጣን ጋር የግል ፀብ ውስጥ በመግባቱ ያልበው ጀመር። ያቺ መላአክ የመሰለች ሚስቱ ጭራሽ አይኗን አፍጣ በወፍራም ድምፅ ዛቻዋን ቀጠለች። “ወንድወሰን ደበበ ጊሚራው” አለችው ሌባ ጣቷን ወደሱ ጠቁማ። {ዳዲ ቀረ በቃ} ነብዩ ዝም ብሎ ያያል። “አንተን ካላጠፋሁ እኔ ጠቋር አይደለሁም” አለ መንፈሱ። ጓደኛዬ እንባ ተናነቀው። በሆዱ "Who TF did i marry?" እያለ ነው “ብዙ ግዜ በተኛህበት በገጀራ እንድትሰነጥቅህ አቅጄ ነበር። ዛሬ ይሄ ነብይ ቀደመኝ” እያለ ማጓራት ጀመረ። ጓደኛዬ እንባውን በአራት መንታ አወረደው። ምን ውስጥ ነው የገባሁት? የሚል ይመስላል። ብቻ አጋንንቱ ከነብዩ ጋር ውጣ አትውጣ እያለ ሲታገል እኔ እንደምንም ሾልኬ ወጥቼ ወደቀበሌ ጃምቦ ቤት ሮጥኩ። ከአዳራሹ ወጥቼ ጥቂት እንደሮጥኩ ሩጫዬን አቀዘቀዝኩና ወደኋላዬ ስዞር ጓደኛዬ ኮቱን ጥሎ በሩጫ ወደኔ ይመጣል። አጠገቤ ሲደርስ እያለከለከ ቆመና “ወዴት ነው ጥለኸኝ ምትሮጠው” አለኝ “እንዴ አንተስ ሚስትህን ጥለህ ወዴት ነው?” ስለው “አፍህን ዝጋ” ብሎኝ አብሮኝ ወደግሮሰሪ አመራ። አሁን ሰባተኛ ጃምቧችን ላይ ደርሰናል። “እኔ ግደሉኝ እንጂ ያቺን ሴት አምኜ እዛች ቤት አላድርም” ስላለ ተሰብስበን ወደቤቱ እንዲሄድ እየለመንነው እንገኛለን። By Noah Daniel

  • አለማየው ገላጋይ ውልብታ መፅሀፍ *"የገጣሚዋ - ገጣሚ"* ገጣሚዋ አይኗ - ያፍራል _ ሲያፍር ያምራል፣ ጉንጯ ያፍራል _ ሲያፍር ይቀላል _ ሲቀላ ግመጡኝ - ግመጡኝ....... ይላል። እግሯ ያፍራል - ሲያፍር - ወንበር ሥር - ይደበቃል። እና ለአይናፋርነቷ እየሳሳሁ _ ለስላሳ ጥያቄ አቀርብላታለሁ። ‹‹እወድሻለሁ›› አይናፋረዋ ገጣሚ _ አፏ ስለሚያፍርባት - ቦርሳዋን ከፍት አድርጋ ከወረቀቶች መካከል _ አንዱን ታቀብለኛለች። ግጥም ነው። እንዲ ይላል ‹‹እወድሻለሁ ማለት _ የልብ አያደርስም እንቀመጥና _ ንገረኝ ሁሉንም›› *" ከዛ _ ካፌ እንቀመጣለን። ‹‹ሻይ ይሻላል? ወይስ ወተት ትጠጪ?›› ... ስላት የገጣሚዋ አይናፋር ጣቶች _ እየተሽኮረመሙ ወደቦርሳዋ ይንሿከኩና _ አንዲት ብጣሽ ወረቀት ያደርሱኛል። ‹‹ሻይማ ውኃ ነው _ ምኑን ይጠቅመኛል፣ ወተት ልጅ አይደለሁ - የእናቴ በቅቶኛል፣ ቀዝቀዝ እንዲያደርገኝ ለስላሳ ይሻለኛል።›› ለስላሳ አዝላትና _ ዝም ተባብለን _ እንቀመጣለን። አሁንም _ ተሽኮርማሚ ጣቶቿ _ ብጣቂ ወረቀት ጠረጴዛ ላይ - ያኖራሉ። ‹‹ዝም አልበል ዝም አትበል እንጫወት በጣም፣ ከእንግዲህ ይቺ ቀን ተመልሳ አትመጣም።›› *" ሲመሽ"* ...... ‹‹ለምን ዝም ትላለህ ጨለማው ሲያጠቃ አንድ ላይ ተኝተን አንድ ላይ እንንቃ።›› Join us and share @e_n_k_u_0

  • አኩርፈሻል መሰል… ➖➖➖➖➖ (ሰለሞን ሳህለ) ግራ እጄን አመመኝ… ከበረዶ በልጦ ይሄው ቀዘቀዘ መራመድ አቃተው… ለእርምጃ ሰነፈ ቀኝ እግሬም ተያዘ የጎረስኩት ሁሉ… አልጣፍጥህ አለኝ ጣእም ጣሙን አጣ የመሬት መንቀጥቀጥ… የሚያስነሳ ንዝረት አናቴ ላይ ወጣ ሁሉም ፉርሽ ሆነ ህዝበ አዳም ተቀጣ ህዝበ አዳም ተቆጣ አኩርፈሻል መሰል… ካልጋየ ተኝቼ.. የምሰማው ዜማ እንቅልፍ እንዲወስደኝ የነካውን እንጃ … ባላሰብኩት ቅጽበት እንቅልፌን ነጠቀኝ ለሽራፊ ሰከንድ… ዜማው አልዘመመም ቅኝቱ አልፈረሰም ልክ እንደ ጥንቱ ነው የጎደለው የለም የሆነው ሆኖ ግን… እንዳረጀ ወንበር… የሚንቋቋ ሆኖ ለኔ ይሰማኛል በጨቀየ መንገድ… ፍሬን እንደያዘ የመኪና ጎማ ድምጹ እንደሚረብሽ ልብስ እንደሚያበላሽ ሰባት አይነት ዘፈን… እንደለቀቁበት የገበያ አዳራሽ እንደ ቆራሌው ድምጽ… እንደ ልዋጭ ጥሪ እንደ ፍራሽ አዳሽ እንደ ደፈኑት ቦይ … እንደ አጥር ምሰሶ እንደ ግንቡ ፍራሽ እንደ ጉቶ ጥላ… እንደ ጫካ መንገድ እንደ ነገር ብላሽ እንደ…እንደ…እንደ…እንደ እንዲያ ይሰማኛል አኩርፈሻል መሰል… የቀየዷት በቅሎ … የጎፈላ በሬ ያልተገራ ፈረስ መስኮት የሌለው ዳስ… በር የሌለው ድንኳን የጨበራ ድግስ ምስክር የፈራው… መሃላ የረሳ ሰው ናፋቂ መቅደስ ከራስ የተጣላ… ሩሁን የሳተ ጥምጣም የጣለ ቄስ መምጫው ያልታወቀ… መሄጃው የጠፋ ከባድ አውሎ ንፋስ እንዲያ እንዲያ…እንዲያ እንዲያ እንዲያ ይሰማኛል እንዲያ ይታየኛል አኩርፈሻል መሰል… Join us and share @e_n_k_u_0

  • ወደ እኔ እስክትመጪ ስንት ቀለም ይንጠፍ ስንት ብዕር ልጨርስ ስንት ግጥም ልፃፍ ስንት መጽሃፍ ልድረስ እስክታዪ ናፍቆቴን እስክትመጪ ድረስ ልብሽ እስኪወስን ስንት ቃላት ልድማ እስክትወጂኝ ድረስ ስንት ሀረግ ላስማማ ወደ እኔ እስክትመጪ ስንት ግዜ ኪሪያላይሶን ስንቴ እግዚኦ ልበል ሱባኤ ገብቼ ስንት አመት ልከልከል ወደ እኔ እስክትመጪ ስንት መስክረም ይጥባ ስንት አደይ ይርገፍ ስንት ክረምት መጥቶ ስንት በጋ ይለፍ ስንት ዝናብ ይምታኝ ስንቴ ልደር ዉጪ መወደዴ አሸንፎሽ ወደ እኔ እስክትመጪ Prince_zeresenay

  • አያቴ አደራ ሰጥታኝ የሚያልፍ ዝናብ እንዳይመታኝ፤ ለሚቀር አውርቼ እንዳልቀር ፣ ለሚሞት ህይወት እንዳልሰጥ ፣ ፀጥ! የሚያልፈው አፌን ሳይከፍተው ዝግ ዝም እንድል እንድተው፤ አያቴ አደራ ብላኝ ተባይ ቃል አፌን ቢበላኝ ፣ መተንፈስ ሁሉ እስኪያቅተኝ ምላሴ ሲተናነቀኝ ምላሼ ሲተናንቀኝ ፣ ታግዬ ስንቱን ዝም አልኩት አይቼ ስንቱን አለፍኩት። ዙሪያዬ የነገር እቁብ ቆጥረዋት ምላሴን ከቁብ ፣ ጣል ቢሉኝ ቃል ካንደበቴ አደራ ይዞኝ ያ'ያቴ ፣ አቋም አቅሜን ደብቄ ስንቱን ያለፍኩት ታምቄ ፣ ምስኪን... ራሴን ባለማወቄ! የሚያልፈው ዝናብ ሳይመታኝ ለማለፍ ዙሪያዬን ስቃኝ ፣ ባየሁት ቃሌ እየቃጣ ስውጠው ፈርቼ ጣጣ ፣ ሳምቀው ኖሬ ሳፍነው ምስኪን... ለካስ እኔው ነኝ የማልፈው! ✍️ረድ 8

  • "እንጋባ" ሲል ጠየቃት አሳምነው ። አልተቀበለችውም አስማሩ "ወንድምና እህትነቱ ይበልጣል" አለችው። ተስማሙ ቤት እየመጣ ይጠይቃታል። ቡና ታፈላለች ይጠጣሉ፣ ካላት ታቀርባለች ይበላሉ። አወግተው ይለያያሉ። የትዳር ነገር ዳግም አልተነሳም። አሳምነው አንድ ቀን በጠራራ ፀሀይ መጣ። እንደመጣ የደረበውን ሹራብ አውልቆ አስቀመጠ። ስለ ሙቀቱ ብዙ አውርተው ተለያዩ። አስምሩ አሰምነው ረስቶት የሄደውን ሹራብ ልብሷን ስታጥብ አጠበችለት። ዳግም ሲመጣ ደርቦ ደራርቦ ነበርና የሚያወልቀው እንጂ የሚደርበው ልብስ አላስፈለገውም ጃኬቱን አውልቆ ሄደ። አስምሩ እሱንም አጥባ አኖረችው ሱሪውን ደርቦ መጣ "ወበቀኝ!" አወለቀው። አስማሩ አጥባ አኖረችው ካፕርቱን ጥሎ ሄደ ፣አጥባ አኖረችው አንድ ቀን በጠራራ ፀሀይ ብርድ ልብሱን ለብሶ መጣ ፣አስማሩ "ምነው?" አለችው በጠራራ ፀሀይ ብርድ ሆዴ ገባ አላት ። "ምች ይሆናል" አለችው ። የምች መድኀኒት ብታሽለት ተሻለው ። ሲሻለው ብርድ ልብሱ አላስፈለገውም ጥሎት ሄደ። አስማሩ አጥባ አኖረችው። ትንሽ ቆይቶ ፍራሹን ተሸክሞ መጣ ። "ምነው?" አለችው ። "ላሳድሰው መሄዴ ነው ። አይቼሽ ልለፍ ብዬ ነው"አላት አመነችው ጨዋታው ደራ ፣ ፍራሹን ረስቶት ሄዶ ኖሮ እኩለ ሌሊት ቢመጣ አስማሩ ቦታ ስላጣች ፍራሹን ፍራሿ ላይ ደርባው ደረሰ..ያኔ "ተነሼ ከማለት "ጠጋ በይ" ማለት ቀልሎ ተገኘ። ጠጋ አለች 😊🅦🦋 ደራሲ:- ዓለማየሁ ገላጋይ

  • (ከላይ የቀጠለ) ---- ‹‹ሆዴ ውስጥ የሚንተከተክ ሚጢጢ እሳተ ገሞራ አለ ልበል ?›› አለች ለራሷ… ነደደች። ሆዷን በእጇ ደግፋ አልጋዋ ላይ ጋደም አለች። ትራስ ደረበች። ተደገፈች። ግን አልተመቻትም። ስልኳን ሳብ አደረገች። ደወለች። ሶስት ጊዜ ጠራ። «ሉላዬ? በደህና ነው የእኔ ቆንጆ?» የሚል በእንቅልፍና ደስታ የተጠመቀ ድምጽ ሰማች። «ሄኒዬ… ደወለልኝ እኮ» አለች ጨለማው ላይ አፍጥጣ፣ ድምጽዋ እየተሰባበረ። «ልታገባ መሆኗን ሲሰማ በዚህ ሰአት ለእኔ ደወለልኝ። ሊያለቃቅስብኝ» «አይዞሽ የእኔ ቆንጆ» ብሎ መለሰላት በፍጥነት። አቀባብሎ ሲጠብቃት የቆየ ምላሽ ይመስላል። ማነው የደወለው ብሎ አልጠየቃትም። መጠየቅ አያስፈልገውም። እሷ ሳሚን በምስጢር ስታፈቅርና በአደባባይ ስታክም አመታትን እንደፈጀች ሁሉ፣ እሱም እሷ ስለ ሳሚ ስታለቃቅስ በማባበል አመታትን አሳልፏል። ሄኖክ የሉላን የልብ ስብራት አብጠርጥሮ ያውቀዋል። ይረዳታል፡፡ «አመመኝ ሄኒዬ» አለችው፣ በመጨረሻ አግታ የያዘቻቸው መንታ መንታ የእንባ ዘለላዎች በጉንጮችዋ ላይ እንዲወርዱ እየፈቀደች። «ምን አባቴ እንደሚሻለኝ አላውቅም።» «አውቃለሁ፣» ሲል መለሰላት፣ ድምፁ ለስላሳ፣ የተረጋጋ እና አፅናኝ ነበር። «ሉላዬ… የሚሰማሽ ስሜት ሁሉ በትክክል ይገባኛል።» ብልጭ ድርግም የሚለው አረንጓዴ የራውተር መብራት ላይ እንደገና አፈጠጠች። ሆድ ባሳት። «እውነት ግን ይገባሃል?» በለሆሳስ ጠየቀችው። «አዎ፣» አለ ሄኖክ፤ «አሳምሮ ይገባኛል።» ✍️ሕይወት እምሻው

  • አባሮሽ…   ከእኩለ ሌሊት በኋላ ነበር የደወለው። ሉላ ገና ስልኩን ሳታነሳው መጥፎ ነገር መሆኑን ቀልቧ ነግሯታል። ሰው በውድቅት ሌሊት የሚደውለው ወይ ለመርዶ፣ ወይ ለመርዶ የቀረበ ዜና ይዞ  ነው። «ሄሎ» ከማለቷ፣ «ሉላዬ… ያንን ብሽቅ ልታገባው እኮ ነው» አላት።   ያለ እንቅልፍ ከተኛችበት ቀና አለችና አልጋዋ መሃል ተቀመጠች። በመኝታ ክፍሏ ግድግዳ ጥግ ካለው የኢንተርኔት ራውተር ጭል ጭል የምትል አረንጓዴ መብራት በስተቀር ክፍሉ ጨለማ ነበር።   «ውይ…» አለች በነገራት ነገር የደነገጠች ለመምሰል እየሞከረች። ምሽቱን ሙሉ የኢንስታግራም ፎቶዎቿን እያፈራረቀች ስታያቸው ነበር። ከውብ የቀለበት ፎቶዎቿ ስር  «ላንተ ያለኝ ፍቅር ልዩ ነው» ብላ የጻፈችውንም አንብባለች፡፡   «አላሳዝንም ሉላዬ…?» ዝም አለችው። ዝምታዋ ቅር ያሰኘው አይመስልም፤ ቀጠለ።   «ለምን ይሄን ያህል እንደደነገጥኩ እንኳን አላውቅም። ሁለት አመት አብረው ቆይተዋል። ይህ እንደሚመጣ አውቅ ነበር ግን በጣም ነው የተሰበርኩት» አላት።   በአጭር በአጭሩ ሲተነፍስ ይሰማታል። አየር እንዳጠረው ቁርጥ ቁርጥ እያደረገ። አላለቀሰም፣ ግን ድምጹ ውስጥ ከዚያ የባሰ ነገር ትሰማለች። ላለማልቀስ የሚያደርገው ትግል ረበሻት።   «ፍቅር ያጃጅላል ሲሉ አይገባኝም ነበር… ተጃጃልኩ። ሉላዬ ታውቂያለሽ… አንድ ቀን ይገባታል… አንድ ቀን የእኔ ትሆናለች ብዬ አስብ ነበር… ይህ ሁሉ ሆኖ እንኳን ተስፋ አልቆረጥኩም ነበር…» ከውጪ አንድ ውሻ ደጋግሞ ይጮኻል። መአት ድመቶች ቀድመው የተስማሙበት ዜማ እንዳለ ሁሉ በሚያበሳጭ ሁኔታ ያላዝናሉ።   የእሱ ንጭንጭ፣ የውሻው ጩኸት፣ የእነሱ ማላዘን… ሁሉ ነገር ተደራርቦ መላ አካሏ በብስጭት ሲግም ይሰማታል። እሱ ላይ ስልኩን ዘግታ ውሻና ድመቶቹን ወጥታ ባንቃቸው ደስ ባላት ነበር።   «በከንቱ ስላሳለፍኩት ጊዜ እያሰብኩ ጸጸት ሊገድለኝ ነው ሉላዬ» አለና ቀጠለ።  «ማለት የነበረብኝን ነገሮች ሁሉ እድሉ እያለኝ ማለት ነበረብኝ። እውነተኛ ስሜቴን ነግሬያት ቢወጣልኝ ጥሩ ነበር… ወይ እሺ ወይ እምቢ ነው… አትገድለኝ…? ከዚህ አይብስብኝም ነበር»   እንደ ሁልጊዜውም በዝምታ እያዳመጠችው ነበር። ማዳመጡን ስለፈለገች ሳይሆን እሱ ስለ ማራኪ ሲብሰለሰል ማዳመጥ የዘወትር ስራዋ ስለሆነ። ማራኪን ምን ያህል እንደሚያፈቅራት፣ ምላሽ ያጣው ፍቅሩ ምንኛ እንደጎዳው መስማት፣ ሰምቶም ከንፈር መምጠጥ ዋናው ስራዋ ነበር።   «እንደማይሆን እያወቅኩ ስለ እሷ ማሰብ ማቆም አልቻልኩም፣ ሉላዬ… አልቻልኩም።» «አውቃለሁ፣» ብላ መለሰችለት። «ጅል ነኝ አይደል…? ጅል የሆንኩ ይመስለኛል» «እሱንም አውቃለሁ» «ዛሬ ደግሞ ልቤ ላይ በጩቤ የተወጋሁ እየመሰለኝ ነው ግን አሁንም ስለ እሷ መብሰልሰሌን ማቆም አልቻልኩም።» «አውቃለሁ»   በተራው ዝም አለ። ጥቂት ሰከንዶች ሳይነጋገሩ አፉ።   «ሉላዬ… ሁልጊዜ ስለ ማራኪ እና ለእሷ ስላለኝ ስሜት ሳወራሽ ‘አውቃለሁ’ እንደምትይኝ ታውቂያለሽ ግን?» አላት።   ስልኩን ከጆሮዋ አጣብቃ እንደያዘች ቤቷ ካለበት የራስ መስፍን ኮንዶሚኒየም ህንፃ በታች ወደተነጠፈችው በብርሃን የተጥለቀለቀች አዲሲቷ ከተማ ተመለከተች። ከዚያ ደግሞ በቆሸሸው የመኝታ ክፍሏ መስኮት መስታወት ላይ በደብዛዛው የሚታየውን የራሷን ነጸብራቅ ገልመጥ አደረገች።   በድንገት ላለፉት ስድስት አመታት አምቃ የያዘችውን ምስጢሯን ዝርገፍ አድርጋ ልትነግረው ዳዳት። ወዲያው ግን እንደ ሁሌው ተንቦቀቦቀችና በምትኩ-  «የሚሰማህ ስሜት ይገባኛል ለማለት ፈልጌ እኮ ነው» አለችው።   «እውነት ይገባሻል?» «አዎ፣ ይገባኛል» «እንዴት? ማለቴ ለምን…?»   አይኖቿን ጨፈነች። ከእንግዲህ የልቧን የምትደብቅበት ምንም ምክንያት አልነበረም። የሚያፈቅራት ልጅ ከሌላ ወንድ ቀለበት አስራለች፣ እሱ ልቡ ተሰብሯል፣ እሷ ደግሞ ማስመሰሉ ከልክ በላይ ታክቷታል፤ አዝሏታል።   «የሌላ የሆነን ሰውን ማፍቀር ምን አይነት ስሜት እንዳለው አውቃለሁ» አለችው ደፈንፈን አድርጋ።   ምንም አልተናገረም። እንዲያውም ስልኩ የተዘጋ መሰላት።   በጨለማው ውስጥ ፈገግ አለች። ከዚህ ሁሉ ጊዜ በኋላም ልቧ ለማን እንደተከፈተና በማን እንደተሰበረ ሊታየው ስላልቻለ ተስፋ የመቁረጥ ፈገግታ ነው።   እሱን ማፍቀር ቦሌ ኤርፖርት ሄዶ ባቡር እንደመጠበቅ ነው።   ምን ልበለው ብላ ስታሰላስል፡ «ሌላ ከሚያፈቅር ሰው ጋር ፍቅር ይዞሻል እንዴ?» ሲል ጠየቃት። ድምጹ ውስጥ ግርምት አለ።   «አዎ» አለችው።   ትንፋሹን አዳመጠችው። ባለፉት አመታት የሸመደደችውን፣ ሲደነግጥ የሚተነፍስበትን መንገድ በአጽንኦ አዳመጠች። ‹‹እየቀለድሽ መሆን አለበት….እሺ ከማን?››  ጠየቃት፡፡ አፏን ከፈተች፣ እውነቱ ምላሷ ላይ ከብዶ ተቀምጧል፣ በመጨረሻም ስሙን ጠርታ መልስ ልትሰጠው ተዘጋጀች። «ከሳሙኤል መኮንን ደሬሳ ጋር» ልትለው ፈለገች።   ግን አቋረጣት።   «ይልቅ ሉላዬ… አሁንም እድል ያለኝ ይመስልሻል? ቀለበት አደረገች ማለት አገባች ማለት አይደለም አይደል? …» ብሎ አቋረጣት።   ስልኳን ከጆሮዋ አውርዳ መዳፏ ላይ እንዳለ ቁልቁል አየችው። በስክሪኑ ላይ ያለው የሰአት ቆጣሪ ለሰባት ሰአት ሃያ ጉዳይ ይላል። የደቂቃዎች ሳይሆን የስድስት አመት የማይታይ ስቃይዋን ልትተነፍስለት የነበረው የምትወደው ልጅ፣ የሚወዳትን ልጅ ስም ከደቂቃዎች በላይ ሳይጠራ መቆየት አቃተው።   «ሉላዬ? አለሽ?» አላት በዝምታዋ ስትጸና። «አዎ ሳሚዬ፣» ለሹክሹክታ በሚቀርብ ሁኔታ መለሰችለት። «አለሁ። አሁን ግን ብንተኛ ይሻላል…ነገ እናውራበት»   መልሱን አልጠበቀችም። ስልኩን ዘጋችው። ⤵️⤵️⤵️

  • ፈገግታ ይሸውደኛል ። መንገዴ ላይ ያጠቃኝ ሁሉ ፈገግታውን ተጠቅሞ ነው የጣለኝ። የጎዳኝ ሁሉ ከጀርባዬ ሰንዝሮ ነው። ፈገግታ ስስ ጎኔ ነው !! ቤተሰቦቼ ቀጥተኛ ነበሩ አጥፍቼ የሚስቅልኝ አልነበረም፤ ወድቄ ፈገግ ብሎ አባብሎኝ የሚያውቅ ኖሮ አያውቅም። ፈገግ እያለ የሚታገል ይጥለኛል ። ፈገግታ ካየሁ ትግሉ የምር አይመስለኝም። አቅፎ ሰላም የሚለኝ ልቡ የሚወደኝ ይመስለኛል። ልቡ ላይ በመጥፎ ያስቀመጠኝ ሰው ጥርሱ ፈገግ የሚልለት እና እጁ አጥብቆ የሚያቅፍለት አይመስለኝም ነበር። እናት እና አባቴ ተደባብረው ፈገግ ብለው ሲጨዋወቱ አይቼ አላውቅም። ወንድም እና እህቴ አታለው ይዘው ቀጥተውኝ አያውቁም። ቤተሰቦቼ ቀጥተኛ ነበሩ ! ፀባቸው ፊት ለፊት ነው። ቅሬታቸው ፊታቸው ላይ ይነበባል ። ከተሰማቸው ስሜት ርቀው አያስመስሉም! አይወደኝም የምለው ሰው ቀረብ ብሎ ለስለስ ብሎ ካዋራኝ ጋሻዬን ጦሬን እጥላለሁ። ስልት ያለው ጥላቻ አይገባኝም አባቴ አጥፍቼ እንዳይመታኝ ከተማፀንኩት ይቅርታ አደረጎልኝ፥ አረሳስቶ መቶኝ አያውቅም ። የተጣላሁት ሰው ፈግግ ብሎ ካወራኝ ይቅር ብሎኝ ነው የሚመስለኝ። ፈገግ እያሉ ክፋት የሚጎነጎኑ ሰዎች ሳይጥሉኝ ቀርተው አያውቁም። በርግጥ የሰው ልጅ መሸነፍያ ሰፍራ አያጣም!! Adhanom Mitiku

  • "እኔን ዋትስ አፕ ወላንሳ? (አሌክስ አብርሃም) የሆነ ጊዜ ከልተው ከልተው እያልኩ ከስራ ስመለስ የተከራየሁበት ቤት ድግስ ተደግሶ፣ ሙዚቃ ተከፍቶ ደረስኩ። የሆነ አሰልቺ «ልዩ ልዩ ቀን ነው...» የሚል ዘፈን ያላዝናል፣ ከዚያ ደግሞ የብሔር ብሔረሰቦች ዘፈን ይጮኻል። እናትየዋ ጥርስ ብቻ ሆነው «ካልገባህ» ሲሉኝ ገባሁ። ጎረቤቱ ቢራ ይራጫል፤ ክትፎው ወጡ በዓይነት ቀርቧል። ጎረቤቱ ሁሉ «እንኳን ደስ ያላችሁ!» ይላል። በኋላ ስሰማ፣ የሐኪሞች ይሁን የሕክምና ቦርድ የሚባል የባለቤቶቹን ልጅ ወላንሳን «ውጭ አገር ትታከም» የሚል ውሳኔ በማሳለፉ ኖሯል። ጭራሽ እዛ ሁሉ ሰው ፊት " በቸሩ መድሃኒያለምና በአንተ እርዳታ ለዚህ በቃች" ብለው የጎረቤት ቆነጃጅቶች ሁሉ ከዚያ በኋላ "አሜሪካ የሚልከው ልጅ" እያሉ በፍቅር ያዮኝ ጀመር። ​በእርግጥ ለቦርዱ «ይህን ጻፍልኝ»፣ ለሆነ ድርጅት «ኢሜይል ላክልኝ» እያሉ ወደ አንድ ዓመት ፍዳዬን አብልተውኛል። በተለይ ቁጥር ስፍር የሌለውን የመድኃኒት ማዘዣ (የሐኪም ጽሕፈት አስባችሁታል?) «አንብብልን» እያሉ ያበሉኝ መከራ አልረሳውም። ኧረ ስንት ቀን ሰው ጠፍቶ እኔና እናቷ እየደገፍን ዋናው መንገድ ድረስ ወስደናታል። የሆነ ሆኖ ልጅቱ «ለሕክምና» ሄደችና በዚያው ቀረች ቀረች። እኔም በሰላምና በጤና አራት ዓመት ኖርኩ። ​በኋላ ግን፣ ያውም በክረምት፣ «ልጄ ከአሜሪካ ልትመጣ ስለሆነ ቤት ልቀቅ» ተባልኩ። ነገረኛ መሆን ፈለግኩና «ኧረ እለቃለሁ! እንኳን ሕክምናዋን ጨረሰች እንጂ» ስላቸው ፊታቸው እንዴት እንደተቀያየረ! 😁 ሁላችንም «ሾርት ሜሞሪ» ያለን ነው እንዴ የሚመስላቸው? ​አጋጣሚ ሆኖ እዚያው ሦስት ግቢ አልፎ ቤት አገኘሁ። ተከራዮ የነበረው ልጅ በትንሽ ፀብ (ስድስት ጥርስ አውልቆ፣) ሦስት ዓመት ተፈርዶበት ታስሮ እስኪፈታ ድረስ «ኑርበት» ተብዬ። ​እናም ልጅቱ ከአሜሪካ መጣች። ከሳምንት በኋላ በሁለት ጎረምሶች በግራና በቀኝ ተደግፋ እየተንቀጠቀጠች ስትሄድ አየኋት። እንደገና ያመማት መስሎኝ (መቼም ቂም የሚባል ነገር አላውቅም) «እኔን እህቴን!» ብዬ በቅንነት ብጠጋ፣ ለካስ ያደረገችው ባለ ረዢም ሂል ጫማ መራመድ አስቸግሯት ኖሯል! (ምንስ ውድ ብራንድ ቢሆን እንዲህ መሰቃየት ምን ይባላል?) ደግሞ ደጋፊወቹስ ቢሆኑ ያኔ የት ነበሩ?! ጭራሽ ስታየኝ አራት ጣቶቿን በቄንጥ አውለብልባ «ዋስ አፕ!» አለችኝ። ​ፋሲል ደመወዝ «እኔን ዋትስ አፕ ፍቅር አዲስ?!» ያለው ወዶ ነው! እኔን ዋትስ አፕ ወላንሳ?!

  • "ፍቅር_እዚህ_ቦታ_ፈገግ_ብሎ_ነበር" . ያሳለፍነዉ ሁሉ አሁን ትዝታ እንጂ ዉስጡ ህይወት የለም እያልሽ ላገሩ ታወሪያለሽ አሉ . . (እኔ ግን ልንገርሽ) የሁለታችን ፍቅር ምን እንደሚመስል. . . እንዴት እንደነበር በሶስት ምስክር 1 አሁን በቀደም ለት የሆነ ቦታ ላይ ድምጻችን ከፍ አርገን የሳቅንበት ቦታ ፒያሳ አደባባይ ድንገት በቀደም ለት በዛ ቦታ ስሄድ ከሰባት ወር በፊት ስቀሽ የነበረዉ ያንቺ ሳቅ ተሰማኝ መራመድ አቃተኝ የሚገርምሽ ነገር ያለፈ ነዉ ያልሺዉ ትዝታ ነዉ ያልሽዉ ፍቅርሽና ሳቅሽ ከሰባት ወር ኋላ እንደ ወንዝ ፍሳሽ ይሰማል ልንገርሽ . (ታዲያ ለምንድን ነዉ) የወንዝ ዉሀ ሳቅሽ ያለፈ ትዝታ ምናምን ነዉ ብሎ ማንም ተራ ዘፋኝ የሚሸነግልሽ (ይልቅ እኔን ስሚኝ) . ወደየትም ሳይሆን ወዴትም ተመለሽ የትም ሳትደርሺ ጊዜን እንዳቆምነዉ እንኳን ጊዜ ቀርቶ ሰዓት እንዳልሄደ ደቂቃ እንዳልሄደ አስረጂ ሊሆንሽ ምስክር ሊሆንሽ ከምንም አቅጣጫ. . . የትም ሳትመለሽ አደባባይ መሀል ከቡና ጠረን ጋር እንደወንዝ የሚፈስ ሳቅሽን ትሰሚያለሽ . 2 ትዝ ይልሽ እንደሆን ካንቺ መኖሪያ ቤት (የመጣሁኝ ጊዜ) የመራራቅ ናፍቆት አስክሮን ቸኩለን ሰማያት ለመዝለቅ ከመሬት ላይ ወድቀን ፍቅር ስንሰራ ፍቅር ስንሰራ ፍቅር ስንሰራ ከሴት ወዝሽ ጋራ የጡትሽ ስር ሽቶ ሸሚዜ ላይ ቀርቶ ሸሚዜ ላይ ቀርቶ ምወደዉን ሸሚዝ ለመልበስ እርም አልኩኝ ለብሼዉ እንዳልሄድ ከበደኝ ጨነቀኝ ያንቺን ጠረን ማጠብ. . . ነፍስ የማጥፋት ያህል ሀጥያት መስሎ ታየኝ (የሚገርምሽ ነገር) እስከ ዛሬ ድረስ በመስኮቱ ዘልቆ. . .በበሬ የሚወጣዉ የማለዳዉ ነፋስ በሽቶሽ ጠረን ነዉ መንደሩን የሚብስ . 3 ታስታዉሽ እንደሆን የሆነ ቅዳሜ የሆነ ዉብ ሆቴል ደግሞም አትረሺዉም. . .ፍጻሜ ምሳ ነዉ ይኼ እንኳን ትዝ ይላል እና. . . እኔና አንቺ ብቻ የተቀመጥንበት ወንበር ጠረጴዛዉ ከዘጠኝ ወር ኋላ. . . እዛዉ ቤት ዳግመኛ ተመልሼ ባየዉ የሚገርምሽ ነገር ጻፊዉን ባላዉቅም #ፍቅር_እዚህ_ቦታ_ፈገግ_ብሎ_ነበር የሚል ጽሁፍ ሰቅለዉ ከዘጠኝ ወር ኋላ አንድ ለብቻዬ ካንድ አንቺ ናፍቆት ጋር ነበር ለምትይዉ ለሁለታችን ፍቅር (ምስክር ሊሆኑን) ያኔ ሁለታችን የጠጣነዉ ወይን ከወይንም. . . Two Ocean እኔ የጨለጥኩት አንቺ ያጋመስሽዉ እኛ ያስተረፍነዉ እስከዛሬ ድረስ ያተረፍነዉ ማዕድ. . . ጠርሙስና ጽዋዉ በክብር ተቀምጧል ማንም ሳያነሳዉ. . .ያኔ እንደነበረዉ (ታዲያ ምን ማለት ነዉ) . . . ፒያሳ አደባባይ የወንዝ ዉሃ ሳቅሽ ከቡና ጠረን ጋ ከኔ መኖሪያ ቤት. . . የምወደዉ ሸሚዝ ላይ የሽቶ መአዛሽ ከሴት ላቦትሽ ጋር ደግሞም እዚያ ዉብ ሆቴል ስር ያስተረፍነዉ . . . ማዕድ ጠርሙስና ጽዋ አንጀት ከሚበላ ከቆንጆ ጥቅስ ጋር ‘’#ፍቅር_እዚህ_ቦታ_ፈገግ_ብሎ_ነበር::’’ . ነበርን እስካሁን በመሆን እያየሽ ሳቅሽ ፈሶ ሳያልቅ ከምወደዉ ሸሚዝ የሽቶ መዓዛሽ ዉብ ጠረኑ ሳይለቅ ማዕድ ሳይነሳ ጽዋዉ ሳይታጠብ ሦሥቱን ምስክሮች በዓይንሽ ፊት እያየሽ (ታዲያ ለምንድን ነዉ) ያሳለፍነዉ ሁሉ # አሁን_ትዝታ_እንጂ ..... # ዉስጡ_ህይወት_የለም ብለሽ ለመንደሩ ላገሩ ማዉራትሽ እዉነት ለምንድን ነዉ? . . . . . ©ኤፍሬም ስዩም(ፍቅር እዚህ ቦታ ፈገግ ብሎ ነበር) @e_n_k_u_0

  • ድመቱ...2 ከላይ የቀጠለ ✨️✨️

  • ድመቱ...1 ✨️✨️✨️ ✍️ሕይወትእምሻው

  • ፍቅር ዓለሜ ☺️ ዕንቁ 🥀

  • 31 мая17021из Kenako_12

    ባፈቅርሽ ምን ጎዳሽ? ምንሽን አሳጣሽ? ካለኝ ላይ ቀንሼ ልቤንስ ብሰጥሽ ፍቅሬ እኮ ጥላ ነው ከፀሀይ መከለያ በብቸኝነት ቀን የነፍስሽ ማረፊያ ​እኔ እሳት አይደለሁ የማቀጣጥልሽ ወይ ነፋስ አይደለሁ የምበታትንሽ ብቻሽን ስታለቅሽ እንባሽን ለማበስ አብሬሽ መሆን ነው የፈለግኩት እኔስ ​ታዲያ ምን ያስፈራል? ምንድነው ስጋቱ? ለምንስ እምቢ አለሽጀበኔ መፅናናቱ? ባፈቅርሽ ምን ጎዳሽ? በሩንስ ብትከፍቺው ይህን ንፁህ ልቤን አምነሽ ብታስገቢው የፍቅርን ፅዋ የፍቅርን መና ሁሌ ብመግቢው ምን ችግር አለው? እስኪ እናንተ ጠይቋት🥺🥺 ልጅ ስሉጥ እንደፃፈው..... https://t.me/Kenako_12

  • እጠብቅሃለው ☺️ ዕንቁ ✨️