tgindex
Ebnu Sitina (BILADEN)

Ebnu Sitina (BILADEN)

Статистика

በቻናላችን የተለያዩ የኡለሞችን አስገራሚ ንግግር እና የተለያዩ ኢስላማዊ ነክ እውቀቶችን ያገኛሉ ሀሳብ እና አስተያየትዎን በዚ ሊንክ መስጠት ይችላሉ @ebnusiti

Последний пост
13 авг.
Последнее чтение
15 авг.
Постов за неделю
3
Всего постов
22
Тип
открытый
Язык
und
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
132
+1 за 3 дн.
Сутки
+1
+0,76%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
93
22 постов
Вовлечённость
70,5%
к подписчикам
Постов в день
0,4
всего 22
Упоминаний
0
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
23
1/48двое суток
26
1/72трое суток
28

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • ናፍቆ ለመንሰቅሰቅ             በሙሀባው ቀልጦ ማን ሸርጥ አደረገው            ሰው መሆንን መርጦ መውሊዱ እየደረሰ ነው እየነሸጥን አህባብ        ቻናሉን ይቀላቀሉ       👇👇👇👇👇   https://t.me/ebnusitina

  • ሀድራ ማለት ለኛ የደም መሬታችን ቅርብ ደምስራችን እሩቅ ሰማያችን ቻናሉን ይቀላቀሉ 👇👇👇👇👇 https://t.me/ebnusitina

  • መውሊዱ ለኛ ብቻ ሳይሆን ለሁለቱ ዒዶች እራሱ እሱ ዒዳቸው ነው ቻናሉን ይቀላቀሉ 👇👇👇👇👇 https://t.me/ebnusitina

  • 👉ዘንድሮ ኢትዮ ቴሌኮም ያተረፈው ትርፍ 215,800,000,000 ብር ነው 😳😳 ያ ማለት የኢትዮጵያ ህዝብ 130 ሚሊየን ው ብለን ብናስብና ቴሌ ያተረፈውን ብንካፈል🙈🙈 ለእያንዳንዱ ሰው 1660ብር ይደርሳል😜😜 ለምን ግን ለቴሌ ሀሳቡን አናቀርብለትም😜😜 ቁጭ ስል የመጣልኝ ሀሳብ ነው😜😜

  • የጋብቻ 💍 ቀለበት ቢደዓ ነው ሽርክም ሊሆን ይችላል 😝😂😂😂😂 መውሊድ ለሚቃወሙ ጣታቸው የጋብቻ ቀለበት ላደረጉ ወሀብዩች ጥሩ ማስታወሻ ይሁንልን ። መውሊድ ቢደዓ ነው ለማለት የጋብቻ ቀለበትሽን አውልቂ ቅድሚያ ቢደዓ እየሰሩ ቢደዓ ማለት አይቻልም ቢደዓ ነው ያሉት ደግሞ የወሀብያ ሼይኽ የሆኑት ኢብኑ ዑሰይሚን ናቸው ። ✍ዘ.ሐ

  • ወሀብዩች ለትውልድ  ያወረሱት ወሳኝ ነገራቶች 1:-የእናትን ጀበና መስበር 2:-ዑለማዎችን መሳደብ 3:-ቀብር ማፈራረስ እና ሙታንን ከቀብር ማውጣት ። # ወሀብያዎች በዚህ ሰሞን ሱዳን ውስጥ  አንድ ታላቅ የአላህ ወዳጅን ቀብር ቆፍረው አውጥተው መስረቃቸው ስሰማ ትዝ ያለኝ ነገር ቢኖር 👉 ሙፍቲ ለምን ኮልፌ መካነ መቃብር አልተቀበሩም ብለው ያበሙሉ ሰጣ ገባ ውስጥ የገቡት ለዚሁ ነበር የሚል ድምዳሜ ላይ እንድደርስ አድርጎኛል ። ነገር ግን አላህ ወዳጁን በሒወትም ከሂወትም በኃላም ጠባቂ መሆኑን  ያሳየበት አጋጣሚ ነበር  ። የሙፍቲ ራህማቱላሂ ዐለይሂ  ቀብር በሀበሻ ታሪክ ትልቅ የከራማ ማሳያ ተደርጎ ይቆጠራል ። ✍ዘ.ሐ

  • ማሰብ ለሚችል ወሀብያ ዋሀብያ በየአመቱ ቀን ጠብቆ የሚያዘጋጃቸው ፕሮግራሞች ፦ 1:- ቁርአን ውድድር 2:- የጎዳና ኢፍጣር 3:- የቁርአን ተማሪዎች ምርቃት 4:- በረመዳን የመጨረሻ አስርቱን ቀናት ለይቶ ተሀጁድ በጀመዐ መስገድ 5:-ነሲሃ ኮንፈረንስ 6:-የሂጃብ ቀን 🔰በየሳምንቱ እየጠበቁ የሚያዘጋጁት ደግሞ ሳምንታዊ ሙሀደራ። ✅ በየወሩ የሚያዘጋጁት ደግሞ ምርኩዝ ሌሎች ፕሮግራሞች። 💎 በየእለቱ ከመግሪብ በኃላ ተፍሲር ፣ ተውሂድ የመሳሰሉት ማስቀራት ። እነዚ ሁሉ ፕሮግራሞች እራሳቸውን ችለው ማስረጃ የላቸውም ወሀብያ ግን ሸዋል ጋር ሲደርስ ደሊል ይጠይቃል ምስኪን‼️ ወሀብዮች የጀመሩት አዲስ ስራ እነርሱ  ጋር ቢድዐ ተብሎ እንዳይሰየም የሆነ ፓውደርማ ይጨምሩበታል አይመስላቹም⁉️ ✍ዘ.ሐ https://t.me/sufiyahlesuna

  • 👉በዒድ ቀን ስትጠያየቁ (ስትዘያየሩ ) የነበራችሁ  ወሀብያዎች ቢደዓ ስትሰሩ ነው የዋላችሁት ።ቢደዓ ሁሉ ደግሞ ጥመት ነው ጥመት ሁሉ የእሳት  ነው ። ይህን ያልኩት እኔ አደለሁም ውሀብያ ዘንድ የሃዲስ ሊቅ እየተባሉ የሚጠሩት አልባኒ ናቸው ይህን ያሉት  ። ማስረጃ ከፈለጋችሁ سلسلة الهدى والنور شريط رقم 527  ሲልሲለቱል ሁዳ ወኑር 527 የካሴት ቁጥር ። 👉እኛ ግን ስንዘይር የነበረው ሰለፎችን በመከተል ነው ደሊላችን ደግሞ ኢማሙ ቡኻሪ በሀዲስ ኪታባቸው ውስጥ ባሰፈሩት ዘገባ "እናታችን አዒሻ ረዐ እንዲህ ትላለች ሁለት ሴቶች እኔ ጋር የቡዓስ ቀን የተባሉ ዘፈኖችን እየዘፈኑልኝ የአላህ መልክተኛ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም ገቡ ፈራሹ ላይ ጋደም አሉ ፊታቸውንም አዞሩ  አቡበክርም ረዐ ገቡ........"  በሌላ በሂሻም ኢብኑ ዑርዋ ዘገባ  የአላህ መልክተኛ ቤት ከገቡ በኃላ አቡበክር ረዐ ገቡ  ሊጠይቃት( ሊዘይራት) የመጡ  ይመስላል ። ፈትህ 👉አቡበክር ረዐ ልጃቸውን አዒሻ ረዐ  ሊዘይሩ መጡ በምን ቀን በዒድ ቀን ። እሺ አሁንስ ወሀብያ ነው ወይስ እኛነን ሰለፎችን ምንከተለው ?? መልሱን ለእናንተ ።!! ✍ዘ.ሐ

  • በኢድ ቀን ስታሽቅ ለሚነቅፍህ ሞኝ ላክለት ያንተን ሀሳብ ወይስ ሸሪዓውን እንከተል ወይ??  በለው 🔸🔸🔸🔸🔺 አዚዝ:- السلام عليكم ورحمة الله وبركاته ዘኪ:-وعليكم السلام ورحمة الله وبركاته አዚዝ:- ኢድ ሙባረክ ዘኪ :-ተቀበለላሁ ሚና ወሚንኩም ሳሊሀል አእማል። አዚዝ:-ዛሬ እንድንወያይ  የፈለኩት በኢድ ቀን ስለሚተገበሩ ትክክል ስላልሆኑ ክንዋኔዎች ነው ። ዘኪ:- ይቻላል ቀጥል ። አዚዝ : መንዙማ እያሉ ዘንበል ዘንበል ማለት ከኢስላም ጋር የሚጋጭ ተግባር ነው ፡ እናንተ ለምንድነው የምትተገብሩት ??? ዘኪ:- በጭራሽ ከኢስላም ጋር አይጋጭም እንደውም እነዚህን ተግባሮች  መተግበር ሱና ነው። የኢድ ቀን ማሸቅ ፣ አላህ በፈቀደው መልኩ መደሰትና መዝናናት  የተወደደ ነው። አዚዝ:- በሰሀባ ዘመን እንዲህ አይነት ነገር ነበር እያልክ ነው ማለት ነው ??በደንብ አስተውል እንጂ ዘኪ:-የምለውን ስለማውቅ ጥርጥር አይግባህ። አዚዝ:- እንዲያ ተሆነ  ከሀዲስ ና ከሰለፎች ተግባር ማሰረጃ  ልትሰጠኝ ትችላለህ ? ዘኪ :- በደንብ ነዋ 1)  👉ለሴቶች         ———— عَائِشَةَ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهَا، قَالَتْ: دَخَلَ أَبُو بَكْرٍ وَعِنْدِي جَارِيَتَانِ مِنْ جَوَارِي الأَنْصَارِ تُغَنِّيَانِ بِمَا تَقَاوَلَتِ الأَنْصَارُ يَوْمَ بُعَاثَ، قَالَتْ: وَلَيْسَتَا بِمُغَنِّيَتَيْنِ، فَقَالَ أَبُو  بَكْرٍ: أَمَزَامِيرُ الشَّيْطَانِ فِي بَيْتِ رَسُولِ اللَّهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ وَذَلِكَ فِي يَوْمِ عِيدٍ، فَقَالَ رَسُولُ اللَّهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ: «يَا أَبَا بَكْرٍ، إِنَّ لِكُلِّ قَوْمٍ عِيدًا وَهَذَا عِيدُنَا ቡኻሪና ሙስሊም በዘገቡት ሀዲስ እናታችን አኢሻ ረዲየሏሁ ዐንሀ እንዲህ ትላለች: - “ እለተ- ዒድ ላይ ከአንሳር ሴቶች መካከል የሆኑ ሁለት የአንሳር ልጆች (የመዲና ነዋሪዎች) የቡአስ (በሁለት ጉሳዎች መካከልየተደረገ ጦርነት ) ጊዜ የተባባሉትን  እያዜሙልኝ እያለ ሰይዱና  አቡ -በከር  አስሲዲቅ ረዲየሏሁ ዐንሁ  ገቡ። አቡ -በከርም ረ፡ ዐ የሸይጣን ቅላፄ በነብዩ ሰለሏሁ አለይሂ ወሰለም ቤት ? ብለው ተቆጡ ። በዚህ ወቅት ነብዩ ሰለሏሁ አለይሂ ወሰለም አንተ አቡ-በክር ሆይ!  ለሁለም ህዝብ ኢድ ( በአል ) አለው ይህ ኢዳችን ነው።አሉ 1)👉ለወንዶች         ————- أخرج الإمام أحمد (12540) وابن حبان (5870) عَنْ أَنَسٍ قَالَ: " كَانَتِ الْحَبَشَةُ يَزْفِنُونَ بَيْنَ يَدَيْ رَسُولِ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ ، وَيَرْقُصُونَ ، وَيَقُولُونَ: مُحَمَّدٌ عَبْدٌ صَالِحٌ ، فَقَالَ رَسُولُ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ : ( مَا يَقُولُونَ؟ ) قَالُوا: يَقُولُونَ: مُحَمَّدٌ عَبْدٌ صَالِحٌ . قال محققو المسند : " إسناده صحيح على شرط مسلم " . ኢማሙ አህመድ በሰሂህ ሰነድ በዘገቡት ሀዲስ ሰይዱና አነስ ረዲየሏሁ ዐንሁ እንዲህ ይላሉ :- ✍️  ሀበሻዎች በአላህ መልክተኛ ሰለሏሁ አለይሂ ወሰለም ፊት “ሙሀመዱን አብዱን ሳሊህ “ እያሉ  ይጨፍሩ ነበር  (በሀበሻ ቋንቋ) ፡ የአላህ መልክተኛም ሰለሏሁ አለይሂ ወሰለም  ምንድ ነው ሚሉት ሲሉ ጠየቁ ፡ ሙሀመዱን አብዱን ሳሊህ(ሙሀመድ ደግ የ አላህ ባሪያ ናቸው )  ነው የሚሉት ተባሉ። ✍️ ቡኻሪና ሙስሊም በዘገቡት ሀዲስ ደግሞ :- ሀበሾች መስጂድ አንነበዊ ወስጥ የኢድ ቀን በጦራቸውና በጋሻቸው ሽለላና  ትርዒት ሲያሳዩ የአላህ መልክተኛ ተመልክተዋቸዋል ለእናታችን አኢሻም ጋብዘዋታል። ሰይዱና ኡመር ረዐ ሊከለክሉ ሲሞክሩ የአላህ መልክተኛ ቀጥሉ ሲሉ ትእዛዝ አስተላልፈዋል። እንዲህ በማለትም ይህን ተግባር ያልከለከሉበትን ምክንያት አስረድተዋል :- "አይሁዶች በዲናችን ላይ ስፋት እንዳለ እንዲያዩ ነው" 👉ሱና መሆኑን ማስረጃ عن قيس بن سعد، قال: ما كان شيء على عهد رسول الله صلى الله عليه وسلم إلا وقد رأيته، إلا شيء واحد، فإن رسول الله صلى الله عليه وسلم كان يقلس له يوم ኢብኑ ማጃህ በዘገቡት ሀዲስ ላይ ፡ ቀይስ ኢብኑ ሰእድ  ረ፡ዐ እንዲህ ይላሉ:- “ በአላህ መልክተኛ ሰለሏሁ አለይሂ ዘመን የነበረን ተግባር  ሁሉ በዚህ ዘመን ተመልክቻለው ፡ ለአላህ መልክተኛ ሰለሏሁ አለይሂ ወሰለም የኢደል - ፊጥር ወቀት ተቀሊስ የሚደረግላቸው ሲቀር። ተቅሊስ ማለት ዱፍ እየመቱ ማዜም ነው

  • ውድ የቻናሎቼ ቤተሰቦችና ለመላው የእስልምና ወንድሞቼና እህቶቼ እንኳን ለ1447ኛው የኢድ አል ፈጥር በአል በሰላም አደረሳችሁ አላህዬ ረመዳናቸውን ተቀብሎ በዛም ላይ የሰሩትን ሁሉ ይቅር ብሏቸው በመጀመሪያዎቹ አስርት ቀናቶች አዝኖላቸው በሁለተኛው ይቅር ብሏቸው በመጨረሻው ከእሳት ነጃ ካላቸው ውድ ባሮቹ ያድርገን አሚንንን🙏🙏🙏 ህይወቱን እንደ ረመዳን የኖረ ሞቱ ኢድ ይሆንለታል      ቻናሉን ይቀላቀሉ       👇👇👇👇 https://t.me/ebnusitina

  • ዒድ ከነገ ወዲያ ጁመዓ ነው አንድ የእዝነት ቀን ተጨምሮልናል

  • የሳዳት ከማል ቢደዓ 😂😂😂😂 ነብዩ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም እና ባልደረቦቻቸው ከዛ በኃላ ወርቃማው ትውልድ ነብዩ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም ምርጥ ያሉት ትውልድ የጁማዓ ኹጥባ አድርገው አሳይተውናል ። ነገር ግን "ነገ" የማደርገው ኹጥባ እንዲህ ነው ብለው የተናገሩበት ቦታ አንድ ሰውም ማምጣት አይችልም  በጭራሽ ይህ አዲሱ የሳዳት ከማል ቢደዓ ነው ። ሳዳት ከማል  ጋር ደግሞ ቢደዓ ሁሉ ጥመት ነው ።  ጥመት ሁሉ ደግሞ የእሳት ነው ። የጁማዓ ኹጥባ ኢባዳ አደለም የሚል የጅል መከራከሪያ እንደማታቀርቡ እርግጠኛ ነኝ ። ✍ዘ.ሐ

  • ሰዎችንም የሰከሩ ሆነው ታያቸዋለህ፤ እነሱም የሰከሩ አይደሉም ። ግን የአላህ ቅጣት ብርቱ ነው።" ወንድሜ/እህቴ ሆይ!  እስኪ ለትንሽ ደቂቃ ቆም ብለህ(ሽ) አስብ(ቢ)። በዚያች ቀን መሬት ስትናወጥ፣ ነፍሰ ጡር የተሸከመችውን ስትጥል፣ የምታጠባው እናት ልጇን ስትረሳ... አንተ(ቺ) የት ትሆን(ኚ) ይሆን ? ሁላችንም ራሳችንን እንጠይቅ

  • 💗💗ለውጣችን💗💗 ቲኒሽ ቆየት ብሎ ወደ  ወሊሶ በኹሩጅ ፊሰቢሊላህ ተጉዘን ነበር ታዲያ መጀመሪያ የገባነው አብሬት መስጂድ ነበር ፆም እንደመሆኑ ስራዎችን አጠናቀን አፍጥረን ተራዊህ ከሰገድን በኃላ ልንተኛ ስንዘጋጅ አንድ የአከባቢ ሰው አሁን ልተኙ ነው እንዴ ተነሱ ብሎ አረብ ሰፈር የሚባለው ወደ እዛ ይዞን ጀውላ ወጣ ጀውላ ስንደርስ ወላሂ ቢላሂ አንድ መቃሚያቤት ውስጥ ያለው ሰው መስጂድ ካለው ሰው ይበልጣል ለካ ቀን ሁሉም ተኝተው ካፍጥር በኃላ እዚህ ነው የሚገቡት ። እኛም አላህ እንድንናገር የፈቀደውን ተናገረን ነገ እንዲመጡ ሁሉንም ቃል አስገብተን አንድ ሶስት መቃሚያ ቤት ዘይረን ተመለስን በአላህ ፍቃድ በቀጣዩ ቀን የተወሰኑ ልጆች ሰግደው ሲወጡ ተመልክቻለሁ  ። አሁን ይህን ያነሳሁት ወሀብያ ሰለሚገርመኝ ነው አንድ ቀን የማይሰግድ ሰው አያሳስበውም ፤ መጠጥ ቤት ያሉ ሙስሊሞች ጉዳዩ አደለም ፤ በረመዳን እንዃን ሙስሊም ሆነው ብዙ ሁኔታ ላይ ያሉ በየአካባቢው ይታወቃል ግን ምን አገባቸው ።!! ወሀብያ ስትሆን ብቻኛው የሚያሳስበው ነገር መስጂድ በአልሃምዱ ሊላህ መጀመሩ  ፤ ዱዓ አለመደረጉ ፤ቁኑት አለመደረጉ፤ ዚክር አለመደረጉ አለቅ ። ለውጣችን ይህ ነው እንግዲህ ። ✍ዘ.ሐ

  • ዛሬ ጨረቃ በመታየቷ የረመዳን ወር ፆምን ነገ ሀ ብለን እንጀምራለን ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለዚ የተከበረና የተላቀ ወር በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን🙏🙏 አላህዬ በዚህ ወር ከሚያተርፉት ለነገው አለም ኸይራትን ከሚከስቡት ያድርገን 🙏 እንዲሁም በዚ ወር እድለ ቢስ ከመሆን ይጠብቀን አሚን 🙏🙏 ረመዳን ሙባረክ 🫶❤️

  • ይህን አለም አሏህ ስለመፍጠሩ ማስረጃው ምንድነው ? ወሀቢው ዑስማን አልኸሚስ ፡ አሏህ ራሱ ነው የነገራቶች ሁሉ ፈጣሪ መሆኑን የነገረን i can't😂😂😂😂 👉 ሲጀመር ጥያቄው በአሏህ ጌትነት ከማያምኑ ሰዎች የሚመጣ ነው ፤ ጭራሹኑ በአሏህ ጌትነት ለማያምን ሰው " አሏህ እንዲህ ብሏል " እያልክ ከቁርአን ማስረጃ ስታመጣለት አስበው ። አህለሱናዎች ደሊል አል ዐቅሊይን በኪታቦቻቸው የሚያስተምሩት " ደሊል አል ዐቅልይ " ከምእመናን አልፎ ጣኦታዊያንንም ሆነ አምላክ የለም የሚሉ ወገኖችን ለማናገር ስለሚመች ነው ፤ አለበለዚያ " ፈጣሪ ለመኖሩ ማስረጃ ስጠኝ " ሲልህ እርሱ ከማያምንበት ቁርአን ማስረጃ አምጥተህ ትዳረቃለህ ።

  • (ለወላጆችህ) የመተናነስ ክንፍን ዝቅ አድርግላቸው ። የታሉ የተውሂድ አረበኛ ነኝ ባዩች  ይህም ሽርክ ይሆናል እኮ።!! ለነገሩ የእናታቸውን ጀበና ሰብረው የጨረሱ ደንቆሮ እኮ ናቸው ፤ አባታቸው ሞቶ በቃ ተበተኑ የሚሉ ፤ያለቀሰ የሚደበድቡ ፤ የልባቸው ድርቅና እንደ ኢማን የሚቆጥሩ ልበ ደንዳና ፍጡራን ። ታላቁ የተውሂድ አባት የተውሂድ አረበኛ "የአባታቹን የኢብራሂም መንገድ ተከተሉ" የተባለላቸው ነብዩላሂ ኢብራሂም ዓለይሂ ሰለም ሙሽሪክ የነበረውን አባታቸው ሲመክሩ ቁርአን እንዲህ እንዳሉ ይነግረናል "አባቴ ሆይ"ከሁሉ ምክራቸው በፊት "አባቴ ሆይ "የሚለውን ልብን የሚገዛ ቀጣይ እርምጃን የሚያስተካክል የሆነ ቃል ያስቀድማሉ "አባቴ ሆይ" ምነኛ ያማረ ቃል በተውሂዱ ፈርጥ በነቢላሂ ኢብራሂም አንደበት አባቴ ሆይ ተውሂድን ከወላጅ ሃቅ ጋር አጣምሮ የያዘ ውብ ቃል "አባቴ ሆይ" ከልብ የሚቀመጥ ንግግር ። አላህ በነቢላሂ ኢብራሂም መንገድ የምንሞት ያድርገን። ✍ዘ.ሐ

  • ሀቢቢ ስራህ ብቻ ነው ሚከተልህ! ፀሀዩ ሳይበረታ ቶሎ ቀብረነው እንመለስ እንደሚባል አትርሳ!🥀 ቻናሉን ይቀላቀሉ 👇👇👇👇 https://t.me/ebnusitina

  • በሰለፊ ስም ተክፊሮችን አንታገስም ሲል ትንሽ አያፍርም እንዴ ??😂😂 ወሀቢያ ሆኖ ሙስሊሙን ኡማ የማያከፍር አለ እንዴ ?? ካላከፈረማ ምኑን ወሀቢያ ሆነ ይህ ሰውየ ማለት በኢብኑ የመስዑድ ሴንተርን አላማ ደሴ ላይ በማስፋፋት ብዙ ዑለማዎችን ያፈናቀለ ፥ ያሳሰረ አሁንም ሃሪማዎችን ካላጠፋን ህልውና የለንም ብሎ በግልፅ የሚናገር የወሎ ሃሪማዎችን በይፋ እናጠፋቸዋለን ብሎ የተናገረ ባሁኑ ሰአት የአማራ ክልል መጅሊስ መሪ የሆነ ፀረ ሱፊያ ሰው ነው። ኧረ በጠመጠማቹት ነጭ ማታለያ ይሁንባችሁ

  • #እኔ የነብዩ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም ነኝ አንተስ⁉️ 💠አቡ አያሽ የተባለ ወሃብያ ነብዩ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም ይሳሳታሉ ኢብኑ ተይምያ አይሳሳትም ሲል አንዴት ቅጥል እንዳልኩ አጠይቁኝ ወላሂ !! ይህ ስሜት ማንኛውም የነብዩን ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም ፍቅር ያለው ሰው እንደሚያንገበግበው እርግጥ ነው ። አብዱላህ አልሃረሪ በሂወታቸው ወንጀል ቀርቶ ከራህ (የሚጠላ )ነገር ሰርተው አያቁም የሚሉ ነብያት ግን ሃቂቃ ማዕሲያ (ወንጀል መሆኑን እያወቁ )ወንጀል ሰርተዋል ብሎ የሚሞግተው የአህባሽ ቡድን ከነብያት ውስጥ የኛው የፍጡራን አይነታ ነብዩ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም መኖራቸው እርግጥ መሆኑን የታወቀ ነው። ታዲያ ይህ ነገር የማይቆረቁረው የአብዱላ አልሃረሪ ጀመዓ ከኢብኑ ተይምያ የወሀብያ ጀመዓ በምን ይለያል ⁉️አንተ ከፈለከው ጋር ሁን። እኔ ግን ከነብዩ ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም ክብር ጋር ከቆሙት ከጥንት ዑለማዎች ጎን ነኝ ፤ አዲስ የመጣን ሃሳብ በተውሂድ ስም ወሀብያንም ሆነ ፤ ወሃብያን በመታገል ስምም አህባሽን አልቀበልም ።‼️ 🔱መኖራችንም መሞታችንም በድሮ ዑለማዎች መንገድ ላይ።‼️ https://t.me/sufiyahlesuna

Ebnu Sitina (BILADEN) — tgindex