- Последний пост
- 14 авг.
- Последнее чтение
- 15 авг.
- Постов за неделю
- 3
- Всего постов
- 24
- Тип
- открытый
- Язык
- ti
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 11
- 1/48двое суток
- 12
- 1/72трое суток
- 13
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
🇮🇱🇺🇸🇸🇾 ፕሬዚዳንት ትራምፕ እስራኤል በሶሪያ ልትፈጽመው የነበረውን ጥቃት እንዳይካሄድ አገዱ እስራኤል በሶሪያ ግዛት ውስጥ ወታደራዊ የአየር ጥቃት ለመፈጸም አቅዳ የነበረ ቢሆንም፣ የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በጉዳዩ ላይ ጣልቃ በመግባት ጥቃቱ እንዳይካሄድ ማገዳቸውን የእስራኤሉ «Channel 13» ዘግቧል። እስራኤል በሶሪያ ውስጥ በሚገኙ ስትራቴጂያዊ ወይም ወታደራዊ ኢላማዎች ላይ አዲስ ጥቃት ለማድረስ ዝግጅት አድርጋ ነበር። ፕሬዚዳንት ትራምፕ ጥቃቱ በቀጠናው ላይ ሊያስከትል የሚችለውን ተጨማሪ ውጥረት እና የጦርነት መስፋፋት በመስጋት እርምጃው እንዲታገድ ውሳኔ አስተላልፈዋል። ይህ ክስተት ዋሺንግተን እና ቴል አቪቭ በቀጠናው በሚያደርጓቸው ወታደራዊ እርምጃዎች ላይ አሁንም የኋይት ሀውስ ቀጥታ ቁጥጥር እና ተፅዕኖ ከፍተኛ መሆኑን የሚያሳይ ነው ተብሏል። 🔗 ለ ፈጣን ዜናዎች ቻናላችንን ይቀላቀሉ! @eneho_heber
13ኛ ዓመት ቴሌግራም! እ.ኤ.አ. ነሐሴ 14 ቀን 2013 የተጀመረው Telegram፣ ዛሬ በዓለም ዙሪያ ወደ 1 ቢሊዮን የሚጠጉ ንቁ ተጠቃሚዎች ያሉት ግዙፍ የመልዕክት መድረክ ሆኗል። ላለፉት 7.5 ዓመታት በዓለም ላይ በብዛት ከሚወርዱ 10 የሞባይል መተግበሪያዎች መካከል ቆይቷል። 🌍📱 ፈጣን፣ ዘመናዊ እና ሰዎችን ከዓለም ጋር የሚያገናኝ መድረክ ስለሆንክ እናመሰግናለን! 🔗 ዜናዎችን ለማግኘት ይቀላቀሉን፦ 👉 @eneho_heber
🧚#እብዷ_ጅልባቢስ🧚 ልብ አንጠልጣይ እና አስተማሪ ኢስላሚክ ታሪክ ነገ በእለተ ጁመዓ ሊጀመር ነው ......🎊🎉🎊🎉🎊🎉 ❄️ወላሂ እውነት ነው ተቀላቀሉ❄️
📣 ለአዲስ ኢስላሚክ ቻናል ባለቤቶች በሙሉ 📣 ቻናላችሁን በአጭር ጊዜ የምታሳድጉበትና ወደ ብዙ ሰዎች ዘንድ የምትደርሱበትን ምርጥ ዕድል ይዘንላችሁ መጥተናል‼️ ✅ መሟላት ያለባቸዉ መስፍርቶች:- 1️⃣ ኢስላሚክ ቻናል የሆነ❴ጀማሪ ብትሆኑም❵ 2️⃣ እዚህኛው👇 ፎልደር ላይ ቻናላቹ ያልተካተተ ብቻ ⭕️ቻናላችሁ እንዳለ ለማወቅ👉 አንድ ጊዜ ተጫኑ 3️⃣ ለንግድና ማስታወቂያ ያልተከፈተ። ✅ መስፈርቶቹን የምታሟሉ ከታች ባለው አድራሻ ቻናላችሁን ማስመዝገብ ትችላላችሁ👐 ለመመዝገብ👉 @ISLAM_WAVE1 ⚡ ☄በተጨማሪ ቻናል መግዛት የምትፈልጉና 👉ከ5k member በላይ የሚሸጥ ቻናል ያላችሁ ደግሞ በዚህ👉@waver_boy1 አናግሩኝ መገበያየት እንችላለን🫂
❗️ AI Agent የጅምናዚየም ድረ-ገጽን ሃክ አደረገ! አውስትራሊያ በAI Agent የተፈጸመ አስገራሚ የሳይበር ክስተት መዝግባለች። በAnthropic Claude የሚሰራ OpenClaw የተባለ AI Agent ለተጠቃሚው የጅምናዚየም ስፖርት ክፍለ-ጊዜ እንዲያስይዝለት ታዞ ነበር። 🤖 በሂደቱ ግን የጅምናዚየሙ ሲስተም ውስጥ ያለ ክፍተት አገኘ። ይህ ክፍተት ያለ ፓስወርድ የሌላ ሰውን ምዝገባ እንዲሰርዝ ያስችለው ነበር። ተጠቃሚው በWaitlist 4ኛ ደረጃ ላይ ነበር። ወደ ላይ እንዲያወጣው ሲጠየቅ፣ AI Agent-ው በ1ኛ ደረጃ የነበረውን ሰው ምዝገባ ሰረዘ። በዚህም ተጠቃሚው ከ4ኛ ወደ 3ኛ ደረጃ ወጣ። 😨 አስገራሚው ነገር ይህ የተፈጸመው በሰው ሃከር ሳይሆን፣ AI Agent የተሰጠውን ግብ ለማሳካት በራሱ የወሰነውን እርምጃ በመውሰድ ነው። ⚠️ ትልቁ ጥያቄ፦ AI Agent በራሱ ሲሰራ እና ጉዳት ሲያደርስ ተጠያቂው ማን ነው? 👤 ተጠቃሚው? 💻 የAI Agent አዘጋጁ? 🏢 የAI ኩባንያው? 🌐 ወይስ የሲስተሙ ባለቤት? AI Agents የበለጠ ራሳቸውን ችለው እየሰሩ ሲመጡ፣ የደህንነትና የህጋዊ ተጠያቂነት ጉዳይ የበለጠ አሳሳቢ እየሆነ ነው።
ሳዑዲ አረቢያ ከእስራኤል ጋር ግንኙነቷን ካላሻሻለች የአሜሪካና የሳዑዲ የኒውክሌር ስምምነት ውድቅ እንደሚሆን ዋይት ሀውስ አስታወቀ! • ሀሩን ሚዲያ | ሐምሌ 17 ቀን 2018 ዓ.ል የዋይት ሀውስ ፕሬስ ሴክሬታሪ ካሮላይን ሌቪት፤ ሳዑዲ አረቢያ የአብርሃም ስምምነትን በይፋ ተቀብላ ከእስራኤል ጋር ያላትን ግንኙነት መደበኛ ካላደረገች (ካላሻሻለች) በስተቀር፤ በቅርቡ የተፈረመው የአሜሪካና የሳዑዲ የሲቪል ኒውክሌር ስምምነት ተግባራዊ እንደማይሆን አረጋግጠዋል። ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በ'ትሩዝ ሶሻል' ማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ላይ ባሰፈሩት መልእክት፤ ስምምነቱ "የሚጸድቅ ቢሆንም፣ ነገር ግን ሙሉ በሙሉ ሳዑዲ አረቢያ የአብርሃም ስምምነትን በመቀላቀሏ ላይ የተመሰረተ ነው" ብለዋል። አክለውም በዚሁ ስምምነት መሠረት ምንም ዓይነት የዩራኒየም "ማበልጸግ ተግባር እንደማይኖር" አስታውቀዋል። የአሜሪካው የኢነርጂ ሴክሬታሪ ክሪስ ራይት እና የሳዑዲ አቻቸው ይህንን ስምምነት ረቡዕ ዕለት ሲፈርሙ ይህን አዲስ ቅድመ ሁኔታ ያላነሱ ሲሆን፤ ሳዑዲ አረቢያ ከእስራኤል ጋር ግንኙነት ለመጀመር ራሷን የቻለች የፍልስጤም ሀገር ምስረታን እንደ ቅድመ ሁኔታ ስታነሳ መቆየቷ ስምምነቱ በቀላሉ ወደ ማጠናቀቂያው እንዳይደርስ እንቅፋት ሊሆንበት እንደሚችል ተገምቷል። 📅 ሰፈር 11 ቀን 1448 ዓ.ሂ © ሀሩን ሚዲያ
📢ታላቅ የምስራች ከተቅዋ መስጂድ ለዲን ዕውቀት ፈላጊዎች! 🔹የተቅዋ መስጂድ መድረሳ በታላላቅ ዑለሞች የሸሪዓ ዕውቀትን እንዲሁም ቁርኣንን ከጀማሪ እስከ ሂፍዝ ድረስ "ኢጃዛ" ባላቸው ኡስታዞች ከመግሪብ - ዒሻ እንዲቀስሙ ጥሪ ያስተላልፋል። 🔹 የሚሰጡ የኪታብ ት/ቶች:- የቁርኣን ተፍሲር:- በሸይኽ ዑመር ጀማል ቡሉጘል መራም:- በሸይኽ ሙሀመድ ጧሂር ፊቅህ: በኡስታዝ አብዱሽኩር ሱልጧን 🔹ትምህርቱ የሚሰጠው በነፃ ነው። 🔗ለበለጠ መረጃ :- በ0941217946 ይደውሉ። #የተቅዋ_መስጂድ_መድረሳ #የነገው_ትውልድ_መገንቢያ
✋የዘንድሮው የዐሹራ ፆም (የሙሐረም 10ኛው) ቀን ሐሙስ ሰኔ 18 ላይ ይውላል። ይህንን ታላቅ ቀን መፆም ያለፈውን የ365 ቀናት (የአንድ ዓመት) ወንጀል ያስምራል። በላጩና ተመራጩ አፆፃም...ነብዩ (ﷺ) አይሁዶችን ለመለየት ዘጠነኛውንም ቀን አብሮ ለመፆም አስበው ስለነበር፣ በላጩ መንገድ ረቡዕ (ሰኔ 17) እና ሐሙስን (ሰኔ 18) አከታትሎ መፆም ነው። ሌሎችንም በማስታዎስ የአጅሩ ተጠቃሚ ያድርጓቸው! ~ t.me/Sle_qelbachn1 t.me/Sle_qelbachn1
💾 SD Card ወይም በተለምዶ ሚሞሪ ካርድ ተፈላጊነቱ ለምን ቀነሰ? ከገበያ ለምን ወጣ? ያኔ.. ቪዲዮና ዘፈን ለማስጫን ቪዲዮ ቤት ሄደን ባለ 2GB ሚሞሪ ሙሉልኝ የምንልበትን ጊዜ ታስታውሳላችሁ? በድንገት Corrupt እንዳይሆንብን የምናደርገው ጥንቃቄ፣ ስልካችን ካርዱን ሳያነበው ሲቀር የነበረን ጭንቀት ሁላችን ቤት የነበረ ታሪክ ነው። ግን አስተውላችኋል? አሁን አሁን አዳዲስ ስልኮችን ስንገዛ የSD Card መሰኪያ (SD Card Slot) የላቸውም። ያ ስንት ትዝታ ያስቀመጥንበት የድሮ ጓደኛችን SD Card ቀስ በቀስ ከገበያ እየወጣ ነው። ለመሆኑ ለምን? 1. Cloud Storage መምጣት አሁን ላይ ፎቶ፣ ቪዲዮ እና ፋይሎቻችንን በስልካችን ውስጥ ከምናስቀምጥ ይልቅ በGoogle Drive፣ iCloud እና ቴሌግራም ላይ Saved Messages ውስጥ ማስቀመጥ እየተለመደ ነው። አብዛኛዎቹ የስልክ አምራች ድርጅቶችም ከእነዚህ የcloude storage አፕሊኬሽኖች ወርሀዊ subscription ስለሚያስከፍሉ በተዘዋዋሪ የገንዘብ ማግኛ አማራጭ ይፈጥርላቸዋል። 2. የስልኮች Internal Storage ማደግ የቀድሞ ስልኮች የነበራቸው ማከማቻ ቢበዛ 8GB ወይም 16GB ስለነበር ሚሞሪ ካርድ የግድ ያስፈልግ ነበር። አሁን ግን አነስተኛ የሚባሉት ስልኮች እንኳ 128GB፣ 256GB አልፎ ተርፎም 1TB ይዘው እየመጡ ነው። ታዲያ ተጨማሪ ካርድ ማን ይፈልጋል? 3. የፍጥነት ጉዳይ (Performance) አዲሶቹ ስልኮች የሚጠቀሙት internal storage በጣም ፈጣን ነው። በአንጻሩ SD ካርዶች data ለማንበብ ረጅም ጊዜ ይፈልጋሉ። ስለዚህ ስልኩ ቀርፋፋ እንዲሆን እንዲሞቅ እና አፕሊኬሽኖች ለመክፈት እንዲዘገዩ ያደርጋቸዋል። ኩባንያዎች የስልካቸውን ስም ለማስጠበቅ ሲሉ ካርዱን አስቀሩት። 4. የስልኮች ዲዛይን እና ውበት ቀጫጭን፣ ውብ እና ውሃ የማይገባቸው (Waterproof) ስልኮችን ለመስራት የስልክ አምራቾች እያንዳንዷ ሚሊሜትር ቦታ ታስፈልጋቸዋለች። ስለዚህ የSD card ማስገቢያን ማስቀረት ለባትሪ እና ለሌሎች ጠቃሚ ነገሮች ቦታ ያስገኛል። ባጭሩ... ቴክኖሎጂው ተቀየረና የኛ ዘመን ታማኝ ጓደኛ የነበረው ሚሞሪ ካርድ ልክ እንደ ካሴት እና CD ታሪክ እየሆነ ነው። እናንተስ የመጨረሻ ጊዜ ሚሞሪ ካርድ የተጠቀማችሁት መቼ ነው? በሚሞሪ ካርድ ምክንያት የጠፋባችሁ ትዝታ ካለ ሀሳባችሁን ኮሜንት ላይ👇 @bighabesha_softwares
видео или голосовое, без подписи
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ (CBE) ከቀናት በፊት የሞባይል ባንኪንግ መተግበሪያ ማሻሻያ (Update) አድርጓል። ይህን ማሻሻያ ተከትሎ ቁጥራቸው ቀላል ያልሆነ ደንበኞች ከፍተኛ የአገልግሎት መስተጓጎል እየገጠማቸው መሆኑን ገልጸዋል። እንደ ደንበኞች ቅሬታ ከሆነ መተግበሪያው አፕዴት ከተደረገ በኋላ፦ - አንዳንዴ ሙሉ በሙሉ ስታክ የማድረግ፣ - Passphrase አስገቡ የማለት፣ - "Unexpected error occurred!" የሚል የቴክኒክ ስህተት መልዕክት የማሳየት፣ - የመዘግየት እና ምንም አለማሳየት ችግር እየገጠማቸው መሆኑን ጠቁመዋል። ቃላቸውን የሰጡን የባንኩ ደንበኞች ችግሩን ለመፍታት በአካል ወደ ባንክ ቅርንጫፍ ቢያመሩም ከቅርንጫፎቹ የተሰጣቸው ምላሽ " ችግሩ ከአቅማቸው በላይ " መሆኑን እንደነገሯቸው ገልጸዋል። በዚህ ችግር ምክንያት ስራ ለመስራት፣ እንቅስቃሴ ለማድረግ ማቸገራቸውንና ለከፍተኛ እንግልት መዳረጋቸውን ጠቁመዋል። ወደ 951 ቢደውሉም ረጅም ደቂቃ የሚያስተናግዳቸውን እያገኙ እንዳልሆነ ገልጸዋል። የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ምሽቱን ይፋዊ ማብራሪያ ሰጥቷል። አዲስ መተግበሪያ በማስተዋወቁ ምክንያት በተወሰኑ ደንበኞች ላይ የአገልግሎት መስተጓጎል ማጋጠሙን አምኖ ይቅርታ የጠየቀ ሲሆን፣ ችግሩን በአፋጣኝ ለመፍታት ርብርብ እያደረገ መሆኑን እና ደንበኞች በ951 የጥሪ ማዕከል ወይም ባዘጋጀው የዋትስአፕ ማህበራዊ ገጽ (https://chat.whatsapp.com/BFR1h7SrAti091qznFEP4u) በኩል ድጋፍ ማግኘት እንደሚችሉ አስታውቋል። ግንቦት 20 ቀን 2018 ዓ/ም @tikvahethiopia
‼️የ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሞባይል ባንኪንግ ተጠቃሚዎች የምትጠቀሙበት አፕ አፕዴት ቢጠይቃቹም አታድርጉት ከዛ በኋላ መስራት ያቆማል።አሁን አገልግሎት እየሰጠ ያለው ወደ አዲስ ሲስተም እየተቀየረ ስለሆነ ለጊዜው አፕዴት ሳታደረጉ ተጠቀሙ እና ቅርብ ባለው ብራንች ሄዳቹ አስተካክሉ።Already Update ያደረጋቹ ምንም አማራጭ ስለሌላቹ ለመጠቀም ግዴታ ብራንች ላይ ማስተካከል አለባቹ። 🦋#Share🦋 👩💻 @ethio_techs 👨💻 @ethio_techs 👩💻
🔹 እንኳን ለ1️⃣4️⃣4️⃣7️⃣ኛው የዒድ አል-አድሃ (ዓረፋ) በዓል በሰላም አደረሳችሁ! 🔹 ይህ ታላቅ በዓል የደግነት፣ የራህማ (እዝነት) እና የጋራ መተሳሰብ ተምሳሌት ነው። መልካም በዓል! 🌛
ፋይዳ ያላያያዛችሁ እንደዚ እያለ ስለሆነ አስተካክሉ። @eneho_heber
YouTube ስልክ ላይ PIP (picture in picture) mode ጀምሯል። ያ ማለት ስልካችሁ ላይ በapplication YouTube ብትከፍቱና home button ብትጫኑ ቪዲዮው አይዘጋም። ስክሪናችሁ ላይ በpicture mode ይጫወታል። ይህን ለማድረግ YouTube ላይ ግቡና የProfile ምልክታችሁን ንኩ። ከዛ Settings -- Playback -- Picture in picture On አድርጉት። በዚህ መሰረት አስተካክላችሁ ስልካችሁ ላይ YouTube እያያችሁ የፈለጋችሁትን ስራ መስራት ትችላላችሁ። ካልሰራላችሁ update አድርጋችሁ ሞክሩት። @bighabesha_softwares
Al-Qalam Printing & Advertising ለተለያዩ ፕሮግራሞች የህትመት ፍላጎትዎ ተመራጭ! ጥራታቸውን የጠበቁ ቲሸርቶች፣ የገቢ ማሰባሰቢያ ኩፖኖችና በራሪ ወረቀቶችን ከ አል-ቀለም ህትመትና ማስታወቂያ ያገኛሉ! ዐረብኛ ይበላሽብኛል ብለው ሳይጨነቁ በተስተካከለ የዐረብኛ ፅህፈት የሚፈልጉትን ህትመት እንሰራለን። በተጨማሪም፦ 🌴ባነር 🌴ስቲከር 🌴ቢዝነስ ካርዶች 🌴 ኩፖኖች 🌴ሎጎ ዲዛይን 🌴የማግ ላይ ህትመት 🌴ሜሽ 🌴የሰርግ ካርዶች 🌴ላይት ቦክስ 🌴የኮፊያ ላይ ህትመት 🌴መጽሔት 🌴 መጽሐፍ 🌴 ቲሸርት 🌴ብሮሸር 🌴 ፖስት ካርድ 🌴ፖስተር 🌴መታወቂያ 🌴 ዲጅታል ህትመት 🌴ቢዝነስ ካርድ 🌴ማህተም 🌴ፍላየር 🌴ቦሎ 🌴ማይካ 🌴በረዶ እና ሌሎች የህትመት እና ማስታወቂያ ስራዎችን በጥራትና በውብ ዲዛይኖች እንሰራለን። እንዲሁም የተለያዩ የኦንላይን ስራዎችን በጥንቃቄ እንሰራለን። ፓስፖርት 👉እድሳት 👉 አዲስ ለማውጣት 👉 ለተበላሸ ፓስፖርት 👉 ለስም ማስተካከያ ንግድ ፍቃድ 👉እድሳት 👉ስረዛ 👉ንግድ ስያሜ ዲጅታል መታወቂያ 👉ኦርጂናል ናሺናል አይዲ በሶፍት ኮፒ እና ሀርድ ኮፒ እኛ ጋር ያገኛሉ ። በተጨማሪም ማንኛውንም የሎጎ እና የሌሎችንም ድዛይን ባማረና ጥራት ባለው መልኩ ሰርተን እናስረክቦታለን። በኦንላይን ይዘዙን በግራፊክ ዲዛይነሮቻችን እንዲሁም በድዛይኖቻችን ይገረማሉ ፣ ይረካሉ ፣ ይደመማሉ፣ ይደሰታሉ ጥራትና ታማኝነት መለያችን ነው !!! አል-ቀለም ህትመትና ማስታወቂያ ለበለጠ መረጃ 📞0944246470 👉👉t.me፡//@Al_Qalam_Printing7 Discussion Group https://t.me/Al_Qalam_Printing Channel https://t.me/Al_Qalam_Printing_Advertising ካሉበት ሆነው ማዘዝ ይችላሉ!! Al-Qalam Print
የቴክኖሎጂው ዓለም ድንጋጤ: ኦራክል 30,000 ሰራተኞችን በአንድ ቀን አባረረ! ታዋቂው የቴክኖሎጂ ኩባንያ ኦራክል (Oracle) በታሪክ ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ በአንድ ቀን ብቻ 30,000 የሚጠጉ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ (IT) ባለሙያዎችን ከሥራ አሰናብቷል። ዋና ዋና ነጥቦች:- 🔹 በሰው ምትክ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ (AI):- ኩባንያው እነዚህን ሰራተኞች ያሰናበተው በሰለጠነ "Neural Network" ወይም በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ለመተካት መሆኑ ተገልጿል። ሰራተኞቹ ከመባረራቸው በፊት ስራቸውን ለ AI ስልጠና እንዲውል በዝርዝር እንዲመዘግቡ ተደርገው ነበር። 🔹 የገንዘብ ኪሳራ:- በድንገተኛው ስንብት ምክንያት በርካታ ሰራተኞች በኩባንያው ውስጥ የነበራቸውን የጥቅማጥቅም ድርሻ (Stock Options) አጥተዋል። አንዳንዶቹ እስከ $300,000 (ከ17 ሚሊዮን ብር በላይ) የሚገመት ጥቅም እንዳጡ ተዘግቧል። 🔹 ስትራቴጂያዊ ለውጥ:- ኦራክል ይህን የወሰደው ከደመወዝ የሚተርፈውን በቢሊዮን የሚቆጠር ዶላር አዳዲስ የ AI ዳታ ሴንተሮችን ለመገንባትና ከሌሎች የቴክኖሎጂ ግዙፎች ጋር ለመወዳደር እንዲረዳው ነው። 🔹 የሰራተኞች እሮሮ:- ኩባንያው ከፍተኛ ትርፍ እያገኘ ባለበት ወቅት እንዲህ ያለ እርምጃ መውሰዱ በቴክኖሎጂው ማህበረሰብ ዘንድ ከፍተኛ ቅሬታን ፈጥሯል። "ስራችንን ለ AI አስተምረን ተባረርን" የሚሉ ድምጾች በስፋት እየተሰሙ ነው። የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ እድገት በስራ ገበያ ላይ እያመጣ ያለው ተጽዕኖ አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን ይህ ክስተት ትልቅ ማሳያ ሆኗል። 🤖 ⚠️ 🤖 @Ethio_Techs 🤖
📌 "እንደ እናት እንደ አባት 5" የኸይር ስራ ጥሪ የየቲሞችና መሳኪን ልጆች የዒድ አል-አድሃ አልባሳት መርሃ-ግብር የዳሩል አርቀም በጎ አድራጎት ማህበር ላለፉት አራት ተከታታይ ዓመታት "እንደ እናት እንደ አባት" በሚል መሪ ቃል፣ የዒድ አል-አድሃ (አረፋ) በዓልን አስመልክቶ ለየቲሞችና በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ለሚገኙ ህፃናት አዳዲስ አልባሳትን ሲያለብስ ቆይቷል። ዘንድሮም ለ5ኛ ዙር ለ300 ህፃናት የዒድ ደስታን ለመፍጠር ዝግጅቱን አጠናቆ ጨርሷል፤ ለዚህ ታላቅ የኸይር ስራ ደግሞ የእናንተ ልግስና እና የተለመደ ትብብር ወሳኝ ነው። 🛍️ የአንድ ልጅ ሙሉ የበዓል አልባሳት ፓኬጅ (5,000 ብር)፦ 🔹 ለወንዶች፦ ጥራት ያለው ጫማ👟 +ሱሪ 👖 + ሸሚዝ 👔 🔹 ለሴቶች፦ ጥራት ያለው ጫማ 👟 + ውብ ቀሚስ 👗 + ሒጃብ 🧕 ለመሳተፍ፦ 💳 የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ (CBE)፦ 1000451773759 📍 አድራሻ፦ ኮተቤ መሳለሚያ 📞 ለበለጠ መረጃ፦ 0939963771/0913219422 ወይም @abu_osman4 / @Amtullahiiiiii 📱 Telegram፦ @darularkemfamily #እንደ_እናት_እንደ_አባት #አረፋ_ከየቲሞች_ጋር #ዳሩል_አርቀም #የበጎ_አድራጎት #የዒድ_ስጦታ
በትግራይ ክልል የሙስሊሞች መካነ መቃብር ለሌላ እምነት የአምልኮ ሥፍራነት ተሰጥቷል - የትግራይ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት የትግራይ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት፤ በክልሉ ዓቢይ ዓዲ ከተማ ከጥንት ጀምሮ በሙስሊም መካነ መቃብርነት እያገለገለ የሚገኝ በተለምዶ “ሓሽዲ” ወይም “እምባ ኣሕዲን” በመባል በሚጠራ ታሪካዊ ቦታ፤ ያለአግባብ ወደ ሌላ የእምነት አምልኮ ሥፍራነት እንዲቀየር በከተማ አስተዳደር ተሰጥቷል ሲል አሳውቋል። ምክር ቤቱ ይህ ያስታወቀው ዛሬ ሚያዝያ 20/2018 ነው። ምክር ቤቱ ሥፍራው በትግራይ ክልል የመሬት ቢሮ “አግባብነት የለውም፣ ሥልጣናችሁም አይደለም” የሚል ደብዳቤ በይፋ ተሰጥቷቸው እያለ፣ ሕጋዊ መመሪያውን ወደ ጎን በመተው በቦታው ላይ በኃይል ህንፃ በመገንባት ላይ ይገኛሉ ብሏል። ይህን ተከትሎም ድርጊቱ በእስልምና እምነት ላይ የተፈፀመ ጥሰት እና የሕዝቡን ሰላማዊ አብሮ የመኖር እሴት የሚያናጋ ነው ሲል ወቀሳ ሰንዝሯል። ጉዳዩን አስመልክቶ የክልሉ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ከዓብይ ዓዲ ኮሚቴ ጋር በመሆን ሰፊ ማብራሪያና ጋዜጣዊ መግለጫ ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል። ሚንበር ቲቪ
~በንግድ ዓለም ውስጥ መጀመሪያ የሚገኝ ትርፍ የስኬት መዳረሻ ሳይሆን የጥንካሬ መፈተኛ ነው። ብዙዎች የንግድ አየር ሲከፈትላቸውና የመጀመሪያዋን ትርፍ ሲጨብጡ፣ ገና ሳይቆሙ ለመሮጥ፣ ሳይደላደሉ ለመታየት ይቸኩላሉ። ነገር ግን እውነተኛ ባለሀብትነት የሚለካው በምትነዳው መኪና ወይም በምትኖርበት ቤት ሳይሆን፣ በገነባኸው ተቋም ጥንካሬና ዘላቂነት ነው። የመጀመሪያውን ትርፍ ለቅንጦትና ለታይታ ማዋል፣ የሚበቅለውን ዘር ገና ሳይዘራ እንደመብላት ይቆጠራል። ለታይታ ብለው መኪና ገዝተው፣ የንግድ ካፒታላቸውን አሟጥጠው በመጨረሻም መኪናውንም ንግዱንም አጥተው ባዶ እጃቸውን የቀሩ ብዙዎች ናቸው። "እዩኝ እዩኝ" የማለት አባዜ የቢዝነስ ትልቁ ጠላት ነው። ስለዚህ፤ ትርፍህን መልሰህ በንግድህ ላይ አፍስሰው። ካፒታልህን አሳድግ፣ አድማስህን አስፋ። ዛሬ የምታገኘውን "እንቁላል" ለቁርስ ከመብላት ይልቅ፣ ነገ ለሚፈለፈለው ጫጩትና ለሚመሰረተው ትልቅ የዶሮ እርባታ ታገስ። ንግድ የሚጸናው በታይታ ሳይሆን በብልህነትና ትርፍን መልሶ ኢንቨስት በማድረግ ነው። መጀመሪያ ቢዝነስህን አሳድገው፤ እሱ ራሱ ነገ የሚገባህን ክብርና ድሎት ያመጣልሃል። (ይህ ምክር የአባቴ ሃሳብ ነው፤ እኔ በቃላት ገለጽኩት እንጂ።) AbuSufiyan