- Последний пост
- 13 авг.
- Последнее чтение
- 15 авг.
- Постов за неделю
- 1
- Всего постов
- 25
- Тип
- открытый
- Язык
- und
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 7
- 1/48двое суток
- 8
- 1/72трое суток
- 8
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
Madrona....
“ሰው በራሱ ተላላነት ሕይወቱን ያበላሻል፤ በልቡ ግን እግዚአብሔርን ያማርራል።” — ምሳሌ 19፥3
.....የልባችንን ስብራት ፤ ፍርሃታችንን ፤ እምንወደውን ነገር ያለ አንዳች መሳቀቅ ለምንነግራቸው ሰዎች !🖤🙌
ሰባራችንን ለመጠገን ልክ የሆነ ግን እሚያመንን ነገር ይዘው ጎናችን ለምናገኛቸው ልበ ውቦች !🖤🙌
🕊እንኳን ለቅዱስ ገብርኤል ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ❕ "የእግዚአብሔር መልአክ በሚፈሩት ሰዎች ዙሪያ ይሠፍራል፥ ያድናቸውማል።" (መዝ. 34፥7) ውድ የቻናላችን ቤተሰቦች፤ ሐምሌ 19 ቀን ሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል ሠለስቱ ደቂቅን ከነበልባል እሳት፣ ህፃኑ ቅዱስ ቂርቆስንና እናቱን ቅድስት ኢየሉጣን ከፈላ ድስት ያዳነበት ታላቅ እለት ነው። ሠለስቱ ደቂቅና ቅድስት ኢየሉጣ በእምነታቸው በመጽናታቸው እግዚአብሔር መልአኩን ልኮ እሳቱን አቀዘቀዘላቸው። ዛሬም በሕይወታችን፣ በቤታችንና በሥራችን የገጠመንን ማንኛውም ፈተና እሳት አምላካችን በቅዱስ ገብርኤል ተራዳይነት ወደ ሰላም ይለውጥልናል። 🕊️የበዓል መልካም ምኞት የቤታችሁንና የልጆቻችሁን ፈተና ይባርክ፤ ያቀዝቅዝላችሁ። እንደ ሠለስቱ ደቂቅ በእምነት የምትጸኑበትን ጥንካሬ ይስጣችሁ። ለየሕፃኑ ቅዱስ ቂርቆስ በረከትና ጥበቃ አይለያችሁ። የሊቀ መላእክት የቅዱስ ገብርኤል አማላጅነትና ጥበቃ አይለየን❕ መልካም የበዓል ቀን❕
Don't ask me again ስለማንም ስለእከሌ ማወቅ ከፈለጋችሁ እከሌን ጠይቁ በቃ እኔን ፍቱኝ...privacy የሚባል አለ ከራሳቸው ጠይቁ ሁሉንም ... Ask the owner about what you want to know.... I'm nah google guys😌 chat gbtም አለ ብቻ I have my own problems so i'm nah available to check the other situation okey🤧 so, please leave me alone ደሞ እንደዚህ ስል ሌላ አስቡ😁😁😁
ስሜት አልባ ከሆንኩኝ ሰንበትኩ። እንጃ ብቻ ምናልባት ድንዛዜ ብቻ ነው እየተሰማኝ ያለው። አው፣ ሁሉም ነገሮች ተደራርበው ተደራርበው ክብደታቸው ልሰማኝ ስገባ አደንዝዘውኛል። አልቀለለኝም አልከበደኝምም። ትላንት እንደነብር ያስቆጣኝ የነበረና በደስታ ያስፈነድቁኝ የነበሩ ነገሮች ምን እንደሆኑ እንኳ ረስቻቸዋለሁ። ብርድ... ሙቀት... ፍቅር... ጥላቻ... ሀዘን... ደስታ... ናፍቆት... እኚህ ሁሉ ስሜቶች ምን እንደሆኑ እንጃ። በተለይ በተለይ ናፍቆት። እዚህ ላይ ስስ እንደነበርኩ አስታውሳለሁ። አሁን መቼለት ቻው ብዬ የተለየሁትን ሰው ትንሽ እርምጃ እንደተራመድኩ ነበረ፣ የናፍቆት መብሰልሰለ ይጀምር የነበረው። አሁን አሁን እሱም ደብዛው ጠፍቷል። እንጃ ብቻ ምንም እየተሰማኝ አይደለም። የነገራቶችን ስሜት መረዳት ካቆምኩኝ ሠነባበትኩኝ። ግን እኔ ብቻ ነኝ??
ከፍ ካለው ሰማይ ክዋክብት ካለበት በጠቆረው ለሊት ቀን በጨለመበት የጠፋውን ልቤን አገኝ እንደሁ ድንገት እንደለመደብኝ ዛሬም ልንከራተት ሆሆሆይ ወይ ፍቅር ሆሆህይ ወይ መውደድ አዬዬዬዬዬዬዬዬዬ... ከአይኔ ወዲያ ማዶ ሩቅ ሀገር ያለኸው ሰባራውን ልቤን ጉዳቴን ባየኸው አይኖቼ እንባ ጋርደው ደጅ ደጁን ያያሉ እንደወፏ በሮ ይመጣል እያሉ🥹😢😭 የትዝታ ጌታ የፍቅር ጀግና ነህ መንገድህን አላውቀው በየት ልከተልህ ልቤ ቤሩን ዘጋ እርም አለ ሌላው በአንተ መሸነፉን መረታቱን ሲያውቀው ተረታሁ ተረታሁሁሁሁሁሁ ተረታሁሁሁሁሁ..... አሃውውውውው...... ከፍ ባለው ሰማይ ክዋክብት ባለበት በጠቆረው ለሊት ቀን በጨለመበት የጠፋሁን ልቤን አገኝ እንደሁ ድንገት እንደለመደብኝ ዛሬም ልንከራተት ሆሆይ ወይ ፍቅር ሆሆሆይ ወይ መውደድ አዬዬዬዬዬ በጎ ነኝ አልልም የባሰብኝን ድኛለሁ አልልም የታመምኩትን በናፍቆት መንደዴን እንቅልፍ ማጣቴን በእኔ ቦታ ሆኖ ማን አየሁ ጉዳቴን ምስልህ ተስሎ ልቤ ውስጥ ያለኸው እንደመስቀሏ ወፍ ታይተህ የጠፋኸው ካለኸበት ሆነህ ቢሰማህ ጩኸቴ ካለኸበት ሆነህ ውጣልኝ ከአንጀቴ😢😢😢😢😢 ተረታሁሁሁሁሁሁሁሁ ተረታሁሁሁ አሃሃሃው.....🥹🥹🥹🥹🥹🥹🥹 (ከልጅነቴ ጀምሮ ከእናቴ አፍ እሰማው ነበር አሁን በኔ🥹....)
ፍቅር በአንድ አዳር ብን ብሎ አይጠፋምና ተስፋ የያዘውን ለመልቀቅ ብዙ ጊዜ ይፈልጋልና አይምሮ አርፎ አይቀመጥምና እያንዳንዱ የቃላት ልውውጥ መልሶ መላልሶ እያመጣ ያሰቃየናልና ነገሮች የተለወጡት የቱ ጋር እንደሆነ ለማወቅ ሲባዝን ይኖራልና መጥፎ ነገር ተናግረን ይሆን እንዴ? ብሎ ይጨነቃልና መታገስ የሚገባንን ያህል አልታገስን ይሆን እንዴ ብሎ ይጨነቃልና የሰዎች አይን ውስጥ ለመግባት አልችል ይሆን እንዴ ብሎ ይጨነቃልና በአግባቡ የመረዳት አቅም ይጎለኝ ይሆን እንዴ ብሎ ይጨነቃልና መልስ የሌላቸው ጥያቄዎችን ተሸክመን እንዞራለን እውነቱ ግን .... የሆነ ሰው ያለመፈለግን ስሜት ሲያሳያችሁ አይምሮዋችሁ ቀድሞ የሚነግራችሁ እራሳችሁን እንድትወቅሱ መሆኑ ነው ይኼ ስህተት ነው አለመፈለግ ሲሰማችሁ መጀመሪያ መታገልን አቁሙ መቼም መልስ ላታገኙ በጥያቄ አትድከሙ ሁሉም ነገር መቋጫ ላይኖረው ይችላል አንዳንድ ነገር እንዲሁ አየር ላይ ተበትኖ የሚቀር ነው ሁሉም ስንብት መተቃቀፍ እና መላቀስ የለውም አንዳንድ ጊዜ እንደወጡ መቅረትም አለና አንዳንዴ ሰዎች መራቅን ይመርጣሉ አንዳንዴ ሰዎች መታገልን ያቆማሉ አንዳንዴ ሰዎች መሞከርን ይተዋሉ አንዳንዴ ሰዎች ይቀዘቅዛሉ አንዳንዴ ሰዎች ማውራት ያቆማሉ አንዳንዴ ሰዎች ትኩረታቸውን ወደሌላ ቦታ ያደርጋሉ ለዚህ ነው እያንዳንዱን ዝምታ የሆነ ትርጉም ለመስጠት መድከም የሌለብን ዝምታም ብቻውን መልስ ነውና ሁለተኛው ነገር በነፃ ሊሰጣችሁ የሚገባውን ነገር በልመና መጠየቅን አቁሙ ፍቅር ስጦታ ነው መከበር የምርጫ ጉዳይ ነው መልካምነት የውሳኔ ጉዳይ ነው ክብራችሁን በልመና አታረጋግጡ ሶስተኛው ነገር ለራሳችሁ ማዘኛ ጊዜ እና እድል ስጡት ጠንካራ መስላችሁ ለመታየት አትድከሙ እራሳችሁን "ደህና ነኝ" ብላችሁ አታታሉት ስብራታችሁን ለመሸፈን ፈገግ አትበሉ ውስጣችሁ እያለቀሰ አትሳቁ መዳን ያልተጎዱ በማስመሰል ውስጥ አይገኝም መጎዳታችሁን ማመን የመዳን የመጀመሪያው እርምጃ ነው ማልቀስ ካለባችሁ አልቅሱ ሰላም ካልተሰማችሁ ፀልዩ የሚያረጋጋችሁ ከሆነ የተሰማችሁን በዲያሪም ሆነ በወረቀት ላይ ፃፉት የሚቀላችሁ ከሆነ ከምታምኑት ሰው ጋር አውሩበት እንባችሁ የድክመት ምልክት አይደለም እንባ የልባችሁ እውነተኛ አፍቃሪነት ማሳያ ነው አራተኛው ነገር ዋጋችሁን በሰዎች አስተያየት መመዘን ማቆም ነው መስታወትን ውሰዱት .... እናንተ አላይም ብትሉም ማንፀባረቁን አያቆምም የእናንተም ማንነት እንዲሁ ነው .... ሰዎች እውቅና ሊሰጡት ስላልፈቀዱ አይጠፋም እናንተ እናንተን ናችሁ አቅማችሁ አብሯችሁ ነው መልካምነታችሁ እንዳለ ነው ለትክክለኛው ፍቅር ትክክለኛ ሰው ናችሁ ለመከበር በቂ ናችሁ መገፋት መታወቂያችሁን አይቀይረው ለእነሱ ስትሉ የተዋችሁትን ልምዳችሁን አስታውሱ ለእነሱ ስትሉ የተዋችኋቸው ጓደኞቻችሁ ጋር ተመለሱ ለእነሱ ስትሉ ነገ ነገ እያላችሁ ሳታነቡ ወዳስቀመጣችኋቸው መፃህፍት ተመለሱ ለእነሱ ስትሉ ሳትራመዱ ያዘገያችሁትን እርምጃ ተራመዱት የሆነ አዲስ ነገር ተማሩ እንደገና መሳቅ ጀምሩ ቀስ በቀስ የማንንም ይሁንታ የማይፈልግ ህይወት ገንቡ AJ *** እንዴት አደራችሁ?? መልካም ቀን🥰
በእውነቱ ማጋነን አደለም ሀጢያት ብትሆን ራሱ ገነት መግባቴ ቀርቶብኝ አንተን ብቻ እሻለሁ ሀጢያት ብትሆን ም እኔ አብሬህ መሆኔን አላቆምም😊
ቻናሉን በስሜ አርጉልኝ✊✊✊ብቻዬን post ሳረግ ሰው የሌለ እየመሰለኝ ነው🙄🙄🙄 አመራሮች ወየት ጠፋችሁ🤔🤔🤔 እየተመካከራችሁ ነው😁😁 አጋፋሪዋ ነኝ ጦቢያ🤭🤭🤭
🥹🥹🥹
የጨነቀ ነገር የጠፋለት መላ፤ እንዴት ይለያያል ሰው ሳይጠላላ። እንዴት አርጎ ይዘለቃል??🤔🥹😢😭😭😭
ኦሮማን (በእውቀቱ ስዩም) ሰሞኑን እንደ አዲስ አስቴር አወቀን ሳደምጥ፣ በአሉ ግርማ ትዝ አለኝ፤ የበአሉን ኦሮማይ ታስታውሱታላችሁ ? ፀጋየ ሀይለማርያም ጋዜጠኛ ነው፤ ሮማን የተባለች ውብ ኩሩ እጮኛ አለችው፤ ሊጋቡ ጥቂት ወራት ሲቀራቸው በቀይ ኮከብ ጥሪ አስመራ ለግዳጅ ተላከ፤ በዚያም በዘመቻው መሀል ፊያሜታ የተባለች ያስመራ ሴት ተዋወቀ፤ ከባድ ፎንቃ ገባለት፤ ባስመራይቱና በሸገሪቱ ሴቶች ፍቅር መሀል ተወጥሮ በታሪካዊው ዘመቻ ላይ ተሳተፈ ፤ በመጨረሻ ሮማን አስመራ መጥታ ከሌላ ሴት ጋር ፍቅር አንደያዘው ተረዳች፤ ፊያሜታ ለሱ ብላ ህይወትዋን ትሰጣለች፤ በመጨረሻም ፊያሜታን በሞት ሮማንን በቅያሜ አጥቶ አጥቶ ብቻውን ሲቀር ልቦለዱ ይጠናቀቃል፤ ሮማን አዲስአበባ ሆና የአስቴር አወቀን ክር ካሴት ልካለት ነበር፤፤ ፊያሜታ ሮማን የላከችውን ካሴት ሰባብራ ክሩን ጎልጉላ ፊቱ ላይ የምትነበትንበት ትእይንት አይረሳኝም፤ አሁን ድንገት ጉደኛ ሀሳብ ብልጭ አለልኝ ፤ ኦሮማይን የደረሰው ስብሀት ቢሆን ኖሮ ብየ አሰብሁ፤ አንዲህ ነበር የሚሆነው፤ ሮማን እና ፊያሜታ አስመራ ተገናኝተው እየተጨዋወቱ ነው፤ -ስትገናኙ እጮኛው መሆኔን ነግሮሽ ነበር ? “አለች ሮማን ፊያሜታ ራስዋን በአዎንታ ነቀነቀች፤ “እና እጮኛ አንዳለው እያወቅሽ አፈቀርሽው?” ፊያሜታ ጸጉሯን ነስንሳ “አዝናለሁ፤ ነገሩ እዚህ ይደርሳል ብየ አላሰብኩም ነበር፤ ሕይወት አንደ ደራሽ ውሀ ገፍቶ የት አንደሚያደርሰን አናውቅም’ አለችና በስፕራይት ጠርሙስ የተቀዳ ቢራዋን ተጎነጨች፤ የቢራ ጠርሙሶች ተለቅመው ለምሽግ መስርያ ወደ ናቅፋ ስለተወሰዱ አስመራ ውስጥ የቢራ ጠርሙስ እጥረት ሰፍኑዋል፤ ለጥቂት ሰከንዶች በዝምታ ተዋጡ፤ “ ጸግሽ ነገ ወደ ግንባር ይሄዳል” አለች ሮማን፤ “ አውቃለሁ “ መለሰች ፊያሜታ፤ “ በወጣበት ይቀራል የሚል ስጋት አለኝ ‘ አለች ሮማን እንባ ባቀረረ አይን የናቅፋ ተራራ ወዳለበት አቅጣጫ እየተመለከተች” “ አትስጊ፣ ሻእቢያ ጋዜጠኛ አይገድልም” አለች ፊያሜታ በውስጥ አዋቂ ስሜት ; “አይምሰልሽ፤ ሻቢያ ከመድፍ በላይ ብእር፣ ወረቀትና ካሜራ ያሰጋዋል፤ ጠመንጃቸውን የሚያሙዋሹት ፀግሽን በመግደል ይሆናል” ፊያሜታ ዝም አለች፤ ሮማንም በጸጥታ ስታስብ ከቆየች በሁዋላ፤ “የምታግዥኝ ከሆነ ለጸግሽ አንድ የመጨረሻ ስጦታ ልሰጠው አስቢያለሁ” “ምን ?” አለች ፊያሜታ፤ ‘ ጸግሽ አንችንም እኔንም እኩል አንደሚያፈቅር አውቃለሁ፤ ለሚያፈቅራቸው ሴቶች አንደ ሞት ማበላለጥ አያውቅም፤ስለዚህ በህይወቱ የመጨረሻዋን ሌሊት አብረነው አንድናሳልፍ እፈልጋለሁ፤ “የምርሽን ነው?” ፊያሜታ በግርምት ጠየቀች፤ “አንድ ጀግና ለብዙሀን ህይወቱን መስጠቱ አግባብ ከሆነ ፣ ብዙሀን ላንድ ጀግና እቅፋቸውን መስጠታቸው ተገቢ ነው” አለች ሮማን ፍርጥም ብላ፤ ያን እለት ማታ፣ ፀጋየ በሮማንና በፊያሜታ መሀል ፣ባራት ጡቶች መሀል፣ አንደተንጋለለ በልቡ አንዲህ አለ፤ “ ይገርማል ! ሻእቢያና ደርግ ስልጣንን እንዲህ መጋራት ቢያውቁ ኖሮ ባፍሪቃ ቀንድ ለዘላለም ሰላም ይነግስ ነበር” ዋሴ https://t.me/Tobiya_kinet
የተነገረን ነገር እውነት የሚመስለን ነገርስ🥺🥹
Abrham F. Yekedas
🔥🔥👏👌
¹ አለሽ የሆነ ነገር...... አለሽ የሆነ መስህብ .... አለሽ የሆነ ግርማ....... (እንዲያ ባይሆንማ.....) ወደ ላይ.... ወደ ላይ...... (ወደ ጥጥ ደመና) ሽቅብ መንጠራራት (መኩራራት) ሳያንሰው ፣ ዝቅ ሊል ወዳንቺ —··· ዋርካን እንደ ሐረግ ምን አልፈሰፈሰው? ያልለመደበትን (ያ'ላፈጣጠሩ) ስለምን ይቸገር? አለሽ የሆነ ነገር....! ² (እኔማ በእኔ ቤት......) ከሆዱ በልጦበት.... ገበሬ ለውበት —···· እርሻውን አይለቅም ፣ ወፍ ያለ አይመስለኝም.... ዝማሬ የማያውቅ —··· ስንጥር የማይለቅም ፣ ሰው ገላ ላይ ሆኖም —···መንደፍ የጠፋበት — ንብ አይቼ አላውቅም ። እንዲህ ያለ ጥበብ — እንዲህ ያለ መላ ፣ ባንቺ አየሁ ፡ ባንቺ አየሁ — የታለ በሌላ?! ³ አለሽ የሆነ ነገር.... አለሽ....! ከጥንት መንፈስ የተዋረሰሽ .... እንደ ደሊላ — የጀግናውን ልብ ያስበረገገ (ሳምሶንን ድኩም ያረገ ) ። እሷስ በአንዲት መቀስ — በፀጉር መላጫ ፤ ይበልጣል ያንቺ ሳቅ — የጥሜ መቁረጫ ። ⁴ አለሽ የሆነ ነገር..... ያቺ “ሔለን” ሚሏት የግሪክ ሀገር ውብ የትሮይ ምርኮኛ ፤ የጠፋች እንደሆን እሷን ለማስመለስ...... በሺህ መርከብ ፈረስ — ዘምቶ አየን ጦረኛ ። ሰውማ አመሉ ነው ይዋጋል ይሞታል ፤ አይበቃም ላንቺ ግን ባህሩም ይዘምታል። ⁵ አለሽ የሆነ ነገር..... አዳም የጥንቱ — ቀልብ የሳተበት ሕግ የሻረበት (የሔዋን ፍቅር) የተቀጣበት ። (የእሱን አየን....) ገነት ሲቀር (ሞት ሲመጣ) በአንዲት ፍሬ — ትንሽ በለስ ፣ እኔስ ባንቺ የገባሁት —··· ሃጢያቴ በምን ይመለስ? አለሽ የሆነ ነገር.... __ @Bekalushumye Inspired by Cole Porter's: “You've got that thing ”