- Последний пост
- 13 авг.
- Последнее чтение
- 13 авг.
- Постов за неделю
- 3
- Всего постов
- 22
- Тип
- открытый
- Язык
- und
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 78
- 1/48двое суток
- 89
- 1/72трое суток
- 96
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
без подписи
без подписи
በኢትዮጵያ በውርስና ስጦታ ላይ አዲስ ታክስ ሊጣል ነው በኢትዮጵያ በውርስ ወይም በስጦታ በሚገኙ ገቢዎች ላይ አዲስ የታክስ ዓይነት ሊጣል መሆኑ ተገለጸ። ከአንድ ሚሊዮን ብር በላይ የሆኑ የውርስና የስጦታ ገቢዎች ለዚህ ታክስ እንደሚዳረጉ ተመልክቷል። ዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም (IMF) የአምስተኛውን ዙር የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ሪፎርም ግምገማ ተከተሎ ይፋ ባደረገው ባለ 132 ገጽ ሙሉ ሪፖርት እንደጠቆመው፣ የአገሪቱ የታክስ መሠረት በጣም ጠባብ በመሆኑ መንግሥት በየዓመቱ የአገር ውስጥ ገቢውን ለማሳደግ አዳዲስ የታክስ ዓይነቶችን ለመተግበር አቅዷል። በዚሁ ሪፖርት መሠረት በውርስና ስጦታ ከአንድ ሚሊዮን ብር በላይ በሚገኝ ገቢ ላይ ታክስ ይጣላል። በሲጋራ፣ በአልኮልና በነዳጅ ምርቶች ላይ የሚጣለው ታክስ እንደሚጨምር የተገለጸ ሲሆን፣ ይህም አገራዊ ገቢን ከመጨመር ባለፈ ለጤና ፖሊሲዎች አተገባበር ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለው ተመልክቷል። የኢኮኖሚ ባለሙያው አቶ ዋሲሁን በላይ በሰጡት አስተያየት፣ እነዚህ አዳዲስ የታክስ እርምጃዎች በአጠቃላይ በአገሪቱ ኢኮኖሚና በህብረተሰቡ ላይ ተጨማሪ ጫና ሊፈጥሩ እንደሚችሉ ጠቁመዋል። ሆኖም መንግሥት አገራዊ ገቢውን ለማሳደግ ሲል ውሳኔዎቹን በቁርጠኝነት እንደሚተገብራቸው ይጠበቃል ብለዋል። ሊዲያ ደሳለኝ ነሐሴ 05/2018 ዓ.ም
1142_የኤሌክትሮኒክ_ደረሰኝ_ሥርዓት_አስተዳደር_መመሪያ_ቁጥር_1142_2018.pdf
без подписи
ኤአይ (AI)ን እንዴት እንጠቀም ? ሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ለረጅም ጊዜ እና ያለገደብ መጠቀም የሰዎችን የፈጠራ ብቃት እና ነገሮችን በጥልቀት የመመርመና የማሰብ ክህሎትን አደጋ ላይ ሊጥል እንደሚችል በቅርቡ የወጡ ተከታታይ ጥናቶች አመልክተዋል። በዘርፉ የተደረጉ ጥናቶች እንደሚያሳዩት ሰዎች መረጃዎችን እና ውሳኔዎችን ሙሉ በሙሉ በኤአይ (AI) ላይ ጥገኞች ሆነው ማከናወን ሲጀምሩ " ኮግኒቲቭ ሰረንደር " ወይም የአእምሮን የማሰብ ስራ ለቴክኖሎጂ አሳልፎ የመስጠት ዝንባሌ ይታይባቸዋል። ይህም አእምሮ በራሱ ጥረት መረጃዎችን የማቀናበር፣ የመተንተን እና አዳዲስ ሀሳቦችን የማመንጨት የተፈጥሮ ብቃቱ እንዲደክም ያደርገዋል። በተለይ #ወጣቶች እና #ተማሪዎች ለተወሳሰቡ ጥያቄዎች እና ስራዎች ፈጣን ምላሽ ከኤአይ ማግኘት መልመዳቸው የራሳቸውን የአእምሮ አቅም የመጠቀም ተነሳሽነታቸውን እንደሚቀንሰው ተመራማሪዎች ያስጠነቅቃሉ። ነገር ግን ቴክኖሎጂውን እየተጠቀሙ አእምሮን ሁል ጊዜ ንቁ፣ ብቁ እና ጤናማ አድርጎ ለማቆየት የሚረዱ በርካታ ሳይንሳዊ መንገዶች እንዳሉ ባለሙያዎች ይጠቁማሉ። የአእምሮን የአስተሳሰብ ብቃት ላለማጣት ምን አይነት ልምዶች ማዳበር ይቻላል ? - ከኤአይ (AI) የተገኙ ምላሾችን ወይም መረጃዎችን በቀጥታ ወስዶ ከመገልበጥ ይልቅ " ይህ መረጃ ትክክል ነው ? ምን ጎደለው ? አመክንዮአዊ ነው ? " በማለት በራስ አእምሮ መርምሮ፣ መዝኖ መጠቀም። - ማንኛውንም ስራ፣ ጽሑፍ ወይም ፕሮጀክት ከመጀመርዎ በፊት መነሻ ሀሳቦችን እና እቅዶችን በራስ አእምሮ ማመንጨት እና ማስታወሻ መያዝ። ኤአይ ስራውን ለማስጀመር ሳይሆን የተጀመረውን ስራ ለማደራጀት ወይም ለመፈተሽ ብቻ መጠቀም። - የፈጠራ እና የጥልቅ አስተሳሰብን የሚያነቃቁ እንደ መጽሐፍ ማንበብ፣ ስልታዊ ጨዋታዎችን መጫወት እና አዳዲስ ክህሎቶችን ያለ ቴክኖሎጂ እገዛ ለመማር መሞከር። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ መረጃዎች/ስራዎችን ለኤአይ ሰጥቶ ያለ ምንም ምርመራ፣ ማስተካከያና ደጋግሞ የማንበብ ጥረት በቀጥታ #በመገልበጥ አንዳንዴም እንደራስ ስራ ማስመሰል እየተለመደ መጥቷል። ይህ በጥልቀት ሳያስቡና ሳይመራመሩ በቴክኖሎጂ ላይ ሙሉ በሙሉ ጥገኛ መሆን አእምሮን የማሰብ ስራውን እንዲተው በማድረግ፣ እውነታን የመተንተን እና የጥልቅ አስተሳሰብ ብቃትን በከፍተኛ ደረጃ እየገደለው ይገኛል ፤ ሰዎች ትንሽ ስራ እንኳን ለመስራት የማይፈልጉ ስልቹና ሰነፍ እያደረጋቸውም ነው። ባለሙያዎች እንደሚመክሩት ኤአይ (AI) የሰውን ልጅ ሙሉ በሙሉ የሚተካ ሳይሆን እንደ ረዳት መሳሪያ ሆኖ ሊያገለግል የሚገባው ነው። ጥቅም የሚኖረውም የሰው ልጅ የራሱን የአስተሳሰብ ልዕልና ጠብቆ ሲቀጥል ብቻ ነው። ቲክቫህ ኢትዮጵያ #TikvahEthiopiaFamily @tikvahethiopia
4. ለረጅም ጊዜ የሚቆይ ውል" ማለት ምን ማለት ነው? አንድ የግንባታ፣ የመትከል ወይም የማምረት (እንዲሁም ከእነዚህ ጋር የተያያዘ) ሥራ፡ · ሥራው በተጀመረበት የግብር ዓመት ውስጥ ያልተጠናቀቀ እና · ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ ከ12 ወራት በላይ የሚወስድ ከሆነ በሕጉ ዘንድ "ለረጅም ጊዜ የሚቆይ ውል" ይባላል። (ማስታወሻ፡ በጽሑፉ ላይ "በ2 ወራት" ተብሎ የቀረበው የፊደል ግድፈት ሲሆን፣ በሕጉ ትክክለኛው ቁጥር 12 ወራት ነው) 5. በረጅም ጊዜ ውል "ኪሣራ ደረሰብኝ" ለማለት ምን መሟላት አለበት? በሥራው ሂደት ገቢ የሚታሰበው "የተጠናቀቀውን ሥራ በመቶኛ ለማስላት በሚያስችለው ዘዴ" (Percentage of Completion Method) ሲሆን፣ ውሉ ሲጠናቀቅ ኪሣራ ደርሷል የሚባለው ሁለቱ ቅድመ-ሁኔታዎች በአንድነት ሲሟሉ ብቻ ነው፡ · ሀ) የገቢ ግምት መብለጥ፡ በየዓመቱ በግምት ሲያዝ የነበረው ገቢ፣ ውሉ ሙሉ በሙሉ ሲጠናቀቅ በእርግጠኝነት ከተገኘው እውነተኛ ገቢ በልጦ ከተገኘ፤ እና · ለ) የልዩነቱ መጠን መብለጥ፡ ይህ በግምት እና በእውነተኛው ገቢ መካከል የታየው የብልጫ መጠን፣ ውሉ በተጠናቀቀበት ዓመት ከታየው የንግድ ሥራ ገቢ እና ወጪ ልዩነት በልጦ ከተገኘ ነው። ግብር÷ ለሀገር ክብር! ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ቴሌግራም፦ https://t.me/mormto2 ፌስቡክ፡- https://web.facebook.com/info.mto2/ ቲክቶክ፡-https://www.tiktok.com/@mto2education ኢሜል፡- mormto2taxeducation2023@gmail.com ዩትዩብ፡- https://www.youtube.com/@ministryofRevenues-MTO2 አድራሻ፡- ከሜክሲኮ ወደ ቄራ በሚወስደዉ መንገድ ገነት ሆቴል ፊት ለፊት ካሳ ግራንድ ሞል ላይ እንገኛለን
ለረጅም ጊዜ የሚቆዩ ውሎች እና ግብር እንደ ኮንስትራክሽን፣ታላላቅ የሶፍትዌር ልማት ወይም የጥገና ፕሮጀክቶች ያሉ ከ12 ወራት በላይ የሚቆዩ ውሎች ሲኖሩዎት ገቢ እና ወጪዎ ለግብር የሚሰላው እንዴት እንደሆነ ያውቃሉ? ህጉ ግብር ከፋዮች ግልጽ እና ፍትሃዊ በሆነ መንገድ ግብራቸውን እንዲያሳውቁ የሚከተሉትን ዋና ዋና ድንጋጌዎች አስቀምጧል። 1. የግብር አከፋፈል ዘዴ (Percentage of Completion Method) በተሰብሳቢና ተከፋይ (Accrual) የሂሳብ መዝገብ ለሚያዙ ቢዝነሶች፦ ገቢ እና ወጪ የሚታሰበው ፕሮጀክቱ ሙሉ በሙሉ ሲጠናቀቅ ሳይሆን፣ በየግብር ዓመቱ የተጠናቀቀውን የመቶኛ መጠን (Percentage) መሰረት በማድረግ ነው። በበጀት ዓመቱ የተጠናቀቀው የሥራ መጠን ያህሉ ገቢ በገቢነት ሲያዝ፣ በተመሳሳይ የመቶኛ ልክ የወጣው ወጪ ደግሞ በተቀናሽነት ይያዛል። 2. የስራው መጠናቀቅ በመቶኛ (%) የሚሰላው እንዴት ነው? በበጀት ዓመቱ የተጠናቀቀው የሥራ ድርሻ የሚሰላው፦ የስራው መጠናቀቅ መቶኛ (%) = በበጀት አመቱ ለውሉ የወጣው ትክክለኛ ወጪ X100 ለውሉ ይወጣል ተብሎ የተገመተው ጠቅላላ ወጪ በዚህ ስሌት መሰረት በየዓመቱ የሚኖሩ የወጪና የገቢ ለውጦች ታስበው ትክክለኛው የሥራ ድርሻ ይወሰናል። 3. በውሉ መጨረሻ ላይ ኪሳራ ካጋጠመ እና ስራ ቢቆምስ? (Carry Back Rule) ልዩ ድንጋጌ፦ አንድ ግብር ከፋይ የረጅም ጊዜ ውሉ በተጠናቀቀበት የመጨረሻ ዓመት ኪሳራ ካጋጠመው፣ ኪሳራውን ወደፊት ማሸጋገር ሳይችል ቀርቶ በኢትዮጵያ ውስጥ የንግድ ሥራውን ሙሉ በሙሉ የሚያቆም ከሆነ፤ ወደ ኋላ የመመለስ መብት (Carry Back): ያጋጠመውን ኪሳራ ወደ ኋላ በመመለስ በአምናው (ባለፈው የግብር ዓመት) ገቢ ላይ ተቀ
https://telegra.ph/%E1%8A%A89%E1%88%BA%E1%88%85-490-%E1%89%A0%E1%88%8B%E1%8B%AD-%E1%8B%A8%E1%88%BD%E1%8B%AB%E1%8C%AD-%E1%88%98%E1%88%98%E1%8B%9D%E1%8C%88%E1%89%A2%E1%8B%AB-%E1%88%98%E1%88%B3%E1%88%AA%E1%8B%AB%E1%8B%8E%E1%89%BD-%E1%8B%A8%E1%89%B5-%E1%8A%A5%E1%8A%95%E1%8B%B3%E1%88%89-%E1%8A%A5%E1%8A%95%E1%8B%B0%E1%88%9B%E1%8B%AD%E1%89%B3%E1%8B%88%E1%89%85-%E1%8B%A8%E1%8D%8C%E1%8B%B0%E1%88%AB%E1%88%8D-%E1%8B%8B%E1%8A%93-%E1%8A%A6%E1%8B%B2%E1%89%B0%E1%88%AD-%E1%8A%A0%E1%88%B5%E1%89%B3%E1%8B%88%E1%89%80-07-22
https://youtube.com/shorts/CyiCxpzQD7k?si=LdJcIYXDj7X2f0iv
без подписи
በአዋጅ ያልጸደቀው የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ 'የደሞዝ ተመን ጥናት' ከፍተኛ ቅሬታና ውዝግብ አስነሳ የግብር ባለሥልጣናት "ያስጠናነው አዲስ ጥናት አለ" በሚል ድርጅቶች ለሠራተኞቻቸው መክፈል ያለባቸውን አነስተኛ የደሞዝ ተመን በራሳቸው በመወሰን ያለፉትን ዘጠኝ ወራት የግብር ልዩነት ወደ ኋላ ተመልሰው እንዲከፍሉ እያስገደዱ መሆኑ ተሰምቷል የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ በበኩሉ እንዲህ ዓይነቱን ጥናት ያካሄደው አንዳንድ የግል ድርጅቶች የሠራተኞቻቸውን ደሞዝ ዝቅ አድርገው በማሳወቅ የደሞዝ ግብር (Payroll Tax) ያጭበረብራሉ በሚል መሆኑን ተገልጾል። Source: Meseretmedia @Ethiopianbusinessdaily
без подписи
без подписи
без подписи
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የባንኮች የብድር ገደብን ሙሉ በሙሉ አነሳ። 👉 ላኪዎች ከሚያገኙት የውጭ ምንዛሬ ግኝት ላይ ለባንኮች እንዲሸጡ የሚያስገድደው የውጭ ምንዛሬ ድርሻ ከነበረበት 50 በመቶ ወደ 30 በመቶ ዝቅ እንዲል ተደርጓል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የገንዘብ ፖሊሲ ኮሚቴ ሐምሌ 6 ቀን 2018 ዓ.ም. ባካሄደው 7ኛ ስብሰባው፣ የተለያዩ የፖሊሲ ምክረ ሃሳቦችን አቅርቦ ማጸደቁን አሳውቋል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የገንዘብ ፖሊሲ ኮሚቴ የዋጋ ንረትን ለመቆጣጠርና ወደ ነጠላ አሃዝ ለማውረድ ያለመ አዳዲስና ወሳኝ የፖሊሲ ውሳኔዎችን ማሳለፉን በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ አሳውቋል። ኮሚቴው ዓለም አቀፍ የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ በሀገር ውስጥ ምርቶች ላይ የሚያሳድረውን ጫና ከግምት ውስጥ በማስገባት፣ ጥብቅ የገንዘብ ፖሊሲ ተጠናክሮ እንዲቀጥል መወሰኑን ገልጿል። እስካሁን ባንኮች በሚሰጡት ብድር ላይ ተጥሎ የነበረው ቀጥተኛ የብድር ዕድገት ገደብ ሙሉ በሙሉ እንዲነሳ ተወስኗል። በባንኮች ላይ የብድር ገደብ ውሳኔ ተጥሎ የነበረው ኢኮኖሚው በወለድ ምጣኔ ላይ ወደተመሠረተ የገንዘብ ፖሊሲ ሥርዓት እስኪሸጋገር እንደነበር በማስታወስ ውሳኔው ግቡን መምታቱን ጠቅሷል። የብድር ገደብ መነሳቱን ጥብቅ የሆነ የፖሊሲ እርምጃ በማስፈለጉ ፣ ብሔራዊ ባንክ የፖሊሲ ወለድ ምጣኔውን በ1.0 በመቶ በማሳደግ ከነበረበት 15 በመቶ ወደ 16 በመቶ ከፍ እንዲል ወስኗል። የወጪ ንግድ ተወዳዳሪነትን ለመጨመርና በገበያው ላይ እምነት ለመገንባት፣ ላኪዎች ከሚያገኙት የውጭ ምንዛሬ ግኝት ላይ ለባንኮች እንዲሸጡ የሚደረገው የውጭ ምንዛሬ ድርሻ ከነበረበት 50 በመቶ ወደ 30 በመቶ ዝቅ እንዲል ተደርጓል። ይህም ላኪዎች ካገኙት የውጭ ምንዛሬ 70 በመቶውን እንዲጠቀሙ ዕድል ይሰጣል። ከአስመጪዎች ጋር የተያያዙ ወጪዎችን ለመቀነስና የዋጋ ንረትን ለመግታት፣ ብሔራዊ ባንክ በውጭ ምንዛሬ ግብይት ላይ የሚወስደው የ2.5 በመቶ ኮሚሽን ወደ 1.5 በመቶ እንዲቀንስ ተወስኗል። የብድር መስፋፋት በዋጋ ንረት ላይ አሉታዊ ጫና እንዳያሳድር፣ ብሔራዊ ባንክ የባንኮችን የብድርና ቁጠባ ጥምርታ (loan-to-deposit ratio) መሠረት ያደረገ የተለየ የመጠባበቂያ ተቀማጭ ሥርዓት ተግባራዊ እንደሚያደርግ አስታውቋል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ አዲስ አበባ ሃምሌ 6 ቀን 2018 ዓ/ም @tikvahethiopia
без подписи
https://youtu.be/wiIJDxfuCkA?si=l_3bGg5HIVJepJ03
без подписи
ታክስ ከፋይ ተቋማት የተወሰነባቸው የታክስ ክፍያ ላይ ቅሬታ ማሰማት ከፈለጉ ቅሬታቸውን በጠቅላይ ሚንስትር ፅ/ቤት ለሚቋቋመው ገለልተኛ የባለሙያዎች ቡድን አቅርበው መፍትሄ ያገኛሉ ተባለ። የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባከናወነው መደበኛ ስብሰባ የፌዴራል የፕላን፣ በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ፣ የፌዴራል ታክስ አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 983/2008ን ለማሻሻል የቀረበውን ረቂቅ አዋጅ በተመለከተ ያቀረበውን የውሳኔ ሐሳብ እና ማሻሻያ በማድመጥ በአብላጫ ድምጽ አጽድቆታል። ቋሚ ኮሚቴው በረቂቅ አዋጁ ላይ ካደረጋቸው ወሳኝ ማሻሻያዎች መካከል የታክስ አለመግባባቶችን የሚያስማማው "አስማሚ" (Mediator) አሰያየምን የተመለከተው ይገኝበታል፡፡ በመጀመሪያው ረቂቅ ላይ አስማሚው በታክስ ባለሥልጣኑ እንዲሰየም ተደንግጎ የነበረ ቢሆንም፣ ቋሚ ኮሚቴው "ገለልተኝነትን ለማረጋገጥ" ሲባል አስማሚው በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት እንዲሰየም በሚል ማሻሻያ አድርጎበታል፡፡ በማሻሻያው መሰረት ታክስ ከፋይ ተቋማት የተወሰነባቸው የታክስ ክፍያ ላይ ቅሬታ ማሰማት ከፈለጉ ቅሬታቸውን በጠቅላይ ሚንስትር ፅ/ቤት ለሚቋቋመው ገለልተኛ የባለሙያዎች(አስማሚ) ቡድን አቅርበው መፍትሄ የሚያገኙ ይሆናል። ሌላኛው ማሻሻያ የቀረበው አዲስ ማስረጃን ከማቅረብ ጋር ተያይዞ የሚጣልን ቅጣት የሚመለከት ነው። ታክስ ከፋዮች በታክስ አወሳሰን ወቅት ያላቀረቡትንና በኋላ ላይ በታክስ ዕዳ ላይ ከፍተኛ ለውጥ የሚያመጣ አዲስ ማስረጃ ሲያቀርቡ የሚጣልባቸው ቅጣት እንዲሻሻል ተደርጓል። በዚህም መሠረት ታክስ ከፋዩ ሊከፈል ከሚገባው የታክስ ዕዳ ላይ 10 በመቶ (ቀድሞ 20 በመቶ የነበረው) ቅጣት እንዲከፍል በማሻሻያው ተደንግጓል። በተጨማሪም ቋሚ ኮሚቴው በድርጅቶች የሚፈጸሙ የታክስ ወንጀሎችን ተጠያቂነት በተመለከተ ማብራሪያ የሚሰጥ ማሻሻያ አድርጓል። የታክስ ሕግን በመተላለፍ ወንጀል የፈጸመው ድርጅት ወይም በግለሰብ ባለቤትነት ሥር ያለ የንግድ ድርጅት በሚሆንበት ጊዜ፣ ወንጀሉ በተፈጸመበት ወቅት የነበሩ የድርጅቱ ሥራ አስኪያጅ ወይም የፋይናንስ ኃላፊ ተጠያቂ የሚሆኑበት አግባብ ተመቻችቷል። ይህ ማሻሻያ የተደረገው የታክስ ህግን በመተላለፍ ወንጀል የፈጸመ የየትኛውም ድርጅት ስራ አስኪያጅ ተጠያቂ ማድረግ ተገቢ መሆኑ ስለታመነበት እንደሆነ ተመላክቷል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ አዲስ አበባ ሰኔ 23 ቀን 2018 ዓ/ም @tikvahethiopia