tgindex
EthioTimes

EthioTimes media ☎️ +251904475404

Последний пост
15 авг.
Последнее чтение
15 авг.
Постов за неделю
24
Всего постов
61
Тип
открытый
Язык
und
В каталоге с
12 авг.
Подписчики
1 906
−5 за 3 дн.
Сутки
0
0,00%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
90
40 постов
Вовлечённость
4,7%
к подписчикам
Постов в день
3,4
всего 61
Упоминаний
0
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
126
1/48двое суток
144
1/72трое суток
155

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • 🚗✍️ ከእስክርቢቶ ወደ መኪና‼️ የዘሩባቤል 13 ቀናት አስደናቂ ጉዞ‼️ በቲክቶክ ዘሩባቤል የተባለ ወጣት የጀመረው “Pen to Car” ቻሌንጅ በርካታ ሰዎችን እያስደነቀ ይገኛል። የቻሌንጁ ሀሳብ ከአንድ እስክርቢቶ በመጀመር ፣ በየቀኑ የሚያገኘውን እቃ ወይም ዕድል በመጠቀም ደረጃ በደረጃ እያደገ በመጨረሻ ወደ መኪና ለመድረስ የሚደረግ ሙከራ ነው። 📍 የመጀመሪያው ቀን ቻሌንጁን ሲጀምር ዘሩባቤል በእጁ እስክርቢቶ ይዞ ታይቷል። በዚያ ጊዜ የነበረው ነገር ቀላል ቢሆንም ፣ የያዘው ሀሳብ ግን ትልቅ ነው፤ ከትንሽ ነገር ተነስቶ ትልቅ ነገር ለመድረስ። ይህም ብዙዎችን “በእርግጥ ከእስክርቢቶ ጀምሮ መኪና ላይ መድረስ ይችላል?” ብለው እንዲጠይቁ አድርጓል። አሁን ግን ቻሌንጁ 13ኛ ቀን ላይ ደርሷል። ከመጀመሪያው ቀን ጋር ሲነጻጸር የታየው ለውጥ በጣም የሚስብ ነው። በ13ኛው ቀን ዘሩባቤል የደረሰበት ደረጃ የ600ሺ ብር ራዉተር ማሽን እንደሆነ የማሽነሪዉ አስረካቢዎች ገልፀዋል። ይህ ማለት በ13 ቀናት ውስጥ ከአንድ እስክርቢቶ ተነስቶ እስከ ኢንጂነሪንግ ማሽነሪ ደረጃ ድረስ የሚያስደንቅ ጉዞ ማድረጉን ያሳያል። ይህ ቻሌንጅ የሚስበው በመጨረሻ ምን እንደሚያገኝ ብቻ ሳይሆን፣ በጉዞው ውስጥ የሚፈጠረው ነገር ነው። ከትንሽ ነገር ጀምሮ በየደረጃው የተሻለ ነገር ለማግኘት መሞከሩ፣ ሰዎችን ማነጋገሩ፣ አዳዲስ እድሎችን መፈለጉ እና በየቀኑ ቻሌንጁን መቀጠሉ ብዙዎችን እያስደነቀ ነው። ከእስክርቢቶ የጀመረው ይህ ሙከራ አሁን 13ኛ ቀኑ ላይ ደርሷል። ቀጣዩ ደረጃ ምን ይሆን? የመኪናው ቀንስ መቼ ይመጣል? 👀🚗 ከእስክርቢቶ ✍️ ➡️ ራዉተር ማሽን ⚙️ ➡️ መኪና 🚗 የዘሩባቤል ቻሌንጅ አሁንም ቀጥሏል። መልካም እድል! 🙏🔥 #PenToCar #Zerubabel #TikTokEthiopia #Ethiopia #Challenge #Innovation #Creativity

  • видео или голосовое, без подписи

  • በ33 ዓመቱ ያረፈው ፕሪቻርድ ኮሎን… የ11 ዓመታት አሳዛኝ የሕይወት ጉዞ‼️ የፖርቶ ሪኮው ቡጢኛ ፕሪቻርድ ኮሎን ትናንት፣ ነሐሴ 13 ቀን 2026፣ በ33 ዓመቱ ሕይወቱ አለፈ። የሞቱ ዜና የተረጋገጠውም በአባቱ ሪቻርድ ኮሎን ነው። ኮሎን በቦክስ ስፖርት ተስፋ የተጣለበት ወጣት ተፋላሚ ነበር። እ.ኤ.አ. ጥቅምት 17 ቀን 2015 ከቴሬል ዊሊያምስ ጋር ባደረገው ጨዋታ የሕይወቱን አቅጣጫ ሙሉ በሙሉ የቀየረ አሳዛኝ ክስተት ተከሰተ። በጨዋታው ወቅት ኮሎን በጭንቅላቱ ጀርባ ተደጋጋሚ ሕገወጥ ምቶች ደረሱበት። እሱም ለዳኛው ቅሬታውን ቢያቀርብም ጨዋታው ቀጠለ። በ9ኛው ዙር ከወደቀ በኋላ በመልበሻ ክፍል ውስጥ ማስመለስና ራስን መሳት አጋጠመው። ሆስፒታል ሲደርስ በአእምሮው ውስጥ Subdural Hematoma የተባለ ከባድ የደም መፍሰስ መኖሩ ተረጋገጠ፤ በአስቸኳይም የአእምሮ ቀዶ ሕክምና ተደረገለት። ከዚያ በኋላ 221 ቀናትን በኮማ ውስጥ አሳለፈ። ከኮማ ቢነቃም የደረሰበት የአእምሮ ጉዳት ከባድ ስለነበር ለቀሪ ዕድሜው በቤተሰቦቹ እና በቋሚ እንክብካቤ ላይ መኖር ነበረበት። ከዚያ አሳዛኝ የ2015 የቦክስ ጨዋታ እስከ ሞቱ ድረስ ያለውን 11 ዓመት የሚጠጋ ጊዜ ኮሎን ከከባድ የአእምሮ ጉዳት ጋር ተዋግቶ አሳለፈ። የፕሪቻርድ ኮሎን ታሪክ የአንድ ቡጢኛ ታሪክ ብቻ አይደለም። በስፖርት ውስጥ የተፋላሚዎች ደህንነት ከድል፣ ከዝና እና ከማንኛውም ውድድር በላይ እንደሆነ የሚያስታውስ ከባድ ትምህርት ነው። ከሪንግ ውስጥ ተስፋ የሰጠው ወጣት ቡጢኛ፣ ከዚያ በኋላ ለዓመታት የጤና ፈተናን በጽናት ተቋቁሞ ኖሯል። የእሱ ታሪክም በቦክስ ዓለም የማይረሳ ትውስታ ሆኖ ይቀራል። ለቤተሰቦቹ፣ ለወዳጆቹ እና ለመላው የቦክስ ማህበረሰብ መጽናናትን እንመኛለን። ነፍሱ በሰላም ትረፍ🙏 #PrichardColon #RIPPrichardColon #Boxing #PuertoRico #Ethiotimes

  • видео или голосовое, без подписи

  • አስቸኳይ‼️ የድረሱልን ጥሪ‼️ ++++++++++++++++ 👇👇👇 በቪዲዮዉ ላይ የምትመለከቷቸዉ የአንጎቫ ጌቴሴማኒ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ አንድነት ገዳም መነኮሳዉያን ሲሆኑ የሚገኙትም በሰሜን ጎንደር ሀገረ ስብከት ደባርቅ ወረዳ ሰጊ ቀበሌ ነዉ። በአሁኑ ሰአት አባቶችና እናቶች በገዳሙ የሚገኘዉን ቤተክርስቲያን ለመጨረስ፣ የሚጠለሉበትን ባዕት ለመስራት የሁላችንም እገዛ ስላስፈለጋቸዉ በመላዉ አለም ያላችሁ ወገኖቻችን የምትችሉትን አግዙን በማለት መነኮሳቶች ጥሪ አቅርበዋልና የበረከቱ ተሳታፊ እንሁን። ድጋፍ ለማድረግ የገዳሙ አካዉንት 👇👇👇 ንግድ ባንክ- 1000727191597 አቢሲኒያ ባንክ- 241335836 ለብዙዎች እንዲዳረስ እባካችሁ ሼር አድርጉት‼️

  • አዲስ አበባ ከ1.5 ሚሊዮን በላይ የትራፊክ ሕግ ጥሰት ተመዘገበ‼️ 🚨 በአዲስ አበባ በአንድ ዓመት ከ1.5 ሚሊዮን በላይ የትራፊክ ሕግ ጥሰቶች ተመዝግበዋል! በአዲስ አበባ ከተማ በተያዘው ዓመት ከ1.5 ሚሊዮን በላይ የትራፊክ ሕግ ጥሰቶች መመዝገባቸውን ዋና ኢንስፔክተር ሰለሞን አዳነ ገልጸዋል። ከተመዘገቡት ጥሰቶች መካከል ከ100 ሺህ በላይ የሚሆኑት የቀይ መብራት ምልክትን በመጣስ የተፈጸሙ ናቸው። በአሁኑ ወቅትም በከተማዋ ከ900 ሺህ በላይ ተሽከርካሪዎች እንደሚንቀሳቀሱ ተገልጿል። ዋና ኢንስፔክተሩ የትራፊክ ሕግን አለማክበር ለሰው ሕይወትና ለንብረት መጥፋት ዋነኛ መንስኤ መሆኑን አስገንዝበዋል። የቁጥጥርና የቅጣት አፈጻጸሙ መጠናከሩ ግን የትራፊክ አደጋዎችን በመቀነስ ረገድ አዎንታዊ ውጤት እያሳየ መሆኑን ጠቁመዋል። 📉 በ2017 ዓ.ም የነበረው 411 የሞት አደጋ በ2018 ዓ.ም 382 ደርሷል። በተመሳሳይ የከባድ አደጋዎች ቁጥርም ከ1,985 ወደ 1,865 በመቀነስ 120 አደጋዎች ቅናሽ አሳይቷል። 🚗 አሽከርካሪዎች በቂ ግንዛቤ በመያዝ የትራፊክ ሕጎችን በማክበር እንዲያሽከረክሩ፣ የሰው ሕይወትንና ንብረትንም ከውድመት እንዲታደጉ ጥሪ ቀርቧል። Via- Addis insider የመንገድ ላይ ጥንቃቄ የሁላችንም ኃላፊነት ነው! #AddisAbaba #Traffic #Ethiopia #ትራፊክ #አዲስአበባ #Ethiotimes

  • አስቸኳይ‼️ የድረሱልን ጥሪ‼️ ++++++++++++++++ 👇👇👇 በቪዲዮዉ ላይ የምትመለከቷቸዉ የአንጎቫ ጌቴሴማኒ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ አንድነት ገዳም መነኮሳዉያን ሲሆኑ የሚገኙትም በሰሜን ጎንደር ሀገረ ስብከት ደባርቅ ወረዳ ሰጊ ቀበሌ ነዉ። በአሁኑ ሰአት አባቶችና እናቶች በገዳሙ የሚገኘዉን ቤተክርስቲያን ለመጨረስ፣ የሚጠለሉበትን ባዕት ለመስራት የሁላችንም እገዛ ስላስፈለጋቸዉ በመላዉ አለም ያላችሁ ወገኖቻችን የምትችሉትን አግዙን በማለት መነኮሳቶች ጥሪ አቅርበዋልና የበረከቱ ተሳታፊ እንሁን። ድጋፍ ለማድረግ የገዳሙ አካዉንት 👇👇👇 ንግድ ባንክ- 1000727191597 አቢሲኒያ ባንክ- 241335836 ለብዙዎች እንዲዳረስ እባካችሁ ሼር አድርጉት‼️

  • በዝናባማዉ ሌሊት የተፈጠረው አሳዛኝ ቅጽበት… “አልፈልግም” ያሉት አባት‼️ በአዲስ አበባ ዝናብና ብርድ በተፈራረቁበት ማታ፣ እድሜያቸው ለገፋ አንድ አባት ከጎዳና ዳር ተቀምጠው ይታያሉ። በዚያ ቀዝቃዛ ሌሊት የሚያልፈውን ጊዜ በጎዳና ላይ እየተቋቋሙ ነበር። በዚህ ወቅት ቲክቶከር ዩቲናስ ከእናቷ ጋር ጎዳና ለሚኖሩ ወገኖች አዳዲስ ብርድ ልብስ እያደለች ነበር። ዩቲናስ እና እናቷ ብርድ ልብስ ይዘዉ ወደ አባቱ ቀረቡ። የያዙትን ብርድ ልብስ እንዲቀበሉና በዚያ ቀዝቃዛ ሌሊት እንዲሸፈኑበት ለማድረግ ሞከሩ። ነገር ግን እኚህ አባት በተሰበረ ስሜት፣ “አልፈልግም…” የሚል ምላሽ ሰጡ። ቲክቶከሯ በዚህ አልተወቻቸውም። ብርድ ልብሱን እንዲቀበሉ ብዙ ለመነቻቸው። በዚያ ቅዝቃዜ በጎዳና ላይ ለሚያድሩት አባት እንዲቀበሉ በተደጋጋሚ ጠየቀቻቸው። ሆኖም አባቱ ፈቃደኛ አልሆኑም። ሁኔታዉ የሚያሳዝነዉ “አልፈልግም” ማለታየዉ ብቻ ሳይሆን እርዳታ በጣም በሚያስፈልጋቸው ሁኔታ ውስጥ ሳሉ ፣ የቀረበላቸውን ብርድ ልብስ እንኳን ለመቀበል አለመፈለጋቸው ከጀርባው የተደበቀ የሕይወት ታሪክ ሊኖር እንደሚችል ብዙዎች አስተያየታቸዉን ሰጥተዋል። ምናልባት ምን እንዳሳለፉ አናውቅም። ምናልባት ለምን እርዳታ መቀበል እንደማይፈልጉም አናውቅም የሚል አስተያየቶች በብዛት ተሰጥቷል። የቲክቶከር ዩቲናስን የደግነት ተግባር ለሌሎችም አርአያ እንደሚሆን እየጠቆምን ፤ አንዳንዴ የምንሰጣቸው እቃዎች ከሚያስፈልጋቸው በላይ ከእኛ ፍቅርን እንደሚፈልጉ መዘንጋትም የለብንም። አስተያየታችሁን በጨዋነት አስቀምጡ።

  • አቡነ መቃሪዮስ ያቀረቡት ጥሪ‼️ አስቸኳይ ***** ብፁዕ አባታችን አቡነ መቃሪዮስ በሰሜን ጎንደር ደባርቅ አካባቢ የሚገኘዉ የኪኖ ኪዳነምህረት ቤተክርስቲያን ተገኝተዋል። ቤተክርስቲያኑ ለረዥም አመታት ግንባታ ላይ ቢሆንም በአሁኑ ሰአት በገንዘብ ችግር ቤተክርስቲያኑ ሙሉ በሙሉ ከመሰራት ቆሟል። ስለሆነም ቤተክርስቲያኑን ለማሰራት አባቶች በእግዚአብሔር ስም ጥሪ አቅርበዋልና የበረከቱ ተሳታፊ እንሁን። ድጋፍ ለማድረግ 👇 ንግድ ባንክ- 1000201850022 አቢሲኒያ- 255527077 አባይ- 2361119451656012

  • “ዓላማዬ ሀብታም መሆን እንጂ የሀብታም ሚስት መሆን አይደለም” — አርቲስት ቬሮኒካ አዳነ አርቲስት ቬሮኒካ አዳነ በቅርቡ የሰጠችው አስተያየት አነጋጋሪ ሆኖ ቀጥሏል። “ዓላማዬ ሀብታም መሆን እንጂ የሀብታም ሚስት መሆን አይደለም” ያለችው አርቲስቷ፣ ግቧ በራሷ ጥረትና ልፋት የፋይናንስ ነፃነትን ማሳካት መሆኑን ገልጻለች። ከሀብታም ሰው ጋር በመጠጋት ወይም በመጋባት ሀብት ማፍራት እንደማትፈልግ የገለጸችው ቬሮኒካ፣ በሙያዋ በመስራት ሀብት መፍጠር እንደምትፈልግ ተናግራለች። “በራሴ ጥረትና ልፋት የፋይናንስ ነፃነት ማሳካት ነው ግቤ” ስትልም አቋሟን አስረድታለች። አስተያየቷ በማኅበራዊ ሚዲያ ውይይት እያስነሳ ሲሆን፣ የሴቶች የፋይናንስ ነፃነት፣ የራስ ጥረት እና ትዳር ከሀብት ጋር ስላለው ግንኙነት የተለያዩ ሀሳቦች እየተሰነዘሩ ነው። የአርቲስቷን አስተያየት እንዴት ተመለከታችሁት? አስተያየታችሁን በጨዋነት አስቀምጡ።

  • видео или голосовое, без подписи

  • አቡነ መቃሪዮስ ያቀረቡት ጥሪ‼️ አስቸኳይ ***** ብፁዕ አባታችን አቡነ መቃሪዮስ በሰሜን ጎንደር ደባርቅ አካባቢ የሚገኘዉ የኪኖ ኪዳነምህረት ቤተክርስቲያን ተገኝተዋል። ቤተክርስቲያኑ ለረዥም አመታት ግንባታ ላይ ቢሆንም በአሁኑ ሰአት በገንዘብ ችግር ቤተክርስቲያኑ ሙሉ በሙሉ ከመሰራት ቆሟል። ስለሆነም ቤተክርስቲያኑን ለማሰራት አባቶች በእግዚአብሔር ስም ጥሪ አቅርበዋልና የበረከቱ ተሳታፊ እንሁን። ድጋፍ ለማድረግ 👇 ንግድ ባንክ- 1000201850022 አቢሲኒያ- 255527077 አባይ- 2361119451656012

  • አስቸኳይ‼️ ታላቅ የበረከት ጥሪ‼️ ይህ ቤተክርስቲያን ጃናሞራ ገጠር ዉስጥ የሚገኝ ጥንታዊ የመስቀለ እየሱስ ቤተክርስቲያን ነዉ። ቤተክርስቲያኑ ከተጀመረ 8 አመታትን አስቆጥሯል። በአሁኑ ሰአት ቤተክርስቲያኑ በገንዘብ እጥረት ሙሉ በሙሉ ከመሰራት የቆመ ስለሆነ እገዛችን ስላስፈለጋቸዉ የበረከቱ ተሳታፊ እንድንሆን በእግዚአብሔር ስም ጥሪ እናቀርባለን። ድጋፍ ለማድረግ የቤተክርስቲያኑ አካዉንት 👇👇👇 ንግድ ባንክ- 1000091602311 ስልክ- 0918055897 ወይም 0957827972 ለብዙዎች እንዲዳረስ እባካችሁ ሼር አድርጉት‼️

  • “ባጫ ዳንሰኛ ነው የሚለውን ትርክት የፈጠረው ተስፋዬ ገብረአብ ነው" ጄነራል ባጫ ደበሌ Ethiotimes | Ethiopia በኬንያ የኢትዮጵያ ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር የሆኑት ጄነራል ባጫ ደበሌ፣ “ባጫ ዳንሰኛ ነው” የሚለው ትርክት ያለማስረጃ የተፈጠረ ሲሆን ይህን ትርክት ያስተዋወቀው ሟቹ ደራሲ ተስፋዬ ገብረአብ እንደሆነ ገልፀዋል። ጄነራል ባጫ ይህን የተናገሩት ከአዲስ ኮምፓስ ሚዲያ ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ ነው። በቃለምልልሱ በግላቸው ስለሚነሱ ትችቶች ምላሽ ሰጥተዋል። ጄነራሉ ምርኮኛም ሆነ ዳንሰኛ እንዳልሆኑ ገልጸው፣ በተለይም “ባጫ ዳንሰኛ ነው” የሚለው አባባል ያለማስረጃ የተፈጠረ ትርክት ነው ብለዋል። “ጄነራልነት የሰጠኝ ብሔራዊ ቲያትር አይደለም፤ የማረከኝ አካል ካለም ይውጣና ይናገር” በማለትም ጄ/ሉ ክሱን አጣጥለዉታል።

  • видео или голосовое, без подписи

  • የብዙዎችን ልብ የሰበረዉ የዕለቱ ምስል‼️ ሰላም ለሀገራችን💚💛❤

  • የእግር ኳሱ ኮከብ ክርስቲያኖ ሮናልዶ እና የፍቅር ጓደኛዉ ጆርጂና ሮድሪጌዝ ከአስር አመታት የፍቅር ጊዜያት በኋላ በዛሬው ዕለት ጋብቻ ፈፅመዋል።

  • የአመታት አደጋውን ያስቆመችዉ ቅ/አርሴማ‼️ +++++++++++++++++++++++++++ በቪዲዮው የሚታዩት ታላላቅ ቀሳዉስት ድንቅ ምስክርነት ይዘዉልን መጥተዋል። አባቶቹ የቆሙበት ቦታ በሰ/ጎንደር አገረ ስብከት ደባርቅ ወረዳ ድብ ባህር ቀበሌ በምትገኘዉ ቅ/አርሴማ ቤተክርስቲያን ነዉ። ቤተክርስቲያኗ ከተመሰረተች ጀምሮ በተደጋጋሚ ይከሰት የነበሩ አደጋዎች በተለይም የመኪና አደጋ እንደቆመና በፀበሉም ብዙ ምዕመናን ከደዌያቸዉ እንደተፈወሱ አባቶች ምስክርነታቸዉን ሰጥተዋል። ነገር ግን ከአመታት በፊት ቤተክርስቲያኗን ማነፅ የተጀመረ ቢሆንም በገንዘብ ችግር ምክንያት ህንጻ ቤተክርስቲያኑ ከመታነፅ ስለቆመ በመላው አለም ያላችሁ ወገኖቻችን የምትችሉትን አግዙ  በማለት አባቶች ጥሪ አቅርበዋልና ከበረከቱ እንሳተፍ በማለት በእግዚአብሔር ስም እንጠይቃችኋለን። ድጋፍ ለማድረግ የቤተክርስቲያኑ አካዉንት ንግድ ባንክ- 1000689606052 ስልክ- 0928436088/ 0918259752 ወይም 0927630425 👉 ለብዙዎች እንዲዳረስ እባካችሁ ሼር አድርጉት‼️

  • የተጀመረዉን ቤተክርስቲያን እንጨርስ‼️ *** ይህ የልደታ ለማርያም አንድነት ገዳም በጎንደር በጎንደር ጃናሞራ የሚገኝ ሲሆን   ቤተክርስቲያኗ በመሬት ናዳ ምክንያት ልትፈርስ ስለሆነ ከእንደገና እየተሰራች ትገኛለች። ስለሆነም ቤተክርስቲያኒቷን ለማነፅ በመላዉ አለም ያላችሁ ወገኖቻችን የአቅማችሁን አግዙን በማለት የበረከቱ ተሳታፊ እንሆን ዘንድ መነኮሳቱ የአደራ ጥሪ አቅርበዋል። ድጋፍ ለማድረግ👇👇👇 ንግድ ባንክ- 1000423896047 ☎️ 0992106771/  0909796625/ 0928436088 ለብዙዎች እንዲዳረስ እባካችሁ ሼር አድርጉት‼️

  • “አዲስ አበባን እንደ እንግዳ ካልሆነ ከዚህ በኋላ ለመኖር አልመጣም” — ዮናስ መኳንንት ከከተማው ጫጫታ ወደ ጎርጎራ ጸጥታ፤ ከሥነ ጥበብ ወደ ግብርና እና ማኅበረሰብ አገልግሎት‼️ የሥዕልና የቅርጻ ቅርጽ ባለሙያው ዮናስ መኳንንት በተወለደባትና ያደገባት አዲስ አበባ ሕይወቱን ትቶ ወደ ገጠር ከገባ ወዲህ የሕይወት አቅጣጫውን ቀይሯል። ዮናስ ከከተማ ሕይወት ወጥቶ በጣና ሐይቅ ዳር ወደምትገኘው ጎርጎራ የመግባቱን ውሳኔ ያደረገው፣ በአዲስ አበባ በተጀመረው የኮሪደር ልማት የቤተሰቡ መኖሪያ ቤት ከፈረሰ በኋላ ነው ይላል ዮናስ። ዋና ዋና መንገዶችን በማስዋብ፣ የእግረኛ መንገድን በማስፋት እንዲሁም የመዝናኛ ቦታዎችን በመገንባት ላይ በሚያተኩረው በዚህ ፕሮጀክት ሳቢያ፣ "ከቤተሰቤ ጋር የምኖርበት ቤት ፈረሰ" በማለትም ቃል በቃል ክስተቱን ገልጾታል። ይህ አጋጣሚ ግን ዮናስ ለረጅም ጊዜ አስቦበት የነበረውን ከከተማ ወጥቶ በገጠር የመኖር ፍላጎት እውን እንዲያደርግ መንገድ ከፈተለት። “በእጄ ላይ ሁለት ምርጫዎች ነበሩኝ፤ ገጠር መግባት ወይም ከአገር መውጣት” ያለው ዮናስ፣ ከአገር መውጣትን ሳይመርጥ በኢትዮጵያ መቆየትን መርጧል። ከኬንያና ኡጋንዳ የሥነ ጥበብ ጋለሪዎች ጋር የሥራ ግንኙነት እንዳለውና ወደእነሱ እንዲሄድ ግብዣ ቢቀርብለትም፣ አገሩን መተው እንደማይፈልግ ገልጿል። “አገር ደስ ሲልህና ሲደላህ ብቻ የምትኖርበት አይደለም። በክፉ ሰዓት ነው ለአገርህ መገኘት ያለብህ” በማለት ውሳኔውን አስረድቷል። ከአዲስ አበባ ወደ ጎርጎራ ጥር 6 ቀን 2017 ዓ.ም. ዮናስ ከአዲስ አበባ ወደ ጎንደር ጉዞ ጀመረ። በወቅቱ በአማራ ክልል የነበረው የጸጥታ ሁኔታ ጉዞው ሦስት ቀናት እንዲፈጅ አድርጎታል። ከብዙ ዕቃዎች ይልቅ ለሥዕል ሥራው የሚያስፈልጉትን ግብዓቶች፣ አልጋ እና ከዛሬ ድረስ አብረውት ያሉትን ውሾቹን ይዞ ተጓዘ። ጎርጎራ ከደረሰ በኋላም ለ11 ዓመታት ተዘግቶ የቆየውን የአያቶቹን ቤት ከፍቶ መኖር ጀመረ። ከከተማው ጫጫታ ተለይቶ በገጠር ጸጥታ ውስጥ መኖር የአእምሮ እረፍት እንደሰጠው ይናገራል። “እዚህ ከመጣሁ ትልቅ እረፍት ነው የሚሰማኝ። የመኪና ድምጽ የለም፤ የምትሰማው የእንስሳት ድምጽ ብቻ ነው” ሲል ገልጿል። ከሥነ ጥበብ ወደ ግብርና ዮናስ በገጠር መኖር ከጀመረ በኋላ ከሥነ ጥበብ ሥራው በተጨማሪ የግብርና ሕይወትንም መሞከር ጀመረ። ዶሮ፣ በግ፣ ፍየል፣ አህያ፣ ፈረስና ከብት ጨምሮ የተለያዩ የቤት እንስሳትን ማርባት ጀመረ። ከ20 በላይ በጎችና ፍየሎች ካሳደገ በኋላ በተከሰተ ወረርሽኝ ሁሉንም በአንድ ሳምንት ማጣቱን ይናገራል። ከ50 ዶሮዎችም ሦስት ብቻ እንደተረፉት ገልጿል። ይህ ልምድ የገበሬን ሕይወት እና ተደጋጋሚ ፈተናዎቹን በተሻለ ሁኔታ እንዲረዳ እንዳደረገው ይገልጻል። ከቲክቶክ ወዳጆች ጋር ለማኅበረሰቡ ዮናስ በገጠር ሲኖር የገጠመውን ብቸኝነት ለመቋቋም ማኅበራዊ ሚዲያ አስፈላጊ ድጋፍ ሆኖለታል። የዕለት ተዕለት ኑሮውን፣ የገጠር ሕይወቱን እና አዲሱን አካባቢ ለመልመድ የሚያደርገውን ጥረት በማኅበራዊ ሚዲያ ማጋራት ከጀመረ በኋላ በርካታ ወዳጆችን አፍርቷል። ከእነዚህ ወዳጆቹ ጋር በመተባበርም ከ500 ሺህ ብር በላይ የሚያወጣ የመለዋወጫ እቃ በመግዛት የአካባቢውን የመጠጥ ውኃ ፓምፕ እንዲጠገን አድርገዋል። ለተማሪዎች ደብተርና የንጽህና መጠበቂያዎችን ከመለገስ ባሻገር፣ በአሁኑ ወቅት የአቅመ ደካማ ሰዎችን ቤቶች በማደስ ላይ መሆናቸውን ይገልጻል። ከ50 በላይ የማኅበራዊ ሚዲያ ወዳጆቹም ባለፈው ዓመት ጎርጎራ ድረስ በመሄድ ቤቱ ድረስ አግኝተውታል። በሠራው ጀልባ ጣና ሐይቅ ላይ ተዘዋውረው የገጠር ሕይወቱንም ተካፍለዋል። ወደ አዲስ አበባ መመለስ አልፈልግም ዮናስ አሁን ወደ አዲስ አበባ ተመልሶ የመኖር ዕቅድ እንደሌለው ይናገራል። “አዲስ አበባን እንደ እንግዳ ካልሆነ ከዚህ በኋላ ለመኖር የምመጣ አይመስለኝም። ምን አለኝ? ከዜሮ ለመጀመር ካልሆነ በስተቀር ምን ቀርቶኛል?” ሲል ይጠይቃል። በጎርጎራ የሚጠብቀው ቀጣይ ትልቅ ዕቅድ ደግሞ በጣና ሐይቅ ዳር ግዙፍ የሥነ ጥበብ ስቱዲዮ መክፈት፣ ሌሎችን ማስተማር እና ጎርጎራን ሰፊ የቱሪዝም መዳረሻ ለማድረግ መሥራት ነው። የዮናስ ታሪክ ከከተማ ወደ ገጠር የተደረገ የአኗኗር ለውጥ ብቻ ሳይሆን፣ በአገሩ መቆየትን፣ ከአካባቢው ማኅበረሰብ ጋር መሥራትን እና ሥነ ጥበብን ከገጠር ሕይወት ጋር ለማጣመር የሚደረግ የግል ጥረት ሆኗል። ምንጭ፦ ቢቢሲ

EthioTimes — tgindex