- Последний пост
- 14 авг.
- Последнее чтение
- 15 авг.
- Постов за неделю
- 16
- Всего постов
- 23
- Тип
- открытый
- Язык
- und
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 36
- 1/48двое суток
- 41
- 1/72трое суток
- 44
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
በአንዲት እናት ጓዳ ===== > ተቃቅፈው ባደጉ _ ከመደቡ ግርጌ ====== > ቦጠሊቃ ፈላ ሁለት ወንድሞችን ===== > ለዛውም መላጣ_ ልባቸውን ወስዶ በሚዶ ሊያጣላ እኔን እንደገባኝ ____! ወደፊት ለመሄድ ===== > ሀሳብ ነው ጠላቱ ==== > ሰው ለራሱ መንገድ ክብሪትም _! ጫፉ ላይ በያዘው ===== > ራሱን ጭሮ ነው ===== > ገላውን የሚያነድ የንጉስ ልጅ ላባ ====== > የደሃ ልጅ ሟቹ ======= > ደንጋይ ነው ትራሱ አትስማው ወንድሜ____ ===== > ከድሮም ጠብ _መንጃ === > ራሱ ገሎ ነው የሚጮህ ለራሱ ደገኛው ነኝ @eyorkis
📖📖 ስንክሳር ዘወርኀ ነሐሴ ፯/7 🤩በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን። 📌 በዚች ቀን የመላእክት አለቃ ቅዱስ ገብርኤል ወደ ጻድቁ ኢያቄም ተልኮ የእመቤታችን የድንግል ማርያምን ፅንስ ያበሠረበትና ቅድስት ሐና የፀነሰችበት ቀን ነው። እንዲሁም የሐዋርያት አለቃ ቅዱስ ጴጥሮስ "አንተ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ነህ" ብሎ የመሰከረበት መታሰቢያ በዓል ነው። 📌ጻድቁ ኢያቄምና ባለቤቱ ቅድስት ሐና ልጅ አጥተው በስደትና በጽኑ ጸሎት ይኖሩ ነበር፤ ልጅ ቢሰጣቸውም ለእግዚአብሔር ቤት አገልጋይ ሊያደርጉ ተሳሉ። ቅዱስ ገብርኤልም ለኢያቄም ተገልጦ የዓለም ሁሉ መመኪያ የምትሆን፣ ለዓለም ድኅነትን የምታመጣ ሴት ልጅ እንደሚያገኙ አበሠረው። ቅድስት ሐናም በዚች ቀን አምላክን የወለደች እመቤታችንን ፀነሰች። 📌በዚችም ቀን ጌታችን በፊልጶስ ቂሣርያ ደቀ መዛሙርቱን "ሰዎች የሰውን ልጅ ማን ይሉታል?" ብሎ በጠየቃቸው ጊዜ፣ ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ "አንተ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ክርስቶስ ነህ" ብሎ መሰከረ። 📌ጌታችንም የቅዱስ ጴጥሮስን ሃይማኖት አድንቆ የመንግሥተ ሰማያትን ቁልፍ ሰጠው፤ የሐዋርያት ሁሉ አለቃና የቤተ ክርስቲያን መሠረት አደረገው። ከእርሱም የክህነትና የሹመት ሁሉ መሠረት ተተከለ። "ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በከበሩ ኢያቄምና ሐና፣ በሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስም ጸሎት ይማረን፤ በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።" ምንጭ፦📖📖#መጽሐፈ_ስንክሳር "ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን" (የቅዱሳንን ዜና/ታሪክ እንድናገር ፍቅር ያስገድደኛል) ✍️አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ (መጽሐፈ ምሥጢር📖) 📌የእመቤታችንን የፅንሷን ብስራትና የታላቁን ሐዋርያ የቅዱስ ጴጥሮስን የእምነት ምስክርነት ታሪክ Share በማድረግ የበረከቱ ተካፋይ ይሁኑ❕
видео или голосовое, без подписи
እምባ እምባ ይለኛል ግና እምባ ከወዴት ይገኛል ? እምባው ደርቆ ቀረጢቱ ሳግ ሳግ ይለዋል ሁሉም በየ ቤቱ ሞት ሞትም ይለኛል ግና ሞት ከወዴት ይገኛል ያ የመጨረሻው ዘመን ፍካሬው ደርሶ ትንቢቱ ሞት ባይገኝም ሞት ሞት ይመኛል ሰው ሁሉ በቤቱ ደገኛው ነኝ 50 /50 የተሰነደ @eyorkis
" አትጥፊብኝ ጀንበር ! " ያለ ጭን መጋዥያ ====> __ መንፈሴ ሲጋልብ ትቀርን መች ያውቃል ====> __ ናፍቆት ያሰረው ልብ በዳዘዘው ሰማይ ====> ___ ጉም ባፈነው ምድር እባክሽ ....! ሰው እጠብቃለሁ ====> __ አትጥፊብኝ ጀንበር ደገኛው ነኝ @eyorkis
ከምድያም ምድር __ ===== > አብርሃም በርስቱ መስጠቱን በመንጠቅ _ ====== > ተተክቷል ቤቱ ሆድ አምላኪው በዝቶ ___ ====== > ሰውን ለኩነኔ እንዴት ያስነቅፋል __ ====== > ክርስቲያን መሆኔ ከዮቶር ዙፋን ስር ___ ====== > ፍትህ ሲደላደል ምነው ዛሬስ ሆነ ___ ====== > አማራነት ወንጀል ! ደገኛው ነኝ @eyorkis
"ቁራም አለቀሰ ?" ጥዋት በለስ በላሁ _ ===== > አንድ ፍሬ ወድቆ ለጦር ሳሾል መሸ _ ===== ወይራ ዘይት ደርቆ እርግቧም በረረች _ ===== > ሰላሟን ፍለጋ ሶሪትም ተጫጨች _ ===== > ከገደል ማሜት ጋ ዋ'ኔስ እና ገዴ __ ===== > ሟች በዝቶ ደረሰ የዘንድሮው ቀንስ _ ===== > ቁራም አስለቀሰ ! ( 😭😭 ጥምብ በዝቶበት ቁራ ካለቀሰ ! ) ደገኛው ነኝ @eyorkis
видео или голосовое, без подписи
የእርዳታ ጥሪ እንድረስላት 🙏 የምትመለከቱዋት ወጣት ታዳጊ ኤልሮኢ ቅዱስ ትባላለች በአጥንት ካንሰርን ህክምና ላይ ትገኛለች በሽታው ከታወቀ አንድ አመት ሆኗታል በበሽታው ምክንያትም የግራ እጇ ሙሉ በሙሉ እንዲወገድ ተደርጓል ሆኖም ግን ኤልሮይ ተስፋ ሳትቆርጥ ህክምናዋን እየተከታተለች ነው አሁን ግን በሽታው ወደ ሳንባዋ በመሠራጨቱ የመተንፈስ ችግር ስላጋጠማት በአሁን ሰአት በአዲስ አበባ Heal Venture Medical and Surgical Center በ ICU ትገኛለች ሆኖም ግን በአሁን ሰአት ላይ የሆስፒታሉ ወጪ በቀን ከ50.000ብር ነው ከቤተሰብ ከአቅም በላይ ስለሆነ እናትም አባትም አጠገቧ ስለሌሉ ጓደኞቿ እያሳከሟት ነው.. እኛ ከጎኗ እንሁን 🥹❤️ CBE - 1000487578828 TeleBirr - 0911179293 Awash Bank - 013471629151800 ሁሉም አካውንት ስም - Rahel Aregay እህታችን ትፈልገናለች እንድረስላት 🙏
"ሰውን ስትረዳው ጎሳውን፣ ጾታውን፣ ሃይማኖቱን ብለህ አትርዳው ስለ ክርስቶስ ስም ብለህ እርዳው።" {ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ} ምሕረቱ እና ቸርነቱን አብዝቶ ዛሬን እንድናይ የረዳን አምላክ ለዘለዓለም የተመሰገነ ይሁን እንደምን አመሻችሁ? 🙏
እግዚአብሔር በምትወዱት አይፈትናቹህ…🥀
видео или голосовое, без подписи
መልዕክተ ዮሐንስ ____ ሀ ግዕዝ አቡጊዳ ሰላም ካልሰበከ ___ ካህን ጦር አይነዳ ተመልሰሽ ግቢ ___ ተማሪ ቤት ቅኔ ከወንዶቹ ጋራ ___ መሄዴ ነው እኔ 50 / 50 የተሰነደ ደገኛው ነኝ @eyorkis
ስቶድቅ ያላነሳህ __ ===== > ታመህ ያልጠየቀህ ===== > ሰው በሰው ጨክኖ አትፍረድ ሲቀብርህ ===== > አፈር ማልበስማ ===== > ቋሚ ስራው ሆኖ ደገኛው ነኝ @eyorkis
ክረምት በዶፍ ዝናብ =====! __ በበጋው አቧራ __ ጠምዳ በአሳረሰች በባዶ እግሯ ሄዳ ======! __ አገር ባለበሰች ___ ህዝብ ባጎረሰች ዘር ቀለሟን ሳትመርጥ ====! ___ አላፊ አግዳሚውን _ አብልታ ከራሷ ፍርደ ገምድል ዳኛ ==== ! ___ እንዴት ለዚች እናት ___ጥይት ይሁን መልሷ ?? ( እናት ካዘነበት መብረቅ የመታው ይሻላል ! 😭😭) ደገኛው ነኝ @eyorkis
አብጄ ከሆነ ወስደሽ አስጠምቂኝ፥ አብደሽ ከሆነ ግን፣ በስተርጅና አያምርም ሀገሬ አታስቂኝ፥😁
"ፍቅር የሞተበት ልብ ውስጥ ፍቅርን የሚሸሽ አእምሮ ይፈጠራል💔" ሰናይ ቀን❤️ @ezreal_1
አንተ ብቻ አይደለህም ! በርታ ! ጥንቸሎቹ በቀበሮዎች፣ በተኩላዎች፣ በአዳኞችና በሌሎች እንስሳት ሁልጊዜ ስለሚታደኑ ሕይወት ሰለቻቸው። አንዱ ጥንቸል "እንዲህ በፍርሃት ከመኖር አንድ ጊዜ ሁላችንም ወደ ሐይቅ ዘለን እንሞት!" ብሎ ሐሳብ አቀረበ። ተስማሙ። ታድያ ሁሉም ወደ ሐይቁ ሲሮጡ፣ በዳርቻው የነበሩ እንቁራሪቶች የጥንቸሎቹን ድምፅ ሰምተው በፍርሃት ወደ ውሃው ዘለው ተሸሸጉ። ይህን የተመለከተው አንድ ጥንቸል እንዲህ አለ። "ተመልከቱ! ከእኛ የበለጠ ፈሪ ፍጥረታት አሉ። ሕይወታችን ያን ያህል መጥፎ አይደለም።" ከዚያም ሐሳባቸውን ቀይረው ተስፋ አድርገው ሕይወታቸውን ቀጠሉ። ራስህን ብቻ መከራ ያለብህ እንዳትመስል፤ ሌሎችም የራሳቸው ችግርና ፍርሃት አላቸው። እናም መጠንከር፣ መላ መፈለግ እንጂ 'ብንሄድ ይሻላል' ብሎ ራስን ለከፋ ጉዳት ማሳለፍ አስፈላጊ አይደለም። ከማዕደ ጥበብ @eyorkis
" በዛ ላይ እንደ አይሁዶች በስብሰባ ምክርን አትምከሩ ። አትፍረድ => ይፈረድብሀል ። አትምከር => ይመከርብሀል ። አይደለ የሚባለው ? ' አትዋል ይዋሉ አትምከር ይምከሩ በቆፈሩት ጉድጓድ ሳይገቡም አይቀሩ ' አለ የአገር ሰው ። ብሎ ብድግ አለ ። አነጋግሩ ግራ አጋብቷቸዋል ። ሊኮንናቸው የተላከ መስሏቸዋል ። እጃቸውን በአፋቸው ላን እንደ ጫኑ በአይናቸው ሸኙት ። ትንሽ እንደተራመደ አንድ የጠመጠመ አርሶ ፈረስ ካህን ባለቤቱን አስከትሎ ይመጣል ። ከእግር እስከራሱ ቅሽር ብሏል ። ሚስቱም በፍታል ቀሚስ እና በፍታል ጃኖ ተሽሞንሙናለች ። ብቻ በእግሯ ጎማ ጫማ አድርጋ አወዘጋገበችን እንጅ ። " አባቴ ስለ ፈጣሪ ? " ሲል አንድ ህፃን ጠየቀው ። " ፈጣሪ ይስጥህ ?" አለው ካህኑ አንገቱን ከፍ ዝቅ እያደረገ ። " ፈጣሪ ሰማይ ቤት ሄጀ ነው የሚሰጠኝ ። ደግሞ ፈጣሪ ይነግዳል ያርሳል እናንተ ያልሳጣችሁኝን ወደ እሱ የምትመሩኝ ? " ሲል ወጣቱ ሰማ እና ልቡ ቀጥ አለች ። " አንተ ልጅ ። ፈጣሪ ይስጥህ አልሁህ አይደለ ? ነው በጉልበት ነው ? " አለ ካህኑ ። " እኔ የማውቀው ፈጣሪ አንተ ነህ ። በአጠገቤ ያለኸው የፈጣሪ መልክተኛ አንተ ነህ ። " ብሎ ዝም አለ ። ወጣቱም መልስ አልሰጠም ። ጀሮውን ጣል አድርጎ አለፍ አለ ። " ሆሆሆ እንዴት ያለ ልጅ ነው ! አደረስን ከተባልህ ዘወር ነው አቡሽ ! " ብላ በባሏ አነጋገር እና ክብር ስትመፃደቅ አያት ልጁ ። " ሀሀሀሀ የቄስ ሚስት እግዚአብሄር አጎቱ ይመስላታል አሉ ' " አለና በረጅሙ ሳቀ ። ወጣቱ አረማምዱን እየቆጠረ ወደ ፊት ተጓዘ ። ካህኑም ልጁን እየዞረ እያየ መንገዱን ቀጠለ ። " እንዴት ያለ ዘመን ነው ? የሰጭ ሆድ ሳያስብ የበይ ሆድ ጮኸ ! አሉ እማሆይ ቁቁቁ " እያኩተመተመች ባሏን ተከትላ ሄደች ። ደገኛው ነኝ @eyorkis
" መንገደኛው ጠቢብ " ( በቡትቶ የተሸፈነ ሀሳብ ) ቁጥር _ 1 ሁለት ሰዎች አግዳሚ ወንበር ላይ ተቀምጠው አፍ ለአፍ ገጥመው እንደ ወፍ ያወራሉ ። " መቸም ሰው የማይሰማው ሚስጢር ቢሆን እንጅ እንደዚህ የነፋስ መሿለኪያ ሳያስቀሩ ተቀራርበው የሚያወሩ ! " እያለ በልቡ ቀረብ አላቸው ወጣቱ ። ሁለቱም ተመሣሣይ የእድሜ እርከን ላይ ያሉ ይመስላሉ ። መቸስ " ሰው ኑሮውን ይመስላል ! " ቢሆንም ተረቱ አንዱ ፊቱ ሞላ ወዙም ጠለል ያለ ነው ። ሌላኛው ደግሞ የፊቱ ቆዳ መሰብሰቡ ብቻ ሳይሆን የተበጣጠሰ እና የተመነጫጨረ ፀጉር ጦጣ የከረመበት ገብስ አስመስሎታል ። " ኖ ኖር !" አሉት ለመቀመጥ ያለውን ፍላጎት ቀድመው ተረድተው ። " በግዜር ! ለነገሩ ባትሉኝሽ መኖሬን አልተወው ። " አለ በልቡ እያጉረመረመ ። ወዙ ጠለል ። ፊቱ ሞላ ያለው ቀና ፥ ሰረቅ እያደረገ ያየዋል ። የሚፈራው አሊያ የሚጠራጠረው ነገር እንዳለ አኳኃኑ ያሳብቅበታል ። " ምን ፈልጎ ነው አይኑን እኔ ላይ የሚወረወር ። ሌባ ነው መሰል ። " ፈስ ያለበት ዝላይ አይችል " ። " መቀመጫው ላይ ቁስል ያለበት እንደ ልቡ አይቀመጥ እንደልቡ አይራመድ ! " አይደለ የሚባል ። " አለ በውስጡ ። " ተው ባክህ ይኸ ምናባቱ ወንጀል ይሰራል ? እያየኸው አንድ ሐሙስ የቀረው መስሎ " አለ ሌላኛው ሀሳቡ ። " የለበሰውን ጃኬት አይተኸዋል ? " " አዎ ! 20 ሽ ቢሆን ነው ! " " ያጠለቀውን ጫማስ ? " " እሱም 10 ሽ ቢሆን ነው ! " " የእጅ ሰአትስ ? " " እሱም 10 ሽ ቢሆን ነው " " አይደለ ? 20 ሽ ይሆናል አይገርምህም ? " " እሽ በቃ ይሁን ! " " የያዘው ስልክስ ? " " እሱ እንኳን 50 ሽ ይሆናል ። " "ፊቱን የተዋበት ቅባትስ ? " "ለእሱ አጠቃላይ 5 ሽ አውጦ ቢሆን ነው ። " " ሱሪው ፥ ቲሸርቱ ፥ ካልሲ እና ፓንቱ እስካርፑን ጨምሮ 15 ሽ ቢሆን ነው ።" " አጠቃላይ 120 ሽ ሰውየው ተሸክሟል ማለት ነው ። ይህ በአይናችን ያየነው ነው ። ወርቅ ጥርስ ያስተክል የዝሆን ጥርስ ? አሊያ የዳይኖሰር ጥርስ ይሁን የአልማዝ ጥርስ የምናውቀው የለም ? ፊቱንም ሰርጀሪ ያሰራ አያሰራ መረጃ የለንም ? " " ይኸ ሁሉ ምን ለማለት ፈልገህ ነው ? " ግማሽ ልቦናው ጠየቀው ። " ምንም ። ብቻ ሰውየው ሀብታም ነው ። ' ከእያንዳንዱ ሀብት ጀርባ ደግሞ ወንጀል አለ ። ' ሰውየውን ሳየው ቀማኛ እና ማጅራት መች መስሎ ይታየኛል ። " አለው ። " አንተ ደግሞ በሰበብ አስባቡ ትጠራጠራለህ ። " " ጅሌ ' እንደ እባብ ልባም እንደ እርግብ የዋህ ሁን ' ማለት ምን ማለት ነው ? ሁሉንም ሰዎችን ውደድ ግን ሁሉንም አትመን ማለት እኮ ነው ። እምነትህን በፈጣሪ አድርግ መውደድህን ግን ከሰው ላይ አታንሳ ማለት እኮ ነው ። ፂፂ " እያለ በራሱ ላይ አሾፈበት ። " ምነው ወንድም ሀሳብ የገባህ ትመስላለህ ? " ሲለው ፊቱ ወዛ ያለው ከሀሳቡ ብንን አለ ። " አይ ደና ነኝ ። ድክም ብሎኝ ነው ። " አለ ወጣቱ ። " እሁሁሁ ባክህ እኔ ጭንቅ ብሎኛል " አለው ከሳ ያለው ። " ምን አስጨነቀህ ። አልሰጥም ካለ ጠቁሞ ማስያዝ ነው ? " አለ ሌላኛው ጓደኛው ። ወጣቱ በዚህ ጊዜ ልቡ ፈጠን ብላ መምታት ጀመረች ። የሆነ ነገር ልቡ ተጠራጠረ ። ፍራት ቢጤ ይንጠው ጀመር ። " እንዴት አድርገን እንጠቁማለን ?" " መንገድ አይጠፋም ። ማኖ አስነክተን እናስቀፈድደዋለን ። " አለ ጓደኛው ። በሴራ የተጠነሰሰ እንደሆነ ዛቻ ያዘለ ንግግሩ ያስታውቃል ። " ይቅርታ ! ምን አድርጓችሁ ነው ? " ሲል በድፍረት ጠየቀ ወጣቱ ። " ገንዘብ ወስዶ ከልክሎን ! " አለ ፊቱ ጭምድድ ፀጉሩ ልክስክስ ያለው ሽማግሌ ። " እኛኮ እዚህ ምድር ላይ የእኔ የምንለው ነገር የለንም ። " አለ አንገቱን እንደ ደፋ ። " ማለት ? ለፍቸ ያገኘሁት እንዴት ነው የእኔ የማይሆን ? " አለ ወፈር ያለው ። " እንድትለፋ ማን ጉልበቱን ሰጠህ ? መንገዱንስ ማን አሳየህ ? " " ፈጣሪየ " አለ ። " ፈጣሪ ይህንን ያደረገልህ አንተን ከእሱ አብልጦ ወዶህ ወይም እሱን ከአንተ አሳንሶ ጠልቶት ይመስልሀል ? ለአንተ ሲሰጥ ለእሱ የነሳው ? ከአንተ ሞሰብ ትራፊ እንዲለምን ያደረገውስ ? " " እኔ እንጃ ! " ግራ በተጋባ ስሜት ውስጥ ሆኖ መለሰ ። " አይደለም አንተንም በመስጠት ሊፈትንህ እሱንም በመቀበል ሊፈትነው ፈልጎ ነው ። ' ከተቀበሉ እጆች የሰጡት ምንኛ ብፁሁ ናቸው ይላልና ' ። " ብሎ ፀጥ አለ ። " እሽ እሱስ ይሁን ። የሠጠሁትን ካልመለሰልኝስ ! " አለ ደግሞ ። " ማንም የወሰደባችሁን መልስልኝ አትበሉት ። እኔ ጨምሬ እሰጣችሁ አለሁና ያለውን አስተውል ። " አለው ወጣቱ ። በዚህ ጊዜ ወጣቱ ከእሳቢያቸው በላይ ሆነባቸው እና ዝም አሉ ። እሱ ባይመለከታቸውም ። ሁለቱም በዝምታቸው ተሸፏፋነው በዓይነ ቁራኛ ይመለከቱት ጀመር ። " አንዳንዱን ሲፈጥረው ለሰዎች ችግር ፈች አድርጎ ይፈጥረዋል ። አንዳንዱን ደግሞ ለሰዎች ጉድጓድ ቆፋሪ ። በሰዎች መንገድ ድንጋይ ካቢ እሾህ ተካይ ያደርገዋል ። ( " በወንድሙ መንገድ ላይ እሾህ የሚተክል ወዮለት " የሚለውን ያላስታወሰ እጅ ) አለ በልቡ ። አንተ ለሰው መቀየሪያ ቁልፉ እጅህ ላይ ካለ ስጠው ። ከእነ ችግሩ አጠገብህ ኩርትም ብሎ ከሚውል ከችግሩ ተላቆ ቢርቅህ ይሻላል ። ከሱ ሳትጠብቅ ከአንተ ማድረግ የምትችለውን አድርግ ። " ብሎ ቀና ብሎ አያቸው ። " እህህህ " ሁለቱም አንገታቸውን ነቀነቁ ። " አይገባችሁም ስትዋሹኝ ነው ። ቀድሞ በንፁህ ልባችሁ ያላደረውን እኔ አንድ መናኛ ነግሪያችሁ ። ለዚያውም በዚች ደቂቃ ... በእድሜ ዘመናችሁ ያላገኛችሁትን ማሰላሰል አሁን ተረዳችሁኝ ? " አለ በልቡ ። " ምን አልኸን ? " አሉት ። " በግ ለአንበሳ ቀለቡ ናት ። " " አዎ ! በሚገባ ! " " አንበሳስ ለበግ ምን ይጠቅማታል ? " " ምንም ! " " አያችሁ ። ፈጣሪ አንዳንዶችን እንደዚህ ይፈጥራል ። ለእነሱ ጥቅም ባይሰጡም ። ለሌሎች ግን ለመኖር ምክንያት ያደርጋቸዋል ። " ብሎ ፀጥ አለ ። ሁለቱም ፀጥታን መርጠዋል ። "በዛ ላይ ሰው ለማስያዝ - ለመጠቆም እና ለማስጠቆር መሯሯጥ ምን ይጠቅማል ? እንኳን ጠቁማችሁ የሰው ልጅ በተፈጥሮው በክፋት ። በተንኮል ። በምቀኝነት ሰንሰለቶች የታጠረ ፋጡር ነው ። " " እንዴት ? " አለ ። " ከንፍር ውሃ በኃላ ኖህ ' ፈጣሪን ከዚህ በኃላስ አታጥፋን ' ሲል ተማፀነ ። ፈጣሪም ' በሰው ልጅ ጥፍት ድጋሜ ምድርን አልቀጣትም ። ነገር ግን ከትንሹ ጀምሮ ክፋት በሰው ላይ ያድራል ! ' ብሏል እና ። በርግጥ እነዚህ ያደሩብን ክፋቶችን ቀና ነገር በመስራት ልናጠፋው እንችላለን ። ግን እገሌ ጎዳኝ ። እገሌ ክፉ ነው አትበሉ ። የክፋት መጠኑ ይለያይ እንጅ ሁሉም ሰው ክፋት አለበት በውስጡ ። ለምን ? ርግመት ነውና ። "