የኢዜማ አባላትና ደጋፊዎች ማህበር
Статистикаማንኛውም ዜጋ፣ በዘር፣ በሀይማኖት፣በጾታ፣ወይም በዕድሜ፣ ሳይበላለጥ፣እኩል መብት፣ እኩል ፍትህ፣እና በፖለቲካ በኢኮኖሚና በማኅበራዊና ሌሎችም መስኮች የመሳተፍ እኩል ዕድል እንዲኖረው ማስቻል።
- Последний пост
- 5 авг.
- Последнее чтение
- 13 авг.
- Постов за неделю
- 0
- Всего постов
- 179
- Тип
- открытый
- Язык
- am
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 67
- 1/48двое суток
- 76
- 1/72трое суток
- 82
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
በ #ኢዜማ ዕይታ፤ «ያለን አንድ ሀገር ነው፤ በዚህ ሀገር ውሰጥ የሚኖር ሕዝብ አንድ ሕዝብ ነው» ይኽ ማለት ይህ ሕዝብ አንድ ቋንቋ፣ አንድ እምነት እና አንድ ባህል ብቻ ያለው ሕዝብ ነው ማለት አይደለም። #ኢዜማ #ezema #ኢትዮጵያ #Ethiopia
видео или голосовое, без подписи
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በጉራጌ ዞን ወልቂጤ ምርጫ ክልል የ #ኢዜማ አባል የሆኑት ደምስ ገብሬ በኃላፊነት የሚመሩት የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጉራጌ ዞን ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ በድጋሚ ስኬታማ ዓመትን አሳለፈ። በክልሉ ሳይንስ፣ ኢንፎርሜሽን እና ቴክኖሎጂ ቢሮ በተካሔደው የ 2018 ዓ.ም. የአፈፃፀም ምዘና የዞኑ መምሪያ 97.4 % እንዲሁም በኮደርስ አፈፃፀም 98.3 በማምጣት ክክልሉ 1ኛ ሆኖ በማጠናቀቅ የዕውቅና እና የተለያዩ ሽልማቶች ተበርክቶለታል። ከዚህ ቀደም ይኸው መምሪያ በአባላችን እየተመራ ባለፈው 2017 በጀት ዓመት አፈጻጸም ግምገማና የ2018 እቅድ መድረክ ላይ በአጠቃላይ አፈፃፀም 1ኛ በመውጣት ሽልማት እንደተበረከተለት ይታወሳል። ኢዜማ እሴቶቼ ናቸው ሲል ካስቀመጣቸው መካከል አንደኛው ልኅቀት (Excellence) ሲሆን የሀገራችን በርካታ ችግሮች መፍትሔ ማግኘት የሚችሉት ልኅቀትን መመዘኛ ባደረገ የሥራ ውጤት መለኪያ ብቻ ነው የሚል ጠንካራ እምነት ያለው ሲሆን ይህንን ልህቀት ለሚያሳዩ አባላት እንዲሁም የፓርቲው ልዩ ልዩ አሀዶች ዕውቅናን እንደሚሠጥም በግልጽ አስቀምጧል። በዚሁ መሠረት የፓርቲያችን አባል ደምስ ገብሬ በአመራርነት ለተቋሙ ስኬታማነት ከሌሎች ሠራተኞች ጋር በመሆን ለዚህ ውጤት ላበረከቱት አስተዋፅኦ ምስጋና እያቀረበ በተጨማሪም ከፍ ያለ ኩራት እንደተሠማው ለመግለጽ ይወዳል። #ኢዜማ #ezema #ኢትዮጵያ #Ethiopia
ለሰላም የቀረበውን ጥሪ አስመልክቶ ከኢዜማ የተሠጠ የድጋፍ መግለጫ!! በ 8 ፓርቲዎችና 11 ሲቪክ ማሕበራት የተቋቋመው የትግራይ ሰላምና ለውጥ ፈላጊዎች እንቅስቃሴ ሕጋዊ አካልነቱን ባጣው ሕወሓት አማካኝነት በትግራይ ህዝብ ላይ እየተደረገ ያለው አፈና፣ ስቃይ እና እንግልት እንዲቆም እና ጦርነት እንዲቀር ጫና ለማድረግ ያለመ የሰላማዊ ሰልፍ በአዲስ አበባ እንደጠራ መረጃ ደርሶናል፤ የለውጥ እንቅስቃሴው ሁሉም ይህን ሰላማዊ ዓላማ የሚደግፉ ኢትዮጵያውያን በሰልፉ ድጋፋቸውን እንዲሰጡም ጥሪ አቅርቧል። ፓርቲያችን ኢዜማ የትግራይን ህዝብ ከዳግም ጦርነት እና ስቃይ ለማዳን የሚደረጉ ሰላማዊ እንቅስቃሴዎች ሁሉ እንደሚደግፍ በተደጋጋሚ በገለፀው መሠረት ለዚህ ሰላማዊ ሰልፍ ይፋዊ ድጋፉን እየገለፀ የኢዜማ አባላትና ደጋፊዎችም በሰልፉ በመገኘት እምቢ ለጦርነት የሚል ድጋፋቸውን እንዲያሳዩ ጥሪውን ያቀርባል። እምቢ ለጦርነት! የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ (ኢዜማ)
የኢዜማ ም/መሪ ንጋቱ ወልዴ ሀገራዊ ምክክሩን አስመልክቶ ከ NBC Ethiopia ጋር ያደረጉትን ቆይታ ነገ ሐምሌ 10/2018 ዓ.ም ከምሽት 3:00 ሰዓት ጀምሮ ይከታተሉ። #ኢዜማ #ezema #ኢትዮጵያ #Ethiopia
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ (ኢዜማ) አመራሮች እና የቋሚ ኮሚቴ አባላት በሀገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ ለመወያያነት የቀረቡ አጀንዳዎችን ፓርቲው ለሃገራዊ ምክክር ካዘጋጃቸው አጀንዳዎች አንፃር ፈተሹ። ውይይቱን የፓርቲው መሪ ኢዮብ መሣፍንት እና ሊቀመንበሩ ዶ/ር ሙሉዓለም ተገኘወርቅ ባቀረቡት መነሻ ሐሣብ የተጀመረ ሲሆን ተሳታፊዎች ተጨማሪ ሐሣቦችን አቅርበው ተወያይተዋል። የውይይቱን መክፈቻ ንግግር ያደረጉት የፓርቲው ምክትል ሊ/መንበር ማዕረጉ ግርማ ሀገራዊ ምክክር የኢዜማ ጉዳይ ብቻ እስኪመስል የተከታተልነው ዓበይት ጉዳይ መሆኑን ገልፀው በጉባኤውም ፓርቲውን ወክለው የሚሣተፉ አመራሮች ምን ያህል እንደተዘጋጀንበት እንደሚያሣዩ ጥርጥር የለኝም ሲሉ ገልፀዋል፤ መድረኩን የፓርቲው ም/መሪ ንጋቱ ወልዴ መርተውታል። #ኢዜማ #ezema #ኢትዮጵያ #Ethiopia
የኢዜማ አመራር የሆኑት ዮሐንስ መኮንን በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ በአሐዱ ራዲዮ አሐዱ መድረክ ላይ ያደረጉትን ቆይታ ይከታተሉ። https://youtu.be/496wrQ6xdH0?si=NGx1sSS4thuzDufF #ኢዜማ #ezema #ኢትዮጵያ #Ethiopia
በትግራይ የሚገኙ ዜጎቻችን ወደጦርነት ላለመግባት በሚያደርጉት ጥረት ሁሉ ከጎናቸው እንደምንቆም እንገልፃለን!! እምቢ ለጦርነት!! ኣብ ትግራይ ዝርከቡ ዜጋታትና ናብ ጦርነት ንዘይምእታይ ኣብ ዝገብርዎለው ፃዕሪ ኹሉ ኣብ ጎኖም ጠጠው ከም እንብል ክንገልፅ ንፎቱ!! እምቢ ንጦርነት!! We reaffirm our unwavering commitment to stand with our citizens in Tigray in all their efforts to prevent war and safeguard peace. No to war!! #ኢዜማ #Ezema #ኢትዮጵያ #Ethiopia #እምቢ_ለጦርነት #NoToWar
ዛሬ ምሽት 3:00 ሰዓት የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ (ኢዜማ) መሪ ኢዮብ መሳፍንት በ FBC (Fana Broadcasting Corporate S.C.) አንድ ዕድል ፕሮግራም ላይ ያደረጉትን ቆይታ ይመልከቱ። #ኢዜማ #ኢትዮጵያ
видео или голосовое, без подписи
የሀገር አቀፉ ምርጫ 2018 ውጤት ይፋ መሆኑን ተከትሎ ከኢዜማ የተሠጠ መግለጫ!! ሀገር አቀፉ ምርጫ 2018 መጠናቀቁን በትላንትናው ዕለት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ይፋዊ የምርጫ ውጤት በማሣወቅ አረጋግጧል፤ ምርጫው ከነእንከኖቹም ቢሆን በሰላም በመጠናቀቁ ፓርቲያችን እንኳን ደስ አለን ለማለት ይወዳል። በተጨማሪም ፓርቲያችን ለውድድር በቀረበባቸው ቦታዎች 13 የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና 73 የክልል እና የከተማ ምክር ቤት ወንበሮችን በድምሩ 86 መቀመጫዎችን በማግኘት በሀገር አቀፍ ደረጃ ቀዳሚው ተፎካካሪ ፓርቲ ሆኖ አጠናቋል። ይህንን ተጨባጭ ስኬት ላስመዘገቡ የፓርቲያችን ዕጩዎች፣ አባላት፣ ደጋፊዎች እና በሂደቱ በቅንነት ለተሳተፉ አካላት ሁሉ እንኳን ደስ አለን እንኳን ደስ አላችሁ ለማለት ይወዳል። ፓርቲያችን ከቀጣዩ ምርጫ በፊት ባሉት ዓመታት ጠንካራ ጎኖቹን በማስቀጠል እንዲሁም የነበሩበትን ክፍተቶች በስትራቴጂ እና ሌሎች አስፈላጊ ተግባራት በመሙላት ተጨባጭ የተፎካካሪ ፓርቲነት ሚናውን ጊዜ ሳያባክን የሚጀምረው ዛሬ መሆኑን እየገለፅን፤ በነዚህ ዓመታት ከዚህ ቀደም ስናደርገው እንደነበረ ሁሉ ብሔራዊ ጥቅሞችን በሚያሣኩ ጉዳዮች ከሁሉም ኢትዮጵያዊ ኃይል ጋር በመተባበር የምንንቀሳቀስበት መፎካከሪያ አጀንዳዎች ላይ ማኅበረሰባችንን በሚመጥን ጨዋነት ልዩነቶቻችንን እና ትችቶቻችንን እያቀረብን የጀመርነውን ጤናማና ዘመናዊ የፖለቲካ ባሕል የማዋለድ ተግባራችንን በተጠናከረ መልኩ የምንቀጥልበት እንዲሁም ለተጨማሪ ስኬት የምንንደረደርበት እንደሚሆን ቃል እንገባለን። በመጨረሻም ገዢ ሆኖ እንዲቀጥል ለተመረጠው ብልጽግና ፓርቲ እንዲሁም በውድድሩ ተሳትፋችሁ የሕዝብ ውክልናን ላሳካችሁ ተፎካካሪዎች እንኳን ደስ አላችሁ ለማለት እንወዳለን። አሸናፊው ፓርቲ ከዛሬ ጀምሮ ዴሞክራሲያዊ ተቋማትን ለመገንባትና ፍትሐዊ የፖለቲካ ምህዳርን ለሁሉም እኩል ተደራሽ ለማድረግ በቁርጠኝነት እንዲሠራ፤ ለሀገር እድገትና ለውጥ ጠቃሚ ሀሳቦች ከማንኛውም ወገን ሊገኙ እንደሚችሉ በመረዳት አማራጭ ሃሳቦችን እንዲሰማ፤ እንዲሁም ትችቶችን በሆደ ሰፊነት እያስተናገደ ሀገራችን የሚያስፈልጋትን ዴሞክራሲ በጋራ እንድንገነባ ጥሪ እናቀርባለን። #ኢዜማ #ኢትዮጵያ #ምርጫ_2018
የኢዜማ መሪ ኢዮብ መሳፍንት ምርጫውን እና ወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮችን አስመልክቶ ከ NBC ቴሌቪዥን ጋር ያደረጉትን ቆይታ ዛሬ ምሽት 3:00 ሰዓት ይከታተሉ። https://youtu.be/q4kVabVLsrI?si=-NmZ6E2AHaPrSibB #ኢዜማ #ኢትዮጵያ