- Последний пост
- 23 дек.
- Последнее чтение
- 15 авг.
- Постов за неделю
- 0
- Всего постов
- 28
- Тип
- открытый
- Язык
- und
- Категория
- Новости и СМИ
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- —
- 1/48двое суток
- —
- 1/72трое суток
- —
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
በበጎ አድራጎት የተሞላ ጥሪ፡ ለወገን ደራሽ ወገን ነው! በችግር ውስጥ ላሉ ወገኖቻችን ለሕፃፅ የሚደረገው ድጋፍ ተጠናክሮ ቀጥሏል። ወጣቱ የቲክቶክ ዝነኛ አዶናይ በወሰደው ቅድሚያ ተነሳሽነት፣ ለወገኖቻችን የሚሆን ልዩ ልዩ ቁሳቁሶችን በማሰባሰብ ላይ ይገኛል። የመሰብሰቢያ ቦታ፦ ለልገሳ የሚያስፈልጉ ቁሳቁሶችን ይዘው በሚከተለው አድራሻ መምጣት ይችላሉ፦ * ቦታ፦ ከዩጎ ቸርች (Yugo Church) ጀርባ * መለያ፦ ምሳሌ አዲስ ስፔሻል ክትፎ እና ቁርጥ ቤት ጀርባ ምን አይነት ድጋፍ ማድረግ ይቻላል? ለወገኖቻችን ይረዳል የምትሉትን ማንኛውንም አይነት ድጋፍ መስጠት ትችላላችሁ፦ * አልባሳት * የምግብ እህሎች * ዘይት * እና ሌሎች መሠረታዊ ቁሳቁሶች የ"100 Challenge" ወቅታዊ መረጃ፦ ትላንት ማታ 3 ሚሊዮን ብር ደርሶ የነበረው የ100 ቻሌንጅ (100 Challenge) አሁን ያለበት የገንዘብ መጠን ዛሬ ይፋ ይደረጋል ተብሎ ይጠበቃል። የሁላችሁም ቅንነት እና ተሳትፎ ትልቅ ለውጥ እያመጣ ነው! "አንድ ሰው ለብዙዎች ተስፋ መሆን ይችላል!" አሁንም ያልረዳችሁ ካላችሁ፣ በ 100 ብር ብቻ የአንድን ወገን ህይወት መቀየር ይችላሉ። * የባንክ አካውንት፦ 1000737705432 * የባንክ ስም፦ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ (CBE) * የአካውንቱ ስም፦ ADONAY&HAILEAB & YORDANOS&BIRUK ይህ መልዕክት ለብዙዎች እንዲደርስ Share በማድረግ ተባበሩን። በጋራ በመሆን የወገኖቻችንን ህመም እናቃልል! ©️ጉርሻ page 🙏🙏🙏 🌴🌴🌴 https://www.facebook.com/share/p/14Nra1DZHfP/?mibextid=wwXIfr
በትግራይ ክልል ረሀብ መከሰቱ እየተነገረ ነው። በተለይ በጦርነቱ ምክንያት የተፈናቀሉ ዜጎች ከፍተኛ የረሀብ አደጋ ላይ እንደ ወደቁ ተገልጿል። የፌደራሉ መንግስትም ሆነ ክልሉን የሚያስተዳድረው ህወሀት ለተራቡት ዜጎቻችን ቅድሚያ ሰጥተው የተደቀነውን አደጋ በአስቸካይ መቀልበስ አለባቸው። ሰብአዊ እርዳታዎችም በስፋት ሊቀርቡ ይገባል። የጦርነት ትርፉ ለረጅም ጊዜ እንደመሆኑ ተዋጊ ሀይሎች ጦርነት አቁመው ለህዝብ ቅድሚያ ሊሰጡና ሀገርን ሊያስቀድሙ ይገባል።
видео или голосовое, без подписи
Ishow Speed ወደ ሀገራችን ኢትዮጽያ ጉዞ እንደሚያደርግ ይፋ ያደረገበት Trailer ቪዲዮ!
የእስር ዜና፡ ቲክቶክሩ እና ድምፃዊ ጆሲ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ዋለ:: በቲክቶክ ማኅበራዊ ሚዲያ መድረክ ላይ ባለው ስራው እና በሙዚቃ ሥራዎቹ የሚታወቀው ወጣት ጆሲ (Josie) ትላንትና አመሻሽ ላይ በፌዴራል ፖሊስ ቁጥጥር ስር መዋሉ ተዘገበ። ሪፖርቶች እንደሚያመለክቱት፣ የጆሲ መታሰር ምክንያት በቅርቡ በተካሄደው የቲክቶክ ሽልማት (TikTok Awards) ሥነ-ሥርዓት ላይ ሙሉ ቀይ ቀለም ያለው ልብስ ለብሶ መቅረቡ ነው። የጆሲ ማብራሪያ፡ አርቲስቱ አለባበሱን የመረጠበት ዋናው ዓላማ ስለ ሴቶች የወር አበባ ጤና (menstrual health) ግንዛቤ ለማስጨበጥ መሆኑን ገልጿል ነበር ከዛ ይቅርታ ማለቱ ተመላክቷል:: ጆሲ ከዚህ ቀደም በተመሳሳይ ‘አግባብ ያልሆነ አለባበስ’ በሚል ምክንያት በቁጥጥር ስር ውለው ከነበሩ ሌሎች ቲክቶከሮች ጋር ተደባልቆ መታሰሩ ታውቋል። የፌዴራል ፖሊስ ከዚህ ቀደም የቲክቶክ ሽልማት ሥነ-ሥርዓት ላይ የታዩ ከባህል የወጡ የአለባበስ ጉዳዮችን እየመረመረ መሆኑን ፍንጭ ሰጥቶ የነበረ ሲሆን፣ አሁን የተወሰደው እርምጃም የዚያ ክትትል አካል እንደሆነ ተዘግቧል።
ወቅታዊ ጉዳይ: ጋዜጠኛው በሐሰተኛ ዘገባ ተወነጀለ—በአዳማ ስም ማጥፋት ክስ መመስረት አለበት ተባለ አዳማ—በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ከፍተኛ ውዝግብ ያስነሳው አንድ ጋዜጠኛ በአዳማ ከተማ "ተዘረፍኩና ተደበደብኩ" በሚል የሰጠው ዘገባ የሐሰት መሆኑን ተከትሎ፣ በአዳማ ከተማ አስተዳደር በኩል በሕግ ሊጠየቅ መሆኑ ተሰማ። * የአዳማ ከተማ ነዋሪዎች ጋዜጠኛው የከተማዋን ስም እያጠፋና ወንበዴና ቀማኛ ያለባት አስመስሎ በማቅረቡ ተችተዋል። * የአዳማ ከተማ አስተዳደር ጋዜጠኛውን በሕግ እንዲጠይቅና የከተማዋን ስም በማጥፋቱ ክስ እንዲመሰረትበት በብዙ ኢትዮጵያውያን ዘንድ ጥያቄ ቀርቧል። * የቪዲዮ ማስረጃ: መረጃዎች እንደሚያመለክቱት፣ አጠቃላይ ክስተቱ በቪዲዮ የተቀረጸ በመሆኑ፣ ጋዜጠኛው ሐሰተኛ ዘገባ መስራቱንና የስሙን መነሳት ለማስቀረት በፍጥነት እርምጃ መውሰዱን ያወቀ መሆኑ ተጠቁሟል። ጋዜጠኛው በአዳማ ከተማ ነዋሪዎች ("በአዳም ልጆች") ላይ ያሰራጨው ዘገባ የውሸት መሆኑ ተነግሯል። እንዲሁም የአዲስ አበባ ፖሊስ ይህንን ጉዳይ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመነጋገር እውነቱን እንዲያጣራና ክትትል እንዲያደርግ ጥሪ ቀርቧል። 🌴🌴🌴 https://www.facebook.com/share/p/1G77eapKko/?mibextid=wwXIfr
የሪሜዲያል መግቢያ ነጥብ ይፋ ሆነ። ትምህርት ሚኒስቴር በ2018 የትምህርት ዘመን የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎችን በተፈጥሮ እና ማህበራዊ ሳይንስ ትምህርት መስኮች ከ49.5% በታች ያስመዘገቡ ነገር ግን ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የሚያሟሉ ተማሪዎች የRemedial ፕሮግራም ተጠቃሚ መሆናቸውን አሳውቋል። 1. በሁሉም አማራጮች (በግል እና በመንግስት ተቋማት) የRemedial ፕሮግራም ለመከታተል ተማሪዎች እንደተፈተኑት የትምህርት አይነት ብዛት 33 ከመቶ እና ከዚያ በላይ ማምጣት አለባቸው። 2. ከላይ በተራ ቁጥር 1 የተገለጸው እንደተጠበቀ ሆኖ በመንግስት ተቋማት (ወጪያቸው በመንግስት ተሸፍኖ) የ Remedial ፕሮግራም የሚከታተሉ ተማሪዎች የመቁረጫ ነጥቡን ያሟሉ ብቻ ይሆናሉ። የመቁረጫ ነጥብ ፦ ➡️ የተፈጥሮ እና የማህበራዊ ሳይንስ ወንድ ተማሪዎች 216 ➡️ የተፈጥሮ እና የማህበራዊ ሳይንስ ሴት ተማሪዎች 204 ➡️ ታዳጊ ክልል እና አርብቶ አደር አካባቢ የተፈጥሮ እና ማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ለሁለቱም ጾታ 198 ➡️ የማህበራዊ እና የተፈጥሮ ሳይንስ መስማት ለተሳናቸው ተማሪዎች ለሁለቱም ጾታ 198 ➡️ ማህበራዊ እና የተፈጥሮ ሳይንስ ዓይነስውራን ተማሪዎች ለሁለቱም ጾታ 165 tikvahethiopia
видео или голосовое, без подписи
የኢትዮጵያ ትራፊኮች🫢 ሰሞኑን የኢትዮጵያ ትራፊኮች "አንድ ግለሰብ መታን" ብለው ወዲያው ግለሰቡን ይዘው አስረዋል። ቤተሰቦቹና ጓደኞቹ ለጉርሻዎች የደረሰው መረጃ እንደሚያመለክተው፣ ግለሰቡ የልጅ አባትና መልካም ሰው ነው። የሆነ ነገር አድርገውት እንጂ "ትራፊክ የሚደበድብ አይደለም" በማለት ተናግረዋል። አሁን ደግሞ ትራፊኮች ህጻን የሆነን ልጅ እየደበደቡት ይገኛሉ። የመደብደብ ህግስ ማን ነው የሰጣቸው? ለእነሱ ሲሆን ህጉ ይሰራል ማለት ነው? ሀሳባችሁ ምንድን ነው? እንወያይበት።
የፍልስጤም አምባሳደር በእንባ ታጅበው ያደረጉት ንግግር!
አሜሪካ በሶሪያ ባንዲራዋን ሰቀለች አሜሪካ በሶሪያ ደማስቆ ባንዲራዋን መስቀሏ የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት እንደሚያጠናክር አዲሱ የሶሪያ መልዕክተኛ ቶም ባራክ ተናገሩ። ከፈረንጆቹ 2012 ወዲህ አሜሪካ ባንዲራዋን ስትሰቅል ይህ ለመጀመሪያ ጊዜ እንደሆነ በሶሪያ የተሾሙት የአሜሪካ አምባሳደር ባራክ ገልጸዋል። አሜሪካ ከበሽር አል አሳድ መውድቅ በኋላ ከሶሪያ ጋር ያላትን ግንኙነት ለማጠናከር በደማስቆ ኢምባሲዋን ዳግም መክፈቷ የሁለቱን ሀገራት ወዳጅነት ከፍ ያደርገዋል ተብሏል። የሶሪያ እርስ በርስ ጦርነት በፈረንጆቹ 2011 ከተቀሰቀሰ በኋላ ዋሽንግተን እና ደማስቆ ግንኙነታቸው ሻክሮ መቆየቱ ይታወቃል። የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በሳውዲ ጉብኝታቸው ከሶሪያ ጊዚያዊ መሪ አህመድ አልሻራ ጋር ተገናኝተው የሶሪያ ማዕቀብን ማንሳታቸው ይታወሳል።
የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር በአፋርና ወልዲያ በኩል የጭነት መኪናዎች እንዳያልፉ የተከለከሉበት ምክንያት ማብራሪያ እንዲሰጠው ጠየቀ፡፡ የክልሉ ንግድና ኤክስፖርት ኤጀንሲ የፃፈው ደብዳቤ ‹‹ጉዳዩ ለትግራይ ክልል ጭነት ይዘው የሚጓዙ ተሸከርካሪዎች መከልከላቸውን ይመለከታል›› ሲል ይጀምራል፡፡ ሲቀጥልም ‹‹በርእሱ እንደተገለፀው ለትግራይ ክልል የተለያዩ ሸቀጦችን ይዘው በአፋር ክልል መስመር የሚጓዙ ተሸከርካሪዎች ከቀን 18/9/2017 ጀምሮ ሰርዶ በሚገኝ ፍተሻ ጣቢያ ወደትግራይ እንዳይሄዱ እንደተከለከሉ ከተለያዩ ምንጮች ስለሰማን በምን ምክንያት እንደተከለከሉ ማብራሪያ እንዲሰጠን እየጠየቅን ለሚሰጠን አዎንታዊ ምላሽ ምስጋናችንን ከወዲሁ እናቀርባለን››
видео или голосовое, без подписи
#RemedialExam የ2017 ዓ.ም የሪሚዲያል ተማሪዎች ፈተና ከግንቦት 25-30/2017 ዓ.ም ይሰጣል፡፡ መርሐግብሩ እንደሚያሳየው ከማዕከል የሚሰጠው ፈተና ለአምስት ቀናት የሚቆይ ሲሆን፤ ግንቦት 25/2017 ዓ.ም ለተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች በሚሰጠው የባዮሎጂ ትምህርት ፈተና ይጀመራል፡፡ በኢድ አል አድሃ (አረፋ) በዓል ምክንያት ፈተናው አርብ ግንቦት 29/2017 ዓ.ም የማይሰጥ መሆኑን መርሐግብር ያሳያል፡፡ ፈተናው ግንቦት 30/2017 ዓ.ም ለተፈጥሮ ሳይንስ እና ለማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች በሚሰጠው የእንግሊዝኛ ትምህርት ፈተና እንደሚጠናቀቅ ይጠበቃል፡፡ የ2017 ዓ.ም የሪሚዲያል ተማሪዎች የማጠቃለያ ግምገማ ከ100% ከማዕከል ብቻ እንደሚሆን ትምህርት ሚኒስቴር መግለፁ ይታወሳል፡፡
ሳልዘረፍ ተዘርፏል ተባልኩኝ - ንግድ ባንክ "ንግድ ባንክ ተዘርፏል" የሚባለዉ መረጃ ባንኩ የሀሰት ነዉ በማለት ከፍተኛ የገንዘብ ስርቆት ሙከራ ግን ተደርጎብኝ ነበር ሲል ገልጿል፡፡ ባንኩ፤ “ግንቦት 19 ቀን 2017 ዓ.ም የኢትዮጵያ ሚዲያ አገልግሎት በተሰኘ የዜና ማሰራጫ እንደ ሰበር ዜና የተላለፈ መልእክት “በኢትዮጵያ ንግድ ባንከ የውስጥ አካውንት ውስጥ ተቀምጦ የነበረ ከ7 ቢሊየን ብር በላይ መዘረፉ ተገለፀ” በማለት ባንኩ ከፍተኛ መጠን ያለው ገንዘብ እንደተዘረፈ፣ ዘራፊዎቹ እንዳልተያዙ እና ባንኩም ጉዳዩን አድበስብሶ እንዳለፈው የሚገልጽ የሐሰት ዜና ስለተዘገበ በጉዳዩ ላይ አጭር መግለጫ ለመስጠት ተገድጃለሁ” ብሏል። በተጠቀሰው ሚዲያ እና ሌሎችም ይህንኑ ሚዲያ ያጣቀሱ ሚዲያዎች ከባንኩ ከፍተኛ መጠን ያለው ገንዘብ እንደተዘረፈ የሚገልጽ ዜና ቢዘግቡም፤ እውነታው ግን በሚዲያዎቹ ከተዘገበው በተቃራኒ ከባንካችን ምንም የተዘረፈ ገንዘብ የለም ብሏል። ይልቁንም ከፍተኛ ገንዘብ ለመዝረፍ የተደረገ ሙከራ መኖሩን እንዳሳወቀ ግን ባንኩ በመግለጫ አመልክቷል። ሙከራው በጥቂት ያልተገባ ጥቅም ለማግኘት ባሰቡ ተጠርጣሪዎች የተፈፀመ እንጂ የባንኩ ሲስተም ተላልፎ የተፈፀመ ጥቃት አለመሆኑንም ገልጿል።
ቅዱስ ሲኖዶስ ለቲክቶከሮች የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ ሰጠ በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገር የሚኖሩ በግልና በቡድን ተደራጅተው ማኅበራዊ ሚዲያዎችን በመክፈት ከሃይማኖት ሥነ ምግባር በወጣ መልኩ የቤተ ክርስቲያናችንን ልዕልና የቅዱስ ሲኖዶስን ክብር የሚጋፋ ፣ የአባቶችንና የአገልጋዮችን ተልእኮ የሚያደናቀፍ ያልተገባና መሠረት የሌለው መግለጫ የሚያሰራጩ አካላት እንዲታረሙ ቅዱስ ሲኖዶስ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ በጥብቅ አስስቧል። #ተዋህዶ_ቲዩብ @factnews4
видео или голосовое, без подписи
ሳፋሪኮም‼️ በአዲስ አበባ ከተማ በጥቂት አከባቢዎች ተቋርጦ የነበረው አገልግሎታችን ወደነበረበት ተመልሷል ሲል ሳፋሪኮም አስታወቀ። ስለተፈጠረው ሁኔታ ይቅርታ ጠይቋል። @factnews4 @factnews4
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи