ፈለገ ህይወት ሰንበት ትምህርት ቤት
Статистика- Последний пост
- 14 авг.
- Последнее чтение
- 13 авг.
- Постов за неделю
- 12
- Всего постов
- 23
- Тип
- открытый
- Язык
- und
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 92
- 1/48двое суток
- 105
- 1/72трое суток
- 113
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
እንኳን ለፅንሰታ ማርያም እና ለቅዱስ ጴጥሮስ ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ! "የሰማይ ደጅ የተከፈተባት፣ የድኅነታችን መጀመሪያ የሆነችው እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በማኅፀን የተፀነሰችበትና ታላቁ ሐዋርያ ቅዱስ ጴጥሮስ ከጌታችን ከመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዘንድ የመንግሥተ ሰማያትን ቁልፍ የተቀበለበት ዕለት ነው።"ጸሎታችንና ልመናችን በቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነት እንዲያርግ፣በቅዱስ ጴጥሮስ እምነትና ታማኝነት ሕይወታችን እንዲባረክ፣የሰማይ ደጅ ለሁላችንም የተከፈተ እንዲሆን የእግዚአብሔር ቸርነት ይርዳን።መልካም በዓል!
አመ ሰብዑ ለወርኃ ነሐሴ በዓለ ጽንሰታ ለማርያም ሥርዓተ ማኅሌት 🌸🌸🌸🌸🌸🌸 ስምዓኒ እግዚኦ ጸሎትየ ሃሌ ሉያ፤ ሃሌ ሉያ ወይብጻሕ ቅድሜከ ገዓርየ ሃሌ ሉያ፤ ሃሌ ሉያ ወኢትሚጥ ገፀከ እምኔየ፤ በዕለተ ምንዳቤየ አጽምእ ዕዝነከ ኀቤየ ሃሌ ሉያ፤ ሃሌ ሉያ አመ ዕለተ እጼውአከ ፍጡነ ስምዓኒ ሃሌ ሉያ፤ ሃሌ ሉያ ለዓለም ወለዓለመ ዓለም፤ ሃሌ ሉያ ዘውእቱ ብሂል፤ ንወድሶ ለዘሃሎ እግዚአብሔር ልዑል፤ ስቡሕ ወውዱስ ዘሣረረ ኲሎ ዓለመ፤ በአሐቲ ቃል። መልክአ ሥላሴ፦ ሰላም ለኲልያቲክሙ እለ ዕሩያን በአካል፤ ዓለመክሙ ሥላሴ አመ ሐወጸ በሣሕል፤ እምኔክሙ አሐዱ እግዚአብሔር ቃል፤ ተፈጸመ ተስፋ አበው በማርያም ድንግል፤ ወበቀራንዮ ተተክለ መድኃኒት መስቀል። ዚቅ ስብሐት ለኪ ኦ ወላዲተ እግዚአ ኲሉ አኮቴት ወክብር ለአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ይእዜኒ ወዘልፈኒ ወለዓለመ ዓለም አሜን ወልድኪ ሣህሎ ይክፍለነ ሰዓሊ ለነ ቅድስት። ዚቅ (ሌላ) ለማርያም ዘምሩ፤ ለማርያም ዘምሩ፤ መስቀሎ ለወልዳ እንዘ ትጸውሩ። ዘጣዕሙ፦ ሰላም ለዝክረ ስምኪ ዘመንክር ጣዕሙ፤ ለወልድኪ አምሳለ ደሙ፤ መሠረተ ህይወት ማርያም ወጥንተ መድኃኒት ዘእምቀዲሙ፤ ኪያኪ ሠናይተ ዘፈጠረ ለቤዛ ዓለሙ፤ እግዚአብሔር ይትባረክ ወይትአኮት ስሙ። ዚቅ፦ ይትባረክ እግዚአብሔር ወይትአኮት ስሙ፤ኪያኪ ሠናይተ ዘፈጠረ ለቤዛ ብዙኃን፤ እስመ መሠረት ለሕይወተ ኩሉ ዓለም፤ማርያም እምነ ወእሙ ለእግዚእነ ሰአሊ በእንቲአነ ነግስ፦ እምጌቴሴማኒ ፈለሰት ኀበ ዘሉዓሌ ምጡቅ፤ በነፋስ ዓውሎ ወቋለ መብረቅ፤ ማርያም አንቲ ሰዋሰወ መብረቅ፤ ይቤለኪ አሮን ሌዋዊ በደብተራ ሙሴ ባለቅ፤ ታቦት ታቦት እንተ ውስቴታ ኦሪት ውቱረ ይከድንዋ በወርቅ ዚቅ፦ እምድኅረ ካልዕ መንጦላዕት ደመና፤ ደብተራ ይብልዋ ቅድስተ ቅዱሳን፤ ወታቦትኒ እንተ ውስቴታ ኦሪት ይከድንዋ በወርቅ ውቱረ፤ ወውስቴታ መሶበ ወርቅ እንተ መና፤ በትረ አሮን እንተ ሠረፀት መልክአ ማርያም፦ ሰላም ለአእዳውኪ እሳተ መለኮት እለ ገሠሣ፣ አውቃፈ ብሩር ወወርቅ ለሥርጋዌሆን ኢኃሠሣ፤ ማርያም ድንግል ለመካን ሕንባበ ከርሳ፤ አንጽሕኒ እግዝእትየ ለፍትወተ ዓለም እምርኲሳ፤ በዲበ ሥጋየ ኢትንብር ነጊሣ። ዚቅ ኦ ድንግል አኮ በፍትወተ ደነሰ ዘተፀነስኪ፤ አላ በሩካቤ ዘበሕግ እምሐና ወኢያቄም ተወለድኪ። ወረብ 'እም ሐና ወኢያቄም'/፪/ ተወለድኪ/፪/ አላ በሩካቤ ዘበሕግ/፪/ መልክዐ ማርያም ሰላም ለፍልሰተ ስጋኪ ወለተ ንጉሥ ይሁዳ ፤ወወለተ ሌዊ እኁሁ ዘሀብተ ክህነቱ አገዳ፤ ማርያም ድንግል ምዕዝት ዘእምፅጌረዳ፤ በጽሒፍ ኢይፌጽሞ ለስብሐትኪ እንግዳ ፤ እመ ኮነ በቅድሜየ ስፍሐ ምድር ሰሌዳ ዚቅ፦ ዘበሕግ እለ ወለድዋ እም ቤተ ክህነት ወመንግሥት ዘኃረይዋ፤ ይዕቲኬ ማርያም ይእቲ መልክዐ ፍልሰታ፦ ሰላም ለፍልሰተ ሥጋኪ መካነ ፍስሓ ወኑዛዜ፤ኀበ ይረስዕዎ ለላህ ወኢይሄልይዎ ለትካዜ፤ ማርያም ህሉት ውስተ ልበ አምላክ እምቅድመ ጊዜ፤ ትፍሥሕተሰ ተፈሣሕኩ በፍልሰትኪ ይዕዜ፤ጊዜ ዚአኪ እሬኢ ማዕዜ። ዚቅ፦ ዘእንበለ ይትፈጠር ሰማይ ወምድር ወዘእንበለ ትሣረር ምድረ ገነት፤ ሀለወት ስብሐት ቅድስት ወብርክት ይእቲ ማርያም እንተ ተሰምየት ሰንበተ ክርስቲያን፤ ጽዮን ቅድስት እሞሙ ለሰማዕት፤ወእኅቶሙ ለመላእክት ምልጣን፦ ማርያም ድንግል እመ መቅድመ ቃል ለክርስቲያን አክሊል ለናዖድ ገብርኪ ኩኒዮ ሰዋሰወ ሣህል ማኅፈዱ ለነበልባል፤መርዓት ዘወንጌል አመላለስ፦ ማኅፈዱ ለነበልባል መርዓት/፪/ መርዓት ዘወንጌል/፬/ እስመ ለዓለም ለልየ በእዴየ ለሐኵዋ ለድንግል፣ እንተ እምኔሃ ተሰባዕኩ ይቤ እግዚአብሔር ፤ መንበሩ ዘኪሩቤል፤ ዘኢዮር ማህደሩ፤ማ፦ ዘኢይትነገር ቃል፤ ኀደረ ላዕሌሃ https://t.me/felege_hiwot_sunday_school
📖📖📖📖📖📖📖📖📖📖 " ኦ ድንግል አኮ በፍትወተ ደነስ ዘተፀነስኪ አላ በሩካቤ ዘበሕግ እምሐና ወኢያቄም ተወለድኪ" "ማርያም ሆይ በኃጢአት ፍትወት የተፀነሽ አይደለም በሕግ በሆነ ሩካቤ ከሐና ከኢያቄም ተወለድሽ እንጂ 🙏ቅዳሴማርያም🙏 📖📖📖📖📖📖📖📖📖📖 #አቤቱ ህዝብህን አድን ርስትህንም ባርክ ጌታ ሆይ ማራቸው ከፍ ከፍ አድርጋቸው/2/ #ወስብሐት ለእግዚአብሔር!! https://t.me/felege_hiwot_sunday_school
видео или голосовое, без подписи
🌹እንኳን ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ዓመታዊ የጽንሰት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። ቁጽረታ (ጽንሰታ) ለማርያም፦ ይህችን ዕለት አበው ሊቃውንት "ጥንተ መድኃኒት፤ የድኅነት መነሻ ቀን" ሲሉ ይጠሯታል። ስለ ምን ነው ቢሉ:- ለዓለም ድኅነት ምክንያት የሆነች የአምላክ እናቱ የተጸነሰችበት ዕለት በመሆኑ ነው። አንድም ከአዳም ስሕተት በኋላ ያለ ጥንተ አብሶ የተጸነሰች የመጀመሪያ ሰው እርሷ ናትና እንዲህ ይላሉ። "ለጽንሰትኪ በከርሥ: እንበለ አበሳ ወርኩስ: ወለልደትኪ እማኅጸን ቅዱስ።" "ድንግል ሆይ! መጸነስሽ ያለ በደል (ያለ ጥፋት) ነው: የተወለድሽበት ማኅጸንም ቅዱስ ነው።" (መጽሐፈ ሰዓታት, ኢሳ. 1:9, መኃ. 4) ይሕች ዕለት ለኢያቄምና ለሐና ብቻ ሳይሆን ለፍጥረት ሁሉ የተስፋ ድኅነት ቀን ናትና ሐሴትን ልናደርግ ይገባል። የእመቤታችን መጸነስስ እንደ ምን ነው ቢሉ:- ከነገደ ይሁዳ የሚወለድ ቅዱስ ኢያቄም የሚባል ደግ ሰው ከነገደ ሌዊ(አሮን) የተወለደች ሐና የምትባል ደግ ሴት አግብቶ: በሕጉ ጸንተው: በሥርዓቱ ተጠብቀው ይኖሩ ነበር። ነገር ግን በዘመኑ ሰዎች "ልጅ የላችሁም" በሚል ይናቁ ነበር። ኦሪታውያን ልጅ የሌለውን "ኅጡአ በረከት-ከጸጋ እግዚአብሔር የራቀ" ነው ብለው ያምኑ ነበር። ኢያቄምና ሐና ልጅ እንዲሰጣቸው ሲያዝኑ: ሲጸልዩ ዘመናቸው አልፎ አረጁ። እነሱ ግን የሚያመልኩት የአብርሃምና ሣራን አምላክ ነውና ተስፋ አልቆረጡም። የለመኑትን የማይነሳ ጌታ በስተእርጅናቸው ድንቅ ነገርን አደረገላቸው። አንድ ቀን ርግቦች ከጫጩቶቻቸው ጋር ሲጫወቱ የተመለከተች ቅድስት ሐና ፈጽማ አለቀሰች። "እንስሳትና አራዊትን: እጽዋትን በተፈጥሯቸው እንዲያፈሩ የምታደርግ አምላክ ምነው ሐናን ድንጋይ አድርገህ ፈጥረሃታልን?" ብላ አዘነች። ይህን የተመለከተ ቅዱስ ኢያቄም ወደ ተራራ ወጥቶ ሱባኤ ያዘ። ለአርባ ቀናትም ሲጸልይና ሲማለል ቆየ። በአርባኛው ቀን ሁለቱም ሕልምን ያልማሉ። እርሱ:- ነጭ ርግብ ሰማያትን ሰንጥቃ ወርዳ: በሐና ቀኝ ጆሮ ገብታ: በማኅጸኗ ስትደርስ አየ። እርሷ ደግሞ:- የኢያቄም በትር አብቦ: አፍርቶ: ጣፋጭ ፍሬውን ሰው ሁሉ ሲመገበው ታያለች። ቅዱስ ኢያቄም ከሱባኤ እንደ ተመለሰ ያዩትን ተጨዋውተው "ፈቃደ እግዚአብሔር ይሁን" አሉ። ለሰባት ቀናትም በጋራ እግዚአብሔርን ሲለምኑ ሰነበቱ። በሰባተኛው ቀን (ማለትም ነሐሴ 7) መልአከ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል ክንፉን እያማታ ወደ እነርሱ ወረደ:: "ዓለም የሚድንባት: የፍጥረት ሁሉ መመኪያ የሆነች ልጅ ትወልዳላችሁ" ብሏቸው ተሠወራቸው። እነርሱም ደስ ብሏቸው እግዚአብሔርን አመሰገኑ። እንደ ሥርዓቱም በዚህች ቀን አብረው አድረው እመ ብርሃን ተጸነሰች። "ኦ ድንግል አኮ በፍትወተ ደነስ ዘተጸነስኪ" "ድንግል ሆይ! ኃጢአት ባለበት ሥጋዊ ፍትወት የተጸነስሽ አይደለም" እንዳለ ሊቁ:: (ቅዳሴ ማርያም) ✝️ ጌታችን መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ የድንግል እናቱን ጣዕም: ፍቅር: ያሳድርብን:: ♡ ነሐሴ ⁷ ♡ ┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈ https://t.me/felege_hiwot_sunday_school ┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
አንኳን ለፆመ ፍልሰታ በሰላም አደረሳችሁ። የነገ ማለትም ሀሙስ ፣ነሀሴ 7/2018 የቅዳሴ አስተባባሪዎች ስም ዝርዝር:- 1, ሜሮን ገ/ፃድቅ 2, መቅደስ ጌትዬ 3, ሜላት መንግስትአብ 4,ህሊና መዐዛ 5,ፍቅርተ ታደሰ 6, ሰላም ደርቤ 7, ሀና ግዛው 8, ሳራ ሙሌ 9, ጌታውቃል 10,አላማየሁ መሰለ 11, ሽመልስ ብዙነህ 12, ተፈራ ስማቸው 13, ዳዊት ደለለኝ ➡️ነገ ሰው ስለሚያስፈልግ የተመደባችሁ እንዳትቀሩ!! 📍ማሳሰቢያ: ያለ አሳማኝ መረጃ መቅረት ክልክል ነው! ለፍቃድ በ0940095182 / 0933823682 ደውላችሁ አሳውቁ።
አንኳን ለፆመ ፍልሰታ በሰላም አደረሳችሁ። የነገ ማለትም ረብዑ፣ነሀሴ 6/2018 የቅዳሴ አስተባባሪዎች ስም ዝርዝር:- 1, ቅድስት ወንዱ 2, ሚልካ ብርሀነ 3, ፍቅርተ ታደሰ 4, ዊንታ እንዳለ 5, ሄራን ጌታቸው 6,ሜላት መንግስታብ 7, ህያብ ብርሀነ 8, የአብሰራ 9,ተፈራ ስማቸው 📍ማሳሰቢያ: ያለ አሳማኝ መረጃ መቅረት ክልክል ነው! ለፍቃድ በ0940095182 / 0933823682 ደውላችሁ አሳውቁ።
አንኳን ለፆመ ፍልሰታ በሰላም አደረሳችሁ። የነገ ማለትም ማክሰኞ፣ነሀሴ 5/2018 የቅዳሴ አስተባባሪዎች ስም ዝርዝር:- 1,ክርስቲያን ታደለ 2, መቅደስ ጌትዬ 3, ቤርሳቤህ ዳንኤል 4,ናርዶስ ቢንያም 5,ፍቅርተ ታደሰ 6, ማህደር ተክለወይኒ 7, ብሩክ ታከለ 8, ዳዊት ደለለኝ 9,በእምነት ታደለ 10, ሜላት መንግስትአብ 📍ማሳሰቢያ: ያለ አሳማኝ መረጃ መቅረት ክልክል ነው! ለፍቃድ በ0940095182 / 0933823682 ደውላችሁ አሳውቁ።
አንኳን ለፆመ ፍልሰታ በሰላም አደረሳችሁ። የነገ ማለትም ሰኞ፣ነሀሴ 4/2018 የቅዳሴ አስተባባሪዎች ስም ዝርዝር:- 1,ሊያ ሙሉጌታ 2,ህያብ ብርሀነ 3,አርሴማ ተመስገን 4,ሚልካ ብርሀነ 5, ቤተልሔም ያረጋል 6, አርያም ጌታቸው 7, ተፈራ ስማቸው 8, ሰመረ ጎይቶም 9, መስፍን ስለሺ ማሳሰቢያ: ያለ አሳማኝ መረጃ መቅረት ክልክል ነው! ለፍቃድ በ0940095182 / 0933823682 ደውላችሁ አሳውቁ።
አንኳን ለፆመ ፍልሰታ በሰላም አደረሳችሁ። የነገ ማለትም አሁድ፣ነሀሴ 3/2018 የቅዳሴ አስተባባሪዎች ስም ዝርዝር:- 1,ሂላርያ ዳንኤል 2,ቤተልሔም ሳምሶን 3,ሀሌታ ማርቆስ 4, ዊንታ እንዳለ 5, ሰላም ደርቤ 6,ቅድስት ወንዱ 7, ጌድዮን አየለ 8, ሰመረ ጎይቶም 9, ዮናስ ላቀው 10, ጥበቡ ዋለ 11, የምክር አምቦይ ማሳሰቢያ: ያለ አሳማኝ መረጃ መቅረት ክልክል ነው! ለፍቃድ በ0940095182 / 0933823682 ደውላችሁ አሳውቁ።
አንኳን ለፆመ ፍልሰታ በሰላም አደረሳችሁ። የነገ ማለትም ቅዳሜ፣ነሀሴ 2/2018 የቅዳሴ አስተባባሪዎች ስም ዝርዝር:- 1,ሳምራዊት መላኩ 2,ቤተልሄም መላኩ 3,ሀሌታ ማርቆስ 4, ኬብሮን አየለ 5,ብሌን መንግስቱ 6,ህይወት አብርሀ 7, ሙሴ ደርበው 8, ኦልያድ ከድር 9, ዳዊት ደለለኝ 10, አዱኛ አማረ ማሳሰቢያ: ያለ አሳማኝ መረጃ መቅረት ክልክል ነው! ለፍቃድ በ0940095182 / 0933823682 ደውላችሁ አሳውቁ።
ግጻዌ ዘነሐሴ ፩ ፍልሰታ🌹✨
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
መልክአ ሥዕል
✨በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን። «ኪዳነ ሰማይ ወምድር ዘኢየኃልፍ ቃለኪ፤ የሰማይና የምድር ቃል ኪዳንሽ ቃልሽ አያልፍም።» የተወደዳችሁና የከበራችሁ የደብራችን የኆኅተ ምሥራቅ ቅድስት ኪዳነ ምሕረት አጥቢያ ምዕመናንና ምዕመናት፦በመጀመሪያ ለአምላክ እናት ለእመቤታችን ለቅድስት ድንግል ማርያም የዕርገትና የትንሣኤ መታሰቢያ ለሆነው ለፍልሰታ ፆም ሱባኤ አምላካችን እግዚአብሔር በጤና እና በሰላም ስላደረሰን ስሙ የተመሰገነ ይሁን!የፍልሰታ ፆም ሐዋርያት የእመቤታችንን ትንሣኤና ዕርገት ለማየት ነሐሴ 1 ቀን ሱባኤ የገቡበት፣ በጾምና በጸሎት ተወስነው ሰማያዊውን ምስጢር ያዩበት ታላቅ የጸጋ ወቅት ነው። እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ደግሞ ከልጇና ከወዳጇ ከኢየሱስ ክርስቶስ ዘንድ «ስምሽን የጠራውን፣ ዝክረሽን ያዘከረውን፣ በቃል ኪዳንሽም የተማጸነውን እምርልሻለሁ» የሚል የማታለፍ የይቅርታ ቃል ኪዳን የተቀበለች የዓለም ሁሉ አማላጅ ናት።ስለሆነም፣ የዚህች የታላቋ ቃል ኪዳን እመቤት የኆኅተ ምሥራቅ ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ልጆች የሆናችሁ ሁሉ፣ ይህንን የሱባኤ ወቅት በከንቱ እንዳያልፍባችሁ በጾም፣ በጸሎት፣ በንስሐና በቁርባን እንድትተጉ መንፈሳዊ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን። በዚህ በጾሙ ወቅት በደብራችን በየዕለቱ የሚከተሉት መንፈሳዊ ሥርዓቶች ይፈጸማሉ፦ሰዓታት (የሌሊት ምስጋና)ኪዳንየውዳሴ ማርያም ትርጓሜ (የምስጢር ትምህርት)የፍልሰታ ቅዳሴበደብራችን በኆኅተ ምሥራቅ ቅድስት ኪዳነ ምሕረት በመገኘት፣ እነዚህን የእለት ተእለት ሰማያዊ መዓድ በመካፈል የእመቤታችንን በረከት እንድትሸምቱና አብረን እንድንጸልይ በታላቅ ክብርና ፍቅር እንጋብዛችኋለን።የእናታችን የቅድስት ኪዳነ ምሕረት አማላጅነትና የፍልሰታ ፆም በረከት ከሁላችን ጋር ይሁን። ሱባኤውን የሰላም፣ የፍቅርና የበረከት ያድርግልን!✨
📣ሰላም እንዴት አደራችሁ የእግዚአብሔር ቤተሰቦች ዛሬ ሐምሌ 30 ከመዝሙር ጥናት በፊት 10 ሰዐት ላይ የ ሰንበት ት/ቤታችን የክፍል ፅዳት ይኖራል 🎯የምንማርበት ክፍል አቧራ እየሞላ ስለሆነ ባላይ እና በታች በኩል ያለውን ክፍሎች የምናፀዳበት ብዙ ሰዐት የማይፈጅ አጠር ያለ ፅዳት እናደርጋለን 🎯የምንችል ከቤታችን መጥረጊያ ይዘን እንምጣ