tgindex
ጌቱ አስናቀው የጥብቅናና የህግ ማማከር አገልግሎት

ጌቱ አስናቀው የጥብቅናና የህግ ማማከር አገልግሎት

Статистика

ይህ ቻናል አነጋጋሪ የህግ ጉዳዮች ላይ ውይይት የሚደረግበት፣ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ከህግ አንጻር ሙያዊ ምልከታዎች የሚቀርብበት ማንኛውም ሰው አባል ሆኖ የሚጠቀምበት አሳታፊና መማማሪያ ገጽ ነው። በመሆኑም እባከዎ ሼርና አድ እንድያደርጉ በአክብሮት እንጠይቃለን። ☎️ስልክ ቁጥር 0913771324 getu.asn@gmail.com

Последний пост
12 авг.
Последнее чтение
15 авг.
Постов за неделю
1
Всего постов
30
Тип
открытый
Язык
und
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
613
+1 за 3 дн.
Сутки
0
0,00%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
181
30 постов
Вовлечённость
29,5%
к подписчикам
Постов в день
0,1
всего 30
Упоминаний
0
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
64
1/48двое суток
73
1/72трое суток
79

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • በውርስ ላይ አዲስ ታክስ ሊጣል ነው‼። ከአንድ ሚሊዮን ብር በላይ የሆኑ የውርስና የስጦታ ገቢዎች ለዚህ ታክስ እንደሚዳረጉ ተመልክቷል። ዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም (IMF) የአምስተኛውን ዙር የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ሪፎርም ግምገማ ተከተሎ ይፋ ባደረገው ባለ 132 ገጽ ሙሉ ሪፖርት እንደጠቆመው፣ የአገሪቱ የታክስ መሠረት በጣም ጠባብ በመሆኑ መንግሥት በየዓመቱ የአገር ውስጥ ገቢውን ለማሳደግ አዳዲስ የታክስ ዓይነቶችን ለመተግበር አቅዷል። በዚሁ ሪፖርት መሠረት በውርስና ስጦታ ከአንድ ሚሊዮን ብር በላይ በሚገኝ ገቢ ላይ ታክስ ይጣላል። 📌በሲጋራ፣ 📌በአልኮልና 📌በነዳጅ ምርቶች ላይ የሚጣለው ታክስ እንደሚጨምር የተገለጸ ሲሆን፣ ይህም አገራዊ ገቢን ከመጨመር ባለፈ ለጤና ፖሊሲዎች አተገባበር ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለው ተመልክቷል። የኢኮኖሚ ባለሙያው አቶ ዋሲሁን በላይ በሰጡት አስተያየት፣ እነዚህ አዳዲስ የታክስ እርምጃዎች በአጠቃላይ በአገሪቱ ኢኮኖሚና በህብረተሰቡ ላይ ተጨማሪ ጫና ሊፈጥሩ እንደሚችሉ ጠቁመዋል። ሆኖም መንግሥት አገራዊ ገቢውን ለማሳደግ ሲል ውሳኔዎቹን በቁርጠኝነት እንደሚተገብራቸው ይጠበቃል ብለዋል። Via :-EthioFM107.8 #WasuMohammed video 👇Like + Follow👇 https://www.facebook.com/share/18ZGvgBVhp/?mibextid=wwXIfr ==================== ወቅታዊ እና የታመኑ መረጃዎች እንዲደርሱዎ  የቴሌግራም ቻናሉን join በማድረግ በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4 https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4 https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4

  • ጀርመን ሴቶች ያለጡት ማስያዣ መዋኛ ገንዳዎች እንዲዋኙ ፈቀደች‼ የጀርመን ዋና ከተማ በርሊን ሴቶች እንደ ወንዶች ሁሉ በህዝብ መዋኛ ገንዳዎች ላይ የላይኛው የሰውነት ክፍላቸውን ክፍት አድርገው (topless) መዋኘት እንደሚችሉ ይፋ አድርጋለች። ይህ ውሳኔ ሊተላለፍ የቻለው በ2021 እ.ኤ.አ. አንዲት ሴት በህዝብ መዋኛ ገንዳ ውስጥ ደረቷን ሳትሸፍን በመዋኘቷ ምክንያት ከተከለከለች በኋላ ያቀረበችውን የመድልዎ አቤቱታ (discrimination complaint) የከተማዋ የዕኩልነት ቢሮ መመርመሩን ተከትሎ ነው። የበርሊን አስተዳደር በሰጠው ውሳኔ የሴቶች ደረት ከወንዶች ደረት በተለየ መልኩ ሊታይና ሊከለከል አይገባም ያለው ሲሆን፣ ውሳኔው የፆታ እኩልነትን ለማረጋገጥና የሰውነት ነፃነትን ለሁሉም ዜጎች እኩል ለማስከበር ታስቦ የተደረገ መሆኑን ገልጿል። #WasuMohammed video 👇Like + Follow👇 https://www.facebook.com/share/18ZGvgBVhp/?mibextid=wwXIfr ==================== ወቅታዊ እና የታመኑ መረጃዎች እንዲደርሱዎ  የቴሌግራም ቻናሉን join በማድረግ በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4 https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4 https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4

  • ኢትዮጵያ 55% ሴቶች "ባል ሚስቱን መደብደብ አሳማኝ ምክንያት ሊኖረው ይችላል" ብለው እንደሚያምኑ ተገለጸ ​ በኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎትና አጋሮቹ በተካሄደው አገር አቀፍ የዴሞግራፊና ጤና ዳሰሳ ጥናት፤ 55 በመቶ የሚሆኑ ሴቶች ባል ሚስቱን ለመምታት የሚያስችሉ አሳማኝ ምክንያቶች አሉ ብለው እንደሚያምኑ ይፋ ሆነ። ​በጥናቱ ከተሳተፉት መካከል ይህንን አመለካከት የሚጋሩት የወንዶች ቁጥር 39 በመቶ ሲሆን፣ አብዛኞቹ ምላሽ ሰጪዎች ለምታ በቂ ምክንያት አድርገው የጠቀሱት "ልጆችን ቸል ማለት" የሚለውን ነው። 📌​የለውጥ ሂደት፡ ድብደባውን የሚደግፉ ሴቶች ቁጥር ከ25 ዓመት በፊት ከነበረበት 85 በመቶ አሁን ወደ 55 በመቶ ቢቀንስም፤ የወንዶች ድርሻ ግን ከ10 ዓመት በፊት ከነበረበት 28 በመቶ ወደ 39 በመቶ አድጓል። 📌​የክልልና የትምህርት ልዩነት፡ በሲዳማ ክልል 74% ሴቶች ድብደባውን ሲደግፉ፣ በሶማሌ ክልል ግን 23% ብቻ ነው። በተጨማሪም ያልተማሩ ሴቶች ድብደባውን የመደገፍ እድላቸው (63%) ከተማሩት (29%) በእጅጉ የላቀ ሆኖ ተግኝቷል። ​በጥናቱ መሠረት ባል ወይም አጋር ካላቸው ሴቶች 30 በመቶ ያህሉ ጥቃት የደረሰባቸው ሲሆን፣ ከእነዚህም ውስጥ 58 በመቶ የሚሆኑት ምንም ዓይነት እገዛ አልጠየቁም። የሴቶች መብት ተሟጋቾች ይህንን ጎጂ አመለካከት ለመቀየር የሴቶችን ኢኮኖሚያዊ አቅም ማሳደግና ሰፊ የግንዛቤ ሥራ መሥራት እንደሚገባ አሳስበዋል ሲል ቢቢሲ ዘግቧል። #WasuMohammed video 👇Like + Follow👇 https://www.facebook.com/share/18ZGvgBVhp/?mibextid=wwXIfr ==================== ወቅታዊ እና የታመኑ መረጃዎች እንዲደርሱዎ  የቴሌግራም ቻናሉን join በማድረግ በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4 https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4 https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4

  • без подписи

  • без подписи

  • без подписи

  • #ኢሰመጉ ፦ " በምስራቅ አርሲ ዞን ከ2014 ዓ.ም ጀምሮ በርካታ ግድያዎች፣ እገታዎችና የንብረት ውድመቶች ተፈጽመዋል ! " የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባዔ (ኢሰመጉ) በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ አርሲ ዞን በተለያዩ ወረዳዎች ከ2014 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ ተፈጽመዋል ያላቸውን የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ይፋ አድርጓል። ሪፖርቱ የተዘጋጀው በሽርካ፣ መርቲ፣ ጀጁ፣ አርሲ ሲሬ፣ ሮቤ፣ ሙኒሳ፣ ጉና፣ ሆንቆሎ ዋቤ እና አሰኮ ወረዳዎች በተካሄደ የመስክ ምርመራ መሰረት መሆኑን ድርጅቱ ገልጿል። ኢሰመጉ እንደሚለው፣ በአካባቢው የሚኖሩ ማህበረሰቦች ለረጅም ጊዜ በሰላም ሲኖሩ ቢቆዩም፣ ባለፉት ዓመታት በታጠቁ ቡድኖች የተፈጸሙ ጥቃቶች በንጹሃን ላይ ያነጣጠሩ ሲሆን ሞት፣ የአካል ጉዳት፣ እገታ፣ አስገድዶ መሰወር፣ መፈናቀል እና የንብረት ውድመት እንዳስከተሉ ጠቁሟል። በተጨማሪም መንግሥት ዜጎችን የመጠበቅ ኃላፊነቱን በሚገባ አለመወጣቱ ጥቃቶቹ በተደጋጋሚ እንዲቀጥሉ ምክንያት ሆኗል ሲል ገልጿል። ሪፖርቱ እንደሚያሳየው፣ ከ2014 ዓ.ም ጀምሮ በምስራቅ አርሲ ዞን በተለያዩ ወረዳዎች በታጠቁ ኃይሎች በተለይም በኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች ላይ ያነጣጠሩ ጥቃቶች ተፈጽመዋል። በእነዚህ ጥቃቶች በሽርካ 116፣ በመርቲ 117፣ በጀጁ 101፣ በሮቤ 47፣ በጉና 26፣ በሆንቆሎ ዋቤ 20፣ በሙኒሳ 19፣ በአሰኮ 5 እና በአርሲ ሲሬ 3 ንጹሃን ዜጎች መገደላቸውን ኢሰመጉ መመዝገቡን ገልጿል። በተጨማሪም 4 የመንግሥት ሚሊሻ አባላት መሞታቸውንም ጠቅሷል። በጉና ወረዳ ብቻ 26 ሰዎች መገደላቸውን የገለጸው ሪፖርቱ፣ በናኖ ጃዊ ቀበሌ በአንድ ቀን 16 ሰዎች መገደላቸውን እና ከእነርሱ 5 ሰዎች በአንድ ጉድጓድ መቀበራቸውን ከቤተ ክህነት በተገኘ መረጃ ማረጋገጡን ገልጿል። ኢሰመጉ በምርመራው ወቅት የተጎጂዎችን፣ የሟቾች ቤተሰቦችን፣ የዓይን እማኞችን፣ የቤተ ክህነት ኃላፊዎችን በማነጋገርና የመስክ ምልከታ በማድረግ ማስረጃዎችን እንዳሰባሰበ ገልጿል። ኢሰመጉ ከኦሮሚያ ፖሊስ፣ ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ እና ከሌሎች ተቋማት ምላሽ ለማግኘት ደብዳቤ ቢልክም፣ ሪፖርቱ እስከተጠናቀቀበት ጊዜ ድረስ ምላሽ አልተገኘም ብሏል። በመጨረሻም ኢሰመጉ የፌዴራልና የክልሉ መንግሥታት የአካባቢውን ሰላምና ደህንነት እንዲያረጋግጡ፣ የጥቃት ፈጻሚዎችን ለፍትሕ እንዲያቀርቡ፣ ተጎጂዎች ካሳና ፍትሕ እንዲያገኙ እንዲሁም ተፈናቃዮች በደህንነት ወደ መኖሪያቸው እንዲመለሱ አሳስቧል። ሙሉ ሪፖርት ፦ https://t.me/tikvahethiopia/107128 ቲክቫህ ኢትዮጵያ አዲስ አበባ ሃምሌ 20 ቀን 2018 ዓ/ም @tikvahethiopia

  • ክፍት የሥራ ቦታ ማስታወቂያ የኢፌዲሪ የፍትሕ ሚኒስቴር በሕግ የተጣለበትን ኃላፊነት በላቀ ለመወጣት ይችል ዘንድ የአምስት ዓመት ስትራቴጂክ ዕቅድ በማውጣት የአሰራር እና የአደረጃጀት ማሻሻያዎችን አድርጓል። በአዲሱ አደረጃጀት መሠረት ባሉ የተለያዩ ማስተባበሪያዎች፣ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች፣ ዳይሬክቶሬቶች ተመድበው ለመስራት ፍላጎቱ እና ተነሳሽነቱ ያላቸው እና ከዚህ በታች የተመላከቱ መስፈርቶችን የሚያሟሉ የሕግ ባለሙያዎችን በዐቃቤ ሕግነት ለመቅጠር ይህ ማስታወቂያ ወጥቷል። በመሆኑም ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 30 ቀናት ውስጥ በተወዳዳሪነት መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እናስታውቃለን። አስፈላጊ የሆኑ መስፈርቶች፡ ኢትዮጵያዊ የሆነ/የሆነች እና በኢትዮጵያ የሚኖር /የምትኖር ፤ ለሕገ መንግስቱ እና ለሕግ የበላይነት ተገዢ የሆነ/የሆነች ፤ የየትኛውም የፖለቲካ ድርጅት አባል ያልሆነ/ያልሆነች ፤ በታታሪነቱ/ቷ ፣ በታማኝነቱ/ቷ ፣ በሥነ-ምግባሩ/ሯ መልካም ስም ያተረፈ/ች መሆኑን/ኗን ይማርበት/ ትማርበት ከነበረበት ዩኒቨርሲቲ ወይም ከሚኖሩበት አካባቢ ካለ የመንግስት ተቋም ማስረጃ ማቅረብ የሚችል /የምትችል ፤ የወንጀል ቅጣት ሪከርድ የሌለበት/ባት ፤ የፌዴራል መንግስቱን የሥራ ቋንቋ የሚችል/የምትችል ፤ እንደ አስፈላጊነቱ የሚሰጠውን የጽሁፍም ይሁን የቃል ወይም ሁለቱንም ፈተና መውሰድ እና ማለፍ የሚችል /የምትችል፤ የሥራ መደብ፡ (ዐቃቤ ሕግ) ዐቃቤ ሕግ ደረጃ ሦስት ተፈላጊ የትምህርት ደረጃ፡ ከከፍተኛ ትምህርት ተቋም በሕግ ትምህርት በመጀመሪያ ዲግሪ በ2018 ዓ.ም የተመረቀ /የተመረቀች፤ የመመረቂያ ነጥብ (Cumulative GPA) 3.6 ከዚያ በላይ ያለው/ ያላት፣ የመውጫ ፈተና (Exit Exam) ውጤት 85 ፐርሰንታይል እና ከዛ በላይ በማምጣት ፈተናውን ያለፈ/ያለፈች፤ ብዝሃነት፣ ሴት እና አካል ጉዳተኛ ተወዳዳሪዎችን እናበረታታለን፤ የሥራ ልምድ - 0 አመት ብዛት -25 የምዝገባ ሁኔታ፡- http://www.justice.gov.et በሚለው የተቋሙ ዌብሳይት ክፍት የሥራ ቦታ በሚለው ሥራ ባለው ማስፈንጠሪያ ወይም https://forms.gle/rWi1n6wi8HYYZubc7 በመጠቀም የሚጠይቀውን መረጃ በመሙላት እና ማስረጃዎችን በማያያዝ መመዝገብ ይቻላል። የምዝገባ ቀን፡- ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 30 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ፤ ማስታወሻ፡- ተወዳዳሪዎች ሲመዘገቡ ሊያሟሏቸው የሚገባቸው ሰነዶች፡- 1. ኢትዮጵያዊ መሆናችሁን የሚገልጽ መታወቂያ/ፓስፖርት እና ብሔራዊ መታወቂያ በpdf scan የተደረገ፤ 2. ዋና የትምህርት ማስረጃ (student copy) ጨምሮ በpdf scan የተደረገ ፤ አጠቃላይ የመመረቂያ አማካይ ውጤት CGPA እና የመውጫ ፈተና ውጤትን Exit Exam የሚገልጽ የትምህርት ማስረጃ፣ 3. ከሚኖሩበት አካባቢ ካለ የመንግስት ተቋም ወይም ከተመረቁበት የትምህርት ተቋም የመልካም ሥነ ምግባር ማስረጃ፣ ለበለጠ መረጃ ፡- በስራ ሠዓት በስልክ ቁጥር ፡- +251-15-15-7432 በመደወል፤ እንዲሁም በኢሜል አድረራሻ፡- mojprosecutorsadministration@justice.gov.et ወይም mojpublicprosecutorsa@gmail.com ላይ በመፃፍ ማግኘት ይችላሉ። የኢፌዲሪ ፍትሕ ሚኒስቴር

  • የእምነት ነፃነት እና የህግ ተጠያቂነት በኢትዮጵያ ሰሞኑን በማህበራዊ ሚዲያ በግል የእምነት ውሳኔዋ ምክንያት በአንዲት ሴት ላይ የተፈጸሙ የማስፈራሪያ እና የዛቻ መልእክቶች የብዙዎችን ትኩረት ስበዋል። ለመሆኑ የኢትዮጵያ ህግ ስለ እምነት ነፃነት እና በሰው እምነት ላይ ጣልቃ ስለመግባት ምን ይላል? 1. የእምነት ነፃነት ህገ-መንግስታዊ መብት ነው በኢፌዴሪ ህገ-መንግስት አንቀጽ 27 መሠረት ማንኛውም ሰው ማንኛውንም እምነት የመያዝ፣ የማመን ወይም የመቀየር ሙሉ መብት አለው። ማንም ሰው የያዘውን እምነት ወይም ሃይማኖት በኃይል ወይም በሌላ ሁኔታ እንዲቀበል ወይም እንዲለውጥ ማስገደድ የተከለከለ ነው። ባጭሩ ሃይማኖት መቀየር ወይም መምረጥ ፍጹም ግላዊ እና በህግ የተጠበቀ መብት እንጂ ወንጀል አይደለም። 2. በሰው እምነት ነጻነት ላይ ጣልቃ መግባት በወንጀል ያስጠይቃል በሰዎች ህይወት፣ አካል ወይም ደህንነት ላይ ስጋት መፍጠር በኢትዮጵያ የወንጀል ህግ መሠረት ያስቀጣል። በሳይበር ወይም በኢንተርኔት የሚፈጸም ዛቻ፦ ማስፈራሪያው በቴሌግራም፣ ፌስቡክ ወይም በሌሎች ማህበራዊ ሚዲያዎች የተሰራጨ ከሆነ፣ በኮምፒውተር ወንጀል አዋጅ ቁጥር 958/2008 መሠረት ተጨማሪ እና ከባድ የህግ ተጠያቂነትን ያስከትላል። 3. እምነትን ለጥላቻ አላማ ማሰራጨት በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ሰዎችን በሃይማኖታቸው፣ በብሔራቸው ወይም በማንነታቸው ምክንያት የሚደረግ የጥላቻ ቅስቀሳ፣ በጥላቻ ንግግር እና ሀሰተኛ መረጃን ለመቆጣጠር የወጣው አዋጅ ቁጥር 1185/2012 መሠረት በህግ ያስጠይቃል። ሲጠቃለል፣ ልዩነቶችን እና የተለያዩ እምነቶችን ማከበር የሰለጠነ ማህበረሰብ መገለጫ ነው። በግለሰቦች የግል የእምነት ነጻነት ላይ በማንኛውም መንገድ ጣልቃ መግባት የወንጀል ተጠያቂነትን ያስከትላል። ለተጨማሪ የሕግ መረጃዎች ቻናላችንን ይቀላቀሉ! ለወዳጅ ቤተሰብዎ ሼር በማድረግ አጋር ይሁኑ! 🔗 https://t.me/getuasnakew 📞 በ 0913771324 ላይ ይደውሉ!

  • መመሪያው በፍርድ ቤት ውድቅ ተደረገ‼ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የትምህርት ሚኒስቴር ያወጣውን «የአጠቃላይ ትምህርት ዘርፍ የትምህርት ቤቶች ፈቃድ አሰጣጥ እና እድሳት መመሪያ ቁጥር 992/2016» ውድቅ አደረገ። የሦስት ዳኞች ችሎት መመሪያው «ሕጋዊ ሥነ-ሥርዓት ሳይከተል የወጣ፣ ከሚኒስቴሩ ሥልጣን በላይ የሆነና ከበላይ ሕጎች ጋር የሚጋጭ» ሲል ብይን ሰጥቷል። ክሱ የተመሠረተው በሳንፎርድ ኢንተርናሽናል ትምህርት ቤት 132 ተማሪ ወላጆች ሲሆን፤ ትምህርት ቤቱ መመሪያውን ለመደበኛ ያልሆነ የክፍያ ጭማሪ እንደ ሕጋዊ መሣሪያ ተጠቅሞበታል ብለዋል። የወጣው መመሪያ በሀገር ውስጥና በውጭ ባለሀብቶች እንዲሁም የማኅበረሰብ ትምህርት ቤቶች ፈቃድና እድሳትን ለመደንገግ ያለመ እንደነበር የሚንበር ዘገባ አመልክቷል። #WasuMohammed video 👇Like + Follow👇 https://www.facebook.com/share/18ZGvgBVhp/?mibextid=wwXIfr ==================== ወቅታዊ እና የታመኑ መረጃዎች እንዲደርሱዎ  የቴሌግራም ቻናሉን join በማድረግ በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4 https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4 https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4

  • без подписи

  • ልብ የሚነካ ደብዳቤ‼ ኦሉሴጉን ኦባሳንጆ በ94 ዓመታቸው ለናይጄሪያውያን ልብ የሚነካ ደብዳቤ ጽፈዋል። ሰዎች ሕይወት ረጅም ናት ይላሉ፤ “ጊዜ አለህ፣ አትቸኩል” ይሉሃል። እኔ ግን አሁን የ94 ዓመት አረጋዊ ነኝ፤ በእርግጠኝነት ልነግራችሁ የምችለው ይህ ፍጹም ስህተት መሆኑን ነው። ሕይወት ረጅም አይደለችም፤ በቅጽበት የምታልፍ እንጂ። ይህችን ዓለም የምሰናበትበት ጊዜ እየቀረበ ሲመጣ፣ ጥቂት የሕይወት ትምህርቶችን ላካፍላችሁ ወደድኩ። ሀብት አጋብሻለሁ፣ ተሰሚነትን አትርፌያለሁ፣ ታዋቂነትንም አግኝቻለሁ፤ ዛሬ ግን እነዚህ ሁሉ በቤቴ ጥግ ላይ እንደተከመረ ትቢያ ይቆጠራሉ። አሁን እጄን ብዘረጋ፣ ከእነዚህ መካከል አንዳቸውም አብረውኝ አይጓዙም። አንደኛ ትምህርት፦ ነገሮች እስኪስተካከሉ አትጠብቅ ከሕይወቴ አብዛኛውን ክፍል ያሳለፍኩት በመጠበቅ ነበር። በትምህርት ቤት እያለሁ፣ እውነተኛው ሕይወት የሚጀምረው ከምረቃ በኋላ ይመስለኝ ነበር። ውትድርና ውስጥ በነበርኩበት ጊዜ፣ ቅዳሜና እሁድን እጓጓ ነበር። ትዳር ስመሰርት፣ ልጆቼ እስኪያድጉ እጠብቅ ነበር። እነሱ ሲያድጉ ደግሞ፣ ጡረታ የምወጣበትን ጊዜ መናፈቅ ጀመርኩ። እውነተኛው ሕይወት ወደፊት መቼም ያለ ይመስል፣ እያንዳንዱን ቀን እንደ ተራ መሻገሪያ ድልድይ ብቻ ነው ያየሁት። አሁን ግን ተረዳሁ፤ ሕይወት ማለት የመጨረሻው መድረሻ ሳትሆን፣ እራሱ አሁን የምንጓዘው ጉዞ ናት። ሁለተኛ ትምህርት፦ ወርቅ ምግብ አይሆንም ሀብት ለማከማቸት 50 ዓመታት ሙሉ ደክሜያለሁ። ሥራ ላይ ከማተኮሬ የተነሳ ከቤተሰቤ ጋር የማሳልፋቸውን ውድ ጊዜያት አጥቻለሁ። ትላልቅ ቤቶችን፣ ውድ መኪናዎችንና የቅንጦት ዕቃዎችን ገዝቻለሁ፤ ነገር ግን የጉዞዬ ማብቂያ ላይ ስቃረብ፣ ከእነዚህ ውስጥ አንዳቸውም ሊከተሉኝ እንደማይችሉ ተገነዘብኩ። አንድ ቀን ልጄ ያገኘችውን አንዲት ጥቃቅን ነፍሳት እንዳይላት ወደ አትክልት ስፍራው የጠራችኝ ዕለት ሁሌም ትዝ ይለኛል። እኔ ግን “አሁን አልችልም፣ ሥራ ላይ ነኝ” አልኳት። ያንን ያመለጠኝን አፍታ ሳስብ እስከ ዛሬ ድረስ ቁጭቱ ይብሰኛል። ሦስተኛ ትምህርት፦ በልብህ ውስጥ ያለውን ግንብ አፍርስ በወጣትነቴ መራራት ወይም ይቅርታ መጠየቅ የድክመት ምልክት ይመስለኝ ነበር። አንድ ወንድም ነበረኝ። አንድ ቀን በትንሽ ነገር ተጣላን፤ እንዲያውም ጠቡ በምን እንደተጀመረ አሁን ላይ ትዝ እንኳን አይለኝም። እሱ መጥቶ ሰላም እስኪለኝና እስክንታረቅ ድረስ እልህ ይዤ ጠበቅኩ። ዓመታት አለፉ። ከዚያም በአንድ ወቅት፣ እሱ ማረፉን የሚገልጽ የስልክ ጥሪ ደረሰኝ። ያኔ ነው እኔ ትክክል ብሆንም፣ ወንድሜን ግን ለዘላለም እንዳጣሁት የተረዳሁት። የምትወዱት ሰው ካለ፣ ዛሬውኑ ንገሩት። ስህተት ሠርታችሁ ከሆነ፣ ዛሬውኑ ይቅርታ ጠይቁ። ነገ ለማንኛችንም ዋስትና የለውም። አራተኛ ትምህርት፦ ፍርሃት ጥላ ብቻ ነው ደራሲ ለመሆን ስመኝ ዕድሜዬ 22 ዓመት ነበር። ማስታወሻዎቼ በሕልሞችና በታሪኮች የተሞሉ ነበሩ። ነገር ግን ሰዎች ይሳቁብኛል ወይም አልቀናኝም በሚል ፍርሃት ያንን መጽሐፍ ሳልጽፈው ቀረሁ።አሁን እጆቼ ይንቀጠቀጣሉ፣ ዓይኖቼም ፈዝዘዋል። ያ መጽሐፍ ግን አሁንም በውስጤ እንዳለ ቀርቷል። በሕይወት ውስጥ ትልቁ አሳዛኝ ነገር ሞት አይደለም፤ በሕይወት እያለን ቀብረናቸው የምንቀራቸው ሕልሞቻችን እንጂ። ልባችሁ የሚፈልገውን ነገር ወደፊት አታስተላልፉት። ዛሬውኑ ጀምሩ። ባይሳካላችሁ እንኳ፣ ቢያንስ “ሞክሬው ነበር” ማለት ትችላላችሁ። የዘመኔ ሰዓት የምታሰማው ድምፅ አሁን በጆሮዬ ላይ እየጎላ መጥቷል። ጭንቀትን፣ ኩራትንና ፍርሃትን ሁሉ አውርጄ ጥያለሁ። እናንተ ግን አሁንም በሕይወት አላችሁ። ሌላ አዲስ ቀን ተሰጥቷችኋል። በከንቱ አታባክኑት። እጆቻችሁን እዩ። ጣቶቻችሁን አንቀሳቅሱ። የአተነፋፈሳችሁን ምት ስሙ።ይህ ሁሉ ትልቅ በረከት ነው። ሕይወት ምን ያህል ውብ መሆኗን ለመረዳት 94 ዓመት እስኪሞላችሁ ድረስ አትጠብቁ።አሁንን ኑሩት። via Hassen Mustefa video 👇Like + Follow👇 https://www.facebook.com/share/18ZGvgBVhp/?mibextid=wwXIfr ==================== ወቅታዊ እና የታመኑ መረጃዎች እንዲደርሱዎ  የቴሌግራም ቻናሉን join በማድረግ በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4 https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4 https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4

  • без подписи

  • без подписи

  • без подписи

  • የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የባንኮች የብድር ገደብን ሙሉ በሙሉ አነሳ። 👉 ላኪዎች ከሚያገኙት የውጭ ምንዛሬ ግኝት ላይ ለባንኮች እንዲሸጡ የሚያስገድደው የውጭ ምንዛሬ ድርሻ ከነበረበት 50 በመቶ ወደ 30 በመቶ ዝቅ እንዲል ተደርጓል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የገንዘብ ፖሊሲ ኮሚቴ ሐምሌ 6 ቀን 2018 ዓ.ም. ባካሄደው 7ኛ ስብሰባው፣ የተለያዩ የፖሊሲ ምክረ ሃሳቦችን አቅርቦ ማጸደቁን አሳውቋል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የገንዘብ ፖሊሲ ኮሚቴ የዋጋ ንረትን ለመቆጣጠርና ወደ ነጠላ አሃዝ ለማውረድ ያለመ አዳዲስና ወሳኝ የፖሊሲ ውሳኔዎችን ማሳለፉን በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ አሳውቋል። ኮሚቴው ዓለም አቀፍ የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ በሀገር ውስጥ ምርቶች ላይ የሚያሳድረውን ጫና ከግምት ውስጥ በማስገባት፣ ጥብቅ የገንዘብ ፖሊሲ ተጠናክሮ እንዲቀጥል መወሰኑን ገልጿል። እስካሁን ባንኮች በሚሰጡት ብድር ላይ ተጥሎ የነበረው ቀጥተኛ የብድር ዕድገት ገደብ ሙሉ በሙሉ እንዲነሳ ተወስኗል። በባንኮች ላይ የብድር ገደብ ውሳኔ ተጥሎ የነበረው ኢኮኖሚው በወለድ ምጣኔ ላይ ወደተመሠረተ የገንዘብ ፖሊሲ ሥርዓት እስኪሸጋገር እንደነበር በማስታወስ ውሳኔው ግቡን መምታቱን ጠቅሷል። የብድር ገደብ መነሳቱን ጥብቅ የሆነ የፖሊሲ እርምጃ በማስፈለጉ ፣ ብሔራዊ ባንክ የፖሊሲ ወለድ ምጣኔውን በ1.0 በመቶ በማሳደግ ከነበረበት 15 በመቶ ወደ 16 በመቶ ከፍ እንዲል ወስኗል። የወጪ ንግድ ተወዳዳሪነትን ለመጨመርና በገበያው ላይ እምነት ለመገንባት፣ ላኪዎች ከሚያገኙት የውጭ ምንዛሬ ግኝት ላይ ለባንኮች እንዲሸጡ የሚደረገው የውጭ ምንዛሬ ድርሻ ከነበረበት 50 በመቶ ወደ 30 በመቶ ዝቅ እንዲል ተደርጓል። ይህም ላኪዎች ካገኙት የውጭ ምንዛሬ 70 በመቶውን እንዲጠቀሙ ዕድል ይሰጣል። ከአስመጪዎች ጋር የተያያዙ ወጪዎችን ለመቀነስና የዋጋ ንረትን ለመግታት፣ ብሔራዊ ባንክ በውጭ ምንዛሬ ግብይት ላይ የሚወስደው የ2.5 በመቶ ኮሚሽን ወደ 1.5 በመቶ እንዲቀንስ ተወስኗል። የብድር መስፋፋት በዋጋ ንረት ላይ አሉታዊ ጫና እንዳያሳድር፣ ብሔራዊ ባንክ የባንኮችን የብድርና ቁጠባ ጥምርታ (loan-to-deposit ratio) መሠረት ያደረገ የተለየ የመጠባበቂያ ተቀማጭ ሥርዓት ተግባራዊ እንደሚያደርግ አስታውቋል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ አዲስ አበባ ሃምሌ 6 ቀን 2018 ዓ/ም @tikvahethiopia

  • የአዲስ አበባ ከተማ የኮንስትራክሽን ማዕድናት ቁፋሮና አስተዳደርን የሚመራ አጠቃላይ መመሪያ ወጣ። የአዲስ አበባ ከተማ አካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን በከተማዋ ክልል ውስጥ የሚካሄደውን የኮንስትራክሽን ማዕድናት ፍለጋ፣ ምርት እና ስርጭት በዝርዝር የሚቆጣጠር አዲስ መመሪያ አወጣ። "የኮንስትራክሽን ማዕድን ፈቃድ አፈጻጸም መመሪያ ቁጥር 191/2018" የተሰኘው ይህ ሰነድ፣ ከዚህ ቀደም በዘርፉ ይታዩ የነበሩ የአሰራር ክፍተቶችን በመድፈን ግልጽነትና ተጠያቂነት የሰፈነበት ሥርዓት ለመዘርጋት ያለመ ነው ይላል። መመሪያው ዋና ዋና የፈቃድ ዓይነቶችን የለየ ሲሆን፣ እነሱም አምርቶ የመሸጥ፣ ለመንግሥት ልማት ሥራዎች አምርቶ የመጠቀም፣ ምርት ለማንሳት የሚሰጥ ፈቃድ፣ ከስራው ጋር ተዘማጅነት ያላቸውን ማሽኖች መትከያ ፈቃድ እንዲሁም ሌሎች ፈቃዶች ይገኙበታል። ፈቃድ የሚሰጥባቸው የኮንስትራክሽን ማዕድን አይነቶችም በዝርዝር የተቀመጡ ሲሆን ፦ - ጥቁር ድንጋይ፣ - ገረጋንቲ፣ - ቀይ አሸዋ፣ - ቀይ አፈር፣ - ነጭ የግንብ ድንጋይ (ጥርብ ድንጋይ)፣ - የወንዝ አሸዋ፣ - ጠጠር እና ሌሎችም ተመሳሳይ ማዕድናት ናቸው ተብሏል። በጥቁር ድንጋይ ማምረት ላይ የተሰማሩ አልሚዎች እስከ 5 ዓመት፣ በገረጋንቲ፣ አሸዋና ነጭ ድንጋይ ላይ የተሰማሩ ደግሞ እስከ 2 ዓመት የሚቆይና በየዓመቱ የሚታደስ ፈቃድ ይሰጣቸዋል። ህጋዊ የመሬት ባለይዞታ የሆነ ለንግድ ላልሆነ ዓላማ ለግንባታ ብቻ በግል ይዞታው ውስጥ ያለ ክፍያና ፍቃድ ሳያስፈልገው አምርቶ መጠቀም ይችላል። ለንግድ ዓላማ ማዋል ሲፈልጉ ግን በሽርክና ወይም በማህበር ተደራጅተው ፈቃድ እንዲያወጡ ይደረጋል። በመንግሥት ፕሮጀክቶች ላይ የተሰማሩ የግል ድርጅቶችም ከቀጣሪ መሥሪያ ቤታቸው የድጋፍ ደብዳቤ በማቅረብ ማዕድን ማውጣት የሚችሉ ሲሆን፣ እንደማንኛውም አልሚ የሮያሊቲ ክፍያ የመክፈል ግዴታ አለባቸው። ለአካባቢ ደህንነት ሲባል ባለሥልጣኑ ማዕድን ማውጣት የተከለከለባቸውን ቦታዎች በግልጽ አስቀምጧል። በዚህም መሠረት፦ • ከመኖሪያ መንደሮችና ከኢንዱስትሪ ፓርኮች በ500 ሜትር ራዲየስ ውስጥ፣ • ከከፍተኛ የኃይል ማስተላለፊያ መስመሮች በ25 ሜትር ራዲየስ ውስጥ፣ • ከወንዝ ዳርቻዎች በ30 ሜትር ራዲየስ ውስጥ ቁፋሮ ማከናወን በጥብቅ የተከለከለ ነው። በተጨማሪም ከመቃብር፣ከፓርክ ፣ከመሰረተ ልማት፣ ከሃይማኖታዊ ስፍራዎችና ከብሔራዊ መታሰቢያዎች ከቆሙባቸው ቦታዎች አቅራቢያ ፈቃድ አይሰጥም። ማንኛውም አልሚ ፈቃድ ለማግኘት የአካባቢ ተጽዕኖ ግምገማ (EIA) እና የአዋጭነት ጥናት ማቅረብ ይኖርበታል። በተጽዕኖ ግምገማ ጥናት መሰረት በአካባቢው ላይ ሊደርስ የሚችለውን ጉዳት ለማስተካከል አስፈላጊ ነው የተባለውን የፋይናንስ ፍላጎት፣ በመስሪያ ቤቱ ስም በተከፈተ የባንክ ሂሳብ ዋስትና ማስያዝ ግዴታ ሆኖ ተጥሏል። አልሚዎች በየሦስት ወሩ የሥራ አፈጻጸም ሪፖርትና በየወሩ የገቢ ሪፖርት ለባለሥልጣኑ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል። መመሪያው የፈቃድ ባለቤትነትን በውርስ፣ በሽያጭ ወይም በፍርድ ቤት ትዕዛዝ ማስተላለፍ እንደሚቻል ቢፈቅድም፣ ፈቃዱን የሚረከበው አካል ከማንኛውም ያልከፈለው ዕዳ እና ኪሳራ ነፃ መሆኑ መረጋገጥ አለበት። አንድ አልሚ ተጨማሪ ቦታ ማስፋፋት የሚችለውም ቀደም ሲል ከተሰጠው ቦታ ቢያንስ 70 በመቶ የሚሆነውን አልምቶ ማጠናቀቁ ሲረጋገጥ ብቻ ነው። ሕገ-ወጥ ቁፋሮን ለመከላከል የክፍለ ከተማ አካባቢ ጥበቃ ጽሕፈት ቤቶች የቅርብ ክትትል እንዲያደርጉ ሥልጣን ተሰጥቷቸዋል። አልሚው የተጣለበትን ግዴታ ካላከበረ፣ ተደጋጋሚ ሕገ-ወጥ ድርጊት ከተገኘበት፣ ወይም ማዕድኑ ሙሉ በሙሉ ካለቀ ፈቃዱ የሚሰረዝ ይሆናል። @tikvahethiopia

  • የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት የወንጀል ሕግ ትርጉም ውሳኔዎች ስብስብ (በየጉዳዮች የተደራጀ ልዩ እትም) ታትሞ ወጥቷል። ‎ ‎ይህንን ህትመት 4 ኪሎ በሚገኘው በብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ዋና መስሪያ ቤት እንዲሁም ልደታ ፍርድ ቤት ቅጥር ጊቢ ውስጥ በሚገኘው የብርሃንና ሰላም ሽያጭ መደብር የሚያገኙ ሲሆን ሶፍት ኮፒውን እዚሁ አያይዘናል። የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን ይቀላቀሉ 👉ዌብ ሳይት ↠ https://www.fsc.gov.et/ 👉ፌስቡክ ↠ https://web.facebook.com/FSCEthiopia 👉ትዊተር (ኤክስ) ↠ https://x.com/federalsupreme1 ሊንክድኢን ↠ https://tinyurl.com/supereme-court-of-ethiopia 👉ቴሌግራም ↠ https://t.me/fscethiopiaPR 👉ዋትስአፕ ↠ https://tinyurl.com/fscethiopia 👉ዩቲዩብ ↠ https://www.youtube.com/@fscethiopia 👉ቲክቶክ ↠ https://tiktok.com/@federal.supreme.court

  • የአዋጅ ቁጥር 1261/2013 አንቀጽ 22(1) የምክር ቤቱን ውሳኔዎች «የመጨረሻና አስገዳጅ» ማድረጉ፣ እነዚህ ውሳኔዎች በሀገሪቱ የሕግ ተዋረድ ፒራሚድ ውስጥ ያላቸውን ከፍተኛ ቦታ በግልጽ ያሳያል። ምክር ቤቱ አንድን ሕግ አስገዳጅ በሆነ ሁኔታ የመተርጎም ወይም ከተፈጻሚነት ውጭ የማድረግ ሥልጣን አለው ማለት፣ የእርሱ ውሳኔዎች በሌሎች መደበኛ ሕጎች፣ አዋጆች፣ ደንቦችና መመሪያዎች ሊሻሩ፣ ሊሻሻሉ ወይም ችላ ሊባሉ እንደማይችሉ ማረጋገጫ ነው። ስለዚህ፣ የፌዴሬሽን ምክር ቤት የሚሰጠው ውሳኔ፣ ራሱን ሕገ-መንግሥቱን ለመተርጎምና ለመጠበቅ የሚወጣ በመሆኑ ከሕገ-መንግሥቱ በታች የሚሰለፍ ሲሆን፣ በሌላ በኩል ደግሞ ሁሉንም የፌዴራልና የክልል አዋጆች፣ ደንቦችና መመሪያዎች የመሻርና የመግራት ፍጹም አስገዳጅነት ስላለው ከሌሎች ሁሉም ዓይነት ሕጎች በላይ ሆኖ በሕግ ተዋረድ ማማ ላይ ይቀመጣል። 🛑የፌደራሉ የገጠር መሬት አስተዳደር እና አጠቃቀም አዋጅ ቁጥር 1324/2016 አንቀጽ 64(2) እጣ ፈንታ ምንድን ነው? ✅በገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም አዋጅ ቁጥር 1324/2016 አንቀጽ 64(2) እና በፌዴሬሽን ምክር ቤት በመዝገብ ቁጥር 140/2017 (በመስከረም 28/2018 ዓ.ም በተሰጠ) ውሳኔ መካከል ግልጽ የሆነ የሕግ ይዘት መጋጨት መኖሩን መገንዘብ ይቻላል። አዋጁ የአንድ አርሶ አደር መሬት ያለአግባብ በሌላ ሰው ከተወሰደበት መብቱን ለማስከበር ክስ ማቅረብ የሚችለው በ15 ዓመት የይርጋ ጊዜ ውስጥ ብቻ እንደሆነና ካልሆነ ግን መብቱ በይርጋ እንደሚታገድ በግልጽ ይደነግጋል። በአንጻሩ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ያስተላለፈው ውሳኔ መሬት የማይሸጥ፣ የማይለወጥ የመንግሥትና የሕዝብ ሀብት በመሆኑ፣ አንድ አርሶ አደር በሕጋዊ መንገድ ያገኘው የመሬት ይዞታ መብት ለረጅም ጊዜ በሌላ አካል ተይዞ በመቆየቱ (በይርጋ) ሊታገድ እንደማይችልና ሕገ-ወጥ ይዞታም በይርጋ ሊጸድቅ እንደማይችል በማስገንዘብ የይርጋ መቃወሚያውን ፍጹም ውድቅ አድርጎታል። በኢትዮጵያ የሕግ ተዋረድ ሥርዓት መሠረት፣ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ሕገ-መንግሥታዊ ትርጉም ውሳኔዎች ከአዋጅ በላይ የበላይነትና አስገዳጅነት ያላቸው በመሆኑ፣ በዚህ የሕግ መጋጨት ውስጥ የአዋጁ ድንጋጌ ተፈጻሚነት ሳይኖረው ቀርቶ የምክር ቤቱ ውሳኔ የጸና እና የበላይ ሆኖ ይቀጥላል። ✅ይህንን የምክር ቤቱን የውሳኔ ልዕልና ይበልጥ የሚያጠናክረውና ሕጋዊ ክብደቱን ከፍ የሚያደርገው ሌላው መሠረታዊ ነጥብ፣ ምክር ቤቱ ውሳኔውን የሰጠው አዋጅ ቁጥር 1324/2016 በሥራ ላይ ከዋለ በኋላ መሆኑ ነው። አዋጁ ቀድሞ በ2016 ዓ.ም የወጣ ቢሆንም፣ ምክር ቤቱ ጉዳዩን መርምሮ የመጨረሻ ውሳኔውን የሰጠው መስከረም 28/2018 ዓ.ም በመሆኑ፣ ምክር ቤቱ ውሳኔውን ሲያሳልፍ የአዋጁን መኖርና ይዘት ከግምት ውስጥ አስገብቶ እንደሆነ በሕግ ግምት ይወሰዳል። ይህም ማለት ምክር ቤቱ የአዋጁን የ15 ዓመት የይርጋ ገደብ ድንጋጌ ወደ ጎን በመተው፣ የመሬት ይዞታ መብት በይርጋ ፈጽሞ ሊታገድ እንደማይችልና ሕገ-ወጥ ይዞታም በይርጋ ሊጸድቅ እንደማይችል የሰጠው ውሳኔ የአዋጁን ይዘት በግልጽ የሚሽር (Overriding) ሕገ-መንግሥታዊ ኃይል አለው። በመሆኑም፣ ከአዋጁ መውጣት በኋላ የተሰጠው ይህ አስገዳጅ ውሳኔ የአዋጁን ድንጋጌ ውድቅ በማድረግ የአርሶ አደሩን ሕገ-መንግሥታዊ የመሬት ባለመብትነት መብት ያለ ምንም የጊዜ ገደብ የሚያስከብር በመሆኑ የሕግ ትርጉም የበላይነቱ ሙሉ በሙሉ የተረጋገጠ ነው።

  • «በሕገወጥ መንገድ የተያዘ የመሬት ይዞታን አስመልክቶ በፌደራል የመሬት አዋጅ ቁጥር 1324/2016 የተቀመጠው የ15 ዓመት የይርጋ ገደብ እና የፌዴሬሽን ምክር ቤት “መሬት በይርጋ አይታገድም” ውሳኔ ተፈጻሚነት ወሰን ክርክር» የትኛው የበላይ ነው? (ጠበቃ አደም ሰይድ ከማል ✅✅✅✅✅✅✅✅✅✅✅✅✅✅ መግቢያ በማንኛውም ሕገ-መንግሥታዊ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ውስጥ የሕግ የበላይነትን ማረጋገጥና የሕጎችን ተፈጻሚነት ወጥነት ባለው መልኩ መምራት የሚቻለው ግልጽና ሥርዓታዊ የሆነ የሕግ ተዋረድ (Hierarchy of Laws) ሲኖር ብቻ ነው። በኢፌድሪ ሕገ-መንግሥታዊ ሥርዓት ውስጥ ደግሞ ይህንን የሕጎች ልዕልና የመጠበቅ፣ የመተርጎምና የመጨረሻ ውሳኔ የመስጠት ፍጹም ሥልጣን ለፌዴሬሽን ምክር ቤት ተሰጥቷል። ይህ የሕግ ትንታኔ፣ የኢፌድሪ ሕገ-መንግሥትን እና የፌዴሬሽን ምክር ቤትን ሥልጣን ለመደንገግ የወጣውን አዋጅ ቁጥር 1261/2013 መሠረት በማድረግ፣ የምክር ቤቱ ውሳኔዎች ከሕገ-መንግሥቱ በታች፣ ነገር ግን ከማናቸውም የፌዴራልና የክልል አዋጆች፣ ደንቦችና መመሪያዎች በላይ ያላቸውን ማዕከላዊ ቦታ በጥልቀት ይፈትሻል። በተጨማሪም፣ ይህንን የሕግ የበላይነት መርህ በተግባር ለማሳየት፣ በገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም አዋጅ ቁጥር 1324/2016 ላይ በተቀመጠው የ15 ዓመት የይርጋ ገደብ እና ምክር ቤቱ በመዝገብ ቁጥር 140/2017 ባሳለፈው "የመሬት መብት በይርጋ አይታገድም" በሚለው አስገዳጅ ውሳኔ መካከል የተፈጠረውን ግልጽ የሕግ መጋጨት በመተንተን፣ የምክር ቤቱ ውሳኔ በአዋጆች ላይ ያለውን የመሻርና የበላይ የመሆን መዋቅራዊ ኃይል በማስረጃ ያሳያል። መልካም ንባብ 🛑ከሕገመንግስቱ አንቀጽ 9(1) አንጻር ሲመዘን በኢፌድሪ ሕገ-መንግሥት አንቀጽ 9(1)ሥር የተቀመጠው የሕገ-መንግሥቱ የበላይነት የሚደነግገው ድንጋጌ፣ ሕገ-መንግሥቱን የሀገሪቱ የሕግ ሥርዓት ከፍተኛ ማማ እና የሁሉም ሕጎች ሕጋዊነት መነሻ (Grundnorm) ያደርገዋል። በዚህ ሕገ-መንግሥታዊ ሥነ-ሕንጻ ውስጥ፣ በአንቀጽ 82(1) መሠረት ለፌዴሬሽን ምክር ቤት የተሰጠው ፍጹም የትርጉም ሥልጣን፣ ከሕገ-መንግሥቱ ጽሑፍ ውጭ የሚቆም ሳይሆን፣ ራሱን የሕገ-መንግሥቱን ሕያው መንፈስና ድብቅ ፍላጎት የመግለጥ መዋቅራዊ መሣሪያ ነው። ✅ በመሆኑም፣ ምክር ቤቱ የሚሰጣቸው ሕገ-መንግሥታዊ የትርጉም ውሳኔዎች ከራሱ ከሕገ-መንግሥቱ ጽሑፍ ጋር ተዋሕደውና አንድ አካል ሆነው (Constitutionalized) የሚጸኑ በመሆናቸው፣ በባሕርያቸው የሕገ-መንግሥታዊ ልዕልና ተጋሪዎች ናቸው። የትርጉም ውሳኔው የሕገ-መንግሥቱ አካል እስከሆነ ድረስ፣ ከአዋጅ በላይ መሆኑን መከራከር የሕገ-መንግሥቱን የበላይነት ከመቀበል የሚመነጭ ምክንያታዊና ቀጥተኛ የሕግ መደምደሚያ ነው። ​✅ የታችኞቹን ሕጎች ሕጋዊ ሕልውና የመወሰን እና የመሻር ፍጹም ሥልጣን በሕግ ተዋረድ (Hierarchy of Laws) መርህ መሠረት፣ የአንድ ሕግ ደረጃ የሚለካው የታችኛውን ሕግ ይዘት የመግራት፣ የመሻር ወይም የሕልውናውን ወሰን የመወሰን አቅም ሲኖረው ብቻ ነው። በአዋጅ ቁጥር 1261/2013 አንቀጽ 5(2) እና 22(1) ላይ በግልጽ እንደተደነገገው፣ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ውሳኔዎች በማንኛውም የፌዴራልም ሆነ የክልል ሕግ አውጪ አካላት የሚወጡ አዋጆችን፣ ደንቦችንና መመሪያዎችን ሕገ-መንግሥታዊ ባለመሆናቸው (Unconstitutionality) ብቻ ሽሮ ከተፈጻሚነት ውጭ የማድረግ ፍጹም አስገዳጅነት አላቸው። አንድ የሕግ መተርጎም ውሳኔ መደበኛውን አዋጅ የመሻር እና የመግራት የቁጥጥር ኃይል ካለው፣ ያ ውሳኔ ከአዋጁ በላይ የላቀ መዋቅራዊና የዳኝነት ልዕልና እንዳለው ማረጋገጫ ነው። ስለሆነም፣ አዋጆች በሕግ አውጪው አካል የሚፈጠሩ መደበኛ ሕጎች ሲሆኑ፣ የምክር ቤቱ ውሳኔ ግን የእነዚህን አዋጆች ሕጋዊ ሕልውና የሚወስን የሕገ-መንግሥቱ የበላይነት መገለጫ በመሆኑ፣ በሕግ ተዋረድ ፒራሚድ ውስጥ ከአዋጆች በላይ ሆኖ በከፍተኛው ማማ ላይ ይሰለፋል። ✅ፌዴሬሽን ምክር ቤት ውሳኔዎች በሕግ ተዋረድ ላይ ያላቸው ቦታ፡ በኢፌድሪ ሕገ-መንግሥታዊ ሥርዓት ውስጥ የሕግ የበላይነትን እና ሕገ-መንግሥታዊ ልዕልናን (Constitutional Supremacy) ለማረጋገጥ ለፌዴሬሽን ምክር ቤት የተሰጠው የሕገ-መንግሥት ትርጉም ሥልጣን መሠረታዊ ምሰሶ ነው። በኢፌድሪ ሕገ-መንግሥት አንቀጽ 62(1) እና 83(1) ላይ በግልጽ እንደተደነገገው፣ ሕገ-መንግሥቱን የመተርጎምና በማንኛውም ሕገ-መንግሥታዊ ክርክር ላይ የመጨረሻ ውሳኔ የመስጠት ሥልጣን የዚሁ ምክር ቤት ነው። ይህንን ሕገ-መንግሥታዊ ሥልጣን ይበልጥ ለማስፈጸም በወጣው አዋጅ ቁጥር 1261/2013 አንቀጽ 4(1) እና 5(1) ሥር የምክር ቤቱ የትርጉም ሥልጣን በድጋሚ የተረጋገጠ ሲሆን፣ በአዋጁ አንቀጽ 22(1) ላይ ደግሞ ምክር ቤቱ የሚሰጠው የመጨረሻ ውሳኔ «አስገዳጅ» መሆኑ ተደንግጓል። ከተጠቀሱት ሕጋዊና ሕገ-መንግሥታዊ ማዕቀፎች የምንረዳው፣ የምክር ቤቱ ውሳኔዎች ከመሠረታዊው ሕገ-መንግሥት ቀጥሎ፣ ነገር ግን በሀገሪቱ ውስጥ ከሚወጡ ማናቸውም የሕግ ዓይነቶች በላይ የበላይነትና የመጨረሻነት ባሕርይ የተጎናጸፉ መሆናቸውን ነው። ✅የፌዴሬሽን ምክር ቤት ውሳኔዎች ከራሱ ከሕገ-መንግሥቱ በታች የሚሰለፉበት ምክንያት የምክር ቤቱ የዳኝነት ሥልጣን ምንጭና መነሻ ራሱ ሕገ-መንግሥቱ በመሆኑ ነው። ምክር ቤቱ አዲስ ሕገ-መንግሥታዊ ድንጋጌዎችን የመፍጠር ወይም ነባሩን የመለወጥ የሕግ አውጪነት ሥልጣን የሌለው ሲሆን፣ ተግባሩ የሕገ-መንግሥቱን መንፈስ፣ መርሆዎችና ፍላጎቶች መግለጥና ማብራራት ብቻ ነው። ስለሆነም፣ በአዋጅ ቁጥር 1261/2013 አንቀጽ 5(2) ላይ እንደተመለከተው፣ ምክር ቤቱ በማንኛውም የትርጉም ሂደት ውስጥ የሕገ-መንግሥቱን የበላይነት የመጠበቅ ግዴታ ያለበት በመሆኑ፣ የእርሱ ውሳኔዎች ምንጊዜም ከሕገ-መንግሥቱ ጽሑፍና መሠረታዊ መርሆዎች በታች ይገዛሉ። ✅ውሳኔዎቹ የሕገ-መንግሥታዊ ትርጉም ውጤቶች እንደመሆናቸው መጠን፣ ከሕገ-መንግሥቱ ጋር ተስማምተውና ተዋህደው የሚኖሩ እንጂ ከራሱ ከሕገ-መንግሥቱ በላይ ሊሆኑ አይችሉም። ✅በሌላ በኩል፣ የምክር ቤቱ ውሳኔዎች በፌዴራልም ሆነ በክልል ደረጃ ከሚወጡ ከማናቸውም ሌሎች ሕጎች በላይ የመሆናቸው ምስጢር፣ ውሳኔዎቹ ያላቸው የቁጥጥርና የመሻር ፍጹም ሥልጣን ነው። አዋጅ ቁጥር 1261/2013 በአንቀጽ 2(3) ሥር «ሕግ» የሚለውን ቃል ሲተረጉም በፌዴራልም ሆነ በክልል ሕግ አውጪ አካላት የሚወጡ አዋጆችን፣ ደንቦችን፣ መመሪያዎችንና የጸደቁ ዓለም አቀፍ ስምምነቶችን እንደሚያካትት አስቀምጧል። የአዋጁ አንቀጽ 5(2) እና አንቀጽ 7(2) ደግሞ እነዚህ ማናቸውም ሕጎች፣ ልማዳዊ አሠራሮች ወይም የመንግሥት ባለሥልጣናት ውሳኔዎች ከሕገ-መንግሥቱ ጋር የሚቃረኑ ሆነው ሲገኙ፣ የምክር ቤቱ የመጨረሻ ውሳኔ «ተፈጻሚ እንዳይሆኑ» የማድረግ ፍጹም ሥልጣን እንዳለው ይደነግጋል። አንድን ሕግ ይዘቱን መርምሮ ሕገ-መንግሥታዊ ያልሆነ (Unconstitutional) በማለት ውድቅ የሚያደርግ ውሳኔ፣ በባሕርዩ ከተሻረውም ሆነ በሥራ ላይ ካለው ሕግ በላይ የበላይነት አለው፤ ምክንያቱም የታችኞቹን ሕጎች ሕጋዊ ሕልውና የሚወስን በመሆኑ ነው።