- Последний пост
- 10 авг.
- Последнее чтение
- 13 авг.
- Постов за неделю
- 2
- Всего постов
- 20
- Тип
- открытый
- Язык
- ti
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 68
- 1/48двое суток
- 77
- 1/72трое суток
- 84
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
በሁለት sim ማድረግም ይቻላል😉✌️
9282 ላይ MZ 33 ብላችሁ በsms vote አርጉ national competition ነውና ድምፃቹ ያስፈልገኛል ለምታውቋቸውም share አርጉላቸው 🙏
ስንት አለፍኩኝ ስቄ ስንቱን ተውኩኝ ንቄ በጆሮዬ በኩል ልቤ ድረስ አልፎ፤ ስንት ንቀት ጎዳኝ ከጎልያድ ገዝፎ፤ ስንቱ አውጥቶ ጣለኝ እንደሰባራ ገል፤ ከእንግዲህ ስለሰው ራሴን አልታገል፤ ማንነት አልቀይር አፈር የለበሰን ዛጎል መልኬን ላውጣው፤ ባይዋጥላቸው ምንድነው የማጣው? አሁንስ ምን አለኝ? ምን ቀረኝ ከእነርሱ? አቤት ሰው ምላሱ! እንኳን ተፈጣሪ የሚሞትበትን ጊዜ ቀን ቆጣሪ ከፈጠረው ሳይቀር ይፈልጋል እንከን፤ ታዲያ ለምን ልብከን? ደልቶኝ ልኑር አቦ! ወዳማረኝ ልፍሰስ ደስ ያለኝን ልንካ፤ ይህም ካወበገነህ በል ያዝ ገመድ እንካ፤ ታነቅ! አይጎርብጥህ አንተን ያወኩት፣ ያመንኩት፤ አንድ እድሌን ልኑር እኔ እንደፈለግኩት። 🖋ON
በትንሽ ትልቁ መበሳጨት ከጀመረ ከረምረም ብሏል በጣም ይወዳት እንደነበር አስታውሳለሁ።አሁን ግን ተለያይተዋሉ። የሷ ጉዳይ ሊቆርጥለት አልቻለም። ትዝ ይለኛል ከወራቶች በፊት ስለሷ ሲያወራልኝ ፊቱ በደስታ ያበራ ነበር። አንዳንዴማ መልአክ ነው እንዴ የወደደው እስክል ድረስ በመልካም ጎኗ እንከን የለሽ አድርጎ ሲስላት ከርሟል። ዛሬ በዛው አፉ ስለሷ መጥፎነት ሲያወራ ለሰማው ሰው ጤንነቱን መጠራጠሩ አይቀሬ ነው። ኧረ አስርን ተጫወት (ዛሬ ብቻ pool ስንጫወት ለሶስተኛ ጊዜ ሚጫወተውን ቁጥር እየነገርኩት ነው።) ምን እየሆንክ ነው ቆይ? “ተወኝ ባክህ!” አሁንም እሷ ናት? ለምን ልትረሳት አትሞክርም ግን ፈታ እንድትል መሰለኝ እንደ ጦስ ዶሮ በየ game zone'ኡ አብሬህ ስሽከረከር ምውለው። ለኔም አስብልኝ እንጂ በቃ አልፈል.... “አዎ አልፈልግህም ብላኛለች። አዎ እንደማትወደኝ ለመናገር ራሱ ለደቂቃ አላሰበችም። አዎ ለተራ ጓደኞቿ የምትሰጠውን ቦታ እንኳን አትሰጠኝም። ሁሉንም አውቃለሁ መደጋገም አያስፈልግም።” ልታለቅስ ባልሆነ ምን ሆነሃል እንዴ እኔ አንተን እንዲህ አላውቅህም። ወደራስህ ተመለስ እንጂ... “ያልሞከርኩ ነው ሚመስልህ? ለመርሳት፣ ለመሸሽ ፣ለመተው እ? ከዚህ ነገር ውስጥ ለመውጣት ያልቧጠጥኩት ያልፈነቀልኩት ድንጋይ የለም ግን ደሞ አልቻልኩም። ልረሳት አልቻልኩም ድምጿን እና ሳቋን ከጭንቅላቴ ማስወጣት አልቻልኩም። ማታ ተኝቼ እንቅልፍ እስኪወስደኝ የማስበው ስለሷ ነው። ነግቶ ስነቃም መጀመሪያ ሀሳቤ ላይ የምትመጣው ሰው እሷ ናት። በሁሉም ሁኔታዎቼ ውስጥ እሷ አለች። ለወራቶች ያለማቋረጥ ናፍቄያታለሁ...” እኮ ራስህን ከመጉዳት ውጪ ምን አተረፍክበት? ባክህ ጓደኛዬ በቃ ይብቃህ እስኪ... “እኔም እንዲበቃኝ እፈልጋለሁ ግን እንዴት? እሷን ከመርሳት ይልቅ ለሷ ያለኝን ስሜት ለምጄው መኖር እንደሚቀለኝ አምኛለሁ።” ግን... “እንዲህ የምሆነው ስላልወደደችኝ ሳይሆን እሷን ለማስደሰት ብዬ የተጓዝኩትን ርቀት ሳስበው ነው። ዘፈኑን አንዴ አድምጠው እስኪ! ያኔ የምልህ ነገር ይገባህ ይሆናል።” አለኝ ከጀርባችን በጂፓስ ወደ ተከፈተው (የ Hachalu) ሙዚቃ በፊቱ እየጠቆመኝ። siif jiraadhe du'un koo (ላንቺ ኖሬ መሞቴ) silaa waan hin olle (የማይቀር ነበረ) gaarif hammenya kee (ጥሩ እና መጥፎነትሽ) walii isaani wallaale (ትርጉማቸው ጠፋኝ) anaan naqabatte (እኔን ይዘሽ(እኔ ኖሬሽ)) maaf anaan namita (ለምን እኔን ትጎጅኛለሽ) beekta anaa anatu (ታውቂያለሽ እኔ እኔው ነኝ) silaa jiru keef jiraataa (ላንቺ ህይወት የምኖረው) kanan gaabbu kan na aarsuu (የማዝነው የምናደደው) an waa lama dhabdun ta'e (ከሁለት ያጣ ስለሆንኩ ነው) kanan gaabbu kan na aarsuu (የማዝነው የምናደደው) bifuma tokkon meeqan du'e (በተመሳሳይ ሁኔታ ስንቴ ሞትኩኝ(ተጎዳዉ)) kan sidinqu maqaa keetin (የሚደንቅሽ በስምሽ) fira faana gargar bahee... (ከዘመዶቼ ተለያየው) “ለሷ ስል ሀሉንም ትቼ ነበር ፈጣሪዬን ሳይቀር። በዚህ ልክ የወደደውን ሰው የመርሳት አቅም ያለው ሰው አለ?” 🖋ON
It's not promotion በዛ መልኩ አትውሰዱት i don't know ብቻ ከሴት ገጣሚ/ፀሃፊ ጥራ ብባል ያለማንገራገር ነፂ ነው የምለው በጣም የምቀናባት ምናለ እንደሷ መፃፍ ብችል ብዬ የምቀናባት ሴት ናት። ገብታችሁ check ማድረግ ትችላላችሁ። https://t.me/netsaaleme
አንዳንድ ልቦች ላለመሞት ሲኖር ሲቃትት ለመክረም፤ ፀልሞ ይጀምራል ያንዳንዱ መስከረም፤ በምሽት ጀምሮ በምሽት ያበቃል፤ ለድጋፍ ለምርኩዝ አንድ ልብ ይበቃል፤ ሞላው ሰው በአለም ሞልቶለት አይደለም! ገርቶለት አይደለም! እንከን አልባ መስሎ ቆሞ መራመዱ፤ ብርታት ሆኖት እንጂ ባንዳንድ ልብ መወደዱ። እስኪ ዛሬ በእነሱ ልብ መፈለጋችን እና መወደዳችን ብቻ ብርታት ለሚሆነን ሰዎች ምስጋናችንን እናድርስ። መነሻ ሀሳብ፦ ለሊት ጆሮዬ ላይ ኮንሰርት ስትሰራብኝ ካደረችው ቢንቢ የተወሰደ። ያው ብትወደኝ ነው ብዬ አሰብኩኝ፤ እንጂማ እንደዛ እንጥሏ እስኪታይ ድረስ አትጮኽብኝም ነበር። ለኔ ብርታቴ ቢንቢዬ ናት ለናንተስ?
ይቅርታ... ምንም ብትዪ አንቺ ልክ ነሽ፤ በዛም አልተቀየምኩሽም።እንዳልሽው ነኝ አውሬ፣ ባፈቀሩት ልቦች ላይ በእሾኻማ እግሮቹ የሚረማመድ ጨካኝ። ልክ ነሽ እኔ ፍቅርን መቀበል እንጂ መመለስ አልችልበትም። በደሌ ከይቅርታም በላይ ነው ቢሆንም ግን ይቅርታ። በፊቴ ደምቀሽ ለመታየት ስትሽቀረቀሪ ለአንዴም ዞሬ እንኳን ማየት ስላቃተኝ ይቅርታ። በለገሽኝ የፍቅር ጠብታ ልክ አጥንትሽ ድረስ ዘልቆ የሚሰማ ህመም ስለሰጠኹሽ ይቅርታ። አዘኔታሽን ስላቃለልኩብሽ ይቅርታ። የሆነ ቀን ይቀየራል በሚል ተስፋ በደሎቼን ተሸክመሽ እንድትኖሪ ስላረኩሽ ይቅርታ። ከዐይኖችሽ ላይ የሚጎርፈው ብርሃን እንኳንስ እኔን አጠገብሽ ያለሁትን፤ ከርቀት የሚመለከቱሽን ጎረምሶች እንደሚስብ አውቃለሁ። የጎደለሽ ነገር የለም። በጭራሽ አንሼበት ነው የሚል ሀሳብ በአዕምሮሽ ውል እንዳይል። ሙሉ ሴት ነበርሽ። ጎዶሎው ሰው እኔ ነበርኩኝ። አንቺ ያሳየሽኝን ሚገዳደር ፍቅር በሰዓቱ ልቤ ውስጥማግኘት አልቻልኩም። ይበልጥ እንዳልጎዳሽ ፈርቼ እንጂ ችላ ያልኩሽ፤ ሳይገባኝ ቀርቶ አልነበረም። ንፁህ ልብሽን ማጠልሸት ፈራሁ። ካመንሽው ልቤ እንዳልጎድል ፈራሁ። ብዙ ጊዜ እንዴት ሆንሽ ብዬ ልጠይቅሽ አስብና፤ የዘጋሽውን ምዕራፍ መልሰሽ እንድታነቢ የማስገድድሽ ስለሚመስለኝ እተወዋለሁ። ይኽን የምልሽ ቃላት ለማደማመቅ አይደለም። የእውነት ከኔ የተሻለው ይገባሻል። ትበዢብኛለሽ። ፍቅር ሁሌም ቢሆን ጎበዝ መምህር ነው አይደል? ሰዎችን እንዴት ማፍቀር እንዳለብሽ፤ በሌሎች ላይ የምትጥዪውን የእምነት ልኬት አሳይቶሻል። አደራ! ባለፈው ቁስልሽ ላንቺ ሲሉ የሚሞቱልሽን ልቦች አፈር ለማልበስ አትሩጪ። ሁለቴ አትሳሳቺ። 🖋ON
ድንገት ብትናፍቂኝ ልቤ እንዲረጋልኝ፤ መልዕክቶችሽን አየኋቸው ድሮ ያኖርሽልኝን፤ ለካ እንዲህ ስቀናል ለካ እንዲህ ብለናል ለካ እንዲህም ሆነናል ጅማሮዋችን ለዚህ እንደተፈጠረ፤ ባውቅ ኖሮ ያኔ እቀልድ ነበረ? ልክ እንደዚህ? አይመስለኝም፤ አንቺም ብትሆኚ በቀሽም ቀልዶቼ አትስቂልኝም፤ ባላጓጓኝ ነበር "ደህና አደርክ?" የሚለው የጠዋት ሰላምታሽ፤ ደስ ብሎኝ ባልተኛው በምሽት ጨዋታሽ፤ ስንደዋወል በዕለት ምክንያት አንፈጥር፤ ርዕስ ፈልግ ነበር ወሬሽ እንዳያጥር፤ ብዙ እንድታወሪ ቃል እንዳያልቅብሽ፤ ኡ'ፋ'! የኔ ቆንጆ ስትስቂ ሲያምርብሽ፤ ጥሩ እንድተኛ ይረዳኛል ድምፅሽ፤ በቀዝቃው ምሽት ያሞቀኛል ሳቅሽ፤ ብዙ ጊዜ አለፈው አድምቀሽ የፃፍሸው መደብዘዝ ጀመረ፤ የዛሬን ብታውቂ ያኔ እንደ ወደድሽኝ ትወጅኝ ነበረ?... 🖋ON
https://t.me/haniyen1621
📎አንፈርድም!📎 እስካሁን በኖርኩት እድሜ የተማርኩት ነገር ቢኖር አለመፍረድን ነው። ያንድን ታሪክ ጫፉን ብቻ ይዘው ብያኔ አለመስጠት። መግቢያውን አንብበው በእርግጥም መፅሐፉ ይህን ሊል ነው የፈለገው ብሎ ድምዳሜ ላይ አለመድረስን። ሙሉ ገፆቹን ጨርሶ ማንበብን። ማንም ሰው ጥሩ ምርጫዎች ቀርበውለት እጁን ወደ እሳት መስደድ አይፈልግም። በላቧ ወዝታ መኖር እየቻለች፤ የትኛዋ ነፍስ ናት ቁራሽ እንጀራ ፍለጋ የመፅዋች ዐይን እንዲገርፋት የምትሻ? የትኛዋ ነፍስ ናት በቢራ ጠርሙሶች ተከባ ከአለም ለመሸሸግ የምትሞክረው? የትኛዋ ነፍስ ናት የተደላደለ ህይወት ተሰጥቷት ገላዋን ለመንገደኛ ቸርችራ በምታገኘው ሳንቲም እስትፋሷን ለማቆየት የምትመርጠው? የትኛዋስ ነፍስ ናት የሰላም እንቅልፍ መተኛት ስትችል፤ እጆቿን በደም አጨማልቃ ህሊናዋ ዘውትር እየጠዘጠዛት እንዲኖር የምትከጅል? እነሱን የነውር ቀለም ቀብተናቸው ራሳችንን ንፁህ ብለን የምንጠራው ጥሩ ምርጫዎች ስላሉን ነው። አንደኛው በር ቢዘጋብን ወደ ሌላኛው በር ፊታችንን ማዞር እንችላለን። ያም ካልሆነ ወደ ሌላኛው። እነሱ ግን ይህን በረከት፤ ይህን የመኖር ነፃነት አያውቁትም። ታዲያ እንዲህ በመሆናቸው ራርተን ልናዝንላቸው እንጂ ልናዝንባቸው ይገባን ነበር? ምናልባት ዛሬ ጨካኝ ብለን ስም የሰጠነው ሰው፤ በጨነቀው ጊዜ ትንሽ እርዳታን እንኳን ከኛ ተብቆ እኛ ግን ዘለፋ እና እርግማን ያወረድንበት ሊሆን ይችላል።በሰዓቱ የሚያነሳው እጅ ቢያገኝ ኖሮ ይህን መንገድ ባልመረጠ ነበር። ለዚህ ነው መፍረድ የማልፈልገው። በዙሪያችን እንዲህ ያሉ ሰዎችም አይጠፉም አይደል? በጌታቸው ላይ ወሰን ያለፉ። ዛሬ ኢ-አማኝ የምንላቸው ምናልባት ባንድ ወቅት መሻኢኮች እና ካህናት በፈጠራቸው ዘንድ ካላቸው ስፍራ ይበልጥ ኖሯቸው ያለፉ አማኞች ይሆናሉ። መከራና ስቃይ በሁሉም አቅጣጫ ሲደቁሳቸው ጭላንጭል ምህረትን እና ተስፋን ጠይቀው ያጡ ሊሆኑ ይችላሉ። አንድ በጣም የሚደንቀኝን ታሪክ ልንገራችሁ። የሆነ ቀን አንድ ሰው አንድ ዐይኑ ይጠፋና፤ በጊዜው ወደነበረው ሀገረ ገዢ ጋር ክስ ለማቅረብ ይሄዳል። አስቡት ይህ ሰው የእውነትም አንድ ዐይኑ ጠፍቷል። ያ ሀገረ ገዢ ግን ምን እንዳለ ታውቃላችሁ? ተከሳሹን አምጡትና ይሰቀል፣ ይወገር ወይም ይታሰር አላለም። እስኪ ተከሳሹን ይዛችሁት ኑ ምናልባትም የእሱ ሁለቱም ዐይኖቹ ጠፍተውበት ይሆናል። ይህን ነው እንግዲህ ሙሉ ታሪኩን ጨርሶ ማወቅ ብለን የምንጠራው። የሚሰ'ጠ'ንም ሆነ የምንሰጠው ትንሽዬ ምላሽ የህይወት አቅጣጫዎቻችንን የመቀየር ትልቅ አቅም አለውና፤ ሁሌም ቢሆን ከመፍረድ ይልቅ ጠጋ ብሎ፣ ረጋ ብሎ ማድመጥን እናስቀድም። ያን ማድረግ ካቃተን ግን ቢያንስ ዝም እንበል። 🖋ON
🦋ማያዬ🦋 በጨቅላ ቡረቃ ፈንድቄ ምውለው፤ ስላንቺ ሳስብ ነው ፈገግ የምለው፤ እፀ በለስ ወይን የምሽት አዝመራ፤ የመለኮት እቅፍ የፍቅር ደመራ፤ የጠዋት መዝሙሬ ማለዳ ብስራቴ፤ ተጠግኗል ባንቺ ደዌ ስብራቴ፤ ሀኪሜ ወዳጅሽ ናፍቆሻል በጠና፤ ነይ መጥተሽ ደባብሽው ይፈወሳልና፤ ብሌኔ ማያዬ ስስት ቁንጅናዬ፤ ድብቋ ጀነቴ ግልጧ መፅናኛዬ፤ ለውለታሽ ምላሽ አሰናዳው ማጀት፤ ዝግጁ ነኝ ሁሌም ካንቺ ጋር ለማርጀት፤ ፊደል ግምጃው ጠርቶኝ ለክብሩ እጁን ስሜ፤ የሚመጥንሽን አሰሳ ታድሜ፤ ድርሻዬን ዘግኜ ድርሻሽን ለቅሜ፤ ይኼን ነው የምልሽ እቺ ናት አቅሜ፤ የነፍስ ወይራ ነሽ እጣን እና ከርቤ፤ ከፃፍኩልሽ በላይ ይወድሻል ልቤ። 🖋ON
📎ድብቅ ገፆች📎 “ሁልጊዜ እየመጣሁ ስጨቀጭቅህ አትሰለቸኝም አይደል፤ ያው ታውቃለህ ሌላ የምሄድበት ቦታ የለኝም። እንዳንተ ዝም ብሎ ያላማቋረጥ ማዳመጥ የሚችልበት ሰው አላውቅም። መቼም አትረሳውም? ለትናንሽ ጉዳዬቼ እንኳን ወዳንተ እየሮጥኩ እመጣ ነበር። ስለ አጠቃላይ ህይወቴ ያለኝን አቤቱታ አንተ ጋር ነበር የማሰማው። አሁንም ያንኑ እያደረኩ ነው። ልክ እንደያኔው ዛሬም ለረጅም ሰዓት እያወራው ነው...” ድፍን አስር አመታቶች አልፈውትም እዚህ መቃብር ስፍራ ከመመላለስ ተሳንፋ አታውቅም። ሀዘኗ አሁንም ድረስ ትኩስ ነው። ልክ ያኔ በሞት ሲለያት አልቅሳ እንደሸኘችው አይነት፤ የእንባ ከረጢቷ አልደረቀም። የልጅነቷ የመጀመሪያ ፍቅሯ በሞት ከተለያት አስር አመታቶች አለፉ። ከለበሰው አፈር ጎን ተቀምጣ የሚሰማትን ሁሉ ተንፍሳ መሄድ የዘውትር ልማዷ ነው። የሷም ልብ ከሱ ስጋ ጋር አብሮ የተቀበረ እስከሚመስለኝ ድረስ ሁኔታዋ ሁሉ ያስገርመኛል። “ሙናዬ ያኔ ያወራነው ትዝ ይልሃል? በኪዳን ተሳስረን፤ ቆንጆ ልጆችን ወልደን በምቾት ስለመኖር እናልም ነበር። ሁሌም ደስተኛ እንድሆንልህ ትፈልግ ነበር አይደል? እኔ ባልኖር እንኳን ወደፊት መጓዝ አለብሽ፤ የራስሽን ቤተሰብ መመስረት፤ እኔን ረስተሽ ደስተኛ መሆን መቻል አለብሽ ብለህ ቃል ያስገባኸኝስ ትዝ ይልሃል? ውዴ ቃሌን ጠብቂያለሁ። መልካም ባል አግንቼ ሁለት የሚያማምሩ ወንድ ልጆችንም ወልጃለሁ። እርሺኝ ያልከውን ቃልህን ግን መጠበቅ አልቻልኩም እሱን ማድረግ አልቻልኩም።አልተናደድክብኝ? አልተቀየምከኝም? ያንን ሰውነት፣ ያንን ደግነት፣ ያንን የመሰለ አዛኝነት እንዴት መርሳት እችላለሁ ቆይማ እንደውም አንድ የፃፍኩልህ ግጥም ነበር። ታውቀኛለህ እኔ እንዳንተ ቃላት ላይ ጎበዝ አይደለሁም ግን ዝም ብለህ አድምጠኝ ” ብዙ በማልቀስ ዐይኖቿ ደም ለብሰዋሉ። እያነባች በቃሏ ሸምድዳ የያዘችውን ግጥሟን ታነብለት ገባች። “ከጎኔ ከሌለህ እንዴት ነው ምኾነው? ከተውከኝ ጀምሮ እያለቀስኩ ነው፤ ካንተ ውጭ ያለውን አለሜን ትቻለሁ፤ ስለምትናፍቀኝ እየመጣሁ አይኻለሁ፤ አብልጦ የወደደህ አፈርህ ይሞቃል፤ እንባና ገላዬ ታከተኝ አይልም ቀብርህ ላይ ይወድቃል፤ ምንም እኮ አላውቅም ስለማወጣው ቃል፤ አንተ የሌለህበት መተንፈስ ይጨንቃል፤ እስኪ መልስልኝ መርጠህ ያፈቀርኸው በስስት ያቅፍሃል? ይሄ ጨካኝ አፈር እንደኔ ያፈቅርሃል? ደግሞስ ምን ብበድልህም ምን ባስቀይምህም እኔ አልሻልህም? የጭካኔህ በትር ለስቃይ ቢዶለኝ፤ አሁንም ድረስ ግን ላንተ ፍቅር አለኝ፤ ካጠገቤ ሳጣህ እንዴት ነው ምኾነው? ታውቃለህ አለሜ ከተውከኝ ጀምሮ እያለቀስኩ ነው። ዛሬ ከማንም በላይ ታስፈልገኛለህ፤ አቅፎ ማረጋጋት ታውቅበት የለ? አለሁሽ በለኛ በጣም ናፍቀኸኛል...” ላገባት ሰው አዘንኩለት። ሚስትነቷን አምኖ ተቀብሎ በድኗን አቅፎ ለሚተኛው ምስኪን። እንግዲህ የህይወት ሌላኛው መልኳ ነው ብለን መውሰድ እንችላለን። የሚስቅ ፊት ሁሉ ደስተኛ አይደለም። ምላሽ ያጣም ሁሉ ጥፋተኛ አይደለም። ሰማንያ የፈረመ ሁሉ ትዳር አለው ማለት አይቻልም። 🖋ON
ህይወት ብታሳዪኝ የገፈትን አፀድ የመኖርን መ'ና'፤ ፍቺሽን ለማወቅ አልበሰልኩም ገና፤ ገና ለጋ ነው እግሬ መጓዝ አልጀመረም፤ ጉልበቴ አልፀናም ሀሞቴ አልመረረም፤ የቅርቡን ከሩቁ፣ የላዩን ከጥልቁ፣ ብስሉን ከጥሬው፣ ገለባን ከፍሬው፣ ለይቼ አላውቅም፤ ከማየት አይዘልም አሁን ያለኝ አቅም፤ ዝም ብሎ መታዘብ እንደሆንሽው ሆኖ፤ በመከራሽ ታጥኖ በፊትናሽ ታፍኖ፤ በተስፋዬ መሀል ያቆምሽው ችንካርሽ፤ ፅዋሽ አዝለፍልፎኝ ባይለቀኝ ስካርሽ፤ ጅራፍሽ ጩኸቱ ምን ቢያስበረግግም፤ ግርፊያሽን ፈርቼ አላፈገፍግም፤ በጥፊ ብትልሽኝ፣ ቡጢ ብታቀምሽኝ፣ በካልቾ ብትጠርጊኝ፣ ምድር ብትዘረጊኝ፣ ህይወት አልሰማሽም፤ እስኪያልፍልኝ አልፈታሽም፤ ትንሽ ግን ልጠንክር በበትርሽ ክብደት ጫንቃዬን እስካገኝ፤ ታያታለሽ ያኔ እኔን አያድርገኝ። አስምሪበት ቃሌን ብለሽ አትውሰጂው የፈሪ ሰው ዛቻ፤ (ቱ! ያገናኘን ብቻ😏) ጠብቂ‼️ 🖋ON
〖couples mini blog d/t reason, z same feelin'🤦♂️〗 ዜማ እወዳለሁ ዜማ ትጠላለች፤ በድርጊቴ ሁሉ ትብከነከናለች፤ እርጋታ የላትም እርካታ የላትም፤ ሆኖም አልጠላትም፤ ታስጨንቀኛለች ፋታ አትሰጠኝም፤ የገዛ ዕድሜዬ ላይ እኔ መብት የለኝም፤ ወይ ቁንጅና ማድነቅ ወይ ሌላ ሴት ብ'ያ'ት፤ እሷ ፍላጎቷ እሷን ብቻ እንዳያት፤ ስልክ መያዝ ሃራም፣ TV ማየት ሃራም፣ መፃፍ ማንበብ ሃራም፣ ዜማ ማድመጥ ክልክል፤ እሷው ነች ትክክል፤ ከቅጥሯ እንዳይወጣ ልቤን ታዘዋለች፤ ፍቅሯ እኮ ደስ ይላል ግን ታበዛዋለች፤ ጁመዓ ነው ብዬ ሀገር ሰላም ብዬ ባዳምጥ ነሺዳ፤ "አትወደኝም" አለች ጨመረችኝ እዳ፤ هٰذا المديح لمسوت من ألبوم «تبسم» و«بلغ العلا» ❴የmesut መድህ ነው ከ 'Tabassam' አልበም ከበለገል ዑላ፤❵ የኔ ድንቡሽቡሽ የኔ ሳዱላ፤ "እውነት ትወደኛለህ? ይደንቀኛል ስራክ፤" For the rest of my life እንደሚለው track፤ maherም ባይገድሽ፤ እንዲያ ነው ምወድሽ፤ ሰምተሽዋል እሱን? "መልስልኝ መልሱን! ከሚዲያ ለቅመህ አታሰማኝ ቅጂ፤ ጊዜ ስጠኝ እንጂ፤ ትኩረት ስጠኝ እንጂ፤ እንደው አቅም ኖሮኝ በእጄ በጨመኩህ እንደ በሶ ጭኮ፤" እሺ ምን ልበልሽ አስጨነቅሽኝ እኮ፤ "እወድሻለሁ በለኝ!" ሁሌም እልሽ የለ? "ብትደግመው ምና'ለ'?" እሺ እወድሻለሁ ከራሴም አብልጬ፤ አንዴ የጀመርኩትን ልጨርስ አድምጬ? "አንተ መቼም አትለወጥም😡" አይ እዳ! በቃ ትቼዋለሁ ምንም ካንቺ አይበልጥም🥀 🖋ON
без подписи
NOT A DAY ON ANY CALENDAR✨ Spring, and everything outside is growing, even the tall cypress tree. We must not leave this place. Around the lip of the cup we share, these words, My Life is Not Mine. If someone were to play music, it would have to be very sweet. We're drinking wine, but not through lips. We're sleeping it off, but not in bed. Rub the cup across your forehead. This day is outside living and dying. Give up wanting what other people have. That way you're safe. "Where, where can I be safe?" you ask. This is not a day for asking questions, not a day on any calendar. This day is conscious of itself. This day is a lover, bread, and gentleness, more manifest than saying can say. Thoughts take form with words, but this daylight is beyond and before thinking and imagining. Those two, they are so thirsty, but this gives smoothness to water. Their mouths are dry, and they are tired. The rest of this poem is too blurry for them to read. ሩሚ በዚህ ግጥሙ የራሳችንን ቀን ስለመፍጠር ይነግረናል። ቀኖቻችንን እኛው እንድናሱባቸው። እርግጥ ነው በብዙ ችግሮቻችን ታጥረናል። የቤተሰብ ውጥረት፤ የመኖር ፈተና፤ ዛሬን ተሻግረን ስለነገ መጨነቅ፤ የፖለቲካ ውዝግብ፤ የዘር የእምነት ትርምስ። የእርስ በእርስ ግጭቶቻችን ሰላም አሳጥተውናል። ግን ትንሽ ቆም ብላቹ ካስተዋላችሁት አሁን ያለን ሁሉ የኛ አይደለም። ይህ መከራ ይሄ ህመም፤ ይህ ምስቅልቅል ይሄ ዓለም፤ የኛ አይደለም።ስግብግበናታችን የሰራው ሰንሰለት እንጂ...እናም አንድ ዕድል አንድ ህይወት ብቻ ነው ያላችሁ፤ ከአለም ገለል ብላችሁ የራሳችሁን ቀን ፍጠሩ። ደስተኛ ሁኑ። እወዳችኋለሁ🤍 from ❝The Essential Rumi❞ Coleman Bark's ቆንጆ አድርጎ አሰናድቶታል ተጋበዙልኝ🤌
... እንደ አበባ ሁኑ! ፧ ፨ ፧ ጦር ይዞ የመጣን በፍቅር መ'ል'ሱ፤ ለሚቀጥፏችሁም መዓዛ ለግሱ። ፨---------------፨ ❝~Ali ibn Abi Talib (ra)❞
የልብ ገመና ለሁሉ አይሰጣም፤ አንዳንድ ስብራት በቃል ብቻ አይወጣም። ፦ለዚህ ነው... ጥልቅ ትንፋሾችን ሞ'ቃ'ት እንባዎችን ረዘም ያለ እንቅልፍ የማረፊያ ቦታ፤ የሚንቀጠቀጥ እጅ ቀዝቃዛ ፈገግታ፤ የቀልቡን ትኩሳት እንዲያስታግስለት፤ መተንፈሻ አድርጎ ጀሊል ያበጀለት። «~Nizar Qabani»
"ምኞቶቻችን ልክ አልፈዋል፤ ሁሉም ሕልሞቻችን ሕልም ሆነው ቀርተዋል። እንዲህም ሆኖ እየታገልን ነው። እኔ አንተን ለመቅደም እየታገልኩ ነው፤ አንተ ከእኔ የምትሻልበትን አንተነትህን ፍለጋ እየታገልክ ነው፤ ትክክል ነን ፍፁም ነን ለማለት እየታገልን ነው። የፈጠረንን ከዙፋኑ አውርደን በመንበሩ መደላደል እንፈልጋለን፤ የራሳችን የሆኑ ባሮች (አገልጋዮች) እንዲኖሩን እንሻለን። ያን ማድረግ ስንችል ብቻ ሰከን የምንል ይመስለኛል። አይመስልህም ወዳጄ?" በጣም የምወደው ጓደኛዬ ነው ባለ ቅን ልብ፤ አስተዋይ፤ ዕድሜውን ቀድሞ የሄደ በሳል ሰው። ግን አንዳንዴ ከዚህ ሰው ጋር መግባባት ያቅተኛል። የሚያወራው ነገር ትርጉም አይሰጠኝም። ያልገባው ሰው ላለመምሰል ግን እኔም ያቅሜን ሀሳብ ጣል ለማድረግ እፍጨረጨራለሁ። ይሄው ድርጊቴ ሁሌም ፈገግ ያስብለዋል፤ "ባንተ ውስጥ ሀገሬን አያታለው" ይለኛል። "እውነቴን እኮ ነው ቅንጡ ሆቴሎች ላይ እራት መብላት፣ቅንጡ መኪና ማሽከርከር፣ ቅንጡ ልብሶችን መልበስ። ምቾቶችን ማሰስ ልክ ነው። ተድላ፣ ሀሴት ማግኘት መንፈሳችንን ያድሰዋል። እየቆየንበት ስንመጣ ግን ያቀዘቅዘዋል፤ የመንፈስ መ'ሸ'ርሸር በምድራዊ ሀይል የሚጠገን አይደለም። ለምን እኔ እና አንተ አንድንም?" እንዴት? "ቀላል ነው በመቃብር ስፍራዎቻችን ሻይ ቡና እንባባል። ሆስፒታል ታካሚዎች መካከል ምሳ እንገባበዝ። እስር ቤት በሮቻችን ፊት ለፊት ሰብሰብ ብለን የሆድ የሆዳችንን እናውጋ።" አንተ ልጅ ለይቶልሃል መሰለኝ! "ምናለበት? ምናልባት ያኔ ምንም እንዳልሆንን፣ ዛሬ ያካበትነው ጥሪታችን እኛው በገዛ እጃችን አሱበነው የምን'ገዛ'ው ጣዖት እንደሆነ፤ እዚያ ያለው ንፋስ ሹክ ብሎን ካባነነን ብዬ እኮ ነው። ማን ያውቃል?... መንቃት እፈልጋለሁ! አንተስ?" 🖋ON
ድማም ቁንጅናሽ ሽቶሽ አይደለም ያርከፈከፍሽው፤ ከንፈርሽ አይደል በውብ ቀለማት ያቀላለምሽው፤ መቃ አንገትሽን ጌጥ ብታለብሽው፤ የሆድሽን ስብ ብትቀንሽው፤ ብታበጃጂም የነብር ወገብ፤ ወጣትነትሽ ካላለ ረገብ፤ ዳሌሽ ቢወጠር፤ ላ'ጀብ ቢፈጠር፤ ባትሽ ቢቀላ ለዐይን ቢሞላ፤ ሃያእ ከሌለው ያ ቆንጆ ገላ፤ ድምፅሽ 'ያማረ፤ በጆሮ አልፎ ልብ እየሰወረ፤ እንደ soul music በፍቅር ቢያደምጡት፤ ሎሚ ተረከዝ ጉች የሚል ጡት፤ ይህ ሁሉ ተዐምር በስብዕናሽ ካልተጋረደ፤ ቀሚስሽ ጥለቱ በአላፊ፣ አግዳሚው ከተቀደደ፤ ገላጣ ስፍራ ላደን ያመቻል፤ የተወደደም ደርሶ ይሰለቻል፤ ንዋይ ቢያዝቅሽም እርድናሽ በግላጭ፤ ሴትነት ክብርሽን ካወጣሽ ለሽያጭ፤ ፍሰሀው ነውና ገዢን አይረብሽም፤ የላይ መልክሽ ብቻ ባለቤት ነው እንጂ ሚስት አያረግሽም!! መጠሪያ ትርጉሙን እስኪ አንቺ ለውጪው፤ ልባም ሴት ሁኚና እርድናን ብለጪው፤ የተመኘሽም አያግኝሽ በአፍታ፤ ይሄ አይደለም 'ሚ'ገባ'ሽ ቦታ፤ ° ° ..... የፈጠረሽን፣ ውብ ያረገሽን፣ ጌታ ስትፈሪ፤ በሙሉ ክብርሽ ስትሞሸሪ፤ ያኔ ይገባሻል! ከገላሽ በላይ እንደምታምሪ። 🖋ON