tgindex
guzo wede jenet

guzo wede jenet

Статистика

ጉዞ ወደ ጀነት አላማው 🌎 ዳእዋዉን ተደራሽ ለማድረግ ነው የተለያዩ የነቢያት ታሪክ ሶሂህ ቡሀሪ ሀዲሶች የሶሀቦች ታሪክ ስለ ጤናዎ መረጃ እዚህ ቻናል ላይ ያያችሁትን ማንኛውም ስተት እንድትነግሩን በአላህ ስም እንጠይቃለን እንዲሁም ገንቢ ሀሳቦን ያጋሩን ሁሌም ከጎናችን ላላችሁ ሁሉ አላህ ጀዛችሁን ይክፈላችሁ። ለአስተያየትዎ @asiye9 @Asutii5

Последний пост
17 янв. 2025 г.
Последнее чтение
15 авг.
Постов за неделю
0
Всего постов
20
Тип
открытый
Язык
und
В каталоге с
15 авг.
Подписчики
198
0 за 1 дн.
Сутки
0
0,00%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
262
20 постов
Вовлечённость
132,3%
к подписчикам
Постов в день
0,0
всего 20
Упоминаний
0
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
1/48двое суток
1/72трое суток

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • 17 янв. 2025 г.2964из Golden_Speech

    ባልና ሚስት ይጣሉና ሽማግሌ ይሰበሰባል። ከዚያም ሁለቱም ችግራችሁን ተናገሩ ሲባሉ ... ባል፦ "እኔ ከስራ ደክሞኝ ስመለስ ማረፍ እፈልጋለሁ። ነገር ግን ልጆችን እያንጫጫች አያሳርፉኝም" አለ ሽማግሌዎቹም "ሌላስ?" ይሉታል "እኔ ከስራ ስመለስ ልጅ ያዝ ትለኝና ወጥ ትሰራለች። የልጅ ወተት ታፈላለች። ምናለ ሳልመጣ ጨርሳ ብጠብቀኝ ተቀምጣ እየዋለች" ይላል በንዴት። ሚስትም በሰዎቹ ፊት "ከዚህ በኃላ በፍፁም አንረብሸውም" ብላ ይቅርታ ስለጠየቀች ሽማግሌዎቹ ትተዋቸው ይሄዳሉ። በነጋታውም ሚስት ልጆቿን ይዛ እናቷ ቤት ሄደች። ከስራ ሲመጣ ቤቱ ተቆልፏል። ልክ ከፍቶ ሲገባ ቤቱ እጅግ ይቀዘቅዛል። ከሰል ለማቀጣጠል ቢሞክር እምቢ አለው። ልብሱን ደራርቦ ሚስት ሰርታ የነበረውን ጠራርጎ በላ። ዝምታው ሲጨንቀው ቴሌቪዥን ከፍቶ ለማየት ሞከረ ግን የለመደው የልጆቹ ድምፅ ናፈቀው እና እየከፋው ተኛ። ጠዋት ሲነሳ ያ የሚጣፍጠው ቁርስና የሚወደው የሚስቱ ፈገግታ የለም። ከፋው። ፊቱን ታጥቦ ወደ ስራው ሄደ። ቁርሱንም ውጪ በላ ግን አላረካውም። ቀኑ እንደከበደው ዋለ። ስልኩን ቢያይም አትደውልለትም። ውሎ ሲመለስ ራቱን ውጭ በልቶ ከጓደኞቹ ጋር ቢያመሽም በመጨረሻ ያ ባዶ ቤት ጠበቀው። ለቅሶ ቤት ይመስል መግባት አስጠላው። ዞር ብሎ ሲያስብ ለካ ያለ ሚስቱ ጎዶሎ ነው። ለካ ልጆቹ ረባሾቹ ሳይሆኑ አጫዋቾቹና የመንፈስ እርካታው ናቸው። ከዚያ በኃላ "በእጅ የያዙት ወርቅ ሆናችሁብኝ ጥቅማችሁን ስላልተረዳሁ በጣም በድያችኃለሁ። እባክሽ ይቅር በይኝ ውዷ ሚስቴ!" ብሎ በሽማግሌ ታረቃትና በሰላም ኖሩ። *** መልዕክቱ፦ ሚስቶች ሸክሞች ሳይሆኑ የቤቱ ተሸካሚዎች፣ ሰራተኞች እና አስተዳዳሪዎች ናቸው። ልጆች የቤቱ ሁከት ፈጣሪዎች ሳይሆኑ ደስታና ሙቀት ፈጣሪዎች ናቸው። ስለዚህ ደስታ የሚሰጠንን ነገር ከማጣታችን በፊት ቀድመን ለይተን አውቀነው ተገቢውን ቦታ እንስጠው ለማለት ነው።

  • 22 дек. 2024 г.245из al_mutehabin

    ኢክራም በድሩ አዲስ አበባ ኮድ 59

  • በአንድ ወቅት ኢማም ሐሰኑል በስሪ በጠና ይታመሙና ሙስሊም ያልሆነው ጎረቤታቸው ሊጠይቃቸው ቤታቸው ይሄዳል። ወደ ቤት ከገባ በኃላ ግን ጥሩ ያልሆነ ሽታ ስለሸተተው: "ያ ኢማም! መጥፎ ሽታ ይሸተኛል።" አላቸው! ... ኢማሙ የመተናነሳቸውን ጥግ የሚያሳይ መልስ መለሱለት። "ምን አልባት በሽታዬ የፈጠረው ሽታ ይኖር ይሆን?" አሉ። ጎረቤትየው ግን ሽታው ሌላ እንደሆነ፤ ይልቅ ከመፀዳጃ ቤት የሚመጣ ሽታ እንደሆነ ግምቱን ነገራቸው። እንዲነግሩትም ጠየቃቸው! ጎረቤታቸው ከእርሱ ቤት የሚወጣው ፈሳሽ ቆሻሻ ወደ ኢማሙ ሐሰኑል በስሪ ቤት እየሄደ እንደሆነ አላወቀውም ነበር። ኢማሙ'ን እንዲነግራቸው ሲያስጨንቃቸው እንዲህ አሉት: "ለወራቶች ካንተ ቤት የሚመጣ ፍሳሽ ወደኔ ከባቢ እየፈሰሰ ነበር። ላስተካክለው ብሞክር ምንም ሊሰካልኝ አልቻለም።" አሉት! ሰውየው በጣም ደነገጠ፤ በእርሱ ቤት ችግር ምክንያት ይህ መፈጠሩ አሳዘነውና እስከዛሬ ለምን እንዳልነገሩት ጠየቃቸው። ታላቁ ኢማም'ም፤ እኚህ ምርጥ ሰው: " ስሜትህን እንዳልጎዳው (እንዳላስከፋህ) ሰግቼ ነው።" ብለው አሉ! ... ጎረቤትየው በኢማሙ ስነምግባር ተደነቀ፤ ይህንን ባህሪ ያላበሳቸውም እምነታቸው እንደሆነ ተረዳ። በዚህ ክስተት ምክንያትም እስልምናን ተቀበለ! ... ...አላህ አላህ! ሱብሓነላህ 🥰🤎 እስልምናን ኖረውት፤ ለሌሎችም የብርሃን መንገድ ሰበብ ሆነው ያለፉትንም በህይወት ያሉትንም መሻዒኮቻችንን አላህ ይጠብቅልን። እኛንም በዚህ ስነምግባር እንታነፅ ዘንዳ አላህ ያግዘን!✨️

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • ሰሀባው አብደላህ (ረ.አ) ረሱል በጣም ይወዳቸው ነበር። ባይሆን ነገረ ስራው ሁሉ ወጣ ያለ ነው። ወደ መዲና የገባን ነጋዴ አግኝቶ ማር ቅቤ ወይም ቆንጆ ነገር ይዘው ካየ በብድር በዚህ ቀን ልከፍል ብሎ ተስማምቶ ይቀበልና ረሱል ጋር አምጥቶ "የአላህ መልክተኛ ሆይ ይሄው ቆንጆ ስጦታ አመጣሁልህ" ብሎ ይሰጣቸዋል። እሳቸውም ተቀብለው አመስግነው ይሸኙታል። ባይሆን የብድሩ መክፈያ ቀን ሰዎቹ ክፈል ብለው ሲመጡበት ተከተሉኝ ብሎ እጃቸውን ይዞ ነብዩ ጋር ያመጣና ረሱልን "ባለፈው ያመጣሁልህ ስጦታ በብድር ነውና ለዚህ ሰው ክፈል ይላቸዋል። እሳቸውም እየሳቁ "ያ አብደላህ ስጦታ ነው ብለህ የለ ?" ሲሉት እሱም "ትክክል ነው ስጦታ ነው ያረሱለላህ፣ እኔ ግን መክፈል አልችልም" ይላቸዋል። እሳቸውም እየሳቁ እዳውን ይከፍላሉ (ሰለዋቱ ረቢ ወሰላሙ አለይህ) ባይሆን አብደላህ አንድ ድክመት አለችበት። አልኮል እናም ሰክሮ መስጅድ ይመጣል። ረሱልም በተደጋጋሚ በህጉ መሰረት ይቀጡታል። ይህ ነገር ሲደጋገም ያየ አንድ ሰሀባ ተናዶ "የአላህ እርግማን ይውረድብህ" ሲል ረሱል ሰሙት ። እናም ሰውየውን ተቆጡት "ተው እንዲህ አትበል፣ በወንድማችሁ ላይ ሸይጧንን አትርዱት፣ ይህ ሰውኮ አላህና ረሱልን የሚወድ ነው አሉት። ሰሉ አለነቢ🥰🥰🥰

  • ⭕️በፖኖርግራፊክ የተጠመደው ወጣት ልብ የሚነካ እውነተኛ ታሪክ⭕️ ---------------------------------------------- ሸይኹ እርሳቸው ጋር ቀርቦ ስላጫወታቸው ወጣት አስገራሚ ታሪክ በመስጅድ ለተሰበሰበው ሰው እንደሚከተለው አወጉ.... ወጣቱ — የልጅነት ጊዜዬ ብሩህ ፣መልካም እና የቤተሰቤ የኢስላማዊ ተርቢያ ውጤት ነበርኩ ። በመንደራችን የጥሩ ሰዎች ሞዴል ተደርጌ እቆጠር ስለነበር አንድ ደግ ሰው ወጣትነቴን አይቶ ሳሊህ(ሳሊሃ) የሆነች ሴት ልጁን ዳረኝ ። ነገር ግን የኔ ኢማን ከመብረቅ በፈጠነ ተምዘግዝጎ ሲወርድ ይታወቀኛል ። የስሜቴ ተገዥ የሸይጣን ሰረገላ ሆንኩ ወደፈለገው ቦታ ይነዳኛል። በስራ ያወቅኳቸው ጓደኞቼ በየእለቱ በ cd እያዘጋጁ በሚሰጡኝ ፀያፍ(porngraphic) ፊልሞች ተጠመድኩ ። ምንም እንኳ ሚስቴ ያማረ ስነ ምግባር ቢኖራትም ቅሉ ተደብቄ በማያቸው ፊልሞች ምክኒያት በትዳሬ ደስተኛ መሆን አልቻልኩም በሆነውም ባልሆነውም መነታረክ ባህሪዬ ሆነ ነገር ግን ለስላሳው የሚስቴ ምላሽ ሁሌም ከህሊናዬ አይጠፋም አይደርስ የለምና ደረሰ። አላህ ውብ የሆነች ልጅን ሰጠኝ ።እናት መድረሳ ናትና ሚስቴ በኢስላማዊ አደብ ኮትኩታ ማሳደጉን ተያያዘችው እኔም በአመፄ ቀጠልኩ ነገር ግን ሚስቴና ልጄ እንዳያውቁብኝ ከፍተኛ ጥንቃቄ አደርጋለሁ። ከቀናቶች አንድ ቀን ይህን ፀያፍ ፊልም አንደያዝኩ ቤቴ ገባሁ ሁሌም እንደምታደርገው ሚስቴ ልጄን ቁርአን እያስተማረቻት ደረስኩ። ሁለቱንም ስሜ ወደ መኝታ ክፍሌ አመራሁ ። መተኛታቸውን እንዳረጋገጥኩ ይህን ኸቢስ መመልከት ጀመርኩ ለካስ ቀደር ሲመጣ አይን ይታወራል አይደል የሚባለው ተኝታለች ብዬ የገመትኳት የ 7 አመቷ ልጄ ልብስ ሳይለብስ ተኝቶ ይሆናል ብላ በማሰብ በሩን ከፍታ ገባች ። ዋ ጥፋቴ በዛች ቅፅበት ምድር ተከፍታ ቃሩን እንደዋጠች ብትውጠኝ ብዬ ተመኘሁ ። ልጄ ያየችውን ማመን አቃታት በሳሊህነቱ የምታውቀው አቧቷ አልመስልሽ አላት ። ባባዬ ኢተቂላህ ብላ በሩን ከፍታ ወጣች ።በቃ አለቀልኝ ልጄ ያየችውን ሁሉ ለእናቷ መናገሯ አይቀር የት ልጥፋ የት ልሂድ ይሄኔ ፈጅር አዛን አለ "ሃያ አለል ፈላህ" ሻወር ወስጄ ወደ መስጅድ አመራሁ ኢማሙ ሲቀራ እንባዬን መቆጣጠር አልቻልኩም ኢማሙ الم يعن للذين امنو أن تخشع قلوبهم لذكر الله ለነዚያ ለአማኞች ልቦናቸው ለ አላህ ግሳፄ የሚ ፈሩበት ግዜ አልደረሰምን? የሚለው ቦታ ሲደርስ ስቅስቅ ብዬ አለቀስኩ በስጁዴ ላይ ጌታዬ እባክህ ነውሬን ደብቅልኝ ። አይነጋ የለም እና ነጋ ቤት ሳልደርስ ወደ ስራዬ አመራሁ ነገር ግን ስራዬን መስራት አልቻልኩም በአቅራቢያ ካለ መስጊድ ገባሁ ሰው አለመኖሩ አላህን ብቻዬን እጄን ወደርሱ ዘረጋሁ ያ አላህ ያ አላህ አለቀስኩ ይህን ወንጀሌን ከሸፈነልኝ ሁለተኛ እንደማላምፅ ከውስጤ ቃል ገባሁ ። ሲመሽ ወደ ቤት መመለስ ነበረብኝ እና ተመለስኩ ሚስቴን በር ላይ ቆማ ሰወችም ወዲህ ወዲያ ይላሉ በቃ ሚስቴ ጉዳዩ ላይ ደርሳበት ፍቺ ልትጠይቅ ሰው ሰብስባ ነው አልኩ አንገቴን እንደደፋው አጠገቧ ደረስኩ ፊት ምንኛ ያበራል ብላ አቅፋ ሳመችኝ ትንሽ ተረጋጋሁ ቀጥላ ልጃችን ፈጅር ላይ ጀምሯት በነበረ ትኩሳት ረፋዱ ላይ በአቅራቢያችን ካለ ሆስፒታል ህይወቷ ማለፉን አረዳችኝ እግሬ ተንቀጠቀጠ ተዝለፍልፌ ወደኩ ነገር ግን አላህ ነውሬን ለመጠበቅ የሰጠኝን ሀዲያ እንዳስከፈለኝ ገባኝ ።

  • 🍃 እውነተኛ ፍቅር 🍃 ሰው እንድን ሰው ሲወድ መቼም ቢሆን እንዲለየው አይፈልግም ሄይወቴም ሞቴም ከሱ ጋር ያድርገው ይላል። ከሱ ጋር መቀስቀስ ይመኛል፡፡ ድንገት የተለየው እንደሆን ሀዘን ይበዛል አብሮት ቢሆን በሃሴት ስሜት ጣሪያ ይነካል፡፡ በርግጥ ከሚወዱት ጋር መሆን ምነኛ ያስደስታል ያአላህ!፡፡ የሰውባን የስጋት ለቅሶ!! "ሰውባን ሰሃባ ነው። ምርጥ የነብዩ ወዳጅና አገልጋያቸው ነው፡፡ የአላህ መልእክተኛ (ﷺ) ብዙን ጊዜ ከጎናቸው አይለዩትም ነበር፡፡ አንድ ቀን ግን ነብዩ (ﷺ) በጠዋት ወጡ እስከ ማታም ድረስ ሳይመለሱ ቆዩ፡፡ ወደ ቤት ሲመለሱ  ሠውባን እንደ ህፃን ልጅ ቁጭ ብሎ ሲያለቅስ አገኙት፡፡ ነብዩም ጠየቁት ?ምን አስለቀሰክ ሰውባን ሆይ! ብቻዬን ትተውኝ ጠፉ እኮ አንቱ የአላህ ነብይ! ይህ ነው የሚያስለቅስህ  አሉት አይደለም አንቱ የአላህ መልእክተኛ! ሙሉውን ቀንና ለሊት ብቻዬን ትተውኝ ሲጠፉ ብቸኝነት ተሰማኝ! ደግሞ ጀነት ብገባም እንኳን ደረጃዬ ከታችኛው እንደሚሆን አውቃለው እርሶ የአላህ መልእክተኛ ኖት እና በጀነት ዉስጥ ደረጃዎት ትልቅ ነው፡፡ በጀነት ከርሶ መለያየቴ አሳሰበኝና ስጋት ገብቶኝ አለቀስኩኝ አላቸው። ነብዩ (ﷺ) የሰውባንን ስጋት እንዲህ በማለት አቀለሉለት" ሰውባን ሆይ!! አንድ ሰው ከወደደው ጋር እንደሚቀሰቀስ አላወክም እንዴ ብለው አረጋጉት። የኛ ውድ ነብይ ሰለዋቱ ረቢ ወሰላሙ አለይክ አሏህ ከምንወዳቸው ጋር ያድርገን !!! ‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌┄┅┅┄┅✶🌹✶┅┄┅┅┄

  • ለመጀመሪያ ጊዜ ሀረም መኖር የጀመረችው ሴት ናት;     ሀጀር!! ለመጀመሪያ ጊዜ በነብዩﷺ ያመነችው ሴት ናት;      ኸድጃ!! ለመጀመሪያ ጊዜ በአላህ መንገድ የፈሰሰው ደም የሴት ደም ነው;      ሱመያ!!

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • "ሰዎች በምንም ነገር ላይ እርግጠኛ ሲኾኑ አይቼ አላውቅም; በመሞታቸው ላይ እርግጠኛ እንደ ሚኾኑት።    ከመኾኑም ጋ ግን በመሞታቸው ላይ ጥርጣሬ ያላቸው ይመስል ለሞት ከመዘጋጀት የተዘናጉ ይኾናሉ።"   (ዑመር ኢብን ዐብዱልዐዚዝ) [ الجامع لأحكام القرآن - القرطبي ]

  • #አስተማሪ #ፅሁፍ!!!! ✅አንድ ወንድ ግንኙነት ካደረገ በኋላ የሚለቀቀው የሴመን(የወንድ የዘር ፈሳሺ) መጠን 400 ሚሊዮን ስፐርም ሴል አለው ይላል ሳይንስ። ስለዚህ በዚህ ሎጂክ መሰረት በሴት ልጅ ማህፀን ውስጥ ያ መጠን  ቦታ ቢያገኝ 400 ሚሊዮን ህፃናት ይፈጠራሉ! ይህ 400 ሚሊዮን የወንድ ፈሳሺ እንደጉድ ወደ ሴት ማህፀን እየሮጠ ከ300-500 ብቻ ነው በህይወት የሚተርፈው። ሌላውስ? በመንገድ ላይ በድካም ወይም በሽንፈት ይሞታል። እነዚህ ከ300-500  ናቸው። ይህም ኦቪውል ላይ መድረስ ችለዋል። አንደኛው ብቻ በጣም ጠንካራው ኦቪውሉን ያዳብራል ወይም ኦቪውል ውስጥ ይቀመጣል። ያእድለኛ አንተ ወይም እኔ፣ ወይም ሁላችንም ነን፡፡ #ይህንን #ታላቅ #ጦርነት #አስበው #ያውቃሉ? 1✅. ስትሮጥ "አይን፣ እጅ፣ እግር፣ ጭንቅላት አልነበረም፣ ሆኖም አሸንፈሃል። 2✅. ስትሮጥ ሰርተፍኬት አልነበረህም ጭንቅላት አልነበረህም ግን አሸንፈሃል። 3✅. ስትሮጥ ምንም ትምህርት አልነበረህም፣ ማንም የረዳህ የለም ግን አሸነፍክ። 4✅. ስትሮጥ መድረሻ ነበረህ በአንድ ጭንቅላት ስትሮጥ ያንን መዳረሻ አላማ አድርገህ በመጨረሻ አሸነፍክ። - ከዚያ በኋላ ብዙ ህፃናት በእናት ሆድ ውስጥ ጠፍተዋል። አንተ ግን አልሞትክም 9 ወር ሞላህ 🚩- ብዙ ህፃናት በወሊድ ጊዜ ይሞታሉ አንተ ግን ተርፈሃል። 🚩- በህይወት በመጀመሪያዎቹ 5 አመታት ብዙ ህፃናት ይሞታሉ አሁንም በህይወት አለህ። 🚩- ብዙ ህፃናት በምግብ እጥረት ምክንያት ይሞታሉ። ምንም አልሆንክም። 🚩-ብዙዎች ይህን አለምን ትተው ሄደዋል፤ አንተ አሁንም አለህ። ዛሬ ደግሞ ...... የሆነ ነገር ሲፈጠር ትደነግጣለህ ትበሳጫለህ ግን ለምን? ለምን የተሸነፍክ ይመስልሃል? ለምን በራስ መተማመን አጣችሁ? አሁን ጓደኞች፣ እህት ወንድሞች፣ ሰርተፍኬት፣ ሁሉም ነገር አሉህ። እጅና እግር አለ፣ ትምህርት አለ፣ ለማቀድ ጭንቅላት አለ፣ የሚረዳ ሰው አለ፣ ሆኖም ተስፋ ቆርጠሃል። በህይወት የመጀመሪያ ቀን ተስፋ ሳትቆርጥ ስትቀር በ400 ሚልዮን ሴመን የሞት ሽረት ትግል በማድረግ ያለምንም አጋዥ ብቻውን ውድድሩን በተከታታይ በመሮጥ አሸንፈሀል። የሆነ ነገር ሲፈጠር ቶሎ ተስፋ አትቁረ፡፡ ኮፒፒፒፒ https:/t.me//guzo5

  • #ቤት_እንግዳ_የመዉሰድ_ጥቅም    ሚስት ባሏ እንግዳ ይዞ እየመጣ ስልችት ብሏት ስሞታ ለማቅረብ ወደ ረሱል ﷺ መጣች ችግሯን ዘርዘር አድርጋ  ነገረቻቸው፡፡ ነብዩ ﷺ ዝም ብለው ሰምተዋት ምንም አልመለሱላትም ሴትዮዋ ከሄደች በኋላ ለባሏ አስጠርተው ዛሬ አንተ ቤት እንግዳ ነኝ አሉት ....ባል በጣም ተደስቶ ለሚስት ነገራት ሚስትም በጣም ተደሰተች ራሕመተል ዓለም እቤቷ ሊገቡ ነዋ ቤት  ያፈራው ነገር በደስታ አዘጋጀች ነብዩ ﷺ ገብተው ከተስተናገዱ በኋላ ለባልየው ስወጣ ሚስትህ እኔ በምወጣበት በር ወደዛ እንድትመለከት ንገራት አሉት     ረሱል ﷺ ሲወጡ ሚስት ትመለከታለች ከኋላቸው ጊንጥ እንሽላሊት ሌላም ጎጂ ነፍሳቶች ተከትሏቸው ሲወጡ አየች ሚስት ደንግጣ ዞረባት ....ከዚያም ነብዩ ﷺ እንዲህ አሉ:- "አንድ እንግዳ ከተጠራበት ቤት ሲወጣ ልክ እንደዚህ ከዛ ቤት ችግር በላ እና ጎጂ ነፍሳቶች ተከትለዉት ይወጣሉ"   እንግዳ የሚበዛበት ቤት አላህ የሚወደው ቤት ነው አሉ ♦በሌላ ዘጋባ ረሱል ﷺ እንዲህ ይላሉ አላህ ኸይር የፈለገለት ሰው ስጦታ ይልክለታል ሲሉ ... ያስጦታ ምንድን ነው???ተብለው ሲጠየቁ እንግዳ ብለዉ መለሱ በሌላ ሀዲስ ☞ "እንግዳ የማይገባበት ቤት መላኢካ አይገባበትም" ☞"እንግዳ ወደ ጀነት አመላካች ነው" ☞"በአላህና በመጨረሻው ቀን ያመነ እንግዳውን ያክብር" ብለዋል ሀቢቡና ሙሀመድ ﷺ  ⚡️⚡️⚡️ እንግዳ መጋበዝ አለብኝ ብለን የግድ ከአቅማችን በላይ መጣጣር የለብንም ቤት ባፈራው ሊላህ ብለን ብቻ እንግዳውን ቀልቡ ለማስደሰት በኢኽላስ ከሆነ እንግዳው የሚያስደስተው የምግቡ አይነት ሳይሆን እሱን አክብረን መጥራታችን ነው! አላህ እንግዳን የምናከብርበት ተውፊቅ አላህ ይስጠን

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • ሰውዬው የልጁን ትምህርት ቤት ለመጎብኘት ሄዶ ግቢው ውስጥ ዞር ዞር እያለ ነው ግቢው ውስጥ ከሚገኙት የተማሪዎች መቀመጫዎች ሁሉ አንደኛው ወንበር ተለይቶ ቀይ ቀለም ተቀብቷል : በአይነትም ይለያል "ይህኛው ወንበር ለምንድነው ከሌላው የተለየው? ከዚህ ወንበር ውጪ መቀመጥ አይቻልም?" ሲል አባትየው ጠየቀ "አባዬ ይህ ወንበር 'አጫውቱኝ' ይባላል" "ምንድነው 'አጫውቱኝ ወንበር'?" አባት ግራ ገባው "ከተማሪዎች አንዱ ለትምህርት ቤቱ አዲስ ከሆነ: ነባር ሆኖ ራሱ ቢከፋው: ሌሎች ተማሪዎች ቢያገሉት: ሆድ ብሶት ቢያዝን እዚህ ወንበር ላይ መጥቶ ይቀመጣል:: እዚህ ወንበር ላይ ከተቀመጠ 'ብቸኛ ነኝ አጫውቱኝ' ማለት ፈልጎ ነው አባት ተገረመ * "አንተ እዚህ ተቀምጠህ ታውቃለህ?" አባት ጠየቀ ** "እዚህ ትምህርት ቤት አዲስ ሆኜ ስመጣ አንድም ተማሪ አላውቅም ነበር: ብቸኝነቱ ከብዶብኝ ነበር:: ከዚያም እዚህ ወንበር ላይ መጥቼ ስቀመጥ አንድ ተማሪ መጥቶ ይዞኝ ሄዶ ከሌሎች ጋር ቀላቀለኝ:: ደስተኛም ሆንኩኝ" "እኔም ብሆን እዚህ ወንበር ላይ ተማሪ ተቀምጦ ካየሁኝ መጥቼ አጫውተዋለሁኝ" 👇🏾 አስባችሁታል? ውሏችን ላይ እንዲህ አይነት ቀይ ወንበሮች ቢኖሩ ሲከፋን:ሆድ ሲብሰን:ስናጣ:ሰው ሲርቀን ቁጭ የምንልበት ። https://t.me/guzo5

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • 🌷 እንኳን ለ1445ኛው የዒድ አል አደሓ በዐል በሰላም አደረሳችሁ 🌷 🌟 تقبلﷲ منا ومنكم صالح الأعمال 🔹 ኢዳችን የተባረከ ይሁንልን አላህ ከኔም ከናንተም መልካም ስራችንን ይቀበለን 🌸መልካም በዓል🌸 https://t.me/guzo5

guzo wede jenet — tgindex