- Последний пост
- 12 авг.
- Последнее чтение
- 15 авг.
- Постов за неделю
- 2
- Всего постов
- 21
- Тип
- открытый
- Язык
- und
- В каталоге с
- 15 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 27
- 1/48двое суток
- 30
- 1/72трое суток
- 33
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
🕌 ibnu Masoud islamic Center t.me/merkezuna
https://t.me/hashimbesena
https://t.me/hashimbesena
https://t.me/hashimbesena
https://t.me/hashimbesena
https://t.me/hashimbesena
https://t.me/hashimbesena
https://t.me/hashimbesena
https://t.me/hashimbesena
https://t.me/hashimbesena
يارب 🕋🤲 « ኢላሂ! የማይዘጋ የኡምራ በር እና የማይመለስ (ተቀባይነት ያለው) ዱዓ ስጠን፤ አሚን ያ ረብ!» «ኢላሂ! ይህ አካል ሩህ እስካለው ድረስ መካን ደጋግሞ መዘየር ወፍቀን..» «ኢላሂ! በየትኛውም ጊዜና ወቅት መካን ለመዘየር አብቃን!
ኢላሂ! ወደ መካ የሚያደርሰንን መንገድ የማይቋረጥ አድርግልን፤ ዱንያ ምንም ያህል ብትጠብብን በእሷ ውስጥ ሰፊ እፎይታ የሚያገኝ ልብንም ስጠን። ❤️ ኢላሂ! ደጋግሜ እንድጎበኛት የሚረዳኝን ሲሳይ (ሪዝቅ) ለግሰኝ... አሚን አሚን አሚን #ያ_ረብ 🤍🤲🕊🕋❤️"
ዑምራ፡ የመንፈስ ጉዞ ወይስ የዱንያ መዝናኛ? ዑምራ—የእስልምናን ቅዱሳት ስፍራዎች የመጎብኘት፣ ወንጀልን የማሰሪያ፣ ቀልብን ከዓለማዊ እና ቁሳዊ ሸክም አጥቦ ወደ አላህ ሱብሓነሁ ወተዓላ የመመለሻ ታላቅ መንፈሳዊ ጉዞ ነው። ነገር ግን ከቅርብ ግዜ ወዲህ የሚስተዋሉ አንዳንድ ልማዶችና የቱር አዘጋጆች ዘይቤ፣ የዚህን ታላቅ ዒባዳ ዋና ዓላማ እያሳቱት ይሆን? የሚል እውነተኛ ስጋት እያስነሳ ይገኛል። 1. የዓለማዊ ነገሮች መጎላትና የመንፈሳዊነቱ መቀጨጭ በዑምራ ጉዞዎች ላይ አሁን አሁን ዋና ትኩረቱ ከዒባዳ ወደ መዝናናት ሲያደላ ይስተዋላል። ፈረስ ግልቢያ፣ የቀስት ውርወራ፣ የባህር ላይ የጀልባ ሽርሽር እና መሰል መዝናኛዎች የጉዞው ዋና ማእከል እየሆኑ መጥተዋል። ከሁሉም በላይ ግን አሳዛኙ ነገር፡ በአል-ሐረመይን (በመካው መስጂደል ሐራም እና በነቢያችን መስጂድ) አንድ ሰላት መስገድ እስከ 100,000 ሰላት እጥፍ በነቢዩ መስጂድ ደግሞ አንድ ሺህ የሚደርስ ታላቅ ምንዳ (አጅር) እንዳለው እየታወቀ፣ ያንን ሁሉ እድል አግኝቶ በጨዋታና በመዝናናት ጊዜን በማሳለፍ በጀማዓ መስገድን ማስመለጥ ትልቅ ሂርማን (የአጅር ኪሳራ) ነው። መዝናናት በራሱ የተከለከለ ባይሆንም፣ ቅዱስ ስፍራ ላይ ቆሞ ጊዜን በእንዲህ አይነት ነገሮች ማሳለፍ ግን የዑምራን ዋና መንፈሳዊ ጥቅም እና የልብ መረጋጋት እያመናመነው ይገኛል። 2. የሱህባ እና የሳሊሆች ሚና መዛባት አንድ ሰው ለዑምራ ሲነሳ ከጎኑ የሚፈልገው አላህን የሚያስታውሱት፣ አምልኮቱን የሚያስተካክሉለት እና ወደ አኼራ የሚጠቁሙትን "ሩፍቀት አስ-ሳሊሃ" (መልካም ጓደኞችን) ነው። አሳዛኙ ነገር ግን፣ የቱር ኤጀንሲዎች ማስታወቂያዎቻቸው ላይ ሸሪዓዊ እውቀት ያላቸውን ረባኒይ መሻይኾች እና ዓሊሞችን መሪ ከማድረግ ይልቅ፣ የቲክቶክ እና የማህበራዊ ሚዲያ ተፅዕኖ ፈጣሪዎችን (Activists) እንደ ዋና ሳቢ ማስታወቂያ ማቅረባቸው ነው። መንፈሳዊ መሪዎችን በቲክቶክ አክቲቪስቶች መተካት የጉዞውን ሚዛን ያሳስታል። የዑምራ ጉዞ በቪዲዮ እይታና በፎቶ ብዛት ሳይሆን በዕንባ፣ በዱዓ እና በኢኽላስ የሚለካ ተግባር ነው። የዑምራ አዘጋጆችም ሆኑ ተጓዦች ወደ ህሊናቸው ሊመለሱ ይገባል። ዑምራ የልብ ህክምና እንጂ የካሜራ ትርኢት ወይም የቱሪዝም ሽርሽር አይደለም። የዑምራ ጉዞ እውነተኛ ዓላማውን ሳይስት፣ የአላህን ፍራቻ እና የመንፈስ እድሳትን ማዕከል ያደረገ ይሆን ዘንድ አቀራረባችንን እና አስተሳሰባችንን ልንፈትሽ ይገባል።
اَلسَلامُ عَلَيْكُم وَرَحْمَةُ اَللهِ وَبَرَكاتُهُ 🌿🌿አስደሳች ዜና🌿🌿 🌿🌹🌲🌴🌷🌸🌹🍀🍁🌺🌼🌻 የሴቶች በሴቶች የሙሀደራ ፕሮግራም 🌹🍂🍀🌿🌺🌾🌸💐🍁🌻🌺🌴 የሙሀደራ ፕሮግራም ቢላል ኮካ መስጂድ እና መድረሳ ከልደታ ክ/ከተማ መጅሊስ ጋር በመተባበር ስለተዘጋጀ እርሰዎን ከወዳጅ ዘመድዎ ጋር በአክብሮት ጋብዘንዎታል 🎤🎤🎤 በእለቱ የሚቀርበው ርእስ 👉 " وَتَزَوَّدُوا فَإِنَّ خَيْرَ الزَّادِ التَّقْوَىٰ ۚ " "ተሰነቁም፤ ከስንቅም ሁሉ በላጩ ጥንቃቄ (አላህን መፍራት) ነው " አል- በቀራ 197 👉 ሌሎችም አጓጊ ፕሮግራሞችን ይዘን እናንተን በመጠበቅ ላይ ነን 📅 የፊታችን እሁድ ሀምሌ 26/ 2018 🕝። ሰዐት ፡- ከጠዋቱ 3፡00-6:30 🕌 አድራሻ ፦ ከአሚን ሆስፒታል ወረድ ብሎ በሚገኘው ቢላል ኮካ መስጂድ እና መድረሳ ጥብቅ ማሳሰቢያ ፦ 🪴ይህንን በአይነቱ ልዩ የሆነ ፕሮግራም እንዳያመልጥዎ ፕሮግራሞትን ከወዲሁ በማመቻቸት ከቤተሰብዎ ፣ ከጓደኛዎ፣ ከስራ ባልደረባዎ ጋር ለመታደም ቁጥር አንድ ፕሮግራምዎ አድርገው ይያዙ ። 🍀 ጥሪን ማክበር ኢስላማዊ ስነ-ምግባር ነው !!! ላልሰሙት በማዳረስ የአጅሩ ተካፋይ ይሁኑ።
https://t.me/hashimbesena
https://t.me/hashimbesena
https://t.me/hashimbesena
https://t.me/hashimbesena
https://t.me/hashimbesena
https://t.me/hashimbesena