Unique Academy
Статистика☆ Welcome to Unique Maths! " LEARN UNIQUELY AND FLUENTLY " Join us for effective learning Process.... ☆ Youtube Channal : https://www.youtube.com/@Uniquemathematic ☆ CEO : Henok Debebe
- Последний пост
- 2 июл.
- Последнее чтение
- 13 авг.
- Постов за неделю
- 0
- Всего постов
- 20
- Тип
- открытый
- Язык
- английский
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- —
- 1/48двое суток
- —
- 1/72трое суток
- —
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
https://youtu.be/1c6YyAi5LSY?si=RuvZ0BOmBbgblSbG
#MekelleUniversity በ2018 ዓ.ም ለአቅም ማሻሻያ ትምህርት (ሪሚዲያል ፕሮግራም) መቐለ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ ተማሪዎች ሪፖርት ማድረጊያ ቀን ታህሳስ 12/2018 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል። ከዛሬ ታህሳስ 06/2018 ዓ.ም ጀምሮ የተዘጋጀውን የGoogle Form (https://forms.gle/FYhfCg3dLhTFyQ477) በመጠቀም መረጃችሁን እንድትሞሉ ዩኒቨርሲቲው አሳስቧል። የምዝገባ ቦታ፦ ➫ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች በዋናው ግቢ፣ ➫ የማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች በዓዲ-ሓቂ ግቢ። ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦ ➫ የ12ኛ ክፍል ውጤት መግለጫ፣ ➫ የ8ኛ ክፍል ካርድ ዋናውና ኮፒው፣ ➫ ፓስፖርት መጠን ጉርድ ፎቶግራፍ፣ ከላይ የተዘረዘሩትን የትምህርት ማስረጃዎች እና ፎቶግራፍ ስካን በማድረግ በተዘጋጀው ሊንክ https://forms.gle/FYhfCg3dLhTFyQ477 ላይ ማያያዝ/መላክ ይጠበቅባችኋል። የለሊት አልባሳት ማለትም አንሶላ፣ ብርድ ልብስ እና የትራስ ልብስ እንዲሁም የስፖርት ትጥቅ መያዝ ይኖርባችኋል።
#DillaUniversity በ2018 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስቴር ለሪሚዲያል ፕሮግራም ትምህርት ዲላ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ ተማሪዎች የመግቢያ ጊዜ ታህሳስ 20 እና 21/2018 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡ የምዝገባ ቦታ፦ ➫ በተፈጥሮ ሳይንስ ዘርፍ የተመደባችሁ አዳያኣ ግቢ፣ ➫ በማኅበራዊ ሳይንስ ዘርፍ የተመደባችሁ ሀሴደላ ግቢ። ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦ ➫ ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣ ➫ የ8ኛ እና የ12ኛ ክፍል ሰርትፍኬት ዋናውና ኮፒው፣ ➫ መጠኑ 3x4 የሆነ አራት ፎቶግራፍ፣ ➫ ብሔራዊ መታወቂያ (ፋይዳ)፣ ➫ አንሶላ፣ ብርድ ልብስ እና የትራስ ልብስ።
#WolaitaSodoUniversity ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ በ2018 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስቴር ለሪሚዲያል ትምህርት ወደ ተቋሙ ለተመደቡ ተማሪዎች ጥሪ አድርጓል። የሪሚዲያል ተማሪዎች ምዝገባ የሚከናወነው ታህሳስ 23/2018 ዓ.ም እና በቦዲቲ ካምፓስ የተመደባችሁ ተማሪዎች ጥር 01/2018 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡ የምዝገባ ቦታ፦ ➫ ስማችሁ ከ A-B የሆነ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ቦዲቲ ካምፓስ፣ ቦዲቲ ከተማ ➫ ስማችሁ ከ C-R የሆነ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ዋናው ግቢ፣ ወላይታ ሶዶ ከተማ ➫ ስማችሁ ከ S-Z የሆነ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ዳውሮ ታርጫ ካምፓስ፣ ታርጫ ከተማ ➫ ስማችሁ ከ A-B የሆነ የማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ቦዲቲ ካምፓስ፣ ቦዲቲ ከተማ ➫ ስማችሁ ከ C-S የሆነ የማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ዋናው ግቢ፣ ወላይታ ሶዶ ከተማ ➫ ስማችሁ ከ T-Z የሆነ የማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ዳውሮ ታርጫ ካምፓስ፣ ታርጫ ከተማ ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦ ➫ የ8ኛ ክፍል ሰርተፊኬት ዋናውና ኮፒው፣ ➫ ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና 2 ኮፒ፣ ➫ የ12ኛ ክፍል ሰርተፍኬት ዋናውና 2 ኮፒ፣ ➫ ብሔራዊ መታወቂያ (ፋይዳ)፣ ➫ ብርድ ልብስ፣አንሶላ፣ የትራስ ልብስ እና የስፖርት ትጥቅ፡፡
#MizanTepiUniversity በ2018 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስቴር ለሪሚዲያል ፕሮግራም ትምህርት ሚዛን-ቴፒ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ ተማሪዎች የመግቢያ ጊዜ ታህሳስ 25 እና 26/2018 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡ የምዝገባ ቦታ፦ ➫ በማኅበራዊ ሳይንስ መስክ የተመደባችሁ ሚዛን አማን ከተማ በሚገኘው ዋናው ግቢ፣ ➫ በተፈጥሮ ሳይንስ መስክ የተመደባችሁ ቴፒ ከተማ በሚገኘው ቴፒ ግቢ። ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦ ➫ የ12ኛ ክፍል ሰርተፍኬት ዋናውና ኮፒው፣ ➫ ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና 3 ኮፒ፣ ➫ መጠኑ 3x4 የሆነ የቅርብ ጊዜ ዘጠኝ ፎቶግራፍ፣ ➫ አንሶላ፣ ብርድ ልብስ እና የትራስ ልብስ፡፡
#ArsiUniversity በ2018 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስቴር ለሪሚዲያል ፕሮግራም ትምህርት አርሲ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ ተማሪዎች የመግቢያ ጊዜ ታህሳስ 20 እና 21/2018 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡ የምዝገባ ቦታ፦ በዩኒቨርሲቲው ዋናው ግቢ ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦ ➫ የ8ኛ ክፍል ሰርተፊኬት ዋናውና ኮፒው፣ ➫ ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣ ➫ የ12ኛ ክፍል ሰርተፍኬት ዋናውና ኮፒው፣ ➫ መጠኑ 3x4 የሆነ 4 ፎቶግራፍ፣ ➫ አንሶላ፣ ብርድ ልብስ፣ የትራስ ልብስ እና የስፖርት ትጥቅ፡፡
በ2018 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስቴር ለሪሚዲያል ትምህርት ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ ተማሪዎች የመግቢያ ጊዜ ታህሳስ 15 እና 16/2018 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡ የምዝገባ ቦታ፦ ➫ ስማችሁ ከ A-H የሆነ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ዋናው ግቢ፣ ሆሳዕና ከተማ ➫ ስማችሁ ከ I-Z የሆነ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ዱራሜ ካምፓስ ፣ ዱራሜ ከተማ ➫ ስማችሁ ከ A-L የሆነ የማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ዋናው ግቢ፣ ሆሳዕና ከተማ ➫ ስማችሁ ከ M-Z የሆነ የማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ዱራሜ ካምፓስ ፣ ዱራሜ ከተማ ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦ ➫ የ8ኛ ክፍል ካርድ ዋናውና ኮፒው፣ ➫ ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣ ➫ የ12ኛ ክፍል ሰርተፍኬት ዋናውና ኮፒው፣ ➫ መጠኑ 3x4 የሆነ 8 ፎቶግራፍ፣ ➫ ብሔራዊ መታወቂያ (ፋይዳ)፣ ➫ ብርድ ልብስ፣ አንሶላ፣ የትራስ ልብስ እና የስፖርት ትጥቅ፡፡
#BongaUniversity በ2018 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስቴር ለሪሚዲያል ትምህርት ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ ተማሪዎች የመግቢያ ጊዜ ታህሳስ 06 እና 07/2018 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡ ትምህርት ታህሳስ 08/2018 ዓ.ም የሚጀምር መሆኑ ተገልጿል። ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦ ➫ የ8ኛ ክፍል ካርድ ዋናውና ኮፒው፣ ➫ ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣ ➫ የ12ኛ ክፍል ሰርተፍኬት ዋናውና ኮፒው፣ ➫ መጠኑ 3x4 የሆነ 6 ፎቶግራፍ፣ ➫ ብሔራዊ መታወቂያ (ፋይዳ)፣ ➫ ብርድ ልብስ፣ አንሶላ እና የትራስ ልብስ፡፡
#DambiDolloUniversity በ2018 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስቴር ለሪሚዲያል ፕሮግራም ትምህርት ደምቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ ተማሪዎች የመግቢያ ጊዜ ታህሳስ 21 እና 22/2018 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡ ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦ ➫ ከ8-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣ ➫ የ12ኛ ክፍል ሰርተፍኬት ዋናውና ኮፒው፣ ➫ መጠኑ 3x4 የሆነ የቅርብ ጊዜ 8 ፎቶግራፍ፣ ➫ ብርድ ልብስ፣ አንሶላ እና የትራስ ልብስ፡፡
በ2018 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስቴር ለሪሚዲያል ፕሮግራም ትምህርት መደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ ተማሪዎች የመግቢያ ጊዜ ታህሳስ 06 እና 07/2018 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡ ትምህርት ታህሳስ 08/2018 ዓ.ም ይጀምራል ተብሏል። ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦ ➫ ከ8-12ኛ ክፍል ያሉ የትምህርት ማስረጃዎች ዋናውና ኮፒው፣ ➫ መጠኑ 3x4 የሆነ ፎቶግራፍ፣ ➫ የታደሰ የቀበሌ መታወቂያ፣ ➫ ብርድ ልብስ፣ አንሶላ እና የትራስ ልብስ፡፡
በ2018 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስቴር ወለጋ ዩኒቨርሲቲ ለሪሚዲያል ፕሮግራም ትምህርት የተመደባችሁ ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ ታህሳስ 02 እና 03/2018 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል። ትምህርት የሚጀምረው ታህሳስ 06/2018 ዓ.ም መሆኑ ተገልጿል፡፡ የምዝገባ ቦታ፡- ➫ የማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ጊምቢ ካምፓስ፣ ➫ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ወንዶች ከፊደል A-D እና ሴቶች ከፊደል A-H ሻምቡ ካምፓስ እንዲሁም የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ወንዶች ከፊደል E-Z እና ሴቶች ከፊደል I-Z ዋናው ግቢ ነቀምቴ ከተማ ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦ ➫ የ8ኛ እና የ12ኛ ክፍል ካርድ ዋናውና ኮፒው፣ ➫ ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣ ➫ አራት መጠኑ 3x4 የሆነ ፎቶግራፍ፣ ➫ ብርድ ልብስ፣ አንሶላ፣ የትራስ ልብስ እና የስፖርት ትጥቅ።
#WolkiteUniversity በ2018 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስቴር ለሪሚዲያል ፕሮግራም ትምህርት ወደ ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ ተማሪዎች የመግቢያ ጊዜ ታህሳስ 06 እና 07/2018 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡ ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦ ➫ የ12ኛ ክፍል ሰርተፊኬት ዋናውና ኮፒው፣ ➫ የ8ኛ ክፍል ካርድ ዋናውና ኮፒው፣ ➫ ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣ ➫ ሁለት መጠኑ 3x4 የሆነ ፎቶግራፍ፣ ➫ ብሔራዊ የፋይዳ መታወቂያ (National ID)፣ ➫ ብርድ ልብስ፣ አንሶላ እና የትራስ ልብስ፡፡
#AksumUniversity በ2018 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስቴር ለሪሚዲያል ፕሮግራም ትምህርት ወደ አክሱም ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ ተማሪዎች የመግቢያ ጊዜ ታህሳስ 06 እና 07/2018 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡ በተጠቀሱት ቀናት አክሱም ከተማ በሚገኘው የዩኒቨርሲቲው ዋናው ግቢ በአካል በመገኘት ሪፖርት እንድታደርጉ ተብሏል። ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦ ➫ የ8ኛ እና የ12ኛ ክፍል ካርድ ዋናውና ኮፒው፣ ➫ ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣ ➫ አራት 3x4 የሆነ የቅርብ ፎቶግራፍ፣ ➫ ብርድ ልብስ፣ አንሶላ እና የትራስ ልብስ፡፡
#DebarkUniversity ደባርቅ ዩኒቨርሲቲ በ2018 ዓ.ም የሪሚዲያል ፕሮግራም ትምህርት ለመከታተል ወደ ተቋሙ ለተመደቡ ተማሪዎች አድርጎት የነበረውን ጥሪ አራዝሟል፡፡ ለህዳር 25 እና 26/2018 ዓ.ም አድርጎት የነበረውን ጥሪ ያራዘመው ዩኒቨርሲቲው፤ የሪሚዲያል ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ ታህሳስ 16 እና 17/2018 ዓ.ም መሆኑን ገልጿል፡፡ ትምህርት ታህሳስ 20/2018 ዓ.ም ይጀምራል ተብሏል፡፡
#InjibaraUniversity በ2018 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስቴር ለሪሚዲያል ፕሮግራም ትምህርት ወደ እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ ተማሪዎች የመግቢያ ጊዜ ታህሳስ 09 እና 10/2018 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡ ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦ ➫ ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣ ➫ የ8ኛ እና የ12ኛ ክፍል ካርድ ዋናውና ኮፒው፣ ➫ አራት 3x4 የሆነ ፎቶግራፍ፣ ➫ ብርድ ልብስ፣ አንሶላ እና የትራስ ልብስ፡፡
#DebreBerhanUniversity በ2018 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስቴር ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ የሪሚዲያል ፕሮግራም ትምህርት ለመከታተል የተመደባችሁ ተማሪዎች ሪፖርት ማድረጊያ ቀናት ታህሳስ 02 እና 03/2018 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡ የምዝገባ ቦታ፦ በተመደባችሁበት ካምፓስ ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦ ➫ ሁለት 3x4 የሆነ ፎቶግራፍ፣ ➫ የ8ኛ ክፍል ውጤት ዋናውና ኮፒው፣ ➫ የ12ኛ ክፍል ውጤት ዋናውና ኮፒው፣ ➫ ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣ ➫ አንሶላ፣ ብርድ ልብስ እና ትራስ ጨርቅ፡፡
#DebreMarkosUniversity በ2018 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስቴር ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የሪሚዲያል ፕሮግራም ትምህርት ለመከታተል የተመደባችሁ ተማሪዎች ሪፖርት ማድረጊያ ቀናት ታህሳስ 02 እና 03/2018 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡ የምዝገባ ቦታ፦ የማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች የሆናችሁና የስማችሁ የመጀመሪያ ፊደል ከ A-L የሚጀምር እንዲሁም የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች የሆናችሁና የስማችሁ የመጀመሪያ ፊደል ከ A-B የሚጀምር በቡሬ ካምፓስ፤ ሌሎች የተፈጥሮ ሳይንስና የማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች በዋናው ግቢ ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦ ➫ የ10ኛ ክፍል እና የመሰናዶ ትምህርት ያጠናቀቃችሀብት ውጤት ዋናውና ኮፒው፣ ➫ ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣ ➫ ስምንት 3x4 የሆነ ፎቶግራፍ፣ ➫ አንሶላ፣ ብርድ ልብስ፣ ትራስ ጨርቅ እና የስፖርት ትጥቅ፡፡
#WerabeUniversity በ2018 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስቴር ለሪሚዲያል ፕሮግራም ወራቤ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ ታህሳስ 02 እና 03/2018 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡ ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦ ➫ ከ8ኛ ክፍል ጀምሮ ያሉ የትምህርት ማስረጃዎች ዋናውና ኮፒው፣ ➫ መጠኑ 3×4 የሆነ ሁለት ፎቶግራፍ፣ ➫ ብሔራዊ መታወቂያ (Fayda)፣ ➫ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN)፣ ➫ ብርድ ልብስ፣ አንሶላ፣ ትራስ ልብስ እና የስፖርት ትጥቅ፡፡ ከህዳር 21 እስከ ታህሳስ 01/2018 ዓ.ም ድረስ registrar.wru.edu.et የሚለውን ማስፈንጠሪያ በመጠቀም የተጠየቁ መረጃዎችን እንድትሞሉ ይጠበቅባችኋል።
#UniversityOfGondar በ2018 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስቴር ለሪሚዲያል ፕሮግራም ጎንደር ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ ህዳር 29 እና 30/2018 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡ ትምህርት የሚጀምረው ታህሳስ 01/2018 ዓ.ም መሆኑ ተገልጿል። የምዝገባ ቦታ፦ የሁሉም ተማሪዎች ምዝገባ በአጼ ፋሲል ግቢ ይከናወናል። ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦ ➫ የ8ኛ ክፍል ሰርተፊኬት ዋናውና ኮፒው፣ ➫ ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣ ➫ የ12ኛ ክፍል ሰርቲፊኬት ዋናውና ኮፒው፣ ➫ መጠኑ 3×4 የሆነ ሁለት ፎቶግራፍ፣ ➫ አንሶላ፣ ብርድ ልብስ እና ትራስ ልብስ፡፡
#SamaraUniversity በ2018 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስቴር ለሪሚዲያል ፕሮግራም ሠመራ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ ህዳር 25 እና 26/2018 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡ ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦ ➫ የ8ኛ እና የ12ኛ ክፍል ሰርተፊኬት ዋናውና ኮፒው፣ ➫ ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣ ➫ መጠኑ 3×4 የሆነ ስምንት ፎቶግራፍ፣ ➫ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN)፣ ➫ አንሶላ፣ ትራስ ልብስ እና የስፖርት ትጥቅ፡፡