tgindex
Profile picture

Profile picture

Статистика

የማውቃትን ትንሽም ብትሆን እናገራለሁ ኑ ስለ ዲናችን እንተዋወስ አልሀምዱሊላህ አላኢእመቲል ኢስላም 👇👇ይህ ግሩፓችን ነው https://t.me/heyruu1 Channel created in october 11 2025

Последний пост
14 авг.
Последнее чтение
15 авг.
Постов за неделю
56
Всего постов
74
Тип
открытый
Язык
ti
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
1 352
+6 за 5 дн.
Сутки
−3
−0,22%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
71
40 постов
Вовлечённость
5,3%
к подписчикам
Постов в день
8,0
всего 74
Упоминаний
1
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
73
1/48двое суток
83
1/72трое суток
90

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • ቆይ ከመተኛታቹ በፊት🖐 ቁርአን መቅራት ካልቻላችሁ ማዳመጡም አጅር አለው መቅራት የምትችሉት ደግሞ ለተደቡር እና ሙራጀኣ ለማድረግ ይሆናችኋል። ለቀልቦ ስንቅ ቁርዓን 👇

  • ➻ብርቱ  ሴት   ማለት  የማትወድቅ ሳይሆን  በወደቀችበት ቦታ ተነስታ  አቦራውን አራግፋ  ጉዞዋን የምትቀጥል  ናት አንቺ ደግሞ ያቺ ብርቱ ሴት ነሽ። ~~~💥🌹

  • 🙈🙂‍↕️

  • https://t.me/mekistudent 👆ኑ እስኪ እዚህ ጀመዓው ነቃ ደንገጥ በሉ 🤭

  • 14. በመውሊድ በዓላት የተከበሩ የአላህ ቤቶች በጭብጨባ፣ በውዝዋዜና በጭፈራ ክብራቸው ይረከሳል። ይሄ ደግሞ አላህ ከሃዲዎችን እንዲህ ሲል ከወቀሰባቸው ነገሮች ውስጥ ነው፡- (وَمَا كَانَ صَلَاتُهُمۡ عِندَ ٱلۡبَيۡتِ إِلَّا مُكَآءٗ وَتَصۡدِيَةٗۚ) {በቤቱ ዘንድም ስግደታቸው ማፏጨትና ማጨብጨብ እንጂ ሌላ አልነበረም።} [አል-አንፋል፡ 35] ሃያሉ ጌታ እንዲከበሩና…

  • ለሽያጭ የቀረበ ኢስላማዊ የቴሌግራም ቻናል 3k subscribers ✅ View ✅ እዉነተኛ ገዢ ብቻ ያናግረኝ 👉 @selluhi

  • ምንድነው ይሄ ነገር ግን እህ

  • 14 авг.7удалён 15 авг.

    📚ኪታቡ ተዉሂድ በነፃ መቅራት ምትፈልጉ ይሄ ማስታወቂያ ለናንተ ነው 🫵 🏮ከናንተ ሚጠበቀው ቻናሉን ተቀላቅሎ መማር ብቻ ነው👇

  • ከ አሁን በኋላ ማለት ነው እኔ የለሁም እዚህ ቻናል ላይ ያው እንደሚታወቀው እናንተ react አላደርግም ብላችኋል እኔም አልፅፍም ደህና ሁኑ react 👍🏼 ስታደርጉ እመለሳለሁ bye bye 🥹

  • 14 авг.732из burhan_tube

    . የይቅርታ ልብ አለኝ እኮ ግን ደግሞ የተደረገብኝን የማይረሳ ጭንቅላት ነው ያለኝ❤️‍🩹

  • без подписи

  • 14 авг.27удалён 15 авг.

    🌿 ነቢያችን የእኔ ስም ተነሥቶ{ﷺ} ሰለዋት የማያወርድ ሰው ____ ብለዋል‼️ ተሳተፉ ቀላል ጥያቄ ነው! ​•┈┈•┈┈•⊰✿◇✿⊱•┈┈•┈┈• © 𝐖𝐚𝐯𝐞⚡️@Ihsan_wave

  • 14. በመውሊድ በዓላት የተከበሩ የአላህ ቤቶች በጭብጨባ፣ በውዝዋዜና በጭፈራ ክብራቸው ይረከሳል። ይሄ ደግሞ አላህ ከሃዲዎችን እንዲህ ሲል ከወቀሰባቸው ነገሮች ውስጥ ነው፡- (وَمَا كَانَ صَلَاتُهُمۡ عِندَ ٱلۡبَيۡتِ إِلَّا مُكَآءٗ وَتَصۡدِيَةٗۚ) {በቤቱ ዘንድም ስግደታቸው ማፏጨትና ማጨብጨብ እንጂ ሌላ አልነበረም።} [አል-አንፋል፡ 35] ሃያሉ ጌታ እንዲከበሩና ስሙ እንዲወሳባቸው ባዘዘባቸው መስጂዶች ውስጥ ድቤ መደብደብ፣ ማጨብጨብና መጨፈር በአራቱም መዝሀብ የተወገዘ እጅግ አስነዋሪ ተግባር ነው። ይህን ቆሻሻ ተግባር መቃረቢያ አድርጎ ማሰብ ደግሞ የለየለት ጥመት ነው። ኢብኑል ጀውዚይ፡ “ዳንስን ወደ ላቀው አላህ መቃረቢያ ነው ብሎ የሞገተ ሰው ከኢስላም እንደሚወጣ የዑለማዎች ኢጅማዕ ተቋጭቷል” ብሏል። [ሶይዱል ኻጢር፡ 168] 15. ብዙ የመውሊድ ዝግጅቶች የሴትና የወንድ ቅልቅል በብዛት አለባቸው። የብል -ግና መናሃሪያ እየሆኑም ነው። በእለቱ እቃ እያዞሩ የሚሸጡ ሰዎች ሲጋራ፣ ኮንዶምና መሰል ነገሮችን እንደሚይዙ ተጨባጭ መረጃ አለ። በአንዳንድ አካባቢዎች ሴተኛ አዳሪዎች መውሊድ በሚከበርበት አካባቢ የተለያዩ ነገሮችን ለመሸጥ በሚል ሽፋን ጊዜያዊ ዳስ በመቀለስ ለጥፋት እንደሚሰማሩ ከሰበሰብኳቸው መረጃዎች አረጋግጫለሁ። አል-መቅሪዚይ በ790 ሂጅሪያ በዒማዱል አንባኒይ በተዘጋጀው መውሊድ ላይ የታዘበውን እንዲህ ሲል ይገልፀዋል፡- “ሜዳው በዓሊሞች እስከሚጨናነቅ ህዝብ ጎረፈ። በዚያች ሌሊት ሴቶችና ወጣቶች ከባለጌዎች ጋር በመቀላቀላቸው ምክንያት ብዙ አይነት ብልግናዎች ተፈፀሙ። ማለዳ ላይ ሌሊቱን የተጠጡ ከሃምሳ በላይ የአስካሪ መጠጥ እንስራዎች በዛውያው ዙሪያ በነበሩ እርሻዎች ውስጥ ተጥለው እንደተገኙ፣ በርካታ ደናግላንም ክብረ-ንፅህናቸው እንደተገሰሰ፣ በጣም ብዙ ገንዘብ የወጣባቸው ሻማዎችም እንደተለኮሱ እጅግ በርካታ መረጃ ወጥቷል። በማግስቱ ጧት አላህ የንፋስ ጥቃት ላከባቸውና ከቦታው የነበሩ ሰዎችን ፊታቸውን አፈር አለበሳቸው። ድንኳኖቹንም ቆራረጣቸው። አንድም ሰው ባህር መሳፈር አልቻለም። ከዚያን ጊዜ በኋላ መውሊድ አልተዘጋጀም።” [ዱረሩል ዑቁዲል ፈሪዳህ፡ 2/501] 16. የመውሊድ ጨፋሪዎች በውዝውዛኔና መሰል ነገሮች ሰውነታቸው ዝሎ ሌሊቱን ገፍተው ስለሚተኙ አብዛኞቹ የፈጅር ሶላትን የተወሰኑት ደግሞ ዙህርንም ጭምር አይሰግዱም። ለነገሩ ክፍለ - ሃገር ላይ አብዛኛው ታዳሚ ከነጭራሹ ሶላት ሰጋጅ አይደለም። 17. መውሊድ ለማክበር አገር አቋርጠው ረጃጅም ርቀቶችን የሚጓዙ ሰዎች ሞልተዋል። ነብዩ ﷺ ግን ለቢድዐ ቀርቶ ለአላህ ታስቦ ለሚፈፀመው አምልኮት እንኳን ከሶስቱ መስጂዶች (መስጂደል ሐራም፣ መዲና የነብዩ መስጂድ እና አቅሷ) ውጭ አገር አቋርጦ መጓዝ እንደማይገባ አሳስበዋል። [ቡኻሪ፡ 1189] [ሙስሊም፡ 3450] አገር አቋርጠው ያለ መሕረም የሚጓዙ ሴቶችም ቀላል አይደሉም። ነብዩ ﷺ ግን “ማንኛዋም ሴት ከቅርብ ወንድ ቤተሰቧ ጋር እንጂ እንዳትጓዝ” ብለዋል። [ቡኻሪ፡ 1862] 18. መውሊድ የልዩነት መንሰኤ ነው። ለዚህም መውሊድ በተቃረበ ቁጥር የሚነሳውን ውዝግብ መስማቱ ብቻ በቂ ነው። በመውሊድ ላይ ስላልተጋሯቸው ብቻ “ወሃ ~ ቢ”፣ “የነቢ ጠ ^ላት”፣ “ከአይ ^ ሁድ በከፋ ዲን ያበላሹ” እያሉ ሙስሊሞችን መወንጀል የተለመደ ዘመቻ ነው። ኢብኑ ተይሚያ ረሒመሁላህ እንደሚሉት “ቢድዐ ከልዩነት ጋር የተቆራኘ ነው።” ስለዚህ ቢድዐው እስካለ ድረስ መለያየቱ አይቀርም። ሸውካኒይ እንዲህ ይላሉ፡- “ደግሞም ይሄ መውሊድ ከተከሰተ በኋላ ውዝግቡ ተጧጡፏል። በዚህም ላይ የሚፃፉት ኪታቦች ከከልካዩም ከፈቃጁም በዝተዋል። … ከነሱ ውስጥ እንደማይፈቀድ ቁርጥ አድርጎ የተናገረ ሲኖር ከነሱ ቢድዐነቱን አምኖ መጥፎ ነገር ካልተቆራኘው በሚል መስፈርት የፈቀደው አለ፣ ምንም ማስረጃ ግን አላመጣም።” [አልፈትሑ ረባኒይ፡ 2/1091 - 1095] ጥፋቶቹ እነዚህ ብቻ አይደሉም። ይህን ሁሉ ጉድ አጭቆ የያዘ ቢድዐ ከጥቃቅን ነገሮች ነውን? ህሊና ያለው ይፍረድ። በርግጥ ከነዚህ ጥፋቶች ውስጥ ከፊሎቹን የሚርቁ አሉ። ግና አንደኛ ጥቂት ናቸው። ሁለትኛ እነዚህ እራሱ ድግሳቸውን በሺርክ የተቀላቀለ መንዙማ ባዮችን ይጋብዙበታል። ከሺርኩ ቢጠራም ድርጊቱ በራሱ መረጃ የለውምና ከቢድዐነት አይዘልም። ሶስተኛ በጥፋት የተወረረውን መውሊድ ሊያወግዙ ቀርቶ የሚያወግዙትን የሚነቅፉ ናቸው። ስለሆነም ጥፋታቸው ከነዚያኞቹ ጥፋት ብዙም የራቀ አይደለም። ኢብኑ ሙነወር

  • በደንብ ይነበብ . Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር): የመውሊድ አደጋዎች ~ ከመውሊድ ቢድዐ የምናስጠነቅቀው መነዛነዝ ስለሚያምረን፣ በአጉል ቡድንተኝነት ተነሳስተን ወይም በሌላ ምክንያት ሳይሆን እነዚህ አደጋዎች ስላሉበት ወገናችን እንዲነቃ በማሰብ ነው። 1. መውሊድን ማክበር የነብዩን ﷺ እና የምርጥ ትውልዶቻቸውን ፈለግ መጣስ ነው። አላህ እንዲህ ይላል፡- (وَمَن يُشَاقِقِ ٱلرَّسُولَ مِنۢ بَعۡدِ مَا تَبَيَّنَ لَهُ ٱلۡهُدَىٰ وَيَتَّبِعۡ غَيۡرَ سَبِيلِ ٱلۡمُؤۡمِنِينَ نُوَلِّهِۦ مَا تَوَلَّىٰ وَنُصۡلِهِۦ جَهَنَّمَۖ وَسَآءَتۡ مَصِيرًا) {ቅኑም መንገድ ከተገለፀለት በኋላ መልእክተኛውን የሚጨቃጨቅና ከአማኞቹም መንገድ ሌላ የሆነን የሚከተል ሰው በተሾመበት ላይ እንሾመዋለን። ጀሀነምንም እንከተዋለን። መጨረሻይቱም ከፋች።} [አን-ኒሳእ፡ 115] 2. መውሊድ “ዒባዳ ነው” ብሎ የሚያስብ ሰው “ዲኑ ሙሉእ ነው” የሚለውን ጌታ እያስተባበለ፣ ነብዩ ﷺ አደራቸውን አልተወጡም እያለ እየሞገተ ነው። ኢማሙ ማሊክ እንዲህ ይላሉ፡- “በኢስላም ውስጥ መልካም ናት ብሎ የሚያስባትን ቢድዐ የፈጠረ ሰው ሙሐመድ ﷺ ተልእኳቸው ላይ ሸፍጥ ሰርተዋል ብሎ እየሞገተ ነው። ምክንያቱም አላህ {ዛሬ ለናንተ ሃይማኖታችሁን ሞላሁላችሁ} ብሏልና።” [ሱነኑ ዳሪሚይ፡ 141] ነብዩ ﷺ በመሰናበቻው ሐጅ ላይ “አጥብቃችሁ ከያዛችሁት ከሱ በኋላ የማትጠሙበትን ነገር በርግጥም ትቼላችኋለሁ፣ የአላህን ኪታብ። እናንተ ስለኔ ትጠየቃላችሁና ምንድን ነው የምትሉት?” ሲሉ ሶሐቦችም “አንተ በርግጥም እንዳደረስክ፣ አደራህን እንደተወጣህና እንደመከርክ ነው የምንመሰክረው” አሉ። ይህኔ አመልካች ጣታቸውን ወደ ሰማይ እያነሱ ከዚያም ወደ ሰዎቹ እየጠቆሙ “ጌታዬ ሆይ! መስክር” አሉ ሶስት ጊዜ በመደጋገም። [ሙስሊም፡ 3009] 3. የመውሊድ ቢድዐን የሚፈፅም ሰው የማይመነዳበትን ከንቱ ልፋት እየለፋ ነው ያለው። ነብዩ ﷺ “የእኛ ትእዛዝ የሌለበትን ስራ የሰራ እሱ (ስራው) ተመላሽ (ውድቅ) ነው” ብለዋል። [ቡኻሪ፡ 3/69] [ሙስሊም፡ 4590] 4. ይህን ቢድዐ የሚፈፅም ሰው ጥመት ላይ ነው። ነብዩ ﷺ “መጤ የሆኑ ነገሮችን ተጠንቀቁ። መጤ ፈሊጥ ሁሉ ፈጠራ ነው። ፈጠራ ሁሉ ጥመት ነው። ጥመት ሁሉ ወደ እሳት ነው” ብለዋል። [ኢርዋኡል ገሊል፡ 608] 5. መውሊድ የሚያከብርና እንዲከበር የሚሟገት ሰው ከሸሪዐ ክፍሎች ውስጥ አንዱ የሆነውን ነብዩን ﷺ የመውደድ ፅንሰ-ሀሳብን እያዛባ ነው። እሳቸውን ስለመውደድ፣ ስለማክበርና ስለመከተል የሚያትቱ ብዙ የቁርኣን አያዎችን፣ ሐዲሦችንና የሰለፎች ንግግሮችን ቀደምቶቻችን ባልተረዱት መልኩ በመተንተን እነሱ ላልፈፀሙት ቢድዐ ማስረጃ በማድረግ ነብዩን ﷺ መውደድ ማለት መውሊድን ማክበር፣ በሶለዋት ስም መጨፈር ተደርጎ እንዲሳል ተደርጓል። ይህ እሳቸውን የመውደድን ሸሪዐዊ ትእዛዝ ማዛባት ነው። 6. መውሊድን ማክበር በአንድምታ ቀደምቶቻችንን በነገር መውጋት አለበት። ሶሐቦችና ተከታዮቻቸው ከኛ በበለጠ ነብዩን ﷺ የሚወዱ ከመሆናቸው ጋር መውሊድን አላከበሩም። ዛሬ መውሊድን የሚያከብረው የነብዩ ﷺ ወዳጅ፣ የሚቃወመው ደግሞ የሳቸው ጠላት ተደርጎ እየተሳለ ነው። በነዚህ ሰዎች አረዳድ መሰረት ቀደምት ሰለፎችም ነብዩን ﷺ “አይወዱም ነበር” ማለት ነው። ይሄ አደገኛ ጥፋት ነው። እነዚያ ለነብዩ ﷺ ሲሉ አጥንታቸውን የከሰከሱ፣ ደማቸውን ያፈሰሱ፣ ቤታቸውን ያፈረሱ፣ ገንዘባቸውን የለገሱ ሶሐቦች መውሊድን ስላላከበሩ እሳቸውን “አይወዱም” ቢባል ማን ያምናል?! 7. መውሊድ በአብዛኛው ከባባድ የሆኑ ሺርኮች ይፈፀሙበታል። ለቀብር ሱጁድ የሚወርዱ፣ ለቀብር የሚሳሉ፣ ቀብር ጦዋፍ የሚያደርጉ፣ የቀብር አፈር ለበረካና ለፈውስ የሚወስዱ፣ በጥብጠው የሚጠጡ፣ ስለታቸውን የሚያደርሱ፣... አሉ። መንዙማዎቹ እራሳቸው በሺርክ የታጨቁ ናቸው። {አላህ በርሱ ማጋራትን በፍፁም አይምርም።} [አን-ኒሳእ፡ 48] 8. መውሊድ ከክርስቲያኖች ጋር መመሳሰል አለበት። የነብይን ልደት በዓል አድርጎ መያዝ ክርስቲያናዊ ሱና ነው። ክርስቲያኖች ገናን የሚያከብሩት የዒሳ ልደት ነው በሚል እንደሆነ የሚታወቅ ነው። ነብዩ ﷺ “ከሆኑ ሰዎች ጋር የተመሳሰለ ከነሱው ነው” ብለዋል። [ኢርዋኡል ገሊል፡ 1269] 9. መውሊድ ውስጥ ብዙ አይነት ድንበር ማለፍ አለ። በነብዩ ﷺ ላይ፣ በሌሎችም ሙታኖች ላይ ድንበር ማለፍ ይፈፀማል። ይሄ በእለቱ በሚነበቡ ግጥሞች፣ መንዙማዎችና ዶሪሖች ላይ በሰፊው የሚንፀባረቅ ነው። ነብዩ ﷺ ግን “ክርስቲያኖች የመርየምን ልጅ ዒሳን ድንበር አልፈው እንዳወደሱት አታወድሱኝ” ብለዋል። [ጋየቱል መራም፡ 123] አንዳንዶች በድፍረት የመውሊድ ሌሊት ከለይለተል ቀድር የበለጠ ነው ብለው እስከሚሞግቱ ደርሰዋል። [አልመዋሂቡ ለዱንያህ፡ 1/135] ሱብሓነላህ! ይህ ሁሉ የሚባለው እንግዲህ የተወለዱበት ቀን አወዛጋቢ ከመሆኑ ጋር ነው። ይህ ሁሉ የሚሆነው የተወለዱት በሌሊት እንደሆነ የሚጠቁም መረጃ በሌለበት ነው። በዚያ ላይ የተወለዱበት ጊዜ ከ 14 ከፍለ-ዘመናት በፊት ያለፈ እንጂ እንደ ለይለተል ቀድር በያመቱ የሚመላለስ አይደለም። ዐልዩል ቃሪ (1014 ዓ. ሂ.) “(የለይለተል ቀድር) በላጭነት ዒባዳ በሷ ውስጥ በላጭ ስለሆነ እንጂ በሌላ ምክንያት አይደለም። ይህም {መወሰኛይቱ ሌሊት ከሺህ ወር በላጭ ናት} በሚለው ቁርኣናዊ ምስክርነት ነው። ለመውሊዳቸው ግን ይህቺ ብልጫ ከቁርኣንም፣ ከሱናም፣ ከሙስሊሙ ህዝብ ዑለማዎች ከአንድም አትታወቅም!” ይላሉ። [አልመውሪዱ ረዊይ፡ 97] 10. መውሊድን ከኢስላማዊ በዓላት ውስጥ ማካተት ሁለት አመታዊ በዓል ያደረጉልንን ነብይ ትእዛዝ መጣስ ነው። ነብዩ ﷺ መዲና ሲገቡ ነዋሪዎቿ የሚጫወቱባቸው ሁለት ቀናት ነበሯቸው። “ምንድን ናቸው እነዚህ ሁለት ቀናት?” ሲሉ ጠየቁ። “በጃሂሊያው ጊዜ እንጫወትባቸው ነበርን” አሉ። ይህኔ “የላቀው አላህ ከነሱ በላጭ በሆኑ ሁለት ቀናት ተክቶላችኋል። እነሱም የአድሓ ቀን እና የፊጥር ቀን ናቸው” አሉ። [ሶሒሕ አቢ ዳውድ፡ 1039] 11. የመውሊድ በዓልን ማክበር ለሌሎች የቢድዐ በዓላት በር መክፈት ነው። የወሊዮች ልደት እያሉ በመቃብር ዙሪያ ለሚልከሰከሱ፣ የልጆች አመታዊ ልደት ለሚያከብሩ ሰዎችና ለሌሎችም ምርኩዝ ማቀበል ነው። 12. የመውሊድ ኪታቦችና የመውሊድ ድግሶች በነብዩ ﷺ ስም በሚነገሩ የውሸት ቂሷዎች የታጨቁ ናቸው። “አብዛኛው በመውሊድ ደስኳሪዎች እጅ ያለው ውሸትና ቅጥፈት ነው” ይላሉ መውሊድ ደጋፊ የሆኑት ሰኻዊ። [አልመውሊዱ ረዊይ፡ 32] መልእክተኛው ﷺ ግን “በኔ ላይ ሆን ብሎ የዋሸ ሰው መቀመጫውን ከእሳት ያዘጋጅ” ይላሉ። [ቡኻሪ፡ 1291] [ሙስሊም፡ 5] 13. በመውሊድ የቢድዐ ድግስ ላይ ነብዩ ﷺ “ከጭፈራው ይታደማሉ” የሚል ሰቅጣጭ እምነት አለ። የቅጥፈታቸው ቅጥፈት የመውሊዱ ሌሊት ላይ “ነብዩ መጡ” እያሉ ከተቀመጡበት መነሳታቸው ነው። በነገራችን ላይ ነብዩ ﷺ ከሞቱ በኋላ ቀርቶ በህይወት እያሉ እንኳን ሲመጡ ሶሐቦች አይነሱላቸውም ነበር። [አስ-ሶሒሐ፡ 358] ሀይተሚ እንዲህ ይላል፡- “የዚህ አምሳያው ብዙዎች የነብዩ ﷺ ልደትና እናታቸው እሳቸውን መውለዷ ሲወሳ የሚያደርጉት መቆም ሲሆን ይህም ምንም አይነት መረጃ ያልመጣበት ቢድዐ ነው።” [አልፈታወል ሐዲሢያህ፡ 58]

  • 🚨ፈጥኖ ማን ይመልስ ‼️🏃‍➡️🏃‍➡️ ትክክለኛውን  መልስ ያገኝ ሰው  ብዙ  ጠቃሚ ኢስላማዊ ቻናሎችን add የሚለውን በመጫን ያገኛል ። Free promoter👉 @selluhi 👉ጥያቄ፦  ቁርዓን ስንት ምዕራፍ አለው⁉

  • 🕋 ረሱል ﷺ በኔ ላይ አንድ ሰለዋት ያወረደ አላህ በርሱ ላይ __ሰለዋትን ያወርድበታል። ғᴏʀ ᴡᴀᴠᴇ ➙ @Suna_waver

  • የነቢዩ አደም (ዐ.ሰ.) ታሪክ ክፍል 6 — ሸይስ (ዐ.ሰ.) እና የአደም (ዐ.ሰ.) የመጨረሻ ዘመን 🌿 አደም (ዐ.ሰ.) ከልጆቹ መካከል ብዙዎችን በተውሂድና በአላህ መታዘዝ ላይ አስተማረ። ከእርሱ በኋላም ሰዎችን ወደ አላህ መንገድ የሚጠራ ሰው ነበረ። 🌱 ሸይስ (ዐ.ሰ.) በኢስላማዊ ታሪክና በአንዳንድ የታሪክ ዘገባዎች ሸይስ (ዐ.ሰ.) ከአደም (ዐ.ሰ.) ልጆች አንዱ እና ከእርሱ በኋላ የመጣ ነቢይ መሆኑ ይጠቀሳል። ⚠️ ነገር ግን ስለ ሸይስ (ዐ.ሰ.) በቀጥታ የሚጠቅሰው ጠንካራ የተረጋገጠ ሐዲስ አለ ማለት አይቻልም። ስለዚህ የሚነገሩትን ዝርዝሮች በጥንቃቄ ማየት ይገባል። 🕊️ የአደም (ዐ.ሰ.) እድሜ በሐዲስ የመጣው አደም (ዐ.ሰ.) 60 ክንድ (ذراع) ቁመት እንደነበረው ነው። ነቢዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦ «خَلَقَ اللَّهُ آدَمَ وَطُولُهُ سِتُّونَ ذِرَاعًا» “አላህ አደምን ፈጠረው፣ ቁመቱም 60 ክንድ ነበር።” 📚 ሶሒሕ አል-ቡኻሪ፣ ሶሒሕ ሙስሊም የአደም (ዐ.ሰ.) የእድሜ ቁጥር ግን በታሪክ መጻሕፍት የተለያዩ ዘገባዎች አሉት። ስለዚህ በተረጋገጠ ማስረጃ የሚደገፈውን ከደካማ ዘገባ መለየት ያስፈልጋል። 🕯️ የሞቱ ጊዜ አደም (ዐ.ሰ.) ሞት በመጣበት ጊዜ ወደ አላህ ተመለሰ። በሰው ልጅ ታሪክ የመጀመሪያው ነቢይ ሆኖ አላህን አመለከ፣ ልጆቹንም ወደ ተውሂድ አስተማረ። ከእርሱ በኋላ የነቢያት መንገድ ቀጠለ። አደም (ዐ.ሰ.) ለልጆቹ ያስተማረው ትልቁ መልእክት፦ “አላህን ብቻ አምልኩ፣ ከእርሱ ውጭ አምላክ የለም።” የሚል ነበር። React አድርጉ አትከፍሉበትም 🙄 ይቀጥላል

  • ✨ ልዩ የሴቶች ለሴቶች ፕሮግራም 💦 በእህቶች 📖 ርዕስ፡ ኢኽላስ 🕰  ጁመዓ ከ ቀኑ 10:30 ጀምሮ 🧕 ተካፋዮች፡ ለሴቶች ብቻ እርሶም ተገኝተው የዚህ በረካ ተካፋይ ይሁኑ፤ ለሌሎች እህቶችም በማጋራት ጥሪውን ያድርሱ። 👇 https://t.me/+XMks5NGR1LM3NGE0 https://t.me/mekistudent

  • ዛሬ በተወዳጁ ነብይ ላይ... ሶለዋት አውርደዋል??? اللَّهم صَلِّ وَسَلَّم عَلَى نَبِيِّنَا وَحبيبُنا مُحَمَّد، ﷺ

  • የልብ ሐረግ" 💔🍃 ክፍል 𝟏⁸ (አስራ ስምንት) ✍️ ጸሐፊ፦ 𝐄ዘዲን•𝐌 ••••••••••••••••••የሸለቆው ንፋስ አሁን ደም ደም የሚሸት ከባድ ጭጋግ ለብሷል። ሰማዩ በደመና ተጋርዶ የቀኑ ብርሃን ሳይወጣ የቀዘቀዘ ጥላ በምድሩ ላይ ሰፍኗል። ሳሊህ ትዕግስቱ ተሟጧል። በፊቱ የታሰረው ዩሱፍ አካል እንጂ ነፍስ አይመስልም። ደሙ መሬቱ ላይ ረግቶ፣ አቧራው ላይ ጥቁር ምልክት ጥሏል። በእውነተኛ ስቃይ ውስጥ ጊዜ ይቆማል፤ እያንዳንዱ ሰከንድ እንደ አመት ይረዝማል። ሳሊህ ግን ግራ ተጋብቷል፤ የሚገርፈው እሱ፣ የሚጮኸውና የሚማጸነው ዩሱፍ መሆን ሲገባው፣ ክፍሉን የሞላው ግን የሳሊህ ቁጣና የዩሱፍ አሰቃቂ ዝምታ ነው። "ዩሱፍ..." አለ ሳሊህ፣ የግርፋቱን ጅራፍ መሬት ላይ እየጎተተ። ድምፁ አሁን ተስፋ መቁረጥ ይጋባበታል። "ይህ መጨረሻህ ነው። ያቺ ልጅ አሁን ጫካው ውስጥ በውሾቼ ተከባለች። አንተ ለምንም ለሌለው ወረቀት ስትል ነፍስህን ለምን ትሰጣለህ? ዝምታህ ማንን ያድናል? °°°°°°°°°°ዩሱፍ አንገቱን ቀና ለማድረግ ሞከረ። እያንዳንዱ የጡንቻው እንቅስቃሴ እንደ እሳት ያቃጥለዋል። በዓይኑ ላይ የረጋው ደም እይታውን ቢጋርደውም፣ በልቡ ውስጥ ግን ከአለት የጠነከረ ብርሃን አለ። "ሳሊህ..." አለ ድምፁ እንደ ሸካራ ወረቀት እየተሰነጠቀ። "አንተ... ለምታየው ዓለም ትዋጋለህ፤ እኔ ግን ለማላየው ጌታ እገዛለሁ። አንተ እኔን ብትገድለኝ አንድ ዩሱፍ ይሞታል፤ ዝምታዬ ግን ሺህ እውነቶችን በነጻነት ያኖራል። ሞት ለኔ እረፍቴ ነው፤ ለአንተ ግን የፍርሃትህ መጀመሪያ።" ሳሊህ በቁጣ ተሞልቶ ጅራፉን አነሳ። የጅራፉ ድምፅ በአየሩ ላይ ሲሰነጠቅና የዩሱፍን ገላ ሲያርሰው፣ ዩሱፍ ህመሙ አጥንቱ ድረስ ዘልቆ ሲሰርጽ ተሰማው። በዚያች የጭካኔ ቅጽበት ዩሱፍ አይኖቹን ጨፍኖ ወደ ኋላ ተጓዘ። በትዝታው ውስጥ የእናቱ የለይላ መሀመድ ፈገግታ መጣለት። እናቱ ልክ እንደ ዛሬው ስቃይ ሁሉ፣ እሱን ለማሳደግ በፀሐይና በብርድ ስትለፋ የነበረችው ትዝ አለው። "ያ አላህ... አንተ ጠብቃት... አደራህን አድርስ" ሲል በልቡ ተማጸነ። የዩሱፍ ጽናት ሳሊህን ከመቼውም በላይ አስፈራው። ዩሱፍን ሲያየው እንደ ሰው ሳይሆን እንደማይናወጥ ተራራ ታየው። በእውነተኛ ጦርነት ውስጥ ትልቁ ድል ጠላትን መግደል ሳይሆን፣ ጠላት በአንተ ጽናት ፊት የራሱን ባዶነት እንዲረዳ ማድረግ ነው። በተመሳሳይ ሰዓት፣ እኔና አደም በጫካው ውስጥ ከሞት ጋር እየተሽቀዳደምን ነው። የውሾቹ ጩኸት አሁን ከአንገታችን ስር የመጣ ይመስላል፤ ሽታቸው በአየሩ ላይ ተከፍቷል። አደም ፈረሱን ወደ ገደላማው መንገድ ሲያዞረው፣ ፈረሱ በድንጋጤ ቆመ። ከፊታችን ያለው መንገድ በቅርብ በደረሰ ናዳ ተዘግቷል! ወደ ኋላ መመለስ አይቻልም፣ ወደ ፊት መሄድ ደግሞ ገደል ነው። "ወረድ!" አለ አደም በጩኸት። ከፈረሱ ላይ ወርጄ መሬት ላይ ወደቅኩ። እርጥቡ መሬት እጆቼን አሟሸሻቸው። የዛፍ ቅርንጫፎች ፊቴንና እጆቼን ሲቧጭሩኝ፣ የሚሰማኝ የሚፋጅ ህመም ከውስጤ ካለው ስብራት ጋር ሲወዳደር ምንም ነበር። "ዩሱፍ በዚያ ጭካኔ ውስጥ ሆኖ 'ሂጂ' ያለኝ ለዚህ ነው? በዚህ ገደል ዳር እንድሞት?" የሚል የጥፋተኝነት ስሜት እንደ ከባድ ሰንሰለት እግሬ ላይ ተጠመጠመብኝ። በዚያች ሰከንድ፣ ጀርባዬ ላይ አንድ ድንገተኛ የማቃጠል ስሜት ተሰማኝ—ልክ እንደ ዩሱፍ ጀርባ። በመካከላችን ያለው መንፈሳዊ ግንኙነት ርቀቱን ያጠፋው መሰለኝ። ዩሱፍ እዚያ ሲገረፍ፣ እኔ እዚህ ህመሙ ይሰማኛል። አደም የፈረሱን ልጓም ለቀቀውና ወደ እኔ መጣ። አይኖቹ ውስጥ ፍርሃት፣ ድካም እና ጥልቅ ሐዘን ተቀላቅለዋል። አደም እኔን ቀና ብሎ ለማየት ፈራ፤ አይኖቹን ወደ መሬት ሰበረ። በዚያ ዝምታ ውስጥ የዩሱፍን መጨረሻ አነበብኩት። "አደም... ዩሱፍ?" አልኩት ትንፋሼ እየተቆራረጠ። "ሂክማ... አሁን በግርጌው በኩል ባለው ጠባብ ዋሻ ውስጥ ማለፍ አለብን" አለ ድምፁ እየተቆራረጠ፣ ለጥያቄዬ መልስ ከመስጠት በመሸሽ። "ፈረሶቹን እዚህ እንተዋቸዋለን። ውሾቹ በቅርቡ ይደርሳሉ።" በእርጥብ መሬት ላይ እየተንፏቀቅን ወደ ዋሻው ስንገባ፣ የውሾቹ ትንፋሽ ከጀርባችን ይሰማኝ ጀመር። ዋሻው ጨለማ፣ ቀዝቃዛና ትንፋሽ የሚከለክል ነው። እጄን ወደ ደረቴ ሰድጄ የአባቴን የቆዳ ከረጢት አጥብቄ ያዝኩት። በዚያች ሰከንድ ውስጥ፣ የዩሱፍ ድምፅ በጆሮዬ ላይ ያቃጨለ መሰለኝ። "ሂክማ... አደራሽን!" የሚለው ቃሉ የልብ ምቴን አፋጠነው። በዋሻው ውስጥ ጥቂት እንደተጓዝን፣ አደም በድንገት ቆመ። "ሂክማ... አንድ ነገር ልነግርሽ ይገባል" አለ ድምፁ እየተሰነጠቀ። አይኖቹን አሁንም ከእኔ ይሰርቃል። "ዩሱፍ ይሄን መንገድ የመረጠው ለምን ይመስልሻል? እሱ እዚያ የቀረው አንቺን ለማዳን ብቻ አይደለም። ሳሊህ አንቺን መፈለጉን ትቶ እሱ ላይ እንዲያተኩርና ጊዜ እንዲሰጠን ነው። ዩሱፍ አሁን የመጨረሻው እስትንፋስ ላይ ሊሆን ይችላል።" ልቤ ሊቆም ደረሰ። የዋሻው ግድግዳ በላዬ ላይ የሚደፋ መሰለኝ። "አይሆንም... ዩሱፍ አይሞትም!" ብዬ ጮህኩ። ግን ድምፄ በዋሻው ግድግዳ ላይ ተመትቶ ወደ እኔ ተመለሰ። ያ ድምፅ ራሱ የዩሱፍን ስቃይ የሚገልጽ መሰለኝ። "አሁን ማልቀሻ ጊዜ አይደለም" አለ አደም፣ እጄን በሃይል ይዞ እየሳበኝ። እጁ ሲንቀጠቀጥ ተሰማኝ። "የሰማያዊው መስጊድ መዳረሻ እዚህ ዋሻ መጨረሻ ላይ ነው። እዚያ መድረስ አለብን። ዩሱፍ የከፈለውን ዋጋ ባዶ ሆኖ እንዳይቀር ብርታት ይኑርሽ።" ከዋሻው ወጥተን ቁልቁለቱን ስናይ፣ ከሩቅ የሚታየው የሰማያዊው መስጊድ ጉልላት በደመናው መሃል ወጥቶ እንደ ተስፋ ምልክት በራ። ነገር ግን በመስጊዱና በእኛ መካከል ያለው ሜዳ በሳሊህ ወታደሮች እየተከበበ ነው። ዩሱፍ በደሙ ዋጋ የገዛልን ጊዜ አሁን እያለቀ ነው። ጀርባዬ ላይ ያለው ምስጢር፣ በልቤ ውስጥ ያለው የዩሱፍ ፍቅር እና ከፊቴ ያለው ሞት... ሁሉም በአንድ ላይ ተጋጩ። "ያ አላህ! አንተ የዩሱፍን ጽናት ለኔ ጉልበት አድርግልኝ" ስል ጸለየሁ። አደም ሰይፉን መዘዘ። ሰይፉ በደበዘዘው ብርሃን ላይ ሲያንጸባርቅ የመጨረሻው ፍልሚያ መጀመሩን አበሰረ። ዩሱፍ በሸለቆው ውስጥ ለብቻው እየደማ፣ እኔ ደግሞ በዚህ ጫካ አፍ ላይ ተስፋ እየቆረጥኩ... ሁለታችንም ለተመሳሳይ እውነት የመጨረሻውን ዋጋ ለመክፈል ቆመናል። ይቀጥላል•••••••••• Like ማድረግ እንዳይረሳ •••••••