HIDRIN ACADEMY
Статистика- Последний пост
- 6 июл.
- Последнее чтение
- 13 авг.
- Постов за неделю
- 0
- Всего постов
- 33
- Тип
- открытый
- Язык
- und
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- —
- 1/48двое суток
- —
- 1/72трое суток
- —
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
በትግራይ ክልል በወረቀት ለመፈተን ለተመዘገቡ 15,325 የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች ፈተናው ከሐምሌ 22-24/2018 ዓ.ም እንደሚሰጥ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቋል። ተፈታኞቹ በተገለፁት ቀናት በመቐለ እና በአክሱም ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ በወረቀት እንደሚፈተኑ አገልግሎቱ ገልጿል። ተፈታኞች ወደተገለፁት ዩኒቨርሲቲዎች ሐምሌ 20/2018 ዓ.ም በመግባት እና ሐምሌ 21/2018 ዓ.ም ላይ ኦሬንቴሽን በመውሰድ መፈተን የሚችሉ መሆኑን አገልግሎቱ አብራርቷል። በተያያዘ በትግራይ ክልል በበይነ መረብ ለመፈተን የተመዘገቡ 14,755 ተፈታኞች በስድስቱ ዙር ከሰኔ 23/2018 ዓ.ም ጀምሮ ፈተናው እየተሰጠ መሆኑ ተመልክቷል። @hidrinacademy
без подписи
без подписи
የ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተና በአዲስ አበባ ከተማ ሙሉ በሙሉ በበይነ መረብ መሠጠት ጀምሯል። በከተማ አስተዳደሩ ፈተናው ለ58,309 ተማሪዎች በአራት ዙር የሚሰጥ መሆኑን የከተማ አስተዳደሩ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዘላለም ሙላቱ (ዶ/ር) ተናግረዋል። የመልቀቂያ ፈተናው በከተማዋ በ131 የፈተና ማዕከላት በበይነ መረብ እየተሰጠ የሚገኝ ሲሆን፤ በሁሉም የፈተና ጣቢያዎች በቂ ኮምፒውተሮችና የኢንተርኔት አገልግሎት እንዲኖር ቢሮው በቅንጅት ሲሠራ መቆየቱን ገልፀዋዋል። ከ2 ሺህ በላይ የፈተና አስፈጻሚዎች በከተማዋ ባሉ 131 የፈተና ጣቢያው ተመድበው ሒደቱን በመቆጣጠር ላይ እንደሚገኙ ጠቁመዋል። @hidrinacademy
Happening now!! 🎓 🎉 join us https://www.youtube.com/live/zjDjL0S_Ujo?si=wZeW7-DjDFYXCMWp
без подписи
#Grade12 #NationalExam የ2018 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና የሚሰጥበት የጊዜ ሰሌዳ ይፋ ሆነ። የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት የ2018 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና የሚሰጥበትን የጊዜ ሰሌዳ ይፋ አድርጓል። በዚሁ መሠረት በኦንላይን (Computer-based Testing (CBT) የሚፈተኑ ተፈታኞች በስድስት ዙር የሚፈተኑ ሲሆን ከአንደኛ እስከ ሶስተኛ ዙር የተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኞች ይፈተናሉ። ከአራተኛ እስከ ስድስተኛ ዙር የማህበራዊ ሳይንስ ተፈታኞች የሚፈተኑ ይሆናል። ፈተናውን በወረቀት የሚፈተኑ ተፈታኞች የተፈጥሮ ሳይንስ በሶስተኛ ዙር ላይ የሚፈተኑ ሲሆን የማህበራዊ ሳይንስ በአራተኛ ዙር በዩኒቨርሲቲ ውስጥ የሚፈተኑ ይሆናል። (ዝርዝሩ ከላይ በምስል ተያይዟል) @hidrinacademy
без подписи
без подписи
#ስፖርት : አርሴናል ከ22 ዓመታት በኋላ የእንግሊዝ ፕሪሜየር ሊግ ዋንጫ ማሸነፉን አረጋገጠ። አርሴናል ብርቱ ተፎካካሪው ማንችስተር ሲቲ ዛሬ ምሽት ከበርንማውዝ 1 ለ 1 በመውጣቱ በሊጉ አንድ ጨዋታ እየቀረ የዋንጫ ባለቤት መሆኑን አረጋግጧል። ኢትዮጵያን ጨምሮ በዓለም ላይ ከፍተኛ ተወዳጅነትና እጅግ በርካታ ተመልካች ባለው የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የዘንድሮው የውድድር አመት አሸናፊና የዋንጫ ባለቤት አርሴናል ሆኗል። አርሴናል ዋንጫውን ያገኘው ከ22 ዓመታት በኋላ ነው። በአሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ መሪነት ላለፉት ዓመታት የተገነባው ስብስብ በዘንድሮው ውድድር ዘመን በሜዳውም ሆነ ከሜዳው ውጭ ባደረጋቸው ወሳኝ ጨዋታዎች ያስመዘገበው ውጤት ለዚህ ታሪካዊ ስኬት አብቅቶታል። ቡድኑ ከዚህ ስኬት በተጨማሪ የአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ የፍጻሜ ተፋላሚም ነው። @hidrinacademy
без подписи
без подписи
#Update የቅድመ-ምረቃ ትምህርት የመውጫ ፈተና በድጋሚ በግል ለመፈተን እየተጠባበቃችሁ የምትገኙ አመልካቾች ምዝገባ ከዛሬ ግንቦት 08/2018 ዓ.ም ጀምሮ ለአምስት ተከታታይ ቀናት ይካሔዳል፡፡ በመሆኑም የመመዝገቢያ ሊንኩን https://exam.ethernet.edu.et በመጠቀምና የተዘረዘሩ መስፈርቶችን በማሟላት ከግንቦት 08-12/2018 ዓ.ም መመዝገብ የምትችሉ መሆኑ ተገልጿል፡፡ የአገልግሎት ክፍያ 750 ብር በቴሌብር በኩል መክፈል የሚጠበቅባችሁ ሲሆን፤ ፈተናውን ለመውሰድ የፋይዳ መታወቂያ የግድ የሚያስፈልግ መሆኑ ተመላክቷል፡፡ የ2018 ዓ.ም የመውጫ ፈተና ከሰኔ 02-12/2018 ዓ.ም እንደሚሰጥ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት መግለፁ ይታወሳል፡፡ @hidrinacademy
ለተማሪዎችና የሚሆኑ ጠቃሚ ዌብሳይቶች ✔️https://topai.tools : AI search and discovery engine ✔️https://dokie.ai/ : AI presentation maker. ✔️https://nasa.gov/learning-resources : Space science and physics learning materials from NASA. ✔️https://www.desmos.com/ : Interactive graphing calculator and math tools. ✔️https://pdf.io : PDF file conversion service ✔️https://howtogeek.com/ : Tech tutorials, tips, and simple explanations for beginners. ✔️https://www.themarginalian.org/ : Essays exploring creativity, philosophy, literature, and critical thinking. ✔️https://ideas.ted.com/ : Inspiring ideas and thought-provoking perspectives from experts worldwide. ✔️https://goodcalculators.com/ : Free online calculators for various subjects. ✔️https://pdfroom.com/ : Free collection of PDFs, manuals, and ebooks. እንደዚህ አይነት አጋዥ materials፣ ጠቃሚ መልዕክቶች፣ ትኩስ መረጃዎች እንድደርሳቸው ለጓደኞቻችሁ share እድርጉላቸው። @hidrinacademy
без подписи
የዲግሪ ሰርተፊኬት ህትመት በአንድ ማዕከል መከናወን፥ ሐሰተኛ የትምህርት ማስረጃን ለመከላከል ያግዛል ተባለ። የዲግሪ ማስረጃ ወይም ሰርተፊኬት ህትመት በሀገር አቀፍ ደረጃ በማዕከል የሚታተም መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር መጋቢት 02/2017 ዓ.ም ለሁሉም የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች እና የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በላከው ደብዳቤ ማሳወቁ ይታወሳል፡፡ ከዚህ በፊት የነበረው አሰራር ማለትም ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጨረታ ባሸነፈ ድርጅት በኩል የተማሪዎችን የትምህርት ማስረጃ የሚያሳትሙበት ሒደት ለሐሰተኛ የትምህርት ማስረጃ ክፍተት የሚሰጥ እንደነበር በሚኒስቴሩ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የአስተዳደርና መሰረተ ልማት መሪ ስራ አስፈጻሚ ሰለሞን አብርሃ (ዶ/ር) ለፋና ሚዲያ ተናግረዋል። በመሆኑም ሁሉም የመንግሥት እና የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተማሪዎቻቸውን ዲግሪ በአንድ ማዕከል ብቻ እንዲያሳትሙ ይደረጋል ብለዋል። የአዲሱ ዲግሪ ህትመት በዚህ ዓመት የሚጀመር ሲሆን፤ ህትመቱ እስኪደርስ ድረስ ትምህርት ሚኒስቴር ዲግሪ ለሚያስፈልጋቸው ተማሪዎች የድጋፍ ደብዳቤ እንደሚፅፍ ገልፀዋል። በ2017 ዓ.ም የተመረቁ ተማሪዎችን ጨምሮ ከዚህ በኋላ የሚመረቁት ተማሪዎች በሙሉ በአንድ ማዕከል የሚታተመውን ዲግሪ ብቻ እንዲወስዱ ይደረጋል ብለዋል፡፡ ከ2017 ዓ.ም በፊት ተመርቀው ነገር ግን ዲግሪያቸውን ያልወሰዱ ተማሪዎች፥ በአዲሱ አሰራር ብቻ እንደሚስተናገዱ ጠቁመዋል። ከዚህ በፊት በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ሲሰጥ የነበረው ጊዜያዊ የትምህርት ማስረጃ (Temporary Degree) አሰጣጥ በነበረበት እንደሚቀጥል ጠቁመዋል። አሁን ላይ ከ160 በላይ በሚሆኑ የፌዴራል ተቋማት ላይ ሐሰተኛ የትምህርት ማስረጃ የማጥራት ሥራ እየተከናወነ ይገኛል። @hidrinacademy
5ኛ ዙር የINSA Cyber Talent Challenge Summer Camp 2026 ምዝገባ ተጀምሯል። ሰመር ካምፑ የሚሰጥባቸው ዩኒቨርስቲዎች ⚫Addis Ababa Science and Technology University ⚫Bahir Dar University ⚫Haramaya University ⚫Jimma University ⚫Debre Berhan University ⚫Wolaita Sodo University ሙሉ መረጃውን በዚህ link ማግኘት ትችላላችሁ https://t.me/insactc/765 ፍላጎት ላላቸው ታዳጊዎች share አድርጉላቸው። @hidrinacademy
Exit-Exam ፈተና ለመውሰድ ይመዝገቡ! የ2018 ዓ.ም የቅድመ-ምረቃ ትምህርት መውጫ ፈተና ምዝገባ ዛሬ ተጀምሯል። ምዝገባው ከሚያዚያ 26 እስከ ግንቦት 07/2018 ዓ.ም የሚከናወን መሆኑን የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ይፋ ማድረጉ ይታወቃል። ተፈታኞች በተሰጠው የምዝገባ ጊዜ ገደብ ውስጥ ብቻ እንድትመዘገቡ አገልግሎቱ አሳስቧል። @hidrinacademy
የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን የምግብ አገልግሎት የሚረከብ ብሔራዊ ተቋም ሊቋቋም ነው። የኢትዮጵያ ትምህርት ሚኒስቴር በመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ያለውን የተማሪዎች የምግብ አገልግሎት በበላይነት የሚመራ ብሔራዊ ተቋም ለማቋቋም እየሠራ መሆኑን አስታውቋል። ይህ አዲስ ፖሊሲ ዩኒቨርሲቲዎች ከዕለት ተዕለት የተማሪዎች የምግብ አቅርቦት ኃላፊነት ተላቀው ትኩረታቸውን በትምህርት ጥራትና በስትራቴጂካዊ ጉዳዮች ላይ እንዲያደርጉ የታለመ ነው። ትምህርት ሚኒስቴር የግዥ የምግብ ዝግጅት እና ስርጭት ስራዎችን በማዕከል ደረጃ የሚመራ ብሔራዊ የምግብ ኤጀንሲ ለማቋቋም የሚያስችል የፖሊሲ ሰነድ እያዘጋጀ መሆኑ ተገልጿል። የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታው ኮራ ቱሹኔ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንደገለጹት "በአሁኑ ወቅት የዩኒቨርሲቲ አመራሮች በስትራቴጂካዊ ጉዳዮች ላይ ከማተኮር ይልቅ ጊዜያቸውን በተማሪዎች የምግብ አገልግሎት አስተዳደር ላይ እያባከኑ ይገኛሉ" ብለዋል። ሚኒስቴሩ በሁሉም የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ወጥ የሆነ የምግብ ዝርዝር (standardised menu) ተግባራዊ ያደረገ ሲሆን አዲሱ ተቋም ደግሞ የአገልግሎት ጥራትንና ቅልጥፍናን ለማሻሻል ይረዳል። ሚኒስቴሩ እ.ኤ.አ. በ2024 ለአንድ ተማሪ የሚመደበውን የቀን የምግብ በጀት ከ22 ብር ወደ 100 ብር ማሳደጉን ተከትሎ በአሁኑ ወቅት አንድ ተማሪ በአራት ዓመት የዩኒቨርሲቲ ቆይታው ለምግብ ብቻ 140,000 ብር ገደማ የወጪ መጋራት እንዲከፍል ይጠበቃል። ይህ ዕቅድ በአሁኑ ወቅት በሚኒስቴሩና በከፍተኛ ትምህርት ባለድርሻ አካላት መካከል ውይይት እየተደረገበት ያለ ሲሆን የአተገባበር ጊዜውና የተቋሙ አደረጃጀት ዝርዝር መረጃዎች ወደፊት ይፋ ይሆናሉ ተብሎ ይጠበቃል። @hidrinacademy
без подписи