tgindex
طوبى لمن وجد في صحيفته استغفرا كثيرا

طوبى لمن وجد في صحيفته استغفرا كثيرا

Статистика
@http_nesihalemuslimochарабский
Последний пост
24 июн.
Последнее чтение
14 авг.
Постов за неделю
0
Всего постов
25
Тип
открытый
Язык
арабский
В каталоге с
14 авг.
Подписчики
151
0 за 1 дн.
Сутки
0
0,00%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
29
25 постов
Вовлечённость
19,2%
к подписчикам
Постов в день
0,0
всего 25
Упоминаний
0
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
1/48двое суток
1/72трое суток

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • 24 июн.25из abulmusayabhamza

    حرص الصحابة على صيام عاشوراء والخوف من فوته ሶሃቦች ዓሹራን ቀን ለመፃም የነበራቸው ጉጉት እና እንዳያመልጣቸው የነበራቸው ፍራቻ ‏  عن عبدالرحمن بن عوف - رضي الله عنه - : 《 أنه أضحى يوم عاشوراء حتى ارتفع النهار ولا يعلم ، ثم علم بعد ، ففزع لذلك ، ثم صام ، وأمر بالصيام بعد أن أضحى 》. ታላቁ ሶሃቢይ ዐብድራህማን ኢብኑ ዐውፍ አንድ ጊዜ ቀኑ ከፍ እስኪል ድረስ የዓሹራ ቀን መሆኑን ሳያውቅ ዋለ ከዛ ትዝ ሲለው ደንግጦ የቀረውን ቀን ፁሞ ዋለ ሰዎችንም እንዲፆሙ አዘዘ። 📚 صحيح/تهذيب الآثار للطبري (٦٥٧) 📚ሶሂህ/ ተህዚብ አልአሳር ሊጠበሪ (657) 🔗 https://t.me/+eAicTR1AQAcwMjA0

  • 24 июн.21из abulmusayabhamza

    📮 የአሹራ ቀን ፆምና ሙሀረም 📌 የአሹራ ቀን ፆም መቼ ነው የተጀመረው? 📌 እነማን ናቸው የጀመሩት? 📌 ነብዩ እንዴት ነው የፆሙት? 📌 በዚ ኡማ ላይ ሁክሙ ምን ነበረ? 📌 አሁንስ ምንድነው ሁክሙ? 🎙️አቡል ሙሰየብ ሀምዛ ቢን ረሻድ አላህ ይጠብቀው። ـــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــ👇👇👇 📎 https://telegram.me/Al_Furqan_Islamic_Studio/18818 📎 https://t.me/abulmusayabhamza/6665

  • ህይወታችሁ ላይ ፍፁም "አጣብቂኝ" ውስጥ የገባችሁበት አጋጣሚ ወይም ሰዓት ይኖራል ብዬ አስባለሁ! በቃ ወደ ፊት እንዳትሄዱ ትልቅ ማዕበል ይጋርዳቹሃል፣ ወደ ኋላ እንዳልትመለሱ ደግሞ ያሳለፋችሁት ስቃይና የትላንት ስህተታችሁ ልክ እንደ ጠላት ይከተላቹሃል። "አበቃልኝ፣ ከዚህ በኋላ ምንም ተስፋ የለኝም" ብለን ማመን ስንጀምር.. ተስፋ መቁረጥ በራችንን ያንኳኳል። ዛሬ የአሹራን እውነተኛ ትርጉም እና የነቢዩላህ ሙሳን (ዐ.ሰ) እጅግ ፈታኝ የትግልና የድል ጉዞ ከቁርአን ውብ ገፆች ላይ ፈልቅቀን፣ ለልባችን ፍጹም እረፍት እንስጠው። #አሹራ ማለት ዝም ብሎ የሚጾምበት ዕለት ብቻ አይደለም። በሰው ልጅ ዕይታ ፈፅሞ የማይታለፍ የመሰለንን ጨለማ፣ አላህ በታላቅ ጥበቡ እንዴት ወደ ብርሃንና ወደ አስገራሚ ድል እንደቀየረው የሚያሳይ ውብ ማስተማሪያ እንጂ። ታሪኩ የሚጀምረው እጅግ አስፈሪ በሆነ አጣብቂኝ ውስጥ ነው። #ሙሳ (ዐ.ሰ) ምስኪኖቹን የእስራኤል ልጆች ይዘው ከፊርዓውን ዘግናኝ ጭቆና ሌሊት ላይ በምስጢር እየሸሹ ነው። ይሁንና አንድ ቦታ ላይ ሲደርሱ ሁኔታዎች ዝግት ግት አለባቸው። እስቲ ሁኔታውን በአይነ ህሊናችሁ ሳሉት... ከፊታችሁ የተደቀነ፣ ሞገድ የሚያናውጠው ጥልቅ ባህር (ቀይ ባህር) አለ፤ ከበስተጀርባችሁ ደግሞ በቁጣና በበቀል እየነደደ፣ እስከ አፍንጫው የታጠቀውን ሰራዊት አስከትሎ ሊጨፈልቃችሁ የሚጋልበው ጨካኙ ፊርዓውን ወደ እናንተ እየቀረበ ነው። ያኔ አብረዋቸው የነበሩት ሰዎች ሁኔታውን ሲያዩ ሙሉ በሙሉ #በድንጋጤ ውሃ ሆኑ። በሰው እይታና በምድራዊ ስሌት ነገሩ ፍጹም አብቅቷል። ወደ ፊት ቢራመዱ ይሰምጣሉ፣ ወደ ኋላ ቢዞሩ ይታረዳሉ። በከባድ ፍርሃትና በተስፋ መቁረጥ ሆነው ጮኹ፦ "ሁለቱ ጭፍሮች (ቡድኖች) በተያዩ ጊዜ፣ የሙሴ ባልደረቦች፦ 'እኛ በእርግጥ ተደረሰብን (ተያዝን)' አሉ።" እዚህ ጋር ነው እንግዲህ ነገሩ የሚገርመው! በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች እያለቀሱ "ተያዝን" ሲሉ፣ ፊርዓውን ደግሞ አቧራውን እያስነሳ እየቀረበ ባለበት የጭንቀት ጣራ ላይ... የነቢዩላህ ሙሳ (ዐ.ሰ) እውነተኛና በ አላህ ላይ ያላቸው የሚያስቀና #የቂናቸው የተገለጠው። ሙሳ የባህሩን ጥልቀት ወይም የጠላትን ብዛት አይተው "አበቃልን" አላሉም። የሰዎቹን ዋይታ ሰምተው አልተረበሹም። ይልቁንም በቃላት ሊገልጹት በማይችሉት ከባድ እርጋታ ፊታቸውን ወደ ሰማይ አቅንተው፣ ለሰማይና ለምድር የሚበቃ ታላቅ ቃል ተናገሩ፦ ​"(ሙሳ) አለ፦ 'አይደለም (አይደርሱብንም)፤ በእርግጥ ጌታዬ ከእኔ ጋር ነው፤ በእርግጥ ይመራኛል።'" (ሹዐራእ፡ 62) ሙሳ "እንዴት?" ብለው አልተጨነቁም፤ የአላህን ቻይነት (القَادِر) ሙሉ በሙሉ አምነው ተቀበሉ። ልክ እሳቸው ይሄን የየቂን ቃል ተናግረው ሳያበቁ፣ የሰማይ መዝገቦች ተከፈቱ። አላህ ባህሩን በበትራቸው እንዲመቱት አዘዛቸው። ያ የማይታሰበውና በምክንያት የማይገለጸው ታላቅ ተአምር ሆነ! ባህሩ ለሁለት ተሰነጠቀ። እያንዳንዱ የተሰነጠቀው ባህር ልክ እንደ ታላቅ ተራራ ቆመ። ያ ለአደጋና ለሞት ሊዳርግ የነበረው ባህር፣ ለእነሱ ወደ ነጻነት የሚያሻግር ውብ መንገድ ሆነላቸው። ሙሳና ህዝቦቻቸው በሰላም ተሻገሩ፤ ፊርዓውንና ሰራዊቱ ግን በአንድ ላይ ባህሩ ዋጣቸው። አላህ ሀቅን አነገሰ።ይህ ታሪክ ዛሬ "በቃ ህይወቴ ተዘጋጋች፣ ከዚህ ችግር የምወጣበት ምንም አይነት ቀዳዳ የለም" ብለን ለምንቆዝም ሰዎች የሚነግረን አንድ በጣም "ትልቅ እውነት" አለ፦ ኡኽታዬ.. በህይወትሽ ውስጥ ፈተናዎች ሲከቡሽና መውጫ ቀዳዳ ስታጪ.. አላህን ከያዝሽ ካልታሰበ ቦታ መውጫ የማበጀት ኃይል እንዳለው እወቂ።

  • Taatee guyyaa kana keessaa baay'ee nama tuqu, ollaan Kiristaana Seetto Semero Sefer kabajaa fi gammachuu isaanii ibsuuf qaamaan Ustaazaa Khadijaaf badhaasa addaa kennuu isaaniiti. Kun agarsiisa Itoophiyummaa fi jaalala dhugaati! Mul'ata Fuulduraa 🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥 Imala gaarii obboleettii ajaa'ibaa kanaa daran cimsuuf ijaarsi gamoo abbaa darbii 4 eegalamee jira, keessummoota kabajaa har'a dhufaniin daawwatameera. Sagantaa guddaa kana irratti miseensonni Mana Maree Ulamaa'ota Majlisa Federaalaa, hayyoonni bebbeekamoon fi du'aan argamaniiru; Isaan keessaa: ✅Ustadz Yaasiin Nuur ✅Ustadz Muhaammad Fareej ✅Abuu Yaasir Abdulmanal Kebede ✅Ustadz Ibsaa Hasan ✅Sheek Alii Jimmaa ✅ Sheek Muhammad Anwaar ✅ Sheek Muhammad Amiin Temaam ✅ Dr. Sheek Mahmuud Huseen ✅Sheek Mekete Muhe ✅ Ustadz Muhammad Mustafaa ✅ Dr. Samehar Teklee ✅ Hajii Hamzaa Muhammad Nuur ✅ Nurediin Baankii Qur'aanaa irraa ✅ Ani Ahmaddin Jabal fi hayyoonni fi duaatonni gurguddoon biroo argamaniiru. Eebbifamtoonni hundi baga gammaddan! Rabbiin addunyaa fi aakhiratti ifa isiniif haa kennu. Obboleettii keenya gootittii Ustaaz Khadiijaa Debebee Rabbiin carraa gaariin haa badhaasu, umrii dheeraa fi fayyaa gaariin isheef haa qananiisu!

  • ቃሪእ አቡሀኒፋ ሙሐሰን Qaarii Abuu Haniifaa ✅✅✅✅✅✅✅✅ የ9 ዓመቱ ቃሪእ አቡሐኒፋ ሙሐሰን፣ የሰለምቴ እናቱ የኡስታዛ ኸዲጃ ደበበ ልጅ፣ ሙሉ ቁርኣንን በልጅነት ዕድሜው ሀፍዞ በተመረቀበት በትናንትና እለት በጅማ ከተማ በመድረኩ ቁርኣንን ቀርቷል።አላህ ከዓይን ያውጣህ።ለታላቅ ደረጃም ያብቃህ። Qaarii Abuu Haniifaa ✅✅✅✅✅✅✅✅ Qaariin ganna 9 Abuu Haniifaa Muhassan, ilmi haadha isaa ishee simannaa Islaamummaa taasiste Ustaazaa Khadiijaa Dababee, umrii ijoollummaa isaatiin Qur'aana guutuu haffazee guyyaa eebba isaa kaleessaa magaalaa Jimmaatti waltajjii irratti Qur'aana qara'ee jira. Rabbin ija iraa si haeegu. Sadarkaa gudaanis sihagahu. 🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴 ድንቅ ሴት፣ ዳግማዊቷ ከዲጃ 🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥 Dubartii ajaa'ibaa, Kadijjaa lammaffaa 🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥 ዛሬ በጅማ ከተማ፣ ታላላቅ ዑለማኦችና ክቡራን እንግዶች በተገኙበት፣ የ"መድረሰቱ ኸዲጃ ብንት ኹወይሊድ" የቁርኣን ተማሪዎች ደማቅ የምርቃት ፕሮግራም ላይ ተሳትፈን በሰላም ተመልሰናል። አልሐምዱሊላህ! ይህንን ድንቅ መድረሳ የቆረቆረችው፣ ብዙዎቻችን በሚንበር ቲቪ "በየኔ መንገድ" ፕሮግራም ላይ የምናውቃት ባለቤት ሰለምቴዋ ባለ ራዕይ ኡስታዛ ኸዲጃ ደበበ ነች። ይህች ጀግና እህታችን ወደ እስልምና ብርሃን ከመጣች በኋላ፣ የዕውቀትን ጥማት ከራሷ አርክታ አልቀረችም። ቤቷን ጭምር ወደ መድረሳ በመለወጥ፣ በመቶዎች የሚቆጠሩ እናቶችን፣ እህቶችንና ወጣቶችን በቁርኣን ኮትኩታ እያስቀራች ነው። የቁርኣን ሐፊዞች ምርቃት 📶📶📶📶📶📶📶 ከተለያዩ አካባቢዎች የተውጣጡ ከ17 በላይ እህቶችን ከሁለት ዓመታት በላይ በገዛ ቤቷ አስጠግታ፣ መግባና ተንከባክባ ሙሉ ቁርኣንን አሳፍዛ ለዚህ ታላቅ ክብር አብቅታለች። ከእነዚህ እህቶች በተጨማሪ፣ የእሷ ፍሬ የሆነው የ9 ዓመቱ ልጇ አቡሐኒፋ ከተመራቂዎቹ መካከል አንዱ በመሆን ልዩ ታሪክ ሰርቷል! የወርቅ ሽልማት 💢💢💢💢 ለተመራቂ እህቶች (ሐፊዞች) በሙሉ፣ በውጭ ሀገር ፋብሪካ ልዩ ትዕዛዝ የተዘጋጀና እያንዳንዳቸው ስማቸው የተቀረጸበት የወርቅ ስጦታ ተበርክቶላቸዋል። ለታዳጊው አቡሐኒፋ ደግሞ በአዲዳስ (Adidas) ካምፓኒ ስሙ ተፅፎበት በልዩ ሁኔታ የተሰራለት ስኒከር ጫማ ተሸልሟል። ሌላኛዋ የከዲጃ ሴት ልጅ ዛሬ ቁርኣንን በመሀዝ የተመረቀችው የአስራ አራት ዓመቷ ሐሰናት ሙሐሰን በምረቃው እለት እኔ ማን ነኝ? የሚል መጽሐፍ ጽፋ በማሳተም እናቷ ጭምር ሳታውቅ ተዘጋጅቶ መቅረቡ በሚንበር ቲቪ በየኔ መንገድ ዝግጅት ሶፊያ ጀውሃር አማካኝነት በመድረኩ ላይ ተገልጿል። በዕለቱ ይበልጥ ልብን የነካው ክስተት፣ የሰጦ ሰመሮ ሰፈር የክርስትና እምነት ተከታይ ጎረቤቶች ለኡስታዛ ኸዲጃ ያላቸውን አክብሮትና ደስታ ለመግለጽ በአካል ተገኝተው ልዩ ሽልማት ማበርከታቸው ነበር። ይህ የእውነተኛው ኢትዮጵያዊነትና የፍቅር ማሳያ ነው! የወደፊት ራዕይ 🔥🔥🔥🔥🔥 የዚችን ድንቅ እህት መልካም ጉዞ ይበልጥ ለማጠናከር ባለ 4 ወለል ፎቅ ህንጻ ግንባታ የተጀመረ ሲሆን፣ ዛሬ በመጡት የክብር እንግዶችም ተጎብኝቷል። በዚህ ታላቅ ፕሮግራም ላይ የፌደራል መጅሊስ የኡለማ ምክር ቤት አባላት፣ ታዋቂ ዑለማዎችና ዱዓቶች ተገኝተዋል፤ ከነዚህም መካከል፦ ✅ኡስታዝ ያሲን ኑሩ ✅ኡስታዝ ሙሐመድ ፈረጅ ✅አቡ ያሲር አብዱልመናል ከበደ ✅ኡስታዝ ኢብሳ ሐሰን ✅ሸይኽ ዓሊ ጅማ ✅ ሼህ ሙሐመድ አንዋር ✅ ሸይኽ ሙሐመድ አሚን ተማም ✅ ዶ/ር ሸይኽ ማሕሙድ ሁሴን ✅ሸይኽ መከተ ሙሄ ✅ ኡስታዝ ሙሐመድ ሙስጠፋ ✅ ዶ/ር ሰመሃር ተክሌ ✅ ሐጂ ሐምዛ ሙሐመድ ኑር ✅ ኑረዲን ከቁርኣን ባንክ ✅ እኔ አሕመዲን ጀበል እና ሌሎችም ታላላቅ ኡለማዎችና ዱዓቶች ተገኝተዋል። ለተመራቂዎች በሙሉ እንኳን ደስ አላችሁ! አላህ በዱንያም በአኺራም ብርሃን ያድርግላችሁ። ለጀግናዋ እህታችን ኡስታዛ ኸዲጃ ደበበ ደግሞ አላህ መልካም ምንዳዋን ይክፈላት፣ በዕድሜና በጤናዋ ላይ በረካውን ያውርድባት! Dubartii ajaa'ibaa, Kadijjaa lammaffaa 🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥 Har'a magaalaa Jimmaatti sagantaa eebbaa ifaa barattoota Qur'aanaa seeminaarii "Khadija bint Khuwaylid" kan hayyoonni gurguddoo fi keessummoonni kabajamoo irratti hirmaanne irratti hirmaannee jirra. Alhamdulillah! Hundeessaan seeminaara ajaa'ibaa kanaa, kan baay'een keenya sagantaa "Beyene Neldi" TV Minber irraan beeknu, mul'ataa fi ogeessa Ustaza Khadija Dababe dha. Obboleettiin gootichi kun erga ifa Islaamaatti dhuftee booda dheebuu beekumsaa ishii balleessuu hin dhiifne. Mana ishee gara seeminaariitti jijjiirtee, haadholii, obboleettii fi dargaggoota dhibbaan lakkaa’aman Qur’aanaan barsiistee jirti. Eebba Haffazoota Qur'aana 📶📶📶📶📶📶📶📶📶📶 Waggaa lamaa oliif mana ofii keessatti obboleettiiwwan naannoo adda addaa irraa dhufan 17 ol kunuunsitee, nyaachiftee fi kunuunsitee Qur'aana guutuu xumurtee jirti. Obboleettiiwwan kana malees ilmi ishee ganna 9 Abuu Haniifaa kan firii gadameessa ishee ta'e eebbifamtoota keessaa tokko ta'uun seenaa addaa galmeessee jira! Badhaasa Warqee 💢💢💢💢💢💢💢 Obboleettiiwwan eebbifaman (Hafiz) hundaaf kennaa warqee warshaa biyya alaatiin addatti ajajamee tokkoon tokkoon isaanii maqaa isaaniitiin bocamee jira. Dargaggeessi Abu Hanifaa kun ispoortii addatti dhaabbata Adidas jedhamu kan maqaan isaa irratti barreeffame badhaafameera. Intalli Khadijaa kan biraan shamarreen ganna 14 Hassanat Muhassan har'a Qur'aana irraa eebbifamte guyyaa eebbifamte "ani eenyu?" Kitaaba "Kitaaba Nabiyyii" jedhamu barreessitee maxxansuu isheen waltajjii irratti kan mul'ifte Sofiyaa Jawhaar sagantaa "Yene Nel" TV Minber irratti.

  • 22 июн.18из MuradTadesse

    የዐሹራእ ጾም‼ ========== (የነብዩ ﷺ ጉጉት እና የሰለፎች ጥልቅ ማስተንተን!) || ✍️ በእስልምና አስተምህሮ ውስጥ የሙሐረም ወር፣ በተለይም የዐሹራእ (የሙሐረም 10ኛ) ቀን እጅግ የላቀ ደረጃ አለው። ይህ ቀን ያለፈውን አንድ ዓመት ወንጀል የሚያስምር ታላቅ ጸጋ ነው። የዚህን ቀን ታላቅነትና ጾሙን በተመለከተ ትክክለኛ ሐዲሦችን እና የዑለማዎችን ድንቅ ንግግሮች ከነ ምንጫቸው እንመልከት፦ 1⃣ የነብዩ ﷺ ብርቱ ጉጉት፦ ነብዩ ሙሐመድ ﷺ ይህን ቀን ለመጾም ልዩ ጉጉት ነበራቸው። ታላቁ ሶሐባህ ዐብዱ-ል'ሏህ ኢብኑ ዐባስ ይህን የነብዩን ﷺ ጉጉት ሲገልጹ እንዲህ ይላሉ፡- «مَا رَأَيْتُ النَّبِيَّ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ يَتَحَرَّى صِيَامَ يَوْمٍ فَضَّلَهُ عَلَى غَيْرِهِ، إِلَّا هَذَا الْيَوْمَ ؛ يَوْمَ عَاشُورَاءَ، وَهَذَا الشَّهْرَ. يَعْنِي شَهْرَ رَمَضَانَ.» «ነብዩ ﷺ ከሌላው አብልጠው የዚህን ቀን (የዐሹራእን) እና የዚህን ወር (የረመዿንን) ጾም ለመጾም እንደሚጓጉት ለሌላ ቀን ሲጓጉ አላየሁም።» 📚[ሶሒሕ አል-ቡኻሪይ፡ 2006፣ ሶሒሕ ሙስሊም፡ 1132] 2⃣ «ካለፈ አይመለስም!» 🎀 የቀደምት ሰለፎች ለዐሹራእ ጾም የነበራቸው ቦታ አስገራሚ ነበር። ታላቁ ታቢዒይ ሙሐመድ ኢብኑ ሺሀብ አዝ-ዙህሪ በጉዞ ላይ እያሉ የዐሹራእን ቀን ጾሙ። በዚህ ጊዜ ሰዎች ተገረሙና እንዲህ ሲሉ ጠየቋቸው፡- (… فقيل له: لم تصوم وأنت تفطر في رمضان في السفر ؟! فقال: إن رمضان له عدة من أيام أخر، وإن عاشوراء يفوت.) «በረመዿን ወር በጉዞ ላይ ሆነህ ጾም እየፈታህ፣ ዛሬ (በጉዞ ላይ) ለምን ትጾማለህ?» ተብለው ሲጠየቁ፤ «ረመዿን በሌሎች ቀናት (ተቆጥሮ) ቀዷ ይወጣል (ይከፈላል)፤ የዐሹራእ ጾም ግን ካለፈ ያመልጣል (ቀዷ አይወጣም)!» ብለው መለሱ።» 📚 [ሸዕቡል-ኢማን ሊል-በይሀቂይ፡ 3518] ⬇️ በእርግጥም የረመዿንን ጾም በህመም ወይም በጉዞ ምክንያት የፈታ ሰው በሌላ ጊዜ መክፈል ይችላል። የዐሹራእ ጾም ግን ዓመት ጠብቆ የሚመጣና ቀዷ የሌለው በመሆኑ፣ ይህ ታላቅ ምንዳ እንዳያመልጠን ሰለፎች እስከዚህ ድረስ ይጓጉለት ነበር! 3⃣ ዓመትን በዒባዳህ መዝጋትና በዒባዳህ መክፈት! 🎀 ታላቁ ሊቅ ኢማም ኢብኑ ረጀብ አል-ሐንበሊ አላህ በሰጣቸው ጥልቅ እይታ፣ የዓመቱ መጨረሻ (ዙል-ሒጃ) እና የዓመቱ መጀመሪያ (ሙሐረም) ወራት ውስጥ ስላለው ጾም እንዲህ ይላሉ፡- «من صام من ذي الحجة وصام من المحرم، فقد ختم السنة بالطاعة وافتتحها بالطاعة فيرجى أن تكتب له سنته كلها طاعة، فإن من كان أول عمله طاعه وآخره طاعة فهو في حكم من استغرق بالطاعة ما بين العامين.» «ከዙል-ሒጃ (ባለፈው ዓመት መጨረሻ) እና ከሙሐረም (በአዲሱ ዓመት መጀመሪያ) የጾመ ሰው፤ ዓመቱን በዒባዳህ (በታዛዥነት) ዘግቶ፣ አዲሱን ዓመትም በዒባዳህ ከፈተ ማለት ነው። በመሆኑም ዓመቱ ሙሉ በዒባዳ እንዳሳለፈ ይጻፍለታል ተብሎ ተስፋ ይደረጋል። ምክንያቱም የመጀመሪያውም ሆነ የመጨረሻው ስራው አላህን መታዘዝ የሆነ ሰው፣ በሁለቱ ዓመታት መካከል ያለውን ጊዜ ሙሉ በዒባዳ እንዳሳለፈ ይቆጠርለታልና።» 📚 [ለጧኢፉል መዓሪፍ ሊብኒ ረጀብ] ⏱ የዚህ ዓመት የዐሹራእ ጾም ቀናት! 📅 ነብዩ ﷺ ዐሹራእን ጾመው፣ ከአይሁዶች ለመለየት ሲሉ ቀጣዩ ዓመት ከደረሰ 9ኛውንም ቀን (ታሱዓእን) አብረው እንደሚጾሙ ተናግረዋል። በመሆኑም፣ የዘንድሮውን የሙሐረም 9ኛ እና 10ኛ ቀን የጾም ቀጠሯችንን እንደሚከተለው አድርገን ይህን የዓመት ወንጀል የሚያስምር ታላቅ ጸጋ እንቋደስ፦ ✅ ታሱዓእ (9ኛው ቀን)፦ ረቡዕ፣ ጁን 24 ✅ ዐሹራእ (10ኛው ቀን)፦ ሐሙስ፣ ጁን 25 አላህ ያለፈውን ዓመት ወንጀላችንን የምንማርበት፣ አዲሱን ዓመትም በዒባዳና በኸይር የምንጀምርበት ያድርግልን! (እነዚህን ቀናት ጓደኛ እና ቤተሰባችሁ እንዳይረሱት ሼር በማድረግ የኸይር ሰበብ ሁኑ!) 🤍 t.me/MuradTadesse

  • 22 июн.19из abulmusayabhamza

    📮 የአሹራ ፆም ቱሩፋቶች። 📌 በሚል ርዕስ መደመጥ ያለበት መካሪ የሆን የጁመዓ ኹጥባ ትርጉም። 🎙 በወንድማችን አቡል ሙሰየብ ሀምዛ ቢን ረሻድ አላህ ይጠብቀው። 📎 https://t.me/abulmusayabhamza/6661 ــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــ

  • 21 июн.19из MuradTadesse

    ይድረስ ለአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ክቡርት ወ/ሮ አዳነች አቤቤ‼ ======================================== (የእናቱን አስክሬን ቤት ውስጥ አስቀምጦ ፈተና የፈተነው የ14 ዓመቱ ብርቱ ታዳጊ እና የታናናሾቹ የእንባ የመታደግ ጥሪ!) || ✍️ ሰሞኑን የሁላችንንም ልብ የሰበረ፣ ነገር ግን ለሀገር ተስፋ የሚሆን ብርቱ ስነ-ልቦና ያለው አንድ የ14 ዓመት ታዳጊ የገጠመውን ፈተና በሁላችንም ዘንድ ተሰራጭቷል። ይህ ታዳጊ ኻሊድ ይባላል። በሸገር ከተማ አስተዳደር፣ የካ ጣፎ ክፍለ ከተማ ነዋሪ ሲሆን፤ በMuuxxannicha) ትምህርት ቤት የ8ኛ ክፍል ተማሪ ነው። ኻሊድ ከሁለት ታናናሽ ወንድሞቹ ጋር ያደገው በብርቱ እናቱ እቅፍ ውስጥ ነበር (ወላጅ አባቱ ርቆ ጂጂጋ ከተማ ሌላ ትዳር መስርቶ ይኖራል)። 🔗የዚህ ልጅ ታሪክ የጀግንነትም፣ የጥልቅ ሐዘንም ተምሳሌት ነው። ሰሞኑን እናቱ በጽኑ ታመው በነበረበት ወቅት፣ ኻሊድን ወደ አልጋቸው ጠርተው «እኔ አንድ ነገር ብሆን እንኳ፣ ምንም ቢፈጠር ዓመት ሙሉ የለፋህበትን ፈተና እንዳታቋርጥ!» በማለት ጥብቅ አደራ እና ቃል ያስገቡታል። እናት ይህንን ኑዛዜ መሰል አደራ በሰጡ በነጋታው፣ የስምንተኛ ክፍል ሚኒስትሪ ፈተና ሊጀመር ጥቂት ሰዓታት ሲቀረው ሕይወታቸው ያልፋል። ገና የ14 ዓመት ታዳጊ የሆነው ኻሊድ፣ በእናቱ ድንገተኛ ሞት ከፍተኛ ሐዘንና ድንጋጤ ቢሰማውም፣ ለብርቱ እናቱ የገባውን የመጨረሻ ቃል ለማክበር ሲል፤ የወላጅ እናቱን አስክሬን እቤት ውስጥ ከታናናሽ ወንድሞቹ ጋር ትቶ፣ እንባውን እያበሰ የጠዋቱን ፈተና ተፈተነ! ከሰዓት በኋላ ደግሞ ወደ ቤት ተመልሶ እናቱን አልቅሶ ከቀበረ በኋላ፣ ዳግም ወደ ፈተና ማዕከል በመመለስ የከሰዓቱን ፈተና አጠናቋል! ይህ የኻሊድ የውስጥ ጥንካሬ፣ ቆራጥነት እና ቃሉን ጠባቂነት የሁላችንንም ልብ በሐዘን የሰበረ፣ በተመሳሳይ ደግሞ አቅሙን ያደነቅንበት ክስተት ነው። አሁን ላይ ኻሊድና ታናናሽ ወንድሞቹ እናታቸው ላይ አፈር አልብሰው ተመልሰዋል፤ አባት በአጠገባቸው የለም። የ14 ዓመቱ ኻሊድ የሁለት ታናናሽ ወንድሞቹ ብቸኛ "አባትም እናትም" ሆኖ ከባዱን የህይወት ኃላፊነት ተሸክሟል። በእድሜው ማነስ ምክንያት በህግ የባንክ አካውንት በብቸኝነት ማንቀሳቀስ አይችልም። እነዚህ ህጻናት አሁን ላይ ትልቁ ስጋታቸው የመኖሪያ ቤት እጦት እና የጎዳና ህይወት ነው። ይህን የመሰለ ቆራጥ፣ ታዛዥ እና ጽኑ አዕምሮ ያለው ተማሪ፣ በመኖሪያ ቤት እጦት ተንገላቶ፣ ትምህርቱን አቋርጦ፣ ከነ ታናናሽ ወንድሞቹ ጎዳና ላይ ወጥቶ የጎዳና ተዳዳሪ እንዲሆን የትኛውም ኢትዮጵያዊ ህሊና አይፈቅድም። በመሆኑም እርስዎ በተለያዩ ጊዜያት ለችግረኞችና ቤት አልባዎች እንደሚያደርጉት ሁሉ፤ ይህ በጽናቱ ለብዙዎች አርዓያ የሆነ ታዳጊ የጀመረውን የትምህርት ጉዞውን ተረጋግቶ ከጫፍ ያደርሰው ዘንድ፣ እንዲሁም ታናናሽ ወንድሞቹን ከጎዳና ህይወት ይታደግ ዘንድ፤ የከተማ አስተዳደሩ የመኖሪያ ቤት ድጋፍ (የጋራ መኖሪያ ቤት/ ኮንዶሚኒየም) እና ቋሚ የትምህርት ስፖንሰርሺፕ እንዲያመቻቹለትና በእናትነት ስሜት እንዲመለከቱት በታላቅ አክብሮት እንጠይቃለን። ኻሊድን እና ወንድሞቹን መደገፍ፣ አንድን ቤተሰብ ከማዳን ባሻገር፤ ቆራጥነት፣ ተስፋ አለመቁረጥ እና ቃልን ማክበር መጨረሻው ብርሃን እንደሆነ ለመላው የሀገራችን ወጣቶች ትልቅ ትምህርት (Moral lesson) የሚሰጥ ተግባር ይሆናል። የብርቱዋን እናታቸውን ነፍስ አላህ በጀነት እንዲያኖርልን፤ ለኻሊድ እና ለወንድሞቹም ጽናቱን እንዲሰጣቸው አላህን እንለምናለን! (ይህ መልዕክት ለክቡርት ከንቲባ አዳነች አቤቤ እና ለሚመለከታቸው የመንግስት አካላት ይደርስ ዘንድ፣ ሁላችሁም ሼር በማድረግ የነዚህ የጀግና እናት ልጆች ድምጽ እንሁን!) || t.me/MuradTadesse

  • ​💬 "በምድር ላይ የአንድ ሰው ህይወት ትልቅ ክብር አለውና፣ አንድን ህይወት ማትረፍ የሰው ዘርን ሁሉ እንደማዳን ነው።" ⚡ ይህ ማለት ምን ማለት ነው? 🤔 ፦ በአንድ ይቅርታ ውስጥ የቁጣ ሰንሰለት ይበጠሳል። ገዳይን ይቅር ማለት የደም መፋሰስን ዑደት በማስቆም፣ ሌላ አዲስ በቀል እንዳይመነጭና ማህበረሰብ ከጥፋት ማዕበል እንዲተርፍ ማድረግ ማለት ነው። 🌳🛡️ ​📖 የእኔ መደምደሚያና ማሳረጊያ 🎭✨ ​ይህንን እውነተኛ ታሪክ እንደ ልብ ወለድ ቂሷ ብናየው እንኳ፣ ፍጻሜው የሚያስተምረን ትልቅ ሀቅ አለ፦ የበቀል መጨረሻው ሁልጊዜም ባዶነትና የልብ ጸጸት ብቻ ነው። 🍂 በቀል የሞተውን ውድ ልጅ አይመልስም፣ የቆሰለውን የቤተሰብ ልብም መቼም ቢሆን አይጠግንም። ነገር ግን ይቅርታ፣ በሰጭውም ሆነ በተቀባዩ ልብ ላይ ሰማያዊ ሰላምን ያሰፍናል። 🕊️ ​እኚህ አባት፣ የገዳዩን እንባና የቤተሰቡን ለቅሶ አይተው የገዛ ልባቸውን ስብራት ለአላህ ብለው የረሱት正式 ለዱንያ ዝና ሳይሆን ለዘላለማዊው የጀነት ደስታ ብለው ነው። 🌟 ​ትልቁ ምክሬ፦ 💡 በህይወታችሁ ውስጥ የቱንም ያህል ብትበደሉ፣ ልባችሁ ቢሰበር፣ ይቅርታን የህይወታችሁ መርህ አድርጉት። ይቅርታ ለበደለን ሰው የሚሰጥ ስጦታ ሳይሆን፣ ለገዛ ልባችን ከቂም እስራት የምንሰጠው ታላቅ ነፃነት ነው! 🔓❤️ ​🤲 የኔ ልባዊ ዱዓ እና ማስታወሻዬ 📿📌 ​ያ አላህ! 🤲 እንደ እኚህ አባት አይነት ሰፊ፣ ታጋሽና ይቅር ባይ ልቦና ለግሰን። የበደሉንን በደል በቸርነት የምናልፍበትን፣ የሰበርንበትን ልብ በሰላም የምንተካበትን ጥንካሬ ስጠን። በምድር ላይ ፍቅርን፣ እዝነትንና መተሳሰብን አብዛልን። አሚን! 🕋✨ ​📌 ማስታወሻ፦ ይህ ታሪክ ዛሬ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ መነጋገሪያ የሆነው እንዲሁ ለወሬ ማድመቂያ ሳይሆን፣ እያንዳንዳችን በየቤታችን፣ በየጎረቤታችንና በየወዳጆቻችን መሃል ያለውን ጥቃቅን ቂምና ቁርሾ አውርደን እንድንጥል አላህ የላከልን ታላቅ የህሊና ማንቂያ ደወል ነው። 🔔 ​(Nesrutube✍️)

  • "የሞት ፍርድ ከአንድ ቀን በፊት... ዓለምን ያስለቀሰው ድንቅ ትዕይንት 💔!" "የሞት ገመዱን የበጠሰው የሰከንድ ይቅርታ ⚖️! 😭" ​🕊️ የሺህ ዓመት በቀልን ያሸነፈው የይቅርታ ንጉሥ፦ ከልብ ስብራት ጀርባ የበቀለው የጀነት ስንቅ! ⚖️✨ ​"የበቀል መጨረሻ የጀነት መጀመሪያ! 🕊️" ​ህይወት በፈተና ማዕበል የተሞላች ናት። 🌊 አንዳንዴ ፈተናው የሚመጣው በጣም በምንወደው ሰው ህይወት ላይ፣ በክፉ መርዶ ታጅቦ ሊሆን ይችላል። 💔 ነገር ግን፣ አንድ እውነተኛ ሙእሚን በፈተናው እቶን ውስጥ አልፎ የሚወስደው ውሳኔ ነው ከሰዎች ለይቶ በታሪክ መዝገብ ላይ በወርቅ ቀለም የሚያሳርፈው። ሰሞኑን ዓለምን ያስለቀሱት እኚህ አባት፣ የልጃቸውን ነፍስ የገደለውን ሰው ቤተሰብ ፊት ቆመው ያሳዩት ትዕይንት፣ ከቃል በላይ የሆነ የኢስላም እውነተኛ መዝገብ ነው። 🕌📜 ​ታሪኩ እንዲህ ነው፦ በሳዑዲ ዓረቢያ የአንድ ቤተሰብ ልጅ የእኚህን አባት ልጅ ይገድላል። በሀገሪቱ የሸሪዓ ሕግ መሠረት "የገደለ ይገደል" የሚል የቂሷስ ፍርድ ይወሰናል። የገዳይ ቤተሰቦች የልጃቸው መገደያ ቀን በቀረበና በደረሰ ጊዜ እጅግ በሀዘንና በጭንቀት ላይ ይወድቃሉ። "ከዛሬ ነገ ልጃችን ሊሰቀል/ሊገደል ነው" ብለው በተስፋ መቁረጥ ውስጥ ሳሉ፣ የሟች አባት የሆኑት እኚህ በእድሜ የገፉ አባት አብረዋቸው ከነበሩ ሰዎች ጋር ድንገት ከገዳዩ ቤተሰብ ደጃፍ ጎራ ይላሉ። ​"አሰላሙ ዐለይኩም" ብለው እንደገቡ፣ የገዳይ እናት በሀዘን ተውጣ፣ ሰውነቷ ክስስ ብሎ የቤቷን ደጃፍ ትከፍትና የሟች አባትንና አብረዋቸው የመጡትን ሰዎች ወደ ሳሎኗ ታስገባለች። ቁጭ እንዳሉ ግን መናገር እስኪያቅታት ድረስ ስቅስቅ ብላ ማልቀስ ትጀምራለች። ይህንን የተመለከቱት እኚህ ታላቅ አባት፣ ከአንደበታቸው አንዲት ቃል ወጣች... ያ ሱብሀን አላህ! ምን ቢሉ ጥሩ ነው? ​"ሰሚኝ ልጄ... እኔ በእድሜ ገፍቻለሁ፣ እድሜዬ ሄዷል። በርግጥ የልጄ መሞት ልቤን ሰብሮታል፤ ነገር ግን የናንተ ልጅ ቢገደል በዚህ አርጅቼ በቆምኩበት እድሜ ላይ ሳለሁ የማገኘው ምንም ጥቅም የለም። የገንዘብ ካሳም (ዲያም) በፍጹም አልፈልግም! ልጄን ዳግም በዱንያ ላይ ላገኘው አልችልምና፣ እናንተም የልጃችሁን የሞት ህመም እንደ እኔ እንዳትቀምሱ... ለአላህ ስል ይቅር ብያችኋለሁ!" 😭☝️ ​ያ አላህ! ይህ ድምፅ የሺህ ዓመት በቀልን በሰከንድ ውስጥ የሚያከስም ሰማያዊ ኃይል አለው። ✨ ያሰላም! ምን አይነት የይቅርታ ልብ፣ ምን አይነት ለአላህ የመሰጠት እምነት ነው? ይህንን ስናይ የጥንቱ ድንቅ ታሪክ ትዝ ይለናል፦ ​🏛️ የዑመር (ረ.ዐ) ዘመን ፍትህና የሰሐባው ታማኝነት 🐎🛡️ ​ይህ የአባታችን ታላቅ ተግባር正式 የጥንቱን የሰሐባዎች ወርቃማ ዘመን ያስታውሰናል። በአሚረል ሙእሚኒን ዑመር ኢብኑል ኸጣብ (ረ.ዐ) የኸሊፋነት ዘመን፣ ሁለት ወጣቶች አንድን አዛውንት ገደሉ ተብለው ፍርድ ቤት ቀረቡ። የሟች ወራሾች የደም መመለስ (ቂሷስ) ጠየቁ። ⚖️ ​ዑመር (ረ.ዐ) የሞት ፍርዱን ሊያስፈጽሙ ሲሉ፣ ከገዳዮቹ አንዱ ወጣት ቆመና፦ "አባቴ ሞቷል፣ ለአንዲት እህቴ ጥሪት መሬት ውስጥ ቀብሬላታለሁ። እሷን የምትንከባከብበትን መንገድ እንዳመቻች 3 ቀን ስጡኝ፤ በአላህ ስም እምላለሁ ተመልሼ እመጣለሁ" ብሎ ተማፀነ። 🤝 ​ዑመርም "ዋስ የሚሆንህ ማን ነው?" አሉ። ወጣቱ በመካከላቸው የነበረውን ታላቁን ሰሐባ አቡ ዘር አል-ጊፋሪን (ረ.ዐ) ጠቆመ። አቡ ዘርም ወጣቱን ሳያውቀው፣ ለአላህ ብሎ ዋስ ሆነ! 😮 ​በሦስተኛው ቀን፣ የተሰጠው ሰዓት ሊያበቃ ጥቂት ደቂቃዎች ሲቀሩ正式 ማንም ሳይከተለው ወጣቱ እየሮጠ መጣ! 🏃‍♂️ ዑመር (ረ.ዐ) በመገረም፦ "እንዲህ ልትገደል እየመጣህ ምን እንዲህ እንድትመለስ አደረገህ?" አሉት። ወጣቱም፦ "በሰዎች መካከል 'ታማኝነትና ቃልን ማክበር' ጠፋ እንዳይባል ፈርቼ ነው!" አለ። 💎 ​ዑመር ወደ አቡ ዘር ዞረው፦ "ሳታውቀው ለምን ዋስ ሆንከው?" አሉት። አቡ ዘርም፦ "በሰዎች መካከል 'ቸርነትና መልካምነት' ጠፋ እንዳይባል ፈርቼ ነው!" አሉ። 💖 ​ይህንን የታማኝነትና የድንቅ እምነት ማዕበል የተመለከቱት የሟች ወገኖች፣ ልባቸው በስሜት ተነክቶ በለቅሶ እንዲህ አሉ።፦ "በሰው ልጅ ምድር ላይ 'ይቅርታና እዝነት' ጠፋ እንዳይባል እኛም ለአላህ ብለን ይቅር ብለናል!" 😭🙌 ​በዚያን ጊዜ ዑመር (ረ.ዐ) በደስታ እንባ እየተናነቃቸው እንዲህ አሉ፦ "ይቅር ባያሉ ኖሮ እውነት በምድር ላይ የት ትገኝ ነበር?" 🌟 ​✨ ለዚህ ትውልድ የቀረቡ 3 ወሳኝ ጥያቄዎች፤ እኛ ከዚህ ታሪክ ምን እንማራለን? ​ይህንን ታሪክ በጭብጨባና በ'ላይክ' ብቻ ማለፍ የለብንም። ይህ ታሪክ ለህሊናችን የሚከተሉትን ጥያቄዎች ያቀርባል፦ ​የይቅርታችን ልክ የት ድረስ ነው? – በገዛ ደማችን የመጣን ሰፊ በደል ለአላህ ብለን መተው ካቃተን፣ በየቀኑ በትንሽ የዱንያ ጥቅም፣ በቃላት መጣላትና በኩርፊያ የምናሳልፈው እኛነታችን የቱ ጋ ነው ያለው? ​ለእምነታችን የምንከፍለው ዋጋ ምንድን ነው? – ታማኝነት፣ ቃልን ማክበርና ቸርነት በሰዎች ዘንድ እንዳይጠፉ ህይወታቸውንና ደማቸውን አሳልፈው የሰጡ ሰዎችን ታሪክ ስንሰማ፣ እኛ ለእምነታችን ውበት ምን እያበረከትን ነው? ​የልብ ስብራትን በምን እናክመው? – ቁጭትና በቀል ልብን ያክማሉ ወይስ ይቅርታና ለአላህ ውሳኔ እጅ መስጠት? ​💡 በእኔ እምነትና እይታ፦ ​በእኔ እምነት፣ ይቅርታ ማለት የበደለን ሰው ድርጊት 'ትክክል ነው' ብሎ መቀበል ሳይሆን፣ ከበደሉ ጀርባ ያለውን የሰይጣን የእሳት ሰንሰለት በእምነት ውሃ ማጥፋት ማለት ነው። ዛሬ ላይ የሰው ልጅ ትልቁ ህመሙ 'እልህና ቂም' ነው። እኚህ አዛውንት አባት የገዳዩን እናት እንባ አይተው የገዛ ልባቸውን ስብራት የረሱት፣ በቀል የሞተውን ልጅ እንደማይመልስ ስላወቁና የቂም እስረኛ መሆንን ስላልፈለጉ ነው። ​በእኔ እምነት፣ ይህ ታሪክ ለዚህ ትውልድ ትልቅ ትዝብት ነው። እኛ በትናንሽ የፖለቲካ፣ የብሔር፣ የገንዘብና የቃላት ልዩነቶች ቂም አርግዘን የምንኖር ሰዎች፣ የደም ዋጋን ለአላህ ብሎ መተው ምን ያህል ታላቅነት እንደሆነ ልንማርበት ይገባል። ይቅርታ ደካማነት ሳይሆን፣ ፍፁም የሆነ የጀግንነትና የመላኢካዊ ባህሪ መገለጫ ነው። ​💡 የኡለሞቻችን ወርቃማ ምክር ምን ነበር — «ምን ማለታቸውስ ነው?» 🤔🔍 ​የእስልምና ሊቃውንት (ኡለሞች) የይቅርታን ምስጢር በወርቃማ ቃላት ሲፈቱት፣ ከጀርባው ያሉት ጥልቅ እውነታዎች እንዲህ ይነበባሉ፦ ​💬 "በቀል ማድረግ የሰዋዊ ተፈጥሮ (ነፍስያ) ስሜት ነው፤ ይቅር ማለት ግን የመላኢካዊ ባህሪ መገለጫ ነው።" ⚡ ምን ማለታቸው ነው? 🤔 ፦ መበቀልና ቁጭትን መወጣት ለማንኛውም ሰው ቀላልና ተፈጥሯዊ ስሜት ነው፤ ነገር ግን ያንን የቁጣ እሳት አጥፍቶ፣ በደልን ረግጦ ማለፍ ከመላኢካዎች እዝነት ጋር የሚመሳሰል የላቀ መንፈሳዊ ማማ ላይ መድረስ ማለት ነው። 😇🔥 ​💬 "የበደለህን ይቅር ስትል正式 አላህ አንተን ይቅር ሊልህ በር ይከፈታል።" ⚡ ይህ ማለት ምን ማለት ነው? 🤔 ፦ እኛ የአላህ ደካማ ባሮች ሆነን ሳለን ሁልጊዜ ጥፋትና ወንጀል እንሰራለን፤ ከአላህም ምሕረትን እንሻለን። ታዲያ እኛ በምድር ላይ ላሉት የአላህ ፍጡራን መሃሪ ካልሆንን፣ ሰማያዊውን ጌታ እንዴት "ማረኝ" እንላለን? ስለዚህ ይቅርታችን ለአላህ ምሕረት መክፈቻ ቁልፍ ነው ማለት ነው። 🔑

  • 8 ማወቅ ያሉባችሁ የሕይወት ህጎች 1.ለማንም ሰው ከሁለት ጊዜ በላይ በአንዴ አትደውሉ 2.ለሰው የተበደራችሁትን ገንዘብ ሳትጠየቁ መልሱ 3.ለሁሉም ሰው መልካም ሁኑ 4.ከማንም ምንም አትጠብቁ 5.ሰዎች ሲያወሩ ጣልቃ አትግቡ 6.በሌላቸው ሰዎች መሀል ስላላችሁ ነገር በብዛት አታውሩ 7.ከሰው ጋር እየተቃለዳችሁ ምቾት ካልተሰማቸው ቶሎ አቁሙ 8.ቃላችሁን አትጠፉ ወይም ጭራሹንም ቃል አትግቡ ጀሊሉ መልካም ስነምግባርን ያላብሰን

  • 15 июн.29из abulmusayabhamza

    🎙የሙሀረም ጨረቃ ታይታለች ዛሬ ምሽት የሙሀረም ወር ጨረቃ የታየች ሲሆን አዲሱን አመተ ሂጅራ 1448 የተቀበልን ይሆናል ማለት ነው ። ታዲያ በዚህ አዲሱ አመት ምን ለማድረግ እቅድ አውጥተሀል? አላህ የለውጥ እና እራሳችንን የምናስተካክልበት አመት ያድርግልን። 🌴1⃣4⃣4⃣8⃣ 📎 https://t.me/+eAicTR1AQAcwMjA0

  • 9 июн.43из IbnulQeyyimMedresa

    ✅የ5 ወር ከግማሽ የዒልም ማዕድ 📚 «አዳእ ወደዋእ» ኪታብን ጨምሮ የልብ መታደስን፣ ከወንጀል አዙሪት መውጣትን የሚያበረታቱ  ቀልብን የሚያረጥቡ ምክሮችንና አላህን መፍራትን የሚያስተምሩ 4 ድንቅ ኪታቦችን በአንድ ላይ ያቀረበ ልዩ ኮርስ ነው። ትምህርቱ ከሰኞ እስከ ሐሙስ ከምሽቱ 3:30  ጀምሮ በኦንላይን የሚሰጥ ሲሆን፣ ፍላጎት ያላችሁ  @KitabAstemari ላይ ተመዝገቡ ። ዝርዝር ገለፃ ከፈለጋችሁ ➡️ t.me/IbnulQeyyimMedresa/28            💎  ኢብኑል ቀይም መድረሳ

  • ሻማን «ማን ጎዳሽ?» አሏት፤ «ከውጭ የመጣው ክብሪት ሳይሆን፣ ከውስጤ አቅፌ የያዝኩት ክር ነው የበላኝ» አለች ይባላል። አንዳንዴ ክፉኛ የሚጎዳችሁ፣ ከሩቅ የመጣ ጠላት ሳይሆን “የእኔ ነው” ብላችሁ የያዛችሁት የቅርብ አካል ይሆናል.... ◈ t.me/Sle_qelbachn1

  • 7 июн.42из rihletulhayat

    🌸ጭንቀት እና ሃሳቡ ሁሉ ቁርአን የሆነ ሰው እንሁን! የቁርአን አያዎችን በመርሳቱ አሊያም ተፍሲሩን የማያውቀው አያ በመኖሩ የሚያዝን፤የሆነ ፊደልን መውጫ ቦታውን ጠብቆ ባለመቅራቱ ተጅዊዱን አስተካክሎ መቅራት ያልቻለው ቦታ በመኖሩ የሚታመም፤በዙሪያው ያሉት በቁርአን እየቀደሙት እሱ ወደ ኋላ በማለቱ ነፋሱን እየበደላት እንደሆነ እያሰበ የሚፈራ፤ከተደሰተም ካዘነም ለቁርአን፤ካሰበም ስለቁርአን፤ከናፈቀም ቁርአንን፤ምላሱንም ቀልቡንም ከቁርአን ጋር ያደረገ……… ያአላህ………እንዲህ ያለ ሰው የሚኖረውን የደስታ እና እርጋታ ሃያት እንዴት ይሁን?

  • 7 июн.35из rihletulhayat

    #ኢብኑል_ቀዪም ረሒመሁሏህ እንዲህ ይላሉ : - «የቁርኣን ባለቤቶች: ማለት ቁርኣንን በልባቸው ሸምድደው ባይዙም እንኳን  የቁርኣንን መልእክት የተረዱና በቁርኣን ውስጥ በተጠቀሱ ብይኖች የሚሰሩ ናቸው። ቁርኣንን ሓፍዞ (ሸምድዶ) መልእክቱን ያልተረዳና በቁርኣን ውስጥ በተጠቀሱ ድንጋጌዎች የማይሰራ የቃላት አሰካኩን አሳምሮና ቀጥ አድርጎ ቢያነበንበውም በፍፁም የቁርኣን ሰው አይባልም።» 📚 ۞ زاد المـــعـاد【1/327】۞

  • 7 июн.39из rihletulhayat

    🌹* የቂያም ቀን ሰዎች ሁሉ በአንድ ቦታ ላይ ይሰበሰባሉ..* ◻ቁርአን የሀፈዘ ሲቀር 🤞 ◻እሱማ ከመላኢኮች ጋር ነው ..! ◻ሊያውም ከተከበሩና ልዩ ከሆኑት ጋር ◻ሁሉም ሰው የቂያም ቀን እርስ በእርሱ ላለመገናኘት ይሸሻል ! ◻ቁርአን የሀፈዘ ሲቀር ◻ወላጆቹን አግኝቶ የክብር ዘውድ ለማልበስ ይፈልጋቸዋል 👑 🔹 *ምን አለፋቹ የቁርአን ትሩፋ እኛን ጀነት ማድረስ ብቻኮ አይደለም ..* እናማ ቁርአኑን ይዘነው እስከቀራነው ድረስ የጀነት ከፍተኛው ደረጃ ከማድረስም አይወገድም እንዲህም ይባላል (اقرأ، وارتَقِ، ورتِّل) 🔹ከቁርአን ጋር ያለውን ግንኙነት ያጓደለ ሰው ይሄን ጉድለቱን ሞልቶ ከቁርአን ጋር መኖርን ሲጀምር የሚያገኘውን ጥፍጥና ቢያውቅና ቢቀምሰው በአላህ ይሁንብኝ ለቅፅበት ያህል ከቁርአን መራቅን አያስብም ነበር..!! 🔹አንድ ሰው በቀን ውስጥ ከቁርአን ጋር የሚያሳልፍበት ጊዜ ከተነፈገ ከመልካም ሁሉ ተነፍጓል ማለት ነው ። 🔸 ከቁርአን በረካዎች መካከል : አላህ ቁርአንን ለቀራና ለሀፈዘ አእምሮ ብቻ የሚሰጠው የተለየ በረካ አለው . . *ለዚህም ነው ዐብዱ አል መሊክ ኢብኑ ዑመይር : *' (ከሰዎች አእምሯቸው ፅኑዎቹ ቁርአን ቃሪኦች ናቸው ይባል ነበር ይላሉ።) ، *በሌላም ዘገባ ላይ :* ' (ከሰዎች አእምሯቸው ንፁሆቹ ቁርአን ቃሪኦች ናቸው ይላሉ። ) ' اللهم اجعلنا من أهل القرءان وخاصته

  • 5 июн.41из abulmusayabhamza

    እያወቀ ውሸትን አይዳፈርም ክፉ ሰው እንጂ (ኢብኑ ተይሚያ)

  • 4 июн.45из bahruteka

    👉 ሶላት ዒባዳ አይደለም ! ከላይ እንደ ምትመለከቱት ኡስታዝ ተብዬው ኻሊድ ክብሮም ተፍሲር ብሎ በሚዘባርቀው ፍልስፍናው ላይ የሶላት ትልቁ ሚና ዒባዳ እውን እንዲሆን የሚያግዝ መሳሪያ እንጂ ሶላት ዒባዳ አይደለም ይላል ‼ ። በጣም የሚያሳፍሩት ከሱ ስር ቁጭ ብለው ይህን የሚማሩት እንጂ እሱ አይደለም ። ምክንያቱም የሱ አላማ ሙስሊሞች ከስማቸው በላይ የሚያውቁዋቸውን የእስልምና ማእዘናቶች ላይ ጥርጣሬ ውስጥ እንዲገቡ በማድረግ ውስጣቸውን ከትክክለኛው እስልምና ባዶ ማድረግ ነውና ! እባካችሁን አላህን እንፈራለን የምትሉ ኡስታዞች ከዚህ ሰው በማስጠንቀቅ ሙስሊሞችን ታደጉ ! ። http://t.me/bahruteka

  • 🚫 የኻሊድ ክብሮም የአክፍሮትና ሽርክ ጉዞ ኻሊድ ክብሮም የተባለው ግለሰብ ሰልሜያለሁ ብሎ ወደ እስልምና ከገባ በኋላ የትና ማን ጋር እንደተማረና ሸይኹ ማን እንደሆነ ሳይታወቅ ወደ ዳዕዋ ሜዳ በመግባት በተለይ ሴቶችን ያለ ሒጃብ ፊት ለፊት በማስተማር ሙሪዶቹ እንዲሆኑ ካደረገ በኋላ በጣም አደገኛ አካሄድ እየሄደ ይገኛል ። ይህ ግለሰብ እየሄደበት ያለው አካሄ በጣም መርዛማና ትክክለኛውን እስልምና የሚበርዝ ነው ። ግለሰቡ እየሄደበት ያለው አካሄድ ምእራባዊያን የሰጡት የቤት ስራ ያለ እስኪመስል እየደረሰ ነው ። ይህ ግለሰብ በረቀቀ መልኩ የነብዩን ሐዲስ ውድቅ በሚያደርግ መልኩ ቁርኣንን ብቻ መያዝና የቁርኣንን መረጃነት ብቻ መቀበል የሚለውን የቁርኣናዊያን ቡድኖች አካሄድ እያሰረፀ ነው ። በዚህ ብቻ አላቆመም ቁርኣንን ራሱ ማንም ቢያብራራው ተቀባይነት እንደሌለውና በቀጥታ ቁርኣንን ብቻ በመገንዘብ መብቃቃት እንደሚቻል መሰረት በመጣል ላይ እየሰራ ነው ። ይህን አስተምሮ በሚቀጥለው ንግግሩ ተመልከቱት 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇 https://t.me/bahruteka/7251 ይህ አካሄድ ሰለፎች ቁርኣንን የፈሰሩበትን መንገድ ውድቅ ለማድረግና ሰዎች በዝንባሌያቸውና ከስሜታቸው ጋር በሚስማማ መልኩ እንዲፈስሩት በዚህም ምእራቦች የሚፈልጉት አይነት ባህላዊ እስልምና እንዲስፋፋ ለማድረግ ያለመ አካሄድ ይመስላል ። ሌላኛው የዚሁ የፈተና ሰው ዳዕዋ ሰዎች በኢማናቸው አማካይነት የፈለጉትን የማድረግ አቅም አላቸው የሚለውን የአሕባሾች ዐቂዳን ለማስፋፋት የሚያደርገው ጥረት ነው ። ይኸው ግለሰብ የለበሱት ልብስ ለሌሎች በረከት የሚያስተላልፍ ትራፊ ውሃቸው ለሌሎች መድሃኒት የሚሆንላቸው ፍፁም የሆነ ሀይል (ፓወር) ያላቸው አሉ እያለ የሰውን ልጅ የረቂቅ ሀይል ባልተቤትና ፍፁም ነው በማለት የቀብር አምልኮና በሙታን መንፈስ ወደ መታገዝ እየተጣራ ይገኛል ። ይህንን አስተምሮ በሚቀጥለው ሊንክ ገብታቸው አዳምጡ ⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️ https://drive.google.com/file/d/1nRc3dU70O311-ljNlE_JueD3-AeG6DQe/view?usp=drivesdk ከዚህ የሚከፋውና በጣም አደገኛው ደግሞ የደጋጎችን ልብስ መልበስ የእነርሱ መንፈስ ወዳንተ እንዲተላለፍ ያደርጋል የሚለው አስተምሮ ነው ! ይሄኛውንም በሚቀጥለው ሊንክ ገብተው ያዳምጡ : – 👇??👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇 https://drive.google.com/file/d/1dR8C1c5Tv4SIVCK1h4IyKFBd8dx75xFy/view?usp=drivesdk ተመልከቱ አንድ ጃሂል ስለጠሃራ የማያውቅ የአንድን ወልይ ልብስ ቢለብስ ወልይ መሆን ይችላል ማለት ሽርክ አይደለም እያለ ነው የሚያስተምረው ። ለማንኛውም ይህ ግለሰብ ብዙ ሴቶችና ወጣቶች ዘንድ እንዲህ አይነቱን የኩፍርና የሽርክ አስተምሮ ተቀባይነት እንዲኖረው እያደረገ ያለ ግለሰብ ስለሆነ ሙስሊሞች ከግለሰቡና ከአስተምሮቱ እንዲርቁና የኢስላም ጠላቶችን ተልእኮ እያስፈፀመ መሆኑን በማስገንዘብ መታደግ ያስፈልጋል እላለሁ ። http://t.me/bahruteka