tgindex
ዜጋ ሚድያ- Zega Media የኢትዮጵያውያን ትክክለኛና ታማኝ የመረጃ ምንጭ

ዜጋ ሚድያ- Zega Media የኢትዮጵያውያን ትክክለኛና ታማኝ የመረጃ ምንጭ

Статистика

The voice of voiceless in Ethiopia ስለእውነት ለኢትዮጵያውያን እንሰራለን ይህ የዜጋ ሚዲያ ቴሌግራም ቻናል ነው!!! ትክክለኛ፣ እውነተኛና ወቅታዊ መረጃ ለሁሉም ዜጎች ከዜጋ ሚዲያ! News and analysis on current National issues

Последний пост
23 июл.
Последнее чтение
13 авг.
Постов за неделю
0
Всего постов
20
Тип
открытый
Язык
ti
В каталоге с
12 авг.
Подписчики
207
+3 за 3 дн.
Сутки
0
0,00%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
1 270
20 постов
Вовлечённость
613,5%
к подписчикам
Постов в день
0,0
всего 20
Упоминаний
0
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
304
1/48двое суток
348
1/72трое суток
375

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • በኢትዮጵያ የሪልስቴት ዘርፍ የታዩ የፖሊሲና የኢንቨስትመንት ክፍተቶችን "ይደፍናል" የተባለለት ስትራቴጂያዊ ስምምነት ተፈረመ በኢትዮጵያ የሪልስቴት ኢንዱስትሪ ውስጥ የሚስተዋሉ የአቅም፣ የኢንቨስትመንት እና የፖሊሲ ትስስር ማነቆዎችን በዘላቂነት ለመቅረፍ "ያስችላል" የተባለለት አዲስ የስምምነት ምዕራፍ በዛሬው ዕለት ተፈርሟል። የኢትዮጵያ ሪልስቴት አልሚዎች ማሕበር (EREDA) እና ዶክሳ ቢዝነስ ትሬዲንግ፣ የአገር ውስጥና የአህጉር አቀፍ የቢዝነስ ትስስሮችን ወደ ላቀ ደረጃ የሚያሸጋግሩ ሁለት ስትራቴጂያዊ የመግባቢያ ሰነዶችን በይፋ ተፈራርመዋል። ይህ ስምምነት በዘርፉ የሚንቀሳቀሱ አልሚዎችን፣ የፋይናንስ ተቋማትን፣ የፖሊሲ አውጪዎችን እና የቴክኖሎጂ አቅራቢዎችን በአንድ ወጥ መድረክ በማገናኘት፣ እስካሁን በዘርፉ ሲታይ የነበረውን የተቆራረጠ አሰራር ለማስቀረት ያለመ እንደሆነ ተገልጿል። እንደስምምነቱ መነሻ፣ ሁለቱ ተቋማት በቅርቡ በሚካሄዱ ዓመታዊ የሪልስቴት ጉባኤዎች እና ቀጣናዊ የኤክስፖ መድረኮች ላይ በጋራ በመሰለፍ የኢንዱስትሪውን ተወዳዳሪነት ለማረጋገጥ ወስነዋል። ተቋማቱ በጋራ በሰጡት መግለጫ እንዳመለከቱት፤ ትብብሩ በደፈናው የሚመራ ሳይሆን፣ የሁለቱን ወገኖች ሃላፊነት፣ የስራ ጊዜ ሰሌዳ እና የሚጠበቁ ውጤቶችን በግልጽ በለየ ይፋዊ ስምምነት የሚመራ ነው። ይህም የዘርፉን ዕድገት በዘፈቀደ ሳይሆን በሳይንሳዊ እና በተጠያቂነት መርህ ለመምራት ታስቦ የተዘጋጀ መሆኑ ተመላክቷል።

  • без подписи

  • የኢትዮጵያ ላኪዎች በማሌዥያ ዓለም አቀፍ ኤክስፖ ላይ እንዲሳተፉ ጥሪ ቀረበ የኢትዮጵያ አምራቾች እና ላኪዎች ከአቻ የማሌዥያ ኩባንያዎች ጋር ጠንካራ የገበያ ትስስር እንዲፈጥሩ ጥሪ ቀረበ። ጥሪው የቀረበው የአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት (አዲስ ቻምበር) ከማሌዥያ ኤምባሲ ጋር በመተባበር ባዘጋጀው የቢዝነስ እድል ገለፃ መድረክ ላይ ነው። የአዲስ ቻምበር ፕሬዝዳንት ወ/ሮ ዘሐራ መሐመድ መድረኩ የንግድ ትስስርን እንደሚያጠናክርና የማሌዥያ ኩባንያዎችን ወደ ኢትዮጵያ እንደሚያስብ ገልጸዋል። የሁለቱ አገራት የንግድ ልውውጥ በ2025 ከ300 ሚሊዮን ዶላር በላይ መድረሱም ተመልክቷል። የማሌዥያ አምባሳደር መሐመድ አፈንዲ በበኩላቸው፣ በመስከረም 2026 በኳላላምፑር በሚካሄደው ታላቁ ዓለም አቀፍ የንግድ ትርኢት ላይ የኢትዮጵያ አባል ኩባንያዎች በአዲስ ቻምበር በኩል እንዲሳተፉ ጥሪ አቅርበዋል።

  • без подписи

  • 23 июл.306из tesfaget55

    የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በዲጂታል ገንዘቦች እና በቨርቹዋል ሀብቶች ዝውውር ላይ ጥብቅ እገዳ ጣለ ​የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በህግ ከተፈቀደው ውጪ በማናቸውም የቨርቹዋል ሀብቶች ግብይት ማድረግ በጥብቅ የተከለከለ መሆኑን አስታወቀ። ​እገዳው ቢትኮይንን ጨምሮ ሌሎች ክሪፕቶከረንሲዎችን ብቻ ሳይሆን፣ ለማንኛውም ክፍያና ኢንቨስትመንት የሚያገለግሉ በዲጂታል መልኩ የሚተላለፉ መግለጫዎችንም ያካትታል። ​በተለይም የሚከተሉት ተግባራት ሙሉ በሙሉ የተከለከሉ ናቸው ብሏል ባንኩ; 👉በቨርቹዋል ሀብት እና በመደበኛ ገንዘብ መካከል የሚደረግ መመንዘር 👉​በቨርቹዋል ሀብቶች መካከል የሚደረግ ልውውጥና ዝውውር 👉​የቨርቹዋል ሀብቶችን ማስቀመጥ፣ ማስተዳደር እና የፋይናንስ አገልግሎት መስጠት ​ህብረተሰቡ ከህጋዊ ተጠያቂነት፣ ከማጭበርበር፣ ከሳይበር ጥቃት እና ከከባድ የገንዘብ ኪሳራ ለመጠበቅ ከነዚህ እንቅስቃሴዎች እንዲቆጠብ ባንኩ አሳስቧል።

  • የኢትዮጵያ የፌደራል ፖሊስ 17 «አደገኛ» ያላቸውን ሕገወጥ የሰዎች አዘዋዋሪዎችን በቁጥጥር ሥር ማዋሉን አስታወቀ። የፌደራል ፖሊስ በማኅበራዊ የትስስር ገጹ ትናንት ባሰራጨው መግለጫ፤ የተጠርጣሪዎች መዝገብን በሰውና በሰነዶች በማጠናቀር ክስ እንዲመሰረትባቸው ለፌደራል አቃቤ ሕግ መላኩን አክሏል። የፌደራል ፖሊስ በምርመራ ሰነዱ እንዳመላከተው ተጠርጣሪዎቹ በምሥራቁ የሐገራችን ክፍል በኩል በጅቡቲና በየመን አድርገው ወደ ሳውዲ አረቢያ ሰዎች በሕገወጥ መንገድ ሲልኩ ነበረ። ለዚሁ ተግባራቸውም ከግለሰቦቹ ከአንድ ቢልዮን ብር በላይ መቀበላቸውን አክሏል። ተጠርጣሪዎቹ ተጎጂዎቹን በመያዣነት በመጠቀም ወደ ቤተሰቦቻቸው ስልክ በማስደወል ከፍተኛ ገንዘብ ሲጠይቁ እንደነበርና መክፈል ላልቻሉትን እያሰቃዩ በተንቀሳቃሽ ምስል በመቅረጽ የሥነ ልቦና ጫና ሲፈጥሩ ነበር ብሏል። ተጠርጣሪዎቹ ከ 40,000 በላይ ሰዎችን በሕገወጥ መንገድ ማዘዋወራቸውን የገለጸው የፌደራል ፖሊስ የወንጀል ፍሬ ያለውን ያካበቱትና በሐገር ውስጥና በውጭ የሚገኝ ጥሬ ገንዘብና ቋሚ ንብረቶቻቸውን ማሳገዱንም አክሏል።

  • ዐበይት ዜናዎች 1፤ በአገራዊ ምክክሩ በንዑስ ቡድኖች ሥር 10 አባላት በመያዝ የተቋቋሙ አምስት “ጥቃቅን” ቡድኖች ምክክር መጀመራቸው ተሰምቷል። 2፤ የሰኔ ወር የምግብ ዋጋ ግሽበት ወደ 15 ነጥብ 1 በመቶ አሻቀበ። በግንቦት ወር የምግብ የዋጋ ንረት 15 በመቶ ነበር። አጠቃላይ የሰኔ ወር የምግብ ዋጋ የጨመረው፣ በተለይ የዳቦ፣ የእህል፣ የስጋ፣ የወተት የእህል እና የአትክልቶች ዋጋ በመጨመሩ መሆኑን ብሄራዊ የስታትስቲክስ አገልግሎት ገልጧል። 3፤ ደብረጽዮን ገ/ሚካኤል የሚመሩት የሕወሃት ቡድን፣ ኢትዮጵያ ውስጥ "ኅልውናቸው በአደጋ ላይ ከወደቁ" ሐይሎች ጋር ጥምረት በመፍጠር ገዥውን መንግሥት እንደሚታገል ገለጠ። 4፤ ቅድሚያ ለሰብዓዊ መብቶች፣ በኃይል ሥልጣን የያዘው የትግራይ ክልል አስተዳደር ያወጣው አዋጅ በክልል ደረጃ መውጣት የሚችል መኾን አለመኾኑን እያጣራ ነው። 5፤ ፌደራል ፖሊስ፣ በጂቡቲ እና የመን በኩል ዜጎችን ወደ ሳውዲ ዓረቢያ ሰዎችን ሲያዘዋውሩና ከተጎጂዎች ከ1 ቢሊዮን ብር በላይ የተቀበሉ 17 ግለሰቦችን በቁጥጥር ሥር በማዋል ክስ እንዲመሠረትባቸው ለፍትሕ ሚንስቴር ላከ። 6፤ ባለፈው ሳምንት ሰኞ 15 ኢትዮጵያዊያን ከዛምቢያ ወደ ቦትስዋና "በሕገወጥ" መንገድ ለመግባት የዛምቤዚ ወንዝን በጀልባ ለመሻገር ሲሞክሩ ከሠመጡት መካከል፣ የሦስቱ አስከሬን መገኘቱን የዛምቢያ ጋዜጦች ትናንት ዘገቡ። ሁለቱ አስከሬኖች የኢትዮጵያዊያን መሆኑን ፖሊስ እንዳረጋገጠ ዘገባዎቹ ጠቅሠዋል። አምስት ኢትዮጵያዊያን በሕይወት እንደተገኙ ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ላይ የወጡ ዘገባዎች አመልክተው ነበር። የአገሪቱ ወታደሮችና ፖሊስ ቀሪዎቹን ኢትዮጵያዊያን ለማግኘት ፍለጋቸውን እንደቀጠሉ ነው ተብሏል። 7፤ በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን የባሶና ወራና ወረዳ ሠላምና ጸጥታ ጽሕፈት ቤት ምክትል ኃላፊ ተስፋዬ ጌታቸው፣ ትላንት ሰኞ ረፋዱ ላይ በደብረ ብርሃን ከተማ ለሥራ በእየተንቀሳቀሱ በነበሩበት ወቅት የወረዳው አስተዳደር ''ማንነታቸው ያልታወቁ ኃይሎች'' ሲል የጠራቸው የታጠቁ አካላት በተኮሱባቸው ጥይት ተመትተው ሕይወታቸው ማለፉ ተገለጠ። 8፤ ኢሕአፓ፣ መንግሥት በግጭት ማቆም ስምምነቱ የገባውን ቃል በመጣስ ትግራይን "በድምጽ አልባ ከበባ" ውስጥ በማስገባት ክልሉን ወደ ዳግም ጦርነት ለመመለስ በትጋት እየሠራ ይገኛል በማለት ከሠሠ።

  • 18 июл.309из addisfortune

    𝐀𝐃𝐕𝐄𝐑𝐓𝐈𝐒𝐄𝐌𝐄𝐍𝐓: ብርሃን ማስተርካርድ አለልዎ!! ********************* ቤትዎ ሆነው በኦንላይን ሲሸምቱ ወይም በሌሎች የአለም አቀፍ ከተሞች በአካል ተገኝተው ከተለያዩ ሱቆች ሲገበያዩ፡ ባንካችን - ነጻ የባህር ማዶ ጉዞ ፣ 85 ኢንች ግዙፍ Smart TV ፣ iPhone 17 እና Smart Watches አዘጋጅቶ ይጠብቅዎታል! ➡️የብርሃን ማስተርካርድዎን (Berhan MasterCard) ይጠቀሙ፣ የኦንላይን ክፍያዎችን ይፈጽሙ፤ እነዚህን ታላላቅ ሽልማቶች በእጅዎ ያስገቡ! ለበለጠ መረጃ፡- በባንኩ የደንበኞች ቁጥር 8292 ይደውሉ ወይም የባንኩን ድረገፅ እና ማህበራዊ ሚዲያዎች ይከታተሉ ፡፡ ብርሃን ባንክ

  • https://chatgpt.com/s/m_6a5b64985bc88191ab2040a312a96c52

  • 9 июл.4871из seledadotio

    #አሳዛኝ ለራሱ ምርቃት የተገዛው በሬ ወግቶት ህይወቱ ያለፈው ተመራቂ የቀብር ስነ-ስርዓት ተፈጸመ። የሰው ልጅ ህይወትና መጨረሻዋ ምንኛ የማይታወቅና ተለዋዋጭ ነው? ዛሬ በደስታና በፈገግታ የደመቀ ቤት፣ በአንድ ጀንበር የልቅሶና የዋይታ ድምፅ ሲሰማበት ማየት ልብን እጅግ ይሰብራል። በቅርቡ ከጎንደር ዩኒቨርሲቲ በኤሌክትሪካል ኢንጅነሪንግ (Electrical Engineering) ዘርፍ በታላቅ ስኬት ተመርቆ፣ ለነገው ህይወቱ ትልቅ ተስፋ ሰንቆ የነበረው ወንድማችን ፍሰሐ አስማማው እጅግ ልብ በሚሰብር አደጋ ከዚህ ዓለም በሞት መለየቱን ስንሰማ የተሰማን ሀዘን ወሰን የለውም። የነገው የሀገር ተስፋ፣ ለቤተሰቦቹ መከታ እና የብዙዎች ኩራት የነበረው ፍሰሐ፣ የለፋበትን የድካሙን ፍሬ አይቶ ገና ሳይጠግብ እንዲህ በወጣትነቱ መቀጠፉ እጅግ ያማል። ይህ ተስፋ የተጣለበት ወጣት ከሳምንት በፊት ነበር የምርቃት ካባውን የደረበው። ወላጆችና ዘመድ አዝማድም የምርቃቱን ደስታ አብረውት ለማሳለፍ ከጎንደር ጋይንት (ጎብጎብ) ከተማ ወደ ተወለደበት አካባቢ ይዘውት አምርተው ነበር። ነገር ግን በትላንትናው ዕለት ለምርቃቱ ድግስ ተብሎ የተገዛው በሬ በድንገት ወግቶት ህይወቱ ሊያልፍ ችሏል። ለአምላክ ምስጋና ይሁን ተብሎ ለደስታ ማክበሪያ የተዘጋጀው በሬ፣ በአሳዛኝ ሁኔታ የቤተሰቡን ተስፋና ደስታ ይዞ ተጓዘ። የዚህ ወጣት ስኬትና ህልም በአጭር የተቀጨበት አሳዛኝ የቀብር ስነ-ስርዓት ዛሬ በጋይንት ጎብጎብ ቀራኒዮ መድሃኒዓለም ቤተክርስቲያን ወዳጅ ዘመዶቹ፣ የክፍል ጓደኞቹና የአካባቢው ማህበረሰብ በተገኙበት ተፈፅሟል። ለወላጆቹ፣ ለወዳጅ ዘመዶቹ እንዲሁም ለጓደኞቹ በሙሉ ፈጣሪ ፍጹም መፅናናትን ይስጥልን። @Seledadotio @Seledadotio

  • የነዳጅ ዋጋዎች (ዛሬ) WTI ድፍድፍ ነዳጅ፡ 69.79 ዶላር (-0.78%) Brent ድፍድፍ ነዳጅ፡ 73.07 ዶላር (-0.91%) Murban ድፍድፍ ነዳጅ፡ 66.35 ዶላር (-0.15%) የተፈጥሮ ጋዝ፡ 3.292 ዶላር (+2.20%) ሰበር ዜና ቻይና ለሐምሌ ወር የነዳጅ ምርቶች ወደ ውጭ የሚላኩ ፈቃዶችን ልታሳድግ ነው ሳዑዲ አረቢያ የወደፊት የታላቅ ኃያል አጋሯን መርጣለች፤ እርሱም አሜሪካ አይደለም በሳይመን ዋትኪንስ – 23 ሰኔ 2026 ከኢራን ጋር የተካሄደውን ግጭት ተከትሎ ሳዑዲ አረቢያ ወደ ቻይናና ሩሲያ የበለጠ እየተጠጋች እንደሆነ ይታያል። በቅርቡ በተካሄዱ ከፍተኛ ደረጃ ስብሰባዎች ዋና ትኩረቱ በኃይል ዘርፍ ትብብርን ማስፋፋት ላይ ነበር። ይህ ለውጥ መነሻው ከ2014-2016 በነበረው የነዳጅ ዋጋ ጦርነት በኋላ የጀመረ ሂደት ነው። በዚያን ወቅት ቻይና በኢንቨስትመንት፣ በነዳጅ ስምምነቶች፣ በሳዑዲ አራምኮ ድጋፍ እና ከልዑል ልዑል መሐመድ ቢን ሳልማን የኢኮኖሚ ራዕይ ጋር በመጣጣም በሳዑዲ ውስጥ ተፅእኖዋን አሳደገች። በተጨማሪም ሪያድ በአሜሪካ የደህንነት ዋስትና ላይ የነበራት እምነት ተናውጧል። ምክንያቱም በ«ኦፕሬሽን ኤፒክ ፊዩሪ» ወቅት ኢራን በሳዑዲ ዋና ዋና የኃይል መሠረተ ልማቶች ላይ ጥቃት ማድረሷ ነው። ሳዑዲ አረቢያ በታሪኳ ውስጥ በአሜሪካና በቻይና መካከል ሚዛናዊ ግንኙነት ለመጠበቅ ሞክራለች። ከ2014-2016 የነዳጅ ዋጋ ጦርነት በፊት አሜሪካ ዋና አጋሯ ነበረች፤ ከዚያ በኋላ ግን ቻይናና ሩሲያ የበለጠ ተፅእኖ አገኙ። በኋላም በአሜሪካ ፕሬዚዳንት Donald Trump ሁለተኛ የስልጣን ዘመን መጀመሪያ ሳዑዲ እንደገና ወደ አሜሪካ ተጠጋች። ነገር ግን ከኢራን ጋር የተያያዘው ግጭት በኋላ ሪያድ እንደገና ወደ ቻይናና ሩሲያ የምትመለስ መስሎ ይታያል። ባለፈው ሳምንት የቻይና ብሔራዊ የኃይል አስተዳደር ምክትል ኃላፊ ሶንግ ሆንግኩን እና የSaudi Aramco የዳውንስትሪም ፕሬዚዳንት መሐመድ አል-ቃህታኒ ተገናኝተው የነዳጅና ጋዝ ትብብርን ማሳደግ ተወያይተዋል። ጽሑፉ እንደሚገልጸው፣ የ1945 የአሜሪካ–ሳዑዲ ስምምነት ለአስርተ ዓመታት የሁለቱ አገሮች ግንኙነት መሠረት ነበር። በዚያ ስምምነት መሠረት አሜሪካ ከሳዑዲ የነዳጅ አቅርቦት ታገኛለች፤ በምትኩም የሳዑዲ መንግሥትን ደህንነት ትጠብቃለች። ከ2014-2016 የነዳጅ ዋጋ ጦርነት በኋላ ግን ሳዑዲ እና ሌሎች የኦፔክ አባላት ከባድ የፋይናንስ ጉዳት ደረሰባቸው። ይህም ሩሲያን ወደ «ኦፔክ ፕላስ» ለማስገባት አስገደዳቸው። ቻይናም ይህን ሁኔታ ተጠቅማ በሳዑዲ ውስጥ ተፅእኖዋን ይበልጥ አስፋፋች። በ2017 ንጉሥ Salman bin Abdulaziz Al Saud ቻይናን በጎበኙበት ወቅት 65 ቢሊዮን ዶላር የሚገመቱ የንግድ ስምምነቶች ተፈርመዋል። ከዚያም በኋላ ሁለቱ አገሮች 20 ቢሊዮን ዶላር የጋራ የኢንቨስትመንት ፈንድ መመስረታቸው ተገልጿል። ጽሑፉ በመጨረሻ የሚያቀርበው ሐሳብ ሳዑዲ አረቢያ አሜሪካን እንደ ብቸኛ የደህንነት አጋር ከማየት ወደ ብዙ ኃያላን በሚሳተፉበት አዲስ ዓለም ሥርዓት እየተመለከተች መሆኑን ነው። በተለይም በኢራን ጥቃቶች ወቅት የሳዑዲ የነዳጅና የጋዝ ተቋማት መጎዳታቸው ሪያድ በአሜሪካ የደህንነት ጥበቃ ላይ ያላትን እምነት እንዲያጠያይቅ አድርጓል። ማስታወሻ: ይህ የOilprice.com ደራሲ ሳይመን ዋትኪንስ የጻፈው ትንታኔ ነው፤ በውስጡ የቀረቡት አስተያየቶች የደራሲው እይታ ናቸው።

  • #ምርጫ2018  : ብልፅግና ፓርቲ ዛሬ ይፋ በተደረገው ውጤት 438 የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት (ፓርላማ) መቀመጫዎችን አግኝቷል። ይህም ፓርቲው መንግሥት መመስረት የሚያስችለው ነው። በሌላ በኩል ፦ - የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ ፓርቲ (ኢዜማ) 👉 13 መቀመጫዎች - የግል ዕጩዎች 👉 8 መቀመጫዎች - አማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) 👉 6 መቀመጫዎች - የአፋር ህዝብ ፓርቲ 👉 1 መቀመጫ - የአማራ ዴሞክራሲያዊ ኃይል ንቅናቄ 👉 3 መቀመጫዎች - አርጎባ አንድነት ጀርበቲ ፓርቲ 👉 1 መቀመጫ - ትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት ፓርቲ 👉 2 መቀመጫዎች - ነጻነት እና እኩልነት ፓርቲ 👉 3 መቀመጫዎች - ጉሙዝ ብሔራዊ ንቅናቄ 👉 1 መቀመጫ - አዲስ ትውልድ ፓርቲ 👉 1 መቀመጫ - ሰላም ለኢትዮጵያ ጥምረት 👉 1 መቀመጫ - የጌዴኦ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ 👉 1 መቀመጫ - የወላይታ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ 👉 1 መቀመጫ - የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ (መድረክ) 👉 3 መቀመጫዎች - የኦጋዴን ብሔራዊ ነጻነት ግንባር 👉 1 መቀመጫ - ህብረት ለዴሞክራሲና ለነጻነት ፓርቲ 👉 1 መቀመጫ - ሶማሌ ፌዴራሊስት ፓርቲ 👉 1 መቀመጫ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ሰኔ 14 ቀን 2018 ዓ/ም @tikvahethiopia

  • ዓርብ፣ ሰኔ 12፣ 2018 ዓ፣ም ዐበይት ዜናዎች 1፤ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ፣ የባሕር በር ጉዳይ "የአገራዊ ልማት" እና "የቀጠናዊ ትስስር" ጉዳይ እንጅ "የጅዖፖለቲካ ፉክክር" ተደርጎ መወሠድ የለበትም በማለት ተናገሩ። ጌዲዮን የባሕር በር ጉዳይ ለኢትዮጵያ "አስፈላጊ የሆነ" ጉዳይ ተደርጎ እንጅ እንደ "ፍጥጫ" መታየት እንደሌለበት ቻታም ሃውስ የተባለ ተቋም ለንደን ውስጥ ሰሞኑን ባዘጋጀው መድረክ ላይ ተናግረዋል። በኢትዮጵያ የባሕር በር ጥያቄ ላይ የሚነሱ ስጋቶች እስካሁን እየተቃኙ ያሉት "ከታሪካዊ አለመተማመን" እንጅ "ከመጻዒ እድሎች" አንጻር አለመኾኑን ጌዲዮን አጽንዖት ሠጥተዋል። የኢትዮጵያ የባሕር በር ፖሊሲ "በንግግር"፣ "በጋራ ተጠቃሚነት" እና "በቀጠናዊ መረጋጋት" ላይ የተመሠረተ መኾኑን የጠቀሱት ጌዲዮን፣ ጉዳዩ የአገሪቱን "ንግድ"፣ "ሎጅስቲክ"፣ "የኢነርጂ ደኅንነት" እና "ዘላቂ የኢኮኖሚ እቅድ" የሚመለከት መኾኑን አስምረውበታል። 2፤ ትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት፣ ኢሰመኮ ባለፈው ወር በኦሮሚያ ክልል አርሲ ዞን አሰኮ ወረዳ በተፈጸመው "ሐይማኖትን" እና "ማንነትን" መሠረት ያደረገ ጥቃት ዙሪያ በቅርቡ ያወጣውን ሪፖርት ተቸ። ትብብሩ፣ ኢሰመኮ በጥቃቱ የተገደሉት ሰዎች ሦስት ብቻ እንደኾኑ መግለጡ፣ ጥቃቱ ሐይማኖትን ማዕከል ያላደረገና የጥቃቱ ፈጻሚም "ኦነግ ሸኔ" እንደኾነ ድምዳሜ ላይ መድረሱ፣ "ፖለቲካዊ ዓላማ" ያለውና ጉዳዩን ለማድበስበስ የፈለገ አስመስሎበታል ሲል ዛሬ ባወጣው መግለጫ ወቅሷል። በጥቃቱ ሕይወታቸውን ያጡ ሰዎች ቁጥር ከተጠቀሠው በ10 እጥፍ እንደሚበልጥ መረጃ እንዳለው የጠቀሠው ትብብሩ፣ ጥቃቱ "ሐይማኖትን ማዕከል" ያደረገ መኾኑን ከታማኝ ምንጮች አረጋግጫለሁ ብሏል። ኢሰመኮ በሪፖርቱ ላይ ማስተካከያ አድርጎ ለሕዝብ ይፋ እንዲያደረግም ትብብሩ ጠይቋል። ኮሚሽኑ በዜጎች ላይ ለሚፈጸሙ ግፎች የመፍትሔ ሃሳቦችን ያቀርብ እንደነበር ትብብሩ የጠቀሠ ሲኾን፣ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን እውነትን የማፈላለግ ሂደቱ እየተቀየረና የመብት ጥሠትን የማድበስበስ አካሄድ እያሳየ ይመስላል ሲል ስጋቱን ገልጧል። 3፤ በኢትዮጵያ የሃይማኖት መሪዎች በሰላም ግንባታ፣ አግላይነትን በመከላከል እና የሰዎችን ሰብዓዊ ክብር በማስጠበቅ ረገድ ውጤታማ አስተዋጽዖ እንዲያደርጉ የሚያግዝ የአጋርነት ስምምነት በኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ እና በኢትዮጵያ የጀርመን ኤምባሲ መካከል ተፈረመ። በሁለቱ ወገኖች መካከል ዛሬ የተፈረመው የአጋርነት ፕሮጀክት፣ የሃይማኖት መሪዎች በአገሪቱ ውስጥ ግጭትን በመከላከልና በመፍታት፣ ብሄራዊ መግባባትን በማስፈን፣ ሕገወጥ የሰዎች ዝውውርን በመከላከል፣ የአየር ንብረት ለውጥ ችግሮችን በመቀነስ፣ ጾታዊ ጥቃትን በማስወገድና ኤችአይቪ ኤድስን በመከላከል ዙሪያ የተለያዩ ሥራዎችን መስራት እንዲችሉ የሚያግዝ መኾኑን የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤው ባሠራጨው መረጃ ላይ ገልጧል። ኾኖም የአጋርነት የፕሮጀክት ስምምነቱ በየትኞቹ የአገሪቱ ክፍሎች እንደሚተገበር፣ ለምን ያህል ጊዜ እንደሚቆይ እና ምን ያህል በጀት እንደተመደበለት የተቋሙ መረጃ አልጠቀሠም። 4፤ ኢትዮጵያ ላስጠለለቻቸው ስደተኞችና ጥገኝነት ጠያቂዎች የነደፈችውን "ማካተት" የተሠኘ ብሄራዊ ፍኖተ ካርታ ትናንት ይፋ አደረገች። "ማካተት"፣ ስደተኞች ከሰብዓዊ እርዳታ ተቀባይነት ወጥተው፣ ከማኅበረሰቡ ጋር እንዲቀላቀሉ፣ ሠርተው ራሳቸውን እንዲችሉና በአገሪቱ ልማት ውስጥ እንዲታቀፉ የሚያስችል ብሄራዊ ፍኖተ ካርታ ነው። መንግሥት ይህንኑ ፍኖተ ካርታ ስደተኞችን ባስጠለሉ ሁሉም የአገሪቱ ክልሎች ተግባራዊ ለማድረግ ቁርጠኛ መኾኑን ፍኖተ ካርታው ይፋ በተደረገበት ስነ ሥርዓት ላይ አረጋግጧል። የተመድ የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን፣ የ"ማካተት" ፍኖተ ካርታ ስደተኞች እና አገራዊ ልማት እጅ ለእጅ ተያይዘው ሊሄዱ እንደሚችሉ ለዓለም ምሳሌ የሚኾን ነው በማለት በመድረኩ ላይ አድናቆቱን ገልጧል። 5፤ በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሸዋ ዞን በወልመራ ወረዳ የፍርድ ቤት ችሎት ውስጥ ሴት ዳኛ ወርቄ ፈከንሳንና ባለቤቱን በሽጉጥ ተኩሶ የገደለውና ራሱን ተኩሶ ያቆሠለው ግለሰብ ለሕክምና ከገባበት ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሕንጻ ላይ ተወርውሮ ዛሬ ራሱን ማጥፋቱን ዋዜማ ሠምታለች። ሟች ራሱን ያጠፋው፣ ከዳኛዋ እና ከባለቤቱ ግድያ ጋር በተያያዘ ፖሊስ ምርመራ እያደረገ በነበረበት እና ሕክምናውን ጨርሶ ከሆስፒታሉ ለማውጣት በሚዘጋጅበት ወቅት ላይ መሆኑን ዋዜማ ከምንጮቿ ተረድታለች። ሟቹ ግለሰብ ዳኛ ወርቄን እና ባለቤቱን ወደ ችሎት ደብቆ ባስገባው ሽጉጥ ተኩሶ የገደለው፣ ባለፈው ግንቦት 27 ከባለቤቱ ጋር በገባበት የፍትሐብሔር ክርክር ላይ ዳኛዋ ብይን እየሠጡ በነበረበት ሰዓት ላይ እንደነበር ዋዜማ በወቅቱ መዘገቧ ይታወሳል። 6፤ ናይጀሪያ ከኢትዮጵያ ጋር በቅርቡ በደረሠችው የፍርደኞች ልውውጥ ስምምነት መሠረት ወደ ናይጄሪያ የሚመለሱ ፍርደኞች በነጻ ሊሠናበቱ ይችላሉ የሚሉ ስጋቶችን ውድቅ አደረገች። የአገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ቢያንካ ኦዴሜጉ ኦጂኩ፣ የሁለትዮሹ የፍርደኞች ልውውጥ የመግባቢያ ስምምነት የእስር ቅጣቱን ከጣለው አገር ይሁንታ ውጭ ለፍርደኞች ምኅረት ማድረግን ይከለክላል ማለታቸውን የአገሪቱ ጋዜጦች ዘግበዋል። ከቃሊቲ እና አባ ሳሙኤል ወህኒ ቤቶች ወደ ናይጀሪያ ወህኒ ቤቶች ተዛውረው የኢትዮጵያ ፍርድ ቤቶች የጣሉባቸውን ቅጣቶች የሚጨርሱ ናይጀሪያዊያን ፍርደኞች ብዛት 98 መኾኑን ሚንስትሯ ተናግረዋል ተብሏል። በናይጀሪያ ወህኒ ቤቶች ውስጥ ስንት ኢትዮጵያዊያን ፍርደኞች እንዳሉ የኢትዮጵያም ኾነ የናይጄሪያ ባለሥልጣናት አልገለጡም። 7፤ ከአስር በላይ የአፍሪካ አገራት ሕግ አውጪዎች የግብረ ሰዶማዊያን መብቶችን የሚገድቡ አዳዲስ ሕጎችን ለማውጣት ቃል መግባታቸውን ሮይተርስ ዘገበ። የቤተሰብ እሴቶችንና የቤተሰብ ሉዓላዊነትን የሚያቀነቅኑ ከአፍሪካና አውሮፓ የተውጣጡ የመብት ተሟጋቾችና የ20 አገራት ሕግ አውጪዎች ጸረ-ግብረ ሰዶማዊያን ሕግ ባወጣችው ጋና በቅርቡ ጉባኤ አካሂደው ነበር። የጉባኤው ተሳታፊዎች፣ የአሜሪካና አውሮፓ ወግ አጥባቂዎች እንቅስቃሴ አፍሪካ ውስጥ ጭምር በግብረ ሰዶማዊያን መብት ዙሪያ ለውጥ እያመጣ መሆኑን እንደገለጡ ዘገባው ጠቅሷል። የጉባኤው ተሳታፊ ሕግ አውጪዎች፣ አገራት የአፍሪካን ባሕልና እሴቶች የሚጠብቁ ሕጎችን እንዲያወጡና ግብረ ሰዶማዊነትን ከሚያራምዱ ዓለማቀፍ ስምምነቶች እንዲወጡ የሚጠይቅ "የአፍሪካ የቤተሰብ፣ ሉዓላዊነትና እሴቶች ቻርተር" የተሠኘ ሠነድ አጽድቀዋል። እንዲሁም:- 1.የድምጻዊ ሮቤል ሚዲቅሳ "ከበር አፍ" የተሰኘ የሙዚቃ ኮንሰርት ነገ ሰኔ 13 ቀን 2018 ዓ.ም በቃና ስቱዲዮ ይካሄዳል። ከሮቤል በተጨማሪም በኮንሰርቱ ላይ ልዑል ሲሳይና ኤደን አይሸሹም የሙዚቃ ሥራቻቸውን ያቀርባሉ። 2.የዋሽንትና ፒያኖ ኮንሰርት ተዘጋጅቷል። ይህ ኮንሰርት ነገ ቅዳሜ ሰኔ 13 ቀን 2018 ዓ.ም ከምሽቱ 1:00 ጀምሮ በአልያንስ ኢትዮ ፍራንሲስ (ፒያሳ) ይካሄዳል። መግቢያ በነፃ። 3.በዛጎል የመጽሐፍት ባንክ በሚዘጋጀው "ነገረ መጻሕፍት" የመጻህፍት ውይይት ላይ ደራሲ ሲሳይ ንጉሱ በክብር እንግድነት ተጋብዟል። ለውይይት የተመረጠው "ሣልሳዊ ልደት" መጽሐፍ ነው።ውይይቱ ነገ ቅዳሜ ሰኔ 13 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 ጀምሮ ምኒልክ ሆስፒታል አካባቢ በሚገኘው "FSS" አዳራሽ ውስጥ ይካሄዳል።

  • ሐሙስ፣ ሰኔ 11፣ 2018 ዓ፣ም ዐበይት ዜናዎች 1፤ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት፣ "አክራሪ" ባላቸው የሕወሓት አባላትና የቅርብ ቤተሰቦቻቸው ላይ የቪዛ እገዳ ጣለ። የቪዛ እገዳ የተጣለባቸው፣ በትግራይ ያለው ቀውስ እንዳይፈታ ተሳትፎ አድርገዋል ወይም ተባባሪ ኾነዋል በተባሉ የቡድኑ አባላትና ቤተሰቦቻቸው ላይ መኾኑን መስሪያ ቤቱ ገልጧል። መስሪያ ቤቱ፣ በክልሉ ሰላምና መረጋጋት እንዳይሠፍን በሚያደርጉ የቡድኑ ባለሥልጣናትና ሌሎች ግለሰቦች ላይ ተጠያቂነትን ለማስፈን ርምጃዎችን መውሠድና ማጋለጥ እንደሚቀጥልም አስጠንቅቋል። በፌደራል መንግሥቱና በሕወሃት አክራሪዎች መካከል ያለው ውጥረት በድጋሚ ጦርነት ሊቀሰቀስ ይችላል የሚል ስጋት መፍጠሩን መስሪያ ቤቱ ጠቅሷል። መስሪያ ቤቱ፣ የቪዛ እገዳ የጣለባቸውን ግለሰቦች ብዛት አልጠቀሠም። 2፤ ከአውሮፓዊያኑ 2024 እስከ 2025 በትምህርት ላይ በተፈጸሙ ጥቃቶች ከፍተኛውን ቁጥር ካስመዘገቡ አገራት መካከል ኢትዮጵያ አንዷ ኾነች። ግሎባል ኮዕሊሽን ቱ ፕሮቴክት ኢዱኬሽን ፍሮም አታክ የተሠኘ ድርጅት፣ በሁለቱ ዓመታት ውስጥ በአገሪቱ በትምህርት ተቋማት ላይ 100 ጥቃቶች ተፈጽመዋል ሲል ሰሞኑን ባወጣው ሪፖርት ገልጧል። በዚሁ ጊዜ ውስጥ የከፍተኛ የትምህርት ተቋማትን ጨምሮ በመምህራን፣ ተማሪዎችና በትምህርት ተቋማት ሠራተኞች ላይ ጥቃቶች ቀጥለው እንደነበር የጠቀሰው ተቋሙ፣ ከ1 ሺሕ 200 በላይ ትምህርት ቤቶች "ለወታደራዊ አገልግሎት" ስለመዋላቸው መረጃ ማግኘቱንም ጠቅሷል። ቢያንስ 12 መምህራን ከግጭቶች ጋር በተያያዘ እንደተገደሉና 15ቱ እንደታገቱ መረዳቱንም ድርጅቱ አስታውቋል። ብዛት ያለው ጥቃት ከተመዘገበባቸው አገራት መካከል፣ ዲሞክራሲያዊት ኮንጎ ሪፑብሊክ፣ ሔይቲ እና ፍልስጤም ይገኙበታል። 3፤ የአማራ ክልል ዓቃቤያን ሕግ የሙያ ማኅበር፣ መንግሥት ከ2016 ዓ፣ም ጀምሮ በተለያዩ ጊዜያት ለመንግሥት ሠራተኞች ባደረገው የደመወዝ ጭማሪ የክልሉ ዓቃቤያነ ሕግ አንድም ጊዜ ተጠቃሚ አልሆኑም ሲል ቅሬታውን ገለጠ። ማኅበሩ ለጠቅላይ ሚንስትር ጽሕፈት ቤትና ለሁለት የፌዴራል መሥሪያ ቤቶች ዛሬ በጻፈው ደብዳቤ፣ ለሌሎች የመንግሥት ሠራተኞች የተደረገው አገር ዓቀፍ የደመወዝ ጭማሪ እስካሁን ተግባራዊ አልተደረገም ብሏል። ለክልሉ ዓቃቢያነ ሕግ የደመወዝ ጭማሪው ተግባራዊ ባለመኾኑ ምክንያት፣ ባለሙያዎቹ ለከፍተኛ ኢኮኖሚያዊ፣ ማኅበራዊ እና ስነ-ልቦናዊ ቀውስ እየተዳረጉ እንደሚገኙ ማኅበሩ በደብዳቤው ጠቅሷል። የደመወዝ ጭማሪው ተፈጻሚ ከኾነበት ጊዜ ጀምሮ ለክልሉ ዓቃቤያነ ሕግ ጭማሪው ተሠልቶ እንዲከፈላቸው ማኅበሩ ጠይቋል። 4፤ አሜሪካ ኢትዮጵያን ጨምሮ ለ40 አገራት ለሰብዓዊ ዕርዳታና ለአደጋ ምላሽ የሚውል 1 ቢሊዮን ዶላር ለተመድ ሕጻናት ድርጅት (ዩኒሴፍ) እና ለዓለም ምግብ ፕሮግራም ለመስጠት ወሠነች። ከገንዘብ ድጋፉ 800 ሚሊዮን ዶላሩ ለዓለም የምግብ ፕሮግራም የሚሠጥ ሲሆን፣ 218 ሚሊዮን ዶላር ደሞ ለዩኒሴፍ እንደሚሠጥ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤቱ ገልጧል። ገንዘቡ ለሁለቱ ድርጅቶች የተፈቀደው፣ የእርዳታ አሠጣጣቸው ሊለካ የሚችል ውጤት የሚያስመዘግብና ተጠያቂነትን የሚያሠፍን በመኾኑ እንደኾነ መስሪያ ቤቱ ጠቅሷል። ድርጅቶቹ፣ ገንዘቡን ለምግብ እርዳታ፣ ለአልሚ ምግብ አቅርቦት፣ ለጤና፣ ለሕጻናት እንክብካቤ፣ ለሎጅስቲክ እንዲሁም ለውሃና ንጽህና አጠባበቅ እንዲያውሉት ተፈቅዶላቸዋል። ከገንዘብ ድጋፉ ተጠቃሚ ከሚኾኑት አገራት መካከል ከኢትዮጵያ በተጨማሪ፣ በርማ እና ዩክሬን ይገኙበታል። 5፤ የቀይ ባሕር አፋሮች ዲሞክራሲያዊ ድርጅት፣ የዓለም መንግሥታት የኤርትራ መንግሥት ከተመድ የሰብዓዊ መብቶች ተቆጣጣሪ ልዩ ራፖርተር ጋር እንዲተባበርና ልዩ ራፖርተሩ ወደ ኤርትራ እንዲገቡ እንዲፈቅድ ተጽዕኖ እንዲያደርጉ ጠየቀ። ልዩ ራፖርተሩ በኤርትራ ዙሪያ ለተመድ የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት ሰሞኑን ያቀረቡትን ሪፖርት እንደሚደግፍ የገለጠው ድርጅቱ፣ ምክር ቤቱ የልዩ ራፖርተሩን ተልዕኮ እንዲያጠናክርና የልዩ ራፖርተሩን የጊዜ ቆይታ እንዲያራዝም ጠይቋል። ድርጅቱ፣ አባል አገራት ኤርትራዊያን ስደተኞችን፣ ጋዜጠኞችንና የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾችን ከኤርትራ መንግሥት የድንበር-ዘለል "ማስፈራሪያዎች" እና "ዛቻዎች" እንዲከላከሉ ጭምር ጥሪ አድርጓል። 6፤ የእስራኤል መከላከያ ሚንስትር እስራኤል ካትዝ፣ እስራኤል እና ሶማሊላንድ ለዓመታት "ሚስጥራዊ ትብብር" ሲያደርጉ መቆየታቸውን ከሶማሊላንድ ፕሬዝዳንት አብድላሂ አብድራህማን ጋር በተወያዩበት ወቅት ተናገሩ። ኾኖም እስራኤል እና ሶማሊላንድ በምን መስኮች ሚስጢራዊ ትብብር ሲያደርጉ እንደቆዩ ሚንስትሩ ከመግለጽ እንደተቆጠቡ መስሪያ ቤታቸው ባወጣው መረጃ ላይ ጠቅሷል። ሚንስትሩ፣ አሁን የሁለትዮሽ ትብብሩን ወደ አዲስ ደረጃ ለማሸጋገር ወስነናል ማለታቸው ተገልጧል። የካትዝ እና የፕሬዝዳንቱ ውይይት "የጸጥታ"፣ "ኢኮኖሚ" እና "ፖለቲካ" ትብብሮችን ለማጠናከር ያለመ ነበር ተብሏል። ፕሬዝዳንት አብድላሂ ለሶማሊላንድ የአገርነት እውቅና በሠጠችው እስራኤል ባለፉት ቀናት የመጀመሪያውን ይፋዊ ጉብኝት በማድረግ ላይ ናቸው። እንዲሁም:- 1. በአለ የሥነጥበብና ዲዛይን ት/ቤት የተዘጋጀውና ለመጀመሪያ ጊዜ የሚካሄደው "የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የፊልም ፌስቲቫል" ከነገ ዓርብ ሰኔ 12 እስከ እሁድ ሰኔ 14 2018 ዓ.ም ድረስ በያሬድ የሙዚቃ ት/ቤት ግቢ ውስጥ ይከናወናል። 2. የድምጻዊት ዶናት ተክሉ "አሐዱ" የተሰኘ አዲስ የሙዚቃ አልበም ነገ ዓርብ ሰኔ 12 ቀን 2018 ዓ.ም በሽርጉድ ኢንተርቴይመንት በኩል ለአድማጮች ይቀርባል። 3.የሃንጋሪ ኤምባሲ (አ.አ) ያዘጋጀው የክላሲካል ሙዚቃ ኮንሰርት፣ ነገ ዓርብ ሰኔ 12 ቀን 2018 ዓ.ም  ከምሽቱ 12:30 ጀምሮ በጣሊያን የባሕል ማዕከል ይካሄዳል።

  • ትዕግስት አሰፋ የዓለም ሪከርድን ሰበረች በስተመጨረሻም ጀግኒቷ አትሌት ትዕግስት አሰፋ ለሁለተኛ ተከታታይ ጊዜ የለንደን ማራቶን አሸናፊ ሆነች። አትሌቷ ርቀቱን ለማጠናቀቅ 2:15.41 ፈጅቶባታል። ይህም በሴቶች አሯሯጮች ብቻ በራሷ ተይዞ የነበረውን የዓለም ሪከርድም ጭምር እንድትሰብር አስችሏታል። ኬንያውያኑ ሄለን ኦብሪ እና ጆስሊን ኬፕኮስጌይ 2ኛ እና 3ኛ ሲወጡ ደጊቱ አዝመራው በ4ኛነት ጨርሳለች።

  • без подписи

  • ሚያዝያ 17፣ 2018 ዓ፣ም ዐበይት ዜናዎች 1፤ በትግራይ ክልል በነዳጅ እጥረት ሳቢያ የመንግሥትና የግል የጤና ተቋማት እንዲኹም የክልሉ ቀይ መስቀል ማኅበር አምቡላንሶች ሥራ ማቆማቸውን ዋዜማ ሠምታለች። ዋዜማ ያነጋገረቻቸው በኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር የትግራይ ቅርንጫፍ ምንጮች፣ የማኅበሩ አምቡላንሶች በነዳጅ መጥፋት ሳቢያ አገልግሎት መሥጠት ካቆሙ ሳምንታት እንደተቆጠሩ ገልጸዋል። በመቀሌ ዩኒቨርሲቲ የዓይደር ጠቅላላ ሆስፒታል፣ የአክሱምና የአዲግራት ሆስፒታል አምቡላንሶችም ለወላድ እናቶችና ለሕሙማን አገልግሎት መሥጠት አቁመዋል ተብሏል። በዚህ ሳቢያ አገልግሎት ለማግኘት ወደ ጤና ተቋማት የሚሄዱ ወላድ እናቶችና ሕሙማን ቁጥራቸው በእጅጉ መቀነሱን ምንጮች ነግረውናል። 2፤ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል፣ መተከል ዞን ግልገል በለስ ከተማ ትናንት ንጋት ገደማ ጣቂዎች ማረሚያ ቤት ላይ በከፈቱት ጥቃት ሰባት ሰዎች መገደላቸውን ከምንጮች መስማቱን ጠቅሶ ቢቢሲ ዘገበ። ጥቃቱን የከፈቱት፣ ወደ ሰላማዊ ሕይወት ያልተመለሱ የቀድሞው የጉሙዝ አማጺ ቡድን አባላት የነበሩ ታጣቂዎች እንደኾኑ ምንጮቹ እንደነገሩት ዘገባው ጠቅሷል። ታጣቂዎቹ ከማረሚያ ቤቱ ፖሊስ ጋር የተኩስ ልውውጥ ባደረጉበት ወቅት በተባራሪ ጥይት የተገደሉት፣ በአካባቢው በሚገኝ የቄራ ድርጅት ውስጥ የሚሠሩ ሠራተኞች መኾናቸውን ምንጮች ተናግረዋል ተብሏል። በተኩስ ልውውጡ፣ አንድ ሚሊሺያ እና ሁለት ታጣቂዎች መገደላቸውን መስማቱንም ዘገባው አመልክቷል።  3. የአርቲስት ቴዎድሮስ ካሣሁን (ቴዲ አፍሮ) ስቱዲዮ መዘረፉን ከድምፃዊው ቅርብ ሰዎች አረጋግጫለሁ ብሏል ዶቼ ቬለ ። ሚያዚያ 15 ቀን 2018 ምሽት የፖሊስ የደንብ ልብስ የለበሱ፣ መሣሪያ የታጠቁ እና በተሽከርካሪ የመጡ አካላት ጠባቂዎችን በመደብደብ አዲስ አበባ ውስጥ በተለምዶ ሲኤምሲ አካባቢ ከሚገኘው የአርቲስቱ ስቱዲዮ ንብረቶች መዝረፋቸውን ዘገባው አመልክቷል። ስቱዲዮው ተሰብሮ አርቲስቱ ለሙዚቃ ሥራው የሚጠቀምባቸው ንብረቶች መዘረፋቸውን፣ አርቲስት ቴዎድሮስ ካሣሁን ግን እንቅስቃሴው ተገትቶም ቢሆን እስካሁን በደኅና ሁኔታ ላይ እንደሚገኝም ምንጮቹ አስረድተዋል።መንግስት በጉዳዩ ላይ እስካሁን ያለው ነገር የለም። 4፤ በደቡብ ኢኢትዮጵያ ክልል ወላይታ ዞን ዳሞት ጋሌ ወረዳ ሚያዝያ 15 በተከሠተ መሬት መንሸራተት የአራት ሰዎች ሕይወት ጠፋ። የመሬት መንሸራተትና ናዳ የተከሠተው፣ ሚያዝያ 15 ቀን ከምሽቱ 10:00 ጀምሮ በወረዳው ከፍተኛ ዝናብ መዝነቡን ተከትሎ መኾኑን የዞኑ አስተዳደር ገልጧል። በመሬት መንሸራተት አደጋው አራቱ ሰዎች ሕይወታቸውን ያጡት፣ ከዳሞታ ተራራ ግርጌ በሚገኙ ሦስት ቀበሌዎች ውስጥ መኾኑን የዞኑ አስተዳደር ጠቅሷል። የዞኑ አስተዳደር፣ ካዎ ኮይሻ፣ ኪንዶ ኮይሻ፣ ኪንዶ ዲዳዬ፣ ድጉና ፋንጎ እና አበላ አባያ በተባሉ አካባቢዎችም በቀጣይ ቀናትም የመሬት መንሸራተት፣ ናዳ እና የወንዝ ሙላት ሊያጋጥም ይችላል ሲል አስጠንቅቋል። 5፤ የአሜሪካው ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር፣ ለሶማሊያ የሚሠጠውን እርዳታ እንዲያቋርጥ የሚጠይቅ ረቂቅ የውሳኔ ሀሳብ ለሕግ መምሪያ ምክር ቤቱ ቀረበ። ረቂቅ የውሳኔ ሀሳቡ፣ በሙስና የተጠረጠሩ የሶማሊያ መንግሥት ከፍተኛ ባለሥልጣናት ወደ አሜሪካ እንዳይገቡ የቪዛ ማዕቀብ እንዲጣልባቸው ጭምር የሚጠይቅ ነው። አሜሪካ በሶማሊያ ላይ የእርዳታ እገዳና የቪዛ ማዕቀብ እንድትጥል የውሳኔ ሀሳብ የቀረበው፣ በአገሪቱ የአስተዳደር ብልሹነትና በዓለማቀፍ እርዳታ ላይ የሚፈጸም ከፍተኛ ሙስና ተንሠራፍቷል በሚል ነው። ረቂቅ የውሳኔ ሀሳቡን ያቀረቡት፣ ሮኒ ጃክሰን እና ሌሎች የምክር ቤት አባላት ናቸው። እንዲሁም:- 1. በሙዚቀኛ ለታሪክ ጥላሁን እና በያሬድ የሙዚቃ ትምህርት ቤት ትብብር የተሰናዳው የ"Young Addis Project" የጃዝ ሙዚቃ ዝግጅት በመጪው ሰኞ ሚያዚያ 20 2018 ዓ.ም ከምሽቱ 12:00 ሰዓት ጀምሮ በያሬድ የሙዚቃ ትምህርት ቤት፣ አሸናፊ ከበደ የኮንሰርት አዳራሽ ይካሄዳል።

  • የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ በፕሮስቴት ካንሰር ተይዘው ህክምና ማድረጋቸውን አስታወቁ የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ በፕሮስቴት ካንሰር ተይዘው እንደነበርና ለህመሙም አስፈላጊውን ህክምና ማድረጋቸውን ይፋ አድርገዋል። "ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ዛሬ በሰጡት መግለጫ፣ የፕሮስቴት ካንሰር እንዳለባቸው በምርመራ መረጋገጡንና ወዲያውኑ ወደ ህክምና መግባታቸውን ተናግረዋል። እንደ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገለጻ፣ ህመሙ በጊዜ በመገኘቱና አስፈላጊው የህክምና ክትትል በመደረጉ በአሁኑ ወቅት በጥሩ ጤንነት ላይ እንደሚገኙ ገልጸዋል። ኔታንያሁ ይህን መረጃ ያጋሩት ግልፅነትን ለመፍጠርና ስለ ጤንነታቸው የሚወጡ መረጃዎችን ለማጥራት እንደሆነ ተመልክቷል። የ75 ዓመቱ ጠቅላይ ሚኒስትር፣ ከህክምናው ጎን ለጎን መደበኛ የመንግስት ስራቸውን እያከናወኑ መሆኑንም መረጃዎች ያመለክታሉ። ይህ መረጃ እስራኤል በከፍተኛ ቀውስና ጦርነት ውስጥ ባለችበት ወቅት መውጣቱ በሀገሪቱ ፖለቲካ ላይ ትኩረትን ስቧል ሲል አል-አረቢያ ዘግቧል ።

  • 28 янв.4 0601

    ረቡዕ፣ ጥር 20፣ 2018 ዐበይት ዜናዎች 1፤ ኢትዮጵያ የሕጻናት የወንጀል ተጠያቂነት የእድሜ ገደብን ከ9 ዓመት ከፍ እንድታደርግ የተመድ የሕጻናት መብት ኮሚቴ ትናንት የኢትዮጵያን የሕጻናት መብት ይዞታ በገመገመበት ወቅት ጠየቀ። የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን፣ መንግሥት በጥናት በሚያገኘው ውጤት ላይ ተመስርቶ የእድሜ ገደቡን ለማሻሻል ዝግጁ መኾኑን በመድረኩ ላይ በሠጠው ምላሽ ገልጧል። አንድ የኮሚቴው ባለሙያ፣ ሕጻናት ጭምር ሰላማዊ ሰዎች በተሳተፉባቸውና ሕይወት በጠፋባቸው ሰላማዊ የተቃውሞ ሰልፎች ላይ "ያልተመጣጠነ ኃይል" በተጠቀሙ የጸጥታ አካላት ላይ ምርመራ ተደርጓል ወይ? በማለት ጠይቀው ነበር። ልዑካን ቡድኑ፣ በሰላማዊ ሰልፎች ላይ ኃይል መጠቀምን ለመከላከል ረቂቅ ሕግ መዘጋጀቱን ጠቅሶ፣ ባንድ ሰላማዊ ሰልፍ ላይ ተይዘው ታስረዋል የተባሉትን ልጃገረድ ሕጻናት ጉዳይ ግን አጣራለሁ ብሏል። ከሕጻናት የጾታ ጥቃት አንጻር፣ በብሄራዊ ደረጃ "የጾታ ጥቃት ፈጻሚዎች መዝገብ" በቅርቡ ተግባር ላይ እንደሚውል ልዑካኑ ገልጧል። መንግሥት ምን ያህል በጀት ለሕጻናት ተኮር ሥራዎች እንደመደበ ለቀረበው ጥያቄም፣ ከአጠቃላይ አገራዊ ምርቱ ሦስት በመቶው ተመድቧል ሲል ልዑካኑ ምላሽ ሠጥቷል። 2፤ ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ፣ ከአሜሪካ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ክሪስቶፈር ላንዳው እና ከአሜሪካ የአፍሪካ ወታደራዊ እዝ አዛዥ ጄነራል ዳግቪን አንደርሰን ጋር ዛሬ በጽሕፈት ቤታቸው ተወያዩ። ዐቢይ፣ ከሁለቱ የአሜሪካ ባለሥልጣናት ጋር "ቀጣይነት ያለው ትብብር" እና "መከባበርን" አጽንዖት የሠጠ "ደማቅ" እና "ገንቢ" ውይይት ማድረጋቸውን በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ገልጸዋል። የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ በበኩላቸው ከላንዳው ጋር ባደረጉት የተናጥል ውይይት፣ የኢትዮጵያ እና አሜሪካ የጋራ ፍላጎቶች በኾኑ ቀጣናዊና ዓለማቀፋዊ ጉዳዮች ዙሪያ መነጋገራቸውን ውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ባሠራጨው መረጃ አስታውቋል። 3፤ ኢትዮ ቴሌኮም እና ሳፋሪኮም ኩባንያ፣ ካልተጣራ ዓመታዊ ገቢያቸው 1 ነጥብ 5 በመቶውን የአገሪቱን የገጠርና ጠረፋማ አካባቢዎች የቴሌኮሙኒኬሽን እና የፖስታ አገልግሎት ተጠቃሚ ለሚያደርገው የሁሉን ዓቀፍ ተደራሽነት ፈንድ መዋጮ እንዲያወጡ ታዘዙ። የኢትዮጵያ ኮሙኒኬሽን ባለሥልጣን፣ ኢትዮ ቴሌኮምና ሳፋሪኮም ተመሳሳይ ክፍያ እንዲከፍሉ እንደሚደረግ መናገሩን ጠቅሶ የዘገበው ሪፖርተር ነው። ሳፋሪኮም ኩባንያ ባለፉት ሦስት ዓመታት ለሁሉን ዓቀፍ ተደራሽነት ፈንድ ምንም መዋጮ አለማዋጣቱንና ከዚህ በኋላ ግን ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር ተመሳሳይ መጠን ያለው መዋጮ እንዲያዋጣ ከውሳኔ ላይ መድረሱን ባለሥልጣኑ መግለጡን ዘገባው ጠቅሷል። ባለሥልጣኑ፣ በጉዳዩ ዙሪያ ከሁለቱ ኩባንያዎች ጋር ውይይት አድርጌያለሁ ማለቱንም የዜና ምንጩ አመልክቷል። 4፤ አብዱራህማን መሃዲ የሚመሩት የኦብነግ ክንፍ እና ሁለት የሶማሌ ክልል ተቃዋሚ ድርጅቶች በቅርቡ ያቋቋሙት ጥምረት፣ በክልሉ በአፍዴር፣ ሸበሌ እና ዳዋ ዞኖች የተከሠተው ድርቅ "ሰብዓዊ ቀውስ" አስከትሏል አለ። ሰብዓዊ ቀውሱ በአየር ንብረት ለውጥ ሳቢያ ብቻ የተከሠተ አይደለም ያለው ጥምረቱ፣ የመንግሥት "የዝግጁነት ማነስ"፣ "የሰብዓዊ እርዳታ ብክነት" እና "የዘላቂ እቅድ አለመኖር" ጭምር የሰብዓዊ ቀውሱ ምክንያት ናቸው ሲል የክልሉን መንግሥት ወቅሷል። የሰብዓዊ ቀውሱ ሰለባዎች "አስቸኳይ" ድጋፍ እንዲደረግላቸው ጥምረቱ የጠየቀ ሲኾን፣ የዕርዳታ አቅርቦቱም "በገለልተኛ" አካል ቁጥጥር ሊደረግበት ይገባል ብሏል። በሦስቱ ዞኖች ተከስቷል ላለው ሰብዓዊ ቀውስ በውጭ የሚኖሩ የክልሉ ተወላጅ ሶማሌዎች ዕርዳታ እንዲያሰባስቡ የጠየቀው ጥምረቱ፣ ኾኖም ዕርዳታው በመንግሥት በኩል ሳይኾን "በታማኝ" የረድኤት ድርጅቶችና "በማኅበረሰብ መዋቅሮች" በኩል ብቻ በቀጥታ ለተጎጂዎች እንዲደርስ ጥሪ አቅርቧል። 5፤ የኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት አሥተዳደር,፣ በዋትሳፕ፣ በቴሌግራም እና በሌሎች የመልዕክት መላላኪያ መተግበሪያዎች ላይ የሚፈጸሙ የባይነ መረብ ጥቃት በእጅጉ ተስፋፍቷል በማለት አስጠነቀቀ። የበይነ መረብ ጥቃት ፈጻሚዎቹ በአገሪቱ የሚካሄዱ የተለያዩ ሲምፖዚየሞችን፣ ዓለማቀፍ መድረኮችንና የበይነ መረብ ስብሰባዎችን ለሐሰተኛ ድርጊቶቻቸው መጠቀሚያ እያደረጓቸው እንደሚገኙ ተቋሙ ገልጧል። ተቋሙ፣ ጥቃት ፈጻሚዎች የግለሰቦችንና ተቋማትን የባንክ ሂሳቦች ለመመዝበር፣ የግለሰቦችን የግል መረጃዎች ለመመንተፍ እና የዲጂታል ደኅንነትን ለማናጋት "በተቀናጀ" መልኩ እየሠሩ ስለመኾኑም በክትትልና ምርመራ አረጋግጫለሁ ብሏል። የበይነ መረብ ጥቃቶቹ የሚፈጸሙት በሕዝቡ ዘንድ ከፍተኛ ትኩረት የሚሠጣቸውን "ተፈላጊ" እና "ወቅታዊ" ጉዳዮች መነሻ በማድረግ በተዘረጋ "ስልታዊ የማታለያ ዘዴ" ነው ያለው ተቋሙ፣ የዲጂታል መገናኛ ዘዴዎች ተጠቃሚዎች ከማይታወቁ ወይም ካልተረጋገጡ አድራሻዎች በዋትሳፕ፣ ቴሌግራምና በሌሎች የዲጂታል የመገናኛ ዘዴዎች የሚላኩላቸውን የድረገጽ መረጃዎች እንዳይከፍቱና አጠራጣሪ መልዕክቶች ሲደርሷቸው ወዲያውኑ "ሪፖርት" እንዲያደርጉም አሳስቧል።

  • ዐበይት ዜናዎች 1፤ ኢሕአፓን እና መኢአድን ጨምሮ ስምንት ተቃዋሚ ፓርቲዎች፣ መንግሥት በቀጣዩ አገር ዓቀፍ ምርጫና አካሄድ ዙሪያ ከተቃዋሚ ፓርቲዎች ጋር በሐቀኛ ድርድር ከመግባቢያ ስምምነት ላይ እንዲደርስ ጥሪ ዛሬ በጋራ ባወጡት መግለጫ ጠይቀዋል። ፓርቲዎቹ፣ "ግልጽነት በጎደለው" እና "በተድበሰበሰ" የእጩዎችና መራጮች የምዝገባ ሂደት "አሳታፊ"፣ "ሃቀኛ"፣ "ተዓማኒ" እና "ዲሞክራሲያዊ" ምርጫ ማካሃድ አይቻልም ብለዋል። ዕጩ ተወዳዳሪዎች ያለ ፓርቲያቸው ዕውቅና በስልካቸው ብቻ ራሳቸውን ከዕጩነት እንዲሠርዙ የሚያስችል አማራጭ መሠጠቱ፣ ገዢው ፓርቲና ካድሬዎቹ በሀብትና ጥቅማ ጥቅም ወይም በሥልጣን፣ በእሥራት በማስፈራራት እንዲያስለቅቋቸው የሚያመቻች ነው ያሉት ፓርቲዎቹ፣ ምርጫ ቦርድ ለጉዳዩ ባስቸኳይ ይህን አሠራር እንዲያርም ጠይቀዋል። እያንዳንዱ ተወዳዳሪ ዕጩ የኢሜይል አድራሻውን እንዲያስገባ ቦርዱ ያስቀመጠውን ግዴታም እንዲሠርዝ ጥያቄ አቅርበዋል። ፓርቲዎቹ፣ መንግሥት ከታጣቂ ኃይሎች ጋር ተኩስ የማቆም ስምምነት በማመቻቸት የዜጎችን የመምረጥ የመመረጥ መብት እንዲያስከብርም ጠይቀዋል። 2፤ ውጭ ጉዳይ ሚንስትር ጌዲዮን ጢሞቲዮስ፣ የዘጋቢነት ፍቃዳቸው በተሠረዘባቸው የዶይቼ ቬለ የኢትዮጵያ ሁለት ዘጋቢዎች ዕጣ ፈንታ ዙሪያ ጣልቃ መግባት አልችልም አሉ። ጌዲዎን፣ ጉዳዩ ተጠሪነቱ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የኾነውን የመገናኛ ብዙኀን ባለሥልጣን እንደሚመለከት በመግለጽ ጣልቃ መግባት እንደማይችሉ የተናገሩት፣ ትላንት ከጀርመን አቻቸው ዮሐን ቫደፉል ጋር አዲስ አበባ ውስጥ ጋዜጣዊ መግለጫ በሠጡበት ወቅት የዶይቸ ቬለ ጋዜጠኛ ላቀረበላቸው ጥያቄ በሠጡት መልስ መኾኑን ዶይቸ ቬለ ዘግቧል። ኾኖም ጌዲዮን፣ የመገናኛ ብዙኃን ይዞታን የሚከታተሉ ዓለማቀፍ ተቋማት እና የፕሬስ ነጻነት ተሟጋች ድርጅቶች እንደ ኢትዮጵያ ባለ አገር ውስጥ ያለውን "ስሱነት" እና "ሁኔታ" ከግምት ማስገባት አለባቸው በማለት መናገራቸውን ጣቢያው ጠቅሷል። ሁሉም የሚዲያ ተቋማትና ጋዜጠኞች በኢትዮጵያ ዙሪያ የሚሠሯቸው ዘገባዎች "ግጭት" እና "ሁከት" ሊያስነሱ እንደሚችሉ እንዲያጤኑት መንግሥታቸው እንደሚያበረታታም ጌዲዮን አሳስበዋል ተብሏል። የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኀን ባለሥልጣን፣ የጣቢያው የትግራይ እና አማራ ክልሎች ሁለት ዘጋቢዎች ፍቃዳቸውን በቋሚነት የተነጠቁት ባለፈው ወር ነበር። 3፤ አረና ትግራይ፣ ሳልሳይ ወያነን እና ባይቶናን ጨምሮ ስድስት የትግራይ ተቃዋሚ ፓርቲዎች፣ የሕወሃት ቡድን ከኤርትራ መንግሥት ኅብረት መፍጠሩን እንዲያቆም ትናንት ባወጡት የጋራ መግለጫ ጠየቁ። ፓርቲዎቹ፣ የኤርትራ መንግሥት ለትግራይ ሕዝብ እዳ እንጅ ፈጽሞ በረከት ሊያመጣ አይችልም በማለት በመግለጫቸው አጽንዖት ሠጥተዋል። ፓርቲዎቹ ሕወሃት ለጦር ጉዳተኞች እና ተፈናቃዮች እርዳታ የሚውል 6 ቢሊዮን ብር ከሕዝቡ አሰባስባለሁ በማለት እየተንቀሳቀሰ መሆኑን የገለጡ ሲኾን፣ ኾኖም ሕወሃት መዋጮውን ለተገቢው ዓላማ ያውለዋል ብለው እንደማያምኑ በመግለጽ ሕዝቡ በሕወሃት አሰባሳቢነት ገንዘብ እንዳያዋጣ ጥሪ አድርገዋል። ፓርቲዎቹ፣ በትግራይ ያለ ምንም ቅድመ ኹኔታ በሁሉም የፖለቲካ ኃይሎች መካከል ሁሉን ዓቀፍ ንግግር እንዲደረግም ጥሪ አድርገዋል። የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር በብርጋዴር ጀኔራል ጉዕሽ ገብረ እና ሌሎች የክልሉ ጸጥታ ኃይል የቀድሞ አዛዦች ላይ ሰሞኑን የወሰደውን የእስር እርምጃ በማውገዝም፣ በቁጥጥር ሥር የዋሉት ግለሰቦች ባስቸኳይ እንዲለቀቁ ፓርቲዎቹ ጠይቀዋል። 4፤ የጋምቤላ ከተማ አስተዳደር፣ ማንኛውንም የመንግስትም ሆነ የግል ሞተር ሳይክሎች ከዛሬ ጥር 15 ጀምሮ ላልተወሰነ ጊዜ ማሽከርከር በጥብቅ ከለከለ።  የከተማዋ አስተዳደር፣ በከተማው የሚገኙ ባጃጆች ከጥዋቱ 1 ሰዓት እስከ ምሽቱ 1 ሰዓት ብቻ አገልግሎት መስጠት እንዳለባቸውም ትዕዛዝ አስተላልፏል። ሆቴሎችና ግሮሰሪዎች ደሞ እስከ ምሽቱ 2 ሰዓት ድረስ ብቻ አግልግሎት እንዲሠጡ ታዘዋል። የከተማዋ አስተዳደር፣ የሰዓት ገደቡን በሚጥስ ማንኛውም ግለሰብ ላይ አስተዳደራዊ እርምጃ እንደሚወስድ አስጠንቅቋል። የከተማዋ አስተዳደር ይህን የሰዓት ገደብ የጣለበትን ምክንያት አላብራራም።