አቡ እክራም እብኑ አህመድ ቻናል Abu Ikram قناة أبي إكرام ابن أحمد
Статистикаየቴሌግራም ቻናል 👇👇👇 https://t.me/ibnahemad
- Последний пост
- 15 авг.
- Последнее чтение
- 15 авг.
- Постов за неделю
- 18
- Всего постов
- 33
- Тип
- открытый
- Язык
- und
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 112
- 1/48двое суток
- 128
- 1/72трое суток
- 138
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
видео или голосовое, без подписи
ምርጫው የእናንተ ነው የተመቻቹን ንኩት👇👇👇
🔑 ወቅታዊ የሆነ ምርጥ የጁምዓ ኹጥባ 🚫ርዕስ :- መውሊድ ቢድዓ ስለመሆኑ ና ለሚያነሷቸው ሹብኃወች መልሶች 🎙በሸይኽ ሙሀመድ ሀያት ሀራ ሀፊዘሁሏህ ቦታ : ሀራ - መስጂድ አልፉርቃን 🗓 ቀን : 8/12/18 ወይም ረቢዓል አወል 1 ✅✅✅ በጣም የሚገርሙ ና ወገብ ሰባሪ የሆኑ ጥያቄወች ለመውሊድ አክባሪወች ተዳሰውበታል ። ለሁሉም በማድረስ ያለብንን የማድረስ ሀላፍትና በቻልነው እንወጣ ። የሸይኻችን ቻናልን ለማገኘት 👇 https://t.me/SheikMohmmedHyatHara https://t.me/SheikMohmmedHyatHara
አላህ ሆይ ! ጠቃሚ የሆነ እውቀት መልካም የሆነ ሲሳይ ተቀባይነት ያለውን ስራ እለምንሀለን !!
https://t.me/Halaba_Ahles_suna/3650
видео или голосовое, без подписи
ልዩ የመውሊድ ስጦታ ለአስተዋዮች!! —————ክፍል 1 ለመውሊድ ስጦታ መሰጣጠት ባይፈቀድም! እንዲህ ያለው ስጦታ ግን ስለሚፈቀድ ይህ ልዩ የመውሊድ ስጦታይ ነው። {በትግስት አንብባችሁ ለሌሎችም #Share_ሼር በማድረግ አሰራጩት።} መውሊድ እንዲከበር የሚተጉ የጥመት ቡድኖችና የሙስሊሙ ጠላቶች "ለነቢዩ ﷺ ውዴታና ፍቅር ስላለን ነው ምናከበረው፣ የሚቃወሙን ሰዎች ደግሞ ለነቢዩ ﷺ ውዴታ ስለሌላቸው ነው" እያሉ ስለ ዲኑ በቂ እውቀት የሌለውን ሙስሊሙን ህብረተሰብ ያሞኛሉ። የትኛው የነቢዩ ﷺ ፍቅርና ውዴታ ነው ያላችሁ?! የነቢዩ ﷺ ፍቅርና ውዴታ መለኪያው ምንድነው?! እናንተ ለነቢዩ ﷺ ውዴታ መለኪያ ያደረጋችሁት መውሊድን ነው። መውሊድን ደግሞ ነቢዩ ﷺ አያውቁትም! አይወዱትም!!። ምክንያቱም በዲናችን የሌለ አዲስ መጤ ነገር ነው!፣ ነቢዩ ﷺ ደግሞ በየ ሳምንት ጁምዓ ኹጥባቸው "አደራ በዲን ላይ አዲስ መጤ ነገርን ተጠንቀቁ!፣ አዲስ መጤ ነገር ሁሉ ጥመት ነው" ይሉ ነበር። ስለዚህ መውሊድ መጤ ነገር ስለሆነ አይወዱትም ማለት ነው። ያውም በመውሊድ ቀን የሚባሉ ስንኞች የተለያዩ ድንበር ያለፉና ሺርክ የተሞላባቸው ናቸው። ታዲያ አንተ የነቢዩን ﷺ ትእዛዝ በመቃረን ነው እንዴ ውዴታቸውን ምትገልፀው?? እንደሚታወቀው ደግሞ የሚወዱትን ሰው ይታዘዙታል እንጂ አያምፁትም!!፣ ሚያስከፋውን ነገር ይጠነቀቁለታል እንጂ ሚያስከፋው ነገር ለመተግበር ፈፅሞ አይታሰብም!!። ምን ይህ ብቻ ከሚወደድ ነገር ሁሉ ኣቻ የሌለው ተወዳጁን አላህን እንኳን እንወዳለን ብለን ብንሞግት አላህ ነቢዩን ﷺ በትክክል እንድንከተል መስፈርት አድርጎብናል፣ እንዲህ በማለትም አዞናል:- ﴿قُل إِن كُنتُم تُحِبّونَ اللَّهَ فَاتَّبِعوني يُحبِبكُمُ اللَّهُ وَيَغفِر لَكُم ذُنوبَكُم وَاللَّهُ غَفورٌ رَحيمٌ﴾ آل عمران ٣١ “አላህን የምትወዱ እንደሆናችሁ #ተከተሉኝ (በላቸው)፣ አላህ ይወዳችኋልና። ኃጢያቶቻችሁንም ለናንተ ይምራልና። አላህ መሃሪ አዛኝ ነው።” ኣል ዒምራን 31 በትክክል አላህን እና ነቢዩን ﷺ የምንወድ ከሆነ በየትኛውም አቅጣጫ ከሚፈልጉት መንገድ ውጪ እየተጓዙ እወዳቸዋለሁ ማለት የማይታሰብ ነው!። ገጣሚው እንዲህ ይላል:- تعصى الإله وأنت تدعي حبه هذا محال في القياس بديع "አምላክህን ታምፃለህ፣ ነገር ግን እንደምትወደው ትሞግታለህ። ይህ ፈፅሞ የማይታሰብና አዲስ ፈጠራ የሆነ ልኬት (ቂያስ) ነው።" አንድ ሰው ፈጣሪውን እና ከፈጣሪው ዘንድ የተላከለትን ታላቁን መልእክተኛ ﷺ ቀርቶ፣ በጣም የሚወደውን ጓደኛውን እንኳን እየተቃረነውና ከርሱ ሀሳብ ተቃራኒ በሆነ መንገድ እየሄድ እወደዋለሁ አይልም። በተለይ ያ! ጓደኛው "እነዚህን ነገሮች አትዳፈርቢኝ" ብሎ በተለየ መልኩ ቀይ ያሰመረበት ነገር ካለና ያንን ነገር ያለ ፈቃዱ ሚነካካና ከርሱ ሀሳብ ተቃራኒ ሆኖ እየተጓዘ እወድሃለሁ ቢለው፣ ጓደኛው የሚረዳው እያፌዘበት መሆኑን እንጂ ፈፅሞ እንደሚወደው አይደለም!። ነቢዩ ﷺ ዒርባድ ኢብን ሳሪያ (ረዲየላሁ ዐንሁ) ባስተላለፈው ሀዲስ እንዲህ በማለት በዲን ላይ አዲስ ነገር ከመፍጠር (ከመጨመር) እንድንጠነቀቅ አሳስበውናል:- «وإيَّاكم ومُحْدَثاتِ الأُمورِ، فإنَّ كلَّ مُحْدَثةٍ بِدْعةٌ، وإنَّ كلَّ بِدْعةٍ ضَلالةٌ» “አደራችሁን (በዲን ላይ) አዳዲስ ነገሮችን (ከመጨመር) ተጠንቀቁ!! ሁሉም (በዲን ላይ አዲስ መጤ) ፈጠራ ነው፣ ፈጠራ ነገር ሁሉም ጥመት ነው።” [ኢማሙ አሕመድ በሙስነዳቸው የዘገቡት ሲሆን ሀዲሱም ሶሂህ ነው።] አላህን በትክክል የምትወድ ከሆነ አላህ ዲኑን ሙሉ አድርጌዋለሁ ብሏልና ስሜትህን በመከተል አዲስ ነገር ካልጨመርኩ ማለትህን ትተህ ሙሉ በሆነው ዲን ውስጥ ያለውን ነገር ተግብር። {اليَومَ أَكمَلتُ لَكُم دينَكُم} “የዛሬ ቀን ሀይማኖታችሁን ሙሉ አደረግኩላችሁ።” አልማኢዳ 3 አዎ! ዲኑ ሙሉ ነው!! አንተ ጎበዝ ከሆንክ ሙሉ በሆነው ዲን ውስጥ ያለውን የታዘዝከውንና ሱንና የሆነውን ብቻ ተግብር። ትክክለኛ ውዴታ የሚገኘውም የሚወዱትን አካል ትእዛዝ በማክበር ነውና!። በትክክል አላህን እና መልእክተኛውን ﷺ የምትወድ ከሆነ በዲኑ የሌለን አዲስ ነገር መፍጠር ትተህ ያዘዙህን ታዘዝ፣ ከከለከሉህ ነገር ሁሉ ተቆጠብ!። እስቲ ልጠይቅህ/ሽ? ① » መውሊድ ከዲኑ ከነበረ ለምን እንደ 2ቱ ዒዶች በቁርኣንና በሀዲስ እንዴት መከበር እንዳለበት በዝርዝር አልመጣም?? ② » በመልካም ነገር ሶሃቦችን ከማነሳሳታቸው በፊት ቀድመው ለራሳቸው የሚተገብሩት ታላቁ ነቢይ ﷺ መውሊድን አክብረውታልን?? ③ » አንተ ቢድዓ በሆነው መውሊድ ላይ እንደምትነቃቃው ለምን ሌሎች ግዴታ በሆኑ ዒባዳዎች ላይ አትነቃቃም (አትነሽጥም) ?? ④ » ነቢዩን ﷺ ኮቴ በኮቴ እየተከታተሉ የሸኑበት ቦታ ሳይቀራቸው፣ ሽንታቸውን በሸኑበት ቦታ የሚሸኑ የነበሩት ብርቅዬ ሶሃቦች መውሊድን አክብረውታል?? ⑤ » አንተ/አንቺ ለነቢዩ ﷺ ሱንና ከሶሃቦችና ከተከታዮቻቸው (ታቢዒዮች) የበለጠ ተቆርቋሪ ናችሁ?? ⑥ » በዲኑ ላይ አዲስ ነገር በቁርኣንም በትክክለኛ (ሶሂህ) ሀዲስም የሌለን ነገር ለመጨመር ከመናፈቅህ በፊት፣ ቁርኣን እና ሀዲስ ውስጥ ያለውን ጨርሰህ ተግብረሃል?? » ነቢዩ ﷺ ልብሳቸውን ያሳጥሩ ነበር አሳጥረሃል? » ነቢዩ ﷺ ፂማቸውን ያሳድጉ ነበር አሳድገሃል? » የነቢዩ ﷺ እጅ ባእድ የሆነችን ሴት ጨብጣ አታውቅም አንተ ሴት መጨበጥ ትተሃል? » ነቢዩ ﷺ የሌሊት ሶላትን እግራቸው እስኪሰነጣጠቅ ይሰግዱ ነበር፣ አንተስ እየሰግድከ ነው? እንደው የለይሉ ሶላት ቢቀር ዊትሯን ትሰግዳታለህ? ውትሯም ባትኖር እንዳው በጊዜ ተነስተህ የሱብሂ ሶላትን በጀመዓ ትሰግዳለህ? » ነቢዩ ﷺ የምርጥ ስነ-ምግባር ባለቤት ነበሩ፣ አንተስ ስነ-ምግባርህ ምንና ማንን ይመስላል? » እንደምትለው እውነት የነቢዩ ﷺ ውዴታ ካሰመጠህ የአውሮፓ ተጫዋቾችን እና ዘፋኞችን፣የፊልም አክተሮችን ባህሪ እርግፍ አድርገህ ትተህ የነቢዩን ﷺ ስነ-ምግባር ለምን አትከተልም?? ይህን ማድረግ ሳትችል ነቢዩ ﷺ ካዘዙበት መንገድ ውጪ፣ ነቢዩን ﷺ እወዳለሁ ማለትህ የለየልህ ተወዳዳሪ የሌለህ ነገ ከሞት በኋላ ተቀስቅሰህ አላህ ፊት እርቃንህ መቆምህን የዘነጋህ በስሜት ምትነዳ ግልብ ውሸታም ነህ!!! ይቀጥላል… ✍🏻ኢብን ሽፋ (t.me/ibnshifa) የተለያዩ ት/ቶችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችን ⤵️ #join ⤵️በማድረግ ይቀላቀሉ https://telegram.me/IbnShifa https://telegram.me/IbnShifa Follow Ibn Shifa's WhatsApp Channel: ⤵️⤵️ https://whatsapp.com/channel/0029VbAU7moHgZWXXXnNiL3f
видео или голосовое, без подписи
https://t.me/ibnahemad https://t.me/ibnahemad
🎁ስጦታ እውቀትን ለምትወዱ ሰዎች ከታች ያለችውን OPEN የምትሉዋን ነገር በመጫን የሰለፊዮችን ቻናል ይቀላቀሉ
ዳር ካልተከበረ መሀል ዳር ይሆናል!
🎧🎧🎧🎧 የቴሌግራም ቻናል 👇👇👇 https://t.me/ibnahemad https://t.me/ibnahemad
አላህ በተሻለ ለመተካት ነዉ የሚወስድብን!💦
🎧🎧🎧 የቴሌግራም ቻናል 👇👇👇 https://t.me/ibnahemad https://t.me/ibnahemad
👉 የሸይጧን መልእክተኛ አትሁን ! አንድ ሰው ወደ ጥበበኛ ሰው መጣና እገሌ የሚባለው ሰው ሰድቦሀል አለው ። ጥበበኛው ሰው ያልከው እውነት ከሆነ ወሬ አመላላሽ ነህ, ያልከው ነገር ውሸት ከሆነ ደግሞ አንተ ፋሲቅ ነህ, እሱ ቀስት ወረወረብኝ ግን አላገኘኘም, ለምንድነው ቀስቱን ተሸክመህ (መጥተህ) ልቤን የወጋኸው ? ለመሆኑ ሸይጣን ካንተ ሌላ መልእክተኛ አላገኘም እንዴ ? አለው ። http://t.me/bahruteka
🔖 አራት ነገሮች የሪዝቅ ምንጭ ናቸው። ①) ሌሊት መቆም ②) እስቲግፋር ማብዛት ③) በቀኑ መጀመሪያ እንዲሁም ④) በቀኑ መጨረሻ አላህን ማውሳት 📖 ابن القيم زاد المعاد ...
видео или голосовое, без подписи
መረጋጋትም ያስፈልገናል፤ ፈተናዎች ሁልጊዜ ቢከተሉንም የአላህ እርዳታ ፈጽሞ አይቋረጥም።" Share
❓ በእውነት እና በሱና ላይ የተመሰረተ ህይወት መኖር ይፈልጋሉ? • ትክክለኛው የሰለፎች (የቀደሙት ደግ ሰዎች) መንገድ ምንድን ነው? • ከተለያዩ ብዥታዎች (ሹብሃቶች) ራስዎን እንዴት መጠበቅ ይችላሉ? • ልብን የሚያረጉ እና እውቀትን የሚጨምሩ የዲን ትምህርቶችን የት ያገኛሉ? ለነዚህና ለሌሎች መሠረታዊ የዲን ጥያቄዎችዎ አስተማማኝ ምላሽ ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉ! 👉 አሁኑኑ ተቀላቀሉን፦ J O I N
✍ታሪክህ አልተፃፈም ማለት ታሪክ ዬለህም ማለት አይደለም