tgindex

ሶባሀል ኸይር 🗣🧠

Статистика

"ነፍስህን በሚጠቅማት ነገር ካላጨናነካት..አሷ በሚጎዳህ ነገር ታጨናንቅሃለች"

Последний пост
7 июн.
Последнее чтение
14 авг.
Постов за неделю
0
Всего постов
21
Тип
открытый
Язык
und
В каталоге с
14 авг.
Подписчики
145
0 за 1 дн.
Сутки
0
0,00%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
71
20 постов
Вовлечённость
49,0%
к подписчикам
Постов в день
0,0
всего 21
Упоминаний
0
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
1/48двое суток
1/72трое суток

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • 7 июн.38из Yetsfa_Gexoch1

    ዛሬህን ተጠቀምበት! «يَا ابْنَ آدَمَ، إِنَّمَا أَنْتَ أَيَّامٌ، فَإِذَا ذَهَبَ يَوْمٌ ذَهَبَ بَعْضُكَ.» "የአደም ልጅ ሆይ! አንተ እኮ የቀናት (የሰከንዶች) ስብስብ ነህ፤ አንዲት ቀን ባለፈች ቁጥር ካንተም አካል አንድ ክፍል አብሮ ይሞታል።" — ሱፍያ_አሰ'ሰውሪ (ረሒመሁላህ) በትናንትናው ቀን ላይ ምንም ዓይነት ሥልጣን የለህም—አልፏል፣ ታሪክ ሆኗል። በነገውም ቀን ላይ ምንም ዓይነት ዋስትና የለህም—ገና አልተወለደም። በእጅህ ላይ ያለችው፣ ልትገዛውና ልትቀይረው የምትችለው ብቸኛ እውነተኛ ሀብት «አሁን» ወይም «ዛሬ» ብቻ ነች። ለዚህ ነው ስኬታማ ሰዎች ስለ ጊዜ ያላቸው እይታ የተለየ የሆነው፦ "በጣም የሚያስደስተው የነገው ምስጢር ሳይሆን፣ ዛሬ በእጅህ ያለችውን ሰዓት በአግባቡ ተጠቅመህ ነገን የምትቀርጽበት ጥበብ ነው።" የትናንቱ ውድቀት፣ ያጋጠሙህ ፈተናዎችና የነበሩብህ ጫናዎች ዛሬህን እንዲያጨልሙት አትፍቀድላቸው። ነገ የተሻለ ነገር ይመጣል እያልክም በባዶ ተስፋ አትቀመጥ፤ ምክንያቱም ነገ የምትባለው ቀን የዛሬው ጥረትህ ውጤት ናት። "ትናንት የታሪክ ማስታወሻ ነው፣ ነገ ደግሞ ገና ያልተገለጠ ምስጢር ነው፤ ዛሬ ግን የተሰጠህ ታላቅ ስጦታ ነው—ለዚህም ነው 'አሁን' የሚባለው።" ነፍስህን ለማደስና ወደ ጌታህ ለመመለስ፦ ዛሬን ተጠቀምባት። ሕይወትህን ለመቀየርና ጠንካራ ለመሆን፦ አሁኑኑ ተነሳ። አዳዲስ ዕውቀቶችንና ጥበቦችን ለመጨበጥ፦ ሰዓቱ አሁን ነው። የጊዜን ዋጋ በሚገባ የተረዳ ሰው፣ እያንዳንዷን ሰከንድ በጥንካሬ፣ በፅናትና በበጎ ተግባር በመሙላት በሕይወቱ ላይ ታላቅ አሻራ ያኖራል። ዛሬ በእጅህ ናት፤ እንዳታመልጥህ! ✨ "ጊዜህን በአግባቡ ካልመራኸው፣ ጊዜህ አንተን መርቶ ወደማትፈልገው ቦታ ይወስድሃል።" 📎https://t.me/Yetsfa_Gexoch1 📎https://t.me/Yetsfa_Gexoch1 📎https://t.me/Yetsfa_Gexoch1

  • ረሱል (ሰ,አ,ወ) ሙስሊም በዘገቡት ሀዲስ እንዲህ ብለዋል የአላህን 99 ስሞች በቃሉ የሀፈዛቸው እና የተገበራቸው ጀነት ይገባል በለዋል። ቁርዓን እና ሀዲሶችን የተከታተለ ሁሉንም ማግኘት ይችላል። ስለዚህ የአላህን ሰም በቃላችን ሀፍዘን ጀነት ብንመኝ ምን ይመስላቹሀል? #አላህ _አምላክ አረህማን— በጣም አዛኝ #አረሂም— በጣም ሩህሩህ ♥ አል መሊክ— ንጉስ #አል_ቅዱስ— ከጉድለት የጠራ አሰላሙ— የሰላም ባለቤት #አል_ሙእሚኑ— ፀጥታን ደህንነትን ሰጭ አል ሙሀይሚኑ— በሰሮቹን ጠባቂ #አል_አዚዙ— አሸናፊ አል ጀባሩ— ሀያል ጠጋኝ ♥ #አል_ሙተከቢሩ— ኩሩ አል ኻሊቁ— ፈጣሪ #አል_ባሪኡ— ከምንም ያስገኘ ፈጣሪ አል ሙሶውሩ— ለሻው ነገር የሻውን ቅርፅ ሰጭ #አል_አወሉ— ፊት ያለ የመጀመሪያ አል አኺሩ— ኋላ ቀሪ የመጨረሻ #አል_ዟሂሩ— ግልፅ አል ባጢሉ— ስውር #አል_ሰሚኡ— ሰሚ አል በሲሩ — ተመልካች #አል_መውላ— ወዳጂ ረዳት ♥ አል ነሲሩ— ድል ሰጭ #አል_አፍው— ይቅር ባይ አል ቀዲሩ— በነገሮች ቻይ #አል_ለጢፍ — ሩህሩህ አል ኸቢሩ— ውስጥ አዋቂ #አል_ዊትሩ— ብቸኛ አል ጀሚሉ— መልካሙ ♥ #አል_ሐዪዩ— አክባሪ ትሁት አል ሲትሩ— ሸፍኝ #አል_ከቢሩ— ትልቅ አል ሙተ— አሊ የላቀ #አል_ወሂዱ— አንዱ አል ቀሀሩ— አሸናፊ #አል_ሀቁ— እውነቱ አል ሙቢኑ— ሁሉን ግልፅ አድራጊ♥ #አል_ቀውዩ— ሀይለ ብርቱ አል መቲኑ— እጂግ ብርቱ #አል_ሀዩ— ህያ አል ቀዩሙ— ራሱን ቻይ #አል_አሊዩ— የሁሉ የበላይ አል አዚሙ— ታላቅ #አል_ሽኩሩ— ውለታን መላሽ አል ሐሊሙ— ሲበዛ ታጋሽ♥ #አል_ዋሲኡ— ችሮታው ሰፊ አል አሊሙ— አዋቂ #አል_ተዋቡ — ንስሀን ተቀባይ አል ሀኪሙ— ጥበበኛ #አል_ገኒዩ— ሀብታሙ አል ከሪሙ — ቸሩ #አል_አሀዱ— ብቸኛ አል ሶመዱ— ሁሉን አስጠጊ #አል_ቀሪቡ— ቅርብ አል ሙጂቡ— ልመናን ጥሪን መላሽ ፣ተቀባይ #አል_ገፍሩ— መሀሪ አል ወዱዱ— ተወዳጂ ፣ወዳድ #አል_ወልዩ— ወዳጅ አል ሀሚዱ— ምስጉኑ #አል_ሐፊዙ— ተጠባባቂ አል መጂዱ— ለጋስ #አል_ፈታሁ— የሚከፍት ፣ድልን አጎናፃፊ አል ሸሂዱ— ተከታታይ #አል_ሙቀዲሙ— አስቀዳሚ ፣የሚያቀርብ አል ሙአኺሁ— አዘግይ ፣የሚያርቅ #አል_መሊኩ— ንጉስ አል ሙቅተድሩ— የችሎታ ያዥ ♥ #አል_ሙሰኢሩ — ወጋ ሰጭ አል ቃቢዱ— ሲሳይን ያዥ #አል_ባሲጡ— ሲሳይን የሚዘረጋ አል ራዚቂ— መጋቢ #አል_ቃሂሩ— አሸናፊ አል ደያኑ— አሸናፊ, #አል_ሻኪሩ— አመስጋኝ አል መናኑ— ለጋስ ፣ችሮታው ሰፊ ሰጭ♥ #አል_ቃዲሩ — ሁሉን ቻይ አል ኸላቁ— ፈጣሪ♥ #አል_ማሊኩ— ንጉስ አል ረዛቁ— ሲበዛ ለጋስ #አል_ወኪሉ— ተወካይ♥ አል ረቂቡ— ተጠባባቂ #አል_ሙህሲኑ— በጎን ወይ አል ሀሲቡ— ተሳሳቢ ፣ተቆጣጣሪ #አል_ሻፊ— ፈዋሽ አል ረፊቁ— አዛኝ #አል_ሙዕጢ— ሰጭ አል ጀወሰዱ— ቸር♥ #አል_ሱቡሁ— የጠራው አል ዋሪሱ— ወራሽ ብቻውን ቀሪ #አል_ረቡ— ጌታ ፣ተንከባካቢ አል አእላ— ከሁሉ በላይ♥ #አል_ኢላሁ— አምላክ

  • Channel photo removed

  • 8 февр.58из Abu_Mohammed_Seid

    https://t.me/Abu_Mohammed_Seid

  • 8 февр.53из Abu_Mohammed_Seid

    ቁርአን ዘመን የማይሽረው የማያረጅ የማይሰለች የማይከዳ ጓደኛ ነው።ቁርአን ስንቀማመጠው ከፍ የሚያደርግ ድንቅ የአላህ ቃል ነው።ቁርአን ሁሌ ማውራት ስለምንፈልገው ነገር ብቻ የሚያወራን ጓደኛ ነው፤ስለ አላህ …ስለ ጀነት እና እሷን ስለማግኛ ሰበቦች…ከጀሃነምም መዳኛ መንገዶችን… የአላህ ተወዳጅ ባሪያ ለመሆን ምክንያት ስለሚሆኑ ነገሮች… የሚያወራን እና የሚያስታውሰን……የውስጣችንን ህመም ፈዋሽ በሆኑ ቃላቶቹ የሚፈውሰን …የተሰበረው ልባችንን የሚጠግንልን ከሁሉም ፍጡራን የሚያብቃቃን የጌታችን ቃል ቁርአን… አስቸጋሪ እና አሳማሚ ጊዜያትን ቁርአን ባይኖር በምን እንሻገራቸው ነበር?መጠገኛ የታጣላቸውን ስብራቶች ቁርአን ባይኖር ምን ይጠግናቸው ነበር?አሳማሚ የሆኑ የብቸኝነት ጊዜያት ቁርአን ባይኖር እንዴት ያልፉ ነበር? በቁርአን ማጽናናት ያለፉ ሃዘኖች በርካታ ናቸው፤ በቁርአን የተጠገኑ ስብራቶች አይቆጠሩም፤ በቁርአን ጓደኝነት ቀለል ብለው ያለፉ የብቸኝነት ጊዜያት የማይባሉ የብቸኝነት ጊዜያት ብዙ ናቸው። ቁርአን…… ቁርአንን የሚገልጹ ቃላት ግን ከየት ይገኛሉ!!!!??የቁርአን ውለታዎችን የሚገልጹ ቃላትስ ከየት ይመጣሉ!!!? اللهم لك الحمد على نعمة القرآن اللهم لا تأخذنا من قلة شكرنا يارب ያረብ ከቃልህ መቼም አትለየን ትክክለኛ የቁርአን ሰዎችም አድርገንhttps://t.me/Abu_Mohammed_Seid

  • ሕይወት አስተማረችኝ …………… 7- በርታ፤ ጠንክር ዱንያ ላይ ከመሥራትና ከመበርታት ዉጭ አማራጭ የለህም፡፡ የሚያበረታታህ ብታጣ እንኳን ራስህን አበርታ፡፡ ለራስህ ነዳጅ ሁን፣ ራስህን ግፋ፣ ራስህን ሸልም፣ ለራሰህ ተናገር፡፡ ሌላዉን እንደምትመክረው ሁሉ ራስህንም ምከር - ጎበዝ! በርታ! በል ራስህን፡፡ የሆነ ነገር ጀምረህ ሰዎች አይሳካልህም ቢሉህ ያ የራሣቸው፣ የግላቸው አስተያየታቸው መሆኑን አስብ፡፡ እነርሱ የራሣቸው አስተያየት እንዳላቸው ሁሉ አንተም የራስህ አቋም ሊኖርህ ይገባል፡፡ ያ አቋም የነርሱ ተቃራኒ መሆን አለበት፡፡ ንግግራቸዉን መስማት የለብህም፡፡ መስሚያህን ጥጥ አርገው፡፡ ንግግራቸዉን ሰማህ ማለት ምኞታቸዉን አሳካህ፣ ፍላጎታቸዉን አሟላህ፣ ግምታቸዉን አፀናህ፣ ለስንፍና እጅ ሠጠህ … ማለት ነው፡፡ ስለዚህ የራስህን ሀሳብ አንግስ እንጂ የነርሱን ሀሳብ አታሳካላቸው፡፡ አስተያየታቸዉን ወደ ሕይወትህ አታምጣ፤ በራስህ ላይ አትተግብር፤ ራስህን አታወናብድ፣ ራስህን አትረብሽ፡፡ ማንም የራሱንና የመሰለዉን አስተያየት መስጠት ይችላልና ተዋቸው፡፡  ራስህ ካላመንክበት በስተቀር በሰዎች አስተያየት መንገድህን አታቋርጥ፡፡ ከሀሳባቸው ከፍ በል፤ ከፍ ብለህም ብረር፡፡ መብረሪያ ክንፍህን እንዲቆርጡ፣ ወደታች እንዲጎትቱህ ዕድል አትስጣቸው፡፡ ሀሳባቸዉን ካላነሳህ፣ ንግግራቸዉን ካልሰማህ፣ አስተያየታቸዉን ካላዳመጥክ ይሳካልሃል፡፡ ማንም ቢናገርህ፣ ቢያሸማቅቅህና ቢስቅብህ እጅ አትስጥ፡፡ ይሰካልኛል በላቸዉን ያለድካም ተጓዝ፡፡ ትክክለኛው መስመር ላይ እያለህ ተው አይሳካልህም ቢሉህ “አልተዉም፤ ያ የናንተ አስተያየት እንጂ የኔ አቋም አይደለም” በላቸው፡፡

  • إِنَّ رَبَّهُم بِهِمْ يَوْمَئِذٍۢ لَّخَبِيرٌۢ ጌታቸው በዚያ ቀን በእነርሱ (ነገር) በእርግጥ ውስጠ አዋቂ ነው፡፡

  • በዚህ በሶሻል ሚዲያ ዘመን፣ ትልቁ በሽታችን "FOMO" (Fear Of Missing Out) ወይም የሆነ ነገር ያመለጠን የመሰለን ስሜት ነው። የሰዎችን ስኬት፣ ፎቶና ቪዲዮ ስናይ "እኔ ምን አለኝ?" ብለን ራሳችንን ዝቅ እናደርጋለን። ነገር ግን አላህ (ሱ.ወ) ለነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) እና ለእኛ የሰጠን ስጦታ ከዱንያ ሀብት ሁሉ እንደሚበልጥ እንዲህ ሲል ያረጋግጥልናል፦ ​وَلَقَدْ آتَيْنَاكَ سَبْعًا مِّنَ الْمَثَانِي وَالْقُرْآنَ الْعَظِيمَ "ሰባቱን ተደጋጋሚ አንቀጾች (ፋቲሓን) እና ታላቁንም ቁርኣን በእርግጥ ሰጠንህ።" (ሱረቱል ሒጅር፡ 87) ​በቀን ውስጥ ስልካችንን በመቶዎች ለሚቆጠሩ ጊዜያት "Refresh" እናደርጋለን። አእምሮአችን በወሬ፣ በጭንቀትና በከንቱ ምስሎች ይሞላል። አላህ ግን በቀን 17 ጊዜ (በግዴታ ሶላቶች) ሱረቱል ፋቲሓን እንድንደግም አዘዘን። ይህ ማለት በቀን 17 ጊዜ ለነፍስህ "System Update" እያደረግክ ነው ማለት ነው። ፋቲሓን ስታነብ ከዱንያ ጫጫታ ወጥተህ ወደ "Source" (ወደ ፈጣሪህ) ትመለሳለህ። ​የዚህን አንቀጽ ታሪክ ስናይ፣ አላህ ቀጥሎ ባለው አንቀጽ (ቁጥር 88) ላይ "በእነዚያ ካፊሮች ለተሰጣቸው ጸጋ አይንህን አትጣል" ይላል። meaning፦ "ቁርኣን እያለህ ሌላው ሰው ባለው ቁሳቁስ አትቅና!" ነው። ዛሬ በቲክቶክና በኢንስታግራም የምታያቸው "Perfect" ህይወቶች የውሸት ሽፋን ሊሆኑ ይችላሉ። አንተ ግን በእጅህ ላይ "ታላቁ ቁርኣን" (አል-ቁርኣነል ዓዚም) አለህ። የዓለማቱ ጌታ ያናገረው ሰው እንዴት ራሱን "ምንም የሌለው" አድርጎ ያስባል? ​በአሁኑ ጊዜ ወጣቱ ለዲፕሬሽንና ለብቸኝነት ተጋላጭ ነው። ፋቲሓን ስትቀራ " إِيَّاكَ نَعْبُدُ وَإِيَّاكَ نَسْتَعِينُ " (አንተን ብቻ እንገዛለን፣ አንተንም ብቻ እርዳታ እንለምናለን) ስትል፣ የህይወትህን ሸክም በሙሉ ወደ አላህ ትወረውራለህ። ያኔ "ብቻዬን አይደለሁም" የሚል ትልቅ የውስጥ እርጋታ ይሰማሃል ማለት ነው። 🍂 ከ ቁርአን አያህ...

  • እውነተኛ ብልህ (ምጡቅ ችሎታ ያለው ሰው) ልዩ መሆኑን አያውቅም፣ ልዩ እንደሆነም አይሰማውም።ይህ ነው የእውነተኛ ምጡቅ መመዘኛው። ልዩ እንደሆነ ከተሰማው እሱ እውነተኛ ችሎታ ያለው ብልህ አይደለም። ልዩ የመሆን ስሜት የሚመነጨው ከበታችነት ስሜት ነው። የበለጠ የበታችነት ስሜት በተሰማችሁ ቁጥር የበለጠ ልዩ ሰው ሆናችሁ ለመቅረብ ትሞክራላችሁ።

  • ከሰዎች ጋር ስትግባባ የራስህን ስብዕና እየፈጠርክ ነው። በዚህ ግንዛቤያቸው መሰረት ካንተ ጋር እንዴት መሆን እንዳለባቸውና አንተን ማክበር ወይም አለማክበር እንዳለባቸው ይወስናሉ፡፡ አንድ ዛፍ ስሮቹ በደንብ ጠለቅ ያሉ ከሆኑ ንፋስ አይገነድሰውም፡፡ ንፋሱ የቱንም ያህል ቢጠነክር፡፡ የአንድ ሰዓት ትዕግስት ድልን ያጎናፅፋል፡፡ አስተዋይ እየሆንክ በሄድክ ቁጥር ድክመትህ እየቀነሰ ይሄዳል፡፡ ብቃትህ እየጨመረ በሄደ ቁጥር ቁጣህ እየቀነሰ ይሄዳል። ምንም እንደማያንቀሳቅሰው ባህር፣ ነፋስ በጭራሽ እንደማያንቀጠቅጠው ተራራ ሁን፡፡ 📙ህይወትህን ተደሰትባት

  • ምን ነካን ወንድሜ...... የትላንቱ ቁስል ሳይደርቅ ሳይሽር፣ የትላንቱ ጠባሳ ሳይጠፋ ሳይቀር። ብዙ ጣርክ፣ ደከምክ፣ ለፋህ ትላንት፣ ጊዜ፥ገንዘብ  ሳይቀርህ እንዲሁም ጉልበት። የፈሰሰው እንባ የተሰበረው ጥርስ፣ የታሰርክለትን የተከሰስከው ክስ። የነበረው ሹራ እስከ እኩለሊት፣ እስኪባል ድረስ ነጋ ወይ ለሊት። ያ ወኔ ያ ህብረት አረ ምን ወሰደው፣ ያ ክብር ያ ሀፍረት አረ ምን ሰለበው። ብለን ለመስጂድ ቁልፍ ነፍጥ እዳላነሳን፣ ከመስጅድ አንወጣም ብለን ካልቀራን። ምት ተገኘ ብለን እንዲህ እንሸሻለን? ባጢልን ሳናከስም እጅ እንሰጣለን? ይህ ሁላ ታሪክ ተረሳ እንደዋዛ፣ ቃላችን ታጠፈ ምቾቱ ሲበዛ። እስኪ ልጠይቅህ ጆሮህን አውሰኝ፣ መስማት ብቻ ሳይሆን ከልብህ አድምጠኝ። ምንያህል ሳትቀራ አሳለፍክ ግዜያት፣ ሳምንት ወይስ ወራት አለፍ ሲል አመት። ምን አወኩ ብለህ ነው ምትሆነው እንዲህ፣ ና ቅራ ስትባል ስንፈት እሚይዝህ። ጊዜ እንጂ ያጣሁት አለኝ ፍላጎት፣ መቅራት እየፈለኩ አጣሁኝ ሰዓት። ብለህ ልትለኝ መፍጠንህ አይቀርም፣ እንደውነቱ ግን ጊዜ አተህ አይደለም። ስንፍና ነው እንጂ እጅጉኑ የጎላ፣ እድሜያችን ወደ ፊት እኛ ወደ ኋላ። ጌዜ እኮ እኩል ነው ለሁሉም ፍጡር፣ አንተ አትለይም ከአደም ሰው ዘር። አሁን ያላወቅከውን መቼ ልታውቅነው፣ አሁን ግዜ የሌለህ መቼ ሊኖርህ ነው። እድሜ እንደሆነ ዝምብሎ ቁጥር ነው፣ ቆሞ አይጠብቅም ሁሌ ወደ ፊት ነው። በል ከእንግዲ ይብቃ መሳነፍ ስንፈት፣ ተነስ ጊዜው ሳይረፍድ ቶሎ ለእውቀት። ሁላችን እንንቃ ይብቃ ማንቀላፋት፣ ሰለፍያን ይዘን እንሂድ ወደፊት። እዝነት አንድነትን በመሀል እጠብቅ፣ የሸይጣን ተንኮሉ ብዙ ነው ረቂቅ። አሁን ምን አይታችሁ ገና ይባል'ላሉ፣ ያልነውም አልቀረ ይጨራረሳሉ። ተብሎ መሰየሙ እጅጉን ያመናል፣ የሱናውን ዳዕዋ በብዙ ያስጠቁራል። መሆኑ ያመናል የጠላት መሳቂያ፣ ያሸማቅቀናል መሆን መሳለቂያ። ይህ እድል አይገኝም ይችላል ሊያመልጥ፣   የሃገሬው ፖለቲካ አይያዝ አይጨበጥ። ታሪክ አመሉ ነው መድገም እራሱን፣ አስቀምጠን እንለፍ  አሻራችንን!!! አስቀምጠን እንለፍ አሻራችንን!!! ጁምዐ/ጥር/15/ 2018 ✍2Morrow

  • ⭐​ሰባቱ የስኬት ዓይነቶች⭐ 🎯​የፋይናንስ (የገንዘብ) ስኬት፦ ዘላቂ በሆነ መንገድ የገንዘብ መረጋጋትንና ብልጽግናን ማረጋገጥ። 🎯​የሥነ-ልቦና ስኬት፦ በውስጣዊ ሰላም እና በስሜታዊ መረጋጋት መደሰት። 🎯​የጤና ስኬት፦ የአካል ብቃትንና አጠቃላይ ጤናን መጠበቅ። 🎯​ከአላህ ጋር ባለ ግንኙነት ስኬታማ መሆን፦ እምነትን ማጠናከርና በአምልኮ ተግባራት ላይ መጽናት። 🎯​የማህበራዊ እና የቤተሰብ ግንኙነት ስኬት፦ ከቤተሰብ እና ከማህበረሰቡ ጋር ጠንካራና ተስማሚ ግንኙነት መገንባት። 🎯​የዕውቀት ስኬት፦ አእምሮን ማበልጸግ እና ቀጣይነት ያለው ዕውቀትን መቅሰም። 🎯​የግብ ስኬት፦ የግል እና የሙያ ግቦችን በዕቅድና በትጋት ማሳካት።

  • በህይወታችን በተደጋጋሚ ከምንፈፅማቸው ፀያፍ ስህተቶች ውስጥ አንዱ የሌሎችን ሚስጥር መዝራት ነው። የሚገርመው የራሳችን ሚስጥር ያመንነው ሰው ለሌላ ቢያወጣብን የማንወድ ሆነን ሳለ ለሌሎች አለመታመናችን ነው። አስገዳጅ ሁኔታ ካልገጠመ በስተቀር የሌላን ሰው ሚስጥር ለባልም ይሁን ለሚስት፣ ለቅርብም ይሁን ለሩቅ ማውጣት አይገባም። የጓደኛውን ሚስጥር እንደ ዋዛ ለሚስቱ ይነግራል። ሚስቱ ለቅርብ ጓደኛዋ፣ ያቺ ደግሞ ለሌላ ቅርብ ጓደኛዋ ወይም ለባሏ፣ ... እያለ ያደባባይ ሚስጥር ይሆናል። የቤቷን መከፋት ለጓደኛዋ ትነግራለች። ወ/ሮ ጓደኛ ለባሏ፣ እሱ ለጓደኛው፣ ... እያለ መጨረሻ መቆራረጥ፣ መቀያየም ያስከትላል። ከዚህ አይነት ጥፋት የሚተርፈው ከስንት አንድ ነው። ከመሰል ጥፋቶች ላይ ላለመውደቅ ይህንን የነብዩን (ﷺ) ሐዲሥ ማስታወስና መተግበር ተገቢ ነው፦ لا يُؤْمِنُ أحَدُكُمْ، حتّى يُحِبَّ لأخِيهِ ما يُحِبُّ لِنَفْسِهِ {አንዳችሁ ለራሱ የሚወደውን ለወንድሙ እስከሚወድ ድረስ አያምንም።} [ቡኻሪ] ሚስጥርህ እንዲጠበቅ ትውዳለህ ኣ? እንግዲያውስ የሌሎችን ሚስጥር ጠብቅ። ለራስህ የምትጠላውንም በወንድምህ ላይ አትፈፅም። ሚስጥርህ ወጥቶ ማግኘት እንደማትፈልግ ነጋሪ አያሻም። ልክ እንዲሁ ወንድምህም ሚስጥሩን ስትዘራበት ድንገት ቢደርስ ምን እንደሚሰማው አሰብ። ያመንከው እንዲከዳህ እንደማትፈልገው አንተም ላመነህ ታመን። የስነ ምግባር፣ የሞራል ቁንጮ የሆኑት ውዱ ነብይ (ﷺ) እንዲህ ይላሉ፦ أدِّ الأمانةَ إلى منِ ائتمنَكَ، ولا تخُنْ من خانَكَ "አምኖ ለሰጠህ አማናውን አድርስ። የካደህን አትካድ።" [አሶሒሐህ፡ 423]

  • 18 янв.531из tmc_21

    видео или голосовое, без подписи

  • ልብህን አስመልስ" (Reclaim Your Heart) የተሰኘው መጽሐፍ ልብን በዱንያዊና ጊዜያዊ ነገሮች (እንደ ሰው፣ ገንዘብ፣ ዝና) ከመጠመድና በእነሱም ላይ ጥገኛ ከመሆን ነፃ ማውጣት። እውነተኛ ሰላምና ደስታ የሚገኘው ብቸኛው ቋሚ በሆነው አምላክ ላይ በመመካትና ልብን ለአላህ ብቻ በማስገዛት :: በሕይወት የሚገጥሙ ስብራቶችና መከራዎች ወደ አላህ መመለሻ መንገዶች እንጂ የሕይወት ማብቂያ እንዳልሆኑ :: የሚያስገነዝብ መፅሐፍ ነው

  • እኛ የት ነበርን??   ሁለት ጓደኛሞች አብረው ከተማ ውስጥ እየዞሩ ናቸው እና አንደኛው ወደ ትላልቅ ህንፃዎች ተመለከተና ለጓደኛው እንዲህ ብሎ ጠየቀው ይህንን ሁሉ ሀብት ሲታደል እኛ የት ነበርን?" አለው   ጓደኛውም "ና" ብሎ እጁን ይዞ ወደ ሆስፒታል አስገባውና   ይህንን ሁሉ በሽታ ሲታደል እኛ የት ነበርን?" ብሎ ጠየቀው። 👌የተሰጠን ብናውቅ የተከለከልነው የለ

  • 🔖በዚህ ወቅት፡ 👉ዝምታን ያበዛ፡ 👉ብቸኝነትን የመረጠ፡ 👉ባለው የተብቃቃ፡ 👉ቤቱና መስጂድን ያዘወተረ፡ 👉አሉባልታና ወሬዎችን እርግፍ አድርጎ የተወ ሰው፡ ጥሩና የተረጋጋ ህይወት ይኖራል ብዬ አስባለሁ።

  • ተፈጥሮዬ ሆኖ ሰውን ማስቀየም አልችልም።እሺታ ባህሪዬ ነው። ያደግኩት በይሉኝታ ነውና 'አይመቸኝም' ወይም 'አይሆንም' ማለት ለኔ ከባድ ፈተና ነው። ሆኖም ይህ ለሌሎች የሚመች ባህሪዬ፣ ለኔ ብዙ ዋጋ አስከፍሎኛል።  ያደግኩበት ቤት ለሰው መኖርን አስተምሮኛልና 'እምቢ' የሚለው ቃል ከአንደበቴ አይወጣም። ይህ መልካም ሰብእና ቢሆንም፣ ልኩን ሲያልቅ ግን እራስን ያስረሳል። ለሌሎች ስትል ራስህን የምትጥልበት፣ የማይመችህን ተቀብለህ የምትሰቃይበት ከሆነ መልካምነቱ ለነሱ እንጂ ለራስህ አይደለም። ስለዚህ አንዳንዴ... ድንበር ይኑራችሁ። መልካምነታችሁ ራሳችሁን እስኪጎዳ ድረስ አይሁን። ሰዎችን ሳታስቀይሙ፣ ነገር ግን ራሳችሁን ሳትጎዱ በጨዋነት 'አይሆንም' 'አይመቸኝም' (No) ማለትን ተለማመዱ። እምቢታ መብት ነው!

  • በርካታ የዱንያን ፈተናዎች እና ደስ የማይሉ የሚረብሹ ስሜቶችን በየቀኑ እንታገላለን። በዚህ ሁሉ መሀል ደህና መስለን ለመታየት የምናደርገው ጥረትም ሌላው ከባድ ትግል ነው። አልሃምዱሊላህ አላ ኩሊሃል!! ረበና...ከበሽታ፣ ከጭንቀት፣ ከሀሳብ፣ ከሀዘን፣ ከትካሴ፣ ከወንጀል፣ ከማይጠቅም እውቀት፣ ተቀባይነት ከሌለው ዱዓ እና ተስፋ ከመቁረጥ አላህ ይጠብቀን!

ሶባሀል ኸይር 🗣🧠 — tgindex