tgindex
✝️ቅዱሳንን እንወቅ✝️

✝️ቅዱሳንን እንወቅ✝️

Статистика

በዚህ ቻናል በእየእለቱ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የሚገኙ የመላዕክት፣የፃድቃን፣የሰማዕታት፣የቅዱሳን ገድል ታሪክ ይነገርበታል፡፡ለሁሉም ተዋህዶ ልጆች እንዲደርስ ሸር አድርጉላቸው፡፡ከኢ/ኦ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ላይ የተገኙ የእለቱ የቅዱሳን(የጻድቃን) አባቶቻችን እና የቅዱሳን(የጻድቃን) እናቶቻችን ጽድቅ እና ገድላት ይነገርበታል።በመሀልም ጠቃሚና አስተማሪ ነው የምንላቸውን ታሪኮች

Последний пост
14 авг.
Последнее чтение
15 авг.
Постов за неделю
12
Всего постов
45
Тип
открытый
Язык
ti
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
370
0 за 2 дн.
Сутки
0
0,00%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
24
40 постов
Вовлечённость
6,5%
к подписчикам
Постов в день
1,7
всего 45
Упоминаний
0
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
11
1/48двое суток
12
1/72трое суток
13

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • ❤ ውድ የቴሌግራሜ ቻናል ተከታታዮች ተወዳጅ ቤተቦቼ እንዴት ሰነበታችሁ ቸር አላችሁ ኔትወርክ ወደ ማይሠራቦት ቦታ ወጣ ስላልኩ #ከነሐሴ_8_እስከ_ነሐሴ_12 ያለው ቀድሜ Post አድጌዋለሁ ወደኋላ እያላችሁ የየቀኑን temeliketu

  • ❤ ሲጠቃቀሱበትም በአየ ጊዜ ሰይጣናት መሆናቸውን አውቆ በላያቸው በመስቀል ምልክት በአማተበ ጊዜ ተበተኑ። በሚመለስም ጊዜ በወዲያም በወዲህም መንገድ አጣ የክብር ባለቤት ወደ ሆነ ጌታችን ጸለየ ከዚህም በኋላ ከአንዱ ገዳም ወደ አንዱ ገዳም የሚዘዋወሩ ከአባ ሲኖዳ ገዳም የሆኑ መነኰሳት ተገለጡለት እነርሱም የዳዊት መዝሙር ያገቡ ነበር ስለ ሥራው ጠየቁቱ በእርሱ ላይ የደረሰውን ሁሉ በነገራቸው ጊዜ ከእነርሳቸው ጋር ወስደውት በፀሐይ የበሰለ ዓሣ እየተመገበ ከእርሳቸው ጋር አንዲት ዓመት ሙሉ ኖረ። ❤ ያመነኰሰው መምህሩ አባ ይስሐቅም ወሬውን በአጣ ጊዜ ፊቱን ያሳየው ዘንድ ወደ እግዚአብሔር ጸለየ። አባ ጋልዮንም በመንፈስ ቅዱስ አውቆ ወደ ርሱ መጣ አባ ይስሐቅም በአየው ጊዜ በእርሱ ደስ አለው "ወዴት ነበርክ" አለው እርሱም ከመጀመርያ እስከ መጨረሻ ነገረው። ❤ ከዚህም በኋላ የሚያርፍበት ጊዜ ደርሶ ነሐሴ 13 ቀን በሰላም ዐረፈ። መነኰሳቱም በክብር ቀበሩት። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በአባ ጋልዮስ ጸሎት ይማረን ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ የነሐሴ 13 ስንክሳር።                             ✝ ✝ ✝ ❤ "#ጸርሐ_አብ_ኪያከ_በውዳሴ። ወበርእስከ ጸለለ መንፈስ ቅዳሴ። አመ ገበርከ በታቦር እግዚኦ ምስለ ሐዋርያት ክናሴ። ኤልያስ መንገለ ቆመ ወኀበ ሀለወ ሙሴ። ዘመለኮትከ ወልደ ከሠትከ ሥላሴ"። #ሊቁ_አርከ_ሥሉስ (አርኬ) #የነሐሴ_13።                             ✝ ✝ ✝ ❤ #የዕለቱ_የማኅሌት_ምስባክ፦ ደብር ርጉዕ ወደብር ጥሉል። ለምንት ይትነሥኡ አድባር ርጉአን። ደብር ዘሠምሮ እግዚአብሔር የኀድር ውስቴቱ። መዝ 67፥15-16። የሚነበበው ወንጌል ማቴ 17፥1-14።

  • ✝ ✝ ✝ ❤ በዚችም ቀን #ቈስጠንጢኖስ ወደ ሮሜ ከተማ ገባ በሮሜ አገሮች ሁሉ ላይ ነገሠ። ዜናውንም መጋቢት ሃያ ስምንት ቀን ላይ ጽፈናል። ለእግዚአብሔር ክብር ምስጋና ይሁን ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የነሐሴ 12 ስንክሳር።                            ✝ ✝ ✝ ❤ "#ሰላም_ለከ_መልአከ_ኪዳኑ_ወምክሩ። ለእግዚአብሔር ልዑል ዘግሩም ግብሩ። በረድኤትከ ረዋጺ ዘአሠረ ነፋስ አሠሩ። ሶበ ላዕሌየ እኩየ መከሩ። ጉባኤ ፀርየ #ሚካኤል ዝሩ"። #ሊቁ_አርከ_ሥሉስ (አርኬ) #የነሐሴ_12።                            ✝ ✝ ✝ ❤ #የዕለቱ_ማኅሌቱ_ምስባክ፦ "በቅድመ መላእክቲከ እዜምር ለከ። ወእሰግድ ውስተ ጽርሐ መቅደስከ። ወእገኒ ለስመከ። መዝ137፥1-2። የሚነበበው ወንጌል ማቴ 25፥31-ፍ.ም።                       ✝️ ✝️ ✝️ ❤ #የዕለቱ_የማኅሌት_ምስባክ፦ "እግዚኦ ኵነኔከ ሀቦ ለንጉሥ። ወጽድቀከኒ ለወልደ ንጉሥ። ከመ ይኰንኖሙ ለሕዝብከ በጽድቅ"። መዝ 71፥1-2። የሚነበቡት መልዕክታት 1ኛ ቆሮ 9፥17-ፍ.ም፣ ይሁ 1፥8-14፣ የሐዋ ሥራ 24፥1-22። የሚነበበው ወንጌል ማቴ 22፥1-15። የሚቀደሰው ቅዳሴ የእመቤታች የማርያም ቅዳሴ ነው። መልካም የጾም ጊዜና                             ❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤             ❤ #ነሐሴ ፲፫ (13) ቀን። ❤ እንኳን #ለጌታችን_ለአምላችን_ለመድኃኒታች #ለኢየሱስ_ለክርስቶስ_ከዘጠኙ_ዐበይት በዐል ለአንዱ ለሆነው #በደብረ_ታቦር_ተራራ ላይ ለቅዱስሙሴ ለቅዱስ ኤልያስ ለሐዋርያት ለቅዱስ ጴጥሮስ ለቅዱስ ያዕቆብና ለለቅድስጨዮሐንስ ብርሃነ መለኮቱ ለገለጠበት በዐልና እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና ቀጤና አደረሰን። በተጨማሪ በዚህ ቀን ከሚታሰቡ፦ #ከሊቀ_ነቢያት_ከቅዱስ_ሙሴ ከልደቱ፣ #ከብንያምም ከመታሰቢያው፣ ከተጋዳይ #ከአባ_ጋልዮን ከዕረፍቱና በሰማዕትነት ከዐረፈች #ከቅድስት_ኦፍራ እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።                                                         ✝ ✝ ✝ ❤ በዚች ቀን ክብር ይግባውና #የጌታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ_ታላቅና_ክቡር_በዓል ነው። በዚች ቀን መድኃኒታችን ሦስቱን ደቀ መዛሙርቶቹን #ቅዱሳን_ጴጥሮስ_ያዕቆብንና_ዮሐንስን_ይዞ_ወደ_ታቦር_ተራራ ላይ አወጣቸው። መልኩም በፊታቸው ተለወጠ ልብሱም እንደ በረዶ ነጭ ሆነ። ❤ ስለ እነርሱም ጌታችን "የሰው ልጅ በጌትነቱ ሲመጣ እስከሚያዩት ድረስ በዚህ ከቆሙት መካከል ሞትን የማይቀምሱት አሉ" አለ። ሰዎች ሁሉ እርሱ ለሙሴ ጌታውና ከሞት ያስነሣው እንደሆነ ለኤልያስም ፈጣሪው እንደሆነና ካሳረገበትም ያወረደው እርሱ እንደሆነ ያውቁ ዘንድ እነሆ ከጌታ ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋራ እየተነጋገሩ ሙሴና ኤልያስ ወደርሱ መጡ። ❤ ስለዚህም ጴጥሮስ ጌታችንን እንዲህ አለው "አቤቱ በዚህ ትኖር ዘንድ ትወዳለህን ሦስት ሰቀላዎችንም አንድ ለአንተ አንድ ለሙሴ አንድ ለኤልያስ እንሠራ ዘንድ"። በዚህም ቃል የደካማነትና የትሕትና ምልክት አለበት። ❤ ደካማነት የተባለ ጴጥሮስ ጌታችን ከሰማይ የወረደበትን ሥራ ትቶ በተራራ ላይ ይኖር ዘንድና እራሱን የሚሰውርበት ቤት ይሠራለት ዘንድ የተጋገረው ነገር ነው። ትሕትና ያልነውም ጴጥሮስ ለራሱና ለባልጀሮቹ ሐዋርያት ቤት ይሠራ ዘንድ ስለ አላሰበ ነው። እራሱንና ባልጀሮቹን ሐዋርያት እንደ ባሮች ነቢያትን ደግሞ እንደ ጌቶች አድርጎ አስቧልና። ስለ ሐዋርያትም የእውቀት ማነስ አታድንቅ በዚያ ጊዜ ፍፁማን አልሆኑምና። ❤ እንዲህም በሚልበት ጊዜ ጌታችን በሰው እጅ የተሠራ ማደሪያን የማይሻ መሆኑን ለጴጥሮስ ያሳየው ዘንድ አነሆ ደመና ጋረዳቸው። የጌታችንን ጌትነነቱ የሚገልጽ በሐዋርያትም ልቡና እምነትን የሚያጸና እንዲህ የሚል ቃል ከደመና ውስጥ መጣ። "ይህ የምወደው በእርሱ ደስ የሚለኝ ልጄ ይህ ነው እርሱንም ስሙት"። ❤ ሙሴና ኤልያስም ከእነርሱ ጋር ሲነጋገሩ ተሰሙ ስለ ርሱ መምጣት የተናገሩትን ትንቢታቸውንም በቸርነቱ አረጋገጠ። ወደ ተራራ ላይ በመውጣቱም ነቢያትና ሐዋርያት ደስ አላቸው። ❤ ሁለተኛም የአብን ቃል በሰሙ ጊዜ ከእነርሱ ሥውር የነበረ የወልድ ዋሕድን በእውነት ሰው መሆን በዚያ ጊዜ ተረዱ ያን ጊዜ የጌትነቱ ክብር ተገልጦአልና። ሐዋርያትም ፍጹም አምላክ ፍጹም ሰው የሆነ እርሱ ሙሴን ከመቃብር ያስነሳው ኤልያስንም ያሳረገው አውርዶም ያወጣው እርሱ እንደሆነ አወቁ። ከእርሱ በቀር ማንም ማን የሙሴን መቃብር የሚያውቅ የለምና ከዐሳረገው ከእርሱ በቀር ማንም ማን ኤልያስ ያለበትን የሚያውቅ የለምና። በሰማይና በምድር ስልጣን ካለው ከሁሉ ጌታ በቀር ሙታንን አድኖ ያስነሳቸው ማንም አይችልም። ❤ ደብረ ታቦርም የቤተ ክርስቲያን አምሳል ሆነች ከብሉይ እና ከሐዲስ በውስጧ ሰብስባለችና። ❤ የአብንም ቃል በሰሙ ጊዜ በግንባራቸው ፍግም ብለው በምድር ላይ ወደቁ እንደሙታን ሆኑ ከዓለም አስቀድሞ ከእርሱ ጋራ በህልውና እንዳለ ለልጁ አብ ምስክርን ሆነ ወዲያውኑ ሙሴ ወደ መቃብሩ ኤልያስ ወደ ቦታው ተመለሱ። ❤ ሐዋርያትን በአነቃቸው ጊዜ ከብቻው ጌታችን በቀር ማንንም አላገኙም። ከባሕርያችን የደዋሐደና ሥጋችንን የለበሰ ፍጹም አምላክ እንደሆነ በዚህ ሐዋርያት አስተማሩ። ❤ እንግዲህ እናስተውል ሰው ካልሆ ቅዱስ ገብርኤል እመቤታችንን ድንግል ማርያም በአበሠራት ጊዜ "እግዚአብሔር ከአንቺ ጋራ ነው" እንዴት አላት። አምላክ ካልሆነስ "ለመግሥቱ ፍጻሜ የለውም" እንዴት አላት። ሰው ካልሆ በበረት እንዴት አስተኙት አምላክስ ካልሆነ መላእክት ከሰማይ ወርደው "ለእግዚአብሔር በሰማያት ምስጋና በምድርም ሰላም ለሰውም ግዕዛኑ ሊሰጠው" እያሉ እንዴት አመሰገኑ። ❤ ሰው ካልሆነ ዮሐንስ በውሃ እንዴት አጠመቀው አምላክስ ካልሆ አልዓዛር ከመቃብር እንዴት ሊያስነሳው ቻለ። ❤ ይህ ተቀዳሚ ተከታይ የሌለው አንድ ልጅ አካላዊ ቃል እግዚአብሔር እርሱ ያለ መለወጥ ያለመለየት አንድ አካል አንድ ባሕሪ በመሆን ፍጹም አምላክ ፍጹም ሰው እንደሆነ እናምንበታለን። እርሱም ከአብ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ሁልጊዜ አንድ ህላዌ ነው ዛሬ ዘወትርም ለዘላለሙ አሜን።                              ✝ ✝ ✝ ❤ #ተጋዳይ_አባ_ጋልዮስ፦ ይህም በቀንና በሌሊት ጸሎት የማይታክት ተጋዳይ ሆነ ጎልማሳ ሆኖ ሳለ ከመነኰሰም ጀምሮ እስከ ሸመገለ ድረስ ከበአቱ ቅጽር ውጪ አልወጣም ከማህበር ጸሎት ጊዜ በቀር ከመነኰሳቱ ማንም አያየውም። ❤ ሰይጣናትም ተጋድሎውን በአዩ ጊዜ መነኰሳትን ተመስለው ወደ እርሱ በመንፈቀ ሌሊት ገብተው እንዲህ አሉት "እኛ ተሰውረን የምንኖር ገዳማውያን ነን ከእኛ አንዱ በሞት ስለተለየ ከእኛ ጋር ልንወስድህ ወደን ወደ አንተ መጣን" ለእርሱም ቃላቸው እውነት መስሎት ልብስና ሲሳይ ወደ ማይገኝበት ጠፍ ወደ ሆነ ተራራ ላይ እስከ አደረሱት ድረስ አብሯቸው ሔደ።

  • ❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤ ❤ እንኳን #ለጾመ_ፍልሰታ_ሁለተኛ_ሳምንት ለዕለተ እሑድ እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን።                           ✝️ ✝️ ✝️ ❤ #የዚህ_ሳምንት_መዝሙር፦ በ፪ ሃሌ ሉያ "ዛቲ ይእቲ #ማርያም_ማኅደረ_መለኮት እንተ ተሰምየት ሰንበተ ክርስቲያን #በከመ_ይቤ_ዳዊት በመዝሙር አንሣእኩ አዕይንትየ መንገለ አድባር አድባረ ድኁኃን ተሰማየት #ዛቲ_ይእቲ_ቅድስት_ድንግል ተዓቢ እምኵሉ ፍጥረት ኢያውዐያ እሳት መለኮት"። ትርጉም፦ ሰንበተ ክርስቲያን የተሰኘችው #የመለኮት_ማደሪያ_ይህቺ_ማርያም_ናት። #ዳዊት_በመዝሙር ዐይኖቼን ወደ ተራራ አነሣሁ (አቀናሁ) ብሎ እንደተናገረው ያቺ ተራራ የተራሮች ራስ ይህቺ #ቅድስት_ድንግል_ማርያም_ናት፤ እርሷም ከፍጥረት ሁሉ ትበልጣለች የመለኮት እሳት አላቃጠላትም። #ሊቁ_ቅዱስ ያሬድ_በድጓው_ላይ።                            ✝️ ✝️ ✝️ ❤ #የዚህ_ሳምንት_የዕለቱ_ምስባክ፦ "እስመ ኃረያ እግዚአብሔር ለጽዮን። ወአብደራ ከመ ትኩኖ ማኅደሮ። ዛቲ ይእቲ ምዕራፍየ ለዓለም"። መዝ 131፥13-14 ወይም 120፥1-2። የሚነበቡት መልዕክታት ዕብ 11፥8-19፣ 2ኛ ዮሐ 1፥1-8፣ የሐዋ ሥራ 27፥31-38። የሚነበበው ወንጌል ሉቃ 1፥39፥47። የሚቀደሰው ቅዳሴ የእመቤታችን የማርያም ቅዳሴ ነው። መልካም የፆም ጊዜና በዓል ለሁላችን ይሁንልን።                 @Teamihokidusan ❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤          ❤ #ነሐሴ ፲፩ (11) ቀን። ❤ እንኳን #ለአውሲም_አገር_ኤጲስቆጶስ #ለአባ_ሞይስስ_ለዕረፍትና ከላይኛው ግብጽ ከመኑፍ ከተማ ለሆነ #ለቅዱስ_አብጥልማዎስ ሰማዕትነት ለተቀበለበት ለዕረፍቱ በዐል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ በሰማዕትነት ከአረፉ በአንጾኪያ ከተማ የሠራዊት አለቃ #ከነበረው_ከቅዱስ_ፋሲለደስ በሰማዕትነት ከዐረፉ ማኅበሮች #ከሦስት_መቶ ሰማዕታት እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።                            ✝ ✝ ✝ ❤ #የአውሲም_አገር_ኤጲስቆጶስ_አባ_ሞይስስ፦ ይህም ቅዱስ ከታናሽነቱ ጀምሮ ንጹሕ ድንግልም ነበረ የቤተ ክርስቲያን መጻሕፍትንም ሁሉ ተምሮ ዲቁና ተሾመ። ከዚህም በኋላ ወጥቶ ወደ አስቄጥስ ገዳም ገባ። በአንድ ጻድቅ ሰው ዘንድም መነኰሰ በዚያም እያገለገለ በጠባብዋ መንገድም ተጠምዶ ያለመብልና መጠጥ ያለእንቅልፍም እየተጋደለ ዐሥራ ስምንት ዓመት ኖረ። ❤ ከብዙ ፍቅርና ትሕትና ጋር ዘወትር በጾምና በጸሎት ይተጋ ነበር። ትሩፋቱም በበዛ ጊዜ ከአባ ገሞስ በኋላ በአውሲም ከተማ ኤጲስቆጶስ ይሆን ዘንድ እግዚአብሔር መረጠው። ይህም አባ ሞይስስ በተሾመ ጊዜ ትሩፋት መሥራትን አብዝቶ ጨመረ ስለ እነርሱም በጸሎት እየተጋ መንጋዎቹን ነጣቂዎች ከሆኑ ከዲያብሎስ ተኲላዎች ጠበቀ። ❤ በሕይወቱም ዘመን ሁሉ ከዚህ ከኃላፊው ዓለም ገንዘብ የሚሰበስብ አልነበረም። አባ ሚካኤልም በእስክንድርያ ከተማ ሊቀ ጵጵስና በተሾመ ጊዜና ደሙ ሳይፈስ ሰማዕት በሆነ ጊዜ ይህ አባ ሞይስስ በእሥር ቤት ከእርሱ ጋር ነበር ብዙ ስለገረፉት እግሮቹንም ለረጅም ጊዜ በእግር ብረት አሥረው ስለ አሠቃዩት ብዙ መከራ ደረሰበት። ❤ በዚህ አባት ሞይስስ እጅም እግዚአብሔር ብዙዎች ድንቆችንና ተአምራቶችን አደረገ የሚያውቁትም በተአምራቶቹ ደግነቱንና ትሩፋቱን ተረዱ። ዳግመኛም ሀብተ ትንቢት የተሰጠው ከመሆኑም በፊት ብዙ ነገርን ተናገረ እንደተናገረውም ይሆን ነበር። የምስር ኤጲስቆጶስ ስለሆነው ስለ አባ ቴዎድሮስ ከሔደበት እንደማይመለስ ትንቢት ተናግሮበት እንዲሁ ተፈጸመበት። ❤ ዳግመኛም ሀብተ ፈውስ ተሰጥቶት ነበር። ብዙዎች ሕሙማንንም ፈወሳቸው። ገድሉንም በመልካም ሽምግልና ፈጸመ። እግዘአብሔርንም አገልግሎ ጥቂት ታመመ የሚያርፍበትንም ጊዜ አውቆ ሕዝቡን ጠራቸውና ባረካቸው በቀናች ሃይማኖትም ጸንተው እንዲኖሩ አዘዛቸው። ከዚህም በኋላ ነሐሴ 11 ቀን ዐረፈ። አለቀሱ ለትም ለኤጲስቆጶሳትም እንደሚገባ በዝማሬና በማኀሌት በታላቅ ክብር ገንዘው ቀበሩት ከሥጋውም ታላላቅ ተአምራቶች ተገለጡ ለሕሙማንም የሚሆን ፈውስ ተገለጠ። ለእግዚአብሔር ምስጋነ ይሁን እኛንም በቅዱስ አባት በአባ ሞይስስ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።                             ✝ ✝ ✝ ❤ #ሰማዕቱ_ቅዱስ_አብጥልማዎስ፦ ይህም ቅዱስ ከላይኛው ግብጽ ከመኑፍ ከተማ ነው። ቅዱሱንም ክርስቲያን እንደሆነ በመኰንኑ ዘንድ ነገር ሠሩበት። መኰንኑም በአስቀረበው ጊዜ በፊቱ ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ታመነ ጽኑዕ የሆነ ሥቃይንም አሠቃይቶ ራሱን በሰይፍ አስቆረጠው የሰማዕትነት አክሊልንም በመንግሥተ ሰማያት ተቀበለ። ❤ ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በሰማዕቱ ቅዱስ አብጥልማዎስ ጸሎት ይማረን ለዘላለሙ አሜን።                             ✝ ✝ ✝ ❤ "#ሰላም_ዕብል_ለሞይስስ_ፍጹም። ኤጲስቆጶስ ዘብሔረ አውሲም። ለጸሎት ዘተግሀ ወተጋደለ በጾም። አመ ርሥእናሁ በንስቲት ሕማም። እምፃማ ዓለም አዕረፈ ዮም"። #ሊቁ_አርከ_ሥሉስ(አርኬ) #የነሐሴ_11።                             ✝ ✝ ✝ ❤ #የዕለቱ_ምስባክ፦ "ህየንተ አበውኪ ተወልዱ ለኪ ደቂቅ። ወትሠይም(ሚ)ዮሙ መላእክተ በኵሉ ምድር። ወይዘክሩ ስመኪ በኵሉ ትውልደ ትውልድ"። መዝ 44፥16-17። የሚነበቡት መልክታት 1ኛ ቆሮ 5፥11-ፍ.ም፣ 1ኛ ዮሐ 2፥14-20 እና የሐ ሥራ 12፥18-ፍ.ም የሚነበበው ወንጌል ሉቃ 6፥20-24። የሚቀደሰው ቅዳሴ የእመቤታች የማርያም ቅዳሴ ነው። መልካም የጾም ጊዜና በዓል ለሁላችንም ይሁንልን።                ❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤           ❤ #ነሐሴ ፲፪ (12) ቀን። ❤ እንኳን #ለሊቀ_መላእክት_ለቅዱስ_ሚካኤል ወደ #ንግሥት_ቅድስት_ዕሌኒ ልጅ ወደ ንጉሥ #ቅዱስ_ቈስጠንጢኖስ ለተላከበት ለእርሱም ጠላቶቹን አሸንፋቸው መንግሥቱም እስከ ጸናች ድረስ ኃይልን ለሰጠበት ለወራዊ መታሰቢያ በዓሉ በሰላምና በጤና አደረሰን። በዚች ቀን በተጨማሪ ከሚታሰበው፦ ከንጉሥ #ቅዱስ_ቈስጠንጢኖስ_ወደ_ሮሜ ከተማ ከገባበትና በሮሜ አገሮችም ሁሉ ላይ ከነገሠበት እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።                                                  ✝ ✝ ✝ ❤ በዚች ቀን #የመላእክት_አለቃ የከበረ #የቅዱስ_ሚካኤል የበዓሉ መታሰቢያ ነው። በዚች ቀን እግዚአብሔር ወደ እሌኒ ልጅ ወደ ንጉሥ ቈስጠንጢኖስ ልኮታልና ለእርሱም ጠላቶቹን እስካሸነፍቸው መንግሥቱን እስከ ጸናች ድረስ ኃይልን ሰጠው የጣዖታትንም ቤት አፍርሶ አብያተ ክርስቲያናትን ሠራ። በጌጥም ሁሉ አስጌጣቸው። ❤ ስለዚህም አባቶቻችን የቤተ ክርስቲያን መምህራን የከበረ የመላእክት አለቃ የቅዱስ ሚካኤልን የበዓሉን መታሰቢያ በየወሩ በዐሥራ ሁለተኛው ቀን እንድናደርግ አዘዙን። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በመልአኩ በቅዱስ ሚካኤል አማላጅነት ይማረን ለዘላለሙ አሜን።

  • ✝ ✝ ✝ ❤ "#ሰላም_ለቢካቦስ_ዘኮኖሙ_ተበያጼ። ለተስዓቱ ወኃምስቱ ሰማዕታተ ክርስቶስ እንበለ ግጋፄ። ጣዖታተ ይዝልፍ ወንጉሠ ዐማፄ። ለዝ ጥቡዕ ኢመጽኦ ድንጋፄ። እስከ መተሩ ሥጋሁ በማሕፄ"። #ሊቁ_አርከ_ሥሉስ_አርኬ_የነሐሴ_10።                            ✝ ✝ ✝ ❤ #የዕለቱ_የማኅሌት_ምስባክ፦ "በማኅበር ባርክዎ ለእግዚአብሔር። ወለአምላክነ በአንቅዕተ እስራኤል። ህየ ብንያም ወሬዛ በኃይሉ"። መዝ 67፥26-27። የሚነበበው ወንጌል ማር 11፥23-27።                          ✝️ ✝️ ✝️ ❤ #የዕለቱ_ቅዳሴ_ምስባክ፦ "ተዘከር ማኅበረከ ዘአቅደምከ ፈጢረ፡፡ ወአድኀንከ በትረ ርስትከ። ደብረ ጽዮን ዘኀደርከ ውስቴታ"። መዝ 73፥2-3። የሚነበቡት መልዕክታት ዕብ 12፥22-ፍ.ም፣ 1ኛ ጴጥ 1፥7-13 እና የሐዋ ሥራ 4፥31-ፍ.ም። የሚነበበው ወንጌል ሉቃ 16፥9-19። የሚቀደሰው ቅዳሴ የእመቤታች የማርያም ቅዳሴ ነው፡፡ መልካም የጾም ጊዜና በዓል ❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤           ❤ #ነሐሴ ፲ (10) ቀን። ❤ እንኳን #ለኢትዮጵያዊ_ጻድቅ ለአባታችን #ለአቡነ_ለዓቢየ_እግዚእ ተከዜ ወንዝ እንደ ባሕረ ኤርትራን ከፍለው ለተሻገሩበትና ከዘጠኝ መቶ አርባ በላይ አሕዛብን ላሳመኑበት ዓመታዊ ለተአምር በዓል በሰላም አደረሰን።                             ✝ ✝ ✝ ❤ #አቡነ_ዓቢየ_እግዚእ_ያደረጉት_ተአምር_ይህ ነው፦ አንድ ጊዜ ደቀ መዛሙርትን አስከትለው ለስብከት ሲንቀሳቀሱ ተከዜ ወንዝ አካባቢ ደረሱ። ቀኑ ነሐሴ ዐሥር ነውና ተከዜ እስከ ገደፉ ሞልቶ ለሦስት ቀናት ባለመጉደሉ ከአንድ ሺ በላይ ሰዎች ሲያለቅሱ ደረሱ። ጻድቁ በአካባቢው የነበሩት ኢ-አማንያን (አሕዛብ) ቢሆኑም ራርተዋልና "አምላከ ሙሴ" ብለው ጸልየው ወደ ጥልቁ ውስጥ ገቡ። ❤ ቅዱስ ሚካኤል አብሯቸው ነበርና ተከዜ ግራና ቀኝ ተከፍሎ መሃሉ የብስ ሆነ። ይሕን ድንቅ ያዩ ከዘጠኝ መቶ አርባ በላይ አሕዛብም አምነው በጻድቁ እጅ ተጠምቀዋል። ይሕም ዘወትር ነሐሴ ዐሥር ቀን በቤተ ክርስቲያናቸው (ጐንደር) ይከበራል። ከአባታች አቡነ ዓቢየ እግዚእ እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን። ምንጭ፦ ከዲያቆን ዮርዳዮስ አበበ።

  • ❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤          ❤ #ነሐሴ ፲ (10) ቀን። ❤ እንኳ #ለማኅበረ_በኵር_መታሰቢያ_በዓል፣ በእስክድርያ ሊቀ ጳጳሳት #በቅዱስ_ድሜጥሮስ ዘመንና በከሀዲው ንጉሥ በዳኬዎስ ዘመነ መግሥት ሰማዕትነት ለተቀበለ #ለቅዱስ_መጥራ ለዕረፍት በዓል፣ በከሀዲ መክስምያኖስ እጅ ሰማዕት ለሆነ #ለቅዱስ_ሐርስጥፎሮስ ለዕረፍት በዓል፣ እስሙናይን ከሚባል አገር ለሆኑ ለከበሩ #ለቅዱሳን_ከቢካቦስና_ዮሐንስ ሰማዕትነት ለተቀበሉበት ለዕረፍታቸው በዓል በሰላም አደረሰን፡፡ በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ #ቅዱስ_ሐርስጥፎሮስ_ጋር_ሰማዕትነት_ከተቀበሉ_ከሠላሳ_ሺህ_ማኅበርተኞቹ_ሰማዕታት፣ ከቅዱሳን #ከቢካቦስና_ዮሐንስ_ከእነርሱ_ጋር_ሰማዕትነት ከተቀበሉ #ከዘጠና_አምስት_ሰዎች እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።                         ✝️ ✝️ ✝️ ❤ በዚህችም ቀን #የማኅበረ_በኲር_በዓልን እንዲከበር የቤተ ክርስቲያን መምህራን ሥርዓት ሠሩ እነዚህም #ከአቤል_ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ እንዲሁም እስከ ምጽአት #ስለጽድቅ_ደማቸውን_ስለሚያፈሱ እና ደስተኞች ስለ ሆኑት #አዕላፍ_መላእክትም_ሁሉ። እግዚአብሔር በጸሎታቸው ይማረን በረከታቸው ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘለዓለሙ አሜን።                                                      ✝ ✝ ✝ ❤ #ሰማዕቱ_ቅዱስ_መጥራ፦ ይህም ቅዱስ የክብር ባለቤት ክርስቶስን ክደው ለጣዖት መስገድን የሚያዝ የንጉሡን ደብዳቤ በሰማ ጊዜ ይህ ቅዱስ ወዲያውኑ ሒዶ ከወርቅ የተሠራ የአጵሎንን ክንድ ሰረቀ በየጥቂቱም ሰባብሮና ቆራርጦ ለድኆችና ለችግረኞች ሰጣቸው። ❤ የጣዖቱም አገልጋዮች ክንዱ ተቆርጦ አጵሎንን በአገኙት ጊዜ ስለርሱ ብዙዎችን ሰዎች ያዟቸው። በዚያንም ጊዜ ወደ መኰንኑ ቀርቦ ክርስቲያን እንደሆነ በፊቱ ታመነ ሁለተኛም "የአጵሎንን የወርቅ ክንድ የወሰድኩ እኔ ነኝ ለድኆችና ለችግረኞችም ሰጠኋቸው" አለው። መኰንኑም በሰማ ጊዜ እጅግ ተቆጣ አስጨናቂ የሆነ ታላቅ ሥቃይንም አሠቃየው ከዚህም በኋላ ከእሳት ውስጥ ጨመሩት እግዚአብሔርም አዳነው ያለ ጥፋትም በጤና አወጣው። ❤ ከዚህም በኋላ እጆቹንና እግሮቹን ቆረጡ ብዙ ደም ከአፍንጫው ወደ ምድር እስከ ሚወርድ ዘቅዝቀው በዕንጨት ላይ ሰቀሉት። በዚያንም ጊዜ የእግዚአብሔር መልአክ ወርዶ ቅዱስ መጥራንን ፈታው ከተሰቀለበትም አውርዶ በመዳሠሥ አዳነው። አንድ ዕውር ሰውም መጣ ከአፍንጫው ከወረደውም ደም ወስዶ ዐይኖቹን ቀባ ወዲያውኑ አየ። መኰንኑም ከማሠቃየቱ የተነሣ በሰለቸ ጊዜ ራሱን በሰይፍ ይቆርጡ ዘንድ አዘዘ። የምስክርነት አክሊልንም በመንግሥተ ሰማያት ተቀዳጀ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በሰማዕቱ ቅዱስ መጥራ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።                             ✝ ✝ ✝ ❤ #ሰማዕቱ_ቅዱስ_ሐርስጥፎሮስ፦ ይህም ቅዱስ በንጉሥ መክስምያኖስ ፊት በአቆሙት ጊዜ "ለአማልክት ሠዋ" አለው። የከበረ ሐርስጥፎሮስም እንዲህ ብሎ መለሰለት "እኔ እግዚአብሔር ኢየሱስ ክርስቶስን አመልከዋለሁ ለእርሱም እሠዋለሁ"። ንጉሡም ተቆጥቶ ሥጋው ተቆራርጦ በምድር ላይ እስቲወድቅ በበትር ይደበድቡት ዘንድ አዘዘ እንዲሁም አደረጉበት። ❤ ከዚህም በኋላ ወደ ወህኒ ቤት ጣሉት በላህያቸውም እንዲአስቱት ሁለት ሴቶችን ንጉሡ ወደርሱ ላከ ቅዱሱ ግን የክርስቶስን ሃይማኖት አስተማራቸው የዛሬ የሆነ የዚህንም ዓለም ኃላፊነት አስገነዘባቸው ወደ መክስምያኖስም በተመለሱ ጊዜ "እንዴት አደረጋችሁ" አላቸው። እነርሱም እንዲህ አሉት "በከበረ ሐርስጥፎሮስ አምላክ የክብር ባለቤት በሆነ በክርስቶስ እኛ እናምናለን" ንጉሡም ሰምቶ አንዲቱን በዕንጨት ላይ ሰቅለው እንዲአቃጥሏት ሁለተኛዋን በአንገቷ ደንጊያ አንጠልጥለው ቊልቊል እንዲሰቅሏት አዘዘና ምስክርነታቸውን እንዲህ ፈጸሙ። ❤ ከዚህም በኋላ ዕንጨቶችን ሰብስበው በማንደጃው ውስጥ አድርገው አነደዱ የከበረ ሐርስጥፎሮስን እጅና እግሩ እንደ ታሠረ ከውስጡ ጨመሩት ያን ጊዜም "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ" አለ እሳቱ ከቶ ምንም አልነካውም። ሕዝቡም ይህን አይተው የክብር ባለቤት በሆነ በጌታችን ኢየሱስ ዐሥር ሺህ ያህል ሰዎች አምነው በሰማዕትነት ሞቱ። ❤ ሁለተኛም የብረት ሠሌዳዎችን በእሳት አግለው አመጡ ቅዱሱንም በላያቸው በአስተኙት ጊዜ ምንም ምን የነካው የለም። ይህንንም ድንቅ ሥራ አይተው በክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሃያ ሺህ አንድ መቶ ሰዎችና አርባ ሕፃናት አምነው ምስክር ሁነው ሞቱ። ❤ ንጉሥ መክስምያኖስም አይቶ እጅግ ተቆጣ የቅዱስ ሐርስጥፎሮስንም ራስ በሰይፍ ይቆርጡ ዘንድ አዘዘ።ከንጉሡም ዘንድ በወጣ ጊዜ ጸሎትን አደረገ ፊቱንም በመስቀል ምልክት አማተበ ከዚህም በኋላ ምስክርነቱን ፈጸመ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱስ ሐርስጥፎሮስ ጸሎት ይማረን ለዘላለሙ አሜን።                              ✝ ✝ ✝ ❤ #ቅዱሳን_ሰማዕታት_ቢካቦስና_ዮሐንስ፦ ይህም ቅዱስ ቢካቦስ ክርስቲያን ሲሆን በሥውር ወታደር ሆነ። አንጥያኮስ ለሚባል መኰንንም ስለ ዮሐንስና ስለ ኤጲስቆጶስ አባ አክሎግ ከተርሴስ አገር ስለ ናሕር ስለ አባ ፊልጶስም እነርሱ ክርስቲያኖች እንደሆኑ ነገር ሠሩባቸው። ❤ መኰንኑም እነርሱን አቅርቦ "እናንት ክርስቲያኖች ናችሁን?" አላቸው "እኛ በእውነት ክርስቲያን ነን በሕያው እግዚአብሔር ልጅ በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እናምናለን" አሉት። መኰንኑም "ይህን ነገር ትታችሁ ለአማልክት ሠዉ" አላቸው። ቅዱሳኑም እንዲህ ብለው መለሱለት "እኛስ ለረከሱና ለተናቁ አማልክት አንሠዋም ሰማይና ምድርን ከፈጠረ ከጌታችን ኢየሱስ በቀር"። መኰንኑም ሰምቶ እጅግ ተቆጣ ምስክርነታቸውንም እስከፈጸሙ ድረስ አሠቃያቸው። ❤ ቅዱስ ቢካቦስን ግን ከአሠቃየው በኋላ አሠረውና ከመንኰራኲር ውስጥ ጨመረው ዘቅዝቆም ሰቀለው ሕዋሳቱንም ቆራረጠው ጌታችንም ያስታግሠውና ያበረታው ነበር ያለ ጉዳትም ጤናማ አድርጎ አስነሳው። ❤ ከዚህም በኋላ በርሙን ወደሚባል አገር ከብዙዎች ሰማዕታት ጋራ ላከው በመርከብም ውስጥ እህልና ውኃ ሳይቀምሱ ሃያ ስድስት ቀኖች ኖሩ። በርሙን ወደሚባል አገርም በደረሱ ጊዜ ጽኑ ሥቃይን አሠቃይተው በምሳር ቆረጡት የምስክርነቱንም ተጋድሎ ፈጸመ መንግሥተ ሰማያትም አክሊልን ተቀበለ። ❤ ከሀገረ በርሙን ሹማምንቶችም አንድ ባለ ጸጋ ሰው መጥቶ የቅዱስ ቢካቦስን ሥጋ ወስዶ በአማሩ ልብሶች ገነዘው ወደ አገሩ እስሙናይንም ላከው። በመከራውም ወራት ቊጥር የሌላቸው ብዙዎች ሰዎች በሰማዕትነት ሞቱ ከእርሱም ጋራ የተገደሉ ዘጠና አምስት ሰዎች ናቸው። ❤ ከዚህም በኋላ ለቅዱሱ ቤተ ክርስቲያን ሠርተውለት ሥጋውን በውስጧ አኖሩ ከእርሱም ብዙ ድንቅ ተአምር ተገለጠ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳን ሰማዕታት ቢካቦስና ዮሐንስ በጸሎታቸው ይማረን በረከታቸው ይድረሰን ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የነሐሴ 10 ስንክሳር።                          ✝️ ✝️ ✝️ ❤ "#ሰላም_እብል_ኪያክሙ_ማኅበረ። እምነቢያት ቅድመ ወእምወንጌላውን አኅረ። ፍሡሐን አእላፍ #እለተሳተፍክሙ_በኲረ። #ጽዮንሃ በጺሐክሙ ሀገረ። በጸሎትክሙ ቅድስት ዝክሩነ ወትረ"።

  • ❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤            ❤ #ነሐሴ ፱ (9) ቀን። ❤ እንኳን #ለአባታች_ለአቡነ_እስትንፋሰ_ክርስቶስ ለወራዊ መታሰቢያ በዓል (በዚች ቀን አባታችን እስትፋሰ ክርስቶስ ከሰማይ የወረደውን የቊርባን ኅብስት ተቀብለው ያቀበሉበት ነው ብሎ ገድላቸው ይናገራል)ና ስጥኑፍ ከሚባል አገር ለሆኑ ለሰማዕቱ ለካህኑ #አባ_ኦር ለዕረፍት በዐል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በፍቅር አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ሚታሰቡ፦ #ከሊቀ_ጳጳስ_አባ_ጲላጦስ ከመታሰቢያ እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።                            ✝ ✝ ✝ ❤ ስጥኑፍ ከሚባል አገር የሆነ የከበረ #ቄስ_አባ_ኦሪ፦ ይህ ቅዱስ ብዙ ርኅራኄ ያለው በሥጋው በነፍሱም ንጹሕ የሆነ ነው ብዙ ጊዜም አምላካዊ ራእይን ያያል። ከዚህም በኋላ የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመሠዊያው ላይ ታይቶ ብዙ ምሥጢራትን ገለጠለት። ❤ ከዚህም በኋላ የአባ ኦሪ ዜናው በኒቅዮስ አገር መኰንን ዘንድ ተሰማ ወደርሱም አስቀርቦ "ለአማልክት ዕጣን አቅርብ" አለው እርሱም "ለረከሱና ለተሠሩ አማልክት አልሠዋም" ብሎ እምቢ አለው። መኰንኑም ተቆጥቶ በብዙ ሥራ አስፈራራው ቅዱስ ኦሪም ሥቃዩን ምንም ምን አልፈራውም ጹኑ ሥቃይንም አሠቃየው። ❤ ከዚህም በኋላ ወደ እስክንድርያ አገር ላከው በዚያም ጽኑዕ የሆነ ሥቃይን አሠቃይተው በወህኒ ቤት ጣሉት። በዚያም ድንቆች ተአምራቶችን በማድረግ በሽተኞችን ፈወሳቸው ። ዜናውም በተሰማ ጊዜ ደዌ ያለባቸው ሁሉ ከየአገሩ ብዙዎች ሰዎች ወደርሱ መጥተው አዳናቸው። ይህንንም መኰንኑ ሰምቶ ራሱን በሰይፍ እንዲቆርጡ አዘዘ በመንግስተ ሰማያትም የሰማዕትነትን አክሊል ተቀበለ። ❤ ከዚህም በኋላ የከበረ ዮልዮስ ሥጋውን አንሥቶ ገንዘው ወደ ሀገሩ ስጥኑፍም ላከው። የመከራውም ወራት ካለፈ በኋላ ውብ የሆነች ቤተ ክርስቲያን ሠርተውለት ሥጋውን በውስጧ አኖሩ ከሥጋውም ድንቆች ተአምራቶች ተገለጡ። በማመንም ለሚመጡ በሽተኞች ሁሉ ታላቅ ፈውስ ሆነ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱስ አባ ኦሪ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የነሐሴ 9 ስንክሳር።                           ✝ ✝ ✝ ❤ #የዕለቱ_ምስባክ፦ "ወትቀውም ንግሥት በየማንከ። በአልባሰ ወርቅ ዑጽፍት ወኊብርት። ስምዒ ወለትየ ወርእዪ ወአጽምዒ ዕዝነኪ"። መዝ 44፥9-10። የሚነበቡት መልዕክታት ፊሊ 1፥12-24፣ 2ኛ ዮሐ 1፥6-ፍ.ም እና የሐዋ ሥራ 15፥19-25። የሚነበበው ወንጌል ዮሐ 10፥1-22። የሚቀደሰው ቅዳሴ የእመቤታችን የማርያም ቅዳሴ ነው። መልካም የጾም ጊዜና በዓል። ለሁላችንም ይሁንልን።

  • ❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤               ❤ #ነሐሴ ፰ (8) ቀን። ❤ እንኳን #ለኢትዮጵያዊው_ጻድቅ ከሰባቱ ከዋክብትን አንዱ ለሆኑት ሁለት ድንጋዮችን በተረአምራት እንደ ታንኳ አድርገው በመጠቀም ጣና ባሕሩን በበትረ መስቀላቸው እየቀዘፉ በመሔድ ታላቁ ገዳም ደጋ እስጢፋኖስን ለመሠረቱት ለታላቁ አባት #አቡነ_ኂሩተ_አምላክ ዕረፍታቸው በዐል በሰላም አደረሰን።                             ✝ ✝ ✝ ❤ #አቡነ_ኂሩተ_አምላክ_ዘጣና፡- ሰባቱ ከዋክብት ከተባሉት ቅዱሳን አንዱ አቡነ ኂሩተ አምላክ ሲሆኑ እሳቸውም ታላቁን ገዳም ዳጋ እስጢፋኖስን የመሠረቱት ናቸው፡፡ እርሳቸውም የዐፄ ይኩኖ አምላክ የወንድም ልጅ ናቸው፡፡ ከደብረ ሊባኖሱ አቡነ ተክለሃይማኖት ጋር ሆነው በሐይቅ እስጢፋኖስ ገዳም ከአባ ኢየሱስ ሞዐ ሥርዓተ ምንኵስናን ተምረዋል፡፡ ንጉሡ አቡነ ተክለ ሃይማኖትን ለመላዋ ኢትዮጵያ ሊቀ ካህናት፣ አቡነ ኂሩተ አምላክን ደግሞ ዓቃቤ ሰዓት አድርገው ሾሟቸው፡፡ ❤ አቡነ ኂሩተ አምላክም በዓቃቤ ሰዓትነት ለጥቂት ጊዜ ካገለገሉ በኋላ በዓለም በመንግሥት ተቀምጦ ከማገልገል ይልቅ ከከተማ ወጥቶ ከሰው ተለይቶ እግዚአብሔርን ማገልግል ይበልጣል በማለት የተቀበሉትን መዓርገ ሢመት ንቀው በመተው አልባሌ መስለው ታቦተ እስጢፋኖስን ከሐይቅ ይዘው መልአክ እየመራቸው ወደ ጣና ባሕር ዳርቻ ደረሱ፡፡ ሁለት ድንጋዮችንም በተረአምራት እንደ ታንኳ አድርገው በመጠቀም ባሕሩን በበትረ መስቀላቸው እየቀዘፉ ዳጋ ወደተባለው ደሴት ገብተው ጥቂት ዕረፍትን አድርገዋል፡፡ እሳቸው ያን ጊዜ ያረፉበት ቦታ ዛሬም ድረስ "ዓቃቤ ሰዓት" እየተባለ በመዓርግ ስማቸው ይጠራል፡፡ የጣናን ባሕር እንደ ታንኳ ተጠቅመው የተሻገሩባቸው እነዚያ ሁለት ትላልቅ ድንጋዮችም ዛሬ በገዳሙ ውስጥ የጻድቃን ማረፊያ (ምዕራፈ ጻድቃን) ተብሎ በሚጠራው ቦታ ላይ በክብር ተቀምጠው ይገኛሉ፡፡ አቡነ ኂሩተ አምላክ በቦታው ላይ ሥርዓቱን አጽንተው ተጋድሎአቸውን ጨርሰው ነሐሴ 8 ቀን በክብር ዐርፈዋል፡፡ ❤ ዳጋ እስጢፋስ ገዳምን ከዐፄ ዳዊት ጀምሮ እስከ ዐፄ ኃይለ ሥላሴ ድረስ የተነሡት ነገሥታት እየተሳለሙት የከበሩ ቅርሶችንና የወርቅ ዘውዳቸውን በስጦታ አበረክተውላታል፡፡ 900 ዓመት ያስቆጠሩ የብራና መጻሕፍትና ሌሎች አስደናቂ ቅርሶች የሚገኙበት ገዳም ነው፡፡ የዐፄ ዳዊት፣ የዐፄ ዘርዐ ያዕቆብ፣ የዐፄ ፋሲልና የሌሎቹም ቅዱሳን ነገሥታት ዐፅም በዚህ ገዳም በክብር ተቀምጦ ይገኛል፡፡ የዐፄ ሱስንዮስም ዐፅም በዚሁ በታላቁ ገዳም ዳጋ እስጢፋኖስ ከብዙ ቅዱሳን ነገስታት ዐፅም ጋር ይገኛል፡፡ ❤ ዐፄ ሱስንዮስ የፖርቱጋልን እርዳታ ለማግኘት ሲሉ የካቶሊክን የክህደት እምነት አምነው በሀገራችንም ላይ አውጀው ከ8 ሺህ በላይ ካህናት ምእመናንን ካስገደሉ በኋላ ምላሳቸው ተጎልጉሎ በክፉ አሟሟት ሊሞቱ ሲሉ ልጃቸው ፋሲል ቅዱሳን አባቶችን በመለመን በጸሎታቸው እንዲፈወሱ አድርጓቸዋል፡፡ እነ አቡነ ምእመነ ድንግል እና አቡነ ዓምደ ሥላሴ ጋር በጸሎታቸው የንጉሡን የተጎለጎለ ምላሳቸውን መልሰውላቸው ከሕመማቸውም ፈውሰዋቸዋል፡፡ "ፋሲል ይንገስ ካቶሊክ ይፍለስ…ተዋሕዶ ይመለስ…የዐፄ ሱስንዮስ ምላስ ይመለስ…እግዚአብሔር ይፍታ" ሲል ተጎልግሉ የነበረው ምላሳቸው ተመልሰ፡፡ በዚያን ጊዜ ዐፄ ሱስንዮስ "ብቆይ ዓመት ብበላ ገአት (ገንፎ)" ብለው በመናገር ምላሳቸው እንደቀድሞው ሆነላቸው። ለንስሐ ሞት በቅተው መንግስታቸውን ለልጃቸው አውርሰው በክብር አርፈዋል፡፡ ለዚህም ነው የዐፄ ሱስንዮስ ዐፅም በታላቁ ገዳም ዳጋ እስጢፋኖስ ከብዙ ቅዱሳን ነገስታት ዐፅም ጋር አብሮ መገኘቱ፡፡ ❤ አቡነ ኂሩተ አምላክ የጌታችንን ቅዱስ መስቀል ወደ ሀገራችን ለማምጣት ብዙ የደከሙ አባት ናቸው፡፡ ንጉሡ ዐፄ ዳዊት በዘመናቸው ርሀብ ስለነተሳ የዘደብረ ቢዘኑን ታላቁን ጻድቅ አቡነ ፊሊጶስን ከገዳማቸው አስጠርተው "ምን ባደርግ ይሻለኛል?" ብለው አማከሯቸው፡፡ እኚህም የዘደብረ ቢዘኑ አቡነ ፊሊጶስ የዐፄ ዘርዐ ያዕቆብን መወለድ በትንቢት የተናገሩ ናቸው፡፡ ንግሥቲቱ የዐፄ ዳዊት ሚስት የአቡነ ፊሊጶስን እግራቸውን አጥባቸው ስትጨርስ የእግራቸውን እጣቢ በእምነት ጠጣችው፡፡ በዚህም ጊዜ አቡነ ፊሊጶስ ንግሥቲቱን "ከማኅፀንሽ ፍሬ ታላቅ ጻድቅ ልጅ ይወጣል" ብለው ትንቢት ከነገሯት በኋላ በትንቢታቸው መሠረት ታላቁ ጻድቅ ንጉሥ ዐፄ ዘርዐ ያዕቆብ ተወልደዋል፡፡ ❤ ዐፄ ዳዊትም በዘመናቸው ስለተነሣው ርሀብ አቡነ ፊሊጶስን ሲያማክሯቸው ጻድቁ ሱባዔ ገብተው በጸሎት ከጠየቁ በኋላ "የጌታችንን መስቀል ያስመጡ" ብለው ንጉሡን መከሯቸው፡፡ ንጉሡ ዐፄ ዳዊትም ከኢየሩሳሌም፣ ከቁስጥንጥንያና ከእስክንድርያ መንግሥታት ጋር ተጻጽፈው ዓሥሩን ታላላቅ የሀገራችንን ቅዱሳን ይዘው ሄደው መስቀሉን መስከረም 10 ቀን አምጥተውታል፡፡ ❤ ቅዱስ መስቀሉን ካመጡት ዓሥሩ ታላላቅ ቅዱሳን ውስጥም አንዱ የጣና ደሴቱ አቡነ ኂሩተ አምላክ ናቸው፡፡ የተቀሩት ዘጠኙ ደግሞ የደብረ ቢዘኑ አቡነ ፊሊጶስ፣ የጣና ደሴቱ አቡነ እንድርያስ፣ አቡነ በትረ ማርያም፣ አቡነ ዮሐንስ፣ አቡነ ታዴዎስ፣ አቡነ ያፍቅረነ እግዚእ፣ አቡነ ዘካርያስ፣ አቡነ ያሳይና አቡነ ቶማስ ናቸው፡፡ ❤ አቡነ ኂሩተ አምላክ ወደ ግብፅ ሄደው ግማደ መስቀሉን ይዘው ከግብፅ ስለመጡ አንዳንድ ሰዎች ግብፃዊ ናቸው ይሏቸዋል ነገር ግን ለሀገራቸው ለቅድስት ኢትዮጵያ ትልቅ ውለታ የዋሉ ታላቅ ጻድቅ ናቸው፡፡ የትውልድ ሀገራቸውም ወሎ ልዩ ቦታው መርጦ እንደሆነ ታሪካቸው ያስረዳል፡፡ ከአቡነ ኂሩተ አምላክ ረድኤት በረከትን እግዚአብሔር አምላክ ያሳትፈን። በጸሎታቸውም ይማረን!፡፡ ምንጭ፦ መዝገበ ቅዱሳን ከሚለው መጽሐፍ የተወሰደ።

  • ✝✞✞✞እንኳን ለካህኑ ሰማዕት ቅዱስ አልዓዛር እና ለቅዱሳን ቤተሰቡ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። ✝✞✞✞ ✝✞✞✞በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! ✝✞✞✞ ✝✞✞✞ቅዱስ አልዓዛር ካህን ✝✞✞✞ ††† ይህ ቅዱስ #የብሉይ ኪዳን ሰማዕታት ተብለው ከሚታወቁት ዋነኛው ነው:: የነበረበት ዘመንም ቅድመ ልደተ ክርስቶስ ሲሆን " #ዓመተ_መቃብያን/ #ዘመነ_ካህናት" ይባላል:: †††በወቅቱ ሰሎሜ የምትባል ደግ ሴት አግብቶ ይኖር የነበረው ቅዱስ አልዓዛር በኢየሩሳሌም ተወዳጅ ነበር:: ሐረገ ትውልዱ ከአሮን ወገን ነውና በክህነቱ ተግቶ ያገለግል ነበር:: በዚያ ላይ ሊቀ ካህንነትን በመመረጡ ሕዝቡን ይሠራ: ያስተምር: ያስተዳድር ነበር:: †††ቅዱስ አልዓዛር ከተባረከች ሚስቱ ሰሎሜ 7 ወንዶች ልጆችን አፍርቷል:: እነርሱንም በሥርዓት አሳድጐ የቤተ እግዚአብሔር አገልጋዮች እንዲሆኑ አድርጐ ነበር:: በዚያው ዘመን በኢየሩሳሌም አካባቢ የሚኖሩ 3 እኩያን (ክፉ) ካህናት ነበሩ:: †††እነዚሁም ሕዝቡን ከማስቸገር: ፈጣሪን ከማሳዘን ቦዝነው አያውቁም ነበር:: የክፋታቸው መጨረሻ ግን የገዛ ሃገራቸውን ማጥፋት ሆነ:: ነገሩ እንዲህ ነው:- 3ቱም ተመካክረው የአልዓዛርን የሊቀ ካህንነት ቦታ ሊቀሙ ወስነው ወደ እርሱ ሔዱና እንዲህ አሉት:: †††"ሹመት በተርታ: ሥጋ በገበታ" ሲሆን ያምራልና እኛ በተራችን በወንበሩ ላይ እንቀመጥ::" እርሱ ግን "ሕዝቡን ጠይቃችሁ ተሾሙ" አላቸው:: እነርሱም ሕዝቡን ጠርተው "ሹመት ይገባናል" ቢሏቸው ሕዝቡ መልሶ "አልዓዛርን የሾመው እግዚአብሔር ነውና እናንተም ከፈጣሪ ጠይቃችሁ ተሾሙ" አሏቸው:: †††በዚህ ጊዜ 3ቱ እኩያን ተቆጡ:: ምክንያቱም እግዚአብሔር እንደ ማይሰጣቸው ያውቃሉና:: ወዲያው ግን 3ቱም ከአካባቢው ጠፉ:: ከኢየሩሳሌም ወጥተው ወደ ጨካኙ የግሪክ ንጉሥ አንጥያኮስ ሔዱ:: †††አንጥያኮስ ማለት "ቀኝ ዐይናችሁን ገብሩልኝ" የሚል ንጉሥ ነው:: እርሱን " #ኢየሩሳሌም ባለቤት የላትምና ሒደህ ውረራት" አሉት:: "አጥሩ ጥብቅ ነው:: በምን እገባለሁ?" ቢላቸው "እኛ በመላ እናስገባሃለን" አሉት:: እርሱም 240,000 ሠራዊት አስከትቶ ወረደ:: †††እነርሱ ቀድመው ወደ ኢየሩሳሌም ገብተው ያስወሩ ጀመር:: "እናንተ ሹመት ብትነሱንም እኛ ግን አንጥያኮስን ያህል ንጉሥ በእሥራኤል አምላክ አሳምነን መጣን" እያሉ ይሰብኩ ገቡ:: ቅዱስ አልዓዛር "አትስሟቸው:: በዚያም ላይ አሕዛብ የተቀደሰውን ምድር መርገጥ የለባቸውም" ብሎ ነበር:: †††ነገር ግን አንዳንድ ችኩሎች አይጠፉምና ፈጥነው የከተማዋን በር ከፈቱት:: ሠራዊቱን ደብቆ ትንሽ ራሱን የቆመ የመሰለው አንጥያኮስ በምክንያት: በክፋትና በመላ ሁሉን ሠራዊቱን አስገባ:: የሚገርመው በጊዜው የከተማዋ ሕዝብ 12 እልፍ (120,000) ሲሆን ንጉሡ ያስገባው ሠራዊት ግን 24 እልፍ (240,000) ሆኖ ተገኘ:: †††ወዲያው አንጥያኮስ ሕዝቡን ሰበሰበና አልዓዛርን ለብቻው ጠርቶ ተናገረው:: "አንተ አምላክህን እንደምትወድ ሰምቻለሁ:: አንተ የበጉን መስዋዕት በልተህ: #ለስዕለ_ኪሩብ ሰግደህ: ሕዝቡን ግን እሪያ (አሳማ) እንዲበላና ለጸፀሐይ እንዲሰግድ አድርግልኝ" አለው:: †††ቅዱስ አልዓዛር መለሰለት:- "እግዚአብሔር የሾመኝኮ በጐ ሃይማኖትን ላስተምር እንጂ ለክፋት አይደለም:: ለሕዝቤ የክፋት አብነት ፈጽሞ አልሆንም" አለው:: ያን ጊዜ ንጉሡ በቅዱሱ ላይ ተቆጣ:: "የምልህን ካላደረግህ ብዙ ግፍ ይደርስብሃል" ቢለው ቅዱሱ መልሶ "የፈለግኸውን አድርግ" አለው:: †††በዚያን ጊዜ ንጉሡ የቅዱሱን ሚስትና 7 ልጆች እንዲያመጡለት አዘዘ:: ቅዱሱ እያየ ከፊቱ ላይ 7ቱንም ልጆቹን በሰይፍ አስመታቸውና 7ቱም ወደቁ:: ለአንድ አባት ይህ የመጨረሻው መራራ ፈተና ነው:: #አልዓዛር ግን ምን አንጀቱ በኀዘን ቢቃጠልም ከልጆቹ ለእግዚአብሔር አድልቷልና ቻለው ታገሠው:: †††በዚህ ለውጥ እንዳልመጣ ያየው ንጉሡ ሌላ ፍርድ ተናገረ:: ቅዱሱንና ሚስቱን ( #ሰሎሜን) በፈትል ጠቅልለው በሠም ነከሯቸው:: (ጧፍ እንደሚሠራበት መንገድ ማለት ነው:: ) †††አሁንም ግን ከአምልኮታቸው ፈቀቅ ባለማለታቸው ትልቅ ብረት ምጣድ ተጥዶ: 2ቱም ከነነፍሳቸው እንዲቃጠሉ ተደረገ:: ቀጥሎም ሕዝቡን እንዲፈጁ አዋጅ ወጣ:: በከተማዋ ከነበረው ሕዝብ 40,000 ያህሉ ተገደሉ:: †††40,000 ያህሉ ሲማረኩ 40,000 ያህሉን ደግሞ #ይሁዳ የሚባል አርበኛ በር ሰብሮ ይዟቸው ሸሸ:: "እንሾማለን: እንሸለማለን" ብለው ሕዝባቸውን ያስፈጁ እነዚያ ካህናትም #እግዚአብሔር ፈርዶባቸው እነርሱም ተገደሉ:: ቅዱሱ የአልዓዛር ቤተሰብ ግን የክብርን አክሊል አግኝተዋል:: ††† #የእሥራኤል_አምላክ ቸሩ እግዚአብሔር እንዲህ ካለው መከራ በኪነ ጥበቡ ይሰውረን:: ከቅዱሳኑ በረከትም አይለየን:: ††† ነሐሴ 8 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ††† 1.ቅዱስ አልዓዛር ካህን (ሰማዕት) 2.ቅድስት ሰሎሜ ሰማዕት (ሚስቱ) 3."7ቱ" ቅዱሳን ሰማዕታት (ልጆቹ) 4.ቅዱስ አሞን ሰማዕት ††† ወርሐዊ በዓላት ††† 1.ቅዱስ ሙሴ ሊቀ ነቢያት 2.ኪሩቤል (አርባዕቱ እንስሳ) 3.አባ ብሶይ (ቢሾይ) 4.አቡነ ኪሮስ 5.አባ ሳሙኤል ዘደብረ ቀልሞን 6.ቅዱስ ማትያስ ሐዋርያ (ከ12ቱ ሐዋርያት) ††† "አቤቱ አሕዛብ ወደ ርስትህ ገቡ:: የቅድስናህንም መቅደስ አረከሱ:: ኢየሩሳሌምንም እንደ መደብ አደረጉአት:: የባሪያዎችህንም በድኖች ለሰማይ ወፎች መብል አደረጉ:: የጻድቃንህንም ሥጋ ለምድር አራዊት:: ደማቸውንም በኢየሩሳሌም ዙሪያ እንደ ውሃ አፈሰሱ:: የሚቀብራቸውም አጡ::" ††† (መዝ. 78:1) <<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>

  • ††† እንኳን ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ዓመታዊ የጽንሰት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። ††† †††በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! ††† ††† ቁጽረታ (ጽንሰታ) ለማርያም ††† ††† ይህችን ዕለት አበው ሊቃውንት "ጥንተ መድኃኒት፤ የድኅነት መነሻ ቀን" ሲሉ ይጠሯታል:: ስለ ምን ነው ቢሉ:- ለዓለም ድኅነት ምክንያት የሆነች የአምላክ እናቱ የተጸነሰችበት ዕለት በመሆኑ ነው:: አንድም ከአዳም ስሕተት በኋላ ያለ ጥንተ አብሶ የተጸነሰች የመጀመሪያ ሰው እርሷ ናትና እንዲህ ይላሉ:: "ለጽንሰትኪ በከርሥ: እንበለ አበሳ ወርኩስ: ወለልደትኪ እማኅጸን ቅዱስ::" "ድንግል ሆይ! መጸነስሽ ያለ በደል (ያለ ጥፋት) ነው: የተወለድሽበት ማኅጸንም ቅዱስ ነው::" (መጽሐፈ ሰዓታት, ኢሳ. 1:9, መኃ. 4) ይሕች ዕለት ለኢያቄምና ለሐና ብቻ ሳይሆን ለፍጥረት ሁሉ የተስፋ ድኅነት ቀን ናትና ሐሴትን ልናደርግ ይገባል:: የእመቤታችን መጸነስስ እንደ ምን ነው ቢሉ:- ከነገደ ይሁዳ የሚወለድ ቅዱስ ኢያቄም የሚባል ደግ ሰው ከነገደ ሌዊ(አሮን) የተወለደች ሐና የምትባል ደግ ሴት አግብቶ: በሕጉ ጸንተው: በሥርዓቱ ተጠብቀው ይኖሩ ነበር:: ነገር ግን በዘመኑ ሰዎች "ልጅ የላችሁም" በሚል ይናቁ ነበር:: ኦሪታውያን ልጅ የሌለውን "ኅጡአ በረከት-ከጸጋ እግዚአብሔር የራቀ" ነው ብለው ያምኑ ነበር:: ኢያቄምና ሐና ልጅ እንዲሰጣቸው ሲያዝኑ: ሲጸልዩ ዘመናቸው አልፎ አረጁ:: እነሱ ግን የሚያመልኩት የአብርሃምና ሣራን አምላክ ነውና ተስፋ አልቆረጡም:: የለመኑትን የማይነሳ ጌታ በስተእርጅናቸው ድንቅ ነገርን አደረገላቸው:: አንድ ቀን ርግቦች ከጫጩቶቻቸው ጋር ሲጫወቱ የተመለከተች ቅድስት ሐና ፈጽማ አለቀሰች:: "እንስሳትና አራዊትን: እጽዋትን በተፈጥሯቸው እንዲያፈሩ የምታደርግ አምላክ ምነው ሐናን ድንጋይ አድርገህ ፈጥረሃታልን?" ብላ አዘነች:: ይህን የተመለከተ ቅዱስ ኢያቄም ወደ ተራራ ወጥቶ ሱባኤ ያዘ:: ለአርባ ቀናትም ሲጸልይና ሲማለል ቆየ:: በአርባኛው ቀን ሁለቱም ሕልምን ያልማሉ:: እርሱ:- ነጭ ርግብ ሰማያትን ሰንጥቃ ወርዳ: በሐና ቀኝ ጆሮ ገብታ: በማኅጸኗ ስትደርስ አየ:: እርሷ ደግሞ:- የኢያቄም በትር አብቦ: አፍርቶ: ጣፋጭ ፍሬውን ሰው ሁሉ ሲመገበው ታያለች:: ቅዱስ ኢያቄም ከሱባኤ እንደ ተመለሰ ያዩትን ተጨዋውተው "ፈቃደ እግዚአብሔር ይሁን" አሉ:: ለሰባት ቀናትም በጋራ እግዚአብሔርን ሲለምኑ ሰነበቱ:: በሰባተኛው ቀን (ማለትም ነሐሴ 7) መልአከ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል ክንፉን እያማታ ወደ እነርሱ ወረደ:: "ዓለም የሚድንባት: የፍጥረት ሁሉ መመኪያ የሆነች ልጅ ትወልዳላችሁ" ብሏቸው ተሠወራቸው:: እነርሱም ደስ ብሏቸው እግዚአብሔርን አመሰገኑ:: እንደ ሥርዓቱም በዚህች ቀን አብረው አድረው እመ ብርሃን ተጸነሰች:: "ኦ ድንግል አኮ በፍትወተ ደነስ ዘተጸነስኪ" "ድንግል ሆይ! ኃጢአት ባለበት ሥጋዊ ፍትወት የተጸነስሽ አይደለም" እንዳለ ሊቁ:: (ቅዳሴ ማርያም) ††† ቅዱስ ጴጥሮስ ሊቀ ሐዋርያት ††† ††† ዳግመኛ ይህች ዕለት የቅዱስ ጴጥሮስ መታሰቢያ ናት:: ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመዋዕለ ስብከቱ በዚህች ቀን ደቀ መዛሙርቱን ወደ ቂሣርያ ፊልጶስ ይዟቸው ሔደ:: በዚያም ጌታ ከእነሱ ራቅ ብሎ ተቀምጦ ነበርና የማይሰማቸው መስሏቸው እርስ በእርስ ይከራከሩ ገቡ:: የክርክራቸው መነሻ ደግሞ ጌታችን ነበር:: የዋሃን (ገና ምሥጢርን ያልተረዱ) ነበሩና አንዱ ተነስቶ "ኤልያስ ነው": ሌላኛው "ሙሴ": ሦስተኛው "ኤርምያስ ነው" በሚል ተከራከሩ:: ቅዱስ ጴጥሮስ ለብቻው ቆሞ ነበርና ጠርተው "ሃሳባችንን አስታርቅልን:: ለአንተስ ማን ይመስልሃል?" አሉት:: አረጋዊው ሐዋርያም ተቆጣቸው:: "እናንተ እንደምታስቡት እርሱ ከነቢያት አንዱ ሳይሆን "እግዚአ ነቢያት-የነቢያት ፈጣሪ ነው" አላቸው:: ወዲያውም ጌታ ጠርቷቸው ወደ እርሱ ቀረቡ:: ቸር አምላክ "ለምን ተጠራጠራችሁኝ" ብሎ መገሰጽ ሲችል እንዳይደነግጡ ጥያቄውን በፈሊጥ አደረገ:: "የሰውን ልጅ ሰዎች ማን ይሉታል?" አላቸው:: እነርሱም በልባቸው ያለውን የሌላ አስመስለው ተናገሩ:: ጌታችን "እናንተስ ማን ትሉኛላችሁ?" ቢላቸው ጸጥ አሉ:: ገና ሃይማኖታቸው አልጸናም ነበርና:: በዚያን ጊዜ ቅዱስ ጴጥሮስ ተነስቶ "አንተ ውእቱ ክርስቶስ ወልደ እግዚአብሔር ሕያው-አንተ የሕያው እግዚአብሔር የባሕርይ ልጁ ክርስቶስ ነህ" አለው:: (ማቴ. 16:16) ይህች ቃል የክርስትና ሃይማኖት መሠረት ናትና ጌታችን "አንተ ዓለት (መሠረት) ነህ" ብሎ የቤተ ክርስቲያንን በዚህ እምነት ላይ መመስረት ተናገረ:: ለቅዱስ ጴጥሮስም "መራሑተ መንግስት-የመንግስተ ሰማያት መክፈቻ ቁልፍ (ሥልጣን)" ተሰጠው:: ††† ሊቀ ሐዋርያትነትንም ደረበ:: ዛሬ ለበርካቶቹ የጸነነባቸው ይሔው እምነት ነው:: ኢየሱስ ክርስቶስን "አምላክ ወልደ አምላክ: ወልደ ማርያም: አካላዊ ቃል: ሥግው ቃል: ገባሬ ኩሉ: የሁሉ ፈጣሪ"ብለው ካላመኑ እንኳን ጽድቅ ክርስትናም የለም:: ††† አፄ ናዖድ ጻድቅ ††† ††† ሃገራችን ኢትዮጵያ ምስፍና ከክህነት: ንግሥናን ከጽድቅ ያጣመሩ ብዙ መሪዎች ነበሯት:: ከእነዚህ አንዱ ደግሞ አፄ ናዖድ ናቸው:: ጻድቁ ንጉሥ የነገሡት ከ1487 እስከ 1499 ዓ/ም ሲሆን ለእመቤታችን በነበራቸው ልዩ ፍቅር ይታወቃሉ:: ካህን እንደ ነበሩም ይነገራል:: ዛሬ ሁላችን የምንወዳትን ጸሎት (ሰላም ለኪ: እንዘ ንሰግድ ንብለኪ . . .) የደረሷት እርሳቸው ናቸው:: ትልቁን መልክአ ማርያምም ደርሰዋል:: ይህ መልክእ ጣዕሙ ልዩ ነው:: የጻድቁ ንጉሥ ሚስት (ማርያም ክብራ): ልጆቻቸው (አፄ ልብነ ድንግልና ቡርክት ሮማነ ወርቅ) እጅግ መልካም ክርስቲያኖች ነበሩ:: ንጉሡ አፄ ናዖድ ከባለሟልነት የተነሳ ድንግል ማርያምን "እመቤቴ ስምንተኛው ሺ መቼ ይገባል? ጊዜውስ እንዴት ያለ ነው?" አሏት:: እመ ብርሃንም በአካል ተገልጻ የዘመኑንና የሰውን ክፋት ነገረቻቸው:: ንጉሡም አዝነው "እመቤቴ! ከዛ ዘመን አታድርሺኝ" አሏት:: በዚህ ምክንያት የስምንተኛው ሺህ ዘመን መስከረም 1 በ1500 ዓ/ም ሊገባ እርሳቸው ነሐሴ 7 ቀን በ1499 ዓ/ም ዐርፈዋል:: ††† ጌታችን መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ የድንግል እናቱን ጣዕም: ፍቅር: የቅዱስ ጴጥሮስን ሃይማኖትና የአፄ ናዖድን በረከት ያሳድርብን:: ††† ነሐሴ 7 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት 1.በዓለ ጽንሰታ ለእግዝእትነ ማርያም 2.ቅዱሳን ኢያቄም ወሐና 3.ቅዱስ ገብርኤል መበሥር 4.ቅዱስ ጴጥሮስ ሊቀ ሐዋርያት 5.አፄ ናዖድ ጻድቅ (ንጉሠ ኢትዮጵያ) 6.ቅዱስ ዮሴፍ ጻድቅ (ወልደ ያዕቆብ-ልደቱ) 7.አባ ጢሞቴዎስ ሊቀ ጳጳሳት ††† ወርኀዊ በዓላት 1.ሥሉስ ቅዱስ (አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ) 2.አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ 3.አባ ሲኖዳ (የባሕታውያን አለቃ) 4.አባ ዳንኤል ዘገዳመ ሲሐት 5.አባ ባውላ ገዳማዊ 6.ቅዱስ አትናቴዎስ ሐዋርያዊ 7.ቅዱስ አግናጥዮስ (ለአንበሳ የተሰጠ) ††† "መሠረቶቿ በተቀደሱ ተራሮች ናቸው:: ከያዕቆብ ድንኳኖች ይልቅ እግዚአብሔር የጽዮንን ደጆች ይወዳቸዋል:: የእግዚአብሔር ከተማ ሆይ! በአንቺ የተደረገው ድንቅ ነው . . . ሰው እናታችን ጽዮን ይላል::" ††† (መዝ. ፹፮፥፩-፮) ††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር

  • без подписи

  • ትናንት የሰው ልጅ መሞት የለበትም ብለን ሪሪራ ስንል ዛሬ ደግሞ ምን ታመጣላችሁ ብለው ሰውን በሕይወት እየቀበሩ ፎቶ አንስተው ለቀቁልን 😭😭 ከዚህ ቀጥሎ ምን እናይ ይሆን ከተነገረው ትንቢት በላይ እየሆነ ነው በእውነት ይህ የኢትዮጵያውያን ባሕርይ ነው? " 😭😭😭 የራሄልን ግፍ የተመለከትህ እግዚአብሔር ሆይ ይህን ግፍ ተመልከት ግፈኞችን በቃችሁ በልልን

  • #ማብራሪያ :- 🔹🔸🔹ስለ አንቺ የሚነገረውን ነገር መናገር የሚቻለው ምን አንደበት ነው ማለቱ የእመቤታችንን ክብሯን ገናንነቷን እንዲሁም አምላክን በማኅፀኗ መሸከሟን በድንግልና ፀንሳ በድንግልና መውለዷን መናገር የሚቻለው አንደበት የለምና ስለዚህ ይህንን አለ። 🔹🔸🔹እመቤታችን በርግብ ትመሰላለችና መልካሟ ርግብ ትባላለች። ርግበ ኖኅም ትባላለች። የኖኅ ርግብ የጥፋት ውኃ ጎደለ ስትል ቅጠል ይዛ እንደ ታየች እመቤታችንም የፍዳ የመርገም የኃጢአት ዘመን አለፈ አበቃ ስትል ጌታን ፀንሳ ተገኝታለችና። ♦️🔹♦️ ተፈሥሒ ኦ ማርያም "ተፈሥሒ ኦ ማርያም እም ወአመት ... ፤ እናትና ገረድ የሆንሽ ማርያም ሆይ ደስ ይበልሽ። የታቀፍሽውን መላእክት ያመሰግኑታል ኪሩቤልም በፍርሐት ይሰግዱለታልና ሱራፌልም ክንፋቸውን ዘርግተው ያለማቋረጥ የሚመሰገን ንጉሥ (የክብር ባለቤት) ይህ ነው በይቅርታው ብዛት የዓለምን ኃጢኣት ያስተሠርይ ዘንድ የመጣው ይህ ነው ይላሉ። ቅድስት ሆይ ለምኝልን።" #ማብራሪያ :- 🔹🔸🔹 እመቤታችን እናትነትን ከገረድነት ወይም ከአገልጋይነት አስተባብራ ይዛለች። እናትነቷን "እናቱን እና ሕፃኑን ይዘህ ወደ ግብፅ ሂድ" ብሎ መልአኩ ነግሮናል። አገልጋይነቷን መልአኩ ባበሠራት ጊዜ እነሆኝ እንደ ቃልህ ይደረግልኝ እኔ ለእግዚአብሔር ባሪያው ነኝ ስትል ሰምተናታልና። 🔹🔸🔹 ሰአሊ ለነ ቅድስት። የሰውን ኃጢአት በቸርነቱ ከሚያስተሠርይ ልጅሽ ጽንዕት በድንግልና ሥርጉት በቅድስና እመቤታችን ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሳን ለምኝልን አእምሮውን ማስተዋሉን በልቡናችን ሳይብን አሳድሪብን። ◊◈◊◈◊◈◊◈◊◈◊◈◊◈◊◈◊ ➢➢ የቀጣይ ትምህርት #ክፍል_ስድስት

  • የማክኞ ውዳሴ ማርያም ማብራሪያ #ክፍል_አምስት ከቃለአብ ሕያው - ተፈሥሒ ኦ ማርያም ♦️🔹♦️ ቃለ አብ ሕያው "ቃለ አብ ሕያው ዘወረደ ውስተ ደብረ ሲና ... ፤ ወደ ደብረ ሲና የወረደ ለሙሴ ሕግን የሰጠ የተራራውን እራስ በጭጋግ በጢስ በጨለማና በነፋስ የሸፈነ ፈርተው የቆሙትንም በነጋሪቶች ድምፅ የገሠፀ የአብ አካላዊ ቃል ነው። ቅድስት ሆይ ለምኝልን። #ማብራሪያ 🔹🔸🔹 በደብረ ሲና ሙሴና አሮን በተራራው ራስ ፣ ሌዋውያኑ በተራራው ወገብ ፣ ሕዝቡ በተራራው እግር ሆነው ፤ ተራራው በደመና ፣ በጭጋግ ፣ በእሳት ፣ በጨለማ ተጋርዶ እግዚአብሔር ሙሴን ቃል በቃል ተነጋግሮ ዐሠርቱ ትእዛዛትን ሰጥቶታል። ዘጸ 19÷18 ♦️🔹♦️ ውእቱኬ ዘወረደ ኀቤኪ "ውእቱኬ ዘወረደ ኀቤኪ ... ፤ በትሕትና የተናገርሽ ተራራ ሆይ ይኸውም ወደ አንቺ የወረደው ነው። ሰውን የወደደ እርሱ ያለመለወጥ ባንቺ ሰው ሆነ እንደ እኛ በሚናገር ሥጋ ፍጹም ሆኖ አምላክ በመንፈስ ቅዱስ በማኅፀኗ አደረና ፍጹም ሰው ሆነ። አዳምን ያድነው ዘንድ ኃጢአቱንም ያስተሠርይለት ዘንድ በሰማያዊ ማዓርግ ያኖረው ዘንድ በቸርነቱና በይቅርታው ብዛት ወደ ቀድሞው ቦታው ይመልሰው ዘንድ። ቅድስት ሆይ ለምኝልን።" #ማብራሪያ 🔹🔸🔹 ዕበያና ውእቱኬ ተያይዘው ነው የሚተረጎሙት። ወደ አንቺ የወረደው እርሱ ነው ማለቱ በሲና ተራራ ለሙሴ የተናገረው ለሕዝቡ የተገለጠው እግዚአብሔር ወደ አንቺ የወረደውም እሱ ነው ሲል ነው። 🔹🔸🔹እመቤታችንን የምትናገር ተራራ አላት በደብረ ሲና ብትመሰልም ቅሉ በሲና ተራራ ጌታና ሙሴ ተነጋግረውባታል እንጂ እሷ አልተናገረችምና ከዚያ ሲለያት የምትናገር ተራራ አላት። በትሕትና የምትናገር ማለቱም የኢሳይያስን ትንቢት ስታነብ "ድንግል በድንግልና ፀንሳ በድንግልና አምላክን ትወልዳለች" ከሚለው በደረሰች ጊዜ ከዚች እሴት ከዘመኗ ደርሼ ወጥቼ ወርጄ አገልግያት አለች እንጂ እኔ ብሆን አላለችምና። ሊቁ ቅዱስ ኤፍሬም የደብረ ሲናውን ለእመቤታችን ሰጥቶ ሲናገር እንዲህ ይላል። "ከደብረ ሲና እሳትና ጨለማ ወጣ ከአንቺ ግን ሰው የሆነ አምላክ ተገኘልን። በደብረ ሲና በአይሁድ ላይ ድንጋፄ ሀውክ ተደረገ። በአንቺም በአይሁድ ፣ በሄሮድስ ፣ በዲያብሎስና በሠራዊቱ ላይ ጽኑ ድንጋፄ ተደረገ።" ሃይ.አበ 47÷8-9 🔹🔸🔹 ሰአሊ ለነ ቅድስት። በቸርነቱ ብዛት አዳምን ወደቀደመው ቦታው ከመለሰው ልጅሽ ጽንዕት በድንግልና ሥርጉት በቅድስና እመቤታችን ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሳን ለምኝልን አእምሮውን ማስተዋሉን በልቡናችን ሳይብን አሳድሪብን። ◊◈◊◈◊◈◊◈◊◈◊◈◊◈◊◈◊ ♦️🔹♦️ ዕበያ ለድንግል "ዕበያ ለድንግል ኢይትከሀል ለተነግሮ ... ፤ የድንግልን ገናንነቷን ሊናገሩት አይቻልም። ጌታ መርጧታልና የሚቀርበው በሌለ ብርሃን ውስጥ የሚኖር እርሱ መጥቶ አደረባት። ዘጠኝ ወር በማኅፀኗ አደረ የማይታይና የማይመረመር እርሱን በድንግልና ወለደችው። ቅድስት ሆይ ለምኝልን።" #ማብራሪያ 🔹🔸🔹 የድንግልን ክብሯን ሊናገሩት አይቻልም ማለት ለክብሯ እንደሚመጥን አድርጎ መናገር አይቻልም ክብሯን የፍጡር አንደበት ተናግሮ አይፈጽመውም አይገልጸውምና። ጌታ መርጧታል ማለትም በእግዚአብሔር የተመረጠችው እንድትመረጥ ሁና በመገኘቷ ነው። 🔹🔸🔹 የማይታይና የማይመረመር እርሱን በድንግልና ወለደችው ሲል ጌታ ሰው ከመሆኑ አስቀድሞ ሰው በሆነ ጊዜ ሰው ከሆነ በኋላ በፍጡራን አንደበት እንዲህ ነው ተብሎ ሊነገር ሊታሰብና ባሕርይው ሊመረመር አይችልም ሲል ነው። ሰውም ቢሆን የባሕርይ አምላክ ነውና። የባሕርይ አምላክን ደግሞ ፍጡር ሊያውቀው ሊመረምረው አይቻለውም ከሕሊናት ሁሉ በላይ ነውና። 🔹🔸🔹 ሰአሊ ለነ ቅድስት። ሰው ከመሆኑ አስቀድሞ ሰው በሆነ ጊዜ ሰውም ከሆነ በኋላ ከማይመረመረው ልጅሽ ጽንዕት በድንግልና ሥርጉት በቅድስና እመቤታችን ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሳን ለምኝልን አእምሮውን ማስተዋሉን በልቡናችን ሳይብን አሳድሪብን። ◊◈◊◈◊◈◊◈◊◈◊◈◊◈◊◈◊ ♦️🔹♦️ ዘውእቱ ዕብን "ዘውእቱ ዕብን ዘርእየ ዳንኤል ነቢይ ... ፤ ነቢዩ ዳንኤል ያየው ያለ እጅ ከረጅም ተራራ የተፈነቀለው ያ ደንጊያ ከአብ ዘንድ የመጣው ቃል ነውና መጥቶ ያለ ወንድ ዘር ከድንግል ተወልዶ አዳነን። ቅድስት ሆይ ለምኝልን" #ማብራሪያ :- 🔹🔸🔹 ነቢየ እግዚአብሔር ዳንኤል ለንጉሡ ታይቶት የተሰወረበትን ሕልም እግዚአብሔር ለእርሱ ባሳየው ጊዜ ከረጅም ተራራ የሰው እጅ ሳይፈነቅለው ወርዶ ጣዖቱን ሰብሮ ተመልሶ ተራራ ሲያክል አየና ወልደ እግዚአብሔር ሰው የመሆኑን ምሥጢር ተረዳ። ምሳሌነቱም ይኸው ነው። ➣ ደንጋይ የወልደ እግዚአብሔር ምሳሌ። ➣ የሰው እጅ ሳይፈነቅለው መውረዱ ያለ ወንድ ዘር የመፀነሱ ምሳሌ። ➣ ጣዖቱን ሰባብሮ ተመልሶ ተራራ ሲያክል ማየቱ : አምላክ ሰው ሁኖ አምልኮ ጣዖትን አጥፍቶ በጣዖቱ አድሮ የሚመለከውን ዲያብሎስንና ሠራዊቱን ድል የመንሣቱ። ተመልሶ ተራራ ማከሉም ደካማ ሥጋ ኃያል አምላክ የመሆኑ ምሥጢር ነው። ይህ ሁሉ የሆነው ከእመቤታችን ተወልዶ ነውና የዳንኤልን ራዕይ አነሣ። ♦️🔹♦️ ኮንኪ "ኮንኪ ዐፅቀ ንጹሐ ... ፤ እንደ ንጹሕ ጫፍ ሆንሽ ፤ የሃይማኖትም መገኛ ነሽ የቀናች የቅዱሳን አባቶቻችን ሃይማኖታቸው ነሽ። አምላክን የወለድሽና በድንግልና የታተምሽ ንጽሕት ሆይ የአብን ቃል ወለድሽልን። ኢየሱስ ክርስቶስ እኛን ለማዳን መጣ። ቅድስት ሆይ ለምኝልን" #ማብራሪያ :- 🔹🔸🔹እስራኤላውያን ተማርከው ፋርስ ባቢሎን በወረዱ ጊዜ የበለስ ቅጠል እንዲያመጣ በመምህሩ ኤርምያስ የታዘዘው አበሜሌክ በለሱን በሙዳይ አድርጎ ይዞ ሲመጣ ከመንገድ አንቀላፍቶት ተኛ ከስልሳ ስድስት ዘመን በኋላም ከእንቅልፉ ነቃ። ነቅቶ ሙዳዩን ቢከፍተው የበለሱ ቅጠል ሳይጠወልግ ደሙ ሳይደርቅ አገኘው። ይህች በለስ የእመቤታችን ምሳሌ ናት ከስልሳ ስድት ዓመት በኋላ የበለሷ ደም እንዳልደረቀ ቅጠሏም እንዳልጠወለገ ሁሉ እመቤታችንም በስልሳ ስድተኛው ትውልድ (ከአዳም እስከ እመቤታችን ሲቆጠር) ንጽሓ ጠባዕይ (የመጀመሪያ የሰው ንጽሕና) ሳያድፍባት ተገኝታለች። 🔹🔸🔹 ሰአሊ ለነ ቅድስት። እኛን ለማዳን ሰው ከሆነ ልጅሽ ጽንዕት በድንግልና ሥርጉት በቅድስና እመቤታችን ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሳን ለምኝልን አእምሮውን ማስተዋሉን በልቡናችን ሳይብን አሳድሪብን። ◊◈◊◈◊◈◊◈◊◈◊◈◊◈◊◈◊ ♦️🔹♦️ አንቲ እሙ ለብርሃን "አንቲ እሙ ለብርሃን ... ፤ የከበርሽ ጌታን የወለድሽ ሆይ የማይታይ ቃልን የተሸከምሽው የብርሃን እናቱ አንቺ ነሽ። እርሱን ከወለድሽው በኋላ በድንግልና ኖረሻልና በፍጹም ምስጋና ያገኑሻል። ቅድስት ሆይ ለምኝልን።" #ማብራሪያ :- 🔹🔸🔹 እመቤታችን ሁልጊዜም ድንግል ትባላለች እናትነቷ ድንግልናዋን ያላስቀረባት ድንግልናዋ ከእናትነት ያለገዳት ናትና። ♦️🔹♦️ አይ ልሳን "አይ ልሳን ዘይክል ነቢበ ... ፤ የአብ ቃል እናቱ ንጽሕት ድንግል ሆይ ስለ አንቺ የሚነገረውን ነገር መናገር የሚቻለው ምን አንደበት ነው። ኪሩቤል ለሚሸከሙት ንጉሥ ዙፊኑ (ማደሪያው) ሆንሽ። የተከበርሽ ሆይ እናመሰግንሻለን የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ እናቱ መልካሟ ርግብ ሆይ ስምሽን ለልጅ ልጅ እንጠራለን። ቅድስት ሆይ ለምኝልን።

  • #ማብራሪያ :- 🔹🔸🔹 እመቤታችን የመላእክት ደስታቸው ናት። ለነቢያት ትንቢት ያናገሩለትን ጌታን ወልዳላቸዋለችና። ዳግመኛም ንጽሕናዋን ቅድስናዋን ወላዲተ አምላክነቷን እያዩ ደስ ይላቸዋልና። 🔹🔸🔹 ሰአሊ ለነ ቅድስት። ሃያው ዓለማትን ከፈጠረ ልጅሽ ጽንዕት በድንግልና ሥርጉት በቅድስና እመቤታችን ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሳን ለምኝልን አእምሮውን ማስተዋሉን በልቡናችን ሳይብን አሳድሪብን። ◊◈◊◈◊◈◊◈◊◈◊◈◊◈◊◈◊ ♦️🔹♦️ ተፈሥሒ እስመ ድልወ "ተፈሥሒ እስመ ድልወ ተሰመይኪ ... ፤ በሚገባ የአምላክ እናት ተብለሻልና ደስ ይበልሽ። የሔዋን መድኃኒት ሆይ ደስ ይበልሽ ፍጥረቱን ሁሉ የሚመግበውን እሱን ጡትሽን አጥብተሽዋልና ደስ ይበልሽ። የሕያዋን የጻድቃን ሁሉ እናታቸው ሆይ ደስ ይበልሽ። ትለምኝልን ዘንድ ወደ አንቺ እናጋጥጣለን። ቅድስት ሆይ ለምኝልን። #ማብራሪያ :- 🔹🔸🔹 እመቤታችንን በሚገባ ወላዲተ አምላክ ተብለሻልኛ ሲላት በእውነት አምላክን የወለድሽ ነሽ ፣ የታመንሽ አምላክን የወለድሽ ነሽ ፣ ለእናትነት በቅተሽ ብትገኝ የአምላክ እናት ሆንሽ ማለቱ ነው። 🔹🔸🔹 የሔዋን መድኃኒት ማለቱ : ሔዋን ዕፀ በለስን በልታ ሞትን አምጥታ ነበር ሞቱም ለሁሉም ለሰው ልጆች (ለልጆቿ) ተረፈ በሰው ልጆች የተፈረደው ሞት የተወገደው ጌታ ከእመቤታችን ተወልዶ ስለሆነ እመቤታችን መድኃኒቱን ያስገኘችልን ምክንያተ ድኅነት ናትና የሔዋን መድኃኒቷ አለ። 🔹🔸🔹 ሰአሊ ለነ ቅድስት። ምልዕተ ጸጋ ምልዕተ ክብር ሆይ ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሳን ለምኝልን አእምሮውን ማስተዋሉን በልቡናችን ሳይብን አሳድሪብን። ◊◈◊◈◊◈◊◈◊◈◊◈◊◈◊◈◊ ♦️🔹♦️ ኦ ድንግል ኦ ቅድስት "ኦ ድንግል ኦ ቅድስት ኦ ወላዲተ እግዚእ ... ፤ ድንግል ሆይ ቅድስት ሆይ ጌታን የወለድሽ ሆይ እኛን ለማዳን ድንቅ ምሥጢር (ተዋሕዶ) በአንቺ ቢደረግ ንጉሥን ወልደሽልናልና ፍጥረታትን በልዩ ልዩ መልክ የፈጠረ የርሱን የገናንነቱን ነገር ፈጽመን መናገር አይቻለንምና ዝም እንበል። ቅድስት ሆይ ለምኝልን።" #ማብራሪያ :- 🔹🔸🔹 ፍጥረታትን በልዩ ልዩ መልክ የፈጠረ የርሱን የገናንነቱን ነገር ፈጽመን መናገር አይቻለንምና ዝም እንበል ማለቱ ፡ ➣ ሃያ ሁለቱን ስነ ፍጥረት የፈጠረ የእርሱን ሰው የመሆኑን (የሥጋዌውን) ነገር ፈጽመን ጠንቅቀን ወስነን እንዲህ ነው ብለን መናገር አይቻለንምና ዝም እንበል ሲል ነው። ➣#አንድም : በብዙ ወገን የተመሰለ (በእሳት ፣ በፀሐይ ፣ በቀላይ የተመሰለ) የእርሱን የአንድነቱን የሦስትነቱን ነገር ፈጽመን ጠንቅቀን ወስነን እንዲህ ነው ብለን መናገር አይቻለንምና ዝም እንበል። ➣#አንድም : ሰው መሆኑ አስቀድሞ በብዙ ትንቢት የተነገረ በብዙ አምሳል የተመሰለ የእርሱን የሥጋዌውን (ሰው የመሆኑን ነገር) ፈጽመን ጠንቅቀን ወስነን እንዲህ ነው ብለን መናገር አይቻለንምና ዝም እንበል ሲል ነው። ለእግዚአብሔር ቃል ሰው መሆን ከተነገሩት ትንቢቶችና ከተመሰሉት ምሳሌዎች መካከል #ትንቢት ➣ "በምድራቸን አበባ ታየ" መኃ 2:12 ➣ "ምድር ፍሬዋን ትስጥ" መዝ 85:12 ➣ "ንጉሥ ከአንቺ ይወጣል" ሚክ 5:2 ➣ "እነሆ ድንግል በድንግልና ፀንሳ በድንግልና ትወልዳለች" ኢሳ 7:14 #ምሳሌ ➣ በእሳትና በቅጠል ➺ ሙሴ ያየው ➣ በጠልና በፀምር ➺ ለጌዴዎን በተደረገው ➣ በኃያል ሰው ➺ ኢሳይያስ የመሰለው ➣ በሚያስፈራ አንበሳ ➺ ኤርምያስ የመሰለው ➣ በቆመ ደንጋይ ➺ ዳንኤል ባየው 🔹🔸🔹 ሰአሊ ለነ ቅድስት። ሥጋዌው በአምሳለ ነበልባል ወሐመልማል ፣ በአምሳለ ጠል ወፀምር ከተመሰለለት ልጅሽ ጽንዕት በድንግልና ሥርጕት በቅድስና እመቤታችን ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሳን ለምኝልን አእምሮውን ማስተዋሉን በልቡናችን ሳይብን አሳድሪብን። ◊◈◊◈◊◈◊◈◊◈◊◈◊◈◊◈◊ ➢➢ የቀጣይ ትምህርት #ክፍል_አምስት የማክሰኞ ውዳሴ ማርያም (ቃለ አብ ሕያው - ተፈሥሒ ኦ ማርያም)

  • የማክኞ ውዳሴ ማርያም ማብራሪያ #ክፍል_አራት ከአክሊለ - ኦ ድንግል ♦️🔹♦️ አክሊለ "አክሊለ ምክሕነ ... ፤ የመመኪያችን ዘውድ የድኅነታችን መጀመሪያ የንጽሕናችንም መሠረት እኛን ስለማዳን ሰው የሆነ የእግዚአብሔርን ቃል በወለደችልን በድንግል ማርያም ተገኘልን። ሰው ከሆነ በኋላም ፍጹም አምላክ ነው። ስለዚህም በድንግልና ወለደችው። ድንቅ የሆነ የመውለዷ ችሎታ የማይመረመር ሊነገር የማይቻል ነው። ቅድስት ሆይ ለምኝልን። #ማብራሪያ :- 🔹🔸🔹በዚህ ዕለት ከደናግል ኤልያስን ፣ ከመሳፍንት ኢያሱን ፣ ከነገሥታት ዳዊትን አስከትላ መጥታ ነበርና። ዳዊት ንጉሠ ነገሥት ብትባል የመመኪያችን ዘውድ ማምጣት አልተቻለህም። ኢያሱ መድኃኒት ብትባል የድኅነታችን መጀመሪያ መሆን አልተቻለህም። ኤልያስ ንጹሕ ድንግል ብትባል የንጽሕናችን መሠረት መሆን አልተቻለህም። የመመኪያችን ዘውድ የድኅነታችን መጀመሪያ የንጽሕናችንም መሠረት ድንግል ማርያም ናት። #አንድም የሰማዕታት አክሊላቸው ፣ የሕይወት መገኛ ፣ የዓለም መሠረት የሚባል ጌታ ከድንግል ማርያም ተገኘልን። 🔹🔸🔹 የእመቤታችን የስሟ ትርጓሜ : #ማርያም ማለት ➣ ፍጽምት ማለት ነው። ለጊዜው መልክ ከደም ግባት አስተባብራ ተገኝታለች። ፍጻሜው ግን ፤ ንጽሐ ሥጋ ፣ ንጽሐ ነፍስ ፣ ንጽሐ ልቡናን ፤ ድንጋሌ ሥጋ ፣ ድንጋሌ ነፍስ ፣ ድንጋሌ ልቡናን አስተባብራ ተገኝታለችና። ➣#አንድም : ጸጋ ወሀብት ማለት ነው። ለጊዜው ለእናት ለአባቷ ጸጋ ሁና ተሰጥታለች ፍጻሜው ግን ለሰው ሁሉ ጸጋ ሁና ተሰጥታለችና። ➣#አንድም : መርሕ ለመንግሥተ ሰማያት ማለት ነው። ምእመናንን መርታ ገነት መንግሥተ ሰማያት አግብታለችና። ➣#አንድም : ልዕልት ማለት ነው። ከፈጣሪ በታች ከፍጡራን በላይ ናትና። ➣#አንድም : የምእመናንና የሕዝብ አንድነት ፣ የሰውና የእግዚአብሔር ተላላኪ ፣ የእሥራኤል ቤትና የይሁዳ ቤት ደስታ ማለት ነው። ➣#አንድም : እግዝእተ ብዙኃን የብዙኃን እመቤት እናት ማለት ነው። 🔹🔸🔹 ሰው ከሆነ በኋላም ፍጹም አምላክ ነው ማለቱ መናፍቃን ቃል ሥጋ ሆነ ያለውን ይዘው ተለወጠ ብለው ነበርና ፍጹም አምላክ ነው አለባቸው። የእመቤታችን የመውለዷ ነገር ፍጡር ሊመረምረው አይችልም። በግብረ መንፈስ ቅዱስ ነውና። የመንፈስ ቅዱስ ሥራ ደግሞ ፈጣሪ እንጂ ፍጡር ሊያውቀው ሊረዳው አይቻለውምና። 🔹🔸🔹 ሰአሊ ለነ ቅድስት። በማይመረመር ግብር ከወለድሽው ልጅሽ ጽንዕት በድንግልና ሥርጉት በቅድስና እመቤታችን ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሳን ለምኝልን አእምሮውን ማስተዋሉን በልቡናችን ሳይብን አሳድሪብን። ◊◈◊◈◊◈◊◈◊◈◊◈◊◈◊◈◊ ♦️🔹♦️ እስመ በፈቃዱ "እስመ በፈቃዱ ወበሥምረተ አቡሁ ... ፤ በእርሱ ፈቃድ በአባቱም ፈቃድ በመንፈስ ቅዱስም ፈቃድ መጥቶ አዳነን። በድንግልና ፍጽምት የሆንሽ ማርያም ሆይ የድንግልናሽ ምስጋናና ክብር ታላቅ ነው። እግዚአብሔር ካንቺ ጋር ቢሆን ባለሟልነትን አግኝተሻልና። ያዕቆብ ከምድር እስከ ሰማይ ደርሳ የእግዚአብሔር መላእክት ሲወጡባት ሲወርዱባት ያያት መሰላል አንቺ ነሽ። ቅድስት ሆይ ለምኝልን። #ማብራሪያ :- 🔹🔸🔹 ጌታ ሰው መሆኑ በእርሱ ፈቃድ በአባቱ ፈቃድ በመንፈስ ቅዱስ ፈቃድ ነው። ሦላሴ በፈቃድ አንድ ናቸውና። "ውእቱ ወልድ ዘኀደረ ውስተ ከርሠ ድንግል በፈቃደ አቡሁ ወበሥምረተ መንፈስ ቅዱስ። እስመ አሐቲ ይእቲ ሥምረት ዘሥሉስ ቅዱስ። የሥላሴ ፈቃድ አንዲት እንደመሆኗ በአባቱ ፈቃድ በመንፈስ ቅዱስ ፈቃድ በድንግል ማኅፀን ያደረ ወልድ ነው።" እንዳለ ሳዊ. ሃይ.አበ 84÷11 🔹🔸🔹 ያዕቆብ በሎዛ ያያት መሰላል አንቺ ነሽ ማለቱ መሰላሉ የእመቤታችን ምሳሌ ስለሆነ ነው። "እነሆም መሰላል በምድር ላይ ተተክሎ፥ ራሱም ወደ ሰማይ ደርሶ፥ እነሆም የእግዚአብሔር መላእክት ይወጡበት ይወርዱበት ነበር።" (ዘፍ 28:12) ➣የወርቅ መሰላል የእመቤታችን ምሳሌ። ➣ መሰላሉ የቆመበት ደንጋይ የነቢያት ትንቢት ምሳሌ። መሰላሉ በደንጋዩ ላይ ጸንቶ መታየቱ እመቤታችን በነቢያት ትንቢት ጸንታ ለመገኘቷ ምሳሌ። ➣ ዙፋን የመኅፀኗ። በዙፋኑ የተቀመጠው ንጉሥ የጌታ ምሳሌ። ➣መላእክት ሲወጡ ሲወርዱ ማየቱ ጌታችን ከእመቤታችን በተወለደ ጊዜ ለምስጋና ለተልእኮ የሚወጡ የሚወርዱ ሁነዋልና። 🔹🔸🔹 ሰአሊ ለነ ቅድስት። ያዕቆብ በፍኖተ ሎዛ በአምሳለ ንጉሥ ካየው ልጅሽ ጽንዕት በድንግልና ሥርጉት በቅድስና እመቤታችን ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሳን ለምኝልን አእምሮውን ማስተዋሉን በልቡናችን ሳይብን አሳድሪብን። ◊◈◊◈◊◈◊◈◊◈◊◈◊◈◊◈◊ ♦️🔹♦️ አንቲ ውእቱ ዕፅ "አንቲ ውእቱ ዕፅ ... ፤ ሙሴ በነደ እሳት ሳትቃጠል ያያት ዕፅ አንቺ ነሽ ይኸውም መጥቶ በማኅፀንሽ ያደረው የእግዚአብሔር ልጅ ነው። የመለኮቱ እሳትነት ሥጋሽን አላቃጠለውም። ቅድስት ሆይ ለምኝልን። #ማብራሪያ :- 🔹🔸🔹እመቤታችንን ሙሴ ያያት ዕፅ ማለቱ ምሳሌዋ ስለሆነ ነው። "እነሆም ቍጥቋጦው በእሳት ሲነድድ ቍጥቋጦውም ሳይቃጠል አየ። " (ዘጸ 3:2) ➣ ሐመልማሉ (ቅጠሉ የእመቤታችን) ፡ እሳቱ የጌታ ምሳሌ ሲሆን። እሳቱ ቅጠሉን ሳያቃጥለው ማየቱ እመቤታችን ጌታን በፀነሰች ጊዜ እሳተ መለኮቱ አላቃጠላትም። "ድንግል ሆይ እሳተ መለኮት በሆድሽ ውስጥ ባደረ ጊዜ እንደምን አላቃጠለሽም" እንዳለ። አባ ሕር 🔹🔸🔹 ሰአሊ ለነ ቅድስት። ሙሴ በእሳትና በቅጠል አምሳል ካየው ልጅሽ ጽንዕት በድንግልና ሥርጉት በቅድስና እመቤታችን ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሳን ለምኝልን አእምሮውን ማስተዋሉን በልቡናችን ሳይብን አሳድሪብን። ◊◈◊◈◊◈◊◈◊◈◊◈◊◈◊◈◊ ♦️🔹♦️ አንቲ ውእቱ ገራኅት "አንቲ ውእቱ ገራኅት ... ፤ ዘር ያልተዘራባት እርሻ አንቺ ነሽ። የሕይወት ፍሬ ከእንቺ ወጣ። ዮሴፍ የዋጃትና የከበረ ዕንቍን ያገኘባት ሣጥን አንቺ ነሽ። ይኸውም መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው ። በማኅፀንሽ አደረ በዚህ ዓለምም ወለድሽው። ቅድስት ሆይ ለምኝልን። #ማብራሪያ :- 🔹🔸🔹 እመቤታችንን በማክሰኞ እርሻ ይመስላታል ያቺ ዘር ሳይዘራባት "ምድር ታብቅል" ባለው ቃል ብቻ አትክልትን ፣ አዝእርትን ፣ ዕፅዋትን እንዳስገኘች እመቤታችንም ትፀንሻለሽ ያለውን ቃል ብቻ ከመልአኩ በመስማት አካላዊ ቃልን አስገኝታለች። 🔹🔸🔹 ዮሴፍ የተወዳጃት ሣጥን የተባለች እመቤታችን ናት። ያቺ ሣጥን በቁልፍ የተቆለፈችና በውስጧ ዕንቍ ያለባት ናት። ቍልፉ የእመቤታችን የማኅተመ ድንግልናዋ ፤ በውስጧ ያለው ዕንቍ የጌታ ምሳሌ ነው። 🔹🔸🔹 ሰአሊ ለነ ቅድስት። በዕንቍ ከተመሰለው ልጅሽ ጽንዕት በድንግልና ሥርጉት በቅድስና እመቤታችን ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሳን ለምኝልን አእምሮውን ማስተዋሉን በልቡናችን ሳይብን አሳድሪብን። ◊◈◊◈◊◈◊◈◊◈◊◈◊◈◊◈◊ ♦️🔹♦️ ተፈሥሒ ኦ ወላዲተ እግዚእ "ተፈሥሒ ኦ ወላዲተ እግዚእ ... ፤ የመላእክት ደስታቸው የሆነ ጌታን የወለድሽ ሆይ ደስ ይበልሽ። የነቢያት ዜናቸው ንጽሕት ሆይ ደስ ይበልሽ። እግዚአብሔር ከአንቺ ጋር ቢሆን ባለሟልነትን አግኝተሻልና ደስ ይበልሽ። የዓለም የሰው ሁሉ ደስታ የሆነ የመልአኩን ቃል ተቀብለሻልና ደስ ይበልሽ። ዓለምን ሁሉ የፈጠረ ጌታን የወለድሽ ሆይ ደስ ይበልሽ። ቅድስት ሆይ ለምኝልን።

  • ††† እንኩዋን ለጻድቃን ቅዱሳን #አባ_አብርሃም: #ቅዱስ_ዮሐንስ እና #አባ_ፊልዾስ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ††† ††† #አባ_አብርሃም_ክቡር ገዳማዊ ††† =>ጻድቁ ግብጻዊ ሲሆን በ4ኛው መቶ ክ/ዘ ከተነሱ ከዋክብት አንዱ ነው:: #ክርስቲያን ወላጆቹ በሥርዓት አሳድገው "ሚስት አግባ" አሉት:: እሺ እንዳይላቸው ከልጅነቱ ጀምሮ የተመኘው ምናኔ ሊቀርበት ሆነ:: እንቢ እንዳይላቸው ደግሞ ወላጆቹ ያዝናሉና የልቡን በልቡ ይዞ "እሺ" አላቸው:: +ሠርግ ተደግሶ: #ተክሊል ተደርሶ: ከአንዲት ክርስቲያን ጋር አጋቡት:: በጋብቻው ማግስት ግን ከነ ድንግልናው ጠፍቶ በርሃ ገባ:: በዚያም አንዲት በዓት አዘጋጅቶ ፈቃደ ሥጋውን እየቀጣ: ፈቃደ ነፍሱን እያለመለመ ለ10 ዓመታት ተቀመጠ:: +በነዚያ ሁሉ ዘመናት የሞቀ አልለበሰም: የላመ የጣመ ነገር አልበላም:: የፀሐይ ብርሃን እንኩዋ አልተመለከተም:: በዚያ ወራትም ወሬ ነጋሪ ወደ በዓቱ መጥቶ "ወላጆችህ ዐረፉ:: በቤት ውስጥ ከ6 ዓመት እህትህ ከማርያ በቀር ማንም የለምና የወላጆችህን ሃብት ውረስ" አለው:: +አባ አብርሃም የሚያደርገውን ያውቃልና ከበርሃ ወጥቶ ወደ ሃገር ቤት ሔደ:: ትንሽ እህቱን (6 ዓመቷ ነበር) ለቤተ ዘመድ አደራ ሰጥቶ: ሃብት ንብረቱን አንድ ሳያስቀር ለነዳያን በትኖ:ወደ በዓቱ ተመለሰ:: በዚያም እንዳስለመደ በጾምና ጸሎት ተወስኖ ለ10 ዓመታት ቆየ:: +ተጋድሎ በጀመረ በ20 ዓመቱ #እግዚአብሔር ለሌላ አገልግሎት ጠራው:: የግብጽ ሊቀ ዻዻስ #አባ_አብርሃምን አስመጥቶ ቅስናን ሾመውና "ሒደህ ወንጌልን ስበክ" አለው:: ችግሩ እርሱ የተላከባት ሃገር አንድም ክርስቲያን የሌለባት ከመሆኗ በባሰ እጅግ ጨካኝ ናቸው:: +ማንም ደፍሮ በዚያ ሃገር ውስጥ ነገረ እግዚአብሔርን የሚናገር ሰው አልነበረም:: አባ #አብርሃም ወደ ሃገር ገብቶ ወንጌልን ቢሰብክላቸው እንደ ልማዳቸው መሬት ላይ ጥለው ደበደቡት: አጥንቶቹንም ሰባበሩት:: ሞቷል ብለው ከከተማ ውጪም ጣሉት:: +እርሱ ግን በፈጣሪው ኃይል ጸንቶ ተነሳ:: ማስተማሩ ብቻውን መፍትሔ እንደማይሆን ተረድቷልና ስለ እነሱ ተግቶ ይጸልይ ጀመር:: አሕዛብ ጠዋት ቢመጡ በከተማዋ መሐል ላይ ሲጸልይ አገኙት:: ስለ ተናደዱ ድጋሚ አካሉን በዱላ ሰባብረው እየጐተቱ ከከተማ አስወጡት:: በዚያም ከነ ሕይወቱ ቀበሩት:: +ነገር ግን ጠዋት ሲመለሱ እዛችው ቦታ ላይ ሲጸልይ አገኙት:: ይሕ የሚደረገው ለእነርሱ ድኅነት መሆኑን አልተረዱምና እነርሱ በየቀኑ እየደበደቡና እያሰቃዩት እርሱ ስለ እነሱ እየጸለየ 10 ዓመታት አለፉ:: ቅዱሳን ተስፋ አይቆርጡምና በመጨረሻው ተሳካለት:: +የቅዱሱ የዘመናት ጸሎት ፍሬ አፍርቶ እግዚአብሔር በአሕዛብ ልቡና ያደሩ አጋንንትን አራቀለት:: አንድ ቀን ጠዋት የሃገሩ ሕዝብ ሁሉ (ወንዱ: ሴቱ: ትልቁ: ትንሹ) ወደ ጻድቁ መጸለያ መጡ:: ለእርሱስ የጠብ መስሎት ነበር:: እነርሱ ግን በአንድነት በፊቱ ተንበርክከው ሰገዱ:: ይቅር እንዲላቸውም ለመኑት:: +ቅዱሱ ይሕንን ሲመለከት ሐሴትን አደረገ:: ሁሉንም #በስመ_ሥላሴ አጥምቆ ክርስቲያን አደረጋቸው:: አብያተ ክርስቲያናትንም አነጸላቸው:: በሁዋላ ግን በጣም ሲወዱትና ሲያከብሩት ተመልክቷልና ከውዳሴ ከንቱ (#ስብሐት_ብጡል) መለየት ፈለገ:: ፈጣሪንም በቸርነቱ እንዲጠብቃቸው ለምኖ: በሌሊት ጠፍቶ ወደ ነበረበት በርሃ ገባ:: +እርሱ በበርሃ ሁኖ ስለ ትንሽ እህቱ #ማርያ ያስብ ነበርና አስጠራት:: "ምን ትፈልጊያለሽ?" አላት:: እርሷም "እንዳንተ መሆን" ስላለችው አስተምሮ: ፈትኖ አመነኮሳት:: ለጥቂት ዓመታት በሥርዓት ከኖረች በሁዋላ ግን ችግር ተፈጠረ:: +ከአንድ መነኩሴ ጋር በነበራት ያልተገባ ቅርርብ የዝሙት ፍላጐታቸውን መቆጣጠር ባለመቻላቸው በኃጢአት ወደቁ:: በዚህ ተስፋ ቆርጠው 2ቱም ቆባቸውን ጥለው ከተማ ገቡ:: ይልቁኑ እርሷ (ማርያ) ሴተኛ አዳሪ ሆነች:: +በዚያ ሰሞን ቅዱሱ አብርሃም ራዕይን ያያል:: ትልቅ ዘንዶ አንዲት ርግብን ሲውጣት: መልሶም ሲተፋት አይቶ እሕቱ መሆኗን ተረዳ:: ወዲያው ጥሩ ልብስና ፈረስ ተውሶ ተነሳና ወደ ከተማ ገባ:: የጦር መኮንን መስሎ እህቱ ቤት ገባ:: +ሸሽታ እንዳታመልጠው ቤቱን ዘጋና ራሱን ገለጠላት:: ደንግጣ እንደ በድን ብትሆንም እርሱ አረጋጋት:: "እህቴ! ንስሃ ግቢ: አምላክ ይራራልሻል" አላት:: ልቧ ወደ ምክሩ አዘንብሏልና የእህቱን ነፍስ ማርኮ ወደ ገዳም ተመለሰ:: +በዚያ በዓት ሠርቶላት: ቀኖናም ሰጥቷት ሔደ:: #ማርያም ስለ ኃጢአቷ ፈንታ የምትገርም የቅድስና ሰው ሆነች:: ያየ ሁሉ እየተደነቀባት ከዓመታት ተጋድሎ በሁዋላ ዐረፈች:: አባ አብርሃም በተረፈ ዘመኑ በንጹሕ ገዳማዊ ሕይወት ተጠምዶ ኑሯል:: +በዘመኑ ሁሉ በጥርሱ ስቆ: በከንፈሩም አልባሌ ነገርን ተናግሮ አያውቅም:: ልቡ በፈጣሪው ፍቅር የታሠረ ነበርና ሕማማተ ክርስቶስን እያሰበ እንባው ያለማቁዋረጥ ይፈስ ነበር:: ደግና ቅዱስ ሰው አብርሃም በዚህች ቀን ዐርፎ ተቀብሯል:: ††† #ቅዱስ_ዮሐንስ_ጻድቅ ††† =>ይህ ቅዱስ የነበረው በዘመነ ሰማዕታት ቢሆንም እንደ ሰማዕታት ስቃይ አልደረሰበትም:: ክርስቲያኖችን እንዲገድሉና አብያተ ክርስቲያናትን እንዲያቃጥሉ ከተመደቡ ወታደሮች አንዱ ነበረ:: ታዲያ እንዲገድላቸው የሚሰጡትን ክርስቲያኖች እየወሰደ ይደብቃቸው ነበር:: +የመከራው ዘመን እስኪያልፍ ድረስም ይንከባከባቸው ነበር:: ሌሎች ወታደሮች እንዳይነቁበት ሁሌም "ክርስቲያኖችን በጣም እጠላለሁ" እያለ ያወራ ነበር:: እርሱ በሌሊት ሁሌም ለጸሎት ይተጋ ነበር:: በእንዲህ ያለ ግብር ኑሮም በዚህች ቀን በሰላም ዐርፏል:: ††† #አባ_ፊልዾስ #ዘደብረ_ቢዘን ††† =>#ደብረ_ቢዘን በቀድሞ የኢትዮዽያ ክፍለ ሃገር (አሁን #ኤርትራ) ውስጥ የሚገኝ ታላቅ ገዳም ነው:: ገዳሙ #እመቤታችን_ድንግል_ማርያም በስደቷ ያረፈችበት: ጌታችን የባረከውና የመረጠው ቦታ ነው:: #አባ_ዮሐንስን: #አባ_ናርዶስንና ሌሎች ከዋክብት አበውን ያፈራ ሲሆን የአባ ፊልዾስን ያሕል ግን አልተገኘም:: +ጻድቁ በግል የተጋድሎ ሕይወታቸው: ገዳሙን በአበ ምኔትነት በመምራታቸውና በስብከተ ወንጌል አገልግሎታቸው ምስጉን ነበሩ:: እርሳቸው ቅዱስ ሆነው አልበቃቸውምና ብዙ ቅዱሳንን ወልደዋል:: ይሕች ዕለትም የዕረፍታቸው መታሰቢያ ናት:: =>አምላከ ጻድቃን ገዳማትን ከመከራ ይጠብቅልን:: ከአባቶቻችን ቅዱሳን ጸጋ በረከትንም ይክፈለን:: =>ነሐሴ 5 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት= 1.ቅዱስ አባ አብርሃም ገዳማዊ 2.ቅድስት ማርያ እህቱ 3.ቅዱስ ዮሐንስ ጻድቅ 4.አባ ፊልዾስ ዘደብረ ቢዘን =>ወርሐዊ በዓላት 1.ቅዱስ ዼጥሮስ ሊቀ ሐዋርያት 2.ቅዱስ ዻውሎስ ብርሃነ ዓለም 3.አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ 4.ቅዱስ ዮሐኒ ኢትዮዽያዊ 5.ቅዱስ አሞኒ ዘናሒሶ 6.ቅድስት አውጋንያ (ሰማዕትና ጻድቅ) =>+"+ በድካም: አብዝቼ በመገረፍ: አብዝቼ በመታሠር: አትርፌ በመሞት ብዙ ጊዜ ሆንሁ:: በድካምና በጥረት: ብዙ ጊዜም እንቅልፍ በማጣት: በራብና በጥም: ብዙ ጊዜም በመጦም: በብርድና በራቁትነት ነበርሁ. . . የቀረውን ነገር ሳልቆጥር ዕለት ዕለት የሚከብድብኝ የአብያተ ክርስቲያናት ሁሉ አሳብ ነው:: +"+ (2ቆሮ 11:23) <<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>

  • без подписи

  • 👉 ወር በገባ በየአራት ቀኑ ከቅዱስ ዮሐንስ ወልደ ነጎድጓድ ጋር እመቤታችን አብረን እናስባታለን ከመስቀሉ ሥር ትውልዱን ወክሎ ከክርስቶስ መረከቡን እራሱ 26. ኢየሱስም እናቱን ይወደው የነበረውንም ደቀ መዝሙር በአጠገቡ ቆሞ ባየ ጊዜ እናቱን። አንቺ ሴት፥ እነሆ ልጅሽ አላት። 27. ከዚህ በኋላ ደቀ መዝሙሩን። እናትህ እነኋት አለው። ከዚህም ሰዓት ጀምሮ ደቀ መዝሙሩ ወደ ቤቱ ወሰዳት። ዮሐ 19:26-በማለት ጽፎልናል እሱን እናስባለን 👉👉የከበረ ስጦታ ( ማርያም ) እመቤታችን ስንት ጊዜ ተሰጠች 👉አንደኛ ከብዙ ጸሎት እና ልመና ደጅ ጥናት በኋላ እግዚአብሔር ለሐና እና ለኢያቄም የሰጣቸውን ድንቅ ሶጦታ ሐና እና ኢያቄምም መልሰው ለእግዚአብሔር ሰጥተዋታል 👉ሁለተኛ በቤተመቅደስ በሶስት ዓመትዋ ለእግዚአብሔር ስጥተዋታል እግዚአብሔርም በካህኑ በዘካርያስ እጅ ተቀብሎዋታል 👉ሶስተኛ አስራ ሁለት ዓመት በቤተመቅደስ ከኖረች በኋላ አይሁድ በቅናት ተነሳስተው ከቤተመቅደስ ትውጣልን በአሉ ጊዜ ለአረጋዊው ዮሴፍ አደራ ጠብቅ ተብሎ ተሰጥቶታል ማቴ 1:20: እርሱ ግን ይህን ሲያስብ፥ እነሆ የጌታ መልአክ በሕልም ታየው፥ እንዲህም አለ፦ የዳዊት ልጅ ዮሴፍ ሆይ፥ ከእርስዋ የተፀነሰው ከመንፈስ ቅዱስ ነውና እጮኛህን ማርያምን ለመውሰድ አትፍራ። 👉አራተኛ በሶስት ዓመትዋ ከሐና እና ከኢያቄም የተቀበላትን በአርባ ዘጠኝ ዓመትዋ በመስቀል እነሆ እናቴ እናት ትሁናችሁ ብሎ ለዮሐንስ ወልደ ነጎድጓድ ሰጦቶታል ለአራተኛ ጊዜ እመቤታችን ተሰጥታለች ድንግል ማርያም በሁለት ነገር እግዚአብሔር አብን ትመስላለች 👉አንደኛ እግዚአብሔር አብ ቅድመ ዓለም ያለ እናት የወለደውን ድንግል ማርያም ድህረ ዓለም ያለ አባት በመውለድ እግዚአብሔር አብን ትመስላለች 👉ሁለተኛ በደብረታቦር እነሆ ልጄን ስሙት እንዳለ እርስዋም በቃና ዘገሊላ ልጄ የሚላችሁን ስሙት በማለት እግዚአብሔር አብን መስላለች ሐና እና ኢያቄም አንድ ልጃቸውን በመስጠት አንድ ልጁን ለቤዛ ዓለም የሰጠንን እግዚአብሔር አብን መስለዋል - ዮሐ 3:16: በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና። አብርሃም አንድ ልጁን በመስጠቱ እግዚአብሔር አብን ይመስላል ይስሐቅ ወደ ተሰዋበት ተራራ ስንሄድ ምስጢራዊ ትርጉሙ የሚያስተምረን ይህን ነው አብርሃም የእግዚአብሔር አብ ምሳሌ ይስሐቅ የዓለም ምሳሌ የሞርያ ተራራ የቀራንዮ ምሳሌ ይስሐቅ የታሰረበት ኃረግ የመስቀል ምስሌ ቢላዋ የችንካር ምሳሌ ሁኖ እናገኘዋለን 👉ቅዱሳን በተለየ ሕይወታቸው እግዚአብሔር አብን መሰሉ እኛስ ማንን ነው የምንመስለው ሕይወታችን ማን ይመስላል እኛ እኮ ፍላጎታችንን ለእግዚአብሔር መተው አልቻልንም ሁሉ ነገራችን ከእግዚአብሔር መንገድ የራቀ ነው እግዚአብሔር ወደ መስመሩ ይመልሰን አሜን የእናታችን በረከት ይደርብን🙏🙏🙏🙏🙏🙏

  • ††† ✝እንኳን ለጻድቅ ንጉሥ ሕዝቅያስ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። †††✝ ††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! ††† †††✝ ቅዱስ ሕዝቅያስ✝ ††† ††† ቅዱስ መጽሐፍ እንደ ነገረን ከመድኃኒታችን ክርስቶስ ልደት ሰባት መቶ ዓመታት በፊት ሕዝቅያስ የሚባል ንጉሥ በይሁዳ ላይ ነግሦ ነበር:: ደጋጉ ዳዊትና ሰሎሞን ካረፉ በኋላ የሕዝቅያስን ያክል ቅን እና የእግዚአብሔር ሰው በእሥራኤል ላይ አልነገሰም:: ንጉሡ ጣዖት አምልኮን ነቃቅሎ አጥፍቶ ሕዝቡ እግዚአብሔርን ብቻ እንዲያመልክ አድርጐም ነበር:: ነገር ግን ቅዱስ ሕዝቅያስ በነገሠ በ14ኛው ዓመት የአሕዛብ (የአሦር) ንጉሥ ሰናክሬም በጠላትነት ተነሳበት:: ወደ አካባቢውም መጥቶ: ከቦ አስጨነቀው:: ሰናክሬም በጦር እጅግ ኃይለኛ ነበር:: በዚያውም ላይ ጦር የሚመዙ ከመቶ ሰማንያ አምስት ሺ በላይ ብርቱ ተዋጊዎች ነበሩትና ሕዝቅያስ እንደማይችለው ተረድቶ መልእክተኛ ላከበት:: "እገብርልሃለሁ: የፈለግከውንም እሰጥሃለሁ:: ነገር ግን ሃገሬን አታጥፋ:: ኢየሩሳሌምን አታቃጥል: ሕዝቤንም አትግደል" በሚል ለመነው:: እጅ መንሻ ግብሩንም ከከተማዋ የተገኘውን ወርቅና ብር ሁሉ ጭኖ ላከለት:: ሰናክሬም ግን ሰይጣን ያደረበት ነውና የሕዝቅያስን ልመና ወደ ጐን ብሎ የእሥራኤልን አምላክ: ቅዱስ ስሙንም ተገዳደረ:: ለሕዝቅያስም "ከእኔ እጅ የሚያድንህ ማነው? ሕዝቡንም እግዚአብሔር ያድናል ብለህ አታታልላቸው" ሲል ላከበት:: ቅዱስ ሕዝቅያስ በዚህ ጊዜ የፈጣሪው ስም ሲቃለል ሰምቷልና ፈጽሞ አዘነ:: መልእክተኞችን ወደ ነቢዩ ቅዱስ ኢሳይያስ ልኮ እርሱ ወደ ቤተ መቅደስ ገባ:: በእግዚአብሔር ፊት ልብሱን ቀድዶ ማቅ ለበሰ:: ስለ ኢየሩሳሌምና ሕዝቡም ፈጽሞ አለቀሰ:: በዚህ ጊዜ እግዚአብሔር የሰናክሬምን መገዳደርና የሕዝቅያስን ልመና ሰምቷልና በኢሳይያስ አንደበት እንዲሕ አለ:- "ስለ ባሪያዬ ስለ ዳዊት ከተማዋን አድናታለሁ::" በዚያች ሌሊትም ድንቅ መልአክ ቅዱስ ሚካኤል ከሰማያት በግርማ ወረደ:: ወደ ሰናክሬም የጦር ሠፈር ደርሶ አንድ ጊዜ የእሳት ሰይፉን መዝዞ ቢያሳያቸው ከአሕዛብ ሠራዊት መቶ ሰማንያ አምስት ሺ ኃያላን እንደ ቅጠል ረገፉ:: በለኪሶ የነበረው ሰናክሬም በጧት ቢነሳ ሠራዊቱ ሁሉ ወደ አስከሬን ክምር ተቀይሯል:: በድንጋጤ ወደ ነነዌ ሒዶ ወደ ጣዖት ቤቱ ሲገባ የራሱ ልጆች (አድራማሌክና ሳራሳር) ገደሉት:: ትዕቢተኛው ሰናክሬም ለአሕዛብ ሁሉ መዘባበቻ ሆነ:: ቅዱስ ሕዝቅያስ ግን በፈጣሪው ታምኗልና ቅዱስ ሚካኤል ሞገስ ሆኖት የዓለም ነገሥታት ሁሉ ፈሩት:: (1ነገ. 18:13, 19:1) ቅዱስ ሕዝቅያስ የነሐስ እባቡን በማጥፋቱ: ሕዝቡን ወደ አምልኮተ እግዚአብሔር በመመለሱ ቢደነቅም ሰው ነውና አንዲት ጥፋት አጠፋ:: በዘመኑ ታላቁ ነቢይ ልዑለ ቃል ኢሳይያስ ነበረና ሐረገ ትንቢትን ያፈስ ነበር:: ከተናገራቸው ትንቢቶችም አንዱ "ድንግል ትጸንሳለች: ወንድ ልጅም ትወልዳለች" የሚል ነበር:: (ኢሳ. 7:14) በወቅቱ የነበሩ አንዳንድ ክፉ መካሪዎች ቀርበው ንጉሡን በውዳሴ ከንቱ ጠለፉት:: "ንጉሥ ሆይ! ሺህ ዓመት ንገሥ:: እንዳንተ ያለ ማንም የለም:: ነቢዩ የተናገረው ትንቢትም እኮ ላንተ ነው:: "ድንግል" የተባለች ኢየሩሳሌም ስትሆን "ወልድ-ወንድ ልጅ" የተባልክ ደግሞ አንተ ነህ" አሉት:: ይሕንን ጠማማ ትርጉም እህ ብሎ የሰማቸው ቅዱስ ሕዝቅያስ አልወቀሳቸውም:: ይልቁኑ ልቡ ወደ እነሱ አዘነበለ እንጂ:: በዚህ ምክንያት እግዚአብሔር ተቆጥቶ ኢሳይያስን ላከው:: ነቢዩም በቀጥታ መጥቶ ንጉሡን አለው:- "ትሞታለህ እንጂ አትተርፍምና ቤትህን ሥራ::" ወዲያውኑ ሕዝቅያስ ታመመ: ደከመ:: ነገር ግን ፊቱን ወደ ቤተ መቅደስ አዙሮ ሊያዝን: ሊተክዝም ጀመረ:: አባቶቻችን ለየት የሚያደርጋቸው ይኼ ነው:: በቅድስና ኑረው: ሰው ናቸውና ይሳሳታሉ:: ነገር ግን ንጹሕና ፍጹም ንስሐን ከማቅረብ አያቋርጡም:: ንጉሡ ቅዱስ ሕዝቅያስ ወደ ፈጣሪ:- "ጌታ ሆይ! እንደ ቸርነትህ በፊትህ በቅን መንገድ መሔዴን አስብና ይቅር በለኝ" ሲል ተማጸነ:: ይህ ሲሆን ቅዱስ ኢሳይያስ ገና ከንጉሡ አካባቢ አልራቀም ነበርና የእግዚአብሔር ቃል ወደ እርሱ መጣ:: ሕዝቅያስን በለው:- "ጸሎትህን ሰምቼ: ስለ ባለሟሌ ስለ ዳዊት ብዬ ምሬሐለሁ:: በዘመንህም ላይ አሥራ አምስት ዓመታትን ጨምሬልሃለሁ በለው" አለው:: ነቢዩም ወደ ንጉሡ ተመልሶ ይሕንኑ ነግሮ "እስከ ሦስት ቀን ድረስ ወደ ቤተ መቅደስ ድነህ ትመለሳለህ" አለው:: ቅዱስ ሕዝቅያስ "ይሕ እንደሚደረግ በምን አውቃለሁ?" አለው:: (ተጠራጥሮ ግን አይደለም: ድንቅ ተአምር ይገለጥ ዘንድ ነው እንጂ) ኢሳይያስም ፀሐይን ዓለም እያየ አሥር መዓርጋትን ወደ ኋላ መለሳት:: በወቅቱ ይህ ተአምር በመላው ዓለም ታይቶ: ተሰምቶም ነበርና ሕዝቅያስ ከፍ ከፍ አለ:: በቅን የሔደ: እግዚአብሔርም የወደደው እንዲህ ነው:: የዓለም ነገሥታት ሁሉ ለሕዝቅያስ አዘነበሉ: ገበሩለትም:: ለእርሱ ጌታ ድንቅ ነገርን አድርጐለታልና:: ቅዱስ ሕዝቅያስ በተጨመሩለት ዘመናት ሁሉ እግዚአብሔርን አመለከ:: በፊቱም በቅን ተጓዘ:: ከክርስቶስ የዘር ሐረግም በቀጥታ ተቆጠረ:: (ማቴ.1:10) ለአሥራ አምስት ዓመታት ሕዝቡን አስተዳድሮ በዚህች ቀን እድሜ ጠግቦ ዐርፏል:: በእርሱ ዙፋን ላይም ልጁ ምናሴ ተተክቷል:: ††† ✝አባ ማቴዎስ ገዳማዊ✝ ††† ††† እኒህ ቅዱስ ሰው በ4ኛው መቶ ክ/ዘ ፋርስ አካባቢ የነበሩ ጻድቅ ናቸው:: በወቅቱ ምንኩስና በአካባቢው ባለመስፋፋቱ ወደ ዱር እየወጡ የሚኖሩ አበው ነበሩና አባ ማቴዎስ አንዱ ናቸው:: እርሳቸው በበርሃ ልብሳቸው አልቆ አካላቸው የሚሸፈነው በጸጉራቸው ነበር:: የአቶር ንጉሥ የሰናክሬም ልጅ መርምሕናምን(እጅግ ታላቅ ሰማዕት ነው) ያሳመኑትና ያጠመቁት እርሳቸው ናቸው:: እኅቱን ሣራንም ከለምጿ አንጽተው ወደ ክርስትና መልሰዋል:: በዚህ ምክንያትም የፋርስ አውራጃ የሆነችው አቶር በሙሉ የክርስቲያኖች ቤት ሆናለች:: አባ ማቴዎስ ከዘመናት ተጋድሎ በኋላ በዚህች ቀን ዐርፈዋል:: ††† አምላከ ቅዱሳን እድሜ ለንስሐ: ዘመን ለፍስሃ አይንሳን:: የጻድቃኑ በረከትም ይደርብን:: ††† ነሐሴ 4 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት 1.ቅዱስ ሕዝቅያስ ጻድቅ (ንጉሠ ይሁዳ) 2.አባ ማቴዎስ ገዳማዊ 3.ቅዱስ ዳዊት ሰማዕት ††† ወርኀዊ በዓላት 1.ቅዱስ ዮሐንስ ወልደ ነጎድጓድ (ወንጌላዊው) 2.ቅዱስ እንድርያስ ሐዋርያ 3.ቅድስት ሶፍያ ሰማዕት 4.ቅዱስ ዮሐንስ ዘሐራቅሊ (ሰማዕት) ††† "አቤቱ በኃይልህ ንጉሥ ደስ ይለዋል:: በማዳንህ እጅግ ሐሴትን ያደርጋል:: የልቡን ፈቃድ ሰጠኸው:: የከንፈሩንም ልመና አልከለከልኸውም:: በበጐ በረከት ደርሰህለታልና:: ከከበረ ዕንቁ የሆነ ዘውድን በራሱ ላይ አኖርህ:: ሕይወትን ለመነህ ሰጠኸውም:: ለረጅም ዘመን ለዘላለሙ:: በማዳንህ ክብሩ ታላቅ ነው::" ††† (መዝ. ፳፥፩-፭) ††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††