ከበላይሁን ግጥሞች
Статистикаይህ ሁለተኛው ቻናሌ ነው። የመጀመሪያው ቻናል አካውንት ስለተደለተ ሌላ እከፍት ዘንድ ግድ ሆኖብኛል። ሃሳብ አስተያየታችሁን በዚህ👉 @Belex_ye16 ፃፉልኝ። ለሌሎችም እንዲደርስ #share #react and Comment አድርጉ💓
- Последний пост
- 10 авг.
- Последнее чтение
- 13 авг.
- Постов за неделю
- 1
- Всего постов
- 20
- Тип
- открытый
- Язык
- ti
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 14
- 1/48двое суток
- 16
- 1/72трое суток
- 17
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
1500+ years ዓመታት… but One Christ! ❤️ 1500+ χρόνια… Ένας Χριστός! #Ortho... https://youtube.com/shorts/BHqYSk3XVvo?si=hObN61qSSZSz3hhu
እድሜ ለዚህ እድር😒 https://t.me/kebelayhungitmoch https://t.me/kebelayhungitmoch
በምድር ቢታወቅ ምን አለ እንደው አስቀድሞ የሠው ልጅ የሆዱ፣ አምነው እና ታምነው ልብን አስረክበው ወደው ከሚጎዱ። ✍Sfraye Tilaye
ክፋት - እንከን - ጊዜ ለማወቅ ሲጥሩ በር ስንጠቀርም፣ ደግመው ሲሞክሩ ስህተት ስንለቅም፣ እኛ የሠው እንጂ የራሳችንንስ ኖረነው አናውቅም። ✍Sfraye Tilaye
መዝሙረ ዳዊት Mezmure Dawit - ሰኞ (መዝ 1-30) 🍿 ዜማ ተዋህዶ Zema Tewahdo | 👀 1277288 [46.1 MiB]
Family youtube arif eyadegelgn new ena please be VPN hulunm eyulgn.... https://youtube.com/@demascotube?si=BGo7t1IVnfoZju-p
Saint John Climacus "Do not imagine that you can overcome the demon of fornication by arguing with it. Flee from the occasion, and pray." ''ከዝሙት መንፈስ ጋር በመከራከር ልታሸንፈው እንደምትችል አታስብ። ከፈተናው ሁኔታ ሽሽ፣ ጸልይም፡፡'' "Hafuura sagaagalummaa mariidhaan mo'uu akka dandeessu hin yaadin. Bakka qoramaa irraa baqadhu; kadhadhu." ''ንመንፈስ ዝሙት ብምክርካር ክትስዕሮ ከም እትኽእል ኣይትሕሰብ። ካብ ምኽንያት ፈተና ህደም፤ ጸልይ፡፡'' Saint John Climacus https://t.me/kebelayhungitmoch YouTube 👇 https://youtube.com/@demascotube?si=rMnJYki0BMldTZX2
Saint John Climacus: "Do not be surprised that you fall every day; do not give up, but stand your ground courageously. "በየቀኑ መውደቅህን እንደ እንግዳ አትቁጠር፤ ፈጽሞ ተስፋ አትቁረጥ፤ ዳሩ ግን በጀግንነት ጽና፣ እንደገናም ተነሣ።" "Guyyaa hunda yoo kufte, hin dinqisiifatin. Abdii hin muratin; garuu ija jabinaan dhaabadhu." "መዓልቲ መዓልቲ እንተ ወደቕካ ኣይትገረም፤ ተስፋ ኣይትቑረጽ፤ ግና ብትብዓት ጽናዕ።" Never give up 🙏 https://t.me/kebelayhungitmoch https://t.me/kebelayhungitmoch
ስይጣነ ጽርፈት ማለት ስድብን የሚያናግር ሰይጣን ማለት ነው:: ይህ ሰይጣን ዋና ሥራው ሰው ሰውን እንዲሰድብና እንዲያዋርድ ከዚያም ሲያልፍ በእግዚአብሔርና በቅዱሳኑ ላይ የስድብን ቃል እንዲናገር ማድረግ ነው:: ...አንዳንዶቻችን ደግሞ “የተሳደብኩት ስለ ተናደድኩ ነው እንጂ አልሳደብም ነበር'' በማለት ለማስተባበል እንሞክራለን፡፡ ሲጀመር ሳይናደድ ወይም ምክንያት ሳይኖረው የሚሳደብ የአእምሮ ጤንነቱ የተቃወሰ ብቻ ነው... ራዕየ ኒፎን ገጽ 24 https://t.me/kebelayhungitmoch https://youtube.com/@demascotube?si=rMnJYki0BMldTZX2 ዩቱዩቤን ሰብስክራይብ እንዲታደርጉልኝ በአክብሮት እጠይቃለሁ። በአሪፍ ስራ ለመንቀሳቀስ እየሞከርኩኝ ነው። እና ድጋፋችሁ አይለየኝ🙏
በእኛ ላይ ሊደርሱ ካሉ ክፉ አደጋዎች የዳንባቸውን ጊዜያቶች እስኪ እናስተውል። ከእነዚያ አስከፊ ሁኔታዎች ተአምር በሚመስል መንገድ የተረፍንባቸውንና ‹ለጥቂት እኮ ነው…› እያልን የምናስታውሳቸውን ሰዓታት እስኪ ለአፍታ ደግመን እናስባቸው። በእነዚያ የጭንቅ ጊዜያቶች ሁሉ የታደገንን የጠባቂ መልአካችንን የተዘረጋች ክንድ እናያለን፡፡ የቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ ደቀ መዝሙር የነበረው ቅዱስ ፖሊካርፐስ በጠባቂ መልአኩ አማካኝነት እንዴት ከሞት በተአምር ሊተርፍ እንደ ቻለ ይናገራል፡፡ ቅዱሱ አብሮት በአገልግሎት ከሚረዳው ዲያቆን ጋር በጉዞ ሳሉ ቀኑ ስለመሸባቸው መንገድ ዳር ካለ አንድ ትንሽ ቤት ገብተው ይተኛሉ፡፡ በእኩለ ሌሊትም የፖሊካርፐስ ጠባቂ መልአክ በሕልሙ ተገልጦ ‹ፖሊካርፐስ ሆይ ሊፈርስ ነውና ፈጥነህ ይህንን ቤት ለቅቀህ ውጣ› እያለ ሶስት ጊዜ አስጠነቀቀው፡፡ ፖሊካርፐስ ራእዩን እንዳየ ያንን ቤት ለቆ በፍጥነት ወጣ፡፡ ወዲያውም ቤቱን እያየው በፊቱ ፈራርሶ ወደቀ፡፡ እርሱም ሊመጣበት ከነበረው ሞት በጠባቂ መልአኩ አማካኝነት ዳነ፡፡ እንኳን ለጠባቂያችን ለሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሰን! መልካም በዓል ይሁንልን! ዲያቆን አቤል ካሳሁን abelzebahiran@gmail.com
https://youtube.com/@demascotube?si=rmlmDt3KmlHlXozA Subscribe family 🙏
ቤተሰብ ሰብስክራይብ እያደረጋችሁ😊 እንደ እግዚአብሔር ፍቃድ በቅርቡ በአድስ ስራ እንመጣለን🙏
ከበላይሁን ግጥሞች kebelayhungtmoch https://youtube.com/@belayhunkebedegoshu5212?si=o_WeWW22kDBDwgEV
አንድ ሰው ለእግዚአብሔር መንግሥት ቅርብ የሚያደርገውን የትኛውንም ዓይነት ሥራ ቢሠራ «የሚጠሉትን የማይወድ›› ከሆነ ግን በሰማዩ መንግሥት ስፍራ አይኖረውም፡፡ If a person does any kind of work that will bring closer to the kingdom of God, "if he doesn't like those who hate him, he will not have a place in the kingdom of heaven. St.paul book page 37
ቀናሁ ባዘኑ ሰዎች የጠበቁትን ባላገኙ የወደዱትን በሸኙ (ታድለው) "ውይ ህይወት ብለው" ባዘኑ የዘገኑትን በበተኑ ውጥን ኖሯቸው በተበተጠሰባቸው (በነዚያ ቀናሁባቸው) ወዮልኝ ለመደንዘዜ በድን ሆኖ ልቤ ምንም አይመኝም እኔ እኮ ቢያንስ የምቆርጠው ተስፋ ራሱ የለኝም ! (elias shitahun)
ሕይወት የብድር በሬ፥ መቼ ሁሌ ይጠመዳል ለጊዜው ብቻ የመጣ፥ ጊዜው ሲደርስ ይሄዳል የተሰጠህ ጸጋ ሁሉ፥ ደሞ ካንተ ይወሰዳል። ቀለበት፥ አምባር አይደሉም እጅህ ላይ ሁልጊዜ የሉም ቀናት ሳምንታት ወራት ዛሬውኑ፥ አሁኑኑ፥ እንደምትወዳት ንገራት። አበቦች ሁሉ ሳይረግፉ ምኡዝ ሽታዎች ሳይጠፉ ያጸድ በሮች ሳይቆለፉ በንቦች ጎዳና ላይ፥ ተርቦች ሳይሰለፉ በንፋስ ክንፍ ሳይመታ ሕይወት የላምባ መብራት አሁንኑ ዛሬውኑ፥ እንደምትወዳት ንገራት። ርቃ ሳትገሰግስ ገና ስንቋን ስትደግስ እንዲሁ እንዳማረባት ቀልብህ እንደቀረባት መቃብር በመዳፉ እንደጠጠር ሳይቀልባት አፈሩን ሳትዛመድ ወደማትቀባው አመድ ወደማትስበው አየር ሳትቀየር አንትም አንደበት ሳለህ፥ እሷም ጆሮ ሳያጥራት ዛሬውኑ! አሁኑኑ! እንደምትወዳት ንገራት። ✍በእውቀቱ ስዩም https://t.me/kebelayhungitmoch https://t.me/kebelayhungitmoch
የምንወዳቸውን ሰዎች እንደምወዳቸው ዛሬውኑ አሁኑ እንንገራቸው! 🫶በተለይ ቤተሰቦቻችንን ምክንያቱም ዛሬ እንጂ ነገ የኛ አይደለምና🙌 ✍በእውቀቱ ስዩም https://t.me/kebelayhungitmoch https://t.me/kebelayhungitmoch
አትናፍቂኝም ደራሲው ለእንስቱ :አመት ይናፍቃል ቀኖችና ወርን : ዘመን ይጠብቃል የበዙት ናፍቆቶች :ገጹን ሞልተውታል : የኔ ግን ይለያል :ሰፋ ይላል ውሉ ከልብ ሚናፍቁኝ : የጻፍኳቸው ሁሉ ስ'ላለምና እግዜር : ስላንቺ ያይደሉ አንቺን እንደ ተስፋ : መች ይናፍቃሉ አንቺን እንደተስፋ መች ይጠብቃሉ፡፡ ✍ በላይሁን ከበደ ሰኔ 2018 ጅማ ኢትዮጵያ
የቤተ-ክርስቲያን ሰላም «አቤቱ ጌታችን ሆይ፣አንዲት፣ ቅድስት፣ ዓለም አቀፋዊትና ሐዋርያዊት የሆነች ቤተ ክርስቲያንህን አስባት፤በሰላምም ጠብቃት።» የሚለው ጸሎት ስለ ቤተ ክርስቲያን በየዕለቱ የሚጸለይ ጸሎት ነው፡፡ ይህን ጸሎት ከሌሎቹ የንስሓ ጸሎቶች ሁሉ በፊት እንጸልየዋለን፡ በመሆኑም በሰርክ ጸሎት ማዕጠንት ላይ እንጸልየዋለን፤በነግህ ጸሎት ማዕጠንት ላይ እንጸልየዋለን፤ካህኑ በመሠዊያው ዙሪያ እየዞረ ዘወትር ሲጸልይም ይህን ጸሎት ይጸልያል፡፡ ቅዳሴ ከመጀመሩ በፊትና መባ ከመቅረቡ በፊትም እንዲህ ብለን እንጸልያለን፡-«አንዲት፣ ቅድስት፣ ዓለማቀፋዊትና ሐዋርያዊት ለሆነችው የእግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያን ሰላምና ቅድስና አድላት::›› ካህናት ሲሾሙም ይህን የዘወትር ጸሎት እንጸልያለን፡ ለንጉሥ ወይም ለፕሬዝደንት በሚደረግ የዘወትር ጸሎት ውስጥም፦ «ኣንዲት፣ ቅድስት፣ ዓለማቀፋዊትና ሐዋርያዊት ለሆነችው ቤተ ክርስቲያንህ ሰላም ስትል ልቡን ዳስሰው፡፡» በማለት ስለ ቤተ ክርስቲያን እንጸልያለን፡ የቤተ ክርስቲያን ሰላም የአባቶቻችን ሐዋርያትና የቅዱሳን ሁሉ አንዱና ዋነኛው ጠቃሚ ጉዳያቸው ነበር። ለእነዚህ ሁሉ አባቶች ይህች ቤተ ክርስቲያን እስከ ሰማያዊው መንግሥት ድረስ የምትዘረጋ በምድር ያለች የእግዚአብሔር መንግሥት ምሳሌ ናት፡፡ የምትወክለውም የእምነትን ምንጭና እግዚአብሔር ከሕዝቡ ጋር የመኖሩን እውነት ነው፡፡ አንድ ሰው በጸሎቱ ውስጥ ለራሱ ከሚያቀርበው ጥያቄ ይልቅ ለእርሷ ስለሚጠይቅ ሰላሟና ደኅንነቷ የእያንዳንዱ ሰው የጸሎት መሠረት ነው፡፡ ይህ ጥያቄ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ባስተማረን ጸሎት ውስጥ የተመስጦአችን ማዕከል ስለሆነ «ስምህ ይቀደስ፤ መንግሥትህ ትምጣ፤ ፈቃድህ በሰማይ እንደ ሆነች እንዲሁም በምድር ትሁን. . .» እያልን እንጸልያለን፡፡ ስለ ቤተ ክርስቲያን መጸለይ በምዕመናን፣ በእረኞቹና በመጋቢዎቹ አንደበት ውስጥ ለብዙ መቶ ዓመታት የቆየ ታላቅ ጸሎት ነው፡፡ ራሳቸውን ከዓለም ለለዩ መነኮሳት በሚደረግ የቅዳሴ ጸሎት ውስጥ እንኳ ስለ ቤተ ክርስቲያን ሰላም እንጸልያለን:: የመናኞች ሁሉ ታላቅ አባት የሆነው የመጀመሪያው ባሕታዊ አባ ጳውሊ ቅዱሱን አባ እንጦንስን ስለ ቤተ ክርስቲያን ሰላም መጠየቁ እንደምን ያለ ድንቅ ነገር ነው! ይህን ጸሎት የምንጸልየው ከልባችን ጥልቀት ውስጥ ነው፡፡ የምንጸልየው የቅዳሴ አንድ ክፍል አድርገን ሳይሆን እንደ ሕያውና እንደሚያቃጥል ስሜት እየሆነብን ነው፡፡ እያንዳንዱ ሰው ስሜቶቹን ሁሉ በዚህ ጸሎት ውስጥ እንዲያሰፋ ይሁን፡፡ አሜን🙏 ከአቡነ ሽኖዳ ሳልሳዊ መንፈሳዊ ቃላትና ጥቅሞቻቸው መጽሐፍ ገጽ 94-94።
ወንድማችን መምህር ዘላለም ታዬ ኃይለ ዑራኤል እግዚአብሔር ፈቅዶ በሰላም ወደ ቤቱ ገብቷል እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁን 🙏