ቅዱሳን ገዳማት
Статистикаይህ የቴሌ ግራም ቻናል • በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ የሚገኙ ቅዱሳን ገዳማት እና አድባራትን ማስተዋወቅ,,, ☆ • የተዘጉ አብያተ ክርስቲያናትን ማስከፈት እና መልሶ ማቋቋም • የአብነት (የቆሎ) ትምህርት ቤቶችን ምንጩ እንዳይደርቅ መደገፍ….. እና ሌሎችንም መንፈሳዊ አገልግሎቶች ያከናዉናል
- Последний пост
- 12 сент. 2025 г.
- Последнее чтение
- 14 авг.
- Постов за неделю
- 0
- Всего постов
- 22
- Тип
- открытый
- Язык
- ti
- В каталоге с
- 14 авг.
- 1/24сутки в ленте
- —
- 1/48двое суток
- —
- 1/72трое суток
- —
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
እንኳን ከዘመነ ማቴዎስ ወደ ዘመነ ማርቆስ አደረሳችሁ‼️ 🌼 "የዕንቁጣጣሽ" ሥያሜ አመጣጥ? ዓመታት ተፈጽመው አዲስ ዓመት ስንጀምር ቅዱስ ዮሐንስ፣ ዓውደ ዓመት፣ አዲስ ዓመት ፣ ዕንቁጣጣሽ እየተባለ ይጠራል፡፡ ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን እንደሚያስረዱት ዕንቁጣጣሽ የሚለው ስያሜው አመጣጥ ወይም ጥንተ ታሪክ በመጀመሪያ ኖኅ ለሦስቱ ልጆቹ አህጉራትን በዕጣ ሲያካፍላቸው አፍሪቃ ለካም ደረሰችው፡፡ በአፍሪቃ ምድርም ሲገባ በመጀመሪያ ያረፈው በኢትዮጵያ ነበር፡፡ ሀገሪቱም በአደይ አበባ አሸብርቃ ነበር፡፡ ወሩ ወርኃ መስከረም በመሆኑ ደስ ብሎት «ዕንቁ ዕጣ ወጣሽልኝ» ይህችን ወቅት እንቁጣጣሽ ብሏታል፡፡ ሁለተኛው ደግሞ የሀገራችን ንግሥት ንግሥተ ሳባ የንጉሥ ሰሎሞንን ዜና ጥበብ እየሰማች ስታደንቅ ትኖር ነበር፡፡ በጆሮዋ የሰማችውን በዓይኗ ዓይታ ለመረዳት ስለፈለገች በግመሎች ላይ ሽቱና እጅግ ብዙ ወርቅ እንዲሁም በኢትዮጵያ የሚገኝ በኢየሩሳሌም የማይገኝ ልዩ ልዩ ገጸ በረከት አስጭና ከብዙ ሠራዊት ጋር ወደ ኢየሩሳሌም ገባች፡፡ ከንጉሡ ሰሎሞንም ጋር ተገናኝታ የያዘችውን ገጸ በረከት ከሰጠችው በኋላ ብዙ ነገሮችን ጠየቀችው፡፡ እርሱም አንድ ነገር ላይ ሰውሮ ሁሉንም ገለጸላት፡፡ ቤተ መንግሥቱንም፣ በቤተ መንግሥቱ የሚገኙ እጅግ በጣም የከበሩ ዕቃዎችን ሁሉ አስጎበኛት፡፡ ሲያበቃ «ዕንቁ ለጣትሽ ጌጥ ይሁንልሽ» ሲል እጅግ በጣም የከበረ ዕንቁ አበረከተላት/ሰጣት/፡፡ ወሩም ወረኃ መስከረም ነበር፡፡ ከዚህ በመነሣት እንቁጣጣሽ የሚለው መጥቷል፡፡ አሁን ከሚፈጸመው ሥነ ሥርዓት ደርሶ በመፈጸም ላይ ይገኛል፡፡ የሚከበረውም መስከረም አንድ ቀን ነው፡፡ አንድም «ዕንቁ ዕፅ አወጣሸ» ብሎ የአበባውን መፈንዳትን ያስረዳናል፡፡ መልካም አዲስ ዓመት ይሁንልን ወስብሐት ለእግዚአብሔር
видео или голосовое, без подписи
🔴 ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን ➠ ክርስቶስ ከሙታን ተለይቶ ተነሣ 🔵 በዐቢይ ኃይል ወስልጣን ➠ በገናና ኃይልና ሥልጣን •• 🔴 አሰሮ ለሰይጣን ➠ ሰይንን አሠረው 🔵 አግዓዞ ለአዳም ➠ አዳምን ነጻ አወጣው •• 🔴 ሰላም ➠ ፍቅር አንድነት ሆነ 🔵 እም ይእዜሰ ➠ ከእንግዲህስ •• 🔴 ኮነ ➠ ሆነ 🔵 ፍስሐ ወሰላም ➠ ደስታ እና ሰላም •• " አሁንስ ግን ክርስቶስ ላንቀላፉት በኩራት ሆኖ ከሙታን ተነሥቶአል። " 1ኛ ቆሮ 15-20 •••• 👉 መልካም በዓል ይሁንልን ። 👉 የቴሌ ግራም ቻናላችን - https://t.me/kedusangdamat 👉 የቲክ ቶክ የገፃችን - https://www.tiktok.com/@eskedarzeleke 👉 የፌስቡኩ ገፃችን - https://www.facebook.com/profile.php?id=100048752932061 ይቀላቀሉን
የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም 5ቱ ታላላቅ ሀዘናት ክብር ምስጋና ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን በእኔ ምክንያት ካገኙሽ ኅዘናት የትኛው ይበልጣል ብሎ በጠየቃት ጊዜ እመቤታችንም ልጄ ወዳጄ ሆይ ባንተ ምክንያት ካገኙኝ ኅዘናት እነዚህን አምስቱ ይበልጣሉ ብላ እመቤታችን የጠቀሰቻቸው ታላላቅ ኅዘናት የሚከተሉት ሲሆኑ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም እነዚህን ያንችን ኅዘናት እያሰበ የጸለየ ኃጢአቱን ይቅር እለዋለሁ ብሎ ቃል ኪዳን ሰጥቷታል። ፩ኛ - ስምዖን በቤተ መቅደስ ትንቢት በተናገረ ጊዜ። => ስምዖን የተባለው ፦ አረጋዊው ስምኦን ነው የእመቤታችን ሐዘን የሚጀምረው ገና አንድዬ ልጇን ከመውለዷ በስምተኛው ቀን ነው ቤተመቅደስ ይዛው በሄደች ጊዜ አረጋዊው ስምዖን “በአንቺም ደግሞ በነፍስሽ ሰይፍ ያልፋል (ልጅሽ በቀራንዮ ይሞታል)” ሉቃስ 2፥34-35 ብሎ በነገራት ጊዜ ድንግል ማርያም አምርራ አዘነች አለቀሰች። እነሆ፥ የብዙዎች ልብ አሳብ ይገለጥ ዘንድ፥ ይህ በእስራኤል ላሉት ለብዙዎቹ ለመውደቃቸውና ለመነሣታቸው ለሚቃወሙትም ምልክት ተሾሞአል፥ በአንቺም ደግሞ በነፍስሽ ሰይፍ ያልፋል አላት። ሉቃ (2፡34-35) ፪ኛ - ከቤተ መቅደስ ፈልጌህ ባጣሁህ ጊዜ። ወላጆቹም በያመቱ በፋሲካ በዓል ወደ ኢየሩሳሌም ይወጡ ነበር። የአሥራ ሁለት ዓመት ልጅ በሆነ ጊዜ፥ እንደ በዓሉ ሥርዓት ወደ ኢየሩሳሌም ወጡ፤ ቀኖቹንም ከፈጸሙ በኋላ፥ ሲመለሱ ብላቴናው ኢየሱስ በኢየሩሳሌም ቀርቶ ነበር፥ ዮሴፍም እናቱም አላወቁም ነበር። ከመንገደኞች ጋር የነበረ ስለመሰላቸው የአንድ ቀን መንገድ ሄዱ፥ ከዘመዶቻቸውም ከሚያውቋቸውም ዘንድ ፈለጉት፤ ባጡትም ጊዜ እየፈለጉት ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ። ከሦስት ቀንም በኋላ በመምህራን መካከል ተቀምጦ ሲሰማቸውም ሲጠይቃቸውም በመቅደስ አገኙት፤ የሰሙትም ሁሉ በማስተዋሉና በመልሱ ተገረሙ። ባዩትም ጊዜ ተገረሙ እናቱም። ልጄ ሆይ፥ ለምን እንዲህ አደረግህብን? እነሆ፥ አባትህና እኔ እየተጨነቅን ስንፈልግህ ነበርን አለችው። ሉቃ (2፡41-48) ፫ኛ - በጲላጦስ አደባባይ በገረፉህ ጊዜ። በዚያን ጊዜም ጲላጦስ ኢየሱስን ይዞ ገረፈው። ወታደሮችም ከእሾህ አክሊል ጐንጕነው በራሱ ላይ አኖሩ ቀይ ልብስም አለበሱት፤ እየቀረቡም። የአይሁድ ንጉሥ ሆይ፥ ሰላም ለአንተ ይሁን ይሉት ነበር፤ በጥፊም ይመቱት ነበር። ጲላጦስም ደግሞ ወደ ውጭ ወጥቶ። እነሆ፥ አንዲት በደል ስንኳ እንዳላገኘሁበት ታውቁ ዘንድ እርሱን ወደ ውጭ አወጣላችኋለሁ አላቸው። ኢየሱስም የእሾህ አክሊል ደፍቶ ቀይ ልብስም ለብሶ ወደ ውጭ ወጣ። ዮሐ (19፡1-5) ፬ኛ - በዕለተ ዓርብ በሰቀሉህ ጊዜ። ኢየሱስንም ይዘው ወሰዱት፤ መስቀሉንም ተሸክሞ በዕብራይስጥ ጎልጎታ ወደ ተባለው የራስ ቅል ስፍራ ወደሚሉት ወጣ። በዚያም ሰቀሉት፥ ከእርሱም ጋር ሌሎች ሁለት፥ አንዱን በዚህ አንዱን በዚያ ኢየሱስንም በመካከላቸው ሰቀሉ። ጲላጦስም ደግሞ ጽሕፈት ጽፎ በመስቀሉ ላይ አኖረው፤ ጽሕፈቱም። የአይሁድ ንጉሥ የናዝሬቱ ኢየሱስ የሚል ነበረ። ኢየሱስም የተሰቀለበት ስፍራ ለከተማ ቅርብ ነበረና ከአይሁድ ብዙዎች ይህን ጽሕፈት አነበቡት፤ በዕብራይስጥና በሮማይስጥ በግሪክም ተጽፎ ነበር። ስለዚህ የአይሁድ ካህናት አለቆች ጲላጦስን እርሱ። የአይሁድ ንጉስ ነኝ እንዳለ እንጂ የአይሁድ ንጉሥ ብለህ አትጻፍ አሉት። ጲላጦስም። የጻፍሁትን ጽፌአለሁ ብሎ መለሰ። ዮሐ. (19፡17-2 ፭ኛ- ዮሴፍና ኒቆዲሞስ ገንዘው ወደ አዲስ መቃብር ባወረዱህ ጊዜ። ከዚህም በኋላ አይሁድን ስለ ፈራ በስውር የኢየሱስ ደቀ መዝሙር የነበረ የአርማትያስ ዮሴፍ የኢየሱስን ሥጋ ሊወስድ ጲላጦስን ለመነ፤ ጲላጦስም ፈቀደለት። ስለዚህም መጥቶ የኢየሱስን ሥጋ ወሰደ። ደግሞም አስቀድሞ በሌሊት ወደ ኢየሱስ መጥቶ የነበረ ኒቆዲሞስ መቶ ንጥር የሚያህል የከርቤና የእሬት ቅልቅል ይዞ መጣ። የኢየሱስንም ሥጋ ወስደው እንደ አይሁድ አገናነዝ ልማድ ከሽቱ ጋር በተልባ እግር ልብስ ከፈኑት። በተሰቀለበትም ስፍራ አትክልት ነበረ፥ በአትክልቱም ማንም ገና ያልተቀበረበት አዲስ መቃብር ነበረ።ስለዚህ መቃብሩ ቅርብ ነበረና ስለ አይሁድ ማዘጋጀት ቀን ኢየሱስን በዚያ አኖሩት። ዮሐ (19፡38-42) እንዚህን አምስቱን የእመቤታችን ሐዘናት እያሰበ ያዘነ ዝክሯን የዘከረ በአማላጅነቷ የታመነ ዋጋው ከቶ አይጠፋበትም፡፡ ቅድስት ሆይ ለምኝልን ቅድስት ሆይ ለምኝልን ቅድስት ሆይ ለምኝልን አሜን ወስብሐት ለእግዚአብሔ
видео или голосовое, без подписи
እንኳን ለጌታችን ለመድሐኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የስቅለት በአል አደረሰን አደረሳችሑ አምላካችን በፈሰሰው ደሙ አገራችን ሰላም ያርግልን ።ለአለም ሕዝብ ጤናውን ፍቅሩን ሰላሙን ያድለነ አሜን
❤️ #የሐዲስ_ኪዳን_ሐሙስ_ይባላል ፦ ምክንያቱም መሥዋዕተ ኦሪት ማለትም በእንስሳት ደም የሚቀርበው መሥዋዕት ማብቃቱን ገልጦ፣ ለድኅነተ ዓለም ራሱን የተወደደ መሥዋዕት አድርጎ ያቀረበበት ዕለት በመሆኑ ነው፡፡ «ይህ ጽዋ ስለ እናንተ በሚፈሰው በደሜ የሚሆን ሐዲስ ኪዳን ነው፡፡ ከእርሱ ጠጡ» በማለቱ ይታወቃል (ሉቃ. 22፥20) ኪዳን ማለት በሁለት ወገን መካከል የሚደረግ ውል፣ ስምምነት፣ መሐላ ማለት ነው፡፡ በዚህ መሠረት ጌታችን ለአዳምና ለልጆቹ ሁሉ ዘለዓለማዊውን ቃል ኪዳን በራሱ ደም የፈጸመበት ዕለት ስለሆነ የሐዲስ ኪዳስ ሐሙስ ተባለ፡፡ ••• ❤️ #የነጻነት_ሐሙስ_ይባላል ፦ ለኃጢአትና ለዲያብሎስ ባሪያ ሆኖ መኖር ማብቃቱ፣ የሰው ልጅ ያጣውን ክብር መልሶ ማግኘቱ የተረጋገጠበት ቀን ስለሆነ ነው፡፡ ጌታችን ስለ ሰው ልጅ ነጻነት ሲናገር «ከእንግዲህ ወዲህ ባሮች አልላችሁም ባርያ ጌታዉ የሚያደርገውን አያውቅምና ወዳጆች ግን ብያችኋለሁ» በማለት (ዮሐ. 15፥15)፤ ከባርነት የወጣንበት ልጆች የተባልንበትን ቀን የምናስብበት በመሆኑ ሊቃውንቱ የነጻነት ሐሙስ አሉት፡፡ እያንዳንዱ ክርስቲያንም ከኃጢአት ባርነት ርቆ፣ ከእግዚአብሔር ጋር የሚያወዳጀውን መልካም ሥራ በመሥራት ሕይወቱን መምራት ይኖርባታል፡፡ ባሮች አልላችሁም ተብለናልና፡፡ •••• 👉 መልካም በዓል ይሁንልን ። 👉 የቴሌ ግራም ቻናላችን - https://t.me/kedusangdamat 👉 የቲክ ቶክ የገፃችን - https://www.tiktok.com/@eskedarzeleke 👉 የፌስቡኩ ገፃችን - https://www.facebook.com/profile.php?id=100048752932061 ይቀላቀሉን
👉 #የሰሙነ_ህማማት_ሐሙስ ••• ❤️ #ጸሎተ_ሐሙስ ፦ በቤተ ክርስቲያን የተለያዩ ስያሜዎች ያሏቸው በርካታ ድርጊቶች የተፈጸሙበት ዕለት ነውና ጸሎተ ሐሙስ ይባላል፡፡ የዓለም መድኃኒት ኢየሱስ ክርስቶስ ሥጋን የተዋሐደ አምላክ፣ መሆኑን ለመግለጥና ለአርአያነት ጠላቶቹ መጥተው እስኪይዙት ድረስ ሲጸልይ ያደረበት ነውና ጸሎተ ሐሙስ ተባለ፡፡ (ማቴ. 26፥36-46 ዮሐ.17) ••• ❤️ #ሕፅበተ_ሐሙስ_ይባላል ፦ ጌታችን በዚህ ዕለት የደቀመዛሙርቱን እግር በፍጹም ትሕትና ዝቅ ብሎ አጥቧል፡፡ ይህም የሚያሳየው የዓለምን ሁሉ ኃጢአት ለማጠብ የመጣ መሆኑን ነው፡፡ ይህን ለማስታወስ ዛሬም ካህናት በተለይም ሊቃነ ጳጳሳት፣ የደብር አስተዳዳሪዎች፤ «በመካከላችን ተገኝተህ የእኛንና የሕዝብህን ኃጢአት እጠብ እኛም የአንተን አርአያ አንዘነጋም የሌላውን እግር እናጥባለን፤» ሲሉ በቤተ ክርስቲያን የተገኙትን ምእመናንን እግር በወይንና በወይራ ቅጠል ያጥባሉ፡፡ ••• ❤️ #የምስጢር_ቀን_ይባላል ፦ ከሰባቱ ምስጢራት አንዱ በዚህ ዕለት ተመሥርቷልና፡፡ ይኸውም «ይህ ስለ እናንተ በመስቀል ላይ የሚቆረሰው ሥጋዬ ነው፡፡ እንካችሁ ብሉ» ጽዋውንም አንስቶ አመሰገነ «ይህ ስለ እናንተ ነገ በመስቀል የሚፈስ ደሜ ነው ከእርሱም ጠጡ» በማለት፤ እኛ ከእርሱ ጋር፣ እርሱ ከእኛ ጋር አንድ የምንሆንበትን ምስጢር ከጠላት ዲያብሎስ ሰውሮ፣ ለደቀ መዛሙርቱ የገለጠበት ቀን በመሆኑ የተሰጠ ሥያሜ ነው፡፡ በዚህ ዕለት ክርስቲያን የሆነ ሁሉ በንስሐ ታጥቦ ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን ለመቀበል ይዘጋጃል፡፡ •••
2. የመልካም መዓዛ ቀንም ይባላል - ምክንያቱም ጌታችን በዚህ ዕለት በቤተ ስምዖን ዘለምጽ ተቀምጦ ሳለ መላ ሕይወቷን ለዝሙት አስገዝታ ትኖር የነበረችው ማርያም እንተ እፍረት / ባለ ሽቶዋ ማርያም / « ከእንግዲህ ወዲህ በኃጢአት ተበላሽቶ ይኖር የነበረውን ሕይወቴን እንደዚህ መልካም ሽቱ የሚያጣፍጥ ኃጢአትን ይቅር የሚል አምላክ መጣ » ስትል ዋጋው እጅግ በጣም ውድ የሆነ ከሦስት መቶ ዲናር በላይ የሚያወጣ አልባስጥሮስ ብልቃጥ የተሞላ ሽቱ ይዛ በመሔድ በጠጉሩ / በራሱ / ላይ በማርከፍከፍ ስለቀባችው የመዓዛ ቀን ይባላል። ••• 3. የእንባ ቀን ይባላል - ባለሽቱዋ ሴት ( ማርያም እንተ እፍረት ) ኃጢአቷን ይቅር እንዲላት እየለመነች በእግሩ ስር ተደፍታ በእንባዋ እግሩን አርሳለችና ማር ፲፬፥፱ የእንባ ቀን ይባላል። ጌታ ሆይ መከራህን ስቃይህን ረሃብ ጥማትህን ሞትህን እያሰብኩ የማነባበት እንባ አብራህ ስለተንከራተተችው በመስቀል ላይ ሳለህም አንዴ ከድንጋይ አንዴም ከእሾህ ላይ እየወደቀች እየተነሳች ወየው አንድ ልጄ እያለች ስታነባ በነበረችው በአዛኝቱ እናትህ ስጠኝ አቤቱ ይቅር በለኝ ኢትዮጵያን ተዋሕዶን አስባት ኪርያላይሶን! •••• ኪራላይሶን አቤቱ ማረን ይቅር በለን ••••• 👉 መልካም በዓል ይሁንልን ። 👉 የቴሌ ግራም ቻናላችን - https://t.me/kedusangdamat 👉 የቲክ ቶክ የገፃችን - https://www.tiktok.com/@eskedarzeleke 👉 የፌስቡኩ ገፃችን - https://www.facebook.com/profile.php?id=100048752932061 ይቀላቀሉን
👉🏻 ረቡዕ || ሰሞነ ሕማማት •• 1. ምክረ አይሁድ ይባላል - ምክንያቱም የአይሁድ ሊቃነ ካህናትና ጸሐፍት ጌታን እንዴት መያዝ እንደሚገባቸው ምክር ያጠናቀቁበት ቀን ነውና፡፡በዚህ ምክራቸው ላይ በጣም ትልቅ ጭንቀት ነበር፡፡ ምክንያቱም ወቅቱ የፋሲካ በዓላቸውን የሚያከብሩበት ቀን የተቃረበ በመሆኑ ብዙው ሕዝብም በጌታችን ትምህርት የተማረኩ ተአምራቱንም የሚያደንቁ ስለ ነበር ሁከት እንዳይፈጠር ነው፡፡በዚህ ጭንቀት ሳሉ ከደቀ መዛሙርቱ አንዱ የአስቆሮቱ ይሁዳ በመካከላቸው በመገኘት የምክራቸው ተባባሪ ሆኖ ጭንቀታቸውን አስወግዶላቸዋል። •• የሐዲስ ኪዳን ካህናትና ምእመናን በዚሁ ዕለት በቤተ ክርስቲያን ተሰብስበው መላ ሰውነታቸውን ለእግዚአብሔር አስገዝተው የሞት ፍርዱን በማሰብና በማልቀስ ሐዋርያት ከጌታችን መያዝ በኋላ በኀዘን በፍርሐት እንደነበሩ እያሰቡ መጻሕፍትን በማንበብ በጾም በጸሎትና በስግደት ተወስነው ይቆዩና ከአሥራ ሁለት ሰዓት በኋላ ወደ ቤታቸው ይሄዳሉ፡፡ ••
✞ ዮሐንስን ይዛ ✞ ዮሐንስን ይዛ ወደ ቀራንዮ ድንግል ማርያም ሄደች እያለች ወዮ ስለ ልጇ ሐዘን ስለ መከራዋ ያስገርም ነበረ የፈሰሰው ዕንባዋ ዮሐንስ ቢደንቀው የሐዘኗ ጽናት አነሳት ደግፎ በብርቱ ሊያጽናናት ድንግልም አለችው ልጄ አሳዘነኝ እህት ወንድም የለው ላልቅስለት ተወኝ ከሁሉም ይበልጣል ያስደፋል አንገትን የማርያም ሐዘን መቅደላዊት ማርያም ሶሎሜ ዮሐና ማርያምን አይዋት ጸንቶባት ሐዘኗ በልቅሶዋ ጣዕም ተነክቶ ልባቸው ዕንባን አፈሰሱ ውለታው ገብቷቸው ከሁሉም ይበልጣል ያስደፋል አንገትን የማርያም ሐዘን ራሔል አልቅሳለች ላላቀፈቻቸው ድንግል ግን ብታለቅስ አዝላው ተሰዳነው ያዕቆብም አልቅሷል በሌላ የሠው ደም ማርያም ግን ብታለቅስ ፈሷል የልጇ ደም ከሁሉም ይበልጣል ያስደፋል አንገትን የማርያም ሐዘን ጠብቶ ስለአደገ የድንግልና ጡቷን መቆም አልቻለችም ስታይ መጠማቱን በደም ተሸፍኖ ብታየው ውበቱን ለይልኝ አለችው ከሥጋዋ ነፍሷን ከሁሉም ይበልጣል ያስደፋል አንገትን የማርያም ሐዘን #እምበለደዌ_ወሕማም፤ ✞✞✞ #እምበለ_ጻማ_ወድካም ✞✞✞ #አመ_ከመ_ዮመ_ያብጸሐነ፤ ✞✞✞ #ያብጸሐክሙ_እግዚአብሔር_በሰላም። ✞✞✞ 🔔 ገጾቹን በመቀላቀል እና ለሌሎች በማጋራት አገልግሎቱን ይደግፉ!!
ሰሙነ ሕማማት 👉 ማክሰኞ የጥያቄ ቀን ይባላል፦ ሰኞ ዕለት በቤተመቅደስ ሲሸጡ እና ሲለውጡ የነበሩትን ሁሉ እየገረፈ በማባረሩ ምክንያት ለሰው ልጅ ሹመትንና ስልጣንን የሰጠ ጌታ “በምን ስልጣን ይህንን ታደርጋለህ?” ማቴ ፳፩፥ ፳፫ ተብሎ በፈሪሳውያን ተጠይቋልና የጥያቄ ቀን ይባላል። የትምህርት ቀን ይባላል፡- በዚህ ዕለት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከመሰቀሉ አስቀድሞ ለመጨረሻ ግዜ በቤተመቅደስ ረጅም ትምህርት ስላስተማረም የትምህርት ቀን ይባላል። ሉቃ ፳፩ ፥፳፰ ፣ ማር ፲፪፥፪። 💚 @kedusangdamat 💚 💛 @kedusangdamat 💛 ❤️ @kedusangdamat ❤️
➻ መርገመ በለስ የሰሙነ ሕማማት የመጀመሪያው ዕለት ዕለተ ሰኑይ መርገመ በለስ ይባላል፡፡ ጌታችን የሆሣዕና ዕለት ቢታንያ አድሮ በማግስቱ ከቢታንያ ሲወጣ ተራበ፤ በመንገድም ሲያልፍ ቅጠል ያላት በለስን ከሩቁ ተመለከተ፡፡ ወደ በለሲቱም በቀረበ ጊዜ ከቅጠል በቀር አንዳች ፍሬ አላገኘባትም፡፡ ያንጊዜም ‹‹ከእንግዲህ ወዲህ ለዘለዓለም ከአንቺ ፍሬ የሚበላ አይኑር›› ሲል በለሲቱን ረገማት፡፡ ደቀ መዛሙርቱም ይህንን ሰሙት፡፡ በዚህም ምክንያት ይህች ዕለት በለሲቱ የተረገመችባት ቀን ናትና መርገመ በለስ ተብላ ትጠራለች፡፡ (ማር.፲፩፥፲፩-፲፬) በዚህ አገላለጽ በለስ የተባለች ቤተ እስራኤል ስትሆን ፍሬ የተባለ ደግሞ ሃይማኖትና ምግባር ነው፡፡ መድኃኒታችን ክርስቶስ ከእስራኤል ፍቅርን፣ ሃይማኖትን፣ ምግባርን ፈልጎ አላገኘባቸውም፡፡ እስራኤል፦ ሕዝበ እግዚአብሔር፣ የአብርሃም ዘር መባልን እንጂ የአብርሃምን ሥራ በመሥራት በምግባር በሃይማኖት ጸንተው መኖር አይፈልጉምና ደግ ሰው አልተገኘባቸውም፡፡ ከዚህም ባሻገር በለስ የተባለች ኃጢአት ናት፡፡ የበለስ ቅጠል ሰፊ እንደሆነች ሁሉ ኃጢአት በዚህ ዓለም ሰፍታ ሰፍና አግኝቷታል፡፡ በለስ ሲበሉት ይጣፍጣል፤ ቆይቶ ግን ይመራል፤ ኃጢአትም ሲሠሩት ለጊዜው ደስ ያሰኛል ኋላ ግን ያሳዝናል፡፡ በአንቺ ፍሬ አይገኝ የሚለውም በአንቺ በኃጢአት ፍዳ ተይዞ የሚቀር አይኑር ሲል ነው፡፡ በለሲቱ ስትረገም ፈጥና መድረቋም በአዳም ምክንያት ያገኘን በደል በእርሱ እንደጠፋልን ለመግለጽ ነው፡፡ ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ሥርዐተ ጸሎት ሰሙነ ሕማማት ከሰኞ እስከ ዕሮብ ካህናት እያዜሙ እየሰገዱ እኛም እየተቀበልን እያዜምን የምንሰግድበትን ሥርዓት ለማውቅ እና ለመፈፀም ከስር ያንብቡ፤ 👉 ከሰኞ ጀምሮ እስከ ዓርብ ድረስ ባሉት ቀናት ውስጥ በመጀመሪያ ዲያቆኑ ቤተ ክርስቲያኑን ሦስት ጊዜ ዞሮ ደወል ካሰማ በኋላ መቶ አምሳው ዳዊት ይታደልና ይደገማል፡፡ የሰባት ቀናት ውዳሴ ማርያምና አንቀጸ ብርሃን እስከ ይዌድስዋ ድረስ ታድሎ ይደገማል፡፡ ከዚያም “እንበለ ደዌ ወሕማም እንበለ ጻማ ወድካም ዓመ ከመ ዮም ያብጽሐኒ ያብጽሕክሙ አግዚአብሔር በፍሥሓ ወበሰላም” ተብሎ አቡነ ይደገምና በዐራቱም ወንጌላት መሠረት ለእያንዳቸው በእየዕለቱና ሰዓቱ የተመደበውን አቡነ ካህናቱ በቀኝና በግራ እየተፈራረቁ ይመራሉ፡፡ ካህናቱና ሕዝቡም ይቀበላሉ፡፡ በመቀጠል፡- (ትእዛዝ፡ ሕዝቡ በጸሎት በተሰበሰቡ ጊዜ ጠዋት ወይም በ3፣ በ6፣በ9፣ በ11ሰዓተ መዓልት መጀመሪያ ሕዝቡ እየሰገዱና እየተከተሉ እንዲህ ይበሉ፡፡ ) ✥ "ለከ ኃይል ክብር ወስብሐት ወእዘዝ ለዓለመ ዓለም ፡፡" ✥ "አማኑኤል አምላኪየ ለከ ኃይል ክብር ወስብሐት ወእዘዝ ለዓለመ ዓለም፡፡" ✥ " ኦ እግዚእየ ኢየሱስ ክርስቶስ ለከ ኃይል ክብር ወስብሐት ወእዘዝ ለዓለመ ዓለም፡፡ " ✥ " ኃይልየ ወጸወንየ ውእቱ እግዚእየ፤ እስመ ኮንከኒ ረዳእየ እብል በአኰቴት ፡፡" ትእዛዝ፡ በዚህ ጊዜ ካህኑ እየተከተሉ አቡነዘበሰማያት ይድገሙ ። ይህን የላይኛውን ጸሎት እያመላለሱ ከአቡነ ዘበሰማያት ጋር 12 ጊዜ ይበሉ ❖ " ለአምላክ ይደሉ ክብር ወስብሐት ወእዘዝ እስከ ለዓለመ ዓለም፡፡ ❖ "ለሥሉስ ይደሉ ክብር ወስብሐት ወእዘዝ እስከ ለዓለመ ዓለም"፡፡ ❖ "ለማሕየዊ ይደሉ ክብር ወስብሐት ወእዘዝ እስከ ለዓለመ ዓለም"፡፡ ❖ "ለዕበዩ ይደሉ ክብር ወስብሐት ወእዘዝ እስከ ለዓለመ ዓለም"፡፡ ❖"ለእዘዙ ይደሉ ክብር ወስብሐት ወእዘዝ እስከ ለዓለመ ዓለም"፡፡ ❖ "ለመንግሥቱ ይደሉ ክብር ወስብሐት ወእዘዝ እስከ ለዓለመ ዓለም"፡፡ ❖ "ስለልጣኑ ይደሉ ክብር ወስብሐት ወእዘዝ እስከ ለዓለመ ዓለም"፡፡ ❖ "ለኢየሱስ ይደሉ ክብር ወስብሐት ወእዘዝ እስከ ለዓለመ ዓለም"፡፡ "ለክርስቶስ ይደሉ ክብር ወስብሐት ወእዘዝ እስከ ለዓለመ ዓለም"፡፡ ❖ "ለሕማሙ ይደሉ ክብር ወስብሐት ወእዘዝ እስከ ለዓለመ ዓለም"፡፡ ❖ "ለመስቀሉ ይደሉ ክብር ወስብሐት ወእዘዝ እስከ ለዓለመ ዓለም፡፡ " ትእዛዝ፡- ይህ ሦስት ጊዜ እየተመላለሰ ይባላል፡፡በመጨረሻም የሚከተለውን ሦስት ጊዜ እያመላለሱ ይበሉ፡፡ ❖ "ለከ ይደሉ ኃይል፣ ወለከ ይደሉ ስብሐት ወለከ ይደሉ አኰቴት ኦ እግዚእየ ኢየሱስ ክርስቶስ ለዓለመ ዓለም" ትእዛዝ፡- ካህኑ ‹ጸልዩ በእንተ ጽንዓ ዛቲ . . .› ብሎ በሚያነብ ጊዜ በየምዕራፉ "እግዚኦ ተሳሃለነ" እየተባለ ይሰገዳል፡፡ ትእዛዝ፡- ከዚህ ሁሉ በኋላ ሕዝቡ የሚከተሉትን ጸሎት በግራና በቀኝ ይበሉ፤ "ክርስቶስ አምላክነ፤ ዘመጽአ ወሐመ በእንቲአነ በሕማማቲሁ ቤዝወነ፤ ንሰብሖ ወናልዕል ስሞ ኅቡረ፤ እስመ ውእቱ ገብረ መድኃኒተ በዕበየ ሣህሉ" (በዐርብ) ዘሐመ ወሞተ በእንቲአነ ይባላል፡፡ ትእዛዝ፡- ቀጥሎም ሕዝቡ በሁለት ክፍል ሆነው የሚከተለውን ጸሎት ሁለት ጊዜ በመከታተል አንድጊዜ በማስተዛዘል ይበሉት፡፡ ኪርያላይሶን፤ኪርያላይሶን፤#ኪርያላይሶን፤ኪርያላይሶን፤ኪርያላይሶን፤ ኪርያላይሶን፤ኪርያላይሶን፤ #አብኖዲ ኪርያላይሶን፤ ኪርያላይሶን፤ኪርያላይሶን #ናይን፣ኪርያላይሶን፤ ኪርያላይሶን፤ኪርያላይሶን ፤ #ታዖስ ናይን፣ ኪርያላይሶን፤ ኪርያላይሶን፤ኪርያላይሶን፤ #ማስያስ ናይን፣ ኪርያላይሶን፤ ኪርያላይሶን፤ኪርያላይሶን፤ #ኢየሱስ ናይን፣ ኪርያላይሶን፤ ኪርያላይሶን፤ኪርያላይሶን፤ #ክርስቶስ ናይን፣ ኪርያላይሶን፤ ኪርያላይሶን፤ኪርያላይሶን፤ #አማኑኤል ናይን፣ ኪርያላይሶን፤ ኪርያላይሶን፤ኪርያላይሶን፤ #ትስቡጣ ናይን፣ ኪርያላይሶን፤ ኪርያላይሶን፤ኪርያላይሶን ትእዛዝ፡- ከዚህ በኋላ ኪርያላይሶን አርባ አንድ ጊዜ ይባላል፡፡ ይኸውም በአንድ ወገን 20 ጊዜ በሌላው ወገን 21 ጊዜ በጠቅላላው 41 ጊዜ ኪርያላይሶን ኪርያላይሶን ኪርያላይሶን እየተባለ ይሰገዳል፡፡ በመጨረሻ ጊዜ፡- ✥ ስብሐት ለእግዚአብሔር ኪያነ ዘፈጠረ ከመ ናምልኮ (እናመልከው ዘንድ ለፈጠረን ለእግዚአብሔር ምስጋና ይገባል)፡፡ ✥ ስብሐት ለማርያም እመ አምላክ እግእዝትነ ወመድኃኒትነ (እመቤታችንና መድኃኒታችን ለሆነች ለአምላክ እናት ለማርያም ምስጋና ይገባል)፡፡ ✥ ስብሐት ለመስቀለ ክርስቶስ ዕፀ መድኃኒት ኃይልነ ወፀወንነ (ኃይላችን መጠጊያችን ለሆነ ድኅነት ለተገኘበት ለክርስቶስ ምስጋና ይገባል)፤፤ ጸሎተ ሃይማኖትን ሐመ እስከ ሚለው ድረስ መድገም ነው፡፡ /ከሰኞ እስከ ረቡዕ ይባላል/ ወስብሐት ለእግዚአብሔር
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи