Yamaha keyboard styles
Статистика- Последний пост
- 22 апр. 2025 г.
- Последнее чтение
- 14 авг.
- Постов за неделю
- 0
- Всего постов
- 21
- Тип
- открытый
- Язык
- und
- В каталоге с
- 14 авг.
- 1/24сутки в ленте
- —
- 1/48двое суток
- —
- 1/72трое суток
- —
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
без подписи
без подписи
Brand new ✨ Yamaha PSR-S975 keyboard 🎹🎹🎹🎹 Available collor⚫️ ⚪️ Price= call We deliver anywhere Around Addis Ababa, Hawasa, Hossana, Durame, Sodo, Arbaminch, Woliso, Welkite.... call 📞 0947125752 0941021284 chat💬@Staid7E You can order 🎹🎹🎹 PSR-SX920 PSR-SX900 PSR-SX700 PSR-SX600 PSR-S950 PSR-S970
✨enjoy
Chord harmonization. ኪይቦርድ በስታይል በምንጫወትበት ጊዜ በግራ እጃችን ኮርዶችን እንይዛለን። በዚህ ጊዜ በቀኝ እጃችን እንዳረፍንበት እንደየድምጽ የምንይዘው ኮርድ ይለያያል። ለአንዲት ቁልፍ(key) ድምጽ የተለያዩ ድምፁን ሊያጅቡልን የሚችሉ ከ3 በላይ አማራጭ ኮርዶችን ልንይዝ እንችላለን። እነዚህን ኮርዶች ከsimple እስከ advance በሰንጠረዥ ቀለል ባለ መልክ አዘጋጅቼላችኋለው። በቅርብ እዚሁ እለጥፍላችኋለው። እስከዛው share and invite friends to this channel.🥰🥰
без подписи
без подписи
без подписи
ቤተሰቦች ዛሬ በጥያቄያችሁ መሰረት ስለ መዝሙር ቅኝት ኣይነቶች አናወራለን። ዝማሬ ውስጥ ካሉ ዋና ነገሮች ውስጥ ኣንዱ ቅኝት ነው ። ዝማሬ ውስጥ የተለያዩብዙ ኣይነት ቅኝቶች ኣሉ። ከሚጠቀሟቸው የቁልፍ ብዛት (PENTATONIC, DIATONIC AND CHROMATIC) ቅኝቶች አሉ። Pentatonic ባለ አምስት ድምጽ መዝሙሮች 4ኛውን እና 7ኛውን ድምጽ የማይጠቀሙ የመዝሙር ኣይነቶች ናቸው ፣ በብዛት የተለመደ የቅኝት ኣይነት ነው። ምናልባት ከምናውቃቸው መዝሙሮች ውስጥ ከ80% በላይ መዝሙሮች pentatonic ናቸው። Diatonic ባለሰባት ድምጽ መዝሙሮችበብዛት hymnal መዝሙሮች አና contemporary music ላይ ምናገኘው የቅኝት ኣይነት ነው። አሁን ላይ ብዙ ዘማሪያን በዚህ ቅኝት መዝሙሮችን እያሰሙን ነው። Chromatic scale የምንለው በሃገራችን ብዙም ኣልተለመደም።ባለ 12 ድምጽ ቅኝት ነው። octave ውስጥ ያሉ ሁሉንም ቁልፎች በመጠቀም (ትርጉም አና ለዛ ያለው መሆን ኣለበት) ብዙ ኣይነት advanced ኮርዶችን በመጠቀም ይታወቃል። በብዛት jazz genre እና Black Gospel musics ላይ በብዛት ይደመጣል። Major scale and Minor scale ስለነዚህ ብዙ ማለት ኣይጠበቅብኝም ብዬ ኣስባለው። ሌሎችም ብዙ ኣይነት ቅኝቶች ሊኖሩ ይችላሉ። በሃገራችን ባሉ ቤተ-ክርስትያኖች ከምንጠቀማቸው ቅኝቶች መካከል ጥቂቶቹ፣ -ትዝታ Major and Minor (Ionian) ደስታዬ በጌታ ሙሉ ነው(major pentatonic) Daniel A/mikael ድሮ ገና (major Diatonic) Dawit getachew ድንቅ ስለሆነ(minor Pentatonic) Aster -Dorian አብዛኞቹ የዳንኤል አምደሚካኤልመዝሙሮች -ሲነጋም ሲመሽም፣ከኔ የሆነ፣ባባቴ ቤት፣አቤት ምህረት የበዛ -Mixo-Lydian (ኣምባሰል Maj) የዳዊት ጌታቸው ኣዲሱኣልበም ውስጥ(አንተ የልቤ ረሃብ፣ኦ ነፍሴ፣) -ባቲ Major and Minor(Aeolian) Minor ምስጋናዬ ከፍ ብሏል፡በዚህ ኣለም ምን ደስ የሚያሰኝ፣ኢትዮጵያ (መስከረም ጌቱ) Major ስትመሰገን (ዛማር መዘምራን)፣ወድሃለው ብዬ (ፓ/ር ዳዊት ሞላልኝ) በሞዶቻቸው ስናያቸው ደሞ 1st, 2nd 5th and 6th mode የምንላቸው ናቸው። እነዚህ በዋነኛነት በብዛት ቤተ-ክርስቲያን ውስጥ የምንጠቀማቸው ቅኝቶች ናቸው።
#harmony ዛሬ Harmony ማለት ምን ማለት ነው ከሚለው እንጀምር። Harmony in music. ስለ Harmony ወይም በአማርኛው ህብረ ድምጽ ስለምንለው የ ሙዚቃ ስልት ብዙ ትንተናዎችን ከተለያዩ ዌብሳይቶች ሰፋ ያሉ ትንተናዎችን ልናገኝ እንችላለን። እኛ ለጊዜው ቀለል አድርገን ለማየት እንሞክራለን። Harmony/ ህብረ ድምጽ ከስሙ እንደምናየው የተለያዩ ድምጾች በአንድ flow (በተለያየ አይነት ስልት ሊሆን ይችላል) አብረው በመሄድ የሚሰጡት ህብረ ዝማሬ ነው። ለምሳሌ በሚቀርበን ነገር ለማውራት ያክል የዚህ ቻናል ቤተሰቦች አብዛኞቻቹ ሙዚቀኞች ናችሁ። እና ስለ chord በደንብ ታውቃላችሁ። ፒያኖ ኮርድ በምንይዝበት ሰአት በትንሹ ሶስት ቁልፎችን(keys) እንይዛለን። አንዳንዴ advanced የሆኑ ኮርዶችን ስንጠቅም አራት አምስት ስድስት ቁልፎችን ልንጠቀም እንችላለን። ቁልፎች ወይም keys እያንዳንዳቸው የራሳቸው ድምጽ አላቸው። ኮርድ አድርገን አንድላይ በምንይዛቸው ጊዜ ግን እንደየአጠቃቀማችን የምንፈልገውን ህብረ ድምጽ አንድላይ ሆነው ይሰጡናል። በሰዎች የሚሰራው ኳየር Harmonyም ከዚህ ጋር ተመሳሳይ ነው። የዝማሬ ቡድኑ ውስጥ ባሉ አባላት ወይም ሰዎች የድምጽ አይነት መሰረት(ስለ ድምጽ አይነት በሌላ ክፍል በሰፊው እናያለን) የሚዘምሩት ፓርት ይለይና በልምምድ ይሰራል። በአጭሩ Harmony ማለት የተለያዩ የማይገናኙ የድምጽ ኖቶች አንድላይ በስርአት ተዋቅረው የሚሰጡት ለጆሮ ለዛ ያለው ድምጽ ነው።
ውድ ቤተሰቦች የharmony አሰራር ቴክኒክ በቅርቡ ባልናችሁ መሰረት ከሰአታት በኋላ የመጀመርያውን ልጥፍ እንለቃለን። ጠብቁን
ቤተሰቦች እንዴት ናችሁ? በዚሁ ቻናል በቅርቡ የኳየር እና ሀርሞኒ (choir & harmony) ቴክኒኮችን እና አሰራር ከsimple ጀምሮ እስከ advance ትምህርቶችን መልቀቅ እና ሐሳቦችን ከተለያዩ ልምድ ካላቸው ሙዚቀኞች ጋር ማውራት እንጀምራለን። እስከዛው ድረስ ሙዚቀኞችን እና ዘማርያንን ወደዚህ ቻናል እንድትጋብዙ እና Add እንድታደርጉ እንጠይቃችኋለን። ይህን መዝሙር እንድትሰሙት ጋበዝናችሁ። የዩትዩብ ቻናሉንም በዚያው subscribe እያደረጋችሁ እያስደረጋችሁ ጠብቁን። https://youtube.com/watch?v=U2Zd8LvgYi0&feature=share
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи