tgindex
ላምባዲና ስፖርት

ላምባዲና ስፖርት

Статистика

🏟️ ላምባዲና ስፖርት ⚽️ 📻 የ 5ቱ ታላላቅ ሊጎች እና የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግን ከአውሮፓ ሊግ ጨዋታዎች ጋር በተወዳጁ ጣብያችን ብስራት FM 101.1 ላይ በቀጥታ። ኮሜንታተር:- መሳይ ተስፋዬ 🎤 የትንታኔ ባለሞያ:- ሙሉቀን ሙጨ እና ፋኑኤል ሀብታሙ እና ተድላ ካሳ " ላምባዲና ስፖርት መርጠው የሚያዳምጡበት ብቻ ሳይሆን መርጠው የሚያዮበት"

Последний пост
12 авг.
Последнее чтение
15 авг.
Постов за неделю
1
Всего постов
28
Тип
открытый
Язык
ti
Категория
Новости и СМИ (по похожим)
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
3 651
−17 за 4 дн.
Сутки
−9
−0,25%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
745
28 постов
Вовлечённость
20,4%
к подписчикам
Постов в день
0,1
всего 28
Упоминаний
0
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
180
1/48двое суток
206
1/72трое суток
222

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • ነሐሴ  6፤2018  -   ውድ የብስራት ሬዲዮ አድማጮች የ facebook ገጻችን like, share እና Comment በማድረግ ሃሳብ አስተያየታችሁን አካፍሉን። በ-#አውሮፓ_ሱፐር_ካፕ  #ፍጻሜ   የ-#ፓሪሰን_ዠርሜን  እና #አስቶንቪላ-ን ጨዋታ #ላምባዲና_ስፖርት    ይዘውላችሁ ይቀርባሉ። ማነኛውንም ሃሳብ አስተያየት አድርሱን። መልሰን ወደ እናንተ አናደርሳለን። ምሽት  ከ3:00-6:00 ሰዓት ይጠብቁን! በመላው #ዓለም  በዩቲዩብ ገፃችን ይጠብቁን። 👇👇👇 https://www.youtube.com/@Bisrat_Fm_101.1 የብስራትን የተለያዩ ማህበራዊ ገጾች በመቀላቀል፤ ወቅታዊ መረጃዎችን እና ፕሮግራሞችን ይከታተሉ… Facebook: https://web.facebook.com/profile.php?id=61577130725400 Website: https://www.bisrattv.com/ Telegram: https://t.me/Bisrat101fm YouTube: https://bit.ly/3zAAOrB Twitter: https://twitter.com/Bisrat101fm TikTok: https://www.tiktok.com/@bisrat.fm

  • መሞከር ፣ መሞከር እና ደጋግሞ መሞከር = ስኬት በዚች ምድር ስንኖር የሚጠበቅብን ለምንኖርለት አላማ መጣር እና መታገል ከዛም ውጤቱን መጠበቅ ነው። ከዚህ ውጣ ውረድ ቡሀላ ቢሳካም ባይሳካም አሸናፊ ነን ሞክረናል እና። ዛሬ የለፋነው ለነገ የስኬታችን ሚስጥር ትልቁን ሚና ይጫወታል። ለዚህ ደግሞ ምሳሌው በዛሬው እለት በይፋ የምንግዜም ታላቅ ቡድን ለሆነው ሪያል ማድሪድ የፈረመው ያን ዲዮሞንዴ ነው!!! ይህንን ስም ከ አንድ አመት በፊት ማን በደንብ ያውቀው ነበር? ማንስ ለዚህ ሰው ከ አመት ቡሀላ ሎስ ብላንኮሶቹ 140 ሚሊዮን ዮሮ በ አጠቃላይ ያወጣሉ ብሎ አሰብ? ማንም የለም ነበር ግን ገና በ አፍላ እድሜ ማንም እሱ ላይ ሳያምን እና ተስፋ ሳያደርግ በፊት አንድ እትብት አብራው የተጋራችው እህቱ የረባ መለያ እና ታኬታ ሳይኖረው እሱን አምና አንድ ቀን እንደ ክርስትያኖ ሮናልዶ እንደሚሆን ትነግረው ነበር። ነገር ግን የህይወት መጥፎ ጎን ያመነችበት እህቱን በሰው ተመስሎ በመርዝ መርዞ ላትመለስ ከዚች ምድር ሸኝቷታል። ግን አሁንም ይችሁ ነፍስ ለወንድሟ የተመኘችው ሲሳካ ከሰማይ ሆና ፈገግ ትላለች ገና 15 አመቷም ነበር። በህይወት ስንኖር የምንኖርለት ሰው ካጣን ባዶነት ይሰማናል ለዛም ይመስላል ዲዮማንዴ " ስለ ትልልቅ ቤቶች ወይም ውድ መኪኖች ምንም አያሳስበኝም ፤ እኔ የምፈልገው እህቴ በ እኔ ላይ የነበራት እምነት ትክክል እንደነበር ማረጋገጥ ብቻ ነው። ካልሆነ ግን ይህንን ለማሳካት ስታገል እሞታለሁ " ሲል የተናገረው። አሁን በትግል መሞት አይጠበቅበትም በልጅነቱ በ ፌክ ማልያ ላይ የፃፈውን የ ሮናልዶ ታሪካዊ ቡድን ውስጥ 15 ሻምፒንስ ሊግ ባሸነፈው ሪያል ማድሪድ ውስጥ ይጫወታል። አስታውሱ ይህ ሰው በሌጋኔስ ከ አንድ አመት ተኩል በፊት ብዙዎች የማያምኑበት አንዳንዶች ደግሞ ትልቁ ኮኮብ እንደሚሆን የዘመሩለት ተጫዋች ነበር። እሱም ቢሆን የዛን ወቅት መለያ እንዲለዋወጡ ከጠየቀው ኪልያን ኤምባፔ ጋር መልበሻ ክፍል ይጋራል። ከመቀመጥ መራመድ ትልቅ ትርጉም እንዳለው ማሳያ ነው። የፅናት እና የ አላማ ምልክትም ተደርጎ ይወሰዳል። ህይወት የለፋንባትን ያሀል ትሰጠናለች ከ እኛ የሚጠበቀው አላማችንን እያዮ መራመድ ነው። እርምጃው ሁሌ መሮጥን አይጠይቅም ስለ ሮጥን ያሰብንበት በ ፍጥነት አንደርስም። ፉክክራችን ከ ትላንት ማንነታች ከሆነ ሁሌም እናሸንፋለን። " ሰላም ውድ ሮክሳኔ ወንድምሽ ያን ዲዮማንዴ አሁን ላይ በ እግርኳስ ታሪክ ወድ የ ዝውውር ገንዘብ ከወጣባቸው ተጫዋቾች ተርታ እራሱን ከቷል። የሰጠሽውን እምነት ቀርጥፎ አልበላም አሁን ኦሪጅናሉ አራያው የተጫወተበትን መለያ ለመልበስ ተዘጋጅቷል። ህልምሽ የወንድምሽ ስኬት ነበር አሁን ነፍስሽ የማረፍያዋ ጊዜ ላይ ደርሷል! የወንድምሽ ስም ያረፈበትን መለያ የከተማቹ የአቢጃን ህዝብ በኩራት ያጠልቀዋል። እሱ ሲነሳ የ አንቺ ስም ከመቃብርም በላይ ይሆናል። የሰው ልጅ አላማውን ካሸነፈ ሞት እንቅልፍ መሆኑንስ ታውቂ ይሆን? ወንድምሽ ተስፋ አመቁረጥ ይልቅ ታግሎ መሞትን ይመርጣል! አንቺም በ እሱ ውስጥ ትኖርያለሽ። አንቺ ወደ ማንቀርበት የዘላለም ቤታችን ሄደሽ ብዙዎች እንዳይረሱሽ ጀግና ወንድምሽን የምድር ፅናቱን እና አልሸነፍ ባይነቱን ፈብረከሻል ለዚህም መላው የእግርኳስ ወዳድ ያመሰግንሻል እናመሰግለን ሮክሳኔ መልካም እንቅልፍ!" በ መሳይ ተስፋዬ ✍️

  • без подписи

  • አርሰናል ከ ዘመነ ማርኪኒዮስ እስከ ቪኒሲየስ 📈 የሰሜን ለንደኑ ቡድን አርሰናል ላለፉት ረዥም አመታት የሚታይበትን ሰንኮፍ በሜዳም ከሜዳም ውጪ እያፀዳ መቷል። በሜዳ ላይ ክለቡ ከ ሀያ አመት በላይ ለመጠበቅ የተገደደውን ፕሪሚየር ሊግን ማሳካት የቻለ ሲሆን ከ 2006 ቡሀላም በ አውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የፍፃሜ ተፋላሚ ሆኗል ምንም እንኳን ዳግም ዋንጫውን ጎምዥተውት ቢያልፉም። ግን ይሄ ከ አርቴታ መምጫ በፊት ወይንም በመጣ በመጀመሪያ አመታቶች ውስጥ የነበረውን ድሪቶ እንደፀዳ የሚያመላከት ነው። ቡድኑ በተደጋጋሚ ሲያሳካ የቆየው ዋንጫ ፌኤ ካፕ መሆኑ የፆም ምግብ በቋሚነት የሚበላ አስመስሎት ቆይቷል። ከ ዋንጫ ስኬቶች ባልተናነሰ አርሰናል ሌላ የሚታማበት ደካማ ጎኑ ደግሞ የዝውውር ተሳትፎዎቹ ነበሩ። አርሰናል በዘመነ ሙክት ሁሌም ጎመን የሚገዛ ቡድን ይመስል ነበር። ከላይ በ ርእሳችን ላይ እንዳስቀመጥኩት አርሰናል በ 2022 ከ ሳኦ ፖሎ የ 19 አመቱን ተጫዋች ማርኪኒዮስን በ 3.5 ሚሊዮን ዮሮ ገዝቶ ነበር። ይህም የክለቡን የዝውውር ስታንዳርድ በ ጥቂቱም ቢሆን የሚያሳይ ነበር። አርሰናል ለረዥም አመታት ሂሳባቸው ቅናሽ ፣ በ ትልልቅ ክለቦች ውስጥ ተጫውተው የእግርኳስ ዘመናቸው ማብቅያ ላይ የደረሱ እና ብዙ ሰው ማያውቃቸውን ተጫዋቾች ብቻውን ተሰልፎ ብቻውን ተጋፍቶ የሚገዛ ለትልልቅ ስሞች ባዳ የሆነ ክለብ ይመስል ነበር። እርግጥ ነው አንድ ቡድን ከ አውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የመሰለ ትልቅ ውድድር ለረዥም አመታት ከራቀ ትልልቅ ተጫዋቾችን የማማለል ብቃቱን ያጣል አርሰናል ላይም ይሄው ነበር የተፈጠረው። በ ቬንገር ጊዜ ደግሞ ለዘመናዊ እግርኳስ መነሻ ይሆነናል ብለው ያስገነቡት ኤሜሬትስ የባንክ እዳ ቁልሎች ትልቅ ስም እንዳያስቡና ወጣት ተጫዋቾችን ከ ሀሌ ኢንድ እንዲያሳድጉ አስገድዷቸው ነበር። አሁን ይህ ሁሉ ታሪክ ነው! አርሰናል ዳግም ወደ ትልቁ ገበያ እንደገባ የሚያሳዮ ሚሊዮኖች በዝውውር መስኮቱ አውጥቷል። ከ 2019 የአርቴታ ስረው መንግስት መቋቋም ቡሀላ ብቻ መድፈኞቹ ከነ ተጨማሪ ክፍያዎች በ አጠቃላይ ወደ 1 ቢሊዮን ፓውንድ ገደማ ለዝውውሮች ወጪ አድርጓል። ለ ትልቅ ስኬት የምትከፍሉት ትልቅ ዋጋ መኖር አለበት ለዚህ ነው እጁ የማይፈታው የክለቡ ባለቤት ስታን ክሮዬንኬ ገንዘብ ማውጣት የጀመረው። ድሮ መሀመድ አሌይኒ እና ጓንዶዚ የመሳሰሉ ስሞችም ሲያስፈርም የቆየው አርሰናል በ አስገራሚ ለውጥ ለ ዴክላን ራይስ 105 ሚሊዮን ፓውንድ ከፍሏል። ይህ የ እድገቱ ማሳያ ነው። ከ ሰሞኑ ደግሞ የበለጠ የክለቡ ስም ከፍ እንዳለ የሚያሳየውን የ ቪኒሲየስ ጁኒየርን የዝውውር ሩመር እየሰማን እንገኛለን። በ አለም ላይ እንደ ቪኒሲየስ ጁኒየር አይነት ትልቅ ብራንድ የፈጠሩ ተጫዋቾችን ማስፈረም ከባድ ነው። አርሰናል ግን ይህንን የማይገፋ የሚመስል ተራራ በሚሊዮን ፓውንዶች ታግዞ ለመግፋት ቆርጦ ተነስቷል። ቪኒ አሁንም ኮንትራቱን በማድሪድ ቤት አላደሰም 11 ወራት ብቻ በ ኮንትራቱ ውስጥ የሚቀር ሲሆን ብራዚላዊው የሳንባ ዳንስ ወዳጅ አሁን ላይ ከማድሪድ ጋር ኮንትራቱን ካላረዘመ ከወርሀ መስከረም ጀምሮ ቅድምያ ስምምነቶችን በመመልከት በ 2027 ክረምት ላይ በነፃ ወኪልነት ማድሪድን እንዲለቅ የሚያደርገውን ውል በ ወርሀ ጥር ከስምምነት መድረስ የሚያስችለውን ውል ከ ሌላ ቡድን ጋር መፈረም ይችላል። የ አውሮፓ ሮያሎቹ ይህንን በፍፁም አይቀበሉም ወይ አሁኑኑ ኮንትራቱን ያራዝማል ወይ በዚኛው ክረምት ትርፋቸውን አጊኝተው ይሸጡታል። በ ቪኒ እና በማድሪድ መሀከል የ 7 ሚሊዮን ዮሮ አከባቢ የደሞዝ ፍላጎት ክፍተት አለ ማድሪድ ግፋ ቢል 20 ሚሊዮን ዮሮ መክፈል ሲፈልግ ቪኒ እስከ 27 ሚሊዮን ዮሮ ድረስ ይጠይቃል። አርሰናል ይህንን ለመክፈል ዝግጁ ይመስላል። መድፈኞቹ እንደዚህ አይነት ትልቅ ስም ያለው ተጫዋች ሲያስፈርሙ ከ እሱ ብቻ ትልቅ የስታድየም የትኬት ሽያጭ ፣ የማልያ ሽያጭ ፣ የሶሻል ሚድያ የተከታዮችን ቁጥር መጨመር ይዞ የሚመጣለት ትልቅ ገቢ ይኖራል። አርሰናል ቤት ደግሞ በዚህ የጥራት ደረጃ የሚጫወት ትልቅ ተጫዋች ላለፉት አመታት አለማየታችን ቡድኑን በ አውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ አሸናፊ እንዲሆንም ሊረዳው እንደሚችል ይጠበቃል ምክንያቱም ቪኒ ሁለት ጊዜ የእሱ አቋም ልዮነት በፈጠረበት የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የፍፃሜ ጨዋታ ማድሪድ እንዲነግስ አድርጓል። አሁን ላይ ከ ወኪሎቹ ጋር ንግግሮች እንደተጀመሩ መረጃዎች እየወጡ ቢሆንም ይህ ዝውውር ባይሳካ እንኳን ከ አሁን ቡሀላ የአርሰናል ካዝና ትልቅ መሆኑን የሚያሳይ ነው። ከ ቀናቶች በፊት ደግሞ የ ስታን ክሮዬንኬ ልጅ ጆሽ ክሮዬንኬ እንዲህ ሲል ተናግሮ ነበር "ትኩረታችን በዋጋው ላይ ሳይሆን በጥራቱ ላይ ነው ፤ ትክክለኛውን ተጫዋች ለማምጣት 200 ሚሊዮን ፓውንድ የሚያስፈልግ ከሆነ እና ያ ተጫዋች ክለቡን ከፍ ሊያደርግና ዋንጫዎችን እንድናሸንፍ ሊያግዘን እንደሚችል በእውነት ካመንን ሁሉንም አማራጮች እንመለከታለን ፤ ዓላማችን በአውሮፓ ካሉ ምርጥ ቡድኖች ጋር መወዳደር የሚችል ስብስብ መገንባት ነው " ሲል አስተያየቱን ሰቷል። አርሰናል በ እርግጥ 11 ወራት ብቻ ኮንትራቱ ላይ ለቀረው ተጫዋች ከ 150 ሚሊዮን ዮሮ በላይ ይከፍላል ተብሎ አይገመትም ማድሪድም ከ ቪኒ ጋር ካልተስማማ ሂሳቡን ከዛም በታች ሊያወርድ ይችላል ምክንያቱም በቀጣይ አመት በነፃ ተጫዋቹን ማጣት ስለማይፈልግ። ነገሮች በሚቀጥሉት ቀናት የመጨረሻ ምእራፍ ላይ ይደርሳሉ ተብሎ ይጠበቃል። በ መሳይ ተስፋዬ ✍️

  • без подписи

  • без подписи

  • ሰኔ 28፤2018 - ውድ የብስራት ሬዲዮ አድማጮች የ facebook ገጻችን like, share እና Comment በማድረግ ሃሳብ አስተያየታችሁን አካፍሉን። በ-#አለም_ዋንጫ የ-#ሜክሲኮ እና #እንግሊዝ-ን ጨዋታ #ላምባዲና_ስፖርት ይዘውላችሁ ይቀርባሉ። ማነኛውንም ሃሳብ አስተያየት አድርሱን። መልሰን ወደ እናንተ አናደርሳለን። ሌሊት ከ8:00-11:00 ሰዓት ይጠብቁን! በመላው #ዓለም በዩቲዩብ ገፃችን ይጠብቁን። 👇👇👇 https://www.youtube.com/@Bisrat_Fm_101.1 የብስራትን የተለያዩ ማህበራዊ ገጾች በመቀላቀል፤ ወቅታዊ መረጃዎችን እና ፕሮግራሞችን ይከታተሉ… Facebook: https://web.facebook.com/profile.php?id=61577130725400 Website: https://www.bisrattv.com/ Telegram: https://t.me/Bisrat101fm YouTube: https://bit.ly/3zAAOrB Twitter: https://twitter.com/Bisrat101fm TikTok: https://www.tiktok.com/@bisrat.fm

  • " ከፍተኛ የ ተጫዋቾች የዋጋ ንረት በ ሀገረ እንግሊዝ " የተጫዋቾች ዝውውር ዋጋ ከዚህ ቀደም ከምናውቀው ሂሳብ ለየት ባለ መልኩ ከ ቀን ወደ ቀን እየጨመረ መቷል። ቀድሞውኑም በ ዮናይትድ ኪንግደም የተጫዋቾች ሽያጭ ዋጋ የተጋነነ ነው ተብሎ ይታማ የነበረ ቢሆንም አሁን ላይ ግን ከዛም የከፋ ሆኖ ከሰሞኑ የብዙሀኑ መነጋገርያ ሆኗል። ግን ይህ በ እግርኳስ ትልቁ የገንዘብ ማሸጋርያ አካል የሆነው የተጫዋቾች ዝውውር ለምን በዚህ ልክ ከፍተኛ የሂሳብ ለውጥ አመጣ ብላቹ ታውቃላቹ? ይህ የሆነበትን ምክንያት በዝርዝር እናብራራዋለን ተከታተሉ። በ ሀገረ እንግሊዝ ከ እግርኳሱ ጥራት የበለጠ ሚድያው የተገነባ ይመስላል። ይህም ደግሞ ነገሮችን በ እራሳቸው ቁጥጥር አድርገው ለዘመናት የእግርኳስ ጥራት መለክያ ጭምር እንዲሆኑ ረድቷቸዋል። በዋናነት ደግሞ በ ፕሪሚየር ሊግ ውስጥ የሚጫወት የ አንድ የተጫዋች ሂሳብን ከፍ ማድረግ እና በገበያው ላይ ረብጣ ሚሊዮኖች እንዲወጡበት ማድረግ አስችሏቸዋል። በተለይ ተጫዋቹ የዛው የሀገሪቱ ተወላጅ ከሆነ ብቃቱ እምብዛም ቢሆን እንኳን በውድድር አመት ውስጥ የሚያሳየው አጀማመር መልካም የሚባል ከሆነ በ እጥፍ ሂሳቡ ይጨምራል። ይህ ከሚሆንባቸው ምክንያቶች አንዱ ቀድሞውኑ የሰሩበት " HUGE TV REVENUE " ወይንም ትልቅ የሆነ የ ቲቪ ገቢ ነው። ፕሪሚየር ሊጉ እንደ አወዳዳሪ አካል የክለቦችን ብቃት መዝኖ በሀላፊነት የ ቲቪ መብቱን ተጠቅሞ ለ ገበያ ያቀርባል ከዛም ደግሞ ለ እያንዳንዱ ክለብ በ እኩሌታ ትርፉን እንዲያዳርስ ያደርገዋል ይህም ክለቦች የሚያገኙት ገቢን ተመጣጣኝ አድርጎ ለተጫዋቾች የሚከፍሉትን ደሞዝ ከፍተኛ ስለሚያደርገው አንድ ክለብ ከ ሌላው ክለብ አያንስም ይህም አካሄድ የተጫዋቾቻቸው ብቃት እላይ ደርሶ በሌሎች ክለቦች ቢፈለግ እንኳን ተጫዋቹን በፍጥነት ሽጠው ትርፉን እንዲያስቡ የሚያስገድዳቸው አንገብጋቢ የ ገንዘብ ችግር ውስጥ አያስገባቸውም። ሌላው " COMMERCIAL INCOME " ወይንም የንግድ ገቢ ነው። ይህንን ስንል በ ሊጉ ያሉ ቡድኖች ሀገሪቱ በ እግርኳሱ ላይ በገነባችበት ትልቅ የ ሚድያ እይታ ምክንያት ተደራሽነታቸውን አለም አቀፍ አድርገው ከተለያዮ ድርጅቶች ጋር እና ትልልቅ ብረንዶች ጋር በመስራት ገቢያቸውን እንዲያካብቱ ያደርጋቸዋል። በ አለም መድረክ በርካታ ደጋፊዎች ስለሚያፈሩ በነሱ በኩል የሚተዋወቁ ምርት እና አግልግሎቶች በቀላሉ ተደራሽ እንዲሆን ያደርግላቸዋል። እነዚህን ማስታወቅያዎች በ መለያ ፅሁፎች ፣ በስቴድየም አሌክትሮኒክ ቢል ቦርዶች እንዲሁም በተለያዮ ዘርፈ ብዙ አማራጮች እንዲያስተዋውቁ ይረዳቸዋል። ሌላው እና አሁን ላይ ደግሞ በጣም እየተለመደ የመጣው የተጫዋች ዋጋ ጣርያ መስቀያ መንደግ ደግሞ " COMPETITION OF PLAYERS QUALITY " ወይንም የተጫዋቾች የ ግል ብቃት ንፅፅር ነው። ይህ በቅርብ የመጣ ነገር ግን ገበያው በከፍተኛ ሁኔታ ከፍ እንዲል እያደረገ የሚገኝ ቁልፍ ተዋናይ ነው። ለምሳሌ ከሰሞኑ የ ኖቲንግሃም ፎረስቱ አማካኝ አሌዮት ኤንደርሰን 116 ሚሊዮን ፓውንድ ወቶበት ወደ ማንቸስተር ሲቲ ዝውውሩን ካጠናቀቀ ቡሀላ የሌሎች ተጫዋቾችን ሂሳብም አብሮ ሰቅሎታል። ይህም ማለት ከዛው ከ እንግሊዝ ሳንወጣ በቅርቡ በ ስኬት ጎዳና ላይ እየተራመደ የሚገኘው አስቶን ቪላ ኮኮቡ ሞርጋን ሮጀርስ ላይ ቀድሞ ከተቀመጠው ሂሳብ ዳጎስ ያለ ጭማሪ በማድረግ ዋጋውን አሁን ላይ 130 ሚሊዮን ፓውንድ እንዲሆን አድርጎታል። ወረርሽኙ ከ ሀገሪቱ አልፎ ፓሪስ ደርሶ የ ሁለት ተከታታይ አመት የአውሮፓ የንግስና ዙፋን የደፉት ፓሪስ ሴንት ጀርሜኖችን የመስመር ተጫዋቻቸው ብራድሌይ ባርኮላን ፈልጎ ለሚመጣ የተኛውም ቡድን ከ ገበያው አንፃር 116 ሚሊዮን ፓውንድ ይገባዋል ብለው በማሰብ ይህንን ሂሳብ ለጥፈውበታል። የተጫዋቹ ሁነኛ ፈላጊዎች ደግሞ ሊቨርፑል እና አርሰናል መሆናቸው ሂሳቡን በ ሀገራቸው መገበያያ " ፓውንድ " እንዲሆን ያደርጉታል። ከሰሞኑ ቶተንሀምን ለመቀላቀል ከ ስምምነት የደረሱት ማትያስ ፈርናንዴዝ እና ቶናሊም በ አጠቃላይ 185 ሚሊዮን ፓውንድ እንደሚወጣባቸው ማስታወስ ያለብን ሲሆን አንድ አመት በ ቼሪዎቹ ቦርንማውዞች ቤት አብቦ ያየነው አሌክስ ስኮትም እስከ 80 ሚሊዮን ፓውንድ የሚገመት መሆኑ በሀገሪቱ የተጫዋቾች ሂሳብ መነሻ ዋጋ ከ 80 እንዲጀምር የገበያውን እጅ ጠምዝዞ እያሳመነው መስሏል። በ እርግጥ የገንዘብ ዋጋ እንደ አምና እና ካቻምና አለመሆን በዛ ላይ ደግሞ የ እንግሊዝ የ ታክስ ክፍያ ንረት በ ተጫዋቾቹ ዋጋ ውድነት ላይ ቁልፉን ሚና ይጫወታል። ይህ ሲስተም ለ እግርኳሱ ግን ጠንቅ እንዳይሆንም ያሰጋል ምክንያቱም በ 100 ሚሊዮን ፓውንድ ዝውውሩን የሚጨርስ አንድ ተጫዋች የሚሸከመው ጫና ከፍተኛ መሆኑ እና እንከን ከታየበት ደግሞ ቢላውን አስሎ የሚጠበቀው የሀገሪቱ ጋዜጣ ፣ ሚድያ ፣ ጋዜጠኛ እና የቀድሞ እግርኳስ ተጫዋቾች ዋነኛ እክሎች ስለሚሆኑ ነው። ፊፋ ወይንም የአውሮፓ እግርኳስ ፌዴሬሽን በመጪዎቹ አመታት ይህንን አካሄድ ጣልቃ ገብቶ መላ ካላበጀለት ከዚህም የከፋ እየሆነ መሄዱ አይቀሬ ይመስላል። በ መሳይ ተስፋዬ ✍️

  • без подписи

  • без подписи

  • 11 июн.1 1943

    የፊፋ ፒስ ፕራይዝ አሸናፊው ሰው አነጋጋሪ ውሳኔዎች በ አለም ዋንጫው! እግርኳስ እራሱን ችሎ የሚቆም በ ቢሊዮን ለሚቆጠሩ ሰዎች ትልቅ የመዝናኛ መስክ የሆነ እና ከ ዘር ፣ ከሀይማኖት ፣ ከ ፖለቲካ ውጪ የሆነ ትልቅ ኢንዱስትሪ ነው። በተለይ ደግሞ የአለም ዋንጫን የመሰለ ትልቅ የእግርኳሱ አንድ አካል ፆታን እና እድሜን ሳይገድብ ለ ሁሉም የሚደርስ አንድ የተወዳጁ የእግርኳስ ምእራፍ ሆኖ ለ በርካታ አመታት ቆይቷል። በዛሬው እለት በጣምራ በ ካናዳ ፣ ሜክሲኮ እና አሜሪካ የሚዘጋጀው የ 2026ቱ የአለም ዋንጫ በ ይፋ የሚጀምር ይሆናል። ነገር ግን በ ጣምራ ሊዘጋጅ ቢችልም እንኳን ከ 80% በላይ የሚሆኑ ጨዋታዎች በ አሜሪካ የተለያዮ ስቴቶች ተከፋፍለው የሚደረጉ ይሆናል። ላለፉት አመታት የአለም ዋንጫ አዘጋጅ ሀገሮች ለጨዋታ የሚመጡ ሀገራት ተጫዋቾች እና በውድድሩ ላይ ተሳትፎዋቸው ወሳኝ የሆኑ አካላትን ትልቅ አቀባበል አድርገው ወደ ሀገራቸው ሲያስገቡ እንመለከት ነበር። ዘንድሮ ግን ነገሮች በተቃራኒ መልኩ እየተጓዙ ይገኛሉ አዘጋጅ ሀገር አሜሪካ ከዚህ በፊት በ አለም ዋንጫው ባልተለመደ መልኩ ወጣ ያሉ ነገሮችን እያሳየች ሲሆን ከ ኢራን ጋር በተያያዘ ባላት አለመስማማት ምክንያት በ ውድድሩ ብሔራዊ ቡድኑ ሀገረ አሜሪካ አይገባም ተብሎ ሲነገር ቢቆይም በስተመጨረሻም ፊፋ ኢራን በ አለም ዋንጫው እንደምትኖር አረጋግጦ ነበር። ይሁን እንጂ የኢራን ብሔራዊ ቡድን በውድድሩ ብትኖርም ከጨዋታ ቡሀላ ከውድድሩ አዘጋጆች መሀከል አንዷ በሆነችው ሜክሲኮ እየሄዱ በተዘጋጀላቸው ቦታ ያርፋሉ እንጂ አሜሪካ አይቆዮም። የ ሀይቲ ብሔራዊ ቡድን ለመጀመሪያ ጊዜ በአለም ዋንጫው ተሳታፊ መሆን ቢችልም ደጋፊዎች ቪዛ ለማግኘት እንኳን ጥያቄ ማቅረብ አይችሉም። ይህ ደግሞ ለ አንዳንድ የአፍሪካ ተወካይ ሀገራትም የሚሰራ ህግ ሲሆን ሌላው ቀርቶ እንደ ሴኔጋል የመሰሉ ሀገራቶች ለወድድሩ አሜሪካ ሲገቡ ጥብቅ የሚባል የረዥም ሰአት ፍተሻ ሲደረግባቸው መስተዋሉ ነገሩን ከ ዘረኝነት ጋርም አያይዞታል። ከሰሞኑ ደግሞ በርካታ የእግርኳስ አፍቃሪያንን እንዲሁም አፍሪካውያንን ያስቆጣው ተግባር የ 34 አመቱ ሶማሌያዊ አልቢተር ኦማር አብዱልቀድር አርታን ላይ የተፈጠረው ጉዳይ ነበር። አልቢተሩ የአፍሪካ የአመቱ ምርጥ ዳኛ ተብሎ የተመረጠ ሲሆን በ ካፍ የአፍሪካ ሻምፒዮንስ ሊግ እና የአፍሪካ ዋንጫ ጨዋታዎችም ላይ ድንቅ ብቃቱን ማሳየት ችሏል። ወጣቱ የጨዋታ ዳኛ ፊፋ ለ አለም ዋንጫው የመጥናሉ ብሎ ለ ውድድሩ ከወከላቸው አፍሪካውያን ዳኞች መሀከል ግንባር ቀደሙ የነበረ ሲሆን ወደ ስፍራው አቅንቶ ሚያሚ አለም አቀፍ ኤርፖርት ሲደርስ ነበር ወደ አሜሪካ እንደማይገባ ተነግሮት ወደ ቱርክ የተላከው ከዛም ግን በስተመጨረሻ ወደ ሶማልያ ተመልሶ ደማቅ አቀባበል በ ሞቃዲሾ ተደርጎለት ወደ እናት ሀገሩ ተመልሷል። ይህ የሆነበት ምክንያት ደግሞ አሜሪካ ከ አፍሪካ ሀገራት ወደ ሀገሯ ዘልቀው እንዳይገቡ ከከለከለቻቸው ሀገራት መሀከል ቀዳሚዋ ሶማልያ መሆኗ ነው። ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕም ቢሆን በተደጋጋሚ ዘለፋ ካደረሰባቸው ሀገራት መሀከል አንዷ የ ኦማር አርታን ሀገር ሶማልያ መሆኗ ይታወቃል። በቅድምያ ጥያቄ የሚነሳው የእግርኳስ አስተዳዳሪ አካል የሆነው ፊፋ ላይ ነው። ፊፋ ቀድሞውኑ የ አሜሪካ መግብያ መብቷን በተነጠቀችው ሀገር ተወላጅ የሆነን አልቢተር ወደ ውድድር ስፍራው ለመላክ በማቀድ ዝርዝር ውስጥ መክተቱ ከዛም ደግሞ ዳኛው እግድ ሲመጣበት ከለላ ከመሆን ይልቅ ሀላፊነት ለመውሰድ አለመጣሩ የተቋሙ ፕሬዝዳንት የሆኑት ጂያኒ ኢንፋንቲኒዮ ላይ ትችት ያሰነዘረ ነበር። ሰውየው ቀድሞውኑ ከ ዶናልድ ትራምፕ ጋር ያለው ጥብቅ ግንኙነት በ ብዙ የሚያስተቸው ሲሆን ይህ ሲደመርበት ደግሞ ነገሩን ሌላ ምስል ሰቶታል። በ መሳይ ተስፋዬ ✍️

  • без подписи

  • без подписи

  • የ ጠላቴ ጠላት ወዳጄ ነው 🤷‍♂ ዛሬ ሪያል ማድሪዶች ለ ጁሊያን አልቫሬዝ የ 150 ሚሊዮን ዮሮ ጥያቄ ለ አትሌቲኮ ማድሪድ ልከዋል። ይሄ አስገራሚ ቢመስልም ግልፅ ሴራ ነው እንጂ በ እውነት አልቫሬዝ በትክክል በማድሪድ የሚፈለግ profile ያለው ተጫዋች ነው? እሱን እንተወውና ቀድሜ እንዳልኩት አትሌቲኮ ማድሪድ እና ሪያል ማድሪድ ባልተመደ መልኩ ለ ተጫዋች የተላከ ጥያቄን ኦፊሻል በማድረግ ውድቅ አድርገውት በ ሶሻል ሚድያ ላይም እንደለመዱት ፌዛቸውን ቀጥለዋል። ቀደም ብሎ ፔሬዝ 150 ሚሊዮን ዮሮ ጥያቄ አቀርባለው አለ እንጂ አስፈርማለው አላለም። በ እውነቱ ገበያው ተዋዷል ነገር ግን አልቫሬዝ 150 ሚሊዮን ዮሮ የሚያወጣ አጥቂስ ነው? ለማድሪድስ በዚህ ሰአት እንደሱ አይነት ተጫዋች 150 ሚሊዮን ዮሮ የሚያወጡበት ሰአት ነው። በ እርግጥ አልቫሬዝ Versatile የሆነ ተጫዋች ነው ነገር ግን ማድሪድ በተደጋጋሚ የባላንስ ጥያቄ እየተነሳበት ከ 9 ቁጥር ቦታ ውጪ የበለጠ ግራ ዘመም አጨዋወትን የሚከተል ተጫዋች ይፈልጋል??? ማድሪድ የተከተለው ስትራቴጂ በግሌ የሚመስለኝ ትልቅ ተጫዋች ወደ ተቀናቃኙ ቡድን ከሚሄድ ያንን ተጫዋች ማዋደድ የሚመስል ነው። ስለዚህ ፔሬዝ የገባው ቃል አቀርባለው የሚል እንጂ አመጣለው የሚል ስላልሆነ ምንም ጫና ውስጥ አይገባም ሞክሬ ነበር የሚለው ቃል በቂ ነው። ስለዚህ ባርሴሎና አሁን ላይ ወደ አልቫሬዝ ገበያ መመለስ ቢፈልግ እንኳን ከ 150 ሚሊዮን ዮሮ ማቅረብ ይጠበቅበታል። በስተመጨረሻም አትሌቲኮ አሁናዊ አቋሙ አልቫሬዝን ከሸጡት እንኳን ከ ስፔን ቡድኖች ውጪ ማድረግ ነው። የዝውውር ወቅቱ ገና ማለዳ ላይ ቢገኝም ለ ባርሴሎና ግን የ PLAN B ጊዜ የደረሰ ይመስላል ማድሪድ ባርሳን ከ ጨዋታው ውጪ ያደረገው ይመስላል። በ መሳይ ተስፋዬ ✍️

  • ግንቦት 22 ፤ 2018 በቅዳሜ ከሰዓት ፕሮግራማችን #ላምባዲና #መዝናኛዎች በተለየ አቀራረብ ይጠብቋችኋል። የሙዚቃ ግብዣዎችም ተዘጋጅተዋል ዛሬም እንደተለመደዉ የኢትዮጲያ የሙዚቃ ባለዉለታ የሆነን ታላቅ ሰዉ እንግዳችን ሆኖ ከእኛ ጋ ቆይታ ያደርጋል። እናንተ ብቻ ከተወዳጁ ጣቢያ ብስራት fm 101.1 ጋር ከሆናችሁ ሁሉ ሙሉ ሁሉ ዝግጁ ማነኛውንም ሃሳብ አስተያየት አድርሱን። መልሰን ወደ እናንተ አናደርሳለን። ከ 9:00-11:00 ሰዓት ይጠብቁን! #BisratNews #BisratFm #BisratRadio #sports የብስራትን የተለያዩ ማህበራዊ ገጾች በመቀላቀል፤ ወቅታዊ መረጃዎችን እና ፕሮግራሞችን ይከታተሉ… Facebook: https://web.facebook.com/profile.php?id=61577130725400 Website: https://www.bisrattv.com/ Telegram: https://t.me/Bisrat101fm YouTube: https://bit.ly/3zAAOrB Twitter: https://twitter.com/Bisrat101

  • ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለ1447ኛው የዒድ አል-አድሃ (አረፋ) በዓል በሰላም አደረሳችሁ ❤️ መልካም በዓል 🙏 ከላምባዲና ስፖርት አዘጋጆች

  • 24 мая1 0716

    https://youtu.be/S9iB5vU2dcY?si=Yh07vX1Kfot8kqWK

  • 21 мая1 04171

    በርንሌይ ከ ባርሴሎና የበለጠ ገቢ ማግኘት ችሏል! ወትሮውንም በገቢ ደረጃ ተፎካካሪ የሌለው የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ከቀሩት ትልልቅ ሊጎች ጋር ያለው የገቢ መጠን እና ክፍፍል እላይ እና ታች ሆኗል። የእንግሊዝ ሚድያ ላለፉት አመታት ተፅዕኖ ላቅ ያለ ነው በተለይ ደግሞ በ እግርኳሱ ላይ። ይህ ደግሞ ካዝናቸውን ከ ግዜ ወደ ግዜ እንዲሞላ ማድረግ ያስቻለ ሲሆን በ ሊጉ ውስጥ ያሉ ቡድኖችንም ባለ ፀጋ እንዲሆኑ ረድቷቸዋል። ለዚህም ነው ከ ፕሪሚየር ሊግ ወደ ሻምፒዮን ሺፕ የወረዱ ቡድኖች ዳግም ራሳቸውን አጎልብተው በመጪው የውድድር አመት ወደ ሊጉ ሲመለሱ የምንመለከተው። የ ቴሌቪዥን መብት ፣ የስፖንሰርሺፕ ስምምነቶች ፣ የስታድየም ትኬት ሽያጭ ደግሞ ለዚህ ባለፀጋነት ምሶሶ ሆኗቸው እናገኘዋለን በተለይ ደግሞ የቴሌቪዥን መብት። ከ ፕሪሚየር ሊጉ ለሚወርዱ ቡድኖች የተዘጋጀ እና ቡድኖቹ የፋይናንስ መዋዠቅ እንዳያጋጥማቸው ተብሎ በማሰብ የሚዘጋጀው የ " Parachute payment " ሂደትም ቡድኖች ከ ቴሌቪዥን መብት 55% እንዲያገኙ የሚረዳቸው ሲሆን በዚህም አንድ ወደ ሻምፒዮንሺፕ የሚወርድ ቡድን ከ 40 ሚሊዮን ፓውንድ እስከ 50 ሚሊዮን ፓውንድ ድረስ ወደ ካዝናው እንዲከት ይረዳዋል። በ እርግጥ ይህ የ ክፍያ ሂደት  ለወራጆች አድልቶ በ ሻምፒዮንሺፑ የሚታገሉ ቡድኖችን የሚጎዳ ነው ሲሉ አንዳንዶች ይተቹታል። ታድያ ወራጅ ቡድኖች ቢያንስ በትንሹ ከ ፕሪሚየር ሊጉ 100 ሚሊዮን ፓውንድ ድጎማ ተደርጎላቸው ወደ ታችኛው ሊግ በ ክብር የሚሸኙም ይሆናል። ይህ ግን በሌሎች ሊጎች የዋንጫ ባለቤት የሆነ ቡድን እንኳን ሊያገኘው የማይችል ገቢ ነው ለምሳሌ በ ሀቪዬር ቴባስ ፕሬዝዳንትነት የሚመራው ላሊጋ አንዱ ነው። ላሊጋ ቢያንስ አንድ 2 አስርት አመታትን ወደ ኋላ የምንሄድ ቢሆን እንኳን ትልቅ ከሆኑ ሊጎች መሀከል አንዱ ተደርጎ የሚወሰድ እና ትልልቅ ኮኮቦች የሚጫወቱበት በ አውሮፓም ጭምር ከባድ ተፎካካሪ የሆኑ ቡድኖች መገኛ ሊግ ነው። ነገር ግን በ ሊጉ ውስጥ ባለ የፋይናንስ ጥብቅ ቁጥጥር ምክንያት ከ ቅርብ ጊዜ ወዲህ በዝውውር መስኮትም የሊጉ ቡድኖች ተሳታፊ ሲሆኑ አናይም እንዲሁም ደግሞ በገቢም ደረጃ በ በቂ ሁኔታ አይደጎሙም። ለዚህም ይመስላል በ ሊጉ ካሉ ጥሩ ቡድኖች መሀከል የሚገኙት ሲቪያ እና ቫሌንሲያ በ ቅርብ ጊዜ የፋይናንስ ቀውስ ውስጥ ገብተው በ ሊጉ ውስጥ ውጤት በማጣት ወደ ሴጉንዳው አዳልጧቸው ለመግባት ሲቃረቡ ያየነው። ቀድሞውኑ በዘመነ ባርቶሚዮ ትልልቅ ቡድሮች ውስጥ ሲገባ ከርሞ የፋይናንስ ቀውሱ ትልቁን ኮኮቡን ሊዮኔል ሜሲንም እንዲያጣ ያስገደደው ባርሴሎናም ቢሆን ላለፉት አመታት በ በቂ ሁኔታ ትርፋማ አልነበረም። ከ ሰሞኑ ደግሞ የእንግሊዙ ቡድን በርንሌይ ከ ፕሪሚየር ሊጉ ወርዶ እንኳን በ ገቢ የ አምስት ጊዜ የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ አሸናፊውን ባርሴሎናን በልጦታል። የ ቲሌቪዥን ገቢ ትርፍ እና የ ሊግ ደረጃን አጠቃሎ ባርሴሎና ዘንድሮ 155 ሚሊዮን ዮሮ ወደ ካዝናው ሲያስገባ በ አንፃሩ ቀጣይ አመት በ እንግሊዝ ታችኛው ሊግ የሚጫወተው በርንሌይ 160 ሚሊዮን ዮሮ ማግኘት ችሏል። በ ስኳድ ጥራት ፣ በደጋፊዎች ብዛት ፣ በ ስቴድየም ስፋት ፣ በታሪክ ለውድድር የማይበቁት ሁለቱ ቡድኖችን ታድያ ምን አበላለጣቸው ከተባለ አለም ሁሉ ትኩረቱን የሚጥልበት የ እንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መልሱ ይሆናል። በ መሳይ ተስፋዬ ✍️

  • без подписи

  • ለመድፈኞቹ 40 ሜዳሊያዎች ተዘጋጅተዋል ሁለት የክለቡ ተጫዋቾች ሽልማቱን ማግኘት አይችሉም የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል በመጪዉ እሁድ በሰል ኸረስት ፓርክ የመጨረሻ ጨዋታቸዉን ከ ክሪስታል ፓላስ ጋር ካደረጉ በኋላ የዋንጫ እና የሜዳሊያ ሽልማታቸዉን በእለቱ ከሚገኙ የክብር እንግዶች እጅ የሚቀበሉ ይሆናል። ፕሪሚየር ሊጉ 40 የሚደርሱ ሜዳሊያዎች ያዘጋጁ ሲሆን ለተጫዋቾች ለክለብ አመራሮች እና ለባለስልጣናት እንደሚከፋፈል ተሰምቷል። የአርሰናል ተጫዋቾች የሆኑት የቀድሞዉ የቼልሲ ተጫዋች የነበረዉ ስፔናዊዉ ኬፓ አሪዛባላጋ እና እንዲሁም ወጣቱ ተጫዋች ማርሊ ሳልሞን የሜዳሊያ መስፈርቱን ስለማያሟሉ ሽልማቱ እንደማይሰጣቸዉ ተነግሯል። ምክኒያቱ ደግሞ ኬፓና ሳልሞን በሊጉ ከ 5 ጨዋታ በታች ነዉ ማድረግ የቻሉት ሜዳሊያዉን ለማግኘት በአመት ዉስጥ በፕሪሚየር ሊጉ 5 ጨዋታ የግድ ማድረግ ያስፈልጋል የሚል ህግ ስላለ ኬፓና ሳልሞን የሜዳሊያ ሽልማቱ እንደሚያመልጣቸዉ ተገልጿል። በ- ሙሉቀን ሙጨ ⚽️