የሕግ ነገር ⚖️
СтатистикаWell come to የሕግ ነገር channel. This channel aims to improve students skill and knowledge about law and raise puplic awareness in law cases 🔸legal Notes 🔸volumes 🔸proclamations 🔸Exit exams
- Последний пост
- 11 авг.
- Последнее чтение
- 15 авг.
- Постов за неделю
- 2
- Всего постов
- 25
- Тип
- открытый
- Язык
- und
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 98
- 1/48двое суток
- 112
- 1/72трое суток
- 121
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
የሰውን ፎቶ ወይም ቪዲዮ ያለፍቃድ ሶሻል ሚዲያ ላይ መፖሰት የሚያስከትለው የወንጀል ተጠያቂነት ⚖️⚖️⚖️⚖️⚖️⚖️⚖️⚖️⚖️⚖️⚖️⚖️ የሰውን ፎቶ ወይም ቪዲዮ ያለባለቤቱ ፈቃድ በማህበራዊ ሚዲያ (Social Media) ላይ መፖሰት በኢትዮጵያ ህግ መሰረት ከባድ የወንጀልና የፍትሐብሔር (የካሳ) ተጠያቂነት ያመጣል። ድርጊቱ የሚዳኘው በዋነኝነት በ2008 ዓ.ም በወጣው የሳይበር ወንጀል አዋጅ (አዋጅ ቁጥር 958/2008)፣ በወንጀል ሕግ (2004) እና በፍትሐብሔር ሕግ ነው፡፡ 1. በወንጀል ሕግ የሚያስከትለው ተጠያቂነት 🔹 የሳይበር ወንጀል አዋጅ (አዋጅ ቁጥር 958/2008)፦ ስም ማጥፋትና ክብርን መንካት (አንቀጽ 13)፦ የሰውን ምስል ወይም ቪዲዮ በመጠቀም የሰውን ስምና ክብር የሚነካ ወይም የሚያዋርድ መረጃ ማሰራጨት እስከ 3 ዓመት በሚደርስ እስራት ወይም በመቀጮ ያስቀጣል። የግል ሕይወት ምስጢርነትን መጣስ (አንቀጽ 14)፦ የአንድን ሰው የግል ሕይወት የሚያሳይ ምስል ወይም ቪዲዮ ያለ ፈቃድ ማሰራጨት ከ 1 ዓመት እስከ 5 ዓመት በሚደርስ ጽኑ እስራት ያስቀጣል። ምስልን በማቀናበር (Edit/AI) ማሰራጨት፦ የሰውን ፎቶ በመቀየር ወይም በማካበብ ሰውን ለመጉዳት ከተለጠፈ ቅጣቱ የበለጠ የከበደ ይሆናል። 🔹 የኢፌዴሪ ወንጀል ሕግ (2004)፦ ስም ማጥፋት (አንቀጽ 613)፦ በማንኛውም መንገድ የሰውን መልካም ስም የሚያጎድፍ ነገር ማሰራጨት በጥፋተኝነት ያስጠይቃል። እፍረተ-ከንቱ ምስሎችን ማሰራጨት (አንቀጽ 640/641)፦ የሰውን ነውረኛ ፎቶ ወይም ቪዲዮ ያለፍቃድ ማሰራጨት (Revenge Porn) እስከ 5 ዓመት ወይም ከዚያ በላይ ጽኑ እስራት ያስቀጣል። 2. በፍትሐብሔር ሕግ የሚያስከትለው ተጠያቂነት (የካሳ ጥያቄ) ተጎጂው ግለሰብ በፍትሐብሔር ሕግ (አንቀጽ 2032) መሠረት፦ የሞራል ካሳ፦ ለደረሰበት የስነ-ልቦና ጉዳትና የእፍረት ስሜት የገንዘብ ካሳ መጠየቅ ይችላል። የቁሳቁስ ካሳ፦ ፎቶው በመፖሰቱ ምክንያት ከስራ ቢሰናበት ወይም የገንዘብ ጉዳት ቢደርስበት ካሳ የማስከፈል መብት አለው። ምስሉ እንዲወገድ የማድረግ መብት፦ ድርጊቱ እንዲቆም፣ ምስሉ እንዲሰረዝ እና ይቅርታ በይፋ እንዲጠየቅ ማድረግ ይቻላል። 3. ሕጋዊ ሊሆኑ የሚችሉ አጋጣሚዎች ለሕዝብ ጥቅም ሲባል፦ ወንጀለኛን ለመያዝ ወይም የጠፋን ሰው ለመፈለግ በሕግ አስከባሪዎች የሚደረግ ከሆነ። በሕዝባዊ መድረክ ላይ ያለ ምስል፦ በባህሪው ለሕዝብ ክፍት በሆነ ትልቅ ስብሰባ ላይ የተነሳ ፎቶ ሆኖ፣ የተወሰነን ግለሰብ ለማጥቃት ካልተፈለገ። 💡 ማጠቃለያ፦ የሰውን ምስል ያለባለቤቱ እውቅና ማህበራዊ ሚዲያ ላይ መፖሰት ከእስራት እስከ ከፍተኛ የገንዘብ ካሳ የሚያስከትል የሳይበር ወንጀል ነው።
🔴25 የሙስና ወንጀሎች🔴 (አዋጅ ቁጥር 881/2007 ) 1. በሥልጣን ያለአግባብ መገልገል (አንቀፅ 9) 2. ጉቦ መቀበል (አንቀፅ 10) 3. የማይገባ ጥቅም መቀበል (አንቀፅ 11) 4. አስታራቂ ሽማግሌዎችና ሌሎች ሰዎች የሚፈፅሙት ጉቦ የመቀበል ወንጀል (አንቀጽ 12) 5. የመንግስት ወይም የሕዝባዊ ድርጅት ስራን በማያመች አኳኋን መምራት (አንቀጽ 13) 6. አደራ በተሠጠው ዕቃ ያለአግባብ ማዘዝ (አንቀፅ 14) 7. በሥራ ተግባር የሚፈፀም የመውሰድና የመሰወር ወንጀል (አንቀፅ 15) 8. በሥልጣን ወይም በኃላፊነት መነገድ (አንቀፅ 16) 9. በህገወጥ መንገድ መሰብሳብ ወይም ማስረከብ (አንቀፅ 17) 10. ያለአግባብ ጉዳይን ማጓተት (አንቀፅ 18) 11. ዋጋ ያለውን ነገር ያለክፍያ ወይም ያለበቂ ክፍያ ማግኘት (አንቀፅ 19) 12. ያለአግባብ ፍቃድ መስጠት ወይም ማፅደቅ (አንቀፅ 20) 13. ምንጩ ያልታወቀ ንብረትና ገንዘብ (አንቀፅ 21) 14. የሥራ ሚስጥርን መግለፅ (አንቀፅ 22) 15. መንግሥታዊ ወይም የህዝባዊ ሰነዶችን አስመስሎ ማዘጋጀት፣ ወደ ሐሰት መለወጥ ወይም በሐሰተኛ ሰነድ መገልገል (አንቀፅ 23) 16. መንግስታዊ ወይም የህዝባዊ ድርጅት ስነዶችን ማጥፋት ወይም ጉዳት ማድረስ (አንቀ8 24) 17. ጉቦ ወይም ተገቢ ያልሆነ ጥቅም መስጠት (አንቀፅ 25) 18. ዋጋ ያለዉን ነገር ያለክፍያ ወይም ያለበቂ ክፍያ መስጠት (አንቀፅ 26) 19. ማቀባበል (አንቀፅ 27) 20. በሌለው ሥልጣን መጠቀም (አንቀፅ 28) 21. በግል ተሰሚነት መነገድ (አንቀፅ 29) 22. በምርጫ ላይ የሚሰጥ መደለያ (አንቀጽ 30) 23. ከባድ የእምነት ማጉደል (አንቀፅ 31) 24.ከባድ አታላይነት (አንቀፅ 32) 25. በሙስና ወንጀል የተገኘን ገንዘብ ወይም ንብረት ህጋዊ አስመስሎ ማቅረብና በወንጀሉ ስለመርዳት (አንቀጽ 33)
⚖️ አዲስ የሕግ መጽሐፍ አያምልጥዎ! ⚖️ በሕግ ሙያ ለምትገኙ ዳኞች፣ ዐቃብያነ ሕግ፣ ጠበቆች፣ የሕግ መምህራንና ተመራማሪዎች እና ተማሪዎች እጅግ ጠቃሚ የሆነ ልዩ መጽሐፍ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት እንካችሁ እያለ ነው! የመጽሐፉ አጠቃላይ መረጃ፡ የመጽሐፉ ርዕስ፡ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት የወንጀል ሕግ ትርጉም ውሳኔዎች ስብስብ (በየጉዳዮች የተደራጀ ልዩ እትም) አሳታሚ፡ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የታተመበት ጊዜ፡ የካቲት 2018 ዓ.ም ይህ መጽሐፍ በአገራችን የወንጀል ፍትሕ ሥርዓት ውስጥ ወጥ የሆነ የሕግ አተረጓጎም እንዲኖር ለማስቻል ታስቦ የተዘጋጀ ድንቅ ማጣቀሻ ነው። የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት የሰጣቸውን አስገዳጅ የሕግ ትርጉም ውሳኔዎች በአንድ ላይ ሰብስቦና በየጉዳዮቻቸው አደራጅቶ ይዟል። የመጽሐፉ ዋና ዋና ይዘቶች እና ጥቅሞች፡ 👉መጽሐፉ በአራት ዋና ዋና ምዕራፎች እና በ45 ክፍሎች ተደራጅቶ የቀረበ ነው። 👉በወንጀል ሕግ ጠቅላላ ክፍል፣ ልዩ ክፍል፣ ልዩ ልዩ አዋጆች እና የወንጀለኛ መቅጫ ሥነ-ሥርዓት ሕግ ላይ የተሰጡ ውሳኔዎችን በስፋት ያካትታል። 👉86 ገላጭ የሆኑ አስገዳጅ የሰበር ውሳኔዎችን ከነሙሉ ይዘታቸው መርጦ አሳትሟል። 👉አንባቢዎች ተጨማሪ መረጃዎችን በቀላሉ እንዲያገኙ ተመሳሳይ እና ተያያዥነት ያላቸውን ሌሎች ውሳኔዎች በግርጌ ማስታወሻ አደራጅቶ ጠቁሟል። 👉በቀላሉ ጉዳዮችን ለማግኘት የሚያስችል የቃላት መፈለጊያ ማውጫ አካትቷል። ይህ ልዩ እትም በግል ቤተ-መጻሕፍትዎ ውስጥ ሊኖር የሚገባ ነው! 📚✨ አሁኑኑ ያውርዱት፤ ለሌሎች ባለሙያዎችም በማጋራት መረጃው እንዲደርሳቸው ያድርጉ! 🔗 ቻናላችንን ይቀላቀሉ፡ https://t.me/abdurahmanlawinfocenter19792015
የጠፋው ሰው በሕይወት መመለስ እና ውጤቱ የመጥፋት ውሳኔ የተሰጠበት ሰው በሕይወት መመለስ የመጥፋት ውሳኔ ቀሪ ከሚሆንባቸው ምክንያቶች ውስጥ አንዱ እንደሆነ በፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 170 ሥር ተደንግጎ የምናገኘው ጉዳይ ነው። ጠፋ የተባለው ሰው መመለስ ደግሞ የራሱ ውጤቶችን እንደሚያስከትል በፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 171 ሥር የተመለከተ ሲሆን እነዚህም፡- • ጠፋ የተባለው ሰው የተወሰዱ ንብረቶችን በሚገኙበት አኳኋን ይወስዳል። ንብረቶቹ ተሽጠው ከሆነ ደግሞ የተሸጡበትን ዋጋ ይወስዳል፣ ስለሆነም ንብረቶቹን የያዙ ግለሰቦች በዚህ አግባብ ለተመለሰው ሰው የማስረከብ ግዴታ አለባቸው። (የፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 171)። ንብረቱን የያዙ ግለሰቦች በተንኮል ወይም በመጥፎ አስተዳደር ላጠፉት ነገር ካሳ የመክፈል ኃላፊነት አለባቸው (የፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 171(3))። • ጋብቻን በተመለከተ ግን በመጥፋት ውሳኔው የፈረሰው ጋብቻ መመለሱ ሕይወት እንዲዘራ ወይም እንደገና እንዲጸና የማድረግ ውጤት የለውም (የፍትሐብሔር ሕግ ሰ/መ/ቁ. 74791 ቅጽ 14፣ ሰ/መ/ቁ. 213917 ቅጽ 27)። ማጠቃለያ የመጥፋት ውሳኔ በሕይወት መኖሩ ባልታወቀ ሰው ምክንያት በቤተሰብ እና በንብረት መብት ላይ የሚፈጠርን ክፍተት ለመሙላት የተቀረጸ ጠቃሚ የሕግ መሣሪያ ነው። ሕጉ በአንድ በኩል የጠፋውን ሰው በሕይወት የመመለስ ተስፋና ንብረት ለመጠበቅ የጊዜ ገደቦችንና የዋስትና ግዴታዎችን የሚያስቀምጥ ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ የቀሩት ቤተሰቦችና ወራሾች ሕይወታቸውን እንዲቀጥሉና ንብረቱን እንዲያስተዳድሩ መብት ይሰጣል። በመሆኑም ሕጉ እንደሚደነግገው ያለ ፍርድ ቤት መደበኛ የመጥፋት ውሳኔ ማስታወቂያና ማረጋገጫ በሰዎች ንብረትና መብት ላይ መወሰን በሕግ ፊት ተቀባይነት የሌለው በመሆኑ ማኅበረሰቡ ይህንን ሥርዓት ተገንዝቦ በሕጋዊ መንገድ መብቱን ማስከበር ይኖርበታል። #ንቃተ ሕግና ሥልጠና ዳይሬክቶሬት የተዘጋጀ
ዕለታዊ🛎 ጠቅላላ የቅጣት ማክበጃ ምክንያቶች ⚖⚖⚖⚖⚖⚖⚖⚖ ✍ ጠቅላላ የቅጣት ማክበጃ ምክንያቶች የምንላቸው በወንጀል ህጋችን በአንቀጽ 84 ስር የተዘረዘሩት ናቸው፡፡ ሀ.ወንጀለኛው ወንጀሉን ያደረገው በከሀዲነት ወይም በወስላታነት ወይም በወራዳነት ወይም መጥፎ አመልን በሚያሳይ ምቀኝነት፣ጥላቻ፣ ስግብግብነት፣ መጥፎ ነገርን ለመስራት ወይም ሰውን ለመጉዳት ፍጹም ፍቃደኛ በመሆን ወይም በተለየ ክፋት ወይም ጨካኝነት እንደሆነ ፡፡ በዚህ ድንጋጌ መሰረት ቅጣትን ለማክበድ ከመካከላቸው የአንዱ መሟላት በቂ ነው፡፡ ለ.ወንጀለኛው ወንጀሉን ያደረገው ስልጣኑን፣ ተግባሩን ወይም የተጣለበትን እምነት ወይም ሀላፊነት ያለአግባብ በመገልገል እንደሆነ የመንግስትን ስራ ለመስራት ወይም ለመምራት ስልጣን የተጣለበት ሰው ስራውን በታማኝነት እና በቅንነት መፈጸም አለበት፡፡ በተጨማሪም ይህንኑ ስልጣን ተገን በማድረግ ለራሱም ሆነ ለሌላው ጥቅም ለማስገኘት ወይም በሌላ ሰው ጥቅም ወይም መብት ላይ ጉዳት ለማድረስ በማሰብ አንድን ወንጀል ከፈጸመ ቅጣት ሊከብድበት እንደሚገባ የወንጀል ህጉ ይደነግጋል፡፡ ሐ.ወንጀለኛው በቀድሞ ጥፋተኛነቱ ወይም ወንጀልን ማድረግ ሙያ ወይም ልማድ አድርጎ መያዙ፣ ወይም የወንጀሉ አፈጻጸም ዘዴ፣ ጊዜ፣ ቦታና የአፈጻጸም አኳሀን፣ በተለይም በሌሊት ወይም በሽብር ወይም በሁከት ለአደጋ ሽፋን ወይም በጦር መሳርያ ወይም በሌላ አደገኛ መሳርያ ወንጀሉን በማድረግ የተለየ አደገኝነቱን አሳይቶ እንደሆነ :: በዚህ የቅጣት ማክበጃ ምክንያት ስር ሶስት ዋና ዋና ምክንያቶች አሉ እነኚህም፡- 1.ወንጀልን ማድረግ ሙያው ወይም ልማዱ አድርጎ መያዝ 2.የወ/ል አፈጻጸም ዘዴ፣ጊዜ፣ቦታ እና የአፈጻጸም አኳሀን 3.ወንጀልን በጦር መሳርያ ወይም በሌላ አደገኛ መሳርያ መፈጸም ናቸው፡፡ በተጨማሪም ሌሊት የሚለው ሀረግ ከስንት ሰዓት ጀምሮ እንደሆነ አሻሚ ቢሆንም በተለምዶ ፍርድ ቤቶች ከሌሊቱ 6፡00-12፡00 ድረስ ያለውን የጊዜ ገደብ በሌሊትነት ወስደው ቅጣት ያከብዱበታል፡፡ በእጅ ወይም በዱላ የውንብድና ወንጀልን የፈጸመ ሰው እና የስለት ወይም የጦር መሳርያዎችን ተጠቅሞ ይህንኑ ወንጀል የፈጸመ ሰው የወንጀል ማድረግ አደገኛነቱ እኩል ሊሆን አይችልም፡፡ መ.ወንጀለኛው ወንጀሉን ያደረገው ወንጀል ለመፈጸም በተደረገ ስምምነት መሰረት ወይም ከሌሎች ጋር በመሆን ወይም ወንጀል ለመፈጸም ከተቋቋመ ቡድን ጋር በመስማማት ወይም አባል በመሆን ይልቁንም እንደ ወንጀል ቡድን ሹም ወይም አደራጅ ወይም መሪ በመሆን እንደሆነ :: ወንጀልን ለመፈጸም ከሌላው ጋር ወይም ለዚሁ አላማ ከተደራጀ ቡድን ጋር በአባልነት በመስማማት ወንጀልን ማድረግ ቅጣትን ሊያከብድ የሚችል በቂ ምክንያት ነው፡፡ ሠ.ወንጀለኛው ወንጀሉን ያደረገው በዕድሜው፣ በጤንነቱ፣ በኑሮው ወይም በስራው ሁኔታ ልዩ ጥበቃ በሚያሻው ሰው ላይ በተለይም ለመከላከል አቅም በሌለው፣ መንፈሰ ደካማ፣ በሽተኛ ወይም አካል ጉዳተኛ ፣ እስረኛ ወይም በቅርብ ዘመዱ ላይ ወይም የበላዩ ወይም የበታቹ በሆነ ሰው ላይ፣ በህግ በተቋቋመ ባለስልጣን ወይም የስራ ግዴታውን በማከናወን ላይ በሚገኝ በአንድ የህዝብ አገልጋይ በሆነ ሰራተኛ ላይ እንደሆነ ቅጣቱ ሊከብድበት ይችላል ::
ስለቀዳሚ ምርመራ (Preliminary Inquiry) ፌርድ ቤት ተልዕኮ፣ ሥልጣን እና ተግባር በዐስማን መሃመድ ሰይድ
ችሎት ውስጥ በዳኛና በባለጉዳይ ላይ ግድያ መፈፀሙ ተሰማ‼ በሆለታ ወልመራ ወረዳ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ዛሬ ረፋድ ላይ በችሎት አዳራሽ ውስጥ በተፈጸመ ጥቃት የዳኛና የባለጉዳይ ሕይወት ማለፉ ከፍተኛ ድንጋጤን ፈጠረ። የቤተሰብ ክርክር ጉዳይን በመመልከት ላይ የነበሩት ወጣት ዳኛ ወርቄ ፈካንሳ የፍርድ ውሳኔ በማንበብ ላይ ሳሉ፣ ተከሳሹ በድንገት ባወጣው ሽጉጥ በከፈተው ተኩስ ዳኛዋንና በዕለቱ…
видео или голосовое, без подписи
የእናቱን አስክሬን ቤት አስቀምጦ የእናቱን ቃል ለማክበር የ8ኛ ክፍል ሚኒስትሪ ፈተና ከቀብር በፊት እና በኃላ ለፈተና የተቀመጠው ካሊድ 🏠📝 ይሕ በምስሉ ላይ የምትመለከቱት ታዳጊ ካሊድ ይባላል 👦 ገና የአስራ አራት ዓመት ልጅ ነው🗓️።ከሑለት ታናናሽ ወንድሞቹ ጋር በሸገር ከተማ አስተዳደር ኤካ ጣፎ ክፍለ ከተማ ከእናቱ ጋር ይኖራል🏡። ካሊድ ከእናቱ ጋር ሲኖር ወላጅ አባቱ ከእነርሱ ርቆ ሌላ ትዳር መስርቶ ጅጅጋ ከተማ ይኖራል🏙️። ካሊድ ሠሞኑን እናቱ ታምወው በነበረበት ወቅት እኔ አንድ ነገር ብሆን ምንም ቢፈጠር አመት የለፋሕበትን ፈተና እንዳታቋርጥ ብለው ቃል ያስገቡታል🤝📜። እናትም በነጋታው የስምንተኛ ክፍል ፈተና ሊሲጥ ሠዓታት ሲቀረው ሕይወታቸው ያልፋል⚰️💔።ካሊድ በእናቱ ሞት ከፍተኛ ሐዘን ቢሰማውም ለእናቱ የገባው ቃል አክብሮ የእናቱን አስክሬን እቤት ጥሎ የጥዋት ፈተናውን ተፈተነ📝🕯️። ካሊድ ከሠዓት እናቱን አልቅሶ ቀብሮ ተመልሶ የከሰዓት ፈተናውን ተፈተነ🙏📚።
ክስ (ጉዳይ) ወደ ሌላ ፍርድ ቤት ወይም ችሎት የሚዘዋወርባቸው (change of venue) ምክንያቶች በኢትዮጵያ ሕግ ውስጥ በዋናነት በፍትሐብሔር ሥነ ሥርዓት ሕግ (Civil Procedure Code) እና በወንጀል ሥነ ሥርዓት ሕግ (Criminal Procedure Code) ውስጥ የተደነገጉ ናቸው። 👉በፍትሐብሔር ጉዳዮች በፍትሐብሔር ሥነ ሥርዓት ሕግ አንቀጽ 31 መሰረት ክስ ወደ ሌላ ፍርድ ቤት የሚዛወርባቸው ዋና ምክንያቶች፦ በአሁኑ ፍርድ ቤት ፍትሃዊ ዳኝነት ማግኘት አለመቻል (impartiality አለመኖር) የምስክሮች ወይም ወገኖች ምቹነት አለመኖር (convenience of parties/witnesses) ጉዳዩ በቂ ምክንያት በማቅረብ ወደ ሌላ ችሎት ወይም ፍርድ ቤት ማዛወር አስፈላጊ መሆኑ ይህን ጥያቄ የሚያቀርብ ከሳሽ ወይም ተከሳሽ ሊሆን ይችላል፣ እና በከፍተኛ ፍርድ ቤት ወይም በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይቀርባል። ጥያቄው ፍርድ ከመሰጠቱ በፊት በማንኛውም ደረጃ ሊቀርብ ይችላል። *በወንጀል ክስ ላይ በወንጀል ሥነ ሥርዓት ሕግ (በተለይ በ Proclamation No. 84/1968 በተሻሻለው) ክስ ወደ ሌላ ፍርድ ቤት የሚዛወርባቸው ምክንያቶች፦ የታችኛው ፍርድ ቤት ጉዳዩን በገለልተኛነት (impartially) ማየት አለመቻሉ ጉዳዩ ተራ ተፈጥሮ ያለው አለመሆኑ (extraordinary nature) ምስክሮች ለመገኘት ምቹ አለመሆናቸው (inconvenience for witnesses) ይህ ጥያቄ በከፍተኛ ፍርድ ቤት ይቀርባል፣ እና ማስረጃ ከመሰማቱ በፊት መቅረብ አለበት። በሁለቱም ሁኔታዎች የዝውውር ጥያቄ በቂ ምክንያት መደገፍ አለበት፣ እና ፍርድ ቤቱ የሚወስነው በጉዳዩ ሁኔታ ነው። ይህ ስርዓት ፍትሃዊ ዳኝነትን ለማረጋገጥና ለጉዳዩ ምቹ ሁኔታ ለመፍጠር ያለመ ነው።
አካሌ ነፃ ይዉጣልኝ ( Habeas Corpus ) ምን ማለት ነው ? ◼️ ሰዎች በተለያዩ ቦታዎች እና ሁኔታዎች በወንጀል ተጠርጥረው ለእስር ሊዳረጉ ይችላሉ ። በወ/ስ/ስ/ህግ ሆነ በህገ _መንግስቱ ከተረጋገጡ መብቶች መካከል በ 48 ሰዓት ዉስጥ በአቅራቢያ ወደሚገኝ ፍርድ ቤት መቅረብ ይገኝበታል ። ይህ ሳይሆን ሲቀር ተጠርጣሪዉም ሆነ የእርሱ ተወካይ ያለ አግባብ መታሰራቸው ቀሪ እንዲሆን ወይም የአካሌ ነፃ ይዉጣልኝ አቤቱታ ማቅረብ ይችላሉ ። ◾️ Habeas Corpus የሚለው ቃል የላቲን ሲሆን " Show me the body " የሚል ትርጓሜ አለው ። ◾️ በዚህ ስርዓትም የታሠረዉን ግለሰብ ያሰረው አካል የማቅረብ ወይም " to produce the body " ግዴታ አለበት ። ⚫️ የዚህ ዓይነቱ ክስ በየትኛው ፍርድ ቤት ይቀርባል ? የፌዴራል ፍርድ ቤቶችን ስልጣን ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር 1234/13 አንቀጽ 5 (1) (ኘ ) መሠረት አካሌ ነፃ ይዉጣልኝ አቤቱታ በፌዴራል ፍ/ቤቶች ይቀርባል ። ◼️ በህገ _ መንግስቱ ምዕራፍ 3 ላይ የተዘረዘሩት መሠረታዊ መብቶች እና ነፃነቶችን ለማስከበር ፍርድ ቤት ለመታየት ብቁ የሆኑ ጉዳዮችን ለመዳኘትም በዚሁ አዋጅ ለከፍተኛ ፍርድ ቤት ስልጣኑ ተሰጥቷል ። ⚫️ ይህ በእንዲህ እንዳለ ስለ አቤቱታ አቀራረቡ የፍትሐብሔር ስነ _ ስርዓት ህጋችን ምን ይላል ? የዚህ ህግ አንቀጽ 177_ 179 ያሉት ድንጋጌዎች የአካሌ ነፃ ይዉጣልኝ ክስ በማን ፣ የትኛው ችሎትና ማንን መክሰስ እንደሚቻል አብራርቶ ያስቀምጣል ። ◾️ አቤቱታው በራሱ በተጠርጣሪው ወይም ለእርሱ ሲል በሚቀርበው ሰው ፦ _ በቃለ _ መሀላ የተደገፈ _ የታሳሪዉን እና የአሳሪዉን ስም _ የተያዘበት ስፍራ እና _ ካሉም ይህንን የሚያስረዱ ምስክሮች ስም ያካተተ መሆን አለበት ። ፍርድ ቤቱም የተያዘውን ሰው በዋስ ወይም ያለ ዋስ እንዲለቀቅ አስፈላጊውን የግራቀኙን ክርክር ከሰማ በኋላ ሊወስን ይችላል ።
ከፍትህ ሚንስትር ስለአዲሱ የወንጀል እና ማስረጃ ህግ የተሰጠ ማሳሰቢያ!
" ለአግራሞት ያክል...😂" አስገራሚ ህግጋቶች😳 ፨ Messi በተወለደበት Rosario, Argentina ከ2014 ወዲህ በወጣው ህግ መሰረት ወላጆች ለልጆቻቸው "Messi" የሚል ስም ማውጣት ክልክል ነው። ፨ በጀርመን የመንገድ መዘጋጋት እና መጨናነቅ ከተፈጠረ መኪኖች ዳራቸውን በመያዝ የመሃሉን መንገድ ለአንቡላንሶች ክፍት የማድረግ ግደታ አለባቸው። ፨በአሜሪካ ግዛት በኦክላህማ በውሻ ላይ መቀለድ በህግ ያስቀጣል። አንድ ሰው ወደ ውሻ ጠጋ በማለት አስቂኝ 😄 የሆነ ፊት ለውሻው ቢያሳይ በገንዘብ ወይም በእስር እንደሚቀጣ በህግ ተደንግጓል። ፨በ1685 ካናዳ ውስጥ(በዚያን ጊዜ new France ነበር የምትባለው) ከፍተኛ የሆነ ገንዘብ እጥረት አጋጥሞ ነበር። እናም በዚያ ስዓት የነበሩ ቅኝ ገዥዎች ባለስልጣናት የመጫዎቻ ካርድን (ካርታ) እንደገንዘብ እንድያገለግል ወስነው በካርድ ሰዎች እየተገለገሉ ነበር። ፨በአንድ ወቅት England ውስጥ እራስን ለማጥፋት መሞከር እንደ ወንጀል ይቆጠር ነበር።እሚገርመው እራሱን ለማጥፋት መሞከሩ ከተረጋገጠ የሞት ፍርድ ነበር የሚፈረድበት😂 ፨በሱዳን ውስጥ ከማን ጋር የፍቅር ግንኙነት እንደያዘዎት ጥንቃቄ ማድረግ አለብዎት። አንድ ወንድ ከሴት ጋር ሲተኛ ከተያዘ የቤተሰቧን ክብር ለማዳን ወዲያውኑ ማግባት እንዳለበት የሚደነግግ ህግ አለ። 2006 ሕጉ በፍየልም ላይ ተፈጻሚ ሆነ። 🐐🙄 ቻርለስ ቶምቤ ከፍየል ጋር ግንኙነት ሲፈጽም ተይዞ በህዝብ እንዲዋረድ በሚል ለባለቤቱ ከፍሎ ፍየሏን እንድያገባ ተገዷል። 🤓😁 ፨ በአሜሪካ ኦሪገን ግዛት አንድ ሰው ከ ዝናብ ውሃ ሲደቅን ተገኝቶ በእስር እና 1,500 ዶላር ተቀጥቶ ነበር።ምክንያቱ ደግሞ የመንግስት ንብረት ነው ማስፈቀድ ነበረበት በሚል። ፨ በአውስትራሊያ ቪክቶሪያ ከተማ ውስጥ አምፖል ከተቃጠለ ማንም ሰው ተነስቶ አምፖል መቀየር አይችልም። ኤሌክትሪሻን ወይም የመብራት ሰራተኛ ካልሆነ ፍቃድ ሰው አምፖል መቀየር በህግ ያስቀጣል።🤓
ችሎት ውስጥ በዳኛና በባለጉዳይ ላይ ግድያ መፈፀሙ ተሰማ‼ በሆለታ ወልመራ ወረዳ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ዛሬ ረፋድ ላይ በችሎት አዳራሽ ውስጥ በተፈጸመ ጥቃት የዳኛና የባለጉዳይ ሕይወት ማለፉ ከፍተኛ ድንጋጤን ፈጠረ። የቤተሰብ ክርክር ጉዳይን በመመልከት ላይ የነበሩት ወጣት ዳኛ ወርቄ ፈካንሳ የፍርድ ውሳኔ በማንበብ ላይ ሳሉ፣ ተከሳሹ በድንገት ባወጣው ሽጉጥ በከፈተው ተኩስ ዳኛዋንና በዕለቱ ከባለቤታቸው ጋር ሲከራከሩ የነበሩትን ግለሰብ በጥይት መትቶ ሕይወታቸውን ቀጥፏል። ድርጊቱ በማኅበራዊ ሚዲያና በሕግ ባለሙያዎች ዘንድ ከፍተኛ ቁጣን የቀሰቀሰ ሲሆን፣ የታጠቀ ግለሰብ ፍተሻ አልፎ ወደ ችሎት መግባት መቻሉ የፍርድ ቤቶችን የጸጥታና ጥበቃ ሥርዓት ድክመት አሳይቷል በሚል የደኅንነት ሥጋት ጥያቄዎችን አስነሥቷል። ለሟቾች ቤተሰቦችና ለፍትሕ አካላት መጽናናትን እንመኛለን። መረጃው ከጉርሻ ፔጅ የተወሰደ ነው
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
" ፍርድ ቤቱ የመጨረሻ ያለውን የሞት ፍርድ ውሳኔ አስተላልፏል " - የዞኑ ፖሊስ እና ዓቃቤ ሕግ ሊያገባ ጥቂት ቀናት በቀሩት ወጣት ላይ "የቀድሞ ፍቅረኛዬን አገባ" በሚል በቀል አሰቃቂ ግድያ የፈጸመው ፀጋዬ ታደሰ በሞት እንዲቀጣ የጌዴኦ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የመጨረሻ ውሳኔ አስተላልፏል። የዞኑ ፖሊስ እና ዓቃቤ ሕግ መምሪያዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ እንደገለጹት፣ ወንጀሉ የተፈጸመው ሚያዝያ 14 ቀን 2018 ዓ.ም በገደብ ከተማ ነው። ተከሳሹ የአቢሲኒያ ባንክ ባልደረባ የነበረውን ወጣት ተመስገን ዳንኤልን ለመግደል የሞከረበት ሽጉጥ በመክሸፉ፣ በስለት ደጋግሞ በመውጋት በአሰቃቂ ሁኔታ ሕይወቱ እንዲያልፍ አድርጓል። ወንጀለኛው የሟች እጮኛ የቀድሞ ፍቅረኛ ሲሆን፣ ድርጊቱንም በቂምና በቀል ተገፋፍቶ ለረጅም ጊዜ አቅዶበት እንደፈጸመው ከአካባቢው ነዋሪዎችና ከፖሊስ የተገኘው መረጃ ያመለክታል። ተከሳሹ ፍርድ ቤት ቀርቦ ክሱን ክዶ በጠበቃ ቢከራከርም፣ ፖሊስና ዓቃቤ ሕግ ጠንካራ የሰውና የሕክምና ማስረጃዎችን በማቅረብ ወንጀሉን ማረጋገጥ ችለዋል። ተከሳሹ በበኩሉ ምንም ዓይነት የመከላከያ ምስክር ማቅረብ አልቻለም። ፍርድ ቤቱ ግንቦት 17 ቀን 2018 ዓ.ም በነበረው ችሎት መነሻ ቅጣቱን ሞት በማድረግ ለዛሬ ግንቦት 26 ቀን የሁለቱንም ወገን የቅጣት አስተያየት ለመስማት ቀጠሮ ሰጥቶ ነበር። በዚህም መሠረት ዛሬ በዋለው ችሎት ከተከሳሽ የቀረቡ ሁለት ማቅለያዎች እና ከዓቃቤ ሕግ የቀረቡ ሁለት ማክበጃዎች እርስ በርስ በመቻቻላቸው ፍርድ ቤቱ የሞት ቅጣቱን አጽድቋል። ውሳኔውን ተከታትሎ እንዲያስፈጽምም ለዲላ ማረሚያ ተቋም ትዕዛዝ መተላለፉን መምሪያዎቹ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አረጋግጠዋል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ ሀዋሳ ግንቦት 26 ቀን 2018 ዓ/ም @tikvahethiopia
በፍርድ ቤት የተደረገ እርቅ ውጤት!! 👉በፍርድ ቤት በክርክር ላይ ባለ ጉዳይ ተከራካሪ ወገኖች ነገሩን በእርቅ ለመጨረስ ተስማምተው እርቁ በፁሁፍ ተደርጎ ፍርድ ቤት ቀርቦ ለሕግ እና ለሞራል ተቃራኒ አለመሆኑ ተረጋግጦ ከመዝገቡ ጋር እንዲያያዝ ከተደረገ የእርቁ ስምምነት እንደ ፍርድ ተወስዶ የአፈፃፀም ክስ ሊቀርብበት የሚችል ሲሆን ከጉዳዩ ጋር ተያይዞ በተከራካሪ ወገኖች መካከል አለመግባባት ቢፈጠር እንደ መደበኛ ውል ፡ውል እንዲፈርስ አድስ ክስ ማቅረብ የማይችል ስለመሆኑ የፍ/ስ/ስ/ህ/ ቁ 386&392 የሰ/መ/ቁ 143086 ቅፅ 28
ስለ ፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የይግባኝ የዳኝነት ስልጣን የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሚከተሉትን ጉዳዮች በይግባኝ የማየት ስልጣን ይኖረዋል፡- 👉የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመጀመሪያ ደረጃ ስልጣኑ ውሳኔ የሰጠባቸው፣ 👉የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በይግባኝ ሰሚነት ስልጣኑ የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ከሰጠው ውሳኔ የተለየ ውሳኔ የሰጠባቸው፣ 👉የክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የፌደራል ጉዳዮችን በተወካይነቱ በመጀመሪያ ደረጃ ስልጣኑ አይቶ ውሳኔ የሰጠባቸው፣ 👉የክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የፌደራል ጉዳዮችን በተወካይነቱ በይግባኝ ሰሚነት ስልጣኑ የክልሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ከሰጠው ውሳኔ የተለየ ውሳኔ የሰጠባቸው፣ 👉በሌሎች ህጎች የተጠቀሱ ጉዳዮችን፡፡ የፌደራል ፍርድ ቤቶች አዋጅ ቁጥር 1234/2013 አንቀጽ 9 ንዑስ አንቀጽ (1-5)
Ethiopian_Law_Exit_Exam_Strategy_Guide" የመውጫ ፈተናን በዕውቀት ብቻ ሳይሆን በብልሃት ዶሚኔት ለማድረግ የተዘጋጀ። ፈተናው በር ላይ ስለሆነ እነዚህን 4 የነብስ አድን ስልቶች በጭንቅላትህ ያዝ፦ ✔️ ምርጫዎቹን አትመናቸው (The 5-Step System): ጥያቄውን ስታነብ መልሱን መጀመሪያ በጭንቅላትህ ገምት። እንደ NOT እና EXCEPT ያሉ ጥያቄውን የሚቀለብሱ ቃላትን በደንብ ፈልግ። ✔️ "ሁልጊዜ" እና "በፍፁም" ጠላቶችህ ናቸው: በሕግ ውስጥ ሁልጊዜ ልዩ ሁኔታዎች (Exceptions) ስላሉ፣ ምርጫ ውስጥ ALWAYS ወይም NEVER ካየህ 80% ስህተት ስለሆኑ ወዲያውኑ ሰርዛቸው። ✔️ የ90 ሰከንድ ህግ እና የነፃ ማርክ አደን፦ ለአንድ ጥያቄ ከ90 ሰከንድ በላይ አታባክን። ጥያቄ አትለፍ፣ ምክንያቱም የተሳሳተ መልስ ማርክ አያስቀንስም። መልስ ስትቀይር የመጀመሪያ ስሜትህ (First Instinct) 67% ትክክል የመሆን ዕድል አለው። ✔️ አንበሶቹን ለይተህ ምታ (Tier 1): Civil/Criminal Procedure, Trade, Criminal እና Evidence ፈተናውን ስለሚቆጣጠሩት (18% ያህሉን ይይዛሉ) ለእነሱ ልዩ ትኩረት ስጥ። Work Smart! መልካም ፈተና!