👍Study Law Without Leaving Your Law! Law at Anywhere and Anytime👍
СтатистикаJoin us to be informed about updated laws and information about Ethiopian Law😍🥰🙏🔥🔥 https://t.me/lawforseekers
- Последний пост
- 19 апр.
- Последнее чтение
- 14 авг.
- Постов за неделю
- 0
- Всего постов
- 21
- Тип
- открытый
- Язык
- английский
- В каталоге с
- 14 авг.
- 1/24сутки в ленте
- —
- 1/48двое суток
- —
- 1/72трое суток
- —
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
ትዕዛዝ፣ ብይን፣ ፍርድና ውሳኔ =================== ትእዛዝ (order ) ,,,ብይን ( Ruling ) ,, ፍርድ (Judgement ),,ዉሳኔ ( Decision /Decree ) እነዚህ አራት ቃላት በሕግና በፍርድ ቤት የሥራ ሂደት ዉስጥ ተመሳሳይ ቢመስሉም የራሳቸው የሆነ የተለየ የሕግ ትርጉምና ደረጃ አላቸው ,,,,,,,, 1, ትእዛዝ ( Order ) " ትእዛዝ " ማለት አንድ የፍርድ ቤት ክርክር ከመጀመሩ በፊት ወይም በሂደት ላይ እያለ ፍርድ ቤቱ አንድን ነገር እንዲደረግ ወይም እንዳይደረግ የሚሰጠው መመሪያ ነው ። ባህሪው ጉዳዩ መዝጋት ወይም መጨረስ ሳይሆን ለሂደቱ መቀላጠፍ የሚሰጥ ነው ። ለምሳሌ : "ይህ ንብረት ለጊዜው እንዳይሸጥ እንዳይለወጥ ታግዶል " ወይም " ተከሳሽ ለቀጣይ ቀጠሮ ምስክሮች ይዞ ይቅረብ " የሚሉ መመሪያዎች ትእዛዝ ይባላል ። 2, ብይን ( Ruling ) " ብይን" የሚሰጠው በክርክሩ ሂደት ዉስጥ ለሚነሱ መከራከሪያ ነጥቦች ( Interlocutory matters ) ምላሽ ለመስጠት ነው ። ባህሪው ዋናው የክርክር ዉጤት ( ማን አሸነፈ ? ማን ተሸነፈ ?) ሳይሆን በመሀል የሚነሱ የህግ ክርክሮችን ለመወሰን ነው ። ለምሳሌ ; " ፍርድ ቤቱ ይህንን ክስ ለማየት ስልጣን አለው / የለዉም " ወይም " ክሱ በይርጋ ይታገዳል / አይታገድም " የሚለው ዉሳኔ ብይን ይባላል ። ብይን ብዙ ጊዜ ክርክሩን አያበቃዉም ይልቁንም ሂደቱን ይቀጥላል ። 3, ፍርድ ( Judgement ) " ፍርድ " ማለት ፍርድ ቤቱ የቀረበለትን ማስረጃዎች መርምሮ ; የግራ ቀኙን ክርክር ሰምቶና መዝኖ የሚሰጥ የመጨረሻ ድምዳሜ ነው ። ባህሪው ፍርድ ቤቱ በጉዳዩ ላይ የደረሰበትን የሐቅና የህግ ድምዳሜ በዝርዝር የሚያስቀምጥበት ሰነድ ነው ። ለምሳሌ ; " ከሳሽ የንብረቱ ባለቤት መሆናቸውን ፍርድ ቤቱ አረጋግጧል " የሚለው ሰነድ ፍርድ ነው 4,ዉሳኔ ( Decision /Decree ) " ዉሳኔ " በፍርድ ላይ ተመስርቶ የሚሰጥ ተግባራዊ ትዕዛዝ ነው ። በፍርድ መደምደሚያ ላይ " በዚህ መሠረት ",,,,,,,,,ተብሎ የሚቀመጠው ነጥብ ነው ። ባህሪው በፍርድ የተረጋገጠውን መብት ወይም ግዴታ ለይቶ የሚያስቀምጥና ተፈፃሚ የሚሆን ነው ። ለምሳሌ ; ፍርዱ " ከሳሽ ባለቤት ናቸው " ካለ,,,,, ዉሳኔዉ " ተከሳሽ ቤቱን ለከሳሽ በአንድ ወር ጊዜ ዉስጥ ያስረክቡ" የሚለው የመጨረሻ ትዕዛዝ ነው ። ማጠቃለያ / ልዩነት /ቃል/ ትኩረት / መቼ ይሰጣል ? # ትእዛዝ ለስራ ሂደት መመሪያ መስጠት በማንኛውም ጊዜ # ብይን በመሀል ለሚነሱ መከራከሪያዎች መልስ መስጠት በሂደት ላይ # ፍርድ ማስረጃ መዝኖ ድምዳሜ ላይ መድረስ በክርክሩ ማብቂያ # ዉሳኔ መብትና ግዴታን ለይቶ መወሰን በፍርድ መጨረሻ ምንጭ:- ጠበቃ እስከዳር አወቀ
"ሎሚ ውርወራ እና Tort Law" "ሎሚ ብወረውር ደረቷን መታሁት፣ አወይ ኩላሊቷን ልቧን ባገኘሁት።...." ጥንት ነበር ያ!... አባቶቻችን ለወደዷት ኮረዳ ሎሚ ወርውረው፣ ፍቅራቸውን ገልጸው፣ በሎሚ ምት ልቧን አሸንፈው ትዳር የሚመሠርቱት — ድሮ ነበር። ዛሬ ግን ዘመን ተቀይሯል። ሎሚው በከረሜላ፣ ደብዳቤው በቴክስት፣ የሎሚው ሽታም በሽቶ ተተክቷል። ነገር ግን የጥምቀት በዓል ሲመጣ ያ የድሮው "ሎሚ የመወርወር" አምሮት በአንዳንዶቻችን (በተለይ በፍቅር ህመም ለተያዝነው) ልብ ውስጥ ማቅበዝበዙ አይቀርም። ዛሬ ከሰዓት... ላይብረሪ እያጠናሁ ሳለሁ አንድ እንግዳ ሀሳብ መጣብኝ። በሚዛን እየተከበረ ያለው የቃና ዘገሊላ ድባብ ከሩቅ ይጠራኝ ዠመር። "ለምን አልወጣም?" አልኩ ለራሴ። ለምን ሄጄ፣ በልቤ ላይ "Exclusive Ownership" ያላትን ያቺን ልጅ ፈልጌ አላገኛትም? ሳስባት የምደነግጥላትን፣ ልቤን በውብ ምስሏ የሞላችውን ልጅ አግኝቼ፣ አንድ ሎሚ ገዝቼ "ውዴ ሆይ፣ የወደድኩሽ እኮ ድሮ ነው!" ብዬ ሎሚ ብወረውርባትስ? Romantic ነው አይደል? በባህል መነጽር ሲታይ "የፍቅር ሰው!" ያስብላል። ነገር ግን ችግሩ እዚህ ጋር ነው። እንደምታውቁት እኔ የሕግ ተማሪ ነኝ። የሕግ ተማሪ ደግሞ እንኳን ሎሚ፣ አበባም ሲሰጥ "ይሄ ነገር በሕጉ አግባብ እንዴት ይታያል?" ብሎ ማሰቡ አይቀርም — አንዳንዴ ባያስብም። እናም Romantic ሀሳቤን ይዤ ከላይብረሪ ልወጣ ስል፣ ከፊት ለፊቴ የተቀመጠው Civil Code (የፍትሐብሔር ሕግ) "ቆይ ወዴት?" ብሎ አፈጠጠብኝ። ወዲያውኑ አንቀጽ 2038 (Tort Law) አይኔ ላይ ድቅን አለብኝ! አንቀጽ 2038 እንዲህ ይላል፦ "አንድ ሰው ሆነ ብሎ ሌላው ሰው ሳይፈቅድ በሚያደርገው መንካት በዚህ በመንካቱ ጥፋተኛ ነው።" ይልና ይቀጥላል... "ሰውዬውን በቀጥታም ሆነ ወይም በሌላ ሕይወት ባለው ወይም በሌለው ነገር አማካይነት ቢነካውም ጥፋተኛ ነው።" እንግዲህ አስቡት! ለፍቅር ብዬ የምገዛው ሎሚ በሕጉ ፊት "ሕይወት የሌለው ነገር(object)" ነው። ያንን ሎሚ ወርውሬ የልጅቷን ደረት ወይም ትከሻ ባገኘው፥ በሕጉ አነጋገር "ያለ ፈቃድ መንካት" (Battery) ፈጽሜያለሁ ማለት ነው። ማሰቤን አላቆምኩም... ሎሚውን ወርውሬባት በፈገግታ ፈንታ "ይሄ ሰው ግን ምን ነካው?" ብላ ብትጮህስ? ወይም ሎሚው ስቶ ግንባሯን ቢላትስ? ወዲያውኑ የፍቅር ጥያቄዬ ወደ "ክስ" ተቀየረ ማለት ነው። "ክቡር ፍርድ ቤት ተከሳሽ፣ ደንበኛዬን ያለ ፈቃዷ በሎሚ በመደብደብ አካላዊና ሥነ-ልቦናዊ ጉዳት አድርሶባታል" ብሎ ሲያነብልኝ ታየኝ — ወፍራሙ ሰውዬ። የፍቅር መዝገብ ሳይሆን ከውል ውጪ የሚመጣ ኃላፊነት (Tortious liability) መዝገብ ሲከፈትብኝ ታየኝ! ግና ተስፋ አልቆረጥኩም። እንደማንኛውም የሕግ ሰው "መውጫ ቀዳዳ" (Defense) መፈለግ ጀመርኩ። ሕጉን ሳገላብጥ ሳገላብጥ ቆይቼ አንቀጽ 2039(ሠ) ላይ ደረስኩ። አንቀጽ 2039(ሠ) እንዲህ ይነበባል፦ "የተከሳሹ ሥራ አእምሮ ባለው ሰው ግምት የሚገባ ነው የሚያሰኝ ሌላ ማናቸውም ምክንያት በተገኘ ጊዜ ሁሉ" ተከሳሹ ነጻ ነው። "አሃ!" አልኩ በልቤ። እዚህ ጋር ነው ጨዋታው! "ክቡር ፍርብ ቤት ድርጊቱ የፈጸምኩት በጥምቀት በዓል ነው። በጥምቀት ደግሞ ሎሚ መወርወር 'አእምሮ ባለው ሰው ግምት' (Reasonable person standard) ተቀባይነት ያለው ባህል ነው" ብዬ መከራከር እችላለሁ። ሎሚ የመልካም መዓዛ እና የፍቅር መግለጫ እንጂ ድንጋይ ወይም ጠብመንጃ አይደለም። ስለዚህ ድርጊቴ በሕጉ ፊት "Socially acceptable" ስለሆነ ጥፋት ሊሆን አይገባም። አይደል!? ነገር ግን... እንደገና አሰብኩት። በዘመናችን "አእምሮ ያለው ሰው" (Reasonable person) ሎሚ መወርወርን እንደ ፍቅር ጥያቄ ይወስደዋል ወይስ እንደ ጥቃት? ልጅቷ "በሎሚ የምትመታኝ ምን አድርጌህ ነው?" ብላ የTort ክስ ብትመሠርትብኝ ዳኛው "ባህል ነው" ብሎ ይለቀኝ ይሆን? ወይስ "አንተ የተማርክ ሰው አይደለህ እንዴ? በዘመኑ አሠራር DM ማድረግ ሲገባህ ለምን በሎሚ ትደበድባለህ?" ብሎ ይፈርድብኝ ይሆን? በመጨረሻም በፍቅር እና በሕግ መሃል ተወጥሬ፥ አንቀጽ 2038ን ከመተላለፍ፥ 2039(ሠ)ን ተማምኖ ከመቆመር... "ይቅርብኝ!" አልኩ። የልቤን ንግሥት በሎሚ ከመምታት፣ በሩቁ ማሰቡን መረጥኩ። ከላይብረሪው አልወጣሁም፤ ቃና ዘገሊላም አልሄድኩም። ግን አንድ ተስፋ አለኝ... ምናልባት በሚቀጥለው ዓመት የፍትሐብሔር ሕጉ ተሻሽሎ "በጥምቀት በዓል ለፍቅር ተብሎ የሚወርወር ሎሚ በልዩ ሁኔታ ይፈቀዳል" የሚል አንቀጽ ከተጨመረበት... ያኔ ወጥቼ መወርወሬ አይቀርም! እስከዚያው ግን እኔና ሕጉ በላይብረሪ ተፋጠን እንውላለን። መልካም ምሽት ዛሬን በድጋሚ ፈግግግግ እድትሉ!!!! @MTULSU
ርዕስ፡- #ለይግባኝ_ማስፈቀጃ "በቂ ምክንያት" ምንድን ነው? (የሰበር መዝገብ ቁጥር 227023) የህግ ነጥቡ (The Issue of Law): ጠበቃ ወይም ነገረ-ፈጅ የይግባኝ አቤቱታን ስልጣን ለሌለው ፍርድ ቤት በማቅረቡ ምክንያት የይግባኝ ማቅረቢያ ጊዜ ቢያልፍ፣ ይህ ስህተት በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህግ ቁጥር 326(2) መሠረት ለይግባኝ ማስፈቀጃ እንደ "በቂ ምክንያት" ሊቆጠር ይችላልን? የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት የሰጠው አስገዳጅ ውሳኔ፡ ጠበቃ ለደንበኛው በቅንነትና በታማኝነት የጥብቅና አገልግሎት የመስጠት ግዴታ ቢኖርበትም፣ በያዘው ጉዳይ ላይ "በፍጹም አይሳሳትም" ተብሎ አይታሰብም። በዚህ መዝገብ (ሰ/መ/ቁ 227023) ላይ እንደታየው፦ ጠበቃው የይግባኝ አቤቱታውን ስልጣን ለሌለው ፍርድ ቤት በማቅረቡ ምክንያት ጊዜው አልፎባታል። ይሁን እንጂ ስህተቱ የጠበቃው የሙያ ስህተት እንጂ ባለጉዳይዋ (አመልካች) ሆን ብላ ያዘገየችው አይደለም። በተጨማሪም ስልጣን የሌለው ፍርድ ቤት ጉዳዩን ተቀብሎ በክርክር ማቆየቱ ለጊዜው ማለፍ እንደ አንድ ምክንያት ተወስዷል። ማጠቃለያ፡ አንድ ጠበቃ በህግ ትርጉም ስህተት ወይም ፍርድ ቤትን በመለየት ረገድ በሚፈጽመው ስህተት የይግባኝ ጊዜ ቢያልፍ፣ ይሄው ስህተት ለባለጉዳዩ እንደ "በቂ ምክንያት" ተቆጥሮ የይግባኝ መብቱ ሊጠበቅለት ይገባል። የጠበቃ ስህተት ሁልጊዜ በባለጉዳዩ ላይ ሊጫን አይገባም ተብሏል።
⚖️ የሰበር ሰሚ ችሎት ውሳኔዎች በወንጀል ሥነ ሥርዓትና በወንጀል ሕግ አተገባበር: ቁልፍ የሕግ መርሆች Abrham Yohanes የመጀመሪያውን የህግ ትርጉም (ሰ/መ/ቁጥር: 235233) እንዴት አያችሁት? በሕብረቱ ውስጥ መገኘት ብቻውን ወንጀለኛ ያደርጋል? 🧑⚖️ በሕብረት የተፈጸሙ ወንጀሎች እና የማስረዳት ሸክም * ሰ/መ/ቁጥር: 235233 * ቁልፍ የሕግ መርህ: 🤝 በሕብረት የተፈጸሙ እንደ አምባጓሮ ያሉ ወንጀሎች ሲፈጸሙ (በወንጀል ሕግ አንቀጽ 35(2))፣ ዐቃቤ ሕግ ተከሳሹ በሕብረቱ ውስጥ መገኘቱን ብቻ ነው የሚያስረዳው። ወንጀሉ ተካፋይ አለመሆኑን የማስረዳት ሸክም የተጠሪ ነው። 👮 የፖሊስ ባልደረባ ሙያዊ ግዴታ እና የቅጣት አወሳሰን * ሰ/መ/ቁጥር: 239931 * ቁልፍ የሕግ መርህ: 🛡️ የፖሊስ ባልደረባ ሥራውን ሲሠራ ወይም ተጠርጣሪን በቁጥጥር ስር ለማዋል ሲጥር እንደ አጥፊ ሊቆጠር አይችልም። የቅጣት አወሳሰን መመሪያው "ለድርጊቱ መፈጸም መንስኤው ሟች ሲሆን" የሚለው አገላለጽ ሙያዊ ግዴታውን ሲወጣ የነበረን ፖሊስ አይመለከትም። 🔒 የዋስትና መብት እና መሠረታዊ መብቶች * ሰ/መ/ቁጥር: 244554 * ቁልፍ የሕግ መርህ: 📜 የዋስትና መብት ህገ መንግስታዊ መሠረታዊ መብት ነው (አንቀጽ 19(6))። ዋስትና ሊከለከል የሚችለው በወንጀል ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 67(ሀ-ሐ) በተደነገጉ ልዩ እና በቂ ምክንያቶች ነው፣ በተደራራቢ ወንጀል መከሰስ ወይም የወንጀሉ ከባድነት ብቻውን ዋስትና ለመከልከል በቂ ምክንያት አይደለም። ⏳ ክስ አለመመስረት እና የዋስትና ጥያቄ * ሰ/መ/ቁጥር: 252231 * ቁልፍ የሕግ መርህ: ⏰ ዐቃቤ ሕግ በተሰጠው ጊዜ ክስ ሳይመሰርት ሲቀር፣ ይህ ሁኔታ ተጠርጣሪው የዋስትና ጥያቄውን በድጋሚ እንዲያቀርብ የሚያስችለው አዲስ ሁኔታ ነው። ክስ ሳይመሰረትበት አንድን ተጠርጣሪ ላልተወሰነ ጊዜ በእስር እንዲቆይ ማድረግ ህገ መንግስታዊ መብቶችን የሚጥስ ነው። ⚖️ የፍርድ እና ቅጣት ለውጥ ተጠቃሚነት ለሌላ ተባባሪ ተከሳሽ * ሰ/መ/ቁጥር: 230945 * ቁልፍ የሕግ መርህ: 🔄 በፍርድ ተሻሽሎ የአንዱ ተከሳሽ ጥፋተኝነትና ቅጣት መቀነሱ ለሌላው ተባባሪ ተከሳሽም የሚጠቅም ከሆነ፣ በወንጀል ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 196(1/ለ) መሰረት ተፈጻሚ መሆን ይገባዋል። 🏛️ የዐቃቤ ሕግ ስልጣን እና የፍርድ ቤት ገለልተኝነት * ሰ/መ/ቁጥር: 250285 * ቁልፍ የሕግ መርህ: 🔀 ዐቃቤ ሕግ ክስ የማቅረብ እና የህግ ድንጋጌ የመጥቀስ ስልጣን አለው። ፍርድ ቤት የዐቃቤ ሕግን ምስክሮች ሳይሰማ እና ወንጀሉን ሳያረጋግጥ በራሱ አነሳሽነት ድንጋጌ ለውጦ "ስልጣን የለኝም" በሚል መዝገብ መዝጋት፣ የገለልተኝነት መርህን የሚጥስ መሰረታዊ የክርክር አመራር ጉድለት ነው። 💰 የዋስትና ክልከላ መስፈርት * ሰ/መ/ቁጥር: 253740 * ቁልፍ የሕግ መርህ: ❌ የዋስትና መብት ሊከለከል የሚችለው በወንጀል ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 67(ሀ) መሠረት ተከሳሹ ግዴታውን አክብሮ ላይቀርብ ይችላል የሚል ተጨባጭ ማስረጃና ምክንያት ሲኖር እንጂ፣ በሚጣለው ቅጣት ክብደት ግምት ብቻ አይደለም። 📝 በክስ ውስጥ ዝርዝር መገለጽ * ሰ/መ/ቁጥር: 240223 * ቁልፍ የሕግ መርህ: 📢 ስለ ወንጀሉ በቂ ዝርዝር በክሱ መገለጽ እንዳለበት በወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 111 ተደንግጓል። ለክሱ መሠረታዊ የሆነው ፍሬ ነገር ሳይገለጽ ክስ መቅረቡ ተከሳሹን የሚያሳስት ከሆነ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ነው። 💀 በሞት ወይም ዕድሜ ልክ ፅኑ እስራት በሚያስቀጣ ወንጀል ላይ ሙከራ * ሰ/መ/ቁጥር: 240910 * ቁልፍ የሕግ
видео или голосовое, без подписи
የግብረ ሶዶም ወንጀል እስከ እድሜ ልክ እስራት (የተመሳሳይ ጾታ ለተፈጥሮ ተቃራኒ የሆነ ግንኙነት) የኢፊድሪ ወንጀል ህግ አንቀጽ 629_632 ጠበቃና የህግ አማካሪ ፋንታሁን ደለለው 0929101037/0983337690 መግቢያ በሀገራችን ሀይማኖት ባህል ልምድ ህግ መሠረት የወንድ ለወንድ የጾታ ግንኙነት የተወገዘ ወይም የተከለከለ ተግባር ነው። ይህን በህግም ሆነ በሀይማኖት የተከለከለ ተግባር የፈጸመ ከቀላል እስራት እስከ እድሜ ልክ እስራት የሚያስቀጣ ሲሆን የዚህ ተግባር ምንነት እና የቅጣት ደረጃውን ምንጭ በዚህ አጭር ጽሁፍ አስቀምጠናል። 1. ግብረሰዶማዊነት(የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነት) ምንነት... ይህ ድርጊት በመሠረቱ የወንድ ለወንድ ወይም የሴት ለሴት ተመሳሳይ ጾታ ግንኙነት ሲሆን ይህን ድርጊት በፈጸሙት ላይ እስከ ሶስት አመት ቀላል እስራት የሚያስቀጣ ነው። 2. በህጻናት ላይ የተፈጸመ የግብረሰዶም ወንጀል... እድሜያቸው ባልደረሰ ወይም 18 አመት ባልሞላቸው ህጻናት ላይ ይህ ድርጊት የተከሰተ እንደሆነ እና የድርጊቱ ውጤት ሞትን ያስከተለ እንደሆነ ይህን ድርጊት በፈጸመው ሰው ላይ እስከ እድሜ ልክ ጽኑ እስራት ያስከትላል። 3. ድርጊቱ በማን ይፈጸማል?.. ድርጊቱ በቀጥታ የሚፈጸመው በተመሳሳይ ጾታ ሴት ወይም ወንድ በሆነ ሰው ነው። በውንድ ሰው ላይ የሚፈጽመው ወንድ ሲሆን በሴት ሰው ላይ የሚፈጽመው በጾታው ሴት የሆነ ሰው ነው። ይሁን እንጂ ይህን ድርጊት ከመተባበር አንጻር የወንጀሉ ተባባሪ አካላት ሰወች በኢፊድሪ ወንጀል ህግ ቁጥር 37 መሠረት ተባባሪ አካላት ሊኖሩ ይችላሉ። እንዚህም በወንጀሉ ተሳታፊነት ልክ የሚጠየቁ ሲሆን የመጨረሻውን ውጤት ለማምጣት ሙሉ ተሳታፊ ከሆኑ በዛው ልክ የሚጠየቁ ናቸው። 4. የግብረሰዶም አስገድዶ መድፈር ወንጀል... የግብረሰዶም አስገድዶ መድፈር ወንጀል በህጉ በግልጽ አልተቀመጠም። ወንጀሎች በተለያየ መንገድ ረቀቅ ባለ አጠቃቀሞች አንድ ወንድ ወይም ሴት በጾታው በሆነ ሰው ላይ በተመሳሳይ ጾታ በአንድ እና ከዚያ በላይ በሆነ ሰው በተመሳሳይ ጾታ ባላቸው ከሰውየው ፍቃድ ውጪ በሆነ ይህ ይህ ድርጊት ሊፈጸም ይችላል። ይሁን እንጂ በማስገደድ የተፈጸመበት ቢሆንም ይህ ተግባር የተፈጸመበት ሰው አብሮ ከመጠየቅ ውጭ የፈጸመበት ሰው ብቻ የሚጠየቅ አይሆንም።ነገር ግን በጥቆማ እና በማስረጃነት ተባባሪ በመሆኑ እንደ ምስክርነት ስለሚቆጠር ተከሳሽ ከመሆን የሚድንበት አግባብ ቢኖርም ነግር ይህ ተግባር የተፈጸመበት ሰው የግል ተበዳይ ሆኖ የሚያመለክትበት እንጂ የሚጠየቅበት እንዳይሆን የህጉ አካል ከማድረግ አንጻር ትኩረት ተሰሮቶ ሊሰራ ይገባል። 5. ማጠቃለያ... የግብረሰዶም ወንጀል በተመሳሳይ ጾታ ሰወች መካከል የሚፈጸም ለተፈጥሮ ተቃራኒ በሆነ መልኩ የሚፈጸም ወንጀል ሲሆን ይህም ከቀላል እስራት እስከ ጽኑ እስራት የሚያስቀጣ ነው። በመሆኑም ይህን የወንጀል ተግባር ለመከላከል ማህበረሰቡ እና የፍትህ አካላት በመተባበር ይህን ድርጊት ለመከላከል አስፈላጊውን የወንጀል መከላከል ተግባራት ሊፈጸሙ ያስፈልጋል።
lady just (lady justice) 👇👇 1. *"Blindfolded, but never blind to justice — Lady Justitia stands for fairness, truth, and the rule of law." ⚖️* 2. *"She holds the scales, not for balance alone, but for the weight of truth and justice." ⚖️👩⚖️* 3. *"Lady Justitia reminds us: Justice must be blind, fair, and strong. Are you ready to uphold her values?"* 4. *"In the courtroom or in society, Lady Justice stands tall — a symbol of what we fight for in law."* 5. *"With her sword, she defends. With her scales, she judges. With her blindfold, she remains fair. Long live Lady Justitia."*
🛑 አሰሪና ሰራተኛ ህግ: የይርጋ (Statute of Limitations) ህግ ማወቅ ያለብን ቁልፍ ነገሮች! Abrham Yohanes የኢትዮጵያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በአሰሪና ሰራተኛ ጉዳዮች ላይ የይርጋ ጊዜን (ክስ የሚቀርብበት የጊዜ ገደብ) በተመለከተ የሰጣቸውን ወሳኝ የሕግ ትርጓሜዎችና መርሆዎች እናጋራችሁ። መብታችሁ በጊዜ ገደብ እንዳይታገድ እነዚህን ነጥቦች ይወቁ! 1. መደበኛ የይርጋ ጊዜ ገደቦች: ⏱️ የተለያዩ የክርክር ዓይነቶች የሚቀርቡበት የይርጋ ጊዜ ገደብ የሚከተለው ነው፦ • ወደ ሥራ ለመመለስ የሚቀርብ ጥያቄ: 3 ወራት ነው (ሰ/መ/ቁ. 238017, 229714)። • ከሥራ መቋረጥ ጋር የተያያዙ ክፍያዎች (ካሳ፣ ስንብት፣ ወዘተ): 6 ወራት ነው (ሰ/መ/ቁ. 238017, 205966)። • ከሥራ መቋረጥ ጋር ያልተያያዙ ክፍያዎች (ትርፍ ሰዓት፣ ደመወዝ ጭማሪ): 6 ወራት ነው (ሰ/መ/ቁ. 79476, 197437)። • አሰሪ በሠራተኛ ጥፋት ውል ለማቋረጥ (ከጥፋቱ እውቀት ጀምሮ): 30 የሥራ ቀናት ነው (ሰ/መ/ቁ. 230388)። • ከቅጥር ግንኙነት የሚመነጩ አጠቃላይ ክሶች: 1 ዓመት ነው (ሰ/መ/ቁ. 229247)። 2. የይርጋ ጊዜ መቆጠር መቼ ይጀምራል? 🗓 የይርጋ ጊዜ መቆጠር የሚጀምረው መብቱን ለመጠቀም ክስ ማቅረብ ከተቻለበት ቀን ጀምሮ ነው። • ግልጽ የውል መቋረጥ: ውሉ ከተቋረጠበት ቀን ጀምሮ ነው (ሰ/መ/ቁ. 238017)። • አሻሚ የውል መቋረጥ: የሥራ ውሉ መቋረጡ ግልጽ ካልሆነ፣ የይርጋው ጊዜ የሚጀምረው ሠራተኛው ስለ ውሉ መቋረጥ አውቆ ክስ ማቅረብ ከቻለበት ቀን አንስቶ ነው (ሰ/መ/ቁ. 237493, 236453, 221212, 218049)። • የማይቀይሩ ሁኔታዎች: ከወንጀል ክስ በነጻ መውጣት ወይም አሠሪው ወደ ሥራ የመመለስ ጥያቄን ውድቅ ማድረጉ የይርጋውን መነሻ ጊዜ አይቀይረውም (ሰ/መ/ቁ. 238017)። 3. የይርጋ ጊዜን የሚያቋርጡ/የሚያቆሙ ልዩ ሁኔታዎች! ⏸️ መብቱን ለማስከበር የሚጥር ወገን መብቱ በይርጋ እንዳይታገድ እነዚህ ምክንያቶች ይርጋን ሊያቆሙ ይችላሉ፦ • ከአቅም በላይ የሆኑ ሁኔታዎች (Force Majeure): o ከባድ ሕመም ክሱን በወቅቱ ማቅረብ ካላስቻለ (ሰ/መ/ቁ. 234501)። o የመንግሥት ዕገዳ ወይም የሥራ ውሉ በመንግሥት ዕገዳ ምክንያት ከቆመ (ሰ/መ/ቁ. 237497)። o የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ለክፍያ ጥያቄዎች (ለ3 ወር የሥራ መመለስ ጥያቄ ግን አያቆምም) (ሰ/መ/ቁ. 233253)። • ስልጣን በሌለው ፍርድ ቤት ክስ መመስረት: ሰራተኛው በስልጣን በሌለው ፍርድ ቤት ክስ መስርቶ መከራከሩ ይርጋን ያቋርጣል (ሰ/መ/ቁ. 216200)። • የአሠሪው ዕውቅና: አሠሪው የክፍያ መብቱን በጽሑፍ ሲያምንለት ወይም በከፊል ሲፈጽምለት (ሰ/መ/ቁ. 197437)። 4. የይርጋ ጊዜን የማያቋርጡ ምክንያቶች 🚫 • የወንጀል ክስ የመጨረሻ ውሳኔ እስኪሰጥ መጠበቅ ወይም ከክስ በነጻ መለቀቅ (ሰ/መ/ቁ. 238017, 229714)። • በእስር ላይ መሆን (ሰ/መ/ቁ. 229714)። • ክስ መስርቶ በፍርድ ቤት ፈቃድ መተው (ሰ/መ/ቁ. 205966)። 💡 የሰበር ሰሚ ችሎት ዋና መልዕክት: የሰበር ሰሚ ችሎት ውሳኔዎች የይርጋ ደንብ ዓላማ መብቱን ለማስከበር የማይተጋን ወገን ለመገደብ እንጂ ትጋት ያለውን መብቱን እንዳይጠቀም ማድረግ እንዳልሆነ ያጎላሉ። ፍርድ ቤቶችም በራሳቸው ተነሳሽነት የይርጋ መቃወሚያ ማንሳት እንደማይችሉ አስቀምጧል (ሰ/መ/ቁ. 230388)። ©አብረሃም
ያላግባብ መበልፀግ የይርጋ ጊዜ:- በሰ/መ/ቁ 34406 (ቅፅ 6)ውሳኔ መሠረት ያላግባብ መበልጸግን አስመልክቶ የሚቀርቡ ክሶች ላይ ተፈጻሚነት ያለው የይርጋ ጊዜ በፍ/ብ/ሕ/ቁ 2143(1) በተመለከተው መሰረት "የሁለት ዓመት" ይርጋ ጊዜ ነው ተብሎ የተወሰነ ቢሆንም በሰ/መ/ቁ 78629 ቅጽ 22 መሰረት ይህ ውሳኔ ተሽሮ በፍ/ብ/ሕ/ቁ 2143(1) የተመለከተው የይርጋ ዘመን አላግባብ መበልፀግን አስመልክቶ በሚቀርቡ ክሶች ላይ ተፈፃሚነት የሌለው ስለመሆኑ እና ተፈፃሚነት ሊኖረው የሚገባው "የ10 ዓመት የይርጋ ዘመን ነው ሲል ሰበር አስገዳጅ የህግ ትርጉም ሰጥቷል።
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
It might look simple but it's not...mokirut 😊 Contract II
....አሜሪካ ሀዘን ላይ ነች...በአሜሪካ south Jersey ከተማ እውቁ እና ተወዳጁ ታታሪው Kaos በመባል የሚታወቀው በአለም ዙሪያ ታዋቂው የፖሊስ ውሻ ዛሬ ከ 2ሰአታት በፊት ከዚህ አለም ድካም መሰናበቱን የsouth Jersey ከተማ ፖሊስ አስታውቋል። Kaos የጀርመን ሼፐርድ ውሻ የነበረ ሲሆን በአለም ዙሪያ የተደረጉ 156 ግዳጆችን ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይል በብቃት ተወጥቷል...ከ1ወር በፊት Kaos የመታመም ምልክት አሳይቶ የነበረ ሲሆን መንግስት 17ሺህ ዶላር በማውጣት ትልቅ ሆስፒታል ወስዶ ቀዶ ጥገና ያረገለት የነበረ ሲሆን ...ለ1ወር ካለ ምንም ስራ ረፍት ላይ ቆይቶ ጤነኛ መሆኑን በቅርብ ዶክተሩ አማካኝነት ተረጋግጦ ዛሬ ለግዳጅ እንዲሰማራ ቢደረግም ግዳጅ ላይ እያለ በኩላሊት በሽታ ህይወቱ ሊያልፍ ችሏል😭... የ Kaos ሬ ሳ ተመርምሮ በደንብ ሳያገግም ወደ ግዳጅ መሄዱ ከታወቀ የቅርብ ዶክተሩ ላይ ከ6 ወር እስከ1አመት በሚደርስ ቀላል እስራት ይጠብቀዋል Kaos ባለትዳርና የ4 ቡችላዋች አባት ነበር.. ስርአተ ቀብሩ ነገ ማለትም ሀሙስ በአሜሪካን ሰአት አቆጣጠር ከጠዋቱ 3ሰአት ላይ በ south Jersey ከተማ ታዋቂ ሰዎችና ከፍተኛ ባለስልጣናት በተገኙበት ይፈፀማል!!
ለማስተላለፍ የሚያደርጋቸውን ጥንቃቄ የሚመለከት ነው፡፡ የሟች ውርስ የሚከፈተውም ሟች መኖሪያ ስፍራና ሟች በሞተበት ጊዜ እንደሆነ በፍትሀ ብሄር ህግ ቁጥር 826 ተመልክቷል፡፡ የሟችን ውርስ ማጣራት የምንለው ደግሞ የሟችን ያለኑዛዜና በኑዛዜ ወራሾች የሚለዩበት፣ የሟች እዳ የሚከፈልበት፣ የሟች አበዳሪዎች እና ተበዳሪዎች የሚለዩበት፣ ንብረቱ በሟች ወራሾች እስኪተላለፍና ውርሱ እስከሚዘጋበት ቀን ድረስ የንብረት ማስተዳደር ስራዎች የሚከናወንበት ውስብስብ ተግባር ነው፡፡ አሁን በስራ ላይ ያለው የውርስ ህግ አጣሪ ስለሚሆኑ ሰዎች ሲደነግግ ቀዳሚውና የመጀመሪያው የውርስ አጣሪ የሚሆነው ሟች በኑዛዜ የውርስ አጣሪ አድርጎ የሾመው ሰው እንደሆነ ከገለጸ በኀላ ሟች በኑዛዜ የውርስ አጣሪ አድርጎ የሾመው ሰው ከሌለና በኑዛዜው የውርስ አጣሪ እንደሚሆንና ጠቅላላ ኑዛዜ የተደረገለት ሰው መገኘት የሟችን ያለኑዛዜ ወራሾች የአጣሪነት ስራ እንደሚያስቀረው በፍትህብሄር ህግ ቁጥር 948 ንኡስ ቁጥር 2 እና 3 የሚደነግግ ሲሆን የሟች ውርስ መዘጋት ማለት ደግሞ የሟችን ንብረት ለወራሾች በአግባቡ የማከፋፈል ስራን አይጨምርም፡፡ የውርስ አጣሪው ሀላፊነት ከላይ ያነሳናቸውን ተግባር በመፈጸምና የሟችን ወራሾችና የሟች ከእዳ ተከፍሎ የሚቀረውን ንብረት በማጣራት፣ ዝርዝርና የመጨረሻ ሪፖርት ለወራሾቹ ማቅረብ ብቻ ነው፡፡ ከዚያ በኋላ የውርሱን ንብረት ማስተዳደርም ሆነ የሟችን ንብረት መከፋፈል የወራሾች መብትና ሀላፊነት እንጂ የውርሱ አጣሪ አይደለም፡፡ በመሆኑም ውርስ አጣሪ በዋነኛነት ሊፈጽማቸው የሚችላቸው ተግባራት፣ ከሟች ውርስ መብት አለን የሚሉትን ሰዎች ሁኔታ መወሰን፣ የሟችን የውርስ ንብረት ማስተዳደር፣ የሟችን የውርስ እዳ መክፈል፣ ናቸው፡፡
ሟች የኑዛዜም ሆነ ያለ ኑዛዜ ወራሽ ያልተወና የሟችን ሀብት መንግስት የሚወርሰው በሆነ ጊዜ፣ የአስተዳደር ሕጐችን ወይም ደንቦችን መሠረት በማድረግ ዳኞች የውርሱን አጣሪ እንደሚሰይሙ የፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 949 ድንጋጌዎች ያስረዳሉ፡፡ እንደዚሁም ዳኞች በሟች ኑዛዜ፣ በሕግ ወይም በፍርድ ቤት የተሰየመውን የውርስ አጣሪ በሌላ የውርስ አጣሪ የመተካት ስልጣን እንዳላቸው የፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 951 ይደነግጋል፡፡ የውርስ አጣሪን በፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 949 መሠረት መሰየምንና በሕግ ወይም በሟች ኑዛዜ ወይም ፍርድ ቤቱ ራሱ የሰየመውን የውርስ አጣሪ መተካት /replacement / እና substitution/ ሁለት የተለያዩ ጽንሰ ሀሣቦች ናቸው፡፡ ፍርድ ቤቱ በሕግ በሟች ኑዛዜ ወይም በፍርድ ቤቱ የተሰየመን አንድ የውርስ አጣሪ ስልጣንና ሀላፊነት በማንሣት ሌላ/ሌሎች/ የውርስ አጣሪ የሚሰይመው፣ ውርስ አጣሪው የተሾመበት ኑዛዜ ዋጋ ያለው ኑዛዜ መሆኑ አከራካሪ ሆኖ ሲገኝ ወይም፣ በሌላ ምክንያት ውርስ አጣሪውን በመለየት ላይ የሚያጠራጥር ነገር ሲኖር ወይም፣ ብዙ ውርስ አጣሪዎች ለምሣሌ ስልጣናቸው 947 የሚመነጭ ብዙ ያለ ኑዛዜ ወራሾች ኖረው በፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 958 በሚደነግገው መሠረት ውርሱን በመተባበር በመግባባት ለማስተዳደርና ለማጣራት ያልተስማሙ እንደሆነ ወይም፣ ከወራሾቹ መካከል አንዱ አካለ መጠን የላደረሰ ልጅ ወይም የተከለከለ ሰው ወይም በማናቸውም ሌላ ምክንያት ለምሣሌ በአገር ባለመኖሩ፣ እብደቱ በግልጽ ያልታወቀ ሰው በመሆኑና በሌሎች ምክንያቶች ጥቅሙን ለማስከበር የማይችል በሆነ ጊዜ ወይም፣ የውርሱ አስተዳዳር ወይም የማጣራቱ ስራ ልዩ ችግር ያስነሣና ልዩ ሙያ ያላቸውን ሰወች ወይም ሌላ ችግሩን ለመቅረፍ የሚችል የውርስ አጣሪ መሰየም አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ወይም፣ በሕግ ሟች ኑዛዜ ወይም በዳኞች የተሰየመው አጣሪ ቸልተኛና ትጉህ ያልሆነ እንደሆነ ወይም የማጭበርበር ባህሪ የሚታይበትና ሀቀኝነት የጉደለው የሆነ አንደሆነ ወይም አጣሪው የማጣራት ስራውን በሚገባ ለመፈፀም ችሎታ የሌለው መሆኑ የታወቀ እንደሆነ፣ ዳኞች ከማናቸውም በጉዳዩ ያገባኛል ከሚል ባለጉዳይ ጥያቄ አቅራቢነት በሕግ፣ በኑዛዜ ወይም በፍርድ ቤት ውሣኔ ተሰይሞ የነበረውን የውርስ አጣሪ በመሻር በአካባቢው ውል ለማዋዋል ስልጣን የተሰጠውን ሰው ወይም ማናቸውንም ለስራው ብቁ ነው ብለው የሚመርጡትን ሌላ ሰው በውርስ አጣሪነት ለመሰየምና ለመተካት እንደሚችሉ የፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 951 ተመልክቶ እናገኘዋለን፡፡ በውርስ ህጋችን በግልጽ እንደተመለከተው በህግ፣ በሟች ኑዛዜ ወይም በፍርድ ቤት ውሳኔ የተመረጠ ወይም የተተካ የውርስ አጣሪ የሚከተሉት ግዴታዎችና ሀላፊነቶች ይኖሩበታል፡፡ ሟች በህይወት ዘመኑ ያደረገው ኑዛዜ ካለ ኑዛዜውን መፈለግና የሟችን የኑዛዜ ወይም ያለኑዛዜ ወራሾች እነማን እንደሆኑ ማረጋገጥ፣ የውርስ ንብረት ከብልሽትና ከብክነት ለመታደግ ተገቢውን የጥንቃቄ እርምጃ በመውሰድና ሌሎችንም አስፈላጊ ተግባራት በመፈጸም የውርሱን ሀብት ማስተዳደር፣ በግልጽ የታወቁ፣ ክርክርን የማያስነሱ መከፈል ያለባቸውን የውርስ እዳዎች በፍትሀብሄር ህግ ቁጥር 1014 በተቀመጠው ቅደም ተከተል መሰረት መክፈል፣ ሟቹ በልዩ ኑዛዜ ያደረጋቸውን ስጦታዎች መክፈልና የሟችን የኑዛዜ ቃል ለመፈጸምና ውጤት ለመስጠት ማንኛውንም አስፈላጊ ጥንቃቄ ማድረግ፣ ጥያቄው ያገባኛል በሚል ማናቸውም ባለጉዳይ ሲቀርብና ዳኞችን የሚያሳምን ሆኖ ሲገኝ ስለስራው መልካም አፈጻጸም አንድ ዋስ ወይም ሌላ የመልካም ስራ አፈጻጸም ማረጋገጫ ሊሆን የሚችል መያዣ ማቅረብ፣ ስራውን ለመተው ሲፈልግ አዲስ አጣሪ እስከሚሰየምና ተተክቶ ስራውን እስከሚጀምር ድረስ የአጣሪነት ስራውን የማከናወን፣ ሟች በአደረገው ኑዛዜ ስለአጣሪነቱ የስልጣን ወሰንና ስለስራው አፈጻጸም የሰጠውን መመሪያና ትእዛዝ ተከትሎ የመስራትና ዳኞችም ስለስልጣኑ ወሰንና ስለስራው አፈጻጸም የሚሰጡትን ትእዛዞች በማክበር የአጣሪነት ስራውን ማከናወን፣ ውርሱን አጣርቶ ከጨረሰ በኋላ ለወራሾቹ ስለማጣራቱ የስራ ክንውን ሪፖርት ማቅረብ፣ ውርስ አጣሪው ማናቸውንም የህጉን ድንጋጌዎች በሟች ኑዛዜ የተሰጡትን መመሪያዎች ወይም በዳኞች የተሰጡትን ትእዛዞች በሚቃረን በጥፋቱ ወይም በቸልተኝነቱ መንገድ ለሚያደርጋቸው ጉዳዮችና በዚያ መሰረት ለሚደርስ ጉዳት በሀላፊነት የመጠየቅ ግዴታ እንዳለበት፣ ከፍትሀብሄር ህግ ቁጥር 952፣ 954-957 እንደዚሁም የፍትሀብሄር ህግ ቁጥር 960 እና 961 በማየት መረዳት ይቻላል፡፡ በሌላ በኩል ህጉ በህግ፣ በሟች ኑዛዜ ወይም በፍርድ ቤት ውሳኔ በውርስ አጣሪነት ለሚሰየሙ ሰዎች ያስቀመጠላቸው መብት አለ፡፡ ከመብቶቹ መካከል እጅግ በጣም አስፈላጊው የውርስ አጣሪነት ስራ ማንም ሰው በፈቃዱ ብቻ ሊያከናውነው የሚገባና ማንም ሰው ያለፈቃዱ የአጣሪነት ስራዎችን ለመቀበል የማይገደድ መሆኑ ነው፡፡ አንድን ተግባር አንድ ሰው ተገድዶ እንዲያከናውን ማድረግ የተከለከለና መሰረታዊ የሆነውን የሰው ልጅ ነጻነት መብት የሚነካ በመሆኑ የውርስ አጣሪነትን ተግባር አንድ ሰው ሳይፈልግ እንዲቀበልና እንዲሰራ ማድረግ እንደማይቻል የፍትሀብሄር ህግ ቁጥር 953 በግልጽ ይደነግጋል፡፡ ሁለተኛው መብቱ ደግሞ ውርስ አጣሪው ስራውን እፍጻሜ ለማድረስ ወይም ለተወሰነ ጊዜ ለመስራት በግልጽ ግዴታ የገባ ካልሆነ በቀር በማናቸውም ጊዜ ስራውን መተው የሚችል መሆኑ ነው፡፡ እዚህ ላይ በጥንቃቄ መታየት ያለበት ጉዳይ ‹በግልጽ ግዴታ የገባ ካልሆነ በቀር› የሚለው ሀረግ ነው፡፡ በዝምታ በህግ፣ በሟች ኑዛዜ ወይም በዳኞች የውርስ አጣሪ ሆኖ እንዲሰራ መመረጡን ተቀብሎ ስራ መጀመሩ ብቻውን የማጣራት ስራውን በማናቸውም ጊዜ የመተው መብቱን አያስቀርበትም፡፡ ስራውን የመተው መብቱ ቀሪ የሚሆነው በግልጽ እራሱን ግዴታ ያስገባ እንደሆነ ብቻ ነው፡፡ ሌላው እዚህ ላይ መታየት ያለበት ውርስ አጣሪው ይህንን የማጣራቱን ስራ የመተው መብቱን እንደፈለገው ሊጠቀምበት አይችልም፡፡ የሟች ውርስ ንብረት የግድ መጠበቅና በጥንቃቄ መያዝ ስለሚገባው ሌላ ተተኪ አጣሪ እስኪመረጥና ስራውን እስኪረከብ ድረስ ስራውን እየሰራ መቆየት ያለበት መሆኑ የፍትሀብሄር ህግ ቁጥር 954 ድንጋጌዎችን በማየት ለመረዳት ይቻላል፡፡ በሶስተኛ ደረጃ ለውርስ አጣሪ የተቀመጠለት መብት አጣሪው ውርሱን ለማጣራት ለሰራው ስራ የአገልግሎት ዋጋ የማግኘት መብት ያለው መሆኑ ነው፡፡ የውርሱ አጣሪ የአገልግሎት ክፍያውን የሚያገኘው ሟች በኑዛዜው ውስጥ በሰጠው መመሪያ ወይም ወራሾቹ በሚያደርጉት ስምምነት ወይም ዳኞች በሚሰጡት ውሳኔ መሰረት ሊሆን እንደሚችል የፍትሀ ብሄር ህግ ቁጥር 959 ይደነግጋል፡፡ በመሆኑም አጣሪው ውርሱን በማጣራት ለሰራው ስራና ግልጋሎት ከውርሱ ንብረት ላይ ከላይ ባስቀመጥናቸው ሁኔታዎች ሲወሰንለት የአገልግሎት ዋጋ የማግኘት መብት እንዳለው መታወቅ ይኖርበታል፡፡ በአጠቃላይ በኢትዮጵያ የውርስ ህግ መሰረት ‹ውርሱን ስለማጣራት› የሚለው ጽንሰ ሀሳብ ምንነትና ይዘት እንደዚሁም ጠቀሜታ በጥንቃቄ ሊታይ የሚገባው ነው፡፡ የመጀመሪያው በምእራፍ ሁለትም ለመጠቆም እንደተሞከረው ‹የሟች ውርስ መከፈት› እና ‹የሟችን ውርስ ማጣራት› የሚሉት ጽንሰሀሳቦች እጅግ በጣም የተለያዩ ናቸው፡፡ የሟች ውርስ መከፈት የምንለው ሟች ህይወቱ ካለፈበት ቅጽበት ጀምሮ ምንም አይነት የሲቪል መብት ግዴታ ሊኖረው ስለማይችል ህጉ የሟች ህይወት ካለፈችበት ሰኮንድ ጀምሮ የሟች መብትና ግዴታ ለሟች ወራሾች
ውርስን ማጣራት እና ውርስን ማስተዳደር ፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨ የዚህ አጭር ጽሑፍ ዋና ዓላማው ውርስን ለማጣራት መከናወን ስላለባቸው ተግባራትና ስለ ውርስ አጣሪ አሿሿም ግንዛቤ ማስያዝ፣ ከሟች የውርስ ንብረት መብት አለኝ የሚሉ ሰዎች ጥያቄ ስለሚወሰንበት ሁኔታ ማሣየት፣ የሟች ወራሾች ውርሱን ለመቀበል ወይም ላለመቀበል ስላላቸው ምርጫ ግንዛቤ ማስጨበጥ፣ ስለ ውርስ እዳ አከፋፈል እና ስለ ወራሽነት የምስክር ወረቀት አንዳንድ ነጥቦችን ማብራራት፣ ስለ ውርስ መዘጋትና የውርስ መዘጋት ስለሚያስከትለው ውጤት ግንዛቤ፣ ማስጨበጥ ነው፡፡ ወራሽነትን ስለማጣራትና ስለ ውርስ አጣሪ የሟች ውርስ ሟች በሞተበት ጊዜና ቦታ የሚከፈት ቢሆንም የሟች ውርስ እስከሚጣራ ድረስ የሟች ንብረት ''አንድ የተለየ ንብረት፣፣ አንደሆነ ይቆጠራል፡፡ ይኸም ማለት የሟች ንብረት ከሌሎች ሰዎች ንብረት ወይም ከወራሾቹ ንብረት ጋር ሣይቀላቀል የባለቤትነት መብቱ ለወራሾች ሣይተላለፍ እንደ አንድ ልዩ ንብረት፣ Distinct estate፣ ሆኖ መያዝ እንዳለበት የፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 942 ይደነግጋል፡፡ ይኸም የሚሆነው ያለ ምክንያት አይደለም፡፡ የሟች ውርስ ሣይጣራ ንብረቱ ከሌሎች ሰዎች ንብረት ጋር ቢቀላቀል ውርሱን ለማስተዳደርም ሆነ ለማከፋፈል የሚያጋጥመው ችግር ከባድ በመሆኑ ነው፡፡ በመሆኑም ውርስን የማጣራቱ ሥራ በሟች የውርስ ስርዓት አፈጻጸም ውስጥ በቀላሉ የማይታይና እጅግ በጣም አስፈላጊ ተግባር ነው፡፡ የውርስ ማጣራት ሥራ በሟች የውርስ ስርዓት ለማስፈፀም አስፈላጊ ተግባር ነው ካልን የውርስ ማጣራቱን ተግባር ሀላፊነት ወስዶ የሚያስፈጽም አንድ ወይም ከዚያ በላይ የሆኑ ሰዎች መኖር አለባቸው፡፡ እነዚህ ውርሱን የማጣራት ተግባር የሚፈጽሙትን ሰዎች የውርስ አጣሪ በመባል ይታወቃሉ። 1. ወራሽነትን ስለማጣራት ውርስ ማጣራት ማለት፣ የሟች ወራሾች እነማን እንደሆኑ አጣርቶ መወሰን፣ የውርሱ ሀብት መጠን አይነትና ግምት እንደዚሁም የሚገኝበትን ቦታ አጣርቶ መወሰን፣ ሌሎች ሰዎች ከሟች የተበደሩትን ገንዘብ መሰብሰብና በሟች ውርስ ላይ ሊከፍላቸው የሚገቡ አስገዳጅ የሆኑ አዳዎችን አጣርቶ መክፈል፣ እንደዚሁም ሟች ልዩ የኑዛዜ ስጦታ ያደረጉላቸውን ሰዎች የተሰጣቸውን ልዩ የኑዛዜ ስጦታ መክፈል፣ ማለት እንደሆነ የፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 944 ድንጋጌዎች ያስረዳሉ፡፡ እነዚህ የውርስ ማጣራት ተግባራት በብቃት እስኪከናወኑ፣ የውርሱ ንብረት እንደ ናአንድ የተለየ ንብረትን እንደሚቆጠርና ከውርሱ ሀብት ላይ ገንዘብ ለመጠየቅ መብት ያላቸው ሰዎች ማለትም የሟች አበዳሪዎች እና የፍርድ ባለመብቶች ለገንዘባቸው ዋስትናና መያዥያ የሚሆናቸው ይኸው በመጣራት ላይ ያለው የውርሱ ንብረት ነው፡፡ ይኸም በመሆኑ ውርሱ በመጣራት ላይ እያለ ከሟች ወራሾች ገንዘብ ጠያቂ የሆኑ ሰዎች በውርሱ ንብረት ላይ አንዳችም የይገባኛል ጥያቄ ማቅረብ እንደማይችሉና ምንም አይነት መብት እንደሌላቸው ከፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 943/1/ እና 943/3/ ድንጋጌዎች ያመለክታሉ፡፡ እነዚህ ድንጋጌዎች የራሣቸው ጠቀሜታና ግብ አላቸው፡፡ ምክንያቱም የሟች ውርስ በሚጣራበት ጊዜ የሟች ወራሾች አበዳሪዎችና ገንዘብ ጠያቂዎች የውርሱን ንብረት በመያዥያነት አንዳይዙ የሚያደርገው የሟች ወራሾች ከውርሱ ንብረት ድርሻ ሊያገኙ የሚችሉት ከሟች እዳ የተረፈ ንብረት ሲኖር ብቻ በመሆኑ ነው፡፡ ህጉ የሟች ወራሾች አበዳሪዎች ውርሱ በመጣራት ላይ እያለ በውርሱ ንብረት ላይ የይገባኛል ጥያቄ እንዳያቀርቡ በሟች ወራሾች እዳ ምክንያት የውርሱ ንብረት በመያዣነት እንዳይያዝ የሚከለክል ነው፡፡ እንደዚሁም ውርሱ በመጣራት ላይ እያለ ከሟች ውርስ ገንዘብ የሚጠይቁ ሰዎች ከሟች ወራሾች የግል ሀብት ላይ አንዳችም መብት እንደሌላቸው እና የሟችን የውርስ ንብረት ብቻ መከታተል እንዳለባቸው የፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 943 ድንጋጌዎች ያሣያሉ፡፡ እዚህ ላይ ውርስን ማጣራት አስፈላጊነት በመጀመሪያ ከሟች ገንዘብ የሚጠይቁ ሰዎች ውርሱ ከመከፋፈሉ በፊት ገንዘባቸውን እንዲያገኙ ለማድረግ፣ በማስከተልም ከውርሱ በእዳነት የሚጠየቁ ለምሣሌ ለሟች የቀብር ስነ ስርዓት የወጣው ወጭ፣ ከውርሱ መከፈል ያለበት የቀለብ እዳ እና ሟች በልዩ ኑዛዜ የሰጣቸው ስጦታዎች በቅደም ተከተል ተከፍለው ሲያበቁ ነውና ከዚህ የተረፈ ንብረት ካለ ነው የሟች የሕግ ወራሾችና ጠቅላላ የኑዛዜ ተጠቃሚዎች ከሟች ውርስ ንብረት ድርሻቸውን ያገኛሉ፡፡ በመጨረሻም የውርስ ሕጋችን ወራሾችና የኑዛዜ ስጦታ የተደረገላቸው ሰወች ውርሱን ስለማጣራት ወይም ስለመካፈል በመካከላቸው በሚደረገው ክርክር ሁሉ አንድ ወይም ብዙ የዘመድ አስታራቂ ዳኞች እንዳያዩት ለመስማማት እንደሚችሉ የፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 945 ይደነግጋል፡፡ 2. የውርስ አጣሪ ከላይ እንደተገለፀው ውርስን ማጣራት በሟች የውርስ ስርዓት አፈጻጸም ወቅት እጅግ በጣም አስፈላጊ ተግባር ነው፡፡ ይህንን ውርሱን የሚያጣራው ሰው ወይም ሰዎች የውርስ አጣሪ ተብለው ይጠራሉ፡፡ የውርስ አጣሪ ከሶስቱ በአንደኛው መንገድ ሊሾም እንደሚችል የውርስ ሕጋችን ይደነግጋል፡፡ የውርስ አጣሪ፣ በሟች ኑዛዜ መሠረት፣ በሕግ ሊመረጥ ወይም ሥልጣኑን ከሕግ ሊያገኝ፣ በዳኞች ሊሾም ይችላል፡፡ የመጀመሪያውን በተመለከተ ሟች አንድ ኑዛዜ የተወ እንደሆነና ሟቹ በዚሁ ኑዛዜ ውስጥ የኑዛዜው አስፈጻሚ የሾመ እንደሆነ ሟች የመረጠው ሰው የውርሱ አጣሪ ሆኖ ያገለግላል፡፡ ሟች በኑዛዜ የውርስ አጣሪ የሾመ እንደሆነ ሟች በግልጽ በኑዛዜው ካላመለከተ በስተቀር በሟች ኑዛዜ ጠቅላላ የኑዛዜ ስጦታ የተደረገለት ሰው ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ውርሱን የማጣራት መብት ይኖረዋል፡፡ ሟች የውርስ አጣሪውን በኑዛዜ የሾመ እንደሆነ ወይም ጠቅላላ የኑዛዜ ስጦታ አድርጐ እንደሆነ ጠቅላላ ኑዛዜ ስጦታ የተደረገለት ሰው ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ውርሱን የማጣራት መብት በቅደም ተከተል ይኖራቸዋል፡፡ ሟች የውርስ አጣሪውን በኑዛዜ የሾመ እንደሆነ ወይም ጠቅላላ የኑዛዜ ስጦታ የተደረገለት ሰው የተገኘ እንደሆነ የሟችን ያሉ ኑዛዜ ወራሾች የውርስ አጣሪነት ስልጣን የሚያስቀረው እንደሆነ በፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 948 ተደንግጓል፡፡ በሁለተኛ ደረጃ ሟች በኑዛዜ የውርስ አጣሪ ያልሾሙ እንደሆነ ወይም ሟች ጠቅላላ የኑዛዜ ስጦታ ያደረገለት ሰው የሌለ እንደሆነ የሟች ያለ ኑዛዜ ወራሽ የሆኑ ሰዎች ሰውየው ከሞተበት ቀን አንስቶ ያለ አንዳች ፎርማሊቲ የውርስ አጣሪነት መብት እንደሚኖራቸው የፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 947 የሚደነግግ ሲሆን ብዙ ሰዎች የውርስ አጣሪ በሆኑ ጊዜ የአጣሪነቱን ተግባር በመተባበር መስራት እንዳለባቸው ወይም አንዱን በመወከል ለማሠራት እንደሚችሉ የፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 958 ይደነግጋል፡፡ ሶስተኛው የውርስ አጣሪ የሚሰየምበት ስርዓት በፍርድ ቤት ውሣኔ የውርሱ አጣሪ የሚሰይምበት ሁኔታ ነው፡፡ የውርስ አጣሪ በፍርድ ቤት የሚሰየመው፣ የሟች ወራሾች የማይታወቁ አንደሆነ፣ ያለ ኑዛዜ ወራሾች ውርሱን ለማጣራት የማይፈቅዱ መሆናቸውን ገልፀው ያሣወቁ እንደሆነ፣
видео или голосовое, без подписи
💰A billionaire gave a journalist an incredible lesson.. During one interview, the journalist asked the billionaire: “Sir, what’s the secret of your success?” 🤔 The billionaire handed her a check and told her to write down the amount she wanted. The journalist replied indignantly: “Sir, that’s not what I meant. I asked you: what’s the secret of your success?” 🙁 He handed her the check again, but she refused to take it. 💸 Then he tore up the check and told her: “The secret of my success is that I don’t miss a single opportunity, unlike you. 😅 You could have just become the richest journalist in the world. But your pride didn’t let you do it.” 🧠 ♥️ – if you would’ve taken such a chance Don't forget to join us👉https://t.me/lawforseekers
I want Born To Win to be a source of happiness, growth, and success for anyone who once believed their dream was out of reach.....gedefaye mengist That vision drives me every single day. Every great dream begins with a single step. Born To Win was created to remind us: your background does not decide your future. What matters most is the courage to start and the discipline to keep moving. Wherever you are today, take one bold step toward your goal—your tomorrow will thank you. Comment below with your biggest dream for 2018 E.C. Let’s inspire and learn from each other. https://t.me/lawforseekers
በኢትዮጵያ የአስገድዶ መድፈር ወንጀል ፈጻሚዎች በሞት ፍርድ እንዲቀጡ የሚፈቅድ ህግ ተዘጋጀ፡፡ ህጉ በደፋሪዎች ላይ እስከ 44 ዓመት እንዲቀጡም የተሻሻለው ህግ ይፈቅዳል፡፡ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዛሬ ይፋ ባደረገው አዲስ የወንጀል ቅጣት አወሳሰን መመሪያ ማሻሻያ መሰረት፣ በአስገድዶ መድፈር ወንጀል ምክንያት ሞት ወይም ከባድ የአካልና የአእምሮ ጉዳት የደረሰ እንደሆነ ወንጀለኛው በሞት እንዲቀጣ ይወስናል። በመመሪያው መሰረት፣ ይህ ወንጀል በደረጃ 44 ስር የሚመደብ ሲሆን፣ ይህም ከእድሜ ልክ እስራት እስከ ሞት የሚደርስ ቅጣትን ይደነግጋል። ይህ ማሻሻያ ለፀረ-ፆታዊ ጥቃት እንቅስቃሴ ትልቅ መሻሻል እና ድል ነው ተብሎለታል። የዚህ አይነቱ ወንጀል ቅጣት መጨመሩ ለወደፊቱ የፍትህ ስርዓቱን ለማጠናከር እና ጥቃቶችን ለመከላከል ትልቅ ሚና ይጫወታል ተብሎ ይታሰባል። በኢትዮጵያ 23 በመቶ ሴቶች ለጾታዊ ጥቃቶች የሚጋለጡ ከዚህ ውስጥ 7 በመቶዎቹ ወሲባዊ ጥቃቶች እንደሚደርስባቸው በ2016 ይፋ የሆነው የኢትዮጵያ ስነ ህዝብ እና ጤና ጥናት ያስረዳል። የተሻሻለው የወንጀል ቅጣት አወሳሰን መመሪያ ቁጥር 3/2017 በመጽሐፍ መልክ ታትሞ ወጥቷል። መመሪያ ቁጥር 3/2017 ሰኔ 26 ቀን 2017 ዓ.ም መጽደቁን ጠቁመው ተፈጻሚ መሆን የጀመረውም ከሐምሌ 11 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ነው። Join us Your Trusted Legal Info Centre https://t.me/Ethiolawinsider https://t.me/Ethiolawinsider https://t.me/Ethiolawinsider