tgindex
የሕግ ነዶና ፍሬ.(free legal service)

የሕግ ነዶና ፍሬ.(free legal service)

Статистика
@lawprecedent76английский

📰📇Here’s the page where you can discover any legal issues you might encounter.📃📄 የዘገየ ፍትህ እንዳልተሰጠ ይቆጠራል(justice delayed, justice denied,)

Последний пост
15 авг.
Последнее чтение
14 авг.
Постов за неделю
1
Всего постов
21
Тип
открытый
Язык
английский
В каталоге с
14 авг.
Подписчики
234
−1 за 1 дн.
Сутки
−1
−0,43%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
316
20 постов
Вовлечённость
135,0%
к подписчикам
Постов в день
0,1
всего 21
Упоминаний
0
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
23
1/48двое суток
26
1/72трое суток
28

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • видео или голосовое, без подписи

  • ##በጋብቻ ውስጥ የተፈራ የጋራ ንብረት ክፍፍል ጥያቄ በይርጋ አይታገድም !! ## የፌደሬሽን ምክር ቤት በመዝገብ ቁጥር 77/12( ሰኔ 3 ቀን 2012 ዓ.ም)በሰጠው አስገዳጅ ውሳኔ በጋብቻ ውስጥ የተፈራ ንብረት የክፍፍል ጥያቄ ጋብቻው ከፈረሰበት ቀን ጀምሮ በ 10 ዓመት ውስጥ ካልቀረበ በይርጋ ይታገዳል የሚለው አተረጎገም ተፈፃሚነት እንደሌለው ወስኗል። ይህ አይነቱ የይርጋ ገደብ የተፋቾችን ሕገ-መንግሥታዊ የንብረት መብት የሚያሳጣ በመሆኑ በ ሕገ-መንግሥቱ አንቀፅ 40(1፣7) ፣50(5)፣55፣79(1)እና 9(1) መሠረት ሕገ-መንግሥታዊ እንዳልሆነ ተወስኗል። #ስለሆነም ከፍቺ ቡሀላ የሚነሳ የንብረት ክፍፍል ጥያቄን በማንኛውም ጊዜ ማቅረብ የሚቻል ሲሆን የ 10 ዓመት የይርጋ ገደብ መከራከሪያ ሆኖ ሊቀርብ አይችልም። የዘገየ ፍትህ እንዳልተሰጠ ይቆጠራል( justice delayed,justice denied) Prepared by Feyisa Ermias(LLB)

  • ...part 3 የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ✅የፌደራል ወይም ከክልል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት የሥራ ክርክር ችሎት የሚከተሉትን ጉዳዮች ተቀብሎ የማየትና የመወሰን ሥልጣን ይኖረዋል:- አዋጅ ቁጥር 1156/2011 አንቀፅ 140(1) 1.በፌደራል ወይም በክልል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤትየሥራ ክርክር ችሎት በተሰጡ ውሣኔዎች ላይ የሚቀርብለትን ይግባኝ፤ 2.አንድን ጉዳይ ለማየት ያለውን ሥልጣን በመቃወም የሚቀርብ ይግባኝ፤ 3.በዚህ አዋጅ በአንቀጽ 123 የማኅበርን ምዝገባ በመከልከል ሚኒስቴሩ ወይም አግባብ ያለው ባለስልጣን የሚሰጠውን ውሣኔ በመቃወም የሚቀርብ ይግባኝ በዚህ አዋጅ በአንቀጽ 180(1) መሠረት የሥራ ሁኔታ ተቆጣጣሪ የሰጠውን ትዕዛዝ በመቃወም የሚቀርብ ይግባኝ፤ 4. በዚህ አዋጅ በአንቀጽ 20(3) መሠረት ሚኒስቴሩ ወይም አግባብ ያለው ባለስልጣን የሰጠውን ውሣኔ በመቃወም የሚቀርብ ይግባኝ፤ 5.በዚህ አዋጅ በአንቀጽ 122(2) መሠረት በሚኒስቴሩ ወይም አግባብ ባለው ባለስልጣን የሚቀርበውን የማኅበር ስረዛ ጥያቄ፤ 6.በዚህ አዋጅ በአንቀጽ 155 መሠረት በአሠሪና ሠራተኛ ወሳኝ ቦርድ በተሰጠው ውሣኔ የሕግ ነጥብ ላይ የሚቀርብ ይግባኝ፡፡ 2.የፌደራል ወይም ከክልል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት የሥራ ክርክር ችሎት በስንት ጊዜ ውስጥ ውሳኔ አለበት❓ ለዚህ ጥያቄ አዋጅ ቁጥር 1156/2011 አንቀፅ 140(3) የጊዜ ገደብ አስቀምጧል። ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት የሥራ ክርክር ችሎት በ60 ቀናት ውስጥ ውሣኔ መስጠት አለበት በማለት ደንግጓል በተጨማሪም የፌደራል ወይም የክልል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የሥራ ክርክር ችሎትም በ60ቀናት ውስጥ ውሣኔ መስጠት አለበት በማለት ደንግጓል 139(2) አ.ቁ 1156/2011። 2.1.የስራ ክርክር ለምን በ60ቀናት ውስጥ ውሣኔ መስጠት አለበት❓ 1.ፈጣን ፍትሕ ማረጋገጥ፡ ጉዳዩ እንዳይጓተት እና ተከራካሪ አካላት በጊዜው ምላሽ እንዲያገኙ ማድረግ። 2.ጉዳት መቀነስ፡ ሠራተኛው ያለ ሥራ የሚቆይበትን እና አሠሪው በውዝፍ ክፍያ የሚጎዳበትን ጊዜ ማሳጠር። 3.መረጋጋት መፍጠር፡ በሥራ ቦታ ላይ አለመግባባቶች ተባብሰው ድርጅቱንና ሠራተኛውን እንዳይጎዱ መከላከል። 3. ከፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቅሬታ ያለው ሰብር ወይስ ጠቅላይ ልጠይቅ ይችላል? ☑️☑️☑️☑️☑️☑️☑️☑️☑️☑️☑️ መልስ ፦ለሰበር ሰሚ ችሎት ይቻላል አዋጅ ቁጥር 1156/2011 አንቀፅ 140 (2) ለይ የሚሰጠው ውሣኔ የመጨረሻ ይሆናል ይላል።የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በሥራ ክርክር ጉዳዮች ላይ የሚሰጠው ውሳኔ «የመጨረሻ» ይሆናል ማለት ይግባኝ ማለት አይቻልም፤ ውሳኔውም ጸንቶ ይቆማል ማለት ነው።የተወሰኑ ልዩ ሁኔታዎች መሠረታዊ የሕግ ስህተት፦ መደበኛ ይግባኝ ባይኖርም፣ በወጣው ሕግ መሠረት ፍርድ ቤቱ መሠረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ሠርቷል ተብሎ ሲታመን ለየፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ብቻ ማመልከቻ ማቅረብ ይቻላል። የዘገየ ፍትህ እንዳልተሰጠ ይቆጠራል (justice delayed,jusuice denied)                            prepared by        charinet getahun (LLB ) legal affairs clerk )

  • ..........part 2 1.መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የሥራ ክርክር ችሎት የሚከተሉትንና ሌሎች ተመሳሳይ የግል የሥራ ክርክር ጉዳዮችን ተቀብሎ የማየትና የመወሰን ሥልጣን ይኖረዋል፦እነሱም ☑️ ከሥራ ማስወጣትን ጨምሮ ሌሎች የዲስፕሊን እርምጃዎችን የሚመለከቱ ክሶች፤ ☑️ የሥራ ውል መቋረጥ የሚመለከቱ ክሶች፤ ☑️.የሥራ ሰዓትን፣ የተከፋይ ሂሣብን፣ ፈቃድንና ዕረፍትን የሚመለከቱ ክሶች፤ ☑️.የአገልግሎትና የስንብት ማስረጃ ሠርተፊኬት መስጠትን የሚመለከቱ ክሶች፣ ☑️. የጉዳት ካሣን፣ የደረጃ እድገት፣ዝውውር፣ ስልጠናና የመሳሳሉትን የሚመለከቱ ክሶች፣ ☑️በዚህ አዋጅ በሌላ አኳኋን ካልተመለከተ በስተቀር በዚህ አዋጅ መሠረት የሚቀርብ ማናቸውም የጥፋትና ደንብ መተላለፍ ክሶች፡፡የአሠሪና ሠራተኛ  አዋጅ 1156/2019 አንቀፅ .139 (1-2) ።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።። 2.የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ከላይ የተዘረዘሩትን ጉዳይ በምን ጌዜ ውስጥ ወሳኔ መስጠትን አለበት? ☑️ 60 ቀናት ውስጥ ውሣኔ መስጠት አለበት፡3.መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የሥራ ክርክር ችሎት በሰጠው ውሣኔ ቅር የተሰኘ ወገን ውሣኔው በተሰጠው በ30 ቀናት ውስጥ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሥራ ክርክር ችሎት ማቅረብ ይችላል፡፡ 1156/2019 አንቀፅ art.139(3) ..... ክፍለ 3 የቀጥላል የዘገየ ፍትህ እንዳልተሰጠ ይቆጠራል (justice delayed,jusuice denied)                            prepared by        charinet getahun (LLB ) legal affairs clerk )

  • ለመሆኑ 3ኛ ወገን ወይም ሰው ባልትዳር ሴትን ወይም ባልን ከትዳር አጋሩ ለመለየት ወይም ከቤቱ ማስጠለል የፍትሐብሔር ተጠያቂነትን እንደሚያመጣ ያውቁ ይሆን!!? *# በዝርዝር ከሕጋችን አንፃር ለመተንተን እንሞክራለን:- ባልን ወይም ሚስትን ካ ባል ወይም ሚስት ፍቃድ ውጭ ማስጠለል ወይም ማስኮብለል ተጠያቂነትን እንደሚያመጣ በፍትሐብሔር ሕጋችን ላይ በግልፅ ተደንግጓ ይገኛል። በፍትሐብሔር ሕግ( አንቀፅ 2050) ንዑስ አንቀፅ 1:- ላይ በግልፅ እንደሚደነግገው አንድ ሰው ሴትየዋ ባለትዳር መሆኑዋን እያወቀ ከባሏ ፍቃድ ውጭ ባሏን ትታ እንድትሄድ ቢያሳምናት ጥፋተኛ እንደሚሆን ያሳያል። #@ እንዲሁም ከባሏ ፍቃድ ውጪ በቤቱ አስገብቶ ቢያሳድራት የህግ ተጠያቂነት እንዳለበት ያሳያል ። ##1*,ስለዚ ባጭሩ አውቀንም ሆነ ሳናውቅ ይህን ድርጊት የምንፈፅም ሰዎች የሕግ ተጠያቂነት እንደሚያመጣ አውቀን ጥንቃቄ ብናደርግ ስል ምክሬን ለገስኳቹ ልዩ ድንጋጌ(Exception) ግን አለው እሱን እንድንወያይበት ፍላጓቱ ካላቹ በላይክ ግለፁልን :: ##################& የዘገየ ፍትህ እንዳልተሰጠ ይቆጠራል(justice delayed,justice denied) Prepared by Feyisa Ermias (LLB)

  • መደበኛ የሆኑ የስራ የክርክር መፍቻ መድረኮች(labour dispute settlement mechanism) Part 1 የአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ አዋጅ …1156/2019 1.ፍርድ ቤቶች አንቀጽ (138-140) ✅.መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የሥራ ክርክር ችሎት ✅. ከፍተኛ ፍርድ ቤት(ይግባኝ) 2.አማራጭ የግጭት መፍቻ ዘዴዎች (141-144) ✅ የማኅበራዊ ምክክር ስርዓት (አንቀጽ 141) ✅. አስማሚ (አንቀጽ 142) ✅. ስለግልግል ዳኝነት እና ስለማስማማት (144) 3.የአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ ወሳኝ ቦርድ(145) ✅.ጊዜያዊ የሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ ወሳኝ ቦርድ ✅.ቋሚ የሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ ወሳኝ ቦርድ ❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤ የዘገየ ፍትህ እንዳልተሰጠ ይቆጠራል (justice delayed,jusuice denied)                            prepared by        charinet getahun (LLB ) legal affairs clerk )

  • 2 июл.1121из Ethiopianlawss

    በእርቅ ሊያልቁ የሚችሉ የወንጀል ዓይነቶች ? ⚫️በኢትዮጵያ የወንጀል ጉዳዮች እርቅ አፈፃፀም መመሪያ ቁጥር 1/2012 መሠረት በእርቅ የሚያልቁ የወንጀል ጉዳዮች በዋናነት የግል አቤቱታ አቅራቢዉ ጥቅም ላይ የሚያተኩር ፣ ቀለል ያሉ ፣ በእርቅ ቢያልቁ  ማህበራዊ ግንኙነትን የሚጠብቁ እና ወጪ ቆጣቢ የሆኑ የወንጀል ዓይነቶች ናቸው ። ⚫️ እነዚህ ወንጀሎች ከህዝብ ጥቅም ይልቅ የግል ጉዳትን መሠረት ያደረጉና በግል ተበዳይ እና አጥፊ መካከል የሚከናወኑ ናቸው ። በእርቅ ሊዘጉ የሚችሉ የወንጀል ዓይነቶች ✍️ 👉 ቀላል የአካል ጉዳቶች ፦ ከባድ ያልሆኑ ፣ በቀላሉ የሚድኑ የአካል ጉዳት ወንጀሎች ። 👉  የንብረት ጉዳቶች ፦ ያለአግባብ ንብረት ማዉደም ፣ የማታለል ድርጊቶች ( ጉዳዩ በአጥፊዉ እና በተበዳዩ መካከል ከቀረ) ። 👉 የስም ማጥፍትና ክብርን የሚነኩ ፦ ስም ማጥፍት ፤ ስድብ እና መሠል የግል ክብርን የሚነኩ ወንጀሎች ። 👉 ዛቻ እና ማስፈራሪያ ፦ የግል ደህንነትን የሚነኩ ቀለል ያሉ ዛቻዎች ።      በዝርዝር እንመልከታቸው ✍️ ✅   የእጅ  እልፊት  ( አንቀጽ  _  560 (1) ) ✅   የዛቻ ወንጀል  ( አንቀጽ  _ 580 ) ✅   ታስቦ የሚፈፀም ቀላል የአካል ጉዳት ( አንቀጽ  556 (1 ) ✅   በቸልተኝነት የሚፈፀም ቀላል የአከልጉዳት  ( አንቀጽ 559(3) ) ✅   አመንዝራነት  (አንቀጽ 652 ) ✅    ስድብና ማዋረድ  ( አንቀጽ 615 ) ✅    የስም ማጥፋት ወንጀል  ( አንቀጽ 618 ) ✅    በቤተዘመድ ንብረት ላይ የተፈፀመ ንብረት ነክ ወንጀል  ( አንቀጽ 664 ) ✅   ቀለብ የመስጠት ግዴታን ያለመወጣት  ( አንቀጽ 558 ) ✅   ጋብቻን በተንኮል ወይም በማታለል መፈጸም  ( አንቀጽ 646 ) ✅    በሌላ ሰው ሀብት ያለአግባብ መገልገል ወይም መጠቀም  ( አንቀጽ 678 ) ✅   አግኝቶ መደበቅ  ( አንቀጽ 679 ) ✅    የሰው ንብረት ላይ ሁከት ማድረግ  ( አንቀጽ 686 ) ✅   በሌላ ሰው ንብረት ላይ ጉዳት ማድረስ ( አንቀጽ  689 ) .... ወዘተ  ይገኙበታል ።    የእርቅ ሂደትና ዉጤት 👉 መቼ ይፈፀማል ? ምርመራ ከመጣራቱ በፊት ፣ ምርመራው ከተጣራ በኋላ ወይም ክስ ከተመሠረተ በኋላ በፍርድ ቤት ሂደት ( ፍርድ ከመሰጠቱ በፊት ) ሊፈፀም ይችላል ። 👉 የህግ ዉጤት ፦ እርቁ ሲፀድቅ የወንጀል ክሱ ይቋረጣል ፣ ተከሳሹ ከእስር ይፈታል ። 👉 ዓላማው ፦ ማህበራዊ ግንኙነት ሰላማዊ ሆኖ እንዲቀጥል ማገዝ ፣ የወጪ ቆጣቢነት እና የአስተማሪነት ሚና ። ⚫️ የእርቅ አፈጻጸም በተለይ የማህበረሰቡን ሰላም ለመጠበቅ እና በፍርድ ቤት ያለውን የጉዳይ ክምችት ለመቀነስ ትልቅ ድርሻ አለው ። እናም አስታርቁ ታረቁ ይላል Click https://t.me/Ethiopianlawss

  • አንድ አሠሪ ስራተኛ ሰራ በምስራበት ቦታ መጥተው ያለፈቃዱ በሞባይል ስልካቸው ሲቀርፁኝ ለምን ተቀርፁኛል በማለት በእጅ ስከለከል የአሠሪ ስልክ መሬት ቢወድቅ አሠሪውም ጠርቶኝ ፈርም በማለት ካስፈረመ በኃላ የሰራበትን ደመወዝ ሳይከፍለኝ ከስራ ያለማስጠንቀቂያ ስራ ውል ብያቋሪጥ ምን ውጤት አለው? በተጨማሪም አምባጓሮ መፍጠር የሚያስብል ነዉ? ✅ስራ ውል ያቋረጠው በሕገወጥ መንገድ ነው። ምክንያቱም የፍ/ብሐር 27 አንቀጽ 29 የሰው ፎቶግራፍ ስፅል መለጠፍ በሚለው ድንጋጌ ስር ባለፎቶግራፉ ወይም ባለስልጣኑ ካልፈቀደ በቀር ማንም ፎተግራፍ ወይም ሥዕል በሕዝብ አደባባይ ሊሰጠፍም ሆነ ሊባዛ ወይም ሊሸጥ አይችልም ይህን አድርጎ የተገኝ የተለጠፈውን ስዕልና ፎቶግራፈ በራሱ ውጭ እጥፍቶ ይቅርታ የሚል ሲሆን የምራል ካሳ ሆነ የወንጀል ተጠያቂነት እንደሚያስከትል ይደነገጋል። ✅አሡሪውን በሞባይል ስልክ ሲቀርፁ ለምን ተቀርፁኛል በማለት አምባጓሮ መፍጠር የሚያስብል ነዉ? አይደለም በአሰሪና ሰራተኛ አዋጁ በስራ ቦታ ላይ አምባጓሮ መፍጠር የሚያስብል አይደለም ምክንያቱም በስራ ቦታ ላይ አምባጓሮ መፍጠር ማለት በሥራ ቦታ ውስጥ ሰላምንና የሥራ ሥርዓትን የሚያውክ ጠብ! ክርክር፤ ረብሻ ወይም ያልተገባ ግጭት መፍጠር ማለት ነው። ለምሳሌ› ከሥራ ባልደረቦች ወይም ከአለቃ ጋር መጣላት መሳደብ ወይም ማስፈራራት የሥራ ሃደትን የሚያውክ ጩኸት ወይም ረብሻ መፍጠር ሌሎች ሠራተኞችን ወደ ግጭት ማነሳሳት በሥራ ቦታ የአካል ጥቃት ወይም የጥቃት ሙከራ ማድረግ ነው ። የዘገየ ፍትህ እንዳልተሰጠ ይቆጠራል (justice delayed,jusuice denied)                            prepared by        charinet getahun (LLB ) legal affairs clerk )

  • 23 июн.1 0865

    ዛሬ በዚህ አጭር ነባብ ወስጥ ሁለት ጥያቄ በማንሳት ጀምራለው ሁለቱን ከህግ እና ውሳኔ ጋር እንመለከት ። አነሱም 1. አሰሪው ፈቃድ(የእክል  ወይም  የዓመት ) እየከለከለ ሰራተኛው ከስራ የሚቀር ከሆነ ያለበቂ ምክንያት ከስራ አንደመቅረት የሚያስቆጥር ተብሎ እንደተወሰነ ያውቃሉ❓❓ 2.አሰሪው ፈቃድ (የእክል ወይም የዓመት ) እየተጠበቀ ምላሽ በይስጥ ሰራተኛው ከስራ ከአምስት(5) ቀን በላይ የሚቀር ከሆነ ያለበቂ ምክንያት ከስራ አንደመቅረት የሚያስቆጥር ነው ወይ አይደለም ❓ 🎤🎤🎤🎤🎤🎤🎤🎤🎤🎤   ✅1. አሰሪው ፈቃድ(የእክል  ወይም  የዓመት ) እየከለከለ ሰራተኛው ከስራ የሚቀር ከሆነ ያለበቂ ምክንያት ከስራ አንደመቅረት የሚያስቆጥር ተብሎ እንደ ወሰነ ያውቃሉ❓❓ ☑️የፌ/ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎትም በቅጽ 26 በሰ/መ/4 209939 ሰራተኛ በህመም ምክንያት አሰሪው ማሳወቅ በማይችሌበት ሁኔታ ውስጥ ካሌሆነ በስተቀር አሰሪውን በማሳወቅ እና በመንግስት እውቅና ከለው የህክምና ተቋም የህክምና ፈቃድ በማቅረብ እረፌት የማግኘት መብት ያለውን ሲሆን ሰራተኛ አሰሪው የሀኪም ፌቃድ ሳያቀርብ በህመም ምክንያት ፌቃድ ሲጠይቅ አሰሪው የስራው ሁኔታ አይፌቅድም በሚሌ ፌቃድኛ ሳይሆን ከቀረ ሰራተኛው በህግ አግባብ መብቱን ከሚያስከብር በስተቀር አሰሪው ፌቃዴ በእራሱ ሰራተኛው በራሱ ፌቃዴ ከስራ የሚቀር ከሆነ ያልበቂ ምክንያት ከስራ እንደመቅረት የሚያስቆጥርና አሰሪው የስራ ውል ለማቋረጥ የሚያስችለው ምክንያት/ጥፊት ስለመሆኑ አሰሪ እና ሰራተኛ ጉዲይ አዋጅ ቁጥር 1156/2011 art 27/1/ለ    ✅2.አሰሪው ፈቃድ (የእክል  ወይም  የዓመት )  እየተጠበቀ ምላሽ በይስጥ ሰራተኛው ከስራ ከአምስት(5) ቀን በላይ የሚቀር ከሆነ ያለበቂ ምክንያት ከስራ አንደመቅረት የሚያስቆጥር ነው ወይ አይደለም ❓ ተገቢነት ያላችው ህግ ☑️የአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ አዋጅ ያለማስጠንቀቂያ የሥራ ውል ስለማቋረጥ 27(1)b ☑️ የፍ/ብ/ሕ/ቁ 1683 እና 1684 ☑️ የፌ/ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎትም በቅጽ 26 በሰ/መ/4 209939 ትንታኔ አሰሪው ፈቃድ(የእክል  ወይም  የዓመት ) እየከለከለ ሰራተኛው ከስራ የሚቀር ከሆነ ያለበቂ ምክንያት ከስራ አንደመቅረት የሚያስቆጥር ተብሎ ውሳኔ የፌ/ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎትም በቅጽ 26 በሰ/መ/4 209939 ተመልክተናል ። ወደ ተያይዘው ጉዳዩ ስመላለስ ሰራተኛ ፈቃድ ጠየቀ ነገር ግን አሰሪው ምላሽ ባይሰጥ ከ 5ቀን በላይ ፈቃዱን እንደተቀበለው ያስቆጥራል ምክንያቱም የፍ/ብ/ሕ/ቁ 1683 እና 1684 መሰረት አስቀድሞ የሁለቱ ወገኖች የንግድ ወይም የውል ግንኙነት ያለ እንደሆነ ዝምታ ውልን እንደመቀበል የሚያስቆጥር መሆኑን እንዲሁም የግንኙነቱ መቀጠል፣ ቀደም ሲል በተደረገ የውል ስምምነት ላይ ሌላኛው ወገን የውሉን ጊዜ ለማስረዘም፣ ለማደስ ወይም ለማሻሻል ጥያቄ አቅርቦ በበቂ ጊዜ ውስጥ ተቃውሞ ወይም አሉታዊ ምላሽ ካልተሰጠ ዝምታው እንደ ስምምነት እንደሚቆጠር ይደነግጋል፡፡ ስለዚህም ያለማስጠንቀቂያ የሥራ ውል ስለማቋረጥ 27(1)b መቋረጥ ተገቢነት የለውም ። ‼️‼️🏗በመጨረሻም ለሰራተኞች ሁሉ አሰሪው ፈቃድ(የእክል  ወይም  የዓመት ) እየከለከለ ሰራተኛው ከስራ የሚቀር ከሆነ ያለበቂ ምክንያት ከስራ አንደመቅረት የሚያስቆጥር ስለሆነ በህጋዊ መንገድ መራመድ ይበጃል ። የዘገየ ፍትህ እንዳልተሰጠ ይቆጠራል (justice delayed,jusuice denied) prepared by charinet getahun (LLB ) legal affairs clerk )

  • 15/10/2018 ዓ,ም # ለመሆኑ👩‍👧‍👧 ስም ማጥፋት(Defamation) የፍትሐብሔር(ከውል ውጪ የሚመጣ ሀላፊነት)እንዲሁም የወንጀል ተጠያቂነት እንደሚያመጣ ያውቃሉ? ስም ማጥፋት(Defamation) በዝርዝር እናየዋለን:- 1#ስምማጥፋት(Defamation) :- ማለት አንድን ሰው በሶስተኛ ወገን ፊት ክብሩን፣ ዝናውን ወይም ማህበራዊ ክብሩን የሚጓዳ ነገር መናገር ወይም ማሰራጨት ነው:: ''(c,c አንቀፅ 2044)''👩‍👧‍👧 በዝርዝር ከፍትሐብሔር እና ከወንጀል ሕጋችን አንፃር ስለ ስም ማጥፋ(Defamation) እና ስለሚያስከትላቸው ውጣቶች እናያለን :- በፍትሐብሔር ሕጋችን ከውል ውጪ ስለሚመጡ ኋላፊነቶች ውስጥ በግልፅ ተደንግጎ እና ገኘዋለን። በፍትሐብሔር ሕግ (አንቀፅ 2044_2047) ስለ ስም ማጥፋት እንዲሁም ስለሚያስከትለው ኋላፊነት በዝርዝር ተገልጿል። ስለዝህ የአንድን ሰው ያለ አግባብ ስምን ማጥፋት ከውል ውጪ የሆነ ተጠያቂነ እንደሚያመጣ ያሳያል። 2#ስም ማጥፋት(Defamation) 👨‍👧‍👧 ከወንጀል ሕጋችን አንፃር(አንቀፅ 613_618) ላይ ተደንግጎ እናገኘዋለን ስም ማጥፋት(Defamation):- አንቀፅ(613)(1) ሰለሚያስከትለው ተጠያቂነት በግልፅ ያትታል ስለዝህ አንድ ግለሰብ የሌላን ግለሰብ ስም ያላግባብ ቢያጠፋ ስሜ ጠፋ ብሎ ያሰበው ግለሰብ በግል አቤቱታ አቅራቢነት(upon compliant) ቢያስገባ ፍርድ ቤቱ አቤቱታው ልክ ነው ብሎ ካመነበት እስከ 6 ውር ቀላ እስራት ወይም የገንዘብ መቀጮ ሊያስተላልፍበት እንደሚችል ተደንግጓልናል። ##@# ስድብ(insult) (በወንጀል ሕጋችን (cri.code) አንቀፅ 615)መሠረት:- አንድን ሰው በቀጥታ በስድብ፣ በአዋራጅ ቃል፣በምልክትወይም በሌላ አሳንሶ የሚያሳይ ድርጊት መፈፅም ወንጀል ነው። ይለናን የወንጀለኛ መቅጫ ሕጋችን !!!!!! ከዚህ መረዳት እንደምንችለው እንደቀልድ ምናደርጋቸው ነገሮች የወንጀልም ሆነ የፍትሐብሔር ተጠያቂነት ሊያመጡ እንደሚችሉ ነው ። ######የተለያዩ ሕግ ነክ ይዘቶችን እና የህግ ምክር እንዲሁም የተለያዩ መረጃዎችን ለማግኘት ተጨማሪ አባላት ወደ ቻናላችን በመጋበዝ በነፃ እንጠቀምበት!!!!!!!!!!!!! የዘገየ ፍትህ እንዳልተሰጠ ይቆጠራል(justice delayed,jusuice denied) prepared by feyisa Ermias (L,LB)

  • 21 июн.981из LawStudentsUnion

    ኒጀር ግብረ-ሰዶማዊነትን በህግ ከከለከሉ ከ30 በላይ የአፍሪካ ሀገራት ተርታ ተቀላቅላለች ።  የኒጀር ወታደራዊ  ሁንታ  ግብረ-ሰዶማዊነትን በወንጀል የሚቀጣ አዲስ የወንጀለኛ መቅጫ ህግ ማውጣቱን አስታወቀ። ከሀገሪቱ የፍትህ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው፣ አዲሱ ህግ ከትናንት በስቲያ ሐሙስ ጀምሮ ገቢራዊ ተደርጓል።  ስራ ላይ የዋለው አዲሱ ህግ  ግብረ-ሰዶማዊነትን ወይም መሰል ድርጊቶችን የፈጸመ ወይም ለመፈጸም የሞከረ ማንኛውም ሰው ከ5 እስከ 10 ዓመት በሚደርስ እስራት እና በገንዘብ ይቀጣል። ቅጣቱ ተመሳሳይ ጾታ ያላቸውን ሰዎች ጋብቻ ያስፈጸሙ ሰዎችን፣ ምስክሮችን፣ ጋብቻው እንዲፈጸም ፍቃድ የሰጡትን እንዲሁም የሰርጉን አዘጋጆች በሙሉ ያጠቃልላል ነው የተባለው። ከዚህ ቀደም በኒጀር ግብረ-ሰዶማዊነት በህግ የተከለከለ ባይሆንም፣ በህብረተሰቡ ዘንድ ከፍተኛ ማግለል ይደርስበት ነበር። ኒጀር ይህንን እርምጃ በመውሰድ ግብረ-ሰዶማዊነትን በህግ ከከለከሉ ከ30 በላይ የአፍሪካ ሀገራት ተርታ ተቀላቅላለች።  ግብረሰዶማዊነት በሴኔጋል፣ ኬንያ፣ ሴራሊዮን እና ታንዛኒያ እስከ 10 ዓመት እና ከዚያ በላይ በሆነ እስራት ያስቀጣል። በሶማሊያ፣ ዩጋንዳ እና ሞሪታኒያ ደግሞ የወንጀሉ ቅጣት እስከ ሞት ፍርድ ሊደርስ እንደሚችል ዘገባው አመልክቷል። ======================

  • 21 июн.881из LawStudentsUnion

    አካሌ ነፃ ይዉጣልኝ ( Habeas Corpus ) ምን ማለት ነው ? ◼️ ሰዎች በተለያዩ ቦታዎች እና ሁኔታዎች በወንጀል ተጠርጥረው ለእስር ሊዳረጉ ይችላሉ ። በወ/ስ/ስ/ህግ ሆነ በህገ _መንግስቱ ከተረጋገጡ መብቶች መካከል በ 48 ሰዓት ዉስጥ በአቅራቢያ ወደሚገኝ ፍርድ ቤት መቅረብ ይገኝበታል ። ይህ ሳይሆን ሲቀር ተጠርጣሪዉም ሆነ የእርሱ ተወካይ ያለ አግባብ መታሰራቸው ቀሪ እንዲሆን ወይም የአካሌ ነፃ ይዉጣልኝ አቤቱታ ማቅረብ ይችላሉ ። ◾️ Habeas Corpus  የሚለው ቃል የላቲን ሲሆን " Show me the body "  የሚል ትርጓሜ አለው ። ◾️ በዚህ ስርዓትም የታሠረዉን ግለሰብ ያሰረው አካል የማቅረብ ወይም  " to produce the body " ግዴታ አለበት ። ⚫️ የዚህ ዓይነቱ ክስ በየትኛው ፍርድ ቤት ይቀርባል ? የፌዴራል ፍርድ ቤቶችን ስልጣን ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር 1234/13  አንቀጽ 5 (1) (ኘ ) መሠረት አካሌ ነፃ ይዉጣልኝ አቤቱታ በፌዴራል ፍ/ቤቶች ይቀርባል ። ◼️ በህገ _ መንግስቱ ምዕራፍ 3 ላይ የተዘረዘሩት መሠረታዊ መብቶች እና ነፃነቶችን ለማስከበር ፍርድ ቤት ለመታየት ብቁ የሆኑ ጉዳዮችን ለመዳኘትም በዚሁ አዋጅ ለከፍተኛ ፍርድ ቤት ስልጣኑ ተሰጥቷል ። ⚫️ ይህ በእንዲህ እንዳለ ስለ አቤቱታ አቀራረቡ የፍትሐብሔር ስነ _ ስርዓት ህጋችን ምን ይላል ? የዚህ ህግ አንቀጽ 177_ 179 ያሉት ድንጋጌዎች የአካሌ ነፃ ይዉጣልኝ ክስ በማን ፣ የትኛው ችሎትና ማንን መክሰስ እንደሚቻል አብራርቶ ያስቀምጣል ። ◾️ አቤቱታው በራሱ በተጠርጣሪው ወይም ለእርሱ ሲል በሚቀርበው ሰው ፦ _ በቃለ _ መሀላ የተደገፈ _ የታሳሪዉን እና የአሳሪዉን ስም _ የተያዘበት ስፍራ እና _ ካሉም ይህንን የሚያስረዱ ምስክሮች ስም ያካተተ መሆን አለበት ። ፍርድ ቤቱም የተያዘውን ሰው በዋስ ወይም ያለ ዋስ እንዲለቀቅ አስፈላጊውን የግራቀኙን ክርክር ከሰማ በኋላ ሊወስን ይችላል ።                        ,,,,,,,,,,,✍️✍️✍️ @LawStudentsUnion

  • 13_10_2018 ዓ.ም ለመሆኑ ከውርስ መነቀል እና ለውርስ የማይገባ መሆን ምን ማለት እንደሆነ ያውቁ ይሆን? #######ሰላም ለሁላችን### ከውርስ መነቀል ማለት:- ከውርስ መነቀል(disinheritance) በኢትዮጵያ የውርስ ህግ አንድ ወራሽ በሕግ ከሚያገኘው የውርስ መብት እንዲነፈግ ወይም የወራሽነት መብት እንዲያጣ ማድረግ ማለት ሲሆን በመቀጠል ደግሞ ከውርስ ሊያስነቅሉ የሚችሉ ምክንያቶችን ለማየት እንሞክራለን። =# ከውርስ የሚያስነቅሉ ዋና ዋና ምክንያቶች :- *. ወራሹ ሟቹን ለመግደል ወይም ለማስገደል መሞከሩ *. በሟቹ ላይ ከባድ ወንጀል መፈፅም *. ሕጉ የሚያስከትለውን '' የውርስ አለመግባትወይም መነቀል(unworthiness to inherit) ሁኔታ ሲፈጠር። እንዲሁም ከውርስ መነቀል እና ውርስ ለሞረስ የማይገባ መሆን(unworthiness) የተለያዩ ፅንስ ሀሳቦች ናቸው አንደኛው በኑዛዜ(will) የሚደረግ ሲሆን ሌላው በሕግ በቀጥታ የሚመጣ ነው። ስለ ትርጓሜው እና ምክንያቱ የዚን ያህል ከተወያየን በሚቀጥለው ክፍል ደግሞ ከ ሕጋችን(legal framework) አንፃር ከውርስ መነቀል እና ለውርስ ተገቢ አለመሆንን እንዴት እናየዋለን በሚለው ነጥብ ላይ እናወራበታለን #* በፍትሐብሔር ሕጋችን(c,c) ላይ በዝርዝር እናየዋለን ''አንቀፅ(937_942)'' እና 838 በፍትሐብሔር ሕግ(civil code) ''ከውርስ መነቀል''(disinheritance) እና ''ውርስ የማይገባ መሆን''(unworthiness) በተለያዩ አንቀፆች ላይ ተደንግገው እናገኛቸዋለን *(1), በኑዛዜ ከውርስ መነቀል c,c አንቀፅ 971ንዕስ አንቀፅ ''1''ኑዛዜ ሚያረገው ሰው(ኑዛዜ አውጪው) ወራሽን ከውርስ ሊነቅለው እንደሚችል ይደነግጋል ነገር ግን ልጅ ወይም ሕጋዊ ወራሽ የሆነን ሰው ከውርስ እንዲነቀል የሚያደርገው ኑዛዜ ሕጋዊ እንዲሆን የመነቀሉ ምክንያት በኑዛዜ ውስጥ በግልጽ(Express will) መፃፍ አለበት አንቀፅ (938 c,c)ላይ በግልፅ ተደንግጓል። *(2), ለውርስ የማይገባ መሆን(unworthiness) # በፍትሐብሔር ሐጋችን አንቀፅ ''838'' መሠረት እንደተደነገገው:- * አውራሹን ሆን ብሎ ከገደለ(intentionally caused the death of the deceased) * የአውራሹን ወይም የሟችን ሚስት/ባል፣ ወላጆች ወይም ልጆች መግደል(intentionally caused the death of the spouse, acendant,or the deceased family) * ከላይ ከተጠቀሱት ውስጥ በአንዱ ላይ የግድያ ሙከራ ማድረግ በተጨማሪም ሌሎች ምክንያቶች በሕጉ ላይ ተዘርዝረው ይገኛሉ። #####የተለያዩ ሕግ ነክ ይዘቶችን እና የሆግ ምክር እንዲሁም የተለያዩ መረጃዎችን ለማግኘት ተጨማሪ አባላትን ወደ ቻናላችን በመጋበዝ በነፃ እንጠቀምበት!!!!!!!!!!!! የዘገየ ፍትህ እንዳልተሰጠ ይቆጠራል(justice delayed,justice denied) Prepared by Feyisa Ermias(LLB)

  • Channel name was changed to «የሕግ ነዶና ፍሬ.(free legal service)»

  • የኢትዮጵያ የፍትሐብሔር ሥነስርዓት ሕግ ስለ ይግባኝ(አቤቱታ) ምን ይላል? የሚለውን በአጭሩ እናያለን # ይግባኝ(Appeal) ማለት በፍርድ ቤት ወይም በሌላ ስልጣን አካል የተሰጠን ውሳኔ በሕግ ወይም በፍሬ ነገር ስህተት አለበት ብሎ በከፍተኛ ደረጃ ፍርድ ቤት እንደገና እንደመረመር ወይም እንዲታይ የሚቀርብ ጥያቄ ነው። # የይግባኝ አላማ * የሕግ ስተቶችን ማረም * ፍትሕ እንዲረጋገጥ ማድረግ * የታችኛው ፍርድ ቤት ውሳኔ ትክክለኛ መሆኑን መፈተሽ። # የይግባኝመሠረቶች ይግባኝ ሊቀርብ የሚችለው:- * ሕግ በተሳሳተ ሁኔታ ሲተረጎም * የማስረጃ ግምገማ ስህተት ሲኖር * ውሳኔው ከማስረጃ ጋ የማይመጣጠን ሲሆን። ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት ሚና(c,p,c Art 348 ,342) * ውሳኔን ማጽናት * ማሻሻል * መሻር * ጉዳዩ በድጋሚ እንዲታይ ለታች ፍርድ ቤት መመለስ። #&. በኢትዮጵያ የፍትሐቤር ስነ-ስርአት ሕጋችን ከአንቀፅ 321_352 በዋናነት ተደንግጓል። በልዩነት አንቀፅ 323(2) መሠረት የይግባኝ አቤቱታ በአጠቃላይ በ 60 ቀን ውስጥ መቅረብ አለበት ። # ይህ ጊዜ ካለፈ ይግባኝ በመርህ ደረጃ አይሰማም በልዩ ድንጋጌ(Exceptional) ሚሰማበት ሁኔታ አለ ማለት ነው። ############ ####የተለያዩ ሕግ ነክ ይዘቶችን ና የህግ ምክር እንዲሁም የተለያዩ መረጃዎችን ለማግኘት ተጨማሪ አባላትን በመጋበዝ በነፃ እንጠቀምበት!!!!!!!!! የዘገየ ፍትሕ እንዳልተሰጠ ይቆጠራል( justice delayed, justice denied) prepared by Feyisa Ermias(LLB)

  • ከፍትህ ሚንስትር ስለአዲሱ የወንጀል እና ማስረጃ ህግ የተሰጠ ማሳሰቢያ! JOIN 👇 👉 @tebekasamuel 👉 @ethiopian_law 👉 @tebeka 👉 CLICK ሳሙኤል ግርማ የሕግ አማካሪና ጠበቃ 0911190299 #moj

  • የስራ ክርክር ይርጋ (labour law period of limitation) በሥራበ ክርክር ጉዳዩ ለይ ለተከራካሪ ወገኖች የይግባኝ መብት ትነግራቸው ይርጋ ጊዜ አለፎ ነገር ግን ማስፈቀጃ ጠይቀው ተፈቀደላቸው ወይም ተፈቅዶለት በ30 ቀናት ውስጥ ይግባኝ ያላልኩት በጠበቃዬ ወይም በጠበቃቸን ምከንያት ነዉ ጊዜ ገደብ የለፈው በሉ ወይም ብሊ ምን ውጤት አለው?? ❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤ አዋጅ ቁጥር. 1156/2019 art. 155 1) በማናቸውም የሥራ ክርክር የቋሚ ወይም ጊዜያዊ ቦርዱ ውሣኔ በሕግ አተረጓጐም ስህተት ምክንያት ውሣኔው ተዛብቷል በሚል ቅር የተሰኘ ወገን ለከፍተኛ ፍርድ ቤት የሥራ ክርክርሎት ይግባኝ ሊጠይቅ ይችላል፡፡ ይግባኙም የሚጠየቀው የቦርዱ ውሣኔ ለተከራካሪ ወገኖች ከተሰጠ ጊዜ ጀምሮ በ30ቀናት ውስጥ መሆን አለበት፡፡ 2.ከፍተኛ ፍርድ ቤቱ የቦርዱን ውሣኔ መርምሮ የማጽናት፤ የመሻር ወይም የማሻሻል ሥልጣን ይኖረዋል፡፡ 3. ከፍተኛ ፍርድ ቤቱ የቀረበለትን ይግባኝ ጉዳዩ በቀረበ በ30ቀናት ውስጥ ውሣኔ መስጠት አለበት፡፡ C.pr.code art.326 2)በፈቃድ መጠየቂያው ማመልከቻ ላይ የተገለጸው ምክንያት ይግባኙን በጊዜው ለማቅረብ ያልቻለው በአመልካቹ ጠበቃ ወይም ነገረ ፈጅ ወይም በወኪሉ ያለመቅ ረብና በነዚሁ ጉድለት መሆኑ የታወቀ እንደሆነ ከዚህ በላይ ባለው ንዑስ ቍጥር እንደተነገረው በቂ ምክንያት ነው ተብሎ ተቀባይነትን ለማግኘት አይችልም ። 3) በዚህ ቍጥር የተመለከተው የፈቃድ መጠየቂያ ማመልከቻ ቀርቦ ተቀባይነት የለውም ተብሎ በተሰጠው ውሳኔ ላይ ይግባኝ ለማለት አይቻልም ። 4) በዚህ ዓይነት የቀረቡ ማመልከቻዎችና በፍርድ ቤቱም የተሰጡት ውሳኔዎች በይግባኝ መመዝገቢ ያደብተር ላይ መጸፍ አለባቸው ። በመጨረሻም መልዕክት አለኝ ጠበቆች ብዙ የህግ ጉዲዮች ተሰራላቸው ነገር ግን የባለጉዳዮች መብት የብልጠት እና ለእውነት ቦታ ስጡ!!!!!!!!!!

  • 16 мая1252из AleHig

    የመጀመሪያው የአፋን ኦሮሞ የሕግ መዝገበ ቃላት ተመረቀ ***** ግንቦት 06 ቀን 2018 ዓ.ም፣ (ሀገሬ ቴቪ)፤ በኢትዮጵያ የፍትሕ ስርዓት ታሪክ ውስጥ የመጀመሪያ ነው የተባለው "ዋላቡ" የአፋን ኦሮሞ የሕግ መዝገበ ቃላት ተመረቀ። ይህ መዝገበ ቃላት የፌደራል የሕግና ፍትሕ ኢንስቲትዩት፣ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ እንዲሁም ጀስቲስ ፎር ኦል ከተሰኘ ድርጅት ጋር ባደረጉት የጋራ ጥረትና ትብብር የተዘጋጀ መሆኑ ተነግሯል። በኢትዮጵያ አብዛኛው የሕግ ትምህርት በእንግሊዝኛ ቋንቋ የሚሰጥ በመሆኑ የሕግ ባለሙያዎች ወደ ስራ ሲገቡ ቃላቱን በየግላቸውና እንደተረዱት ወደ አፋን ኦሮሞ ይተረጉሙ ነበር። ይህ ወጥነት የሌለው ትርጉም በፍትሕ አሰጣጡ ጥራት ላይ የራሱን አሉታዊ ተጽእኖ ሲፈጥር መቆየቱ ተገልጿል። መዝገበ ቃላቱ የተዘበራረቁ የሕግ ቃላትን፣ ሀረጎችን እና ጽንሰ-ሀሳቦችን ወጥ በማድረግ ለሕግ ባለሙያዎችም ሆነ ለጠቅላላው ህብረተሰብ ግልጽ የሆነ የፍትሕ ስርአት እንዲኖር ትልቅ መሰረት እንደሚጥልም ተመላክቷል። ባሳለፍነው ዓመት የአማርኛ የሕግ መዝገበ ቃላት ወደ ሥራ መግባቱ ተገልጿል፡፡

  • 13 мая118из housinginaddisababa

    видео или голосовое, без подписи

  • 8 мая1311из gechilawyer

    Ibsa Gaddaa ------------------ Godina Booranaatti Abbaa Seeraa MMA Dirree kan ta’an Obbo Saayibuddiin Baantaa dhibee tasaa isaan muudateen guyyaa hardhaa du’aan addunyaa kana irraa du'aan foyamaniiru. Du'aan addunyaa kana irraa boqachuu Abbaa seeraa Obbo Saayibuddiin Baantaatiin gadda nutti dhagayame ibsaa maatii fi firoottan isaaniif jajjabina hawwina. የሐዘን መግለጫ -------------------- በቦረና ዞን የድሬ ወረዳ ፍርድ ቤት ዳኛ የሆኑት አቶ ሳይቡዲን ባንታ ባጋጠማቸዉ ድንገተኛ ህመም በዛሬዉ ዕለት ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል። ቻናላችን በዳኛ ሳይቡደዲን ህልፈት የተሰማዉን ጥልቅ ሐዘን እየገለፀን ለቤተሰቦቻቸዉና ዘመድ ወዳጆቻቸዉ መጽናናትን ይመኛል።

የሕግ ነዶና ፍሬ.(free legal service) — tgindex