"በመጀመርያ ቃል ነበር ቃልም በእግዚአብሔር ዘንድ ነበር....... ቃልም ሥጋ ሆነ" ዮሐ 1:-1-14
Статистикаእግዚአብሔር መሃሪ ነው እግዚአብሔር ፈራጅ ነው።
- Последний пост
- 10 янв.
- Последнее чтение
- 13 авг.
- Постов за неделю
- 0
- Всего постов
- 21
- Тип
- открытый
- Язык
- und
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- —
- 1/48двое суток
- —
- 1/72трое суток
- —
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
https://youtu.be/IFP3QDVU5NA
የገና በዓል መዝሙራትን ማግኘት ከፈለጉ ከላይ☝️ ያለውን forward በመንካት ወደ ቻናላችን ይቀላቀሉ
https://t.me/appgiftbbot/gift?startapp=4797301364421261196 • WinBox — Unbox and Win! • I just hit the prize — come try your luck!
ቤተ ክርስቲያን መሄድ ለማትችሉ ሰሙነ ሕማማትን በስደት በሥራ ለምታሳልፉ በየቤታችሁ ሁናችሁ ለምትሰግዱ እንዲህ እያላችሁ ስገዱ 👉 በመጀመሪያ በስመአብ ብለን የዘወትር ጸሎትን አድርሰን ውዳሴ ማርያምን ቆመን እንደግማለን በመቀጠል 👇 👉 ለከ ኃይል ክብር ወስብሐት ወእዘዝ እስከ ለዓለመ ዓለም 👉 አማኑኤል አምላኪየ ለከ ኃይል ክብር ወስብሐት ወእዘዝ እስከለዓለመ ዓለም 👉 ኦእግዚእየ ኢየሱስ ክርስቶስ ለከ ኃይል ክብር ወስብሐት ወእዘዝ እስከለዓለመ ዓለም 👉 ኃይልየ ወጸወንየ ውእቱ እግዚእየ እስመ ኮንከኒ ረዳእየ እብል በአኮቴት አቡነ ዘበሰማያት / አባታችን ሆይ/ ከቻልን እየመላለስን 12 ግዜ እያልን መስገድ 12 ጊዜ ካልቻልን የቻልነውን ያህል 👇 ይህን ስንጨርስ በዛው ቀጥለን ለአምላክ ይደሉ ይደሉ ክብር ወስብሐት ወእዘዝ እስከ ለዓለም ለሥሉስ ይደሉ ክብር ለማኅየዊ ይደሉ ክብር ለእዘዙ ይደሉ ክብር ለመንግሥቱ ይደሉ ክብር ለሥልጣኑ ይደሉ ክብር ለምኩናኑ ይደሉ ክብር ለኢየሱስ ይደሉ ክብር ለክርስቶስ ይደሉ ክብር ለሕማሙ ይደሉ ክብር 👉 እስከ አርብ ድረስ እስከዚህ ሲሆን አርብ ለመስቀሉ ይደሉ ይጨምራል እንዲህ እያልን ከሰገድን በኋላ መዝሙረ ዳዊትን መጽሐፍ ቅዱስ ከኦሪት ከነቢያት ከወንጌል የቻልነውን እናነባለን ከዛም 👇 👉 ኪርያላይሶን እብኖዲ ናይን 👉 ኪርያላይሶን ታኦስ ናይን 👉 ኪርያላይሶን ማስያስ ናይን 👉 ኪርያላይሶን ኢየሱስ ናይን 👉 ኪርያላይሶን ክርስቶስ ናይን 👉 ኪርያላይሶን አማኑኤል ናይን 👉 ኪርያላይሶን ትስቡጣ ናይን እንዲህ እያልን ከሰገድን በኋላ 👇 👉 41 ጊዜ የቻለ ከዛም በላይ ኪርያላይሶን እያሉ መስገድ ነው። ✍ የቃላት ትርጉም 👉 ኪርያላይሶን :- ቃሉ የግሪክ ሲሆን አጠራሩ "ኪርዬ ኤሌይሶን" ሲሆን "ኪርያ" ማለት "እግዝእትነ" ሲሆን "ኪርዬ" ማለት ደግሞ "እግዚኦ" ማለት ነው። ሲጠራም "ኪርዬ ኤሌይሶን" ተብሎ ነው ይህም "አቤቱ ማረን" ማለት ነው። በተለምዶ "ኪርያላይሶን" ይባላል ይኸውም "ኪርዬ" ከሚለው "ዬ" ኤላይሶን ከሚለው ደግሞ "ኤ" በመሳሳባቸው በአማርኛ "ያ" ን ፈጥረው ነው። 👉 ናይናን :- የቅብጥ ቃል ሲሆን ትርጉሙ "መሐረነ / ማረን" ማለት ነው። 👉 እብኖዲ :- የቅብጥ ቃል ሲሆን ትርጉሙ "አምላክ" ማለት ነው። "እብኖዲ ናይን" ሲልም "አምላክ ሆይ ማረን" ማለት ነው። 👉 ታኦስ ፦ የግሪክ ቃል ሲሆን ትርጉሙ «ጌታ፣ አምላክ» ማለት ነው፡፡ «ታኦስ ናይናን» ማለትም «ጌታ ሆይ ማረን» ማለት ነው፡፡ 👉 ማስያስ ፦ የዕብራይስጥ ቃል ሲሆነ ትርጉሙ «መሲሕ» ማለት ነው፡፡ «ማስያስ ናይናን» ሲልም «መሲሕ ሆይ ማረን» ማለት ነው 👉 ትስቡጣ ፦ «ዴስፓታ» ከሚለው የግሪክ ቃል የመጣ ሲሆን ትርጉሙም ደግ ገዥ ማለት ነው 👉 አምነስቲቲ ሙኪርያቱ አንቲ ፋሲልያሱ ፦ የቅብጥ ቃል ሲሆን ትርጉሙም «ተዘከረነ እግዚኦ በውስተ መንግሥትከ- አቤቱ በመንግሥትህ አስበኝ» ማለት ነው፡፡ 👉 አምንስቲቲ ሙዓግያ አንቲ ፋሲልያሱ ፦ የቅብጥ ቃል ሲሆን «ተዘከረነ ኦ ቅዱስ በውስተ መንግሥትከ -ቅዱስ ሆይ በመንግሥትህ አስበን» ማለት ነው፡፡ 👉 አምንስቲቲ ሙዳሱጣ አንቲ ፋሲልያሱ ፦ የቅብጥ ቃል ሲሆን ትርጉሙም «ተዘከረነ እግዚአ ኩሉ በውስተ መንግሥትከ- የሁሉ የበላይ የሆንክ ወይ በመንግሥትህ አስበን» ማለት ነው፡፡ "ጸልዩ ከመ እግዚእ አምላክነ ይምሐረነ ወይሣሃለነ ወይትወከፍ ስእለተነ ወያፈጽመነ ዛተ ሰሙነ በደኅና ወበሰላም ወያርእየነ ብርሃነ ትንሣኤሁ በፍስሐ ወበሐሴት ወይስረይ ለነ ኃጣዉኢነ [ጌታችን አምላካችን ራርቶ ይቅር ይለን ዘንድ ልመናችንንም ተቀብሎ ይችን ሳምንት በደኅናና በሰላም ያስፈጽመን ዘንድ የትንሣኤውንም ብርሃን በፍጹም ደስታ ያሳየን ዘንድ ኃጢአታችንንም ያስተሰርይልን ዘንድ ጸልዩ]" ✞ በእንተ ጽንዐ ዛቲ(ግብረ ሕማማት ገፅ ፻፳፪) ----------------------------------- ኪርያላይሶን እብኖዲ ናይን ኪርያላይሶን ታኦስ ናይን ኪርያላይሶን ማስያስ ናይን ኪርያላይሶን ኢየሱስ ናይን ኪርያላይሶን ክርስቶስ ናይን ኪርያላይሶን አማኑኤል ናይን ኪርያላይሶን ትስቡጣ ናይን [በቀኝና በግራ በመቀባበል በል፡፡] "እንበለ ደዌ ወሕማም፣ እንበለ ጻማ ወድካም፣ አመ ከመ ዮም ያብጽሐነ ፤ ያብጻሕክሙ፣ እግዚአብሔር በፍስሐ ወበሰላም አሜን። ✠ ተሰጥዖ ✠ *_👉 በሰሙነ ሕማማት ከሰኞ - ዓርብ እየሰገድን ተሰጥዖ የምንቀበላቸው_* ( በቃል የምንላቸው ) ከአሁን ጀምረን እንድንለማመዳቸው እንሆ ብለናል፡፡ • ለከ ኃይል ክብር ወስብሐት ወዕዘዝ እስከ ለዓለም (ለኣንተ ኃይል ክብር ጌትነት ገዥነት ለዘለዓለሙ ገንዘብህ ነው • አማኑኤል አምላኪየ ለከ ኃይል ክብር ወስብሐት ወዕዘዝ እስከ ዓለም (ፈጣሬዬ አማኑኤል ሆይ ኃይል ክብር ጌትነት ገዥነት ለዘለዓለሙ የኣንተ ነው) • ኦ እግዚእየ ኢየሱስ ክርስቶስ ለከ ኃይል ክብር ወስብሐት ወዕዘዝ እስከ ለዓለም (ጌታዬ ኢየሱስ ድርስቶስ ሆይ ኃይል ክብር ጌትነት ገዥነት ለአንተ ይገባል) • ኃይልየ ወፀወንየ ውእቱ እግዚእየ እስመ ኮንከኒ ረዳእየ እብል በአኮቴት አቡነ ዘበሰማያት እስከ ይእቲ መንግሥት ኃይል ወስግሐት ለዓለም ዓለም ድረስ ብቻ • ኃይሌና ኣምባዬ መጠጊያዬ እርሱ ጌታዬ ነው ረዳቴ ሆነህልኛልና በምስጋና እንዲህ እላላው አባታችን ሆይ እስከ ኃይል ክብር ምሥጋና ለዘለዓለሙ አሜን ድረስ ብቻ ካህናት፡- ጸልዩ በእንተ ጽንዐ ዛቲ መካን ወኲሎን መካናት እንተ አበዊነ ቅዱሳን ወገዳማት ኣዕሩግ እለ የኅድሩ ውስቴቶን ወዕቀበተ ዝንቱ ዓለም በምልዑ ከመ ይዕቀቦሙ እግዚእ ምኲሉ እኲይ ወይሥረይለነ ኃጣውኢነ፡፡ ❤ሕዝብ፡- እግዚኦ ተስሃለነ ካህናት፡- ስለዚች ቦታ መጽናት በቅዱሳን አባቶች ስም ስለሚጠሩም ቦታዎችና ገዳማት በውስጣቸውም ስለሚኖሩ ሽማግሎች በጠቅላላው ስለዚህ ዓለም መጠበቅ ጌታ ከክፋ ሁሉ ይጠብቃቸው ዘንድ የእኛንም ኃጢኣት ያስተሰርይ ዘንድ ጸልዩ ✝️ ሕዝቡ፡- አቤቱ ይቅር በለን ከላይ ያለውን ዓይነት ጸሎት በግእዝ ወይም በኣማርኛ በሚጸለይበት ጊዜ በመሓል በመሓል እግዚኦ ተስሃለነ ወይም አቤቱ ይቅር በለን እያለን እንሰግዳለን 22 ጊዜ ይባላል፡፡ ኪርያላይሶን ኪርያላይሶን ኪርያላይሶን ኪርያላይሶን እብኖዲ ናይናን ኪርያላይሶን ኪርያላይሶን ታኦስ ናይናን ኪርያላይሶን ኪርያላይሶን ማስያስ ናይናን ኪርያላይሶን ኪርያላይሶን ኢየሱስ ናይናን ኪርያላይሶን ኪርያላይሶን ክርስቶስ ናይናን ኪርያላይሶን ኪርያላይሶን አማኑኤል ናይናን ኪርያላይሶን ኪርያላይሶን ትስቡጣ ናይናን ኪርያላይሶን ከዚህ በኋላ ኪርያላይሶን ብቻ በመቀባበል በተናጥል 20 ጊዜ ይባላል፡፡ 👉 *በዕለተ ዓርብ ከጠዋት ሦስት ሰዓት ጀምሮ እስከ 12 ሰዓት የምንቀበላቸው* ✝️ • ጠዋት ሦስት ሰዓት ዲያቆን፡- ከመዝሙረ ዳዊት ላይ መዝ 21፡17 በዜማ ይላል ‹‹እግዚኦ ኢትጸመመኒ ለክስትየ እስመ አፈ ዐማፂ ወአፈ ኃጥእ አብቀው ላዕሌየ ወነበቡ ላዕሌየ በልሳነ ዐመፃ›› ❤ትርጉም፡- አቤቱ ልመናዬን ቸል ኣትበል የኃጢኣተኛና የተንኮለኛ ኣፍ በላዬ ላይ ተነቃንቀውብኛልና የሽንገላን ኣንደበትም በላዬ ላይ ተናገሩ፡፡ ካህኑ፡- የማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ 27 ከቁትር 15 እስከ 26 ካነበቡ በኋላ በሕብረት ፡- ‹‹ጊዜ ሠለስቱ ሰዓት አኃዝዎ ለኢየሱስ ወወስድዎ ይሰቅልዎ›› እየተባለ ይሰገዳል ❤ ትረጉም፡-ሦስት ሰዓት በሆነ ጊዜ ኢየሱስን ይዘው ይሰቅሉት ዘንድ ወሰዱት
"ክርስቶስሃ መድኅነ ንሰብክ" *** "በክርስቶስ ኢየሱስ የነበረ ይህ አሳብ በእናንተ ዘንድ ደግሞ ይሁን። እርሱ በእግዚአብሔር መልክ ሲኖር ሳለ ከእግዚአብሔር ጋር መተካከልን መቀማት እንደሚገባ ነገር አልቈጠረውም፥ ነገር ግን የባሪያን መልክ ይዞ በሰውም ምሳሌ ሆኖ ራሱን ባዶ አደረገ፥ በምስሉም እንደ ሰው ተገኝቶ ራሱን አዋረደ፥ ለሞትም ይኸውም የመስቀል ሞት እንኳ የታዘዘ ሆነ። በዚህ ምክንያት ደግሞ እግዚአብሔር ያለ ልክ ከፍ ከፍ አደረገው፥ ከስምም ሁሉ በላይ ያለውን ስም ሰጠው፤ ይህም በሰማይና በምድር ከምድርም በታች ያሉት ሁሉ በኢየሱስ ስም ይንበረከኩ ዘንድ፥ መላስም ሁሉ ለእግዚአብሔር አብ ክብር ኢየሱስ ክርስቶስ ጌታ እንደ ሆነ ይመሰክር ዘንድ ነው።" (ፊል. 2፥5-11) *** ጥንተ ስቅለቱ ለመድኃኔዓለም!
https://youtu.be/c55EvEAKhvE?si=Jh-ytbGkJoL6SH-E
https://youtu.be/_Fv5bTrh2Us?si=WnMh3hHpmds9UUqN
🛑ሌሎች የገና መዝሙራትን ማግኘት ከፈለጉ ከላይ ያለውን forward በመንካት ወደ ቻናላችን በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑን እሠይ_ተወለደ_የአለም_መድሀኒትየገና መዝሙር orthodox_Ethiopia ||
🥀#Na_ilaali_maalo🥀 Na ilaali maalo anoo nama hin qabu Of biraatin dhabee namaa ol na qabu Beekumsiif humnikoo si'idha abdin koo Na bira hin darbinii na fayis uumakoo 🥀 #Ceesisa 🥀 Beela'ee dheebodhe yoon bules hagabuu Marromaan koo maree yemmuuttin gaggabuu Nama si waamatee si'i kan qaaqabu Maalo naa gargaari anoo nama hin qabu 🥀 #Ceesisa 🥀 Jaamadha naan jedhee hundumtu na gatee Anis naman dhabe namnis natt hammaate Boolla dukkanatti gadi na daarbatu Si qofadhaa gofta kan na fayyifatuu 🥀 #Ceesisa 🥀 Si barbaachun dhufe mana kooti ka'e Si arguun barbaade mukaattan olba'ee Na dura gorani na dhoksun fuula kee Anoo nama hin qabu na fayis ilma kee 🥀 #Ceesisa 🥀 Nama of biraa dhabee yoon dhabees fayinaa Fayyuu osoon barbaadu ciisee bishaan cinaa Dhukubsadhee ciisee waggoota hedduu kanaa Fayyii galii jettee deemi garaa mana ለሁሉም ኦርቶዶክሳዊያን እንዲደርስ 👉#share እና #join ያድርጉ ያስደርጉ 👉@enatachinmaryam
https://www.youtube.com/watch?v=4Ks1bvvMoKM
🛑Na Ilaali Maloo,F/taa Biqilaa Mitikkuu,Faarfannaa Afaan Oromoo Ortodoksii Tewahidoo haaraa ,2022 ለሁሉም ኦርቶዶክሳዊያን እንዲደርስ 👉#share እና #join ያድርጉ ያስደርጉ 👉@enatachinmaryam
https://t.me/gemzcOin_bot/tap?startapp=Vedsl-UOlC53kRh9wdvxaR Play gemz with me and earn coins! 🏆+2.5K coins as a first-time bonus 💎+50K coins if you have Telegram Premium
https://manybeckon.top/8d48fwgJCUNbW3dWe3F6CgICATVhYFt6YRwKNX01IhwCEDYfSiotKS0HNR4pAHw6IEsGSAQgDyA4ThsYSDczaB5JCwx-HnswHw&p=vymhtg&_mi1726500575473
a
ቀና ስል ከሰማይኮከብ ይመራኛል የፍቅርህ መአዛ ልቤን ይጠራኛል እንደ አጭሩ ቀራጭ ሾላ ላይ ብወጣ ከቤቴ ሊገባ መምህሩ መጣ እንዴት እንዴት ብለህ ተገኘህ እኔ ቤት/2/ እንዴት አልሰለቸህ መተኛት ከበረት/2/ ለሁሉም ኦርቶዶክሳዊያን እንዲደርስ 👉#share እና #join ያድርጉ ያስደርጉ 👉@enatachinmaryam
ሌሎች የእንቁጣጣሽ እና የመስቀል መዝሙሮችን ማግኘት ከፈለጉ ከላይ ያለውን forward በመንካት ወደ ቻናላችን በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑን 🌺🌼አበባዮሽ🌺🌼 እሰይ /ደስ ደስ ይበለን/(፪)🌼 አዲሱ አመት መጣልን ደስ ደስ ይበለን ሆ ብለን መጣን ሆ ብለን(፪) ጌቶች አሉ ብለን🌻 ሆ ብለን መጣን ሆ ብለን(፪) እሜቴ አሉ ብለን ሆ ብለን መጣን ሆ ብለን(፪) ዘመን መጣ ብለን 🌼🌼 አበባዮሽ - - - ለምለም(፪) ባልንጀሮቼ - - - ለምለም ግቡ በተራ - - - ለምለም🌼 በእግዚአብሔር መቅደስ - - - ለምለም በዚያች ተራራ - - - ለምለም እንድታደንቁ - - - ለምለም የአምላክን ሥራ - - - ለምለም ህይወት ያገኛል - - - ለምለም እርሱን የጠራ - - - ለምለም 🌺አበባ አበባ ፈካ ዘመን ሲተካ(፪)🌼 አበባዮሽ - - - ለምለም (፪) ክረምት አለፈ - - -ለምለም ጨለማው ጠፋ- - - ለምለም የመስቀሉ ቃል - - -ለምለም ሆነልን ደስታ - - -ለምለም እናገልግለው - - - ለምለም ቤቱ ገብተን - - - ለምለም ትንሽ ትልቁ - - - ለምለም ተሰልፈን - - - ለምለም🌾 🌺አበባ አበባ ፈካ ዘመን ሲተካ(፪)🌼 አበባዮሽ - - -ለምለም(፪) ያንን ኩነኔ - - - ለምለም ዘመነ ፍዳ - - - ለምለም የሞቱ በራፍ - - - ለምለም ያ ምድረበዳ - - - ለምለም ልክ አንደ ክረምት - - - ለምለም ሄደ ተገፎ - - - ለምለም ፀሐይ ወጣልን - - - ለምለም ጨለማው አልፎ - - - ለምለም🌼 🌸አበባ አበባ ፈካ ዘመን ሲተካ(፪)🌺 አበባዮሽ - - - ለምለም(፪) ይኸው መስከረም - - - ለምለም ይኸው ፀሐይ - - - ለምለም ንጉሡ ወርዶ - - - ለምለም ከላይ ሰማይ - - -ለምለም🌼 አውደ ዓመት ሆነ - - - ለምለም ደስታ ሰላም - - - ለምለም ፍቅር ሲገለጥ - - - ለምለም በአርያም🌿 - - - ለምለም 💐አበባ አበባ ፈካ ዘመን ሲተካ(፪)🌻 አበባዮሽ - - - ለምለም(፪) ይኸው አበባ - - - ለምለም ለምለም ቄጤማ🌾 - - - ለምለም አዲሱ ዘመን - - - ለምለም አምጥቷልና - - - ለምለም በሩን ክፈቱ - - - ለምለም መኳንንቶቹ - - - ለምለም የክብር ንጉሥ - - - ለምለም ይግባ ቤታችሁ - - - ለምለም 🌹አበባ አበባ ፈካ ዘመን ሲተካ(፪) 🌼 አበባዮሽ - - - ለምለም(፪) ቤታችሁ ይሙላ - - - ለምለም ሰላም ደስታ - - - ለምለም🌼 ሰጥቷችሁ እርሱ - - - ለምለም የሁሉ ጌታ - - - ለምለም ከዘመን ዘመን - - - ለምለም ያሸጋግራችሁ - - - ለምለም🌺 የሽበትን ዘር - - - ለምለም ይሸልማችሁ - - - ለምለም 🌼አበባ አበባ ፈካ ዘመን ሲተካ🌼 ይሸታል ዶሮ የእማምዬ ጓሮ ይሸታል ጠጅ ጠጅ የአባብዬ ደጅ🌼 አብዬ ኧኸ አባብዬ ደግሞም እማምዬ መጣሁ ለሰላምታ🌺 ከቤት አሉ ብዬ እንኳን ለአዲሱ ዓመት አደረሰዎት ብዬ💐 🌼 ከብረው ይቆዩን ከብረው የክብርን ወንጌል ሰምተው🌼 የበጉን ሥጋ በልተው የአምላክን ፊቱን አይተው ከብረው ይቆዩን ከብረው🌸 መዝሙር 🌺በዘማሪያን🌼 ወርቅነሽ ተፈራና ፅጌሬዳ ጥላሁን << በቸርነትህ ዓመትን ታቀዳጃለህ ምድረ በዳውም ስብን ይጠግባል >> መዝ ፷፭፥፲፩🌼
t.me/catsgang_bot/join?startapp=PL9s5ypuP5D9Tv40vipDF Meow, lets see who is OG 😼
ገብታችሁ start በልሉኝ ከታላቅ ይቅርታ ጋር 👆👆👆👆
t.me/empirebot/game?startapp=hero467752847 🔥Play with me, grow your startup. 💸 +5k coins as your first gift 💵 +25k coins if you have Telegram Premium
ጥያቄኽ ምንድነው ሳትሄድ ፈልገው: 🌫🌫🌫🌫🌫🌫🌫🌫🌫🌫🌫🌫🌫 ደብረ ታቦር በአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ “እንግዲህስ ወደ ታቦር ተራራ ስለመውጣት ወደተናገሩ ወደ ወንጌላውያን ዜና ነገር እንመለስ፡፡ ማቴዎስ እንዲህ አለ፡- ከስድስት ቀን በኋላ ጴጥሮስንና ዮሐንስን ያዕቆብንም ይዟቸው ብቻቸውን ወደ ረጅም ተራራ አወጣቸው መልኩም በፊታቸው ተለወጠ ልብሱም እንደመብረቅ ብርሃን ነጭ ሆነ ሙሴና ኤልያስም ከእርሱ ጋር ሲነጋገሩ ታዮአቸው፡፡ (ማቴ 17፡1-8) ማርቆስ በስድስተኛው ቀን ጌታ ኢየሱስ ጴጥሮስንና ያዕቆብን ዮሐንስንም ወሰዳቸው ብቻቸውንም ወደ ረጅም ተራራ አወጣቸው መልኩም በፊታቸው ተለወጠ ልብሱም እንደመብረቅ አብለጨለጨ በምድር ላይ ሳሙና እንደዚያ አድርጎ ማንጻት እንደማይቻለው እንደበረዶ ነጭ ሆነ፡፡ ሙሴና ኤልያስም ከጌታ ኢየሱስ ጋር ሲነጋገሩ ታዩአቸው አለ፡፡ (ማር 9፡2-8) ሉቃስም ከዚህም ነገር በኋላ በስምንተኛው ቀን ጌታ ኢየሱስ ጴጥሮስንና ያዕቆብን ዩሐንስንም ይዟቸው ሊጸልይ ወደተራራ ወጣ ሲጸልይም መልኩ ተለወጠ ልብሱም እንደመብረቅ ሆነ ከእነርሱም በክብር ተገልጠው በኢየሩሳሌም ይሆን ዘንድ ያለውን ክብሩን የተናገሩ ሙሴና ኤልያስ ናቸው፡፡ (ሉቃ 9፡28-31) ማቴዎስና ማርቆስ አንድ ቃል ተናገሩ፡፡ በስድስተኛው ቀን ማለትም በአንድ በኩል በስድስተኛው ቀን ተብሎ ይተረጎማል ከዚህ በኋላ በስምንተኛው ቀን ማለትም ደግሞ ሌላ መንገድ አሳየ እንግዲህ ሉቃስ በመናገር ከወንድሞቹ (ከማቴዎስና ከማርቆስ) እንዴት ተለየ? ትርጓሜውን እንናገር፡፡ ማቴዎስ እና ማርቆስ በዕብራውያን በሮማውያን በወር መባቻ ተናገሩ ነሐሴ ስምንት ቀን በዕብራውያን ወሮች የአብ መግቢያ በሮሜም ወሮች የአውግስጦስ መግቢያ ነውና፡፡ ሰባቱን የነሐሴን ቀኖች ከተውኸው በዕብራውያን ወሮች ወደ ሐምሌ በሮሜም ወሮች ወደ መስከረም ይሆናል በአሥራ ሦስቱ ስድስት ከዕብራይስጥና ከሮማይስጥ ከመባቻ ስድስት ቀን ይቀርልሃል በሰርቅ አንድ ናቸው በወሮቻቸው ስም ግን በየአጠራራቸው ነው፡፡ ስለዚህም ሁለቱ ወንጌላውያን ጌታ ወደ ታቦር ተራራ ከመውጣቱ አስቀድሞ እውነት እውነት እላችኋለሁ ከዚህ ከቆሙት የእግዚአብሔርን መንግሥት እስኪያዩት ድረስ ሞትን የማይቀምሱት አሉ ማለትን እንዳስቀደመ ተናገሩ፡፡ ማቴዎስና ማርቆስ በዕብራውያን አምስተኛ ወር መባቻ ወደ ታቦር ተራራ እስከወጡበት ድረስ ያሉት ቀኖች ቆጠሩ ስድስት ቀንም ሆነላቸው ስለዚህም በስድስተኛው ቀን ወሰዳቸው አሉ፡፡ ሉቃስም ጌታ ኢየሱስ በፊሊጶስ ዘቂሳሪያ አውራጃ እውነት እውነት እላችኋለው በዚህ ከቆሙት መካከል የእግዚአብሔርን መንግሥት ሳያዩ ሞትን የማይቀምሱ አሉ ካለበት ቀን ጀምሮ የፊቱ መልክ በታቦር ተራራ በጴጥሮስና በያዕቆብ በዮሐንስም ፊት ብርሃን እስከሆነበት ቀን ድረስ ያሉትን ቀኖች ቆጠረ፡፡ ስምንት ቀን ሆነለት፡፡ ስለዚህም ከዚህ ነገር በስምንተኛው ቀን ጴጥሮስንና ያዕቆብን ይዟቸው ሊጸልይ ወደ ተራራ ወጣ ሲጸልይም መልኩ ተለወጠ አለ፡፡ ...ዳግመኛም ጌታችን በታቦር ተራራ ለምን ከነቢያት አንድ ድንግል ከሐዋርያትም ሁለት ደናግልን ከነቢያት ከነቢያት አንድ ያገባ ከሐዋርያትም አንድ ያገባ አመጣ አለቅነት ግን ባገቡት ዘንድ ጸና፡፡ ሙሴ የነቢያት አለቃ ጴጥሮስም የሐዋርያት አለቃ ነው ይህ ስለምን ሆነ? (ቢሉ) ደናግል ባገቡት ላይ እንዳይመኩ እግዚአብሔር በጥበቡ ያደረገው ሥርዓት ነውና፡፡ ምእመናንም ያገባ ኤጲስ ቆጶስ መሆን አይቻለውም እንዳይሉ ነው፡፡ እግዚአብሔር ይህን ያደረገው የድንግልና ክብር አቃልሎ አይደለም የመመካትን ሸለፈት ከደናግል ልብ ያስወግድ ዘንድ ነው እንጂ እግዚአብሔር በድንግልናው ከሚመካ ድንግል ይልቅ ስለኃጢአቱ የሚያለቅሰውን አመንዝራ ይወዳልና፡፡ የመብራት ፈትል ያለ ዘይት በጾምና በጸሎት መትጋትስ ያለ የዋህነት ቤተክርስቲያንንም መከተል ለድሆች ያለመራራት ድንግልናም ያለትህትና ምን ይጠቅማል፡፡ ስለ መመካትም ከአለቅነት ያራቃቸው በያዕቆብና በዮሐንስ ዓመፃ ተገኝቶ አይደለም፡፡ ዓመፃስ ቢኖርባቸው በእቅፍ ባላስቀመጣቸው ነበር ዘወትር ራስን ከፍ ያለማድረግ ትኖር ዘንድ ለቤተክርስቲያን ሥርዓት ሠራላት እንጂ ድንግል የሆነውም ድንግል ባልሆነው ላይ እንዳይመካ፡፡ ድንግል ያልሆነው ጴጥሮስ በቀኖናው ትእዛዝ ዮሐንስን እንዳከበረው ድንግሉን በመላእክት ሥርዓት እንዲያየው ሥርዓት ሠራ፡፡” 👉 መጽሐፈ ምስጢር 30፡19-27 አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ስለ ታቦሩ ምሥጢር "ጴጥሮስ ሆይ! የእግዚአብሔርን ልጅ ፤ እንደምን <መምህር ሆይ በዚህ እንኖር ዘንድ ይሻላልና ፤ ሦስት ሰቀላዎችን እንሥራ አንዱን ለአንተ አንዱን ለሙሴ አንዱን ለኤልያስ> አልኽው? ፤ ለአንተስ የቀደመውን የአዳምን ደም ግባት አይተህ ከአዳም ሴት ልጅ ፣ በሥጋ በተወለደው ፣ 'በፊቱ ብርሃን' እየተደሰትህ በዚያ ትኖር ዘንድ በተሻለህ ነበር። + እናንተ በዚያ ኖራችሁ ቢሆን የፊቱ መልክ በታቦር ተራራ ብርሃን በሆነው በእርሱ በጉንጮቹ በጥፊ መመታት ካልሆነ በቀር ፣ ቤተ ክርስቲያን በማን ፊት ትድን ነበር? + እናንተ በዚያ ከኖራችሁ በቀራንዮ ተራራ በመስቀል ላይ ለዓለም መዳን ማን እጁን ይቸነከር ነበር? ከማንስ ጎን የሕይወት ውኃ ወደ አዳም መቃብር ይፈስስ ነበር? + እናንተ በዚያ ከኖራችሁ ለሙታን ሕይወት ይሆን ዘንድ ማን በሥጋ ሞትን ይቀምስ ነበር? ማንስ የጻድቃንን ነፍሳት ከአንጦርጦስ ሊያወጣቸው ይችል ነበር? + እናንተ በዚያ ኖራችሁ ቢሆን ጦርነትን ያደርግ ዘንድ ማን ከጨለማ ሠራዊት ጋር ለመዋጋት ይዘጋጅ ነበር? አሕዛብን ከጣዖት አምልኮ ይታደጋቸው ዘንድ በቤልሆር ሠራዊት ላይ ማን ጦረኛ ያስነሣ ነበር? + እናንተ በዚያ ኖራችሁ ቢሆን ማን ቤተ ክርስቲያንን በአንተ ላይ ይሠራት ነበር? ምሰሶዎቿ ሐዋርያትን ፣ በሮቿ ነቢያትን ፣ ግድግዳዎቿ ሰማእታትንስ ማን ያቆም ነበር? + እናንተ በዚያ ኖራችሁ ቢሆን ማን ሂዱና በዓለም ዳርቻዎች ሁሉ የመንግሥትን ወንጌል አስተምሩ ፤ ስታጠምቁአቸውም "በአብና በወልድ በመንፈስ ቅዱስም ስም በሉ' ብሎ ይልካችሁ ነበር? "ጌታችን በደብረ ታቦር የለበሰው ብርሃን ፣ የመለኮት ብርሃን አይደለም። የመለኮት ብርሃን የታየስ ቢሆን ምድርን ባነዋወጣት ፣ ባሕርን ባናወጻት ፣ ዓለምም እርሱን መቻል በተሳነው ነበር። ጌታ የለበሳት የብርሃን ጸዳል ግን አዳም ከኤዶም ገነት ውስጥ በነበረ ጊዜ የነበረችው ብርሃን ናት።" አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ (መጽሐፈ ምሥጢር ምዕ 30፥36 -