Lex Ethiopia
СтатистикаLex Ethiopia is a platform for sharing Ethiopian legal knowledge and resources. It provides codes, proclamations, regulations, and directives. The channel also shares legal news, lawyers’ insights, academic materials and legal opportunities for lawyers.
- Последний пост
- 15 авг.
- Последнее чтение
- 14 авг.
- Постов за неделю
- 12
- Всего постов
- 36
- Тип
- открытый
- Язык
- английский
- Категория
- Новости и СМИ
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 51
- 1/48двое суток
- 58
- 1/72трое суток
- 63
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
የባንክ ደረሰኝ (bank receipt) የብድር ዉል መኖሩን አያረጋግጥም፡፡ የባንክ ገንዘብ መላኪያ ሰነድ ገንዘቡ መላኩን እንጂ በምን ምክንያት እንደተላከ ወይም በአደራ ስለመላኩም ሆነ በሕግ የብድር ዉል ግንኙነት መኖሩን ለማስረዳት ተቀባይነት ያለዉ ማስረጃ አይደለም። የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በሰበር መዝገብ ቁጥር 221476 ጥቅምት 28 ቀን 2015 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ.
#የስራ__ማስታወቂያ_ማስተካከያ ወልድያ ዩኒቨርስቲ ለሕግ ትምህርት ቤት ረዳት ምምህርነት ባወጣው ማስታወቂያ ላይ ቀደም ሲል ለወልድያ ዩኒቨርስቲ ምሩቃን ብቻ የነበረው ተስተተካክሎ ለሁሉም ዩኒቨርሲቲ የመጀመሪያ ድግሪ ተመራቂዎች ተደርጓል። ፍላጉቱ ያላቹ አዲስ እና ነባር የመጀመሪያ ድግሪ ተመራቂዎች ማመልከት ትችላላችሁ። ተፈላጊ ብዛት: 06 የትምህርት ደረጃ: LL.B)
без подписи
በአድሱ አዋጅ መሰረት የተዘጋጀ አድሱ የቤት ኪራይ ውል ፎርም https://t.me/lex_ethiopia https://t.me/lex_ethiopia https://t.me/lex_ethiopia
የመቐለ ዓቃቤ ሕግ በፍርድ ቤቱ ውሳኔ ይግባኝ ጠየቀ። ከዘውዱ ሃፍቱ ግድያ ተያይዞ የተሰጠውን የሁለቱን ተከሳሾች " ነጻ ናችሁ " የፍርድ ቤት ውሳኔ በመቃወም ይግባኝ ማቅረቡን የመቐለ ከተማ ዓቃቤ ሕግ ፅህፈት ቤት አስታወቀ። የፅህፈት ቤቱ ኃላፊ ታደሰ ባይሩ የመቐለ ማዕከላይ ፍርድ ቤት በዘውዲ ሃፍቱ ግድያ ተከሰው በነበሩ ግለሰቦች ላይ የዕድሜ ልክ እስራት ውሳኔ ሰጥቶ መዝገቡን ዘግቶ እንደነበር ገልጸዋል። ነገር ግን ተከሳሾቹ ለሰበር ሰሚ ችሎት ባቀረቡት ይግባኝ በነፃ እንዲሰናበቱ መወሰኑን ኃላፊው ጠቁመዋል። ዓቃቤ ሕግም ውሳኔውን እንደማይቀበል በመግለጽ ለትግራይ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኝ ማቅረቡን አስረድተዋል። ታደሰ እንደገለጹት፣ ተከሳሾቹን በነፃ የሚያሰናብተው ውሳኔ አግባብ አይደለም በሚል እና የቀደመው ውሳኔ በዳኞች 2 ለ1 ድምፅ መሻሩን በመጥቀስ ይግባኙ ቀርቧል። ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ “ማስረጃ ጠፍቷል” ተብሎ የተሰራጨው መረጃ ግን ፍጹም ከእውነት የራቀ መሆኑን የዓቃቤ ሕግ ፅህፈት ቤቱ ኃላፊ ገልጸዋል። በተጨማሪም፣ ከዘውዱ ሃፍቱ ግድያ ጋር በተያያዘ የተከሰሱት ሁለቱ ግለሰቦች በአሁኑ ወቅት በመቐለ ከተማ መኖራቸውንም ሆነ አለመኖራቸውን እንደማያውቁ አስታውቋል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ መቐለ ነሐሴ 8 ቀን 2018 ዓ/ም @tikvahethiopia
без подписи
" የዘውዱ ገዳዮች በነጻ መሰናበታቸው 'ዘውዱን ለሁለተኛ ጊዜ እንደመግደል ነው' " - ዘጠኝ ማኅበራት የ32 ዓመቷ ዘውዱ ሃፍቱን በመግደል የዕድሜ ልክ እስራት የተፈረደባቸው ያሬድ ገብረስላሴ በላይ እና አንገሶም ሃይለማርያም በነፃ መለቀቃቸውን ተከትሎ 9 የሴቶች መብት እና የፍትሕ ጉዳይ ላይ ሚሰሩ ሲቪል ማኅበራት ተቃውሞ አሰምተዋል። ዘውዱ ነሐሴ 2015 ዓ/ም በመቐለ ከተማ ከጓደኛዋ ሰምሃል ገብረዝያብሔር ጋር በመንገድ ላይ ሳለች አንድ ተሽከርካሪ አጠገባቸው ይደርሳል። ዘውዱ ተሽከርካሪው ውስጥ ካሉ ሰዎች ጾታዊ ጥቃት ይፈጸምባታል። ይህን ድርጊት ለመቃወም ብትሞክርም ሊለቋት ፈቃደኛ አልሆኑም። በኋላም በያዙት ተሽከርካሪ ገጭተው ገድለዋታል። በዚህ ጉዳይ ያሬድ ገብረስላሴ በላይ እና አንገሶም ሃይለማርያም ዘውዱ ሃፍቱ ላይ ግድያ ፈጽመዋል በሚል ሐምሌ 11 ቀን 2017 ዓ.ም. የመቐለ ማዕከላዊ ፍ/ቤት የዕድሜ ልክ እስራት ፈርዶባቸው ነበር። የትግራይ ጠቅላይ ፍርድ ቤትም ጉዳዩን በይግባኝ መርምሮ የመጀመሪያውን የጥፋተኝነት ውሳኔ ማጽናቱ ተገልጿል። የማኅብራቱ የጋራ መግለጫ እንደሚጠቅሰው፣ ያሬድ ገብረስላሴ በላይ ሙሉብርሃን መኮንን ወለገርስ የተባለች ሌላ ወጣት ሴትን በመግደልም ተከሷል ፤ በእሱ ላይ የቀረቡትን ክሶችም ሙሉ በሙሉ አምኖ ተቀብሏል። አሁን ከዘውዱ ሀፍቱ ግድያ ጋር በተያያዘ ሁለቱም ፍርደኞች ላይ የተላለፈው የእድሜ ልክ እስራት የጥፋተኝነት ውሳኔ ለመለወጥ የሚያስችል አዲስ ማስረጃ ሳይቀርብ በነፃ መለቀቃቸው ቁጣ ቀስቅሷል። ማኅበራቱ፣ " የዘውዱ ሃፍቱ ገዳዮች በነፃ መሰናበታቸው እሷን ለሁለተኛ ጊዜ እንደመግደል ነው " ብለዋል። እንዴት ነጻ ተባሉ ? ጉዳዩ ወደ ሰበር ሰሚ ችሎት ሲደርስ፣ ሁለቱ ተከሳሾች ላይ ለመፍረድ ጥቅም ላይ የዋለው ዋናው ኦሪጅናል የስልክ ማስረጃ ከይግባኝ መዝገቡ ውስጥ መጥፋቱ ታወቀ። ሰበር ሰሚ ችሎቱም በዚህ ምክንያት ጉዳዩን ወደ ቀድሞው ታችኛው ፍርድ ቤት በመመለስ፣ የመጀመሪያው ማስረጃ በትክክል እንዲቀርብና ብቃት ያለው ባለሙያ ማስረጃውን እንዲያብራራ ትዕዛዝ ሰጥቶ ነበር። ሆኖም ይህ ትዕዛዝ ሳይፈጸም 5 ወራት እና ቢያንስ 8 ችሎቶች ማለፋቸውን መግለጫው ያስረዳል። በዚህ ወቅት የትግራይ ፖሊስ ኮሚሽን ትዕዛዙ እንደደረሰው ለፍርድ ቤቱ ቢያሳውቅም ትዕዛዙን ለመፈጸም የሚያስፈልገው ማስረጃ አልቀረበም ተብሏል። በኋላ በመጀመሪያው ማስረጃ ምትክ የተቃኘ ቅጂ ቀርቦ እንደነበር፤ የዐቃቤ ሕጉም ቢሮ በተመሳሳይ የራሱን ቅጂ እንዳቀረበ ተገልጿል። የፌዴራል ባለሙያ በመጠቀም ማስረጃውን እንዲያስረዳ በቀረበው ጥያቄ ምትክ በትግራይ ክልል ባለሙያ ተቀይሯል ተብሏል። ሐምሌ 20 ቀን 2018 ዓ.ም. የፖሊስ መኮንን በጽሑፍ ማስረጃው ላይ ማብራሪያ ሰጥቷል። ከ9 ቀናት በኋላም ፍርድ ቤቱ ይህንን ማብራሪያ በቂ ነው በማለት ሁለቱን ተከሳሾች በነፃ እንዲሰናበቱ ወስኗል። የትግራይ ፖሊስ እና የአንደኛው ፍርደኛ አባት ላይ የተነሳው ጥያቄ ምንድነው ? የጋራ መግለጫው የማስረጃው መጥፋትና ለ5 ወራት ሳይቀርብ መቆየት ከትግራይ ፖሊስ ኮሚሽን ጣልቃ ገብነት ጋር በቀጥታ ያያይዛል። በወቅቱ የትግራይ ፖሊስ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ሆነው ያገለገሉት ኮሎኔል ገብረስላሴ በላይ (አሁንም የትግራይ ኃይል አመራር ናቸው) የመጀመሪያው ፍርደኛ ያሬድ ገብረስላሴ በላይ አባት መሆናቸውን ማኅበራቱ ጠቅሰዋል። በግንቦት 2016 ዓ.ም. የፖሊስ መርማሪዎች ፍርድ ቤት " ይፈታ " ያለውን አንድ ተጠርጣሪ ከእስር እንዳይለቀቅ ያቀረቡትን ይግባኝ በተመለከተ፣ ኮሎኔል ገብረስላሴ ይግባኙን እንደጥፋት ለመቁጠር የጉዳዩን ኃላፊ ፖሊስ መኮንን በስልክ " አስፈራርተዋል " የሚል ቅሬታ ቀርቦ ነበር። የጉዳዩ የሚመለከተው የፖሊስ ክፍልም በወቅቱ በጽሑፍ ቅሬታ ማቅረቡ ተገልጿል። ይህ ክስተት በዘውዱ ጉዳይ ላይ የሥልጣን ጣልቃ ገብነት ጥያቄ እንዲነሳ አድርጓል። ከዚህ በተጨማሪ ... ተቋማቱ የዘውዱ ግድያ ብቸኛዋ የዓይን ምስክር ሰምሃል ገብረዝያብሔር ለ8 ወራት ያለ ክስ በእስር መቆየቷን ጠቅሰዋል። እንዲሁም ግንቦት ወር 2017 ላይ ከደህንነት ስጋት ጋር በተያያዘ የመቐለ ማእከላይ ፍርድ ቤት ጨምሮ በሰባቱ ክፍለ ከተሞች የሚገኙ ዳኞችና ፍርድ ቤቶች ማንኛውም የዳኝነት አገልግሎት ከመስጠት ተቆጥበው/ስራ አቁመውም ነበር። የጋራ መግለጫውን ያወጡት ዘጠኝ ማኅበራት ምን ጠየቁ ? - በነጻ እንዲሰናበቱ በተባለው ውሳኔ ላይ በአስቸኳይ ይግባኝ እንዲባል፤ - የመጀመሪያው የስልክ ማስረጃ (ከNISS የመጣው) እና ሰበር ሰሚ ችሎቱ የጠየቀው ብቃት ያለው የፌዴራል ባለሙያ በሙሉ እንዲቀርቡ፤ - ኮሎኔል ገብረስላሴ በጥቅም ግጭት ምክንያት ከኃላፊነታቸው እንዲነሱ እና በተቋማቸው የተፈጸመው የአምስት ወራት መዘግየትና በግንቦት 2016 ዓ/ም የተነሳው የጣልቃ ገብነት ክስ በነፃ አካል እንዲጣራ፤ - በግንቦት 2017 ዓ/ም በፍርድ ቤት ላይ የተፈጠረው መስተጓጎልና በዚያ ምክንያት የተፈጠረው የፍርድ አገልግሎት መቋረጥ በተመለከተ ተጠያቂነት እንዲሰፍን፤ - ሰምሃል ገብረዝያብሔርና ብርቱካን ሃፍቱ፣ እንዲሁም ፍርድ ያስተላለፉ ሁሉም ዳኞች፣ ዐቃቤ ሕጎችና መርማሪዎች የጽሑፍ እና ተፈጻሚ የሆነ የጥበቃ ዋስትና እንዲያገኙ፤ - UN Women እና የተመድ የሴቶችና ሴት ልጆች ላይ የሚፈጸም ጥቃት ልዩ ሪፖርተር ስለዚህ ውሳኔ መቀልበስ ሕዝባዊ ማብራሪያ እንዲሰጡ ጠይቀዋል። (መግለጫውን ያወጡ 9 ማኅበራት ዝርዝር ከላይ ተመልከቱ) ቲክቫህ ኢትዮጵያ ነሐሴ 8 ቀን 2018 ዓ/ም @tikvahethiopia

📌አዲሱ የጉምሩክ አዋጅ ማሻሻያ ቁጥር 1425/2018 📌New _ Customs Amendment Proclamation No. 1425/2026 📌This New Proclamation is Effective from July 23, 2026
የምክክር ኮሚሽኑ የተመሰረተበት ዋና አላማ የሆነው አጀንዳ ፀደቀ‼🙄🙄 ኢትዮጵያ በፕሬዚዳንት እንድትመራ ተመካካሪዎች ሙሉ በሙሉ መግባባት መደረሳቸው ታውቋል። ኢትዮጵያ በጠ/ሚኒስትር ቀርቶ በፕሬዚዳንት እንድትመራ፣ የመንግሥት አደረጃጀትና ቅርጽ፣ እንዲሁም የፖለቲካ ሥርዓት፣ የፖለቲካ ውክልናና የምርጫ ሥርዓት አጀንዳ ላይ የ500 ቡድን ተመካካሪዎች ሙሉ በሙሉ ተሰምቷል። በዚሁ አጀንዳ ላይ ተወያይ የነበሩ ተመካካሪዎች ለሪፖርተር በሰጡት አስተያየት፣ በቀረቡት አብዛኞቹ ምክረሐሳቦች መግባባት ላይ መደረሱን ሆኖም ያላግባቡና ወደ ቀጣይ የተሻገሩ ጉዳዮች መኖራቸውንም ገልጸዋል። በዚህም የ500 ቡድን ተመካካሪዎች የአገሪቱ አስተዳደር ሥርዓት ፓርላሜንታሪ ሆኖ እንዲቀጥል፣ የአገሪቱ መሪ ፕሬዚዳንት እንዲሆን፣ አዲሱ ተመራጭ ፕሬዚዳንትም የጠቅላይ ሚኒስትሩና የፕሬዚዳንቱ ሥልጣንና ተግባርን ጠቅልሎ እንዲወጣ በምክረሐሳብ ደረጃ ከመግባባት ላይ መደረሱን፣ ይህም ጠቅላይ ሚኒስትር እንዲቀር የሚያደርግ መሆኑን ተናግረዋል። የአገሪቱ መሪ የሥልጣን ዘመን 6 ዓመት ሆኖ ለሁለት ዙር እንዲደረግ፣ የክልል መሪዎችም ከፌዴራሉ ጋር ተመሳሳይ እንዲሆን በምክረሐሳብ ደረጃ ከመግባባት ላይ መደረሱን ገልጸዋል። የሕገመንግሥት ጉዳዮች ተርጓሚ ፍርድ ቤት እንዲቋቋም፣ አሁን ያለው የፌዴሬሽን ምክር ቤት አሠራር ያልመለሳቸው የማንነትና የራስን በራስ የማስተዳደር ጥያቄዎች “ሕብረ ብሔራዊ አንድነት ኮሚሽን" የሚል ሥያሜ ያለው ገለልተኛ ተቋም በአስቸኳይ ተቋቁሞ በአጭር ጊዜ ውስጥ ምላሽ እንዲሰጥባቸው ለዚህም ይረዳ ዘንድ ልዩ የባለሙያዎች ቡድን እንዲቋቋም በምክረሐሳብ ደረጃ ከመግባባት ላይ ተደርሷል። ምንጭ - አዲስ ኢንይደር
የክፍት ሥራ ቦታ ማስታወቂያ ማስተካከያ **** የፍትህ ሚኒስቴር በሀምሌ 17 ቀን 2018 ዓ.ም ባወጣው ክፍት የሥራ ማስታወቂያ ላይ የተቀመጡት የመግቢያ መስፈርቶች ማስተካከያ ተደርጎባቸዋል። በዚሁ መሠረት የሚፈለገው ውጤት፦ የፐርሰንታይል (Percentile) መስፈርት፡ ለወንድ አመልካቾች 88 እና ከዚያ በላይ | ለሴት አመልካቾች 86 እና ከዚያ በላይ የአካዳሚክ ውጤት (CGPA) መስፈርት፡ ለወንድ አመልካቾች 3.6 እና ከዚያ በላይ | ለሴት አመልካቾች 3.25 እና ከዚያ በላይ ተደርገው የተሻሻሉ መሆኑን እየገለጽን፤ ተወዳዳሪዎች ይህንኑ አውቃችሁ ማመልከት የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን። የፍትሕ ሚኒስቴርን የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገፆችን እና ድረ-ገፅን ይቀላቀሉ Website https://www.justice.gov.et Facebook https://web.facebook.com/MOJEthiopia/ (x) Twitter https://x.com/MOJEthiopia YouTube channel https://youtube.com/@fdreministryofjustice...3701... Telegram https://t.me/fdreattorneyGeneral_external Join https://t.me/lex_ethiopia
የፌዴራል ሕግና ፍትሕ ኢንስቲትዩት በኢትዮጵያ፣ ፈረንሳይ እና ጀርመን ያለውን የተፋጠነ የወንጀል ፍትሕ ሂደት (RTD) የሚያነፃፅር ጥናት ይፋ አደረገ። ጥናቱ በተመረጡት ሀገራት ያለውን የሕግ ማዕቀፍ፣ የተጠርጣሪዎች ማቆያ ጊዜ እና የጠበቃ የማግኘት መብት አሰራር በዝርዝር ዳስሷል። ተጠርጣሪው በ48 ሰዓት ውስጥ በቁጥጥር ስር ሆኖ ጉዳዩ መታየት አለበት፤ ዋናው ችሎት ካላየው ወዲያው ይፈታል። ጀርመን፦ አቃቤ ሕግ ልዩ ውሳኔ ሳይጠብቅ ጉዳዩን በቅርብ በሚገኝ ችሎት ወዲያው ያቀርባል። በፌዴራል እና በኦሮሚያ ክልል መደበኛው የ48 ሰዓት ገደብ የሚተገበር ሲሆን፣ በአማራ ክልል በስምምነት ሰነድ (MoU) እስከ 72 ሰዓት የማቆየት አሰራር ይታያል። በፍጥነት በሚደረግ የፍርድ ሂደት ላይ ተከሳሹ በግዴታ ጠበቃ የማቆም ወይም በመንግሥት የመመደብ መብት አለው፤ ያለ ጠበቃ ሂደቱ አይቀጥልም። ጉዳዩ ከ6 ወር በላይ የሚያስቀጣ ከሆነ ጠበቃ በግዴታ ይመደብለታል። የተፋጠነ ፍትሕ ማለት ቅድመ-መዝገብ ምርመራን ማጥፋት ሳይሆን አላስፈላጊ ውጣ ውረዶችን በማስወገድ ሂደቱን ማፋጠን መሆኑን ጥናቱ አመላክቷል። ኢንስቲትዩቱ ይህንን ጨምሮ በአምስት አበይት ርዕሶች ላይ ያዘጋጃቸውን ጥናቶች ሐምሌ 30 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ በድሪም ላይነር ሆቴል ለባለድርሻ አካላት አቅርቦ ግብዓት እና ማረጋገጫ (validation) ሰብቧል። https://www.facebook.com/share/1FHmTCUepy/

#የምትክ ዳኛ ዋና ተግባራት እና ስልጣናት #በኢትዮጵያ የፍትሐብሔር ሥነ-ሥርዓት ሕግ ቁጥር 124፣ 125፣ 132-134 ድንጋጌዎች መሠረት፣ የምትክ ዳኛ (Commissioner) ዋና የሥልጣን ክልል ፍርድ ቤቱ የክርክሩን ፍሬ ነገር በበለጠ ሁኔታ ለማጣራት እንዲችል እውነታውን የማረጋገጥ እና መረጃዎችን የማሰባሰብ ተግባር ላይ ያተኩራል (ሰ/መ/ቁ. 222624)። ምትክ ዳኛው በፍርድ ቤት የሚሰጠውን የውክልና ሥልጣን መሠረት በማድረግ የቀረበለትን ጉዳይ በዝርዝር ለማጣራት የሚያስችሉ ሰፊ ሥልጣኖች የተሰጡት ሲሆን፣ በሹመት ትእዛዙ ላይ በግልጽ ሌላ መመሪያ ካልተሰጠ በስተቀር ተከራካሪ ወገኖችንና እነርሱ የሚያቀርቧቸውን ምስክሮች የመመርመር ሥልጣን አለው (ፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ. 124)። #ከዚህም በተጨማሪ ስለ ጉዳዩ በቂ ማስረጃ ሊሰጡ ይችላሉ ብሎ የሚያስባቸውንና ተገቢ ናቸው ያላቸውን ማናቸውንም ሌሎች ሰዎች ጠርቶ የመመርመር መብት የተሰጠው ሲሆን (ፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ. 124)፣ እነዚህን ተግባራት በሚያከናውንበት ወቅት እንደ ፍትሐብሔር ፍርድ ቤት ተቆጥሮ ምስክሮችን የመጥራት፣ የመመርመርና አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝም ምስክሮች ላይ ቅጣት የመጣል ሥልጣን ይኖረዋል (ፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ. 125)። ተግባሩን በሚያከናውንበት ወቅት ማንኛውም ወገን ባይገኝ እንኳ ምርመራውን ከማከናወን አይገደብም፤ #የምትክ ዳኛው ዋነኛ ተግባር ክርክር የተነሳበት ቦታ ድረስ በአካል በመሄድ ተጨባጭ ሁኔታዎችን ማረጋገጥ (On-site Investigation) ሲሆን በተለይም በሁከት ይወገድልኝ ክርክሮች ወቅት ሁከቱ ተፈጠረ በተባለበት ወቅት ይዞታው በተጨባጭ በማን እጅ እንደነበረ እና ማን ይገለገልበት እንደነበር የማጣራት ሥልጣን አለው (ሰ/መ/ቁ. 225158፣ ሰ/መ/ቁ. 216142)። #በመሬት ላይ ያሉ ንብረቶችን ለምሳሌ መኖሪያ ቤት፣ እንደ ቡና፣ እንሰትና ጫት ያሉ ቋሚ ተክሎች መኖራቸውን እና ሁኔታቸውን በአካል አይቶ የማረጋገጥ ኃላፊነት ያለበት ሲሆን (ሰ/መ/ቁ. 234426)፣ በንብረት ላይ የተደረጉ ግንባታዎች መሰረታዊ ለውጥ አምጥተዋል ወይስ አላመጡም የሚሉ በዕይታ የሚረጋገጡ ነጥቦችን ለፍርድ ቤቱ ሪፖርት ያደርጋል (ሰ/መ/ቁ. 160483)። #ከሰው ምስክርነት ባሻገር ለምርመራውና ለቀረበው አቤቱታ አስፈላጊ የሆኑ ሰነዶችንና ሌሎች ተጨባጭ ማስረጃዎች እንዲቀርቡለት የመጠየቅ፣ የማስቀረብና የመመርመር ሥልጣን ያለው ሲሆን፣ ምርመራውን ይበልጥ ውጤታማ ለማድረግ በፍርድ ቤት ትእዛዝ ውስጥ የተጠቀሱ ማናቸውንም መሬቶች ወይም ሕንፃዎች ውስጥ በማንኛውም ተገቢ ሰዓት የመግባትና የመመልከት ሥልጣን ተሰጥቶታል (ፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ. 124)። #ውስብስብ የሆኑና የባለሙያ እገዛ የሚፈልጉ የድንበር መገፋፋት ክርክሮች ሲያጋጥሙ ምትክ ዳኛው ከከተማ ወይም ከመሬት አስተዳደር ባለሙያዎች ወይም ከሌሎች ልዩ አዋቂዎች ጋር በመሆን ልኬቱ በትክክል መከናወኑን ይከታተላል (ሰ/መ/ቁ. 231800)። የባለሙያውን የማጣራት ሂደት በቦታው ተገኝቶ መታዘቡና ሪፖርት ማቅረቡ ለፍርድ ቤቱ የባለሙያውን ግኝት ትክክለኛነት ለማረጋገጥ የሚረዳ ሲሆን (ሰ/መ/ቁ. 185699)፣ እንደ XY ኮርዲኔት ያሉ ቴክኒካዊ መረጃዎችን በማካተት የትኛው ወገን የተሟላ ካርታ እንዳለው ለማረጋገጥ የባለሙያዎችን ቡድን የማስተባበርና የመምራት ሥልጣን አለው (ሰ/መ/ቁ. 231800፣ ሰ/መ/ቁ. 192327)። እንደ የስራ ቦታ አደጋ ወይም የጥራት ጉድለት ያሉ ቴክኒካዊ ጉዳዮችን ከቦታው በመገኘትና ባለሙያዎችን በማነጋገር መረጃ የመሰብሰብ ሥልጣን ያለው ሲሆን (ሰ/መ/ቁ. 165486)፣ ጉዳዩ እጅግ ውስብስብ ሲሆን ፍርድ ቤቱ ከተለያዩ የመንግስት መስሪያ ቤቶች የተውጣጡ ባለሙያዎችን ያካተተ የምትክ ዳኛ ቡድን በማቋቋም ጥልቅ ምርመራ እንዲካሄድ ሊያዝ ይችላል (ሰ/መ/ቁ. 224858)። በተጨማሪም ከአካባቢው ሽማግሌዎችና ከአስተዳደር አካላት ጋር በመሆን ፍሬ ነገሩ በተሟላ ሁኔታ እንዲጣራ የማድረግ ሥልጣን ተሰጥቶታል (ሰ/መ/ቁ. 166111)። #በፍርድ አፈጻጸም ወቅትም የምትክ ዳኛው ሚና ወሳኝ ሲሆን፣ ንብረቱ ለሚገባው ወገን በህጋዊ መንገድ መተላለፉን ለማረጋገጥ በቦታው ይገኛል፤ ይህም ድርጊቱ ሁከት ሳይሆን ህጋዊ አፈጻጸም መሆኑን ለማስረዳት ይጠቅማል (ሰ/መ/ቁ. 227151)። በአፈጻጸም ወቅት ንብረቱ ፈርሷል ወይም የለም የሚሉ ተቃውሞዎች ሲነሱ እውነታውን አጣርቶ ሪፖርት ያቀርባል (ሰ/መ/ቁ. 184738)። ምትክ ዳኛው ማጣራቱን ካከናወነ በኋላ ውጤቱን ለፍርድ ቤቱ በጽሑፍ ያቀርባል፤ ይህ ሪፖርት ፍርድ ቤቱ ውሳኔ ለመስጠት እንደ ዋና የማስረጃ አካል ሆኖ ያገለግላል (ሰ/መ/ቁ. 133479፣ ሰ/መ/ቁ. 180950)። ይሁን እንጂ ምትክ ዳኛው ሰፊ የማጣራት ሥልጣን ቢኖረውም የፍርድ ቤቱን የዳኝነት ሥልጣን ሙሉ በሙሉ ሊተካ አይችልም (ሰ/መ/ቁ. 155771)። ፍርድ ቤቱ በምትክ ዳኛው ሪፖርት ላይ ብቻ ተመስርቶ የግራ ቀኙን ሌሎች ማስረጃዎች ለምሳሌ የሰው ምስክሮችን ሳይሰማ ውሳኔ መስጠት አይችልም (ሰ/መ/ቁ. 226330፣ ሰ/መ/ቁ. 155771)። #ፍርድ ቤቱ የምትክ ዳኛውን ሪፖርት የመመዘን እና የተቀበለበትን ወይም ውድቅ ያደረገበትን ምክንያት በውሳኔው ሐተታ ላይ በዝርዝር የመተንተን ግዴታ አለበት፤ ዝም ብሎ በምትክ ዳኛ ተጣርቷል ማለት ብቻ መሰረታዊ የሥነ-ሥርዓት ስህተት በመሆኑ ለውሳኔ መሻር ምክንያት ይሆናል (ሰ/መ/ቁ. 181232)። #በተጨማሪም የምትክ ዳኛው መኖሩ ተከራካሪዎች ማስረጃ የማቅረብ ግዴታቸውን አያስቀረውም (ሰ/መ/ቁ. 222624)። በአጠቃላይ የምትክ ዳኛው ተግባር ፍርድ ቤቱ በቦታው ተገኝቶ ሊያያቸው የማይችላቸውን ፍሬ ነገሮች በማጣራት ለፍትሃዊ ውሳኔ አስፈላጊ የሆኑ መረጃዎችን ማቅረብ ቢሆንም፣ የመጨረሻውን የማስረጃ ምዘና እና የዳኝነት ስራ የመስራት ሥልጣን ግን የፍርድ ቤቱ ብቻ ነው (ሰ/መ/ቁ. 155771)።
የክልሉ ፍርድ ቤቶች ከነሐሴ 01/ 2018 ዓ.ም እስከ መስከረም 30/2019 ዓ.ም ድረስ በከፊል ዝግ ይሆናሉ ባሕርዳር ፣ ሐምሌ 27/2018 (የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት) በተሻሻለው የዳኞች አስተዳደር ጉባኤ አዋጅ ቁጥር 282/2014 መሰረት ከነሐሴ 01 እስከ መስከረም 30 የክልሉ ፍርድ ቤቶች ዳኞች መደበኛ የረፍት ጊዜ መሆኑ ይታወቃል። በመሆኑም የክልሉ ፍርድ ቤቶች ከነሐሴ 01/2018 እስከ መስከረም 30/2019 ዓ.ም በከፊል ዝግ ሆነው የሚቆዩ ሲሆን፣ በቀጣዮቹ ሁለት ወራቶች ውስጥ በፍርድ ቤቶቻችን የሚስተናገዱ ጉዳዮችን ከስር በተያያዘው ደብዳቤ ይመልከቱ 👇
ጋዜጠኛ ተክለሃይማኖት አዳነ ታሰረ። የ"እግረኛው ሚዲያ" መስራችና ባለቤት የሆነው ጋዜጠኛ ተክለሃይማኖት አዳነ በቁጥጥር ስር መዋሉ ተሰምቷል። ጋዜጠኛው በቁጥጥር ስር የዋለው በትናንትናው ዕለት ሐምሌ 23 ቀን 2018 ዓ.ም እንደሆነ የታወቀ ሲሆን፤ ለእስሩ ምክንያት ከመከላከያ ሰራዊት አልባሳት (ዩኒፎርም) ጋር ተያይዞ ከቀረበው ዘገባ ጋር ሳይያያዝ እንዳልቀረ ምንጮቹ ጠቁመዋል። ጉርሻ page @Addis_Reporter @Addis_Reporter
ወይም የኢሰብዓዊ ድብደባ ድርጊቶችን በፈፀሙ ሰዎች ላይ ክስ ማቅረብ በይርጋ አይታገድም። ማጠቃለያ የወንጀል ክስ በአንድ በኩል ተጎጂዎች ፍትሕ የሚያገኙበት የሕግ ሂደት ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ በወንጀል የተጠረጠሩ ወይንም የተከሰሱ ግለሰቦች ነፃነት በሕግ የሚገደብበት ነው። በዚሁ መሠረት የወንጀል ክስ መመስረቻ ጊዜ ገደብ በሕግ ወስኖ ማስቀመት በሁለቱ ተፃራሪ መብቶች መካከል ሚዛን ለመጠበቅ የሚያስችል ነው። ስለሆነም ማንኛውም ክስ በሕግ በተቀመጠው ጊዜ ውስጥ ሊቀርብ ይገባል፡፡ በንቃተ ሕግና ሥልጠና ዳይሬክቶሬት የተዘጋጀ
የወንጀል ክስ ይርጋ በኢትዮጵያ ******** መግቢያ ወንጀል ፈፃሚዎች ለፈፀሙት ጥፋት በሕግ ፊት መጠየቃቸውና ተገቢውን ቅጣት መቀበላቸው ተገቢና አስፈላጊም ነው፡፡ ይህም በኢትዮጵያ የወንጀል ሕግ አንቀጽ አንድ እንደተመለከተው በወንጀል ሕጉ መሰረት ወንጀል የተደረጉ ድርጊቶች እና የሚያስከትሉትን ቅጣት በመደንገግ ሰዎች ወንጀል ከመፈፀም እንዲቆጠቡ አሰቀድሞ ቅድመ-ማስጠንቀቂያ የሚሰጥ ቢሆንም ቅድመ-ማስጠንቀቂዎች በቂ ባልሆኑ ጊዜ ወንጀል ፈፃሚዎች ተቀጥተው ሌላ ወንጀል ከመፈፀም እንዲታቀቡና ለሌሎችም ማስተማሪያ እንዲሆኑ ማድረግን ግቡ ያደረገ ነው፡፡ ይህ እንዲሆን ግን በወንጀል ሕጉ በተመለከተው የጊዜ ገደብ ውስጥ ክስ ሊመሠረት እና አጥፊዎችን ለሕግ ማቅረብ የሚገባ ሲሆን ይህ ካልሆነ ግን ክሱ በይርጋ የሚታገድ ይሆናል፡፡ በዚህ አጭር ጽሑፍ የወንጀል ክስ ይርጋን ምንነት፣ በሕግ የተመለከተውን የክስ ይርጋ ዘመን እናአቆጣጠር እንዲሁም የክስ ይርጋ ዘመን መቋረጥና መታገድ በአጭሩ እንመለከታለን፡፡ የወንጀል ክስ ይርጋ ምንነት የወንጀል ሕጉ የወንጀል ክስ ይርጋን ምንነት በተመለከተ ቀጥተኛ ትርጓሜ ባይሰጥም ከወንጀል ሕግ አንቀጽ 217 በመነሳት የወንጀል ክስ ይርጋ ማለት በማናቸውም ወንጀል ጉዳይ በግል አቤቱታ ወይም በወንጀል ክስ አቅራቢነት ጉዳዩ በዳኝነት ከመታየት የሚታገድበት በሕግ የተመለከተ ጊዜ መሆኑን መረዳት ይቻላል፡፡ የመደበኛ ክስ ይርጋ የወንጀል ሕጉ አንቀጽ 217 መደበኛ የክስ ማቅረቢያ ጊዜን የደነገገ ሲሆን • የሞት ፍርድ ወይም የዕድሜ ልክ ጽኑ እስራት ለሚያስቀጣ ወንጀል በሃያ አምስት ዓመት • ከአስር ዓመት በላይ እስከ ሃያ አምስት ዓመት ለመድረስ የሚችሉ ጽኑ እስራት ለሚያስቀጣ ወንጀል በሃያ አመት • ከአምስት ዓመት በላይ እስከ አስር ዓመት ለመድረስ የሚችል ጽኑ እስራት ለሚያስቀጣ ወንጀል በአስራ አምስት አመት • ከአምስት አመት በማይበልጥ ጽኑ እስራት ለሚያስቀጣ ወንጀል በአስር ዓመት • ከአንድ ዓመት በላይ በቀላል እስራት ለሚያስቀጣ ወንጀል በአምስት ዓመት • እስከ አንድ ዓመት ቀላል እስራት ለሚያስቀጣ ወይም በመቀጮ ብቻ ለሚያስቀጣ ወንጀል በሦስት ዓመት ውስጥ ክስ ካልቀረበ ክሱ በይርጋ ይታገዳል፡፡ ከዚህ ጋር በተያያዘ ተደራራቢ ወንጀሎች ተፈጽመው ሲገኙ የወንጀሎቹ ከፍተኛ ቅጣቶች ተመሳሳይ በሚሆኑበት ጊዜ የአንዱ ወንጀል የክስ ማቅረብያ የይርጋ ዘመን በሁለቱም ወንጀሎች ላይ ተፈፃሚ እንደሚሆንና የወንጀሎቹ ከፍተኛ ቅጣቶች የተለያዩ በሚሆንበት ጊዜ ደግሞ ከሁሉም ከባድ የሆነው ወንጀል የክስ ማቅረቢያ የይርጋ ዘመን በሌሎች ወንጀሎች ላይ ተፈፃሚ እንደሚሆን የወንጀል ሕጉ አንቀጽ 217(2) ይደነግጋል፡፡ በግል አቤቱታ አቅራቢነት የሚያስቀጡ ወንጀሎች ይርጋ በወንጀል ሕጉ ልዩ ክፍል ወይም በሌላ ማሟያ የወንጀል ሕግ በግል አቤቱታ አቅራቢነት ብቻ እንደሚያስቀጡ የተደነገጉ ወንጀሎች የግል ተበዳዩ ወይም ሕጋዊ ወኪሉ የግል አቤቱታ ካላቀረበ በስተቀር ክስ እንደማይመሰረት በወንጀል ሕጉ አንቀጽ 212 ተደንግጓል ፡፡ ለአንብነትም በወንጀል ሕጉ አንቀጽ 560 የእጅ እልፊት ወንጀል በግል አቤቱታ ሲቀርብ የሚስቀጣ ወንጀል መሆኑ ተደንግጓል፡፡ መሰል በግል አቤቱታ የሚቀርቡ ወንጀሎች የተፈፀመበት የግል ተበዳይ በወንጀል ሕጉ አንቀጽ 213 መሠረት አቤቱታውን ማቅረብ የሚጠበቅበት ሲሆን የእነዚህ በግል አቤቱታ አቅራቢነት ብቻ የሚያስቀጡ ወንጀሎች የክስ ይርጋ ዘመን ሁለት አመት እንደሆነ በወንጀል ሕጉ አንቀጽ 218 ተደንግጓል፡፡ ፍፁም የሆነ የይርጋ ዘመን በወንጀል ሕጉ አንቀጽ 222 ፍፁም የሆነ የይርጋ ዘመን የተደነገገ ሲሆን በማናቸውም ምክንያት ከላይ የተመለከትነው መደበኛ የክስ ማቅረቢያ የይርጋ ዘመን እጥፍ ጊዜ ካለፈ ወይም በግል አቤቱታ የሚያስቀጡ ወንጀሎች ሲሆኑ ደግሞ ከላይ ከተመለከትነው በግል አቤቱታ የሚያስቀጡ ወንጀሎችን የይርጋ ዘመን በግማሽ የሚበልጥ ጊዜ ካለፈ በወንጀሎቹ ላይ የሚቀርብ ክስ በይርጋ ቀሪ ይሆናል፡፡ የክስ ይርጋ አቆጣጠር በወንጀል ሕጉ አንቀጽ 219 መሠረት የክስ የይርጋ ዘመን የሚታሰበው የቅጣት ማክበጃ ወይም ማቅለያ ሁኔታዎች ግምት ውስጥ ሳይገቡ በወንጀል ሕግ ልዩ ክፍል የተደነገገውን ከፍተኛ ቅጣት መሠረት በማድረግ ሲሆን የተፈፀመው ወንጀል በተለዋጭ ወይም በተደራራቢ ተፈፃሚነት በሚኖራቸውም ቅጣቶች የሚያስቀጣ ሲሆን የይርጋ ዘመኑ የሚታሰበው ከሁሉም ከባድ ለሆነው ወንጀል በወንጀል ሕግ ልዩ ክፍል የተደነገገውን ከፍተኛ ቅጣት መሠረት በማድረግ ይሆናል፡፡ የይርጋ ዘመኑ መቆጠር የሚጀምረውም ጥፋተኛው የወንጀል ድርጊቱን ከፈጸመበት ቀን አንስቶ ሲሆን የወንጀል ድርጊቱ እየተደጋገመ የተፈፀመ ከሆነም የይርጋ ዘመኑ መቆጠር የሚጀምረው የመጨረሻው የወንጀል ድርጊት ከተፈፀመበት ቀን አንስቶ ነው፡፡ የወንጀል ድርጊቱ ለረጅም ጊዜ ሲፈፀም የቆየ ከሆነ ደግሞ የይርጋ ዘመኑ መቆጠር የሚጀምረው የወንጀል ድርጊቱ ካቆመበት ቀን ጀምሮ ይሆናል፡፡ የክስ ይርጋ መታገድ የወንጀል ሕጉ አንቀጽ 220 የወንጀል ክስ ይርጋ የሚታገድበትን ሁኔታ የደነገገ ሲሆን ይኸውም በሕግ ወይም በፍሬ ነገር ክሱ እንዳይጀመር ወይም እንዳይቀጥል የሚያግድ መሰናክል ካለ መሰናክሉ እስካለ ድረስ ክስ ቀርቦ ነገሩ በዳኝነት በመታየት ላይ ከሆነ ወይም በሌላ ችሎት የቀረበ ክስ ሳይፈፀም ተከሳሹ በተከሰሰበት የወንጀል ክስ ላይ ውሳኔ ሊሰጥ የማይገባ በሆነ ጊዜ የይርጋ ዘመኑ ታግዶ ይቆያል፡፡ መታገዱን ያስከተለው መሰናክል ሲወገድ ግን የይርጋ ዘመኑ ወዲያውኑ መቆጠር ይጀምራል፡፡ የይርጋ ዘመን መቋረጥ የወንጀል ሕጉ አንቀጽ 221 እንደሚያመለክተው ከወንጀሉ ወይም ከወንጀለኞቹ ጋር በተያያዘ ሁኔታ ምርመራ እንዲካሄድ፣ ብርበራ እንዲደረግ፣ መጥሪያ እንዲሰጥ ወይም ክስ እንዲቀርብ የሚሰጥ ትዕዛዝ፣ የሚፈፀም ድርጊት ወይም የሚሰጥ ውሳኔ የይርጋ ዘመኑን መቆጠር ያቋርጣል፡፡ ይህ በሚሆንበት ጊዜ ሁሉ የይርጋ ዘመን እንደገና እንደ አዲስ መቆጠር ይጀምራል፡፡ በድንጋጌው መሠረት የይርጋ ዘመኑ መቋረጥ ፍፁም የሆነ ውጤት የሚኖረው ሲሆን በወንጀሉ ተካፋይ መሆናቸው ለታወቀውም ሆነ ላልታወቀው ሁሉ መቋረጡ ይፀናባቸዋል፡፡ ይህ ማለት የወንጀል ተካፋይ መሆናቸው ወንጀሉ በተከሰተበት ጊዜ ያልታወቁ ሰዎች ያኔ ባለመታወቃቸው ምክንያት የይረጋ መቋረጥ አስመልክቶ ሊኖር የሚችል ልዩነት እንደሌለ መረዳት ይቻላል፡፡ በይርጋ የማይታገዱ ጉዳዮች በመርህ ደረጃ የወንጀል ድርጊቶች ከተፈፀሙ በኋላ ክስ ለማቅረብ የሚቻልበት የጊዜ ገደብ በግልፅ ሰፍሮ ያለ ቢሆንም በልዩ ሁኔታ በሌላ ሕግ ከተደነገገ በይርጋ የማይታገዱ ወንጀሎች እንዳሉ ከወንጀል ሕጉ እንቀጽ 216(1) መገንዘብ ይቻላል፡፡ ከዚህ አንፃር የኢ.ፌ.ድ.ሪ ሕገ መንግሥት ቀዳሚው ሲሆን በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 28(1) መሠረት ኢትዮጵያ ባፀደቀቻቸው ዓለም ዓቀፍ ስምምነቶችና በሌሎች የአገራችን ሕጎች የሰው ልጅ ላይ የተፈፀሙ ወንጀሎች ተብለው የተወሰኑ ወንጀሎች፣ የሰው ዘር የማጥፋት፣ ያለፍርድ የሞት ቅጣት እርምጃ የመውሰድ፣ በአስገዳጅ ሰውን የመሰወር