Lij sami fact And fast news in the world
СтатистикаLij sami tizazu news
- Последний пост
- 4 сент. 2025 г.
- Последнее чтение
- 15 авг.
- Постов за неделю
- 0
- Всего постов
- 22
- Тип
- открытый
- Язык
- английский
- Категория
- Новости и СМИ
- В каталоге с
- 15 авг.
- 1/24сутки в ленте
- —
- 1/48двое суток
- —
- 1/72трое суток
- —
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
без подписи
ሰበር መረጃ‼️ ነዋሪዎች ከሰፊ የቴህራን ክፍል ‘በአስቸኳይ’ ለቀው እንዲወጡ የእስራኤል ጦር አስጠነቀቀ "በቀጣዮቹ ሰዓታት የእስራኤል መከላከያ ኃይል ባለፉት ቀናት በመላዋ ቴህራን ውስጥ ሲያካሂድ እንደበረው የኢራን አገዛዝ ወታደራዊ መሠረተ ልማቶችን ለመምታት በአካባቢው ዘመቻ ያካሂዳል” በማለት የእስራኤል መከላከያ ኃይል ቃል አቀባይ አቪቻይ አድሬ ማስጠንቀቂያቸውን በኤክስ ገጻቸው ላይ አስፍረዋል። የጦር ሠራዊቱ ቃል አቀባዩ "በእዚህ አካባቢ የምትቆዩ ከሆነ ሕይወታችሁን ለአደጋ ታጋልጣላችሁ ሲሉ አስጠንቅቀዋል። @Sheger_Press @Sheger_Press
ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለ1446ተኛው የኢድ አል አድሃ (አረፋ) በዓል በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከኢቲቪ ጋር ያደረጉትን ቃለ መጠይቅ የመጀመሪያ ክፍል ዛሬ ምሽት 2፡30 ይለቀቃል ተብሏል። @Sheger_Press @Sheger_Press
без подписи
без подписи
без подписи
ቼልሲ የአውሮፓ ኮንፈረንስ ሊግ ሻምፒዮን ሆነ ቼልሲ ሪያል ቤቲስን 4 ለ 1 በማሸነፍ የአውሮፓ ኮንፈረንስ ሊግ ሻምፒዮን ሆኗል። ዛሬ ምሽት በተደረገው የአውሮፓ ኮንፈረንስ ሊግ የፍፃሜ ጨዋታ ሪያል ቤቲሶች 1 ለ 0 እየመሩ ዕረፍት መውጣት ቢችሉም ቼልሲዎች ከዕረፍት መልስ ባስቆጠሯቸው 4 ግቦች ሻምፒዮናነቱን ተጎናፅፈዋል። ሪያል ቤቲስን ቀዳሚ ያደረገችውን ግብ ኤዛልዙሊ በ9 ደቂቃ ቢያስቆጥርም ቼልሲን አሸናፊ ያደረጉ ግቦችን ኢንዞ ፌርናንዴዝ፣ ጃክሰን 70ኛ፣ ጄደን ሳንቾ በ83ኛ እና ሞይሰስ ካይሴዶ በ91ኛ ደቃቂዎች ላይ አስቆጥረዋል። የእንግሊዙ ክለብ ክለብ ቼልሲ ዛሬ ምሽት የአውሮፓ ኮንፈረንስ ሊግን ማሸነፉን ተከትሎ አራቱንም የአውሮፓ እግርኳስ ማኅበር የሚያዘጋጃቸው የክለብ ውድድሮች ያሸነፈ የመጀመሪያው ክለብ ሆኗል።
без подписи
без подписи
በኢትዮጵያ የእሳተ ገሞራ ፍንዳታ ብርቅዬ የተባለውን ሰማያዊ ላቫ አመነጨ #Ethiopia | የኢትዮጵያ እሳተ ገሞራዎች ውስጥ እጅግ ብርቅዬ የሚባለውን ሰማያዊ ላቫ እየፈነጠቀ መሆኑ እንደ ክስተት እየታየ ይገኛል። ከኢንዶኔዢያ ጃቫ ግዛት ካዋ ኢጄን እሳተ ገሞራ ጋር ተመሳሳይነት አለው የተባለው ሰማያዊ ላቫው በመጀመሪያ እይታ ላቫው ከተራራው ላይ እየፈሰሰ ይመስላል፣ ነገር ግን ይህ ያልተለመደ ፍካት እንደሚታሰበው አይደለም። "ሰማያዊ እሳት" እየተባለ የሚጠራው ይህ ክስተት በላቫ የተፈጠረ ሳይሆን ከእሳተ ገሞራው ስንጥቆች በሚወጡት የሚቃጠሉ የሰልፈር ጋዞች የሚመጣ መሆኑ ተገልጿል። እስከ 600°C (1,100°F) የሚደርስ ሙቀት ያላቸው ትኩስ ጋዞች በአየር ውስጥ ከሚገኘው ኦክሲጅን ጋር ሲገናኙ፣ በእሳት ተያይዘው ደማቅ ሰማያዊ ነበልባል ይፈጥራሉ። በካዋህ ኢጄን ያለው ትክክለኛው ላቫ እንደ አብዛኞቹ እሳተ ገሞራዎች የተለመደው ቀይ-ብርቱካናማ ቀለም ያለው ቢሆንም፣ የሚቃጠለው ሰልፈር ነበልባል የሚያብረቀርቅ ሰማያዊ ላቫ ምስልን የሚፈጥር ሲሆን በሌሊት ብቻ የሚታይ አስደናቂ ትዕይንት ነው ተብሏል፡፡ #menahriaFm
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ " አልተዘረፍኩም ግን የዝርፊያ ሙከራ ተደርጎብኝ አከሽፊያለሁ " አለ። በማህበራዊ ሚዲያ ላይ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ውስጥ የነበረ 7.7 ቢሊዮን ብር መዘረፉን ወይም ከባንኩ ወደ ግለሰቦች አካውንት መዞሩን ፤ ዘራፊዎቹ እንዳልተያዙ ፤ በዚህ ላይ የተሳተፉ አካላት እያንዳንዳቸው 50 ሚሊዮን ብር እንደደረሳቸው እና ባንኩም ጉዳዩን አድበስብሶ እንዳለፈው የሚገልጽ መረጃ እየተሰራጨ ነው። ባንኩ ግን ይህ " ፍጹም ውሸት ነው ፤ ምንም የተዘረፈ ገንዘብ " የለም ብሏል። " ከባንካችን ምንም የተዘረፈ ገንዘብ የለም " ያለው ንግድ ባንክ " ይልቁንም ከፍተኛ ገንዘብ ለመዝረፍ የተደረገ ሙከራ ነው " ሲል ገልጿል። ባንኩ ፤ የመዝረፍ ሙከራው በተደረገ በጥቂት ደቂቃዎች በውስጥ ቁጥጥር ስርአቱ አጠራጣሪ ግብይት መፈፀሙን ደርሶበት ምንም ዓይነት ገንዘብ ወጪ ሳይደረግ ሙከራውን ወዲያውኑ እንዳከሸፈው አሳውቋል። " ሙከራው በጥቂት ያልተገባ ጥቅም ለማግኘት ባሰቡ ተጠርጣሪዎች የተፈፀመ እንጂ የባንካችንን ሲስተም ተላልፎ የተፈፀመ ጥቃት አይደለም " ብሏል። ባንኩ፥ " የገንዘብ ዝርፊያ ሙከራው ከከሸፈ በኃላ ጉዳዩን ለሚመለከተው የሕግ አካል በማሳወቅ ተጠርጣሪዎቹ በፖሊስ ቁጥጥር ስር እንዲውሉ ተደርጎ የምርመራ ስራ እየተከናወነ ይገኛል " ሲል ገልጿል።
без подписи
" ከነገ ግንቦት 21 ጀምሮ ወደ ስራ ገበታ ይመለሳሉ " - ፅ/ቤቱ ላለፉት 12 ቀናት በስራ ማቆም አድማ የቆዩት የመቐለ ዳኞች ስራ ለመጀመር መግባባት ላይ መደረሳቸው ተነግሯል። ዳኞቹ ያቀረቡት የደህንነት ስጋት ጥያቄ ጊዚያዊ አስተዳደሩ ትኩረት ሰጥቶ እንደሚከታተለው በተደረሰው ስምምነት ምክንያት ነው ወደ ስራ ገበታቸው ለመመለስ የወሰኑት። የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር የፕሬዜዳንት ፅህፈት ቤት " ዳኞቹ ያለባቸው የድህንነት ስጋት በማስመልከት ከፕሬዜዳንት ታደሰ ወረደ (ሌ/ጀነራል) እና ከፍትህ አካላት አመራሮች ጋር ተወያይተዋል " ብሏል። " በውይይቱ በዳኞቹ ላይ ያንዣበበው የደህንነት ስጋት በጥልቀት ተዳሷል ፤ ችግሩን ከስሩ በመረዳት ለመፍትሄው ትኩረት ተሰጥቶ ይሰራል " ሲል ገልጿል። " የደህንነት ስጋቱ በዘላቂነት ለመፍታት የአጭርና የረጅም ጊዜ የመፍትሄ አቅጣጫዎች ተቀምጠዋል። በተደረሰው መግባባት መሰረት የመቐለ ሰባቱ ክፍለ ከተማ ፍርድ ቤቶች ከነገ ግንቦት 21/2017 ዓ.ም ጀምሮ ወደ ስራ ገበታ ይመለሳሉ " ብሏል።
без подписи
የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ዛሬ ይጠናቀቃል #Ethiopia | የ2024/25 የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የመጨረሻ ሳምንት ጨዋታዎች በተመሳሳይ ምሽት 12 ሰዓት ላይ ይደረጋሉ። ሻምፒዮኑን እና ወራጅ ክለቦችን የለየው ፕሪሚየር ሊጉ ከሊቨርፑል እና አርሰናል በመቀጠል ማን ለቀጣይ ዓመት የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ተሳትፎ ይደርሳል የሚለው የሚጠበቅ ሆኗል። የፔፕ ጋርዲዮላው ማንችስተር ሲቲ ከሜዳው ውጪ ከፉልሃም የሚጫወት ይሆናል፡፡ በ68 ነጥብ 3ኛ ደረጃ ላይ የሚገኘው ማንችስተር ሲቲ የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ተሳትፎን ለማሳካት ከጠንካራው ፉልሃም ከባድ ፈተና ይጠብቀዋል። ማንችስተር ዩናይትድ በኦልድትራፎርድ የኡናይ ኤምሬውን አስቶንቪላን የሚያስተናግድበት ጨዋታ ለአስቶንቪላ ወሳኝ መርኃ ግብር ነው፡፡ በ66 ነጥብ 6ኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠው አስቶንቪላ የቀጣይ ዓመት የሻምፒዮንስ ሊግ ቦታን ለማግኘት በጨዋታው 3 ነጥብ ማሳካት የግድ ይለዋል። ኖቲንግሃም ፎረስት እና ቼልሲ የሚያደርጉት ጨዋታ የመጨረሻ ሳምንት ሌላው ወሳኝ መርኃ ግብር ሲሆን፤ ቼልሲ በ66 ነጥብ 5ኛ ኖቲንግሃም ፎረስት በ65 ነጥብ 7ኛ ደረጃ ላይ ሆነው የሚያደርጉት ተጠባቂ ጨዋታ ነው። በተመሳሳይ ኒውካስትል በቀጣይ አመት በሻምፒዮንስ ሊግ ለመሳተፍ ከኤቨርተን ጋር በሜዳው ወሳኝ ጨዋታ ያደርጋል። የሊጉ ሻምፒዮን ሊቨርፑል በአንፊልድ ዛሬ ዋንጫውን የሚረከብ ሲሆን ከክሪስታል ፓላስ ጋር ጨዋታውን የሚያደርግ ይሆናል። ሳውዝሃምተን ከ አርሰናል፣ ቶተንሃም ከ ብራይተን፤ ወልቭስ ከ ብሬንትፎርድ፣ ኢፕስዊች ከ ዌስትሃም እና በርንማውዝ ከ ሌስተር ሲቲ ዛሬ በተመሳሳይ ምሽት 12 ሰዓት ላይ የሚደረጉ የመጨረሻ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መርኃ ግብሮች ናቸው።
እንኳን ለብርሀነ ትንሣኤው በሰላም አደረሰን! አደረሳችሁ! የትንሣኤ በዓል እየሱስ ክርስቶስ ከሙታን መካከል የተነሳበትን የትንሳኤ ቀን ማሰብያ ዕለት ነው። ይህንን ታላቅ ሀይማኖታዊ በዓል ስናከብር ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ ሠው ልጆች ሲል ብዙ መከራ የተቀበለበት ፤ ትንሣኤው ተበስሮ እውነትና ደግነት ድል አድርገው እስኪታዩ ድረስ ክፋትና ውሸት እንደ ቋጥኝ ገዝፈው የታዩበትና እንደ ተራራ የማይነቀነቁ የመሰሉበት በድህረ እውነት በይቅርታ እና በፍቅር የታረሙበት በዓል በመሆኑ በዚህ ተምሳሌት በጎ ተግባራትን ለማጠናከር በመትጋትና ለተሻለ ውጤት በመስራት በዓሉን ልናከብረው ይገባል፡፡ በዓሉን ስናከብር ኢትዮጵያዊ ባህላችን የሆነዉን መደጋገፍ በማጎልበት እኛ ስንበላ በልተው የማያድሩ ፤ እኛ ስንለብስ መልበስ ያልቻሉ ወገኖቻችንን በማሰብ እንዲሁም የዕምነቱ አስተምህሮ የሚጠይቀውን መልካም ተግባር በመፈፀም በፍቅርና በመተሳሰብ ከጎናቸው ልንሆንና ልናግዛቸው ይገባል፡፡ በድጋሜ እንኳን ለብርሀነ ትንሣኤው በሰላም አደረሰን! አደረሳችሁ!
" ስቅለት " በክርስትና አስተምሮ ይህ ዕለት የአይሁድ ካህናት ያለ በደል ያለ ጥፋት ንጹሕ እና ጻድቅ የኾነውን ኢየሱስ ክርስቶስ የሰቀሉበት ዕለት ነው። ዕለቱ በእምነቱ ተከታዮች ዘንድ ኢየሱስ ክርስቶስ የዓለም ዂሉ መድኀኒት ለአዳምና ለልጆቹ ሲል በመልዕልተ መስቀል በቀራንዮ አደባባይ ተሰቅሎ መዋሉን የሚታሰብበት ታላቅ ቀን ነው። በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን እና ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን #በስግደት እና #በጾም የሚታሰብ ሲሆን በወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ህብረትም በተለያዩ ስነ-ስርዓቶች ታስቦ ይውላል፡፡ በተለይ ደግሞ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ከንጋታው ጀምሮ እስከ ማምሻው በዕለቱ የተፈጸሙትን ክስተቶች በሰዓት ከፍላ በልዩ መንፈሳዊ ሥርዓትና በስግደት ታከብረዋለች ፦ ✝ ዓርብ ጠዋት ዓርብ ጠዋት ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ በጲላጦስ ፊት በፍርድ አደባባይ መቆሙ ይታሰባል። የካህናት አለቆችና ሕዝቡ ሽማግሎች ሁሉ ሊገድሉት በኢየሱስ ላይ ተማከሩ፤ አስረውም ወሰዱት ፥ ለገዢው ለጰንጤናዊው ጲላጦስም አሳልፈው ሰጡት። ✝ በ3 ሰዓት ጲላጦስ በወቅቱ በነበረው ሕዝብ ግፊት መሠረት ወንጀለኛውን በርባንን ከእስር አስፈትቶ በምትኩ ኢየሱስን አሳልፎ የሰጠበት፤ አካሉ እስኪያልቅም 6,666 የገረፉት ከሊቶስጥራ - ቀራኒዮ እርጥብ መስቀል አሸክመው የወሰዱበት ነው። ✝ በ6 ሰዓት ኢየሱስ ክርስቶስን እጆቹን እና እግሮቹን ቸንክረው በቀራንዮ ጎልጎታ ተራራ በ2 ወንበዴዎች መካከል የተሰቀለበት ነው። ✝ በ9 ሰዓት በእምነቱ አስተምሮ ይህ ሰዓት ኢየሱስ ክርስቶስ ነፍሱን ከሥጋው በባሕርይ ሥልጣኑ የለየበት ወደ ሲዖል ወርዶም የታሠሩትን ሁሉ ያስፈታበት ነው። ✝ 11 ሰዓት ዮሴፍና ኒቆዲሞስ ከታላቅ ክብር እና ሐዘን ጋር በአዲስ መቃብር የቀበሩበት ነው።
без подписи
ሆሳዕና‼️ ሆሳዕና ማለት የዕብራይስጥ ቃል ሲሆን ትርጉሙም አቤቱ አሁን አድን አሁን ባርከን ማለት ነው። "ሆሳዕና ለዳዊት ልጅ በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው ፤ ሆሳዕና በአርያም እያሉ ይጮሁ ነበር" ; ማቴ 21 ÷ እንኳን አደረሳቹ።