tgindex
⛪️ ሰንበት ተማሪዎች ነን

⛪️ ሰንበት ተማሪዎች ነን

Статистика

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን የጥበብ መጀመሪያ እግዚአብሔርን መፍራት ነው ;ሰነፎች ግን ጥበብንና ተግሳጽን ይንቃሉ " ምሳሌ 1:7 👉 የቻናሉ አላማ ✔️💠 መንፈሳዊ መዝሙሮች : ትምህርቶች ✔️💠 የዕለቱን ስንክሳር ✔️💠ወቅታዊ የቤተ ክርስቲያን መረጃ ያገኙበታል ለማንኛውም ሀሳብ 👉@helentekia 👇share & join

Последний пост
15 апр.
Последнее чтение
15 авг.
Постов за неделю
0
Всего постов
21
Тип
открытый
Язык
ti
В каталоге с
15 авг.
Подписчики
131
0 за 1 дн.
Сутки
0
0,00%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
187
21 постов
Вовлечённость
142,7%
к подписчикам
Постов в день
0,0
всего 21
Упоминаний
0
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
1/48двое суток
1/72трое суток

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • 💖 🍒 💖 ከትንሣኤ እሁድ በኋላ ያሉ ዕለታት ስያሜ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን፡፡ ✞ ሰኞ- ማዕዶት ይባላል፡- 💛 ማዕዶት ማለት መሻገር፣ ማለፍ ማለት ነው፡፡ በዚህ ዕለት በፋሲካችን በክርስቶስ ትንሣኤ ከድቅድቅ ጨለማ ወደ ሚደነቅ ብርሃን፣ ከሞት ወደ ሕይወት፣ ከሲኦል ወደ ገነት፣ ከሃሳር ወደ ክብር መሻገራችንን እናስባለን፡፡ ✞ ማክሰኞ- ቶማስ ይባላል፡- 💛 በዚህ ዕለት ቶማስ ጌታን አይቶ ማመኑ፤ "ጌታዬና አምላኬ" ብሎ መመስከሩ ይዘከራል፡፡ ዮሐ.፳፥፳፯-፳፱ ✞ ረቡዕ- አልአዛር ይባላል፡- 💛 በዚህ ዕለት ትንሣኤና ሕይወት የሆነው ጌታችን አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ አልአዛርን ከሞት እንዳስነሳው እናስባለን፡፡ ክርስቶስ የሞትን ስልጣን የሻረ የሕይወት ራስ ፤ የመቃብርን ሥርዓት ያጠፋ ትንሣኤ፡ በድልም ያረገ ንጉሥና የባህርይ አምላክ መሆኑን እንመሰክራለን፡፡ ✞ ሐሙስ- አዳም ሐሙስ ይባላል፡- 💛 በዚህ ዕለት ለአዳም የተሰጠው ተስፋ እና የተገባለት ኪዳን እንደተፈጸመ አዳምና ልጆቹ ነጻ እንደወጣን እናስባለን፡፡ ✞ አርብ- ቅድስት ቤተክርስቲያን ይባላል፡- 💛 በዚህ ዕለት ቤተክርስቲያን በክርስቶስ ሞትና ትንሣኤ ስለመመስረቷ ይሰበካል፡፡ ክርስቶስ ስለ እርሷ ራሱን አሳልፎ ሰጥቶ ቤዛ ሆኖ በደሙ አንጽቶ በትንሣኤው ድል ሰጥቶ እንዳከበራት ይነገራል፡፡ ✞ ቅዳሜ- ቅዱሳት አንስት ይባላል፡- 💛 በዚህ ዕለት ቅዱሳት አንስት የክርስቶስን አካል ሽቶ ለመቀባት ጨለማ አቋርጠው ወደ መቃብር መምጣታቸውና ትንሣኤውንም ቀድመው ማየታቸው ይሰበካል፡፡ ✞ እሁድ- ዳግም ትንሣኤ ይባላል፡- 💛 በዚህ ዕለት ክርስቶስ ለሦስተኛ ጊዜ ለደቀ መዛሙርቱ ተገልጦ ሰላምን መስበኩ እና ሥልጣንን መስጠቱ ይሰበካል፡፡ 💛 ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር አሜን፡ #Via @EOTCmahlet 🇪🇹🇪🇹🇪🇹 Join$share it

  • #ሥላሴ ትትረመም ሥላሴ ትትረመም ወት ትትነከር ሥላሴ ትትረመመም ወት ትነከር(3) ×2 ሥላሴ ትትረመም ወትትነ ይገባል ምስጋና ይገባል ውዳሴ ሁሉን ለፈጠረ ለቅድስት ሥላሴ ከዘመናት በፊት ቀድሞ የነበረ ፍጥረቱን በሙሉ ለክብሩ ፈጠረ /አዝ===== ልበል ሀሌ ሉያ ኪሩቤልን ለብሰን በእግረ ምስጋና ያሬድን ልከተል ላቅርብ ምስጋናውን ዘምስለ ሱራፌል ውዳሴ ምስጋና ነው እና ለልዑል                            /አዝ===== በስም ሶስት ሲሆን እንዲሁም በአካል በግብርም ሶስት ነው ያለመቀላቀል ፍጥረትን በመፍጠር በአምላክነት በባህሪይ እና ደግሞም በመግስት አምላክነውእንጂ አይባልምሶስት /አዝ===== በኪሩቤል ጅርባ ዙፋኑን ዘርግቶ ክብሩን ጌትነቱን ከፍጥረት ለይቶ ይኖራል ዘላለም በመንግስቱ ፀንቶ ይኖራል ዘላለም በመንግስቱ ፀንቶ /አዝ===== ይመስክር ዬርዳኖስ ይናገር ታቦር የአምላክን ጌትነት የሥላሴን ክብር ይኼው በዬርዳኖስ ወልድ ተገለጠ መንፈስ ቅዱስ ታየ አብም ቃሉን ሰጠ

  • ሂዱ ንገሩ አውሩ ለአለም ሂዱ ንገሩ አውሩ ለአለም ተነሥቷል በዚህ የለም/2/ መድኃኔ አለም ሞት የማይችለው የበረታ ኃያል ነው የማይረታ ማኅተሙን የፈታ የትንሳኤው ጌታ ገዳዩ ሞት በእርሱ ድል መንሳት ተዋጠና ሰንሰለቴን ቀንበሬን ተካው በበገና ሞት ሆይ መውጊያህ የታል እያልን እምንዘምረው መስቀልህ ጦር ስምህ ጋሻችን ሆኖልን ነው ዳንን የምንለው ተሻግረናል ስላሻገርከን ለዘላለም በመቃብር ሞት ይይዘህ ዘንድ ከቶ አልቻለም ኃይለኛውን በኃይል አስረኸው ላይፈታ መመርንልህ አሸናፊ ነህ የእኛ ጌታ ከፍ በል በእልልታ ማቶ ማዳን ለማን ተችሏል ካንተ በቀር ጌትነትህ ስራህ ይኖራል ሲመሰከር ወዳጄ ሆይ ውበትህ ውብ ነው የሚያበራ ተጨነቀ ተንቀጠቀጠ ጥላት ፈራ ዕጹብ ያንተ ስራ መስክሩለት የምስራች ነው ታላቅ ዜና መላዕክቱ ነጭ ለብሰዋል ድል ነውና ከተማዋ አንዳች ሁናለች በሌሊቱ በዝማሬ ተንቀጠቀጠ ወኅኒ ቤቱ ከበረውን ምቱ አሁን ግን ክርስቶስ ላንቀላፉት በኩራት ሆኖ ከሙታን ተነሥቶአል። 1ኛ ቆሮ 15፥20

  • ማክሰኞ ቶማስ ጌታችን ለሐዋርያቱ ሲገለጥ ቶማስ ለአገልግሎት አብሯቸው አልነበረም እና የጌታን ትንሣኤ ተጠራጣረ ጌታችን በጦር የተዋጋ ጎኑን ሲያስነካ አመነ ስለዚህም ቶማስ ተብሎ ተሰየመ ፳÷፳፯-፳፱ እውነት ስንት ቶማሶች ተነሳን በእውቀት ማንስ በእግዚአብሔር ከሃሊነት ላይ ተነሳን ትግስቱን አንደ አላዋቂነት ወሰድን ??︎ በምህረቱ ይማረን

  • ሰኞ ማዕዶት ከትንሳኤ በኃላ ያለችውን ሰኞ መጠሪያው ሲሆን ፨ ማዕዶት ማለት ማለፍ መውጣት መሻገር ማለት ነው በክርስቶስ ትንሣኤ ከሲኦል መንጋጋ ወደ ገነት ክብር ከዳቢሎስ ምርኮ ወደ ክርስቶስ ደስታ አሸጋገርከን እያል በፍጹም ደስታ ደስ ተሰኝተን እንውላለን # ቤተ ክርስቲያናችን የሚስጥር ቤት ናትና ሁላችንም ቀርበን በእቅፉ እንግባ ግን ስቶቻችን የክርስቶስ ትንሣኤ ተቀበልን በአብይ ጾም አይናችን ተገለጠ? ወይ እንደ አይሁድ ክርስቶስን ገድለን የቂጣ በአላችንን በደስታ አከበርን? ክርስቶስን ከመስቀል ላይ በተነሳበት ቀን ደግመን ሰቅለን በፍቅር የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅር በላቸው ብሎ ማረን ሁላችንም ከትንሣኤ በኃላ ወደ ዳቢሎስ እስራት ከመግባት ይሰውረን ትንሣኤን በአፍ ብቻ የተቀበልን ደሞ በዳግማ ትንሣኤው ክርስቶስን ከቤታችንም ከልባችንም አስገብተን እንነሳ ዘንድ የተዘጋጀን ያድርገን

  • እንበለ ደዌ ወሕማም እንበለ ፃማ ወድካም አመ ከመ ዮም ያብጽሐነ ያብጽሕክሙ ለብርሃነ ትንሣኤሁ እግዚአብሔር በፍስሓ ወበሰላም! "ያለ ደዌና ያለ ሕማም፥ ያለ ፃማና ያለ ድካም እግዚአብሔር ለትንሣኤው ብርሃን እንደ ዛሬ ቀን በደስታና በፍቅር በአንድነት ያድርሰን ያድርሳችሁ!" ብለን እየጸለይን ያለ ደዌ ያለ ሕማም እስከዚች ሰዓት አድርሶናል ምን ይሳነዋል?🙌 እንኳን አደረሳችሁ 😍 ማሕሌቱን ለምትቆሙ ሁሉ መልካም አገልግሎት ይሁንላችሁ 🙏 ዛሬን በልዩ በልዩ ምክኒያት በጦርነት  በመቅደሱ ማሳለፍ ላልቻሉ ወገኖቻችን በጸሎት እያሰባችሁ (አደራ) እናመሰግናለን በድጋሜ መልካም በዓል ይሁንላችሁ መልካም በዓል ❤️🙏

  • https://vm.tiktok.com/ZMH3s2QuT69J9-urkCv/ This post is shared via TikTok Lite. Download TikTok Lite to enjoy more posts: https://www.tiktok.com/tiktoklite

  • видео или голосовое, без подписи

  • 14 нояб.1305из mierafekidusan

    🌹እንኳን አደረሳችሁ🌹 ፰ኛ ዓመት የምስረታ በዓል ✨ፈለገ ሕይወት ሰንበት ት/ቤት✨ 🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔 ህዳር ፮ እና ፯ በቱሉ ዲምቱ አቦ ታላቅ መንፈሳዊ ጉባኤ ተዘጋጅቷል አይቀርም። https://t.me/mierafekidusan

  • “ተነሥቶአል በዚህ ፣ የለም” ማር. 16፡6 ። እንኳን ለ2017 ዓ.ም. የጌታችንና የመድኃታችን የኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ትንሣኤ በሰላም አደረሳችሁ ! “ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን በዐቢይ ኃይል ወሥልጣን አሰሮ ለሰይጣን አግዐዞ ለአዳም ሰላም እምይእዜሰ ኮነ ፍሥሐ ወሰላም ፤” ትርጓሜ፡- “ክርስቶስ በታላቅ ኃይልና ሥልጣን ከሙታን ተለይቶ ተነሣ ። ዲያብሎስን አሰረው ፤ አዳምን ነጻ አወጣው ። ሰላም ! ከዛሬ ጀምሮ ደስታና ሰላም ሆነ ።” /ኦርቶዶክሳዊ አዋጅ/ . . . በዓለም ላይ አንድ መቃብር ብቻ ባዶ ነው ። በጠባቆች የሚጠበቁ ብዙ መቃብሮች አሉ ። መቃብሩ እየተጠበቀ ግን ከተማውን የሞላ አንድ ብቻ ነው ። ተነሥተው ሕያው የሆኑ ሰዎችን አናውቅም ፣ ዳግም ሞት ላይዘው የተነሣውን ጌታ ግን እናውቃለን ። መግነዙን ቢያልፍ ፣ የተዘጋውን ቋጥኝ አያልፍም ፤ ቋጥኙን ቢያልፍ ወታደሮችን አያልፍም ፤ ወታደሮችን ቢያልፍ ገንዘብ የሚያስለፈልፋቸውን እውነትን ሐሰት የሚሉትን ማለፍ አይችልም ተብሎ ሳለ ምድርን የሞላው አንድ ብቻ ነው ። የሥጋውያንና የረቂቃንን ምክር ፣ የሲኦልና የሮማ ቤተ መንግሥትን ትብብር ፣ የቤተ ክህነትና የቤተ መንግሥትን ሽርክና ፣ የሊቀ ካህናትና የንጉሠ ነገሥትን ፊርማ አሸንፎ ልብን ግዛቱ ያደረገ አንድ ብቻ ነው ። እርሱም ከሞት የተነሣው የእግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው ። እንደ እርሱ ሞት ያስገረመ ፣ እንደ እርሱ ትንሣኤ ያስደመመ የለም ። የማይሞተው ሲሞት “የምትወዱት አልቅሱለት” ተባለ ፣ በራሱ ኃይልና ሥልጣን ሲነሣ “ክብርና በረከት ይገባዋል” ተባለ ። መቃብሮች ሁሉ አጽሞች እንዳይሰረቁ ይጠበቁ ይሆናል ፣ እንዳይነሣ የሚጠበቅ መቃብር ግን የለም ።ክርስቶስ ግን እንዳይነሣ መቃብሩ ዘብ ቆመበት ፤ ከወዳጆቹ ይልቅ መነሣቱ በጠላቶቹ የታመነ ነበር ። ጠላቶቹ መሞቱንና መነሣቱን  ቢያምኑም አልዳኑም ። ለመዳን ከእርሱ ጋር መሞትና መነሣት ያስፈልጋልና ። ገደልነው ብለው ደስ ይላቸዋል ፣ ወዲያው እነሣለሁ ብሏል እያሉ መረበሽ እንቅልፍ ይነሣቸዋል ። የማያስተኛ ሟች ፣ የማይያዝ የትንሣኤ ጌታ ነው ። መቅደስ እያከበሩ መቅደስ ሰውነቱን አፈረሱ ፣ የሦስት ቀን ድልን ፈቀደላቸው ። ያዘኑ ወዳጆቹ ይደሰቱ ዘንድ ፣ የተደሰቱ ጠላቶቹ ያፍሩ ዘንድ ክርስቶስ ተነሣ ። የእስራኤልን መነሣት ተስፋ እያደረጉ የሚያነሣትን ገደሉት ። እንደ አቅማቸው ከእንቅልፍ እየተነሡ እንደ አቅሙ ከሞት እንደሚነሣ ዘነጉ ። የኃጢአት አውራው ዝንጋዔ ነው ። አይቶ እንዳላየ መሆን ነውና ። ወትሮም እነርሱ በመቅደስ ሆነው እርሱ በመንደር ሲያስተምር አላፈሩም ። ከመቅደስ ሳይሆን ከከተማው አውጥተው ሰቀሉት ። ዛሬም ክርስቶስ በደጅ ነው ፣ መቅደሱ በሰቃዮች ሲሞላ ክርስቶስ በደጅ ይኖራል ። በመቅደስ በአሮናዊ ሥልጣን ፣ በደጅ በሮማውያን ሥልጣን ከምድረ ገጽ ይጥፋ ብለው ተነሡ ። ከመቅደስ ቢያባርሩት መቅደሱ ፈረሰ ፣ ከከተማ ቢያባርሩት ኢየሩሳሌም ተደመሰሰች ። ከዓለም ቢያባርሩት ዓለም ምጥ ያዘው ። እውቀቱ ወደ አለማወቅ ተለወጠ ። የመግደል እውቀት የማዳን እውቀት መሆን አቃተው ። እርሱ ግን ሰማይ ቤቱ ፣ ምድር ግዛቱ ፣ ምእመን ርስቱ ነው ። ዮናስ በዓሣ አንበሪ ሆድ ሦስት ቀን እንደ ቆየና ሕያው እንደ ነበረ ክርስቶስም በሙታን መንደር ሙታንን እየፈለገ ሕያው ነበር ። ዮናስን የጣሉ እንደ ሞተ ያውቃሉ ፣ የጣሉት ሳያዩት ንስሐ የገቡ አዩት ። ክርስቶስም ያረዱት ሳይበሉት ፣ ኃጢአተኛ ነን ያሉ ጠገቡት ። ዮናስ ከሦስት ቀን በኋላ ወደ ነነዌ በንስሐ ድምፅ መጣ ፣ ጌታም ወደ ነነዌ ዓለም “መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ” እያሉ ወደሚሄዱት ደቀ መዛሙርት መጣ ። ከትንሣኤ በኋላ ቂምና መተዛዘብ የለም ፣ ለካደው ጴጥሮስ ቅድሚያ ተገለጠ ፣ አፍሮ እንዳይጠፋበት ። ለማናፍረው እያፈረ ስንት ዘመን አባበለን ። የሸሹትን ደቀ መዛሙርት ሳይታዘብ “ሰላም ለእናንተ ይሁን” አለ ። እርሱ “የሰውን ድካም ያውቀዋልና” ። ሞት ፍቅሩን አልገደለበትም ። እኛ ጭረት ፣ ትንሽ ቍስል ፍቅራችንን ገድላብን ይኸው ተስፋ ቢስነት ያሰቃየናል ። ለይቅርታ ካልተነሣን ሳንነሣ እንቅር ። መነሣት ብቻ በቂ አይደለም ፣ ለምንድነው የተነሣነው ማለት ያስፈልጋል ። ጌታ ለይቅርታ ፣ ብዙዎች ለበቀል ተነሡ ። ክርስቶስ ጊዜ ሰጥቶት አልተነሣም ፣ በራሱ ኃይል ተነሣ ። በእግዚአብሔር መንግሥት ጊዜ የሚባል ቸር የለም ፣ ሁሉን የሚያደላድል የመለኮት እጅ ነው ። ሰዎች ማደሪያ ከልክለውት በደብረ ዘይት ጫካ ያድር የነበረው ምድር ግን ለሦስት ቀን ሸሸገችው ። ገጣሚው፡- “ሞት ይቅር ይላሉ ፣ ሞት ቢቀር አልወድም ፤ አፈሩም ድንጋዩም ከሰው ፊት አይከብድም” ያለው ለዚህ ነው ። እርሱ በሥጋ ሞተ ፣ በመለኮቱ ግን ሕያው ነው ። ሰንበትን በመቃብር አከበረ ። የሕይወት ሰንበታችን ነውና ልናከብረው እንደሚገባን አስተማረን ። መነሣቱን አይሁድም ይጠብቃሉ ጦር ይዘው ፣ ቅድስት እናቱም ትጠብቃለች ምስጋና ይዛ ። አጠባበቃችን እንጂ መጠበቃችን ዋጋ አይሰጠውም ። እግዚአብሔር ወራጁን ትቶ ምንጩን ያያል ። ሰው ግብዝ ነውና ወራጁን እያየ ያብዳል ። የእግዚአብሔር ልጅን መቃብር ከሦስት ቀን በላይ አልቻለውም ። በፈቃዱ ሞተ ፣ ተቀበረ ። ጠባቂዎቹ እስከ ሦስት ቀን ድረስ ብቻ እንዲጠብቁ ታዘዙ ። በአይሁድ ልማድ ሦስተኛው ቀን ሞት እርግጥ የሚሆንበት ነው ። ጌታችን ግን ሞት እርግጥ በሚሆንበት ቀን ትንሣኤውን እርግጥ አደረገ ። እርሱ ባይነሣ ኑሮ ሐዋርያት አፍረው ወደ ገሊላ ይመለሱ ነበር ። እርሱ ባይነሣ ኑሮ ሐዋርያት ተነሣ በማለታቸው ወንጀለኛ ተብለው መከሰስ ሳይሆን አበዱ ተብለው መታከም ይኖርባቸው ነበር ። የሚከሰስም ጤነኛ ነውና ። የምታምኑት እስኪ እልል በሉለት ። ምንድነው ዝምታው ? ስለ ሞት እያወራችሁ ስለ ሕያው ጌታ ምነው ዝም አላችሁ ? ጌታ ሆይ ተነሥተሃል አምናለሁ ። አይሁድ በጥፊ የመቱትን ጉንጭህን እስመው ዘንድ ወዴት አገኘዋለሁ ? ከበው ርኩስ ምራቃቸውን የተፉብህ ከብቦ የሚያስጨንቀንን በትንሣኤህ ጉልበት በትነው ። ጸሎት ቅድስት ሞትህን ቡርክት ትንሣኤህን አምናለሁ ፣ እባክህ ጽድቄን ይቅር በለው ። ፎቶ የሚያነሣ ይዤ እመጸውታለሁ ፣ መልክ ቀራጭ አቁሜ ስግደት እሰግዳለሁ ። ለዝና ደግ ነኝ ፣ ለወሬ ሰጪ ነኝ ። ዛሬ ኃጢአቴን ሳይሆን ጽድቄን ይቅር በለው ። ክፉ መስሎ የሚከፋውን ሁሉ ይጠላዋል ፣ ደግ መስሎ መክፋትን አንተ ትጠላዋለህ ። እባክህን ግብዝነት ያሸተተውን ይህን ሁሉ ሬሣ አንሣው ። አደራህን ብቻህን እንዳትነሣ የሞተ ወገንህን ይዘህ ተነሣ ። ታርደህ በጽዮን ለቆምከው በግ ምስጋና አቀርባለሁ ። በማይፈጸም ዘመን ለዘላለሙ አሜን ።

  • https://youtube.com/channel/UCIuep9fdnlm8Qunb_knouXg?si=guPQPDho16XAE9T6

  • видео или голосовое, без подписи

  • 5 мар. 2025 г.287из finottebiirhan

    ✨ወደ እግዚአብሔር ቤት እንሂድ ባሉኝ ጊዜ ደስ አለኝ ✨መዝ 121-1   ☘☘   የትኬት ሽያጭ ቀን ሊያበቃ 2 ቀናት ብቻ ቀርተውናል  ትኬቱን እጆ ያስገቡ ☘☘ ☘️#ፍኖተ_ሕይወት☘️ ✨✝️ መንፈሳዊ የሕይወት ጉዞ ወደ ፈታሔ ማኅጸን ካራ ደጋ ደብረ ገነት ቅድስት ሥላሴ ቤተ-ክርስቲያን ✝️✨ ☘️#ባሉበት_ሆነው_ጉዞውን በኦንላይን_ይመዝገቡ_ጉዞውን_ይጓዙ ☘️ @finotebirhanbot

  • ❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤ እንኳን ለዐቢይ ጾም በሰላም አደረሳችሁ ፤ አደረሰን። አምላካችን መድኃኒታችን ልዑል እግዚአብሔር ጾሙን የበረከት ፣ የረድኤት ፣ የድኅነት ፣ የንስሐ ፣ ዲያቢሎስን ድል መንሻ እንዲሁም ቤተክርስቲያናችንን ፣ ሀገራችንን ኢትዮጵያን ከመዓት ሕዝቦቿን ከክፉ መቅሰፍት የምንታደግበት ያድርግልን ፤ አሜን።

  • የካቲት ፲፮ ፡ የእመቤታችን ክብረ በዓል ለምን ይከበራል ? በመ/ር ጌታቸው በቀለ                                                                                                                                                                                                                                                     ኢትዮጵያዊው ሊቅ ቅዱስ ያሬድ፡- “ ለወገኖችሽ  የኃጢአት  ይቅርታን  ታሰጪ ዘንድ፤  ዘለዓለማዊ  ሕይወትንም  ለሚወርሱ  ዅሉ  መሸጋገሪያ  ድልድይ  ትኾኚ  ዘንድ  ከአብ  ከወልድ  ከመንፈስ  ቅዱስ ዘንድ ሥልጣን  አግኝተሻል”   ያላት /አንቀጸ ብርሃን/፡፡ አባ ጽጌ ድንግልም በማኅሌተ ጽጌ ድርሰታቸው፡- “የድኅነት ምክንያት ቃል ኪዳንሽ ባይኖር ኖሮ የጥፋት እሳት፣ መርገም (ኀጢአት) ባጠፋን ነበር” ያሏት፤  አባ ሕርያቆስም በቅዳሴው፡- “ጥፋትን ያይደለ ይቅርታን አሳስቢ፡፡ መዓትን ያይደለ ምሕረትን አሳስቢ፡፡ ለጻድቃን ያይደለ ለኀጥአን አሳስቢ፡፡ ለንጹሐን ያይደለ ለተዳደፉት አሳስቢ”  /ቅዳሴ ማርያም ቍ.፻፷፭-፻፸፩/፡፡ በማለት  ያመሰገኗት፣ የተማጸኗት፣ የቅድስተ ቅዱሳን የድንግል ማርያም ዓመታዊ መታሰቢያ ክብረ በዓል የካቲት ፲፮ ቀን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በታላቅ ድምቀት ይከበራል ።  በዓሉም እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ቃል ኪዳን የተቀበለችበት ነውና ኪዳነ ምሕረት ይባላል፡፡ ኪዳነ ምሕረት ማለት የምሕረት መሐላ ማለት ነው፡፡ ከ፴፫ቱ በዓላተ እግዝእትነ ድንግል ማርያም አንዱ ነው፡፡  በየዓመቱ የካቲት ፲፮ ቀን የምናከብረው ይህ በዓል እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በጎልጎታ በልጇ በመቃብር ላይ ኾና “ልጄ ወዳጄ ሆይ ከሥጋዬ ሥጋ፣ ከነፍሴ ነፍስ ነሥተህ ሰው ስለመኾንህ፤ ዘጠኝ ወር ከአምስት ቀን ስለቻለችህ ማኅፀኔ፤ ከአንተ ጋር ከአገር ወደ አገር ስለመሰደዴ መጥተህ ልመናዬን ትሰማኝ ዘንድ እለምንሃለሁ” እያለች ስትጸልይ ጌታ እልፍ አእላፍ መላእክቱን አስከትሎ ወደ እርሷ መጥቶ “እናቴ ማርያም ሰላም ላንቺ ይኹን! እንዳደርግልሽ የምትለምኚኝ ምንድን ነው?” አላት፡፡ እመቤታችንም በስሟ የሚማጸኑትን፣ መታሰቢያዋን የሚያደርጉትን፣ ለችግረኛ የሚራሩትን፣ ቤተ ክርስቲያን የሚያንጹትን፤ ዕጣን፣  ዘይትና መብአ ለቤተ ክርስቲያን የሚሰጡትን ዅሉ እንዲምርላትና ከሞተ ነፍስ እንዲያድንላት ጠየቀችው፡፡  ጌታችንም “ይህን ዅሉ እንዳደርግልሽ በራሴ፣ በአባቴ እና በመንፈስ ቅዱስ ማልኩልሽ”  ብሎ ቃል ኪዳን ገብቶላት ወደ ሰማይ ዐርጓል፡፡   በላዔ ሰብእ-ስምዖን፡ ሰባ ስምንት ሰዎችን የበላ በተአምረ ማርያም እንደተመዘገበው በዚህ ዕለት ከሚታሰቡ ከሁለቱ ተአምራት አንደኛው የስምዖን ታሪክ ነው፡፡ ስምዖን እንደ  አብርሃም  እንግዶችን  እየተቀበለ  ድኾችን  እየመገበ  የሚኖር  ጻድቅ  ነበር፤ ሰይጣን  በዚህ  ሥራው  ቀናበት፣  ሊፈትነውም  በሦስት  አረጋዊ  ሽማግሌዎች ሥላሴ  ነን  ብሎ  ተገለጠለት፡፡  ልክ  እንደ  አብርሃም፤  ሐዋርያው  ጳውሎስ  ሰይጣን  የብርሃን  መልአክ  መስሎ  ይመጣል  እንዳለ እርሱም  ሥላሴ  መስለውት  ተቀበላቸው፤  ተንከባከባቸውም፤  ምግብ  አቀረበላቸው፡፡  ምግብ  አንበላም  የምንጠይቅህን  ግን  ትፈጽምልን  ዘንድ  ቃል  ግባልን  አሉት፡፡  ቃል  ገባላቸው  እንግዲያውስ  የምትወደን  ከሆነ  አንድያ  ልጅህን  ሰዋልን  አሉት፤ መጀመሪያ ደነገጠ “ልጅህን  አርደህ  ካላበላኸን ሌላ ምግብ  አንበላም”  አሉት፡፡ በዚህ ጊዜ ስምዖን ሲያወጣና ሲያወርድ ቆየና  “አብርሃም  ልጁን  ሰውቶ  ነው የእግዚአብሔር  ሰው  የተባለው”  በማለት፣ “የእግዚአብሔርን እንግዳ” ላለማሳዘን ሲል ልጁን አርዶ አቀረበ፡፡ እንግዳ መሰሉ ሰይጣንም መጀመሪያ ሥጋውን ቅመስልኝ ብሎ ግድ አለው፡፡ ወዲያው ተሰወረበት፤ ስምዖንም (በላዔ ሰብእ) አርዶ ያዘጋጀውን የልጁን ሥጋ በቀምሰ ጊዜ ሰይጣን ስላደረበት (ስለ ተዋሐደው) ከዚያች ሰዓት ጀምሮ አእምሮውን ሳተ፣ ተቅበዘበዘ ከዚያ በኋላ ምግብ አላሰኘውም የሰው ሥጋ እንጂ፤ ከዚያም ቤተሰቦቹን፣ ጎረቤቶቹንና መንገደኛውን ዅሉ ይበላ ጀመር፡፡ በአጠቃላይ ፸፰ ሰዎችን ከበላ በኋላ፤ መንገድ ተቀምጦ የሚለምን አንድ በቍስል የተመታ ድኻ ሰው አገኘና ሊበላው  ወደ እርሱ ተጠጋ ግን ቁስሉን አይቶ ተጸየፈው፡፡ ስምዖንም “ስለ እግዚአብሔር ብለህ ከያዝከው ውኃ  አጠጣኝ”  ብሎ ለመነው፤ እርሱም ዝም አለው፡፡ በመጨረሻም “በድንግል ማርያም ስም”  አለው፡፡ ስምዖን የእመቤታችንን ስም በሰማ ጊዜም ወደ ልቡናው ተመልሶ  “እስኪ  ቃሉን  ድገመው ስለ ማን አልከኝ?” አለው፤ በሽተኛውም መልሶ  “ስለ ድንግል ማርያም ውኃ አጠጣኝ”  ብሎ ለመነው፡፡ ያን ጊዜ  “ይህችስ  እንደምታስምር  በልጅነቴ  ሰምቻለሁ”  ብሎ ጥቂት ውኃ ሰጠው፤ ውኃው ጕሮሮውን እንኳን ሳያርስለት  “ጨረስህብኝ”  ብሎ ነጥቆት ሔደ፡፡ በለዔ  ሰብ  ከዚያች  ደቂቃ  በኋላ  አዕምሮው  ተመለሰለት፡፡  እንዲህም  አለ  “በአንድ  ዋሻ  ውስጥ  ገብቼ  ስለ  ኃጢያቴ  አለቅሳለሁ፣  ሥጋዬ  ከአጥንቴ  እስኪጣበቅ  እጾማለሁ፣ ብሎ ዋሻ ገብቶ በመጸጸት በዚያው ሞተ /ተአምረ ማርያም/፡፡ ነፍሱንም መላእክተ ጽልመት መጥተው ሲወስዷት እመቤታችን  “ልጄ በማይታበል ቃልህ ይህችን ነፍስ ማርልኝ?”  አለችው፡፡ ጌታችንም “ሰባ  ስምንት ነፍስ  ያጠፋ፣ ፈጣሪውን  የካደ  ሰው  ይማራልን?”  አላት፡፡ እመቤታችንም “በስሜ  የተጠማውን  ውኃ  አጥጥቶ  የለምን?”  ብላ ስምዖንን (በላዔ ሰብእን) አስምራዋለች፡፡ ነፍሱንም መላእክተ ብርሃን መጥተው ወደ ገነት አስገብተዋታል፡፡ እንደ ማጠቃለያ እግዚአብሔር አምላካችን  “ከመረጥኳቸው ጋር ቃል ኪዳን አደረግሁ”  ባለው ቃል ኪዳን መሠረት  ከቅዱሳን ጋር ያደረጋቸው ቃል ኪዳኖች ብዙዎች ናቸው፡፡ በዚሁ መሠረት ከእግዚአብሔር በታች ከቅዱሳን ዅሉ በላይ ከፍ ከፍ ያለችና የከበረች እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከእግዚአብሔር በተሰጣት የማማለድ ሥልጣን  “ሰአሊ ለነ ቅድስት፤ ቅድስት ሆይ ለምኚልን”   እያሉ ለሚለምኗት ዅሉ ከእግዚአብሔር እያማለደችና እየለመነች ምሕረትን እንደምታሰጥ እናምናለን፡፡ እንደ በላዔ ሰብእ በቃል ኪዳኗ ተጠቅመን፣ ንስሐ ገብተን፣ ቅዱስ ሥጋውን ክቡር ደሙን ተቀብለን የመንግሥቱ ወራሽ ለመሆን ያብቃን፡፡ የእግዚአብሔር ቸርነት፣ የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነት፣                የቅዱሳን ተራዳዒነት አይለየን፡፡                 ወስብሐት ለእግዚአብሔር ዋቢ መጻሕፍት           ✍️ ቅዳሴ ማርያም           ✍️ ተአምረ ማርያም           ✍️ ማኅሌተ ጽጌ          ✍️ ስንክሳር          ✍️ አማርኛ መዝገበ ቃላት ከ @eotctvchannel የተወሰደ

  • ❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤               የካቲት ፲፮ (16) ቀን ኪዳነ ምህረት /እመቤታችን ቃልኪዳን የተቀበለችበት/ ❤ እንኳን አምላክን ለወለደች ለእናታችን ለእመቤታች ለቅድስት ድንግል ማርያም ከተወደደ ልጅዋ ከጌታችንና ከመድኃኒታችን እየሱስ ክርስቶስ የምሕረት ቃል ኪዳንን ለተቀበለችበት (ለኪዳነ ምሕረት) ዓመታዊ በዓልና ለመጥምቀ መለኮት ለቅዱስ ዮሐንስ እናት ለከበረች ለቅድስት ኤልሣቤጥ ለዕረፍቷ መታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ፤ አደረሰን።

  • አይቀርም ❤️🙏

  • ❤️ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አሜን"። ❤️                       ጥር 28 ቀን ቅዱስ አማኑኤል እንኳን ለቅዱስ አማኑኤል ተአምራት አድርጎ አምስት እንጀራንና ሁለት ዓሣን አበርክቶ ሕፃናትና ሴቶች ሳይቆጠሩ አምስት ሺህ (አምስት የገብያ ሕዝብ ለመገበበት (ላጠገበበት) ዓመታዊ መታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ፤ አደረሰን።

  • ❤️ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አሜን"። ❤️                ጥር 24 ቀን አቡነ ተክለሃይማኖት እንኳን ለታላቁ አባት ለሐዲስ ሐዋርያ ለፀሐይ ዘኢትዮጵያ ለአቡነ ተክለሃይማኖት በቁመትና በጸሎት ብዛት አንዲቱ የእግሩ አገዳ ለተሰበረበት (ለስብተ አፅማቸው) ዓመታዊ  መታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ፤ አደረሰን።

  • ❤️ "በስመ አብ  ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ  አሜን"። ❤️ ጥር 22 ቀን ቅዱስ ኡራኤል /ቃል ኪዳን የተቀበለበትና የተሾመበት ቀን/ 🌹በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ትውፊት መሰረት ከሰባቱሊቃነ መላእክት አንዱ ነው 🌹ዑራኤል: ማለት ትርጉሙ የብርሃን ጌታ የአምላክ ብርሀን ማለት ነው ከፍጥረተ አለም ጀምሮም በመብረቅ እና በነጎድጓድ ላይየተሾመ ሀያል መላእክ ነው ምስጢረ ሰማይንም ለሔኖክ ገልጿል 🌹ድንግል ማርያም በአካለ ሥጋ እያለች ወደ ሰማይ አሳርጓታል በሠረገላ ብርሃንም ጭኖ አስቀድሞ ገነትን በመቀጠልም ሲኦልን አስጎብኝቷታል 🌹በስደቷም ጊዜ ወደ ኢትዮጵያ መርቶ መምጥቷታል በክንፍ ተሸክሞም በአራቱም አቅጣጫ አዙሮ አሳይቶ አሥራት እንድትቀበል አድርጓል 🌹ጌታችን በተሰቀለም ጊዜ ደሙን በጽዋዕ አድርጎ በኢትዮጵያ ወንዞች ላይ አፍስሷል 🌹እውቀትን ጥበብን በመግለፅ ለአባ ጊዮርጊስ ዘ ጋሰጫ ድንቅ አድርጓል 🌹በቅድስት ሀገር ኢትዮጵያ የተመሰረቱ አብዛኞቹ ገዳማት በቅዱስ ዑራኤል መሪነት ነው 🌹ጥር 21 ቅዱስ ዑራኤል የተሾሙበት ነው በረከቱ ከሀገራችን ከኢትዮጵያ ከሕዝቦቿ ጋር ይሁን ለዘለዓለሙ አሜን 🌹

⛪️ ሰንበት ተማሪዎች ነን — tgindex