ሰኞ መርሃ ግብር / ማኅበረ ጽዮን
Статистикаሰኞ መርሃ ግብር / ማኅበረ ጽዮን: ✍የኢትዮጲያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተከርስቲያን ያከበረቻቸው ቅዱሳን ታሪክ ✍ የቤተክርስትያኗን ትክክለኛ አስተምህሮዋን የያዙ መዝሙራት ✍ አጭርና ተከታታይ ትምህርቶች ✍ ለመናፍቃን ጥያቄዎች መልስ ✍ ወቅታዊ መረጃዎችና ሌሎችንም የሚያገኙበት ቻናል ➾ሀሳብ አስተያየት ካላችሁ @Hailegebereal19አድርሱን
- Последний пост
- 31 июл.
- Последнее чтение
- 13 авг.
- Постов за неделю
- 0
- Всего постов
- 21
- Тип
- открытый
- Язык
- ti
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 180
- 1/48двое суток
- 206
- 1/72трое суток
- 222
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
без подписи
✝✞✝ እንኩዋን ለሐዋርያው ቅዱስ ቶማስ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ✝✞✝ +"+ ቅዱስ ቶማስ ሐዋርያ +"+ =>ከ12ቱ ቅዱሳን ሐዋርያት አንዱ የሆነው ቅዱስ ቶማስ ብዙ መከራን በማሳለፉና የጌታችንን ጐን በመዳሰሱ ይታወቃል:: +ቅዱስ ቶማስ እንደ ሌሎቹ ሐዋርያት በእሥራኤል ተወልዶ በዚያውም በሥርዓተ ኦሪት አድጐ ገና በወጣትነቱ የሰዱቃውያንን ማሕበር ተቀላቅሏል:: ሰዱቃውያን ሰው ከሞተ በሁዋላ አይነሳም (አልቦ ትንሳኤ ሙታን) የሚሉ ናቸው:: +መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ማስተማር ሲጀምር ግን ቅዱስ ቶማስ ከነበረበት ማሕበር ወጥቶ ጌታችንን ተከተለ:: ጌታችንም ከ12ቱ ሐዋርያት አንዱ ይሆን ዘንድ ሾመው:: የቀደመ ስሙ ዲዲሞስ ሲሆን ጌታችን ቶማስ ብሎታል:: +ቅዱስ ቶማስ ጌታ አልዓዛርን ለማስነሳት በሔደ ጊዜ ሌሎች ሐዋርያት ጌታን "አይሁድ ይገድሉሃል ቅር" ሲሉት እርሱ ግን "እንሒድና አብረን እንሙት" ሲል ፍቅሩን አሳይቷል:: (ዮሐ. 11:16) +ጌታችን ትንሳኤውን ለደቀ መዛሙርቱ በገለጠ ጊዜ ያልነበረው ቶማስ ካላየሁ አላምንም አለ:: ምክንያቱም:- 1.ለጌታችን ከነበረው ፍቅር የተነሳ እውነት አልመስልህ ቢለው 2.አንድም ሌሎቹ ሐዋርያት ትንሳኤውን አየን እያሉ ሲያስተምሩ እኔ ግን ሰማሁ ብየ ማስተማሬ ነው ብሎ በማሰቡ ነበር:: +ለጊዜው ጌታ ተገልጾ ቢገስጸው "እግዚእየ ወአምላኪየ (ጌታየና አምላኬ)" ብሎ ፍጹም ሃይማኖቱን ገልጿል:: ለፍጻሜው ግን የጌታችንን ጎን (መለኮትን) ይዳስስ ዘንድ ባለቤቱ እንዳደለው ያጠይቃል:: መለኮትን የዳሰሰች ይሕቺ ቅድስት እጁ ዛሬም ድረስ ሕያው ናት:: በሕንድ ቤተ ክርስቲያን ውስጥም በክብር ተቀምጣለች:: +ቅዱሳን ሐዋርያት መንፈስ ቅዱስን ተቀብለው ሐገረ ስብከት ሲከፋፈሉ ለቅዱስ ቶማስ ሕንድና በዙሪያዋ ያሉ ሃገራት ደረሱት:: ከዚህ በሁዋላ ነው እንግዲህ ዘርዝረን የማንጨርሰውን ተጋድሎ የፈጸመው:: ቅዱሱ በነበረው ፍጹም ትጋት አባቶቻችን "ዘአሠርገዋ ለብሔረ ሕንደኬ (ሕንድን በወንጌል ያስጌጣት)" ሲሉ ያከብሩታል:: +ቅዱስ ቶማስ ንጉሥ ሉክዮስንና የሃገሩን ሕዝብ ለማሳመን በችንካር መሬት ላይ ወጥረው ቆዳውን ገፈውታል:: ቆዳውንም እንደ ገና ሰፍተው: አሸዋ ሞልተው አሸክመውታል:: +በየመንገዱ የተገፈፈ ገላውን ጨው ቢቀቡት በጎች መጥተው ግጠው በልተውታል:: በዚሕ ምክንያት:- "ኩሉ የአኪ እንዘ የአኪ ዘመኑ: አባግዒሁ ለቶማስ እስመ አራዊተ ኮኑ" ብለዋል ሊቃውንቱ:: +በሁዋላ ግን ከፎቅ ወድቃ የሞተችውን የንጉሡን ሚስት በተገፈፈ ቆዳው በማዳኑ ሁሉም አምነው ተጠምቀዋል:: +ቅዱሱ ሐዋርያ ልክ እንደ ቅዱስ ዻውሎስ አንዳንዴ በፈሊጥ: ሌላ ጊዜም በመከራ ለወንጌልና ለቤተ ክርስቲያን ተጋድሏል:: ያለ ማቁዋረጥም ከሕንድ እስከ ሃገራችን ኢትዮዽያ ድረስ ለ38 ዓመታት ወንጌልን ሰብኩዋል:: +በመጨረሻም በ72 ዓ/ም በዚሕች ቀን በሰማዕትነት አርፏል:: መቃብሩና ቅድስት እጁ ዛሬ ድረስ ሕንድ ውስጥ አሉ:: ከኘሮቴስታንቶች በቀር መላው ዓለም ያከብረዋል:: +እንደ አባቶቻችን ትርጉም ቶማስ (ቶማስስ) ማለት ጸሐይ (ኦርያሬስ) እንደ ማለት ነው:: በተሰጠው የወንጌል ጸጋ በሃገረ ስብከቱ አብርቷልና:: =>ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከአገልጋዩ ቅዱስ ቶማስ ጸጋ በረከት ይክፈለን:: =>ግንቦት 26 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት= 1.ቅዱስ ቶማስ ሐዋርያ (ከ12ቱ ሐዋርያት) 2.ቅድስት አርሶንያ (የቅዱስ ቶማስ ተከታይ) 3.አቡነ ሐብተ ማርያም ጻድቅ =>ወርሐዊ በዓላት 1.አቡነ ኢየሱስ ሞዐ ዘሐይቅ 2.ቅዱሳን ሰማዕታተ ናግራን 3.አቡነ ሰላማ ከሣቴ ብርሃን =>+"+ ደጆች ተዘግተው ሳሉ ኢየሱስ መጣ:: በመካከላቸውም ቆሞ "ሰላም ለእናንተ ይሁን" አላቸው:: ከዚያም በሁዋላ ቶማስን "ጣትህን ወደዚህ አምጣና እጆቼን እይ:: እጅህንም አምጣና በጐኔ አግባው:: ያመንህ እንጂ ያላመንህ አትሁን" አለው:: ቶማስም "ጌታዬ አምላኬም" ብሎ መለሰለት:: ኢየሱስም "ስላየኸኝ አምነሃል:: ሳያዩ የሚያምኑ ብጹዓን ናቸው" አለው:: +"+ (ዮሐ. 20:26-29) <<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>
✝✝✝ በስመ አብ : ወወልድ : ወመንፈስ ቅዱስ : አሐዱ አምላክ . . . አሜን :: ✝✝✝ "✝" ግንቦት 26 "✝" +*" አቡነ ኢየሱስ ሞዐ ዘሐይቅ "*+ =>እግዚአብሔር በ13ኛው መቶ ክ/ዘ እነ አቡነ ኢየሱስ ሞዐን ባያስነሳ ኑሮ ምናልባትም ዛሬ የኢትዮዽያ ቤተ ክርስቲያንን በምናያት መንገድ ላናገኛት እንችል ነበር:: እውነተኛ አባቶቻችን ፈጽሞ ከሚቆረቁራቸው ነገር አንዱ የጻድቅና ሐዋርያዊ አባት አቡነ ኢየሱስ ሞዐ መዘንጋት ነው:: +እርሳቸው ፍሬ ሃይማኖት ሆነው ከጽድቅ ፍሬአቸው አዕላፍ ቅዱሳንን ወልደው ሃገራችን በወንጌል ትምሕርትና በገዳማዊ ሕይወት እንድታሸበርቅ አድርገዋል:: እስኪ በዕለተ ዕረፍታቸው ስለ ጻድቁ ጥቂት ነገሮችን እናንሳ:: +አቡነ ኢየሱስ ሞዐ ዘሐይቅ የተወለዱት ጐንደር : የድሮው ስማዳ (ዳኅና) አካባቢ ሲሆን ወላጆቻቸው ዘክርስቶስና እግዚእ ክብራ ይባላሉ:: የተወለዱት በ1210 ዓ/ም ነው:: ነገር ግን አንዳንድ ምንጮች በ1196 ዓ/ም ያደርጉታል:: +ጻድቁ ከክርስቲያን ወላጆቻቸው ጋር እንደሚገባ አድገዋል:: በልጅነታቸው በብዛት ወላጆቻቸውን ያግዙ ነበር:: በትርፍ ጊዜአቸው ደግሞ ትምሕርተ ሃይማኖትንና ሥርዓቱን ያጠኑ ነበር:: በ1240 ዓ/ም ግን (ማለትም 30 ዓመት ሲሞላቸው) ይሕቺን ዓለም ይተዋት ዘንድ አሰቡ:: +አስበውም አልቀሩ ፈጣሪን እየለመኑ ደብረ ዳሕሞ ገቡ:: በወቅቱ ዳሞ የትምሕርት : የምናኔ ማዕከል ከመሆኑ ባሻገር የአቡነ አረጋዊ 5ኛ የቆብ ልጅ ካልዕ ዮሐኒ ነበሩና የእርሳቸው ደቀ መዝሙር ሆኑ:: +አቡነ ኢየሱስ ሞዐ በደብረ ዳሞ በነበራቸው ቆይታ ቀን ቀን ሲታዘዙ : ሲፈጩ : ውሃ ሲቀዱ ውለው ሌሊት እኩሉን በጸሎት በስግደትና የቀረውን ሰዓት ደግሞ ቅዱሳት መጻሕፍትን በመገልበጥ አሳለፉ:: +በመጨረሻም ልብሰ ምንኩስናን ለበሱ:: ይህን ጊዜ 37 ዓመታቸው ሲሆን ዘመኑም 1247 ዓ/ም ነው:: ወዲያውም በዳሞ ሳሉ መልአከ ሰላም ቅዱስ ገብርኤል ተገልጦ "ወደ ወሎ ሐይቅ ሒድ : ብዙ የምትሠራው አለና" አላቸው:: +በአንዴም ከዳሞ (ትግራይ) ነጥቆ ሐይቅ እስጢፋኖስ (ወሎ) አደረሳቸው:: በዚያም ለ7 ዓመታት በዼጥሮስ ወዻውሎስ ቤተ መቅደስ በተጋድሎ : በስብከተ ወንጌል : በማዕጠንትና ሐይቁ ውስጥ ሰጥሞ በመጸለይ ኖሩ:: +ቅድስናቸውን የተመለከቱ አበውም በግድ አበ ምኔት አድርገው ሾሟቸው:: ይህ ነው እንግዲህ በኢትዮዽያ ቤተ ክርስቲያን ላይ ትልቁ መሠረት የተጣለበት አጋጣሚ:: ነገሩ እንዲህ ነው:- +ስም አጠራሯ የከፋ ዮዲት ጉዲት ለ40 ዓመታት ሃገሪቱን እንዳልነበረች ብታደርጋት ክርስትና ተዳከመ:: ባዕድ አምልኮም ነገሠ:: አቡነ ኢየሱስ ሞዐ (ትርጉሙ ኢየሱስ ክርስቶስ አሸነፈ ማለት ነው) ደግሞ ሃይማኖታቸው የቀና ከ800 በላይ ክርስቲያኖችን ሰበሰቡ:: +በሃገሪቱ ትልቅና የመጀመሪያው ሊባል የሚችል ቤተ መጻሕፍት አደራጁ:: እነዚያን አርድእት በቅድስናና በትምሕርት አብስለው አመነኮሱና "ሒዱ! ሃገሪቱን ታበሩ ዘንድ ተጋደሉ" ብለው አሰናበቷቸው:: +ክእነዚህ መካከልም ታላላቁን አቡነ ተክለ ሃይማኖትን: አቡነ በጸሎተ ሚካኤልን እና የሁዋላውን ፍሬ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫን መጥቀስ እንችላለን:: በዚህም ምክንያት ጻድቁ "ወላዴ አእላፍ ቅዱሳን - አእላፍ ቅዱሳንን የወለደ" ሲባሉ ይኖራሉ:: +ጻድቁ ከዚህ በተጨማሪ የወቅቱን ንጉሥ አፄ ይኩኖ አምላክን በማስተማር ለሃገርና ለቤተ ክርስቲያን ጠቃሚ ሰው አድርገዋል:: በግላቸው ሐይቅ ውስጥ ገብተው ሲጸልዩ የብርሃን ምሰሶ ይወርድላቸው ነበር:: ሐይቅ እስጢፋኖስ ገዳምንም ከጠፋ ከ300 ዓመታት በሁዋላ አቅንተዋል:: +እንዲህ ለቤተ ክርስቲያን ሲተጉ : በተለይ በአበ ምኔትነት በቆዩባቸው 45 ዓመታት ለዓይናቸው እንቅልፍን አላስመኙትም:: ጐድናቸውም ከምኝታ ጋር ተገናኝቶ አያውቅም:: "እንዘ የኀሊ ዘበሰማያት ዐስቦ:: መጠነ ዓመታት ሃምሳ ኢሰከበ በገቦ::" እንዲል:: +ከዚህ በሁዋላ የሚያርፉበት ዕለት ቢደርስ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወርዶ ቃል ኪዳን ሰጥቷቸዋል:: በተወለዱ በ82 ዓመታቸው (በ86 ዓመታቸው የሚልም አለ) በ1282 ዓ/ም በዕለተ ሰንበት ዐርፈው ተቀብረዋል:: {ይህች ቀን (ግንቦት 26) ለጻድቁ ዕለተ ልደታቸው ናት::} << ጻድቁ ስም አጠራራቸው እጅግ የከበረ ነው !! >> =>+"+ ለመንጋው ምሳሌ ሁኑ እንጂ ማሕበሮቻችሁን በኃይል አትግዙ:: የእረኞችም አለቃ በሚገለጥበት ጊዜ የማያልፈውን የክብርን አክሊል ትቀበላላችሁ:: እንዲሁም ጐበዞች ሆይ! ለሽማግሌዎች ተገዙ:: ሁላችሁም እርስ በርሳችሁ እየተዋረዳችሁ ትሕትናን እንደ ልብስ ታጠቁ:: እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ይቃወማልና:: ለትሑታን ግን ጸጋን ይሰጣል:: +"+ (1ዼጥ. 5:3) <<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>
"" ስንክሳር - ግንቦት ፳፮/26 "" ❖በዓለ ቅዱስ ቶማስ ሐዋርያ
без подписи
без подписи
без подписи
አጋንንት እንደ ዝንብ እሽ ብለው የሚያባርሩት የወሊሶው መብራት የድሆች አባት በክርስቲያን በሙስሊሙ የተወደዱ የፍቅር አብነት ገባሬ ተአምራት ወመንክራት ኃብተ ልሣን የተሰጣቸው ብዙ ቋንቋ የሚናገሩ ሐዋርያ የጻድቁ አቡነ ተክለሃይማኖት የስጋ ዘመድ 11ኛው ትውልድ፡፡ አባ ወልደ ትንሳዔ (ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ) ''የምናውቀውን እንናገራለን ያየነውን እንመሰክራለን።" ዮሐንስ ወንጌል 3፤11 ''ጌታ ሆይ አጋንንት በስምህ ተገዙልን።" ሉቃስ ወንጌል 10፤17 ጵጵስና ከትሕትና ጵጵስና ከብሕትውና ጵጵስና ከቅድስና አስተባብረው የያዙ መነኮስ።!!! ለ40 ዓመታት በዓታቸውን በጊዮን ወሊሶ ከተማ በማጽናት ህሙማነ ስጋን በጸበል ድውያነ ነፍስን በወንጌል ሲፈውሱ የኖሩ። 35ሺ ሕዝብ ካላመኑት ወገን ሐብተ ውልድና ስመ ክርስትና እንዲያገኙ ያደረጉ ከ10 ሚሊዮን ሕዝብ በላይ የፈወሱ ይኸ በመዝገብ የሰፈረ ነው። ለታላቁ ጵጵስና ማዕረግ በቅተውም የአራት ኪሎ ውሐ ያልቀየራቸው መናኝ ባህታዊ ገባሬ ተአምር እነ ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ካልዕ ዘሸዋ እነ ብፁዕ አቡነ ሰላማ ዘባሌ በረከት ይሁነን ብለው ጋቢና ፎጣቸውን አባታችን በረደን ይስጡን እያሉ የሚወስዱባቸው የበረከት አባት መምህር አባ ወልደ ትንሳዔ!!!! " አንተ የእኛ ጸር ነህ ዘመድህ ተክለ ሐይማኖት ያስቸግረን ነበር እርሱን አረፍን ስንል ደግሞ አንተን ማን ላከብን" በሰዎች ያደሩ ርኩሳን መናፍስት እንዲህ እያሉ በነው ይጠፉ ነበር ። አባ ወልደ ትንሳዔ እንደ ዝንብ ነው አጋንንት የሚያባርሩ። በነገራችን ላይ አባታችን የጻድቁ ተክለሐይማኖት የስጋ ዘመድ ናቸው በእናታቸው በቅድስት እግዚሐሪያ በኩል አባታችን 11 ትውልድ ናቸው የተወለዱትም ጻድቁ ተወልደው ባደጉባት ኢቲሳ ደብረ ጽላልሽ ገዳም ነው አባታችን እንደ ሐዋሪያት ብዙ ቋንቋ የተገለጸላቸው ከአለምም ሆነ ከመላ ኢትዮጵያ ለመጠመቅ የሚመጡ ሁሉ በቋንቋ ችግር አይመለሱም ነበር። ከተአምራቶቻቸው አንዱ። ለኩዌት ተወላጇ ድንቅ ተአምራት ከተደረገላቸው በእምነት ከኛ ወገን ካልሆኑት ከነዚህም አንድዋ የኩዌት ባለስልጣን ልጅ የሆነች ናት በብዙ አጃቢ ዜና ገድላቸውን ሰምታ የመጣችው ይህችው ሴት አይንዋ ከቦታው ጠፍቶ ጉድጉዋድ እንደሆነና በጀርመን እንግሊዝ ጃፓን አሜሪካ ከፍተኛ ህክምና ብታደርግም አይንዋ ሊገኝ አልቻለም የጎደጎደው አይንዋ ውስጥም ነፍሳት እየገቡ ሲያስቸግሩ የፕላስቲክ አይን ገብቶላታል በላዮም ላይጥቁር መነጽር ታደርጋለች ተስፋ ቆርጠን ዝናዎን ሰምተን መጣን ይላሉ ጸሎት አድርጉ አዳኙ ፈጣሪ ነው ጠዋት ኑ ብለው ተለያዮ ጉዳዮ ከባድ ነውና ከእመቤታችን ስእል ስር ሲማጸኑ ያድራሉ ጠዋት የኪዳን ጸሎት ማድረስ ሲጀምሩ ታማሚዋ ባልተጠበቀ ሁኔታ መጮህ ትጀምራለች "ዛሬ ተዋረድን እዚህ እሳት ሐገር መጣሁ "እያለ መንፈሱ ይለፈልፋል ባለ ግርማው መነኩሴ ጸሎታቸውን ሲጨርሱ መስቀላቸውን አንስተው ግንባርዋ ላይ ሲያደርጉት የአየር አጋንንት ነን ሶስት ነን አንዱ አይንዋን አንዱ ልብዋን አንዱ አእምሮዋን ይዘነዋል በወሊድ ምክንያት በደምዋ ያዝናት ይላል መንፈሱ አይንዋን የት አደረሳችሁት ቢሉዋቸው ጡትዋ ስር ደብቀነዋል ይላል መንፈሱ በሉ አይንዋን ወደ ቦታው መልሱ ቢሉ ተገጥሞላት የነበረው የፕላስቲክ አይን እንደ ጥይት ጮሆ አይንዋ ቦግ ብሎ ከተደበቀበት ይወጣል በደስታ ትፈነጥዛለች አምላክንም አብረዋት ያሉ ያመሰግናሉ በስላም ሐገርዋ ገብታ ልጅ ወልዳ የሚሞትባትም ቀርቶ 2ልጅ ወልዳ ስማለች ይህ ተአምር በአደባባ የተፈጸመ ከ1500 ህዝብ ፊት የተደረገ ነው በአባ ወልደ ትንሳኤ እጅ የተደረጉት ተአምራት ተነግሮ አያልቅም ዛሬ በወሊሶዋ ቤተሳይዳ ደብረ ምጥማቅ እጹብ ድንቅ ተአምራት ይፈጸማል ረድኤታቸው ረቦባታልና። በጊዜ ዕረፍታቸው ድፍን የወሊሶ ሕዝብ አንብቶ ደረት እየደቃ የቀበራቸው ከሞታቸው በፊት መቃብርዎ ሐገርዎ ይሁን ቢባሉ መነኩሴ ምን ሐገርአለውና ሕይወቴም ሞቴም ከወሊሶ ሕዝብ ጋር ነው ብለው ያስደመሙ ታላቅ አባት ናቸው፡፡ ጸሎታቸው ከድፍረት ኃጥያት ከክሕደት አሽክላ ከዘረኝነት ደዌ ከፍቅርረሐብ ከዝሙት እሳት ይጠብቀን ዛሬም በአጸደ ልጆቻቸውን አይዘንጉን አጽራረ ቤተክርስቲያንን ያስታግስልን አሜን አሜን አሜን ምንጭ:አንተነ ኃይሌ
без подписи
без подписи
https://youtu.be/cwAaOWnS0M8?si=ML7MA6QZYWlFONG9
https://youtu.be/9QKf_b_ktMo?si=i-yw769Y2cyq92R-
ሰኞ መርሃ ግብር / ማኅበረ ጽዮን pinned a photo
@SaintGebrielSundaySchoolbot ካስገቡ በኋላ ደረሰኙን በዚህ bot ይላኩልን እናመሠግናለን.
#ወንድሞቼ! ከእናንተ መካከል አንድ አይነ ሥውር ሰው ወደ ጉድጓድ ገብቶ ሊወድቅ ሲል እጁን ዘርግቶ የማይደግፈው ማን ነው? ታድያ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን በልቡናቸው ታውረው ወደ ሲዖል ጉድጓድ ለዘለዓለም ሲወድቁ እንደ ምን እጃችንን የበለጠ አይዘረጋም?ወገኖቼ!በነፍስም በሥጋም የታመመ ሰውን ስታዩ "ይህ የእኔ ሥራ አይደለም: የቀሳውስትና የመነኮሳት ሥራ እንጂ፡፡ ምክንያቱም ሚስት አለችኝ: ልጆችንም አሳድጋለሁ" አትበሉ፡፡ እስኪ ምሳሌ መስዬ ልጠይቃችሁ እናንተም መልሱልኝ፡፡ አንድ ትልቅ በወርቅ የተሞላ ሳጥን ወድቆ ብታዩ "ይህ እኔን አይመለከተኝም፡ ሌሎች መጥተው ያንሡት እንጂ" ትላላችሁን? ግራ ቀኛችሁን አይታችሁ በፍጥነት የምታነሡት አይደለምን? ይህ ወደ ዘለዓለም ጉድጓድ እየወደቀ ያለው ወንድማችሁም ከዚያ ወርቅ በላይ ውድ የእግዚአብሔር ሀብት ነውና አንሡት እንጂ የበለጠ እንዲወድቅ አትግፋት፡፡ እግዚአብሔር ይህን በተመለከተ በአፈ ያዕቆብ እንዲህ ብሏልና፡- "ወንድሞቻችን ሆይ! ከእናንተ ወገን ከጽድቅ ወጥቶ የበደለ ቢኖር መክሮ አስተምሮ ከበደሉ የመለሰው ቢኖር ራሱን አንድም ወንድሙን ከሞት እንዳዳነ ይወቅ፡፡ የራሱን አንድም የወንድሙን ብዙ ኃጢአቱን እንዳስተሠረየ ይወቅ፡፡ አንድም የወንድሙን ነፍስ እንዳዳነ ይወቅ"(ያዕ.5:19-20)፡፡ ✞ ✞ ✞ ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ ✞ ✞ ✞ ✞✞✞ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ✞✞✞ ✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞ ✞ @mahberetsion ✞ ✞ @segnomerhagbir ✞ ✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
"ቅዱስ፣ ጥንቁቅ፣ ግልጽና ብልህ ሁን፡፡ እርጋታን የተላበሰ ሰብእና ይኑርህ፡፡ ደስተኛ ሁን፤ ሰላምታህ በፈገግታ የታጀበ ንጹህ ይሁን፡፡ ንግግርህ የታረመ አጭርና በጨው እንደተቀመመ ጣፋጭ ይሁን፡፡ ቃላቶችህ የተመጠኑ እና ጤናሞች ሁሉም የሚረዳቸው ይሁኑ፡፡ የጓደኛህን ምስጢር አትግለጥ፤ ለሚወዱህ ሁሉ የታመንክ ሁን፡፡ ወደ ጭቅጭቅ እና ንትርክ ከመግባት ራህን ጠብቅ፡፡ የሚሰሙህ ሁሉ እንዳይጠሉህ ወደ ጠብ አትግባ፡፡ ከሰይጣን በቀር ምንም ጠላት አይኑርህ፡፡ የሰዎችን ስህተት አትመራመር፤ የባልንጀራህ ኃጢአት አትግለጥ፡፡ የባልጀራህ ውድቀት ደጋግመህ አታውራ፡፡ በራስህ ኃጢአት ላይ ፍረድ እንጂ በሌሎች ላይ አትፍረድ ገዢያቸው አይደለህምና፡፡ ኃጢአትን በፈጸመ ሰው ላይ ወቀሳ አታብዛ አንተም ትበድላለህና፡፡ ነገር ግን ከኃጢአቱ ይመለስ ዘንድ ረዳትና መካሪ ሁነው፡፡ ከወደቀበትም የስህተት ሥራ እንዲወጣ አበርታው፡፡ ተስፋውን በእግዚአብሔር ላይ ቢያደርግ ኃጢአቱን ልክ በእሳት ፊት እንደወደቀ ገለባ ፈጥኖ እንደሚወገድለት ንገረው፡፡ ተፈጥሮ እንደ መጽሐፍ ፍጥረታት እንደ ጽላት ይሁኑህ። ከእነሱ ሕግጋትን ተማር፤ በተመስጦ ሆነህ በመጽሐፍ ያልሰፈሩትን ምስጢራት ተረዳ፡፡ እግዚአብሔርን ከሚፈራ በቀር ባለጸጋ የሆነ ሰው ማነው? የእውነት እውቀት ከጎደለው ሰው በላይ ፍጹም ደሃ የሆነ ማን ነው? ሁል ጊዜም እውነተኛ ፍቅራችን ጸንቶ ይቀጥል ዘንድ ወደ እግዚአብሔር ጸልይ፡፡ እርሱን ለምነው፡፡ ስለ ቸርነቱ ምስጋና አቅርብ፤ ምክሬን ፈጽሞ ቸል አትበል፡፡" (ምክር ወተግሳጽ ዘቅዱስ ኤፍሬም) ✞✞✞ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ✞✞✞ ✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞ ✞ @mahberetsion ✞ ✞ @segnomerhagbir ✞ ✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
እኔና ጓደኛዬ (ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ስለ ጓደኛው ባስልዮስ) አንድ ዓይነት ፍላጎት ነበረን:: በተወለድንበት ሀገር ታላቅነት አንዳችን በሌላችን ላይ አንመካም:: ወደ ምንኩስናና ወደ እውነተኛው የሕይወት ፍልስፍና ጉዳይ ስንመጣ ግን ተለያየን:: እሱ ወደላይ ከፍ ሲል እኔ ደግሞ በዓለማዊ ምኞት መውረድ ጀመርሁ:: በወጣትነት ከንቱ ምኞት ክብደት ወደ ታች እስበው ጀመር:: ጓደኝነታችን ቢኖርም ቅርርባችን ግን ተሰበረ:: ምክንያቱም ፍላጎቶቻችን ተለያይተዋልና ውሎአችንን ማውራት አልቻልንም:: ቀስ ብዬ ወደ መንፈሳዊነት ስመጣ ግን ታግሦ በተዘረጋ እጅ ተቀበለኝ:: ከሌሎች ጋር ያለውን ጓደኝነት ትቶ ከእኔ ጋር ለማሳለፍ ፈቀደ:: ሆኖም ልዩነቶቻችንን ማጥበብ አልተቻለም:: በሕግ ችሎት ውስጥ ሁልጊዜ የሚውልና የዚያን መድረክ ደስታ የለመደ ሰው ሁሌም መጻሕፍትን ብቻ ከሚያይና ገበያ እንኳን ወጥቶ ከማያውቅ ሰው ጋር እንዴት አንድ መሆን ይችላሉ? [ክህነት ሊሠጠን እንደሆነ] ዜናውን ያልሰማሁ መስሎት ሊነግረኝ መጣ:: 'ክህነት እንቀበል ወይስ አንቀበል?' በሚለው ላይ እሱ የእኔን ውሳኔ ሊከተል ወስኖአል:: እኔ ደግሞ [ለክህነት ብቁ ባልሆንም] የእርሱን ዓይነት ብቁ ሰው ወደ ኋላ ልጎትት አልችልም:: ስለዚህ እሺ አልሁ:: ክህነት የሚሠጥ ቀን ግን ተደብቄ አመለጥኩ:: እርሱ ግን ያለሁ መስሎት ተቀበለ:: ሳገኘው እጁን ስቤ በግድ ተባረክሁ:: አውቄ እንዳደረግሁት ሲያውቅ ተጎዳ:: ክህነትን ብቀበል አልጠላም ነበር:: በግ መሆን ያልቻለ ሰው ግን እንዴት እረኛ ሊሆን ይቻለዋል? [St. John Chrysostom: On Priesthood] (Photo ትርጉም ባለው ቀን የተነሣ) ጴጥሮሳዊ ቅጽበት አርብ ዕለት ጌታ ከሰማቸው ስድቦች ሁሉ በፊት ጌታን የሚያቆስል አንድ ቃል ነበረ:: የሚወደው ደቀ መዝሙሩ ጴጥሮስ "አላውቀውም" እያለ ሲምል ሲገዘት ጌታ ሲሰማው ምንኛ ይሰማው ይሆን? እየሰማህ ስትታማ እንኩዋን ይከብዳል:: እየሰማህ አላውቀውም መባል ደግሞ የባሰ ነው:: ጴጥሮስ ያደረገው ታውቆት መራራ ለቅሶ አለቀሰ:: የእኔና የአንተ የአንቺ ጴጥሮሳዊ ቅጽበት መቼ ይሆን?
без подписи
без подписи
без подписи